Bank of Abyssinia
188K subscribers
2.14K photos
176 videos
51 files
635 links
Bank of Abyssinia – The Choice for All
Welcome to BoA’s official Telegram channel!

Use @BOA_ATM_bot to access:

ATM locators
Card services & support
Real-time updates
Download Telegram
ባንካችን የተሟላ የዲጂታል የውጭ ምንዛሪ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችሉ 3 ፕሮዳክቶችን አስመረቀ

ባንካችን አቢሲንያ የተሟላ የዲጂታል የውጭ ምንዛሪ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችሉ አቢሲንያ ሬሚት የገንዘብ ማስተላለፊያ (ሐዋላ አገልግሎት)፣ የዲጂታል የውጪ ምንዛሪ ሂሳብ ለመክፈት የምንገለገልበት ፕሮዳክት እና የአቢሲንያ ዓለም አቀፍ ቨርቹዋል ካርዶችን በይፋ አስመረቀ።

ትናንት መጋቢት 25 ቀን 2018 ዓ.ም በሸራተን አዲስ ሆቴል በተካሄደ የምረቃ ሥነ-ሥርዓት ላይ የተገኙት የባንካችን ቺፍ ዲጂታል ባንኪንግ ኦፊሰር ወ/ሮ ሶስና መንገሻ እንደተናገሩት እነዚህ ፕሮዳክቶች የውጭ ምንዛሪ ተደራሽነትን ለማሻሻል፣ የገቢ ፍሰትን መደበኛ ለማድረግ እና ብሔራዊ የፋይናንስ ስርዓቱን ለማዘመን ያስችላሉ ብለዋል። 

ወ/ሮ ሶስና የዲጂታል ዘርፍ ለባንካችን ያለውን የጎላ ጠቀሜታ ሲገልጹ “ለአብነትም በዘንድሮው በጀት አመት የዘጠኝ ወራት አፈጻጸም በዲጅታል ቻናሎቻችን የተዘዋወረው የብር መጠን ከብር 2.2 ትሪሊዮን  በላይ ሆኖ ተመዘግቧል። ከባንካችን አጠቃላይ ትራንዛክሽን ወይም ግብይት አንጻር 84 በመቶ የሚሆነው በዲጂታል ቻናሎቻችን አማካኝነት የተከናወነ መሆኑን ስንመለከት በዘርፉ ያስመዘገብነው እድገት ለተጨማሪ አዳዲስ ዕድሎችም በር ከፋች መሆኑን ያሳያል” ብለዋል።

ወ/ሮ ሶስና አክለውም ባንካችን የኢኮኖሚ መረጋጋትን በመደገፍ እና የውጪ ምንዛሪን በመደበኛ የባንክ ስርዓት ውስጥ በማቆየት በዲጂታል አገልግሎት ግንባር ቀደም ሆኖ መጓዙን ይቀጥላል ሲሉም በአጽንኦት ተናግረዋል።

የባንካችን ቺፍ ኢንፎርሜሽን ኦፊሰር አቶ ዳንኤል ሐይሉ በበኩላቸው አነዚህን ፕሮዳክቶች ለማቅረብ ባንካችን ከበስተጀርባ በርካታ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን የተጠቀመ እና ሲታሰብበት የቆየ ሲሆን፣ አሁን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ሲፈቅድ ወዲያው ሞክረን ወደ ገበያ አቅርበናቸዋል ብለዋል።

እነዚህ ፕሮዳክቶች አቢሲንያ ሬሚት የገንዘብ ማስተላለፊያ (ሃዋላ አገልግሎት)፣ የዲጂታል የውጪ ምንዛሪ ሂሳብ ለመክፈት የምንገለገልበት ፕሮዳክት እና የአቢሲንያ ዓለም አቀፍ ቨርቹዋል ካርዶች ሲሆኑ ደንበኞች የውጭ ምንዛሪ እንዲልኩ፣ እንዲያስተዳድሩ እና እንዲጠቀሙ የሚያስችሉ ናቸው።

