Christ Army Youth Fellowship
344 subscribers
69 photos
1 video
4 links
"፤ በወንጌል አላፍርምና...
(ወደ ሮሜ ሰዎች 1: 16)
የቡታጅራ አማኑኤል ሕብረት
የወጣቶች ፕሮግራም
ዘወትር ሰኞ 12፡00
Download Telegram
በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የዘማሪ ተካልኝ ፀጋዬ “ባንተ ጊዜ”አዲስ መዝሙር እነሆ ተባረኩበት on YouTube
https://youtu.be/G4fdLr0guiM
በውስጥ ገጾቿ በልዩ ልዩ ርዕሰ ጉዳዮችን እያነሳች አስተማሪ የሆነች መጽሔት ለአንባቢዎች በቅርብ ቀን ትበረከታለች የ2012 ዓ/ም የገናን በዓል " ከዘመን ተሻጋሪ ስጦታ " መጽሔት ጋር
ሞቱና ትንሳኤው
እግዚአብሔር ከልጆቹ መካከል አንዱን ሳይሆን አንድያ ልጁን ነበር የላከው...መሲሁ ከደረቅ ምድር እንደሚበቅል ቡቃያ በበረት ትኩረት ሳይስብ የተወለደና ተቀባይነት የሌለው ነበር..የንግስና ግርማም ሆነ ውበት እንደነዳዊትም ሆነ እንደሎሎቹ አልነበረውም ስቁይ ባሪያ ሆኖ ነበርና የመጣው፣ በአዕምሮውም ሆነ በአካሉ የህማም ሰው ሆኖ በነገር ሁሉ እንደኛ ተፈትኖ በኅጢአተኞች መካከል ያለኅጢአት ኖረ...በእርሱ ባልሆነ ኅጢአት ስለኅጢአተኞች ኅጢአት ሆኖ በምትክነት ከወንበዴዎች መካከል ተሰቅሎ ሞተ...ሞቱም ለኅጢአታችን እዳ ማስተሰረያ ሆነ የሁላችንንም በደል በእርሱ ላይ እግዚአብሔር አድርጎታልና...ይህም ሰማይ ከምድር የታረቀበት የዕርቅ መሰላል ሆነ፣ እግዚአብሔርን ከሰው የለየው የቤተ መቅደሱ መጋረጃ ከላይ ወደታች ተቀደደ፣ የሰማይ በር ተከፍቷልና...ሞቱ ብቻውን የምስራች አልነበረም ምክንያቱም ትንሣኤው ከሌለ ይህ በእግዚአብሔር እንደሆነ በምን እናውቅ ነበር? መስዋዕቱስ ተቀባይነት ማግኘቱ በምን ይታወቅ ነበር? ሞት መሸነፉስ በምን ይታወጅ ነበር? ትንሣኤ ሙታንስ እንዴት ይኖር ነበር? በርግጥ በሶስተኛው ቀን ከሙታን መካከል በመነሳት ትንሣኤው እውን ሆነ፤ መነሳቱም መስዋዕቱ ተቀባይነት ማግኘቱን ማሳያ ነበር፤ ለእኛም የዘላለም ፅድቅ፣ ቅድስና እና መዳን ማግኛ መንገድ ሆነ...በእርሱ የምናም እኛ እርሱ እንደተነሣ ብንሞትም እንኳን መነሳታችን እርግጥ ሆነ...ኢየሱስን በዚህች ሕይወት ብቻ ተስፋ የማናደርገው ለዚው ነው፤ እርሱ ፅድቅ ለሞላባት፣ ህመም፣ ለቅሶና ሞት ለማይኖርባት ለምትመጣው አለም የተባረከ ተስፋችን ሆነ...ስለዚህ በኑሮው ያገኘው ፅድቁ ለእኛ ይቆጠር ዘንድ ስለእኛ ኅጢአት ሆነ...በመነሣቱም ይህ እውን ሆነ።
(በዶ/ር ዛክ ተፃፈ)
Christ Army Youth Fellowship:
የእግዚአብሔር ብሩካን በሌላ ቅኔ ሊያረሰርሱን ነው....ተባረኩልን
“ቸር ነውና፥ ምህረቱም ለዘላለም ነውና እግዚአብሔርን አመስግኑ።”
አይቀርም
እግዚአብሔር ታላቅ ምስጋናውም ብዙ ነውና፥ በአማልክትም ሁሉ ላይ የተፈራ ነውና።”
መዝ 96፥4....ኑ እግዚአብሔርን ስለ ታላቅነቱ ..ጌትነቱ እናወድሰው።ሰኞ ነሀሴ 24 2013 ,,,,,,,,,11:30