Butajira City Communication Office
1.19K subscribers
3.35K photos
26 videos
1 file
136 links
Newscampany
Download Telegram
አስደሳች ዜና ቡታጅራ !!

በ10ኛው ሀገር አቀፍ የከተሞች ፎረም የቡታጅራ ከተማ አስተዳደር ከፈርጅ ሁለት ከተሞች መካከል 1ኛ ሆና አጠናቀቀች።

በምስራቅ ጉራጌ ዞን የቡታጅራ ከተማ አስተዳደር በአፋር ብሄራዊ ክልል ሰማራ-ሎጊያ ከተማ በተካሄደው 10ኛው የከተሞች ፎረም ከፈርጅ ሁለት ከተሞች መካከል 1ኛ ሆና አጠናቃለች።

እንኳን ደስ አላችሁ እንኳን ደስ አለን !!
የቡታጅራ ከተማ አስተዳደር
👏15👍54
የቡታጅራ ከተማ አስተዳደር የፖሊስ ተቋማት የአመራርና የአባላት አቅም ግንባታ ስልጠናና ግምገማ ተካሄደ

ታህሳስ 13/2018 በምስራቅ ጉራጌ ዞን የቡታጅራ ከተማ አስተዳደር የፖሊስ ተቋማት የባለፉት አምስት ወራት የተግባር አፈፃፀም መነሻ ያደረገ የአመራርና የአባላት አቅም ግንባታ ስልጠናና ግምገማ ተካሄዷል።

"ፖሊስ ነፃና ገለልተኛ ሆኖ ለሙያውና ለገባው ቃል ታማኝ በመሆን በከተማችን ዘላቂ ሰላም ለማስፈን በሚፈፀመው ተግባር ግንባር ቀደም ሆኖ ሊሰራ ይገባል" በሚል ርዕሰ ጉዳይ ላይ ስልጠና እና የተግባር አፈፃፀም ግምገማ ተካሄዷል።

የቡታጅራ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ አብዱ አህመድ ህግ ለማስከበር እየተሰራ ያለው ስራ ጥሩ ነው የሚስተዋሉ ችግሮችን መቅረፍና ማስቀረት በሚያስችል መልኩ አጣጥሞ መስራት ያስፈልጋል።

አባላቱ የተቋሙ እንዳሁም የከተማው ደጀን መሆን እንዳለበት፤አሰራሮች ህዝቡ በተቋሙ ላይ ያለውን አመኔታ በማይሸረሽር ሁኔታ መፈፀም ይገባል ብለዋል።

ከተማዋ የሰላም አብነት ሰገነት መሆኗን ገልፀው ሰላም ወዳድ ከሆነው ህዝዝባችን ፣የፀጥታው አካል እንዳሁም ከባለድርሻ አካላት በቅንጅት በመስራት ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

መድረኩ ያለውን ሰላም በዘላቂ በማስቀጠል እና የሚስተዋሉ ችግሮችን ማረም ከችግር በመውጣት ማህበረሰቡ በሰላምና ፀጥታው ዘርፍ እምነት እንዲጥል ማስቻል ያስፈልጋል።

የከተማው ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊና ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ ሳሙኤል ማርቆስ የወንጀል መከላከል ስራን ማጠናከር እና ህዝቡ እንዲያመሰግን በማድረግ ተቋሙን ማጠናከርና ማስተካከል ይገባል።

የፀጥታ ኃይሉ አብዛኛው በጥሩ ሥነ-ምግባር በአሰራርና ስርዓት እየሰራ መሆኑን ገልፀው ችግር እንዳይፈጠር እያረሙና እያስተካከሉ መስራት እንደሚገባ ጠቁመዋል።
👍51
የቡታጅራ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት በዲጂታል አገልግሎት ላይ ለትምህርት ቤቶች ስልጠና ሰጠ

ታህሳስ 16/2018 የቡታጅራ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤት የመረጃ ጥራት እና የሪሶርስ ብክነትን መቀነስ የሚያስችል የዲጂታል (ከወረቀት ነፃ) አገልግሎት ላይ ለመረጃ ባለሙያዎች እና ርዕሳነ መምህራን በቡታጅራ 2ኛና ከፍተኛ ደረጃ ት/ቤት ስልጠና ሰጥቷል።