ፕሮዳክቶቹን በተመለከተ ለታዳሚያን የተደረገ ገለጻና የተለያዩ ሽልማት የሚያስገኙ ውድድሮች ለዝግጅቱ ድምቀት የሰጡ ሌሎች ሁነቶች ነበሩ። 

በምርቃት ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የባንካችን ከፍተኛ አመራሮች፣ የቪዛ ተወካዮች እንዲሁም ሌሎች በርካታ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
35👍7👏2
10👍10
21👍5👏4
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የአቢሲንያ አለም አቀፍ ቨርቹዋል ካርድን ቅርንጫፍ በአካል መሄድ ሳያስፈልጎት በኦንላየን በማውጣት ለአስተማማኝ ዓለም አቀፍ ግብይት እንዲሁም የወጪ አገልግሎትዎን ለማዘመን እና ቀልጣፋ ለማድረግ ይጠቀሙበት። አሁኑኑ ይሞክሩት … ይወዱታል !
38👍11🤩3
ለዛውም መኪና ደግሞ በቀላሉ!

አዲስ የአቢሲንያ አካውንት ክፈች፣ ከ500 ብር ጀምረሽ ቆጥቢ፣ በQR/POS ገበያሽን አዘምኚዉ  የኤሌክትሪክ መኪና ዕጣሽን ያዢ!  አንቺ ብቻ በዘመናዊ መንገድ ጀምሪው፣ ቀሪውን ጉዞ እኛ ብሩህ እናደርገዋለን!
 
በቀላሉ ፎርሙን ሙይ ፤ ቤተሰበ ሁኚ፤ ወደ መኪናሽ ቅረቢ👉 https://mcnpkmnf81rz7s-0mxl8ql8p6yz8.pub.sfmc-content.com/3b0xvmmsgsr?src=telegram &cmp=I_can_women
30👍4😱2👏1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
More value, more convenience, more possibilities  use Abyssinia Remit and enjoy an additional 12% bonus on the existing FCY exchange rate.
At the same time, open your digital FCY account and unlock seamless global payments with our Virtual International Card.
#AbyssiniaRemit #BOA #Remittance #FCYBonus #ExchangeBonus #DigitalBanking #DigitalAccountOpening #VirtualInternationalCard #ApolloDigitalBank #SmartBanking #GlobalFinance
49👍9🔥3
4% ተጨማሪ ጉርሻ!

የውጭ ገንዘብ ምንዛሪ ተመን (መጋቢት 28፣ 2018 ዓ.ም)

ከውጪ ሃገር በደሃብሺል፣ በዌስተርን ዩኒየን፣ መኒግራም፣ ትራንስ ፋስት፣ ቴራፔይ፣ ኢትዮ ዳሽ፣ ፋስትፔይ፣ ሪያና ሌሎች ገንዘብ አስተላላፊዎች በኩል የተላከልዎትን ገንዘብ በባንካችን በኩል ሲቀበሉ ወይም ሲመነዝሩ፤ በሁሉም ቅርንጫፎቻችን ከቀልጣፋ መስተንግዶ ጋር ተጨማሪ ጉርሻ እናበረክትልዎታለን!
አቢሲንያ የሁሉም ምርጫ!

April 06, 2026 - Exchange rate at Bank of Abyssinia

Facebook
| Instagram | LinkedIn | Twitter | Website |TikTok | Telegram
10👍5👌2😱1🤩1
አቢሲንያ ሬሚት እንደራስ የሚያምኑት ቤተኛ ነው! የልብ ሥጦታዎን ሲያደርስ መዘግየት አያውቅም! ጭራሽ የእርስዎ ቤተሰብ የእኔም ወዳጅ ነው ብሎ ከ12% ጭማሪ ቦነስ ጋር የልብ ያደርሳል! አቢሲንያ ሬሚት ከአቢሲንያ ባንክ!

ይጠቀሙ እና 12% ቦነስ ይውሰዱ: https://onelink.to/abyssiniaremit
37👍13🥰3🤩2