Bank of Abyssinia
182K subscribers
2.47K photos
185 videos
51 files
768 links
Bank of Abyssinia – The Choice for All
Welcome to BoA’s official Telegram channel!

Use @BOA_ATM_bot to access:

ATM locators
Card services & support
Real-time updates
Download Telegram
11👍4👏3
👍81👏1
የደንበኞች የዕውቅና እና የምስጋና ቀን ከአ.አ ውጭ በሚገኙት በ7ቱም የባንካችን ዲስትሪክቶች ተከበረ

ባንካችን አቢሲንያ ትናንት ሐምሌ 9 ቀን 2018 ዓ.ም የደንበኞች የዕውቅና እና የምስጋና ቀንን ከአዲስ አበባ ውጭ በሚገኙት በሰባቱም ዲስትሪክቶች አብረውት የሰሩ ደንበኞቹን እና አጋሮቹን በመሸለም እና ዕውቅና በመስጠት አከበረ።

የዕውቅና እና የምስጋና ቀኑ በአዳማ፣ በባህር ዳር፣ በድሬዳዋ፣ በደሴ፣ በመቀሌ፣ በጅማ፣ እና በሐዋሳ ዲስትሪክቶች የባንካችን ከፍተኛ አመራሮች፣ ደንበኞች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በደማቅ ዝግጅት ተከብሯል።

የዝግጅቱ ዓላማ ባንካችን ከደንበኞቹ ጋር ያለውን ስትራቴጂካዊ አጋርነት ማጠናከር፣ ላስተዋጿቸው ምስጋና ማቅረብና ለባንካችን ስኬት የላቀ ድርሻ ላበረከቱ ደንበኞችና ባለድርሻ አካላት ደግሞ ተገቢውን ተቋማዊ ዕውቅና ለመስጠት የታሰበ እንደሆነ በዝግጅቶቹ ላይ ተገልጿል።

በየዲስትሪክቶቹ የተገኙት የባንካችን የስራ ሃላፊዎችም ባንካችንን ምርጫቸው አድርገው ይበልጥ እንድንሻሻል ላበረታቱን እና ሁልጊዜም ከጎናችን ለቆሙ ደንበኞቻችን በባንካችን ስም ላቅ ያለ ምስጋና አቅርበዋል።

ባንካችን በሰባቱ ዲስትሪክቶች በተከናወኑት ዝግጅቶች ላይ በውጭ ምንዛሪ፣ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት፣በመርቻንት፣በኮንቬንሽናል እንዲሁም ፓርትነርሺፕ በሚሉ ዘርፎች በአጠቃላይ ወደ 740 ለሚጠጉ ተቋማት፣ድርጅቶች እና ግለሰቦች ሽልማት እና ዕውቅና ሰጥቷል። 

ባንካችን በቅርቡም የደንበኞች የዕውቅና እና የምስጋና ቀንን በሸራተን አዲስ በደማቅ ዝግጅት ባከበረበት ዝግጅት ከ400 በላይ ለሚሆኑ ደንበኞቹ እና አጋሮቹ ሽልማት እና ዕውቅና መስጠቱ ይታወሳል።
31👏8👍4