የባንካችን የዘመን መለወጫ በዓል ድጋፍ ዛሬም በአ.አ.፣ በሸገር ሲቲ እና ቢሾፍቱ ቀጥሏል
ትናንት በአ.አ. ትንሿ ስታዲየም የተጀመረው እና ባንካችን አቢሲንያ ለወገኖቻችን የሚያደርገው የዘመን መለወጫ የአስቤዛ ስጦታ ዛሬም በአዲስ አበባ፣ በሸገር ሲቲ እና በቢሾፍቱ ተከናውኗል።
በዚህም መሠረት ባንካችን ዛሬ ጳጉሜን 3 ቀን 2018 ዓ.ም በከተማችን የሀገር ፍቅር ቲያትር ቤት ግቢ ውስጥ በአርቲስት ሙናዬ መንበሩ ስም ለተቋቋመው የበጎ አድራጎት ድርጅት፣ በሸገር ሲቲ መልካ ኖኖ ክፍለ ከተማ ልዩ ስሙ አሸዋ ሜዳ አካባቢ በመልካ ኖኖ የአይነ ስውራን ማኅበር ለሚታገዙ ወገኖች እንዲሁም ቢሾፍቱ ከተማ ለሚገኙ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ ወገኖቻችን ስጦታውን አስረክቧል።
ስጦታው በተሰጠባቸው ቦታዎች የባንካችን የሥራ ኃላፊዎች እና የክፍለ ከተማ አመራሮች ተገኝተው ስጦታውን አበርክተዋል።
ስጦታው ባንካችን አቢሲንያ በአነስተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚገኙ የኅብረተሰብ ክፍሎች ለዘመን መለወጫ በዓል መዋያ ካዘጋጀው የብር 4 ሚሊዮን የዓይነት (የአስቤዛ) ድጋፍ አካል ነው።

❤45👏7👍6
2% ተጨማሪ ጉርሻ!
የውጭ ገንዘብ ምንዛሪ ተመን ( ጳጉሜ 04 ፣ 2018 ዓ.ም)
ከውጪ ሃገር በደሃብሺል፣ በዌስተርን ዩኒየን፣ መኒግራም፣ ትራንስ ፋስት፣ ቴራፔይ፣ ኢትዮ ዳሽ፣ ፋስትፔይ፣ ሪያና ሌሎች ገንዘብ አስተላላፊዎች በኩል የተላከልዎትን ገንዘብ በባንካችን በኩል ሲቀበሉ ወይም ሲመነዝሩ፤ በሁሉም ቅርንጫፎቻችን ከቀልጣፋ መስተንግዶ ጋር ተጨማሪ ጉርሻ እናበረክትልዎታለን!
አቢሲንያ የሁሉም ምርጫ!
September 09, 2026 - Exchange rate at Bank of Abyssinia
Facebook | Instagram | LinkedIn | Twitter | Website |TikTok | Telegram

❤15👍4🔥4
ኪሴም የስራ ልምዴም ከ0 ከፍ ብሏል!
አፖሎ ለኮሌጅ እና ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ባዘጋጀው ዕድል ተማሪዎች ለሚያስከፍቱት አዲስ የአፖሎ አካውንት በአንድ አካውንት 100 ጉርሻ እንዲሁም እንደ ስራ ልምድ የሚያገለግል ሰርተፍኬት ያገኛሉ።
አሁኑኑ ተመዝገቡ! አፖሎ ካምፓስ ቻምፒዮን ይሁኑ: https://bit.ly/ApollocampusTelegram

