ባንካችን ለጌርጌሴኖን የአዕምሮ ሕሙማን መርጃ እና ማገገሚያ ማዕከል የ 3 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ
ባንካችን አቢሲንያ ዛሬ የካቲት 25 ቀን 2018 ዓ.ም ለጌርጌሴኖን የአዕምሮ ሕሙማን መርጃ እና ማገገሚያ ማዕከል የህንጻ ግንባታ ዕገዛ ይውል ዘንድ የ 3 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ።
ባንካችንን በመወከል በስፍራው የተገኙት የባንካችን ዴፒዩቲ ቺፍ ከስተመር ሪሌሽንሺፕና አክዊዜሽን ኦፊሰር የሆኑት አቶ ወሰንየለህ አበራ ድጋፉን ካስረከቡ በኋላ “እናንተ አብዛኞቻችንን በግልና በቡድን የማንችለውን ሸክም ተሸክማችኋል“ ያሉ ሲሆን አክለውም “መጥተን ስለጎበኘናችሁ እጅግ በጣም ተደስተናል፡ የዛሬው ድጋፋችንም የመጀመሪያው እንጂ የመጨረሻው አይሆንም” ብለዋል።
የጌርጌሴኖን የአዕምሮ ሕሙማን መርጃ እና ማገገሚያ ማዕከል መሥራችና ሥ/አስኪያጅ የሆኑት ሊቀህሩያን መለሰ አየለ በበኩላቸው ለተደረገላቸው ድጋፍ አመስግነው “አቢሲንያ ባንክ ዛሬ ያደረገልን የገንዘብ ድጋፍ በባንክ ደረጃ ከተደረጉልን ድጋፎች ሁሉ ከፍተኛው ነው“ሲሉ ተናግረዋል። “የባንኩ ሠራተኞች በተለይ በበዓል ወቅት በግልም ሆነ በጋራ መጥተው የሚጎበኙን ሲሆን የዛሬው ግን የተለየ ነው“በማለት አድናቆታቸውንም ገልጸዋል።
በዚህ የድጋፍ ርክክብ ሥነ-ሥርዓት ላይ የባንካችን የበላይ የሥራ አመራሮች እና ሠራተኞች የተገኙ ሲሆን 720 ለሚሆኑና በማዕከሉ ተጠልለው ለሚገኙ የአዕምሮ ሕሙማንም የምሳ ግብዣ ተደርጓል ።
በመጨረሻም የማዕከሉ መስራችና ሥ/አስኪያጅ የሆኑት ሊቀህሩያን መለሰ አየለ ለባንካችን የምስጋና የምስክር ወረቀትና ዋንጫ ያበረከቱ ሲሆን እንደ አቢሲንያ ሁሉ ሌሎች ባንኮችም የድጋፍ እጆቻቸውን እንዲዘረጉላቸው ጥሪ አቅርበዋል።

❤51👍14👏3
ለአቢሲንያ ባንክ አ.ማ ባለአክሲዮኖች በሙሉ
የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለሥልጣን ባፀደቀው የአቢሲንያ ባንክ አ.ማ የደንበኛ ሳቢ መግለጫ እና በተሠጠው ፈቃድ መሠረት 3,125,000 (ሶስት ሚሊዮን አንድ መቶ ሃያ አምስት ሺህ) መደበኛ አክሲዮኖችን በአንድ የአክሲዮን ዋጋ ብር አንድ ሺህ ስድስት መቶ (1,600) ሽያጭ ያከናውናል፡፡
ሆኖም ለአክሲዮን ሽያጭ የተፈቀደውን ጊዜ ማራዘም አስፈላጊ ሆኖ ስለተገኘ ቀደም ሲል እስከ የካቲት 24 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ የነበረው የአክሲዮን መግዣ የጊዜ ገደብ እስከ መጋቢት 9 ቀን 2018 ዓ.ም የተራዘመ መሆኑን እያስታወቅን በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ በኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን እውቅና ከተሠጣቸው የሰነደ ሙዓለ ንዋይ አገበያዮች (ደላሎች) በኩል የግብይት ሂሳብ (Trading Account) በመክፈት የአክሲዮን ግዢውን ማከናወን የምትችሉ መሆኑን በአክብሮት እንገልፃለን፡፡
ማሳሰቢያ
ሁሉም ባለአክሲዮኖች የአቢሲንያ ባንክ ደንበኛ ሳቢ መግለጫውን በሙሉ እንዲያነቡ ይበረታታሉ፤ ለውሳኔ የተቸገሩ ከሆነ በኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለሥልጣን ፈቃድ ከተሰጣቸው ገለልተኛ የፋይናንስ አማካሪዎች ምክር ይጠይቁ። የደንበኛ ሳቢ መግለጫው መጽደቅ ሰነድ ሙዓለ ንዋዬችን ባለሀብቶች እንዲገዙ የተሠጠ ምክር ወይም ድጋፍ ተደርጎ አይወሰድም፡፡
ይህ ማስታወቂያ በኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለሥልጣን ፈቃድ አግኝቷል፡፡
ለበለጠ መረጃ ለገሐር በሚገኛው የአቢሲንያ ባንክ አክስዮን ማህበር ዋና መስሪያ ቤት በአካል ቀርቦ ማናገር ወይም በስልክ ቁጥር +25111526314 መደወል ይቻላል፤ እንዲሁም የባንኩን ድህረ ገፅ www.bankofabyssinia.com
በመጎብኘት ተጨማሪ መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

