Bank of Abyssinia
188K subscribers
2.14K photos
176 videos
51 files
635 links
Bank of Abyssinia – The Choice for All
Welcome to BoA’s official Telegram channel!

Use @BOA_ATM_bot to access:

ATM locators
Card services & support
Real-time updates
Download Telegram
ባንካችንና ቪዛ የዓለም ዋንጫን ለመታደም ዕጣ የወጣላቸዉን የ3ኛ ዙር ዕድለኞች ይፋ አደረጉ።

ባንካችን አቢሲንያ እና ቪዛ ደንበኞችን ለማበረታታት ብሎም ለመሸለም የ2026 ፊፋ ዓለም ዋንጫን በስፍራው በአካል ተገኝተው ለመከታተል የሚያስችል ዕጣ የወጣላቸዉን የሶስተኛ ዙር 4 ዕድለኞች በጋራ ይፋ አደረጉ። መጋቢት 22 ቀን 2018 ዓ.ም በዋናው መ/ቤት የባንካችን የሥራ ሐላፊዎችና የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ታዛቢዎች በተገኙበት መርሐ ግብር ላይ የባንካችን ማርኬቲንግ ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ አበበ የዕጣ ማውጣቱን ሥነ-ሥርዓት በይፋ አስጀምረዋል። በወጣው ዕጣ መሠረትም 2 የባንካችን የምስራቅ አዲስ ዲስትሪክት ደንበኞች (የዕጣ ቁጥር 500010553 እና 000023676 ) ፣ 1 የምዕራብ አዲስ ደንበኛ (የዕጣ ቁጥር 900030682) እና 1 የሃዋሳ ዲስትሪክት ደንበኛ (የዕጣ ቁጥር 900033744) በድምሩ 4 የባንካችን ደንበኞች ዕድለኞች ሆነዋል። በዚህ የሽያጭ ዘመቻ ጠንካራ የደንበኞች ተሳትፎ የታየ ሲሆን፣ ባለፈው አንድ ሳምንት ብቻ ከ8,600 በላይ ኩፖኖች የአቢሲንያ ባንክ ቪዛ ካርዶችን በመጠቀም ከ1,000 ብር በላይ ግብይቶችን ለፈጸሙ ደንበኞች ተልከዋል። ይህ የሽያጭ ዘመቻ በባንካችን እና በቪዛ መካከል በመላው ኢትዮጵያ የክፍያ ስርዓቶችን ፍጥነት፣ ደህንነት እና ቅልጥፍና ለማሻሻል ያለመ ሰፊ ስትራቴጂካዊ ትብብር አካል ነው። ተጨማሪ ዕጣዎች በቀሪዎቹ ሳምንታት በሚኖሩ ቀጣይ ዙሮችም የሚወጡ ሲሆን፣ ይህም ለደንበኞች በየዕለቱ የቪዛ ካርድ ሲጠቀሙ የዓለም ዋንጫ ታዳሚ የመሆን ዕድል የሚሰጥ ይሆናል።
49👍8
ባንክ መሄድ ሳያስፈልጋችሁ በአፖሎ የዶላር አካውንት በመክፈት ያላችሁን ዶላር በማስቀመጥ በፈለጋችሁት ጊዜ በዶላር ታገኙታላችሁ፤ ከሀገር ውጪ የሚደረጉ የተለያዩ ክፍያዎችን እዚሁ ሆናችሁ መክፈል ያስችላል።

ዛሬውኑ ይሞክሩት › https://onelink.to/pf962z
64👍18🔥5👏3🤩3🤔2😱1
4% ተጨማሪ ጉርሻ!

የውጭ ገንዘብ ምንዛሪ ተመን (መጋቢት 24፣ 2018 ዓ.ም)

ከውጪ ሃገር በደሃብሺል፣ በዌስተርን ዩኒየን፣ መኒግራም፣ ትራንስ ፋስት፣ ቴራፔይ፣ ኢትዮ ዳሽ፣ ፋስትፔይ፣ ሪያና ሌሎች ገንዘብ አስተላላፊዎች በኩል የተላከልዎትን ገንዘብ በባንካችን በኩል ሲቀበሉ ወይም ሲመነዝሩ፤ በሁሉም ቅርንጫፎቻችን ከቀልጣፋ መስተንግዶ ጋር ተጨማሪ ጉርሻ እናበረክትልዎታለን!
አቢሲንያ የሁሉም ምርጫ!