❤29👍14
2% ተጨማሪ ጉርሻ!
የውጭ ገንዘብ ምንዛሪ ተመን ( ጳጉሜ 05 ፣ 2018 ዓ.ም)
ከውጪ ሃገር በደሃብሺል፣ በዌስተርን ዩኒየን፣ መኒግራም፣ ትራንስ ፋስት፣ ቴራፔይ፣ ኢትዮ ዳሽ፣ ፋስትፔይ፣ ሪያና ሌሎች ገንዘብ አስተላላፊዎች በኩል የተላከልዎትን ገንዘብ በባንካችን በኩል ሲቀበሉ ወይም ሲመነዝሩ፤ በሁሉም ቅርንጫፎቻችን ከቀልጣፋ መስተንግዶ ጋር ተጨማሪ ጉርሻ እናበረክትልዎታለን!
አቢሲንያ የሁሉም ምርጫ!
September 10, 2026 - Exchange rate at Bank of Abyssinia
Facebook | Instagram | LinkedIn | Twitter | Website |TikTok | Telegram
የውጭ ገንዘብ ምንዛሪ ተመን ( ጳጉሜ 05 ፣ 2018 ዓ.ም)
ከውጪ ሃገር በደሃብሺል፣ በዌስተርን ዩኒየን፣ መኒግራም፣ ትራንስ ፋስት፣ ቴራፔይ፣ ኢትዮ ዳሽ፣ ፋስትፔይ፣ ሪያና ሌሎች ገንዘብ አስተላላፊዎች በኩል የተላከልዎትን ገንዘብ በባንካችን በኩል ሲቀበሉ ወይም ሲመነዝሩ፤ በሁሉም ቅርንጫፎቻችን ከቀልጣፋ መስተንግዶ ጋር ተጨማሪ ጉርሻ እናበረክትልዎታለን!
አቢሲንያ የሁሉም ምርጫ!
September 10, 2026 - Exchange rate at Bank of Abyssinia
Facebook | Instagram | LinkedIn | Twitter | Website |TikTok | Telegram
❤8👏2🤩2👍1
እንኳን ለ፳፻፲፱ ዓ.ም ዘመን መለወጫ በዓል አደረሳችሁ!!!
ጊዜው የበአል ወቅት ከመሆኑ ጋር በተያያዘ ክቡራን ደንበኞቻችን ብዙ ግብይት እንደሚፈፅሙ ይታወቃል። በተቃራኒው ደግሞ አጋጣሚውን በመጠቀም ደንበኞችን የሚያጭበረብሩ አካላት ይበራከታሉ፡፡
አጭበርባሪዎቹ ከባንክ በማስመሰል ወደ ደንበኞች ስልክ በመደወል በተለያዩ የማህበራዊ ትስስር ገፆች ሀሰተኛ መልእክት በማስተላለፍ እንዲሁም ግብይት በሚፈጸምበት ወቅት የደንበኞችን እንቅስቃሴ በማጥናት የተለያዩ የማታለያ መንገዶችን በመጠቀም ከደንበኞች አካውንት ገንዘብ ለመውሰድ ይሞክራሉ።
ስለሆነም የሚከተሉትን የጥንቃቄ መንገዶች በመተግበር ክቡራን ደንበኞቻችን ራሳችሁን ከአጭበርባሪዎች ጠብቁ።
- ክፍያ በዲጅታል መክፈያ ስርዓቶች በሚፈጽሙበት ጊዜ የሂሳቡን ባለቤት መረጃ ትክክለኛነት ያረጋግጡ
- ገንዘብ በሚያስተላልፉበት ወቅት ያለምንም ችኮላ ተረጋግተው ግብይትዎን ይፈጽሙ
- የሞባይል ባንኪንግ አገልግሎት እናስተካክልልዎ በማለት የምንነግርዎትን ቁጥር ወይም ኮድ ያስገቡ ብለው ከሚመጡ አጭበርባሪያዎች ምንም ኮድ ባለማስገባት ራስዎን ይጠብቁ
- መረጃችሁን በትክክል ስላልሞላችሁ እናስተካክልላችሁ፤ የሞባይል ባንኪንግ መተግበሪያ እናዘምንላችሁ (Update) ከሚሉ አጭበርባሪዎች ይጠበቁ
- የበዓል ሽልማት ስለደረሰዎ ሽልማቱ እንዲላክልዎት ገንዘብ ያስገቡ ከሚሉ መልእክቶች ይጠንቀቁ
በመሆኑም ከቡራን ደንበኞቻችን በማንኛውም ዘዴ የምታገኙትን መልእክት ወደ ባንካችን ቅርንጫፍ በመሄድ ወይም ወደ 8397 በመደወል ሳታጣሩ ምንም ዓይነት እርምጃ መውሰድ እንደሌለባቸሁ ለማሳሰብ እንወዳለን፡፡

