Bank of Abyssinia
183K subscribers
1.67K photos
154 videos
51 files
513 links
Bank of Abyssinia – The Choice for All
Welcome to BoA’s official Telegram channel!

Use @BOA_ATM_bot to access:

ATM locators
Card services & support
Real-time updates
Download Telegram
👍436🤩5👏2😱1
👍57👏10🤩6🔥41
ባንካችን አቢሲንያ የአእምሮ ዕድገት ውስንነት ለገጠማቸው ሕጻናት የትምህርት እና ሥልጠና ማዕከል በማቋቋም ከ2,000 በላይ ሕጻናትን እያገዘ ያለው ዲቦራ ፋውንዴሽን “መጋቢትን ከዲቦራ ጋር” በሚል ዛሬ ለ5ኛ ጊዜ የሚያከብረውን ዓለም አቀፍ የዳውን ሲንድረም ክብረ በዓል  የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ አጋር ሆነ፡፡

በኢትዮጵያ ከአእምሮ ዕድገት ውስንነት ሕመም ጋር የሚኖሩ ከ600,000 በላይ ሕጻናት አሉ የሚል ግምት አለ፡፡ እነዚህን ሕፃናት እና ወላጆቻቸውን የማገዝ ዓላማን አንግበው የተቋቋሙ ሌሎች የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ያሉ ሲሆን፣ ከዚህ አኳያም የምስረታ ጊዜው ከአምስት ዓመት በላይ የሆነው ዲቦራ ፋውንዴሽን ያቀደው ግዙፍ ፕሮጀክት ወደ መሬት ሲወርድ ጎዶሎ የሚሞላ፣ አገራችን ያለባትን ትልቅ ክፍተት የሚደፍን እና በየቤቱ ተዘግቶባቸው ያሉ የብዙ ሕጻናትንና መኖር ስቃይ የሆነባቸውን እናቶች ችግር የሚያቀል ነው። 

ባንካችን አቢሲንያ ከመንግሥት፣ ከግብረ ሠናይ ድርጅቶችና ሌሎች ተቋማት ለተጠየቁ የድጋፍ ጥያቄዎችና ሀገራችን እና ሕዝቧ የገጠሟቸውን ችግሮች በተቻለ ለመቅረፍ ያለስስት እጆቹን በመዘርጋት ማኅበራዊ ኃላፊነቱን በሚገባ ሲወጣ ቆይቷል፡፡
ባንካችን አቢሲንያ የኢትዮጵያ ቅርስ ባለአደራ ማኅበር፣ የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር፣ ሜሪ ጆይ፣ ፓርኪንሰንስ ፔሸንት ሳፖርት ኦርጋናይዜሽን የንግድና አሠሪዎች ምክር ቤት የክብር አባል በመሆን በተጨማሪ ማኅበራዊ ኃላፊቱን እየተወጣ ይገኛል፡፡

እንዲሁም ባንካችን ዲቦራ ፋውንዴሽንንም ከምስረታ ጀምሮ አጋርነት በሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች  አጋርነቱን ሲያሳይ ቆይቷል፡፡

ብዙ ቤተሰቦች ከአእምሮ ዕድገት ውስንነት ያለባቸውን ሕፃናት ከማሳደግ ጋር ተያይዞ ከባድ ፈተና ይገጥማቸዋል፡፡ ዲቦራ ፋውንዴሽን እነዚህን ወገኖች ለማገዝ ታስቦ የተቋቋመ እንደመሆኑ ከዚህ ጋር ተያይዞ እየሠራቸው ያሉትን የትምህርት፣ ጤና እና ማኅበረሰብ አቀፍ የሆኑ ሥራዎችን አጠናክሮ እንዲቀጥል በማበረታታት የሀገር የወገን አለኝታነቱን በቀጣይም አጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል።
👍7114🔥3🤩2🥰1😁1
👍5516😁3🤩2
ባንካችን ማርች 8 አስመልክቶ ያዘጋጀው ባዛር ነገ በመስቀል አደባባይ ይከፈታል

ባንካችን አቢሲንያ በየዓመቱ የሚከበረውን ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን ማርች 8 አስመልክቶ ለ4ተኛ ጊዜ ባዘጋጀው የ”እችላለሁ!” መርሐ ግብር ካዘጋጃችው የተለያዩየተሰጥኦ ውድድሮች በተጨማሪ ማኅበራዊ ኃላፊነትን ከመወጣት አንጻር የሚሰሩ ስራዎችም አሉት፡፡