April 02, 2026 - Exchange rate at Bank of Abyssinia
21👍8👏1
የአቢሲንያ ባንክ ደንበኞችን  የእርካታ ደረጃ ለመለካት የተዘጋጀ መጠይቅ!

ውድ ደንበኞቻችን! አቢሲንያ ባንክ የውድ ደንበኞቹን የእርካታ ደረጃ ለመለካት፤ እንዲሁም ደንበኞቻችን በዕለት ተዕለት አገልግሎታችን ላይ የሚያዩቸው የአገልግሎት ጥራት ማነስ ካለ መረጃ በመውሰድ ወጥ፣ ዘላቂና የተሻለ አገልግሎት መስጠት የሚያስችሉንን ስልቶች ለመቀየስ በማሰብ ለተነሱት ጥያቄዎች ምላሽ እንዲሰጡን በአክብሮት እየጠየቅን፣ መጠይቁን ለመሙላት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎች ይጠቀሙ፡፡
 
 
የአማርኛ መጠይቅ ለማግኘት፡ https://forms.gle/rgMH9KX9YwbHQ57v8
የእንግሊዝኛ መጠይቅ ለማግኘት፡ https://forms.gle/o14tNnovqqbzkSm9A
24👍5🤩3👌3👏1
ንግድሽን አሳድጊ! መኪናሽን አሸንፊ!

በአቢሲንያ ባንክ POS/QR ገበያሽን አዘምነሽ በቀላሉ ከ500 ብር ጀምሮ ክፍያ ስትቀበይ ዘመናዊ የኤሌክትሪክ መኪና እንሸልምሻለን

በቀላሉ ፎርሙን ሙይ፤ ደንበኛ ሁኚ፤ ወደ መኪናሽ ቅረቢ👉https://mcnpkmnf81rz7s-0mxl8ql8p6yz8.pub.sfmc-content.com/3b0xvmmsgsr?src=linkedin&cmp=I_can_women
29👍10
4% ተጨማሪ ጉርሻ!

የውጭ ገንዘብ ምንዛሪ ተመን (መጋቢት 25፣ 2018 ዓ.ም)

ከውጪ ሃገር በደሃብሺል፣ በዌስተርን ዩኒየን፣ መኒግራም፣ ትራንስ ፋስት፣ ቴራፔይ፣ ኢትዮ ዳሽ፣ ፋስትፔይ፣ ሪያና ሌሎች ገንዘብ አስተላላፊዎች በኩል የተላከልዎትን ገንዘብ በባንካችን በኩል ሲቀበሉ ወይም ሲመነዝሩ፤ በሁሉም ቅርንጫፎቻችን ከቀልጣፋ መስተንግዶ ጋር ተጨማሪ ጉርሻ እናበረክትልዎታለን!
አቢሲንያ የሁሉም ምርጫ!

April 03, 2026 - Exchange rate at Bank of Abyssinia

Facebook
| Instagram | LinkedIn | Twitter | Website |TikTok | Telegram
16👍9😱2
እግረኛ መሆን አልሰለቸሽም? BYD ሲጉል ኤሌክትሪክ መኪና ባለቤት የምትሆኚበት ዕድል አይለፍሽ! አሁኑኑ በአቢሲንያ ፖስ፣ QR CODE ወይም በ P2M ግብይት መኪና የሚያሸልም የዕጣ ቁጥርሽን ያዢ!
38👍12🔥12👏7😁4
4% ተጨማሪ ጉርሻ!

የውጭ ገንዘብ ምንዛሪ ተመን (መጋቢት 26፣ 2018 ዓ.ም)

ከውጪ ሃገር በደሃብሺል፣ በዌስተርን ዩኒየን፣ መኒግራም፣ ትራንስ ፋስት፣ ቴራፔይ፣ ኢትዮ ዳሽ፣ ፋስትፔይ፣ ሪያና ሌሎች ገንዘብ አስተላላፊዎች በኩል የተላከልዎትን ገንዘብ በባንካችን በኩል ሲቀበሉ ወይም ሲመነዝሩ፤ በሁሉም ቅርንጫፎቻችን ከቀልጣፋ መስተንግዶ ጋር ተጨማሪ ጉርሻ እናበረክትልዎታለን!
አቢሲንያ የሁሉም ምርጫ!