❤19👍5👏1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የአዲስ ዓመት ብስራት ቤታችሁ ጎህ ሳይቀድ ይድረስ። ሰርታችሁ የምትከብሩበት፣ ነግዳችሁ የምታተርፋበት የጤና የሰላም አዲስ ዓመት ይሁንላችሁ።
👍28❤19👏2
የነገ ተስፋ የሆኑ ሕፃናት እና ታዳጊዎች በባንካችን ተገኝተው የአበባ አየሽ ሆይ ጭፈራ አቀረቡ
በቶራ የበጎ አድራጎት ድርጅት ስር የሚረዱ ሕፃናት እና ታዳጊዎች እንዲሁም በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች በባንካችን ዋና መ/ቤት በመገኘት ነገ የምናከብረውን የ2019 አዲስ ዓመት ማብሰሪያ የሆነውን የእንቁጣጣሽ ወይም “አበባ አየሽ ሆይ” ዜማ አቀረቡ።
እነዚህ በቁጥር 30 የሆኑ ሕፃናት፣ ታዳጊዎች እና ድርጅቱን በበጎ ፈቃደኝነት የሚያገለግሉ ወጣቶች በሃገር ባህል ልብስ አምረውና ደምቀው ሲጨፍሩ እና ሲወዛወዙ የታዳሚውን አይን በእጅጉ ስበው ነበረ።
ማኅበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣትና የማኅበረሰባችንን ችግሮች ለማቃለል ሁሌም የሚተጋው ባንካችን አቢሲንያም እነዚህን ሕፃናት ሰብስቦ ለሚያሳድገው ቶራ የበጎ አድራጎት ድርጅት የብር 200,000(ሁለት መቶ ሺሕ) ድጋፍ
አድጓል፡፡
በዝግጅቱ ላይ የተገኙት የቶራ በጎ አድራጎት ድርጅት ዋና ሥ/አስኪያጅ የሆኑት አቶ ሳምሶን ገብረ እግዚአብሔርም ባንካችን
ላደረገላቸው የገንዘብ ድጋፍ ከልብ አመስግነዋል፡፡
ቶራ የበጎ አድራጎት ድርጅት ከተቋቋመበት 2012 ዓ.ም ጀምሮ ወላጅ አልባ ሕፃናትን እና በችግር ውስጥ ያሉ ሴቶችን በምግብ፣ በገንዘብ፣ በቁሳቁስ እንዲሁም የሙያ ክህሎት ስልጠናዎቸን በመስጠት ሲደግፍ እንደቆየ ከድርጅቱ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
ዛሬ ጷግሜ 5 ቀን 2018 ዓ.ም በባንካችን ዋና መ/ቤት በተካሄደው በዚህ ደማቅ ሥነ-ሥርዓት ላይም የባንካችን የበላይ የስራ አመራሮች እና ሠራተኞች የቶራ የበጎ አድራጎት ድርጅት ተወካዮች እንዲሁም ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

❤23👍9👏7
ባንካችን አቢሲንያ የዘመን መለወጫ በዓልን ምክንያት በማድረግ ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ወገኖቻችን 4 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ የአስቤዛ ድጋፍ አድርጓል። ይህን የሚያሳየውን ቪዲዮ ለመመልከት ከታች ሊንኩን ይጫኑ ፡ -https://youtu.be/NegjNen61VU?si=TiZ0Q3qHqt58e-9e
❤34👍12👏2👌2