ባንካችን አቢሲንያ የአእምሮ ዕድገት ውስንነት ለገጠማቸው ሕጻናት የትምህርት እና ሥልጠና ማዕከል በማቋቋም ከ2,000 በላይ ሕጻናትን እያገዘ ያለው ዲቦራ ፋውንዴሽን “መጋቢትን ከዲቦራ ጋር” በሚል ዛሬ ለ5ኛ ጊዜ የሚያከብረውን ዓለም አቀፍ የዳውን ሲንድረም ክብረ በዓል የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ አጋር ሆነ፡፡
በኢትዮጵያ ከአእምሮ ዕድገት ውስንነት ሕመም ጋር የሚኖሩ ከ600,000 በላይ ሕጻናት አሉ የሚል ግምት አለ፡፡ እነዚህን ሕፃናት እና ወላጆቻቸውን የማገዝ ዓላማን አንግበው የተቋቋሙ ሌሎች የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ያሉ ሲሆን፣ ከዚህ አኳያም የምስረታ ጊዜው ከአምስት ዓመት በላይ የሆነው ዲቦራ ፋውንዴሽን ያቀደው ግዙፍ ፕሮጀክት ወደ መሬት ሲወርድ ጎዶሎ የሚሞላ፣ አገራችን ያለባትን ትልቅ ክፍተት የሚደፍን እና በየቤቱ ተዘግቶባቸው ያሉ የብዙ ሕጻናትንና መኖር ስቃይ የሆነባቸውን እናቶች ችግር የሚያቀል ነው።
ባንካችን አቢሲንያ ከመንግሥት፣ ከግብረ ሠናይ ድርጅቶችና ሌሎች ተቋማት ለተጠየቁ የድጋፍ ጥያቄዎችና ሀገራችን እና ሕዝቧ የገጠሟቸውን ችግሮች በተቻለ ለመቅረፍ ያለስስት እጆቹን በመዘርጋት ማኅበራዊ ኃላፊነቱን በሚገባ ሲወጣ ቆይቷል፡