April 04, 2026 - Exchange rate at Bank of Abyssinia

Facebook
| Instagram | LinkedIn | Twitter | Website |TikTok | Telegram
16👍9
ባንካችን የተሟላ የዲጂታል የውጭ ምንዛሪ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችሉ 3 ፕሮዳክቶችን አስመረቀ

ባንካችን አቢሲንያ የተሟላ የዲጂታል የውጭ ምንዛሪ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችሉ አቢሲንያ ሬሚት የገንዘብ ማስተላለፊያ (ሐዋላ አገልግሎት)፣ የዲጂታል የውጪ ምንዛሪ ሂሳብ ለመክፈት የምንገለገልበት ፕሮዳክት እና የአቢሲንያ ዓለም አቀፍ ቨርቹዋል ካርዶችን በይፋ አስመረቀ።

ትናንት መጋቢት 25 ቀን 2018 ዓ.ም በሸራተን አዲስ ሆቴል በተካሄደ የምረቃ ሥነ-ሥርዓት ላይ የተገኙት የባንካችን ቺፍ ዲጂታል ባንኪንግ ኦፊሰር ወ/ሮ ሶስና መንገሻ እንደተናገሩት እነዚህ ፕሮዳክቶች የውጭ ምንዛሪ ተደራሽነትን ለማሻሻል፣ የገቢ ፍሰትን መደበኛ ለማድረግ እና ብሔራዊ የፋይናንስ ስርዓቱን ለማዘመን ያስችላሉ ብለዋል። 

ወ/ሮ ሶስና የዲጂታል ዘርፍ ለባንካችን ያለውን የጎላ ጠቀሜታ ሲገልጹ “ለአብነትም በዘንድሮው በጀት አመት የዘጠኝ ወራት አፈጻጸም በዲጅታል ቻናሎቻችን የተዘዋወረው የብር መጠን ከብር 2.2 ትሪሊዮን  በላይ ሆኖ ተመዘግቧል። ከባንካችን አጠቃላይ ትራንዛክሽን ወይም ግብይት አንጻር 84 በመቶ የሚሆነው በዲጂታል ቻናሎቻችን አማካኝነት የተከናወነ መሆኑን ስንመለከት በዘርፉ ያስመዘገብነው እድገት ለተጨማሪ አዳዲስ ዕድሎችም በር ከፋች መሆኑን ያሳያል” ብለዋል።

ወ/ሮ ሶስና አክለውም ባንካችን የኢኮኖሚ መረጋጋትን በመደገፍ እና የውጪ ምንዛሪን በመደበኛ የባንክ ስርዓት ውስጥ በማቆየት በዲጂታል አገልግሎት ግንባር ቀደም ሆኖ መጓዙን ይቀጥላል ሲሉም በአጽንኦት ተናግረዋል።

የባንካችን ቺፍ ኢንፎርሜሽን ኦፊሰር አቶ ዳንኤል ሐይሉ በበኩላቸው አነዚህን ፕሮዳክቶች ለማቅረብ ባንካችን ከበስተጀርባ በርካታ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን የተጠቀመ እና ሲታሰብበት የቆየ ሲሆን፣ አሁን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ሲፈቅድ ወዲያው ሞክረን ወደ ገበያ አቅርበናቸዋል ብለዋል።

እነዚህ ፕሮዳክቶች አቢሲንያ ሬሚት የገንዘብ ማስተላለፊያ (ሃዋላ አገልግሎት)፣ የዲጂታል የውጪ ምንዛሪ ሂሳብ ለመክፈት የምንገለገልበት ፕሮዳክት እና የአቢሲንያ ዓለም አቀፍ ቨርቹዋል ካርዶች ሲሆኑ ደንበኞች የውጭ ምንዛሪ እንዲልኩ፣ እንዲያስተዳድሩ እና እንዲጠቀሙ የሚያስችሉ ናቸው።

ፕሮዳክቶቹን በተመለከተ ለታዳሚያን የተደረገ ገለጻና የተለያዩ ሽልማት የሚያስገኙ ውድድሮች ለዝግጅቱ ድምቀት የሰጡ ሌሎች ሁነቶች ነበሩ። 

በምርቃት ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የባንካችን ከፍተኛ አመራሮች፣ የቪዛ ተወካዮች እንዲሁም ሌሎች በርካታ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
35👍7👏2
10👍10
21👍5👏4