❤70👍22🔥9👏6😱3🤔2
2% ተጨማሪ ጉርሻ!
የውጭ ገንዘብ ምንዛሪ ተመን (የካቲት 26፣ 2018 ዓ.ም)
ከውጪ ሃገር በደሃብሺል፣ በዌስተርን ዩኒየን፣ መኒግራም፣ ትራንስ ፋስት፣ ቴራፔይ፣ ኢትዮ ዳሽ፣ ፋስትፔይ፣ ሪያና ሌሎች ገንዘብ አስተላላፊዎች በኩል የተላከልዎትን ገንዘብ በባንካችን በኩል ሲቀበሉ ወይም ሲመነዝሩ፤ በሁሉም ቅርንጫፎቻችን ከቀልጣፋ መስተንግዶ ጋር ተጨማሪ ጉርሻ እናበረክትልዎታለን!
አቢሲንያ የሁሉም ምርጫ!
March 05, 2026 - Exchange rate at Bank of Abyssinia
Facebook | Instagram | LinkedIn | Twitter | Website |TikTok | Telegram

❤83👍15😱7👌4🤔3🤩3🔥1
2% ተጨማሪ ጉርሻ!
የውጭ ገንዘብ ምንዛሪ ተመን (የካቲት 27፣ 2018 ዓ.ም)
ከውጪ ሃገር በደሃብሺል፣ በዌስተርን ዩኒየን፣ መኒግራም፣ ትራንስ ፋስት፣ ቴራፔይ፣ ኢትዮ ዳሽ፣ ፋስትፔይ፣ ሪያና ሌሎች ገንዘብ አስተላላፊዎች በኩል የተላከልዎትን ገንዘብ በባንካችን በኩል ሲቀበሉ ወይም ሲመነዝሩ፤ በሁሉም ቅርንጫፎቻችን ከቀልጣፋ መስተንግዶ ጋር ተጨማሪ ጉርሻ እናበረክትልዎታለን!
አቢሲንያ የሁሉም ምርጫ!
March 06, 2026 - Exchange rate at Bank of Abyssinia

❤38👍3👏2😱2
የምህረት ሰሞናችንን እያገባደድንና፤ ወደ መጨረሻዎቹ አሥር የብርታት ቀናት እየተንደረደርን እንገኛለን።
በነዚህ ውድ ቀናትና ሌሊቶች የበለጠ እንትጋ!
ለቀሪ ዘመናችን ፍሬ እንልቀም!!
#በአሽሩል_አዋኺር_ደጃፍ_ላይ_!
ጁሙዓ ሙባረክ
አቢሲንያ አሚን
እሴትዎን ያከበረ!
#AbyssiniaAmeen #IFB #bankofabyssinia #አቢሲኒያአሚን #Banking #BanksinEthiopia #AddisAbaba #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ #አቢሲንያአሚን

❤14👍12😱1👌1
ባንካችን ማርች 8 ን በማስመልከት ሴቶችን ዕድለኛ የሚያደርግ መርሐ ግብር ጀመረ
• የቢ.ዋይ.ዲ ሴጉል መኪና ለዕድለኛ ተዘጋጅቷል
ባንካች አቢሲንያ ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀንን (ማርች 8) በማስመልከት ለ5ኛ ጊዜ “እችላለሁ!” በሚል መሪ ቃል ከማርች 8 እስከ ኤፕሪል 8 ቀን 2026 ድረስ የሚቆይ ልዩ የሴቶች ወር መርሐ ግብር መጀመሩን ገለጸ።
የባንካችን ቺፍ ኢንተርፕራይዝ ሰርቪስ ኦፊሰር ወ/ሮ መሠረት አስፋው ትናንት የካቲት 26 ቀን 2018 ዓ.ም በዋናው መ/ቤት በተከናወነው የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ላይ እንደተናገሩት ይህ ዓመታዊ መርሐ ግብር አቢሲንያ ባንክ ለሴቶች ኢኮኖሚያዊ አቅም ግንባታ እና ተጠቃሚነት ያለውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ነው ብለዋል።
በመላ ሃገሪቱ የሚገኙ ሴቶችን ለማበረታታት የታለሙ የማኅበራዊ ኃላፊነት ተግባራትን ከሽልማት ጋር አጣምሮ በያዘው በዚህ መርሐ ግብር ለሴት ስራ ፈጣሪዎች የብድር ዕድል፣ የደም ልገሳ መርሐ ግብር፣ የፋይናንስ ዕውቀት ስልጠና እና ለሴት ስራ ፈጣሪዎች ባዛር ተካትተዋል።
በተጨማሪም በቲክቶክ የፈጠራ ውድድር አዲስ ሐሳብ ላላቸው ወይም ሥራቸውን ማሳደግ ለሚፈልጉ ሴቶች የሚሰጥ 1ኛ ለምትወጣ 500,000 ብር፣ ለ2ኛ 300,000 ብር እና ለ3ኛ 150,000 ብር የገንዘብ ሽልማት ተዘጋጅቷል።
እንዲሁም የአደይ እና የዛህራ ምርቶች የሚያስተዋወቅ ፈጠራ የታከለበት የቲክቶክ ማስታወቂያ ለሚሠሩ ሴቶች ለ1ኛ አሸናፊ 200,000 ብር፣ ለ2ኛ 150,000 ብር እና ለ3ኛ 100,000 ብር ሽልማት ተዘጋጅቷል።
ከሁሉም በላይ በዘንድሮው “እችላለሁ!” መርሐ ግብር ከቀደሙት ዙሮች በተለየ ሁኔታ ለአሸናፊ ሴቶች የ2025 ቢ.ዋይ.ዲ ሴጉል ዘመናዊ የኤሌክትሪክ መኪና ዕድልን ይዞ መጥቷል።
ደንበኞችም የዕጣው ተሳታፊ ለመሆን አዲስ ሂሳብ በመክፈት ቢያንስ እስከ 500 ብር መቆጠብ፣ ቁጠባን ማሳደግ፣ ሳይንቀሳቀሱ የቆዩ ሂሳቦችን ማንቀሳቀስ፣ በQR ኮድ እና በP2M (ከግለሰብ ወደ ነጋዴ) የዲጂታል ክፍያዎችን መፈጸም እና ከባንካችን ጋር ከሚሰሩ ሴት ነጋዴዎች ላይ ቢያንስ የ500 ብር ግብይት ማከናወን ይጠበቅባቸዋል።
በመጨረሻም ውድ ደንበኞቻችን፣ አጋሮቻችን እና መላው ሴቶች በዚህ መርሐ ግብር ላይ በንቃት እንዲሳተፉ እና የዕድሎቹ ተቋዳሽ እንዲሆኑ ባንካችን ጥሪውን ያቀርባል።

❤59👏9👍5👌4🤩3
የታላቁ የረመዳን ወር የበጎነት ተግባራት ከመቼውም ጊዜ በላይ በጉልህ የሚስተዋሉበት ጊዜ እንደመሆኑ፣ ባንካችን እየከወነው የሚገኘው ከወገኖቻችን ጋር በአብሮነት የመቆምና የኢፍጣር አስቤዛ የማቅረብ ተግባር ዛሬም ተጠናክሮ ቀጥሏል።
ለበጎነት የተዘረጉት የአቢሲንያ አሚን እጆች እንደ ሁልጊዜውም በፆም ወቅት በቂ ማፍጠሪያ ማግኘት ለማይችሉና ለተቸገሩ ወገኖቹ በመድረስ ላይ የሚገኝ ሲሆን፣ በዚህም በኮምቦልቻ ከተማ ከሚገኙ የተራድኦ ተቋማት ጋር በመቀናጀትና ድጋፍ በማድረግ ማኅበራዊ ኃላፊነቱን በመወጣት ላይ ይገኛል።
የበጎነት አሻራውን በማሳረፍም ከተቸገሩ ወገኖቹ ጎን እንደሚቆም አስመስክሯል።
አሚን ለበጎነት!

❤37👏3😱2