የመረጃ አያያዝን በቴክኖሎጂ በመታገዝ በኦን ላይን መለዋወጥ የሚያስችል እና የትምህርት ቤቶችን አሰራር ለማዘመን ታስቦ የተሰጠ ስልጠና ነው።

የከተማው ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ አብዶ አሊ ትምህርት ቤቶች አሰራራቸውን በቴክኖሎጂ በመታገዝ እንዲያዘምኑ እየተሰራ ነው።

ስልጠናው የተጀመረውን ስራ በማጠናከር ትምህርት ቤቶች ሙሉ በሙሉ አገልግሎታቸውን ማዘመን የሚያስችል እንደሚሆን ገልፀዋል።

የመረጃ ጥራትን ከፍ የሚያደርግና የሪሶርስ ብክነትን የሚቀንስ በቴክኖሎጂ የታገዘ ዘመናዊ አገልግሎት በትምህርት ቤቶች መስጠት የሚያስችል ስልጠና መሆኑን ነው የጠቆሙት።

ጥራት ያለው መረጃ በአንድ ቋት በማስተሳሰር መለዋወጥና ክትትል ለማድረግ የሚያስችል እንደሆነ ነው ብለዋል።

ትምህርት ቤቶች አገልግሎቱን በመጀመር ተግባራዊ እያደረጉ እንደሆነ የገለፁት ኃላፊው ሁሉም የመንግስትና የግል ትምህርት ቤቶች ከታህሳስ 17/2018 ጀምሮ ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ የሚያደርጉት እንደሚሆንም ጠቁመዋል።
👍71
በዓሉ በሰላምና በድምቀት እንዲከበር በቂ ዝግጅት ተደርጓል

በዓልን አስመልክቶ በሚኖር ሰፊ የገበያ እንቅስቃሴ ከስርቆት ከሀሰተኛ የብር ኖት እና አደጋ እንዳይከሰት ጥንቃቄ ማድረግ ይገባል፦የቡታጅራ ከተማ ፖሊስ

የ2018 የገና (የእየሱስ ክርስቶስ የልደት) በዓል በሰልም እንዲከበር ፖሊስ ከሰላምና ፀጥታ በመተባበር በቂ ዝግጅት መደረጉን በምስራቅ ጉራጌ ዞን የቡታጅራ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ሳጂን ሙህዲን አምዛ ገልፀዋል።

የቡታጅራ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ቃሲም ግርማ በዓሉ በሰላምና በድምቀት እንዲከበር ተቋሙ ከፖሊስ እና ከባለድርሻ አካላት በመተባበር ሰፊ ስራዎችን በማከናወን ዝግጅት መጠናቀቁን ጠቁመዋል።

በኤሌክትሪክ እያበሰሉ ወይም ከሰል ለኩሰው በስራ ጫና ድካም ትንሽ ልረፍ በማለት መተኛት ወይም ከቤት ለቆ መውጣት የወገኖችን ህይወት አሳጥቷል።

በመሆኑም በሚደረግ የምግብ ዝግጅቶች ከከሰል ጭስ እና ከኤሌክትሪክ አደጋ እንዳይገጥም ጥንቃቄ በማድረግ መስራት የኤሌክትሪክ ኃይልን መጥኖ መጠቀም ይገባል ሲሉ አቶ ቃሲም አፅንኦት ሰጥተው አሳስበዋል።

ዋና አዛዡ ሳጂን ሙህዲን በዓሉን አስመልክቶም በሚከናወን ሰፊ የገበያ እንቅስቃሴ ከስርቆት፣ ከሀሰተኛ የብር ኖት ፣ ከትራፊክ አደጋ እና መሰል ጉዳዮች እንዳይከሰቱ በቅንጅት እየተሰራ እንደሆነ ገልፀው ማህበረሰቡም አስፈላጊውን ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባ ጠቁመዋል።

ህዝባችን በሰላምና ፀጥታ እና በልማት ጉዳይ አይደራደርም እያበረከተ ያለውም ድጋፍ እና ተሳትፎ የጎላ መሆኑን እውቅና ሰጥተው የተለመደውንም ትብብር እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል።

አጠራጣሪ ጉዳይ ሲኖር በተለመደው የፖሊስ መደበኛ ስልክ ፦#0461151322 መረጃ እንዲሰጣቸው ፖሊስ ፈጣን ምላሽ የሚሰጥ መሆኑንም ጠቁመዋል።
👍2