ከእነዚህም መካከል ሴት ደንበኞቻችንና ከባንካችን ብድር የወሰዱ ሴት የሥራ ፈጣሪዎች ሥራቸውን የሚያስተዋውቁበትናምርቶቻቸውን ለሽያጭ የሚያቀርቡበት የንግድ ትርዒትና ባዛር ነው፡፡

በዚህ ከነገ መጋቢት 16 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ለ 3 ቀናት በመስቀል አደባባይ በሚካሄደው የንግድትርኢትና ባዛር ላይ ወደ 100 የሚደርሱ ሴት የሥራ ፈጣሪዎች ይሳተፋሉ፡፡ ይምጡና ይጎብኙት፣ ያሻዎትን ይሸምቱ፣ ይደሰቱበት!
👍9611😁7👏4🤩4🔥1
የባንካችን እችላለሁ መርሃ ግብር አካል የሆነው የሴት ስራ ፈጣሪዎች የንግድ ትዕይትና ባዛር ዛሬ በድምቀት ተከፈተ

ባንካችን አቢሲንያ የአለም አቀፍ የሴቶች ቀንን ማለትም (ማርች 8ን) ምክንያት በማድረግ ለአራተኛ ጊዜ ያዘጋጀው የእችላለሁ መርሃ ግብር ዘንድሮ በአይነቱ ለየት ብሎ ፣ በተለያዩ ማህበረሰቡን በሚያሳትፉ ተግባሮች ታጅቦ እንደቀጠለ ይገኛል፡፡
በዛሬው ዕለት በመስቀል አደባባይ በይፋ የተከፈተው የንግድ ትርኢት እና ባዛር፣ ሴት የስራ ፈጣሪዎችን ለማበረታታት ይቻል ዘንድ፤ የንግድ ትስስር ለመፍጠር እንዲግዝ በተጨማሪም ሴት የስራ ፈጣሪዎች የተለያዩ ምርትና አገልግሎታቸውን ለማህበረሰብ ማቅረብ ይችሉ ዘንድ ታስቦ የተከወነ ነው፡፡
መርሃ ግብሩን በይፋ መርቀው የከፈቱት የባንካችን ዋና -ኢንተርፕራይዝኦፊሰር የሆኑት ወ/ሮ መሠረት አስፋው እንዲሁም ወ/ሮ ትሁና ስንሻው በሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የሴቶች ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ማጎልበት ዴስክ ሃላፊ ሲሆኑ በተጨማሪም የኢትዮጵያ ሴት ነጋዴዎች ማህበር ፕሬዝዳንትና ለስራ ፈጣሪ ሴቶች ተምሳሌት በመሆን የበኩሏን እየተወጣች የምትገኘው ወ/ሮ በረከት ወርቁ (በረከት ገበሬዋ)፣ የባንካችን ከፍተኛ የስራ መሪዎች፣ በተለያየ ደረጃ የሚገኙ የስራ ሃላፊዎችና የቅርንጫፍ ስራ አስኪያጆች ናቸው፡፡
እንደሚታወሰው ባንካችን አቢሲንያ ማኅበራዊ ሃላፊነቱን ከሚወጣባቸው ተግባራት አንዱ አካል በሆነው የእችላለሁ መርሃ ግብር ውድድር እስከ መጋቢት 22 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ የሚቆይ ከድምፅ ውድድር በተጨማሪ በቲክታክ የባንካችንን አደይ እና ዘሃራ የቁጠባ ሂሳቦችን በተለየ መልኩ ማስተዋወቅን ጨምሮ የመርሃ ግብሩ አካል የሆነው ለሴት የስራ ፈጣሪዎች በአነስተኛ ወለድ ያለ ማስያዣ አስከ ብር 500 ሺህ ድረስ ብድር ተመቻችቷል፡፡
በዛሬው ዕለት በይፋ የተከፈተው የንግድ ትርኢትና ባዛር በመስቀል አደባባይ እስከ መጋቢት 18 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ የሚቆይ በመሆኑ በመጎብኘትና ግብይት በመፈፀም ስራ ፈጣሪዎችን እንድታበረታቱ እንጋብዛለን፡፡
👍567
👍265🔥3🤩1