Bank of Abyssinia
183K subscribers
1.68K photos
154 videos
51 files
514 links
Bank of Abyssinia – The Choice for All
Welcome to BoA’s official Telegram channel!

Use @BOA_ATM_bot to access:

ATM locators
Card services & support
Real-time updates
Download Telegram
ባንካችን ማርች 8 አስመልክቶ ያዘጋጀው ባዛር ነገ በመስቀል አደባባይ ይከፈታል

ባንካችን አቢሲንያ በየዓመቱ የሚከበረውን ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን ማርች 8 አስመልክቶ ለ4ተኛ ጊዜ ባዘጋጀው የ”እችላለሁ!” መርሐ ግብር ካዘጋጃችው የተለያዩየተሰጥኦ ውድድሮች በተጨማሪ ማኅበራዊ ኃላፊነትን ከመወጣት አንጻር የሚሰሩ ስራዎችም አሉት፡፡

ከእነዚህም መካከል ሴት ደንበኞቻችንና ከባንካችን ብድር የወሰዱ ሴት የሥራ ፈጣሪዎች ሥራቸውን የሚያስተዋውቁበትናምርቶቻቸውን ለሽያጭ የሚያቀርቡበት የንግድ ትርዒትና ባዛር ነው፡፡

በዚህ ከነገ መጋቢት 16 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ለ 3 ቀናት በመስቀል አደባባይ በሚካሄደው የንግድትርኢትና ባዛር ላይ ወደ 100 የሚደርሱ ሴት የሥራ ፈጣሪዎች ይሳተፋሉ፡፡ ይምጡና ይጎብኙት፣ ያሻዎትን ይሸምቱ፣ ይደሰቱበት!
👍9611😁7👏4🤩4🔥1
የባንካችን እችላለሁ መርሃ ግብር አካል የሆነው የሴት ስራ ፈጣሪዎች የንግድ ትዕይትና ባዛር ዛሬ በድምቀት ተከፈተ

ባንካችን አቢሲንያ የአለም አቀፍ የሴቶች ቀንን ማለትም (ማርች 8ን) ምክንያት በማድረግ ለአራተኛ ጊዜ ያዘጋጀው የእችላለሁ መርሃ ግብር ዘንድሮ በአይነቱ ለየት ብሎ ፣ በተለያዩ ማህበረሰቡን በሚያሳትፉ ተግባሮች ታጅቦ እንደቀጠለ ይገኛል፡፡
በዛሬው ዕለት በመስቀል አደባባይ በይፋ የተከፈተው የንግድ ትርኢት እና ባዛር፣ ሴት የስራ ፈጣሪዎችን ለማበረታታት ይቻል ዘንድ፤ የንግድ ትስስር ለመፍጠር እንዲግዝ በተጨማሪም ሴት የስራ ፈጣሪዎች የተለያዩ ምርትና አገልግሎታቸውን ለማህበረሰብ ማቅረብ ይችሉ ዘንድ ታስቦ የተከወነ ነው፡፡
መርሃ ግብሩን በይፋ መርቀው የከፈቱት የባንካችን ዋና -ኢንተርፕራይዝኦፊሰር የሆኑት ወ/ሮ መሠረት አስፋው እንዲሁም ወ/ሮ ትሁና ስንሻው በሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የሴቶች ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ማጎልበት ዴስክ ሃላፊ ሲሆኑ በተጨማሪም የኢትዮጵያ ሴት ነጋዴዎች ማህበር ፕሬዝዳንትና ለስራ ፈጣሪ ሴቶች ተምሳሌት በመሆን የበኩሏን እየተወጣች የምትገኘው ወ/ሮ በረከት ወርቁ (በረከት ገበሬዋ)፣ የባንካችን ከፍተኛ የስራ መሪዎች፣ በተለያየ ደረጃ የሚገኙ የስራ ሃላፊዎችና የቅርንጫፍ ስራ አስኪያጆች ናቸው፡፡
እንደሚታወሰው ባንካችን አቢሲንያ ማኅበራዊ ሃላፊነቱን ከሚወጣባቸው ተግባራት አንዱ አካል በሆነው የእችላለሁ መርሃ ግብር ውድድር እስከ መጋቢት 22 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ የሚቆይ ከድምፅ ውድድር በተጨማሪ በቲክታክ የባንካችንን አደይ እና ዘሃራ የቁጠባ ሂሳቦችን በተለየ መልኩ ማስተዋወቅን ጨምሮ የመርሃ ግብሩ አካል የሆነው ለሴት የስራ ፈጣሪዎች በአነስተኛ ወለድ ያለ ማስያዣ አስከ ብር 500 ሺህ ድረስ ብድር ተመቻችቷል፡፡
በዛሬው ዕለት በይፋ የተከፈተው የንግድ ትርኢትና ባዛር በመስቀል አደባባይ እስከ መጋቢት 18 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ የሚቆይ በመሆኑ በመጎብኘትና ግብይት በመፈፀም ስራ ፈጣሪዎችን እንድታበረታቱ እንጋብዛለን፡፡
👍567
👍265🔥3🤩1
👍5620👏6🤩4😁2
የኛ አይቆርጥም!
ከአቢሲንያ ባንክ ሂሳብዎ ወደ ሌላ አቢሲንያ ባንክ ሂሳብ በባንካችን ሞባይል ባንኪንግ ገንዘብ ሲልኩ የአገልግሎት ክፍያ አይጠየቁም

#Mobilebanking #Unlimited_Transfer #withinBoa #bankofabyssinia #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ
👍156😁1816👏16🤔12🔥6
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የእህቶቻችንን ህልም ያሳካ ብድር

ክፍል ሁለት

በክፍል አንድ ዝግጅታችን ላይ በባንካችን የሶስተኛ ዙር የሴቶች የስራ ፈጠራ ውድድር ላይ “በስራ ፈጠራ“ ዘርፍ አሸናፊ ከነበሩ በርካታ ስኬታማ ሴቶች መካከል የትዝታን የምስክርነት ቪዲዮ ተከታትለንነበር። የትዝታ ተሞክሮ ሴት እህቶቻችን የፋይናንስ ድጋፍ ካገኙ ህልማቸውን ከማሳካት ወደ ኋላ የሚያስቀራቸው
አንዳችም ነገርእንደሌለ ጥሩ ማሳያ ነው።

ለዛሬ ደግሞ የሌላኛዋን የስራ ፈጠራ ውድድር አሸናፊ የደስደስ ጥላሁንን
ምስክርነት እናቀርብላችኋለን። የደስደስጥላሁንና በርካታ ለሌሎች አርአያ የሚሆኑ እንስቶች በአቢሲንያ የገንዘብ ድጋፍ ታግዘው አሁን ላይ ህልማቸውን ወደ ትልቅ ቢዝነስ ቀይረዋል። የደስደስና
ሌሎች እንደሷ ያሉ ወጣት የስራ ፈጣሪዎች ከአቢሲንያ ባንክ በወሰዱት ብድር የጀመሩትን ቢዝነስ በማስፋፋትና ለሌሎች ወገኖቻቸው የስራ ዕድል በመፍጠር፣ ሴቶች ድጋፍ ካገኙ የማያሳኩት ነገር እንደሌለ አስመስክረዋል።

የደስደስን ተሞክሮ ከቪዲዮው እንድትከታተሉት
እንጋብዛለን።
👍6032👏4
ዱዓና ምልጃችሁ መቅቡል ይሁን፣
ከወሩ ያገኛችሁት ምንዳና በረከት አብሯችሁ ይሰንብት፣
በስኬት ላይ ስኬትን አጎናጽፎ፤ ለከርሞ ረመዷን በአማንና በኢማን ያድርሳችሁ!!
አሚን!
ጁሙዐ ሙባረክ!

አቢሲንያ አሚን
ዕሴትዎን ያከበረ!
👏55👍3325🤩4🔥1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ለመላው የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች እንኳን ለኢድ አል ፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ ! ኢድ ሙባረክ !
👍10410👏6
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ሀገር ቤት ሩቅ ቢመስልም በካሽ ጎ ሃዋላ ለወዳጅ ዘመድ ቅርብ ይሁኑ!
#CashGo #visa #mastercard #BankofAbyssinia #የሁሉም_ምርጫ #The_Choice_For_all
👍504😱2🔥1🤩1
አቢሲንያ አሚን የዕውቅና እና የምስጋና ዋንጫ ተበረከተለት

አቢሲንያ አሚን በባንክ ኢንዱስትሪው እያስመዘገበ ካለው አመርቂ ውጤት ጐን ለጐን ባንካችን ካስቀመጣቸው ዕሴቶች መካከል አንዱ ከሆነው ማህበራዊ ኃላፊነትን ከመወጣት አኳያም ማህበረሰብን የማገልገል ሥራ በሰፊው እየሰራ እንደሚገኝ የሚታወቅ ነው፡፡ታዲያ ባንካችን ላደረገው አስተዋፅኦ የኦሮሚያ ክልል አስተዳደር እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ዕውቅናና ምስጋና በማቅረብ የክብር ዋንጫ አበርክቷል፡፡

መጋቢት 6 ቀን 2017 ዓ.ም በስካይላይት ሆቴል በተዘጋጀው የዕውቅና ሥነ-ሥርዓት ላይ በመገኘት ሽልማቱን የተረከቡት የባንካችን ዋና የአቢሲንያ አሚን ኦፊሰር አቶ አብዱልቃድር ሬድዋን ሲሆኑ ባንካችን ለተሰጠው ዕውቅና ምስጋና በማቅረብ ባንኩ መሰል ስራዎች ላይ እያደረገ ያለውን ማህበራዊ አስተዋፅኦ ወደፊትም አጠናክሮ እንደሚቀጥል ቃል ገብተዋል፡፡

በፕሮግራሙ ላይ የፌደራል እስልምና ጉዳዮች ፕሬዚዳንት እና ም/ፕሬዚዳንት፣ የኦሮሚያ መጅሊስ ፕሬዚዳንት እና ም/ፕሬዚዳንት፣ የአዲስ አበባ መጅሊስ ፕሬዚዳንት፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የተከበሩ ኡስታዝ ካሚል ሸምሱና ሌሎችም ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች ተገኝተዋል፡፡

#AbyssiniaAmeen #IFB #bankofabyssinia #አቢሲኒያአሚን #Banking #BanksinEthiopia #AddisAbaba #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ
👍10313🔥4🤩3🤔2