Bank of Abyssinia
184K subscribers
2.63K photos
189 videos
51 files
831 links
Bank of Abyssinia – The Choice for All
Welcome to BoA’s official Telegram channel!

Use @BOA_ATM_bot to access:

ATM locators
Card services & support
Real-time updates
Download Telegram
ባንካችን መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ወገኖች የ4 ሚሊዮን ብር የአይነት ድጋፍ አደረገ   

ባንካችን አቢሲንያ መጪውን የዘመን መለወጫ ምክንያት በማድረግ ዛሬ  ዿግሜ 2 ቀን 2018 ዓ.ም ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ወገኖቻችን 4 ሚልዮን ብር የሚወጣ የአስቤዛ ድጋፍ አደረገ።  

ማህበራዊ ሃላፊነትን መወጣት ዋነኛ መገለጫው እና ቁልፍ ተቋማዊ ዕሴቱ የሆነው ባንካችን አቢሲንያ ይህን የአይነት ድጋፍ ያደረገው በከተማችን አዲስ አበባ በተለያዩ ክፍለ ከተሞች ለሚገኙ አረጋውያን፣ወላጆቻቸውን ላጡ ሕጻናትና ሴቶች ነው።

የባንካችን ቺፍ ፋይናንስ ኦፊሰር አቶ አብርሃም ገበየሁ እና ሌሎች የባንካችን የስራ ሃላፊዎች ድጋፉን ለገሀር በሚገኘው በትንሿ ስታዲየም ተገኝተው አስረክበዋል።

አቶ አብርሃም ድጋፉን ካስረከቡ በኋላ “ድጋፉ በመጪው የዘመን መለወጫ በዓል ባንካችን አቢሲንያ ከጎናችሁ እንደሆነና አጋርነቱን ለማሳየት ያደረገው ተግባር ነው” ሲሉ ተናግረዋል።   

በዝግጅቱ ላይ የለሚኩራ፣ የልደታ ክፍለ ከተሞች እንዲሁም የተለያዩ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ተወካዮች የተገኙ ሲሆን የቂርቆስ ክ/ከተማ የወረዳ 7 ዋና ስራ አስፈፃሚ የሆኑት ወ/ሮ ነኢማ ሎባ በበኩላቸው ባንካችን በየጊዜው ለተቸገሩ ወገኖቻችን የሚያደርገውን ድጋፍ በማድነቅ በወረዳቸው ስም አመስግነዋል፡፡

ድጋፉ በነገው ዕለትም በከተማችን አዲስ አበባና በቢሾፍቱ ለሚገኙ ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ወገኖቻችንም የሚደረግ ይሆናል፡፡
41👍19👏6🤩1
2% ተጨማሪ ጉርሻ!

የውጭ ገንዘብ ምንዛሪ ተመን ( ጳጉሜ 03 ፣ 2018 ዓ.ም)

ከውጪ ሃገር በደሃብሺል፣ በዌስተርን ዩኒየን፣ መኒግራም፣ ትራንስ ፋስት፣ ቴራፔይ፣ ኢትዮ ዳሽ፣ ፋስትፔይ፣ ሪያና ሌሎች ገንዘብ አስተላላፊዎች በኩል የተላከልዎትን ገንዘብ በባንካችን በኩል ሲቀበሉ ወይም ሲመነዝሩ፤ በሁሉም ቅርንጫፎቻችን ከቀልጣፋ መስተንግዶ ጋር ተጨማሪ ጉርሻ እናበረክትልዎታለን!
አቢሲንያ የሁሉም ምርጫ!

September 08, 2026 - Exchange rate at Bank of Abyssinia

Facebook
| Instagram | LinkedIn | Twitter | Website |TikTok | Telegram
18👍3
አዲስ ዓመት ደረሰ!  ለሚወዷቸው  በአቢሲንያ ሬሚት ደስታቸውን እጥፍ ድርብ ያድርጉ።
መተግበሪያውን ዛሬውኑ ያውርዱ፣ ይጠቀሙ እና 10% ጉርሻ ያግኙ! ዛሬውኑ ይመዝገቡ እና ይጀምሩ
16👏6👍4🤔3
የባንካችን የዘመን መለወጫ በዓል ድጋፍ ዛሬም በአ.አ.፣ በሸገር ሲቲ እና ቢሾፍቱ ቀጥሏል  

ትናንት በአ.አ. ትንሿ ስታዲየም የተጀመረው እና ባንካችን አቢሲንያ ለወገኖቻችን የሚያደርገው የዘመን መለወጫ የአስቤዛ ስጦታ ዛሬም በአዲስ አበባ፣ በሸገር ሲቲ እና በቢሾፍቱ ተከናውኗል።  

በዚህም መሠረት ባንካችን ዛሬ ጳጉሜን 3 ቀን 2018 ዓ.ም በከተማችን የሀገር ፍቅር ቲያትር ቤት ግቢ ውስጥ በአርቲስት ሙናዬ መንበሩ ስም ለተቋቋመው የበጎ አድራጎት ድርጅት፣ በሸገር ሲቲ መልካ ኖኖ ክፍለ ከተማ ልዩ ስሙ አሸዋ ሜዳ አካባቢ በመልካ ኖኖ የአይነ ስውራን ማኅበር ለሚታገዙ ወገኖች እንዲሁም ቢሾፍቱ ከተማ ለሚገኙ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ ወገኖቻችን ስጦታውን አስረክቧል።

ስጦታው በተሰጠባቸው ቦታዎች የባንካችን የሥራ ኃላፊዎች እና የክፍለ ከተማ አመራሮች ተገኝተው ስጦታውን አበርክተዋል።

ስጦታው ባንካችን አቢሲንያ በአነስተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚገኙ የኅብረተሰብ ክፍሎች ለዘመን መለወጫ በዓል መዋያ ካዘጋጀው የብር 4 ሚሊዮን የዓይነት (የአስቤዛ) ድጋፍ አካል ነው።
45👏7👍6
2% ተጨማሪ ጉርሻ!

የውጭ ገንዘብ ምንዛሪ ተመን ( ጳጉሜ 04 ፣ 2018 ዓ.ም)

ከውጪ ሃገር በደሃብሺል፣ በዌስተርን ዩኒየን፣ መኒግራም፣ ትራንስ ፋስት፣ ቴራፔይ፣ ኢትዮ ዳሽ፣ ፋስትፔይ፣ ሪያና ሌሎች ገንዘብ አስተላላፊዎች በኩል የተላከልዎትን ገንዘብ በባንካችን በኩል ሲቀበሉ ወይም ሲመነዝሩ፤ በሁሉም ቅርንጫፎቻችን ከቀልጣፋ መስተንግዶ ጋር ተጨማሪ ጉርሻ እናበረክትልዎታለን!
አቢሲንያ የሁሉም ምርጫ!

September 09, 2026 - Exchange rate at Bank of Abyssinia

Facebook
| Instagram | LinkedIn | Twitter | Website |TikTok | Telegram
15👍4🔥4
ኪሴም የስራ ልምዴም ከ0 ከፍ ብሏል!

አፖሎ ለኮሌጅ እና ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ባዘጋጀው ዕድል ተማሪዎች ለሚያስከፍቱት አዲስ የአፖሎ አካውንት በአንድ አካውንት 100 ጉርሻ እንዲሁም እንደ ስራ ልምድ የሚያገለግል ሰርተፍኬት ያገኛሉ።

አሁኑኑ ተመዝገቡ! አፖሎ ካምፓስ ቻምፒዮን ይሁኑ: https://bit.ly/ApollocampusTelegram
28👍13
2% ተጨማሪ ጉርሻ!

የውጭ ገንዘብ ምንዛሪ ተመን ( ጳጉሜ 05 ፣ 2018 ዓ.ም)

ከውጪ ሃገር በደሃብሺል፣ በዌስተርን ዩኒየን፣ መኒግራም፣ ትራንስ ፋስት፣ ቴራፔይ፣ ኢትዮ ዳሽ፣ ፋስትፔይ፣ ሪያና ሌሎች ገንዘብ አስተላላፊዎች በኩል የተላከልዎትን ገንዘብ በባንካችን በኩል ሲቀበሉ ወይም ሲመነዝሩ፤ በሁሉም ቅርንጫፎቻችን ከቀልጣፋ መስተንግዶ ጋር ተጨማሪ ጉርሻ እናበረክትልዎታለን!
አቢሲንያ የሁሉም ምርጫ!

September 10, 2026 - Exchange rate at Bank of Abyssinia

Facebook
| Instagram | LinkedIn | Twitter | Website |TikTok | Telegram
8👏2🤩2👍1
እንኳን ለ፳፻፲፱ ዓ.ም ዘመን መለወጫ በዓል አደረሳችሁ!!!

ጊዜው የበአል ወቅት ከመሆኑ ጋር በተያያዘ ክቡራን ደንበኞቻችን ብዙ ግብይት እንደሚፈፅሙ ይታወቃል። በተቃራኒው ደግሞ አጋጣሚውን በመጠቀም ደንበኞችን የሚያጭበረብሩ አካላት ይበራከታሉ፡፡

አጭበርባሪዎቹ ከባንክ በማስመሰል ወደ ደንበኞች ስልክ በመደወል በተለያዩ የማህበራዊ ትስስር ገፆች ሀሰተኛ መልእክት በማስተላለፍ እንዲሁም ግብይት በሚፈጸምበት ወቅት የደንበኞችን እንቅስቃሴ በማጥናት የተለያዩ የማታለያ መንገዶችን በመጠቀም ከደንበኞች አካውንት ገንዘብ ለመውሰድ ይሞክራሉ።

ስለሆነም የሚከተሉትን የጥንቃቄ መንገዶች በመተግበር ክቡራን ደንበኞቻችን ራሳችሁን ከአጭበርባሪዎች ጠብቁ።
- ክፍያ በዲጅታል መክፈያ ስርዓቶች በሚፈጽሙበት ጊዜ የሂሳቡን ባለቤት መረጃ ትክክለኛነት ያረጋግጡ
- ገንዘብ በሚያስተላልፉበት ወቅት ያለምንም ችኮላ ተረጋግተው ግብይትዎን ይፈጽሙ
- የሞባይል ባንኪንግ አገልግሎት እናስተካክልልዎ በማለት የምንነግርዎትን ቁጥር ወይም ኮድ ያስገቡ ብለው ከሚመጡ አጭበርባሪያዎች ምንም ኮድ ባለማስገባት ራስዎን ይጠብቁ
- መረጃችሁን በትክክል ስላልሞላችሁ እናስተካክልላችሁ፤ የሞባይል ባንኪንግ መተግበሪያ እናዘምንላችሁ (Update) ከሚሉ አጭበርባሪዎች ይጠበቁ
- የበዓል ሽልማት ስለደረሰዎ ሽልማቱ እንዲላክልዎት ገንዘብ ያስገቡ ከሚሉ መልእክቶች ይጠንቀቁ

በመሆኑም ከቡራን ደንበኞቻችን በማንኛውም ዘዴ የምታገኙትን መልእክት ወደ ባንካችን ቅርንጫፍ በመሄድ ወይም ወደ 8397 በመደወል ሳታጣሩ ምንም ዓይነት እርምጃ መውሰድ እንደሌለባቸሁ ለማሳሰብ እንወዳለን፡፡
16👍5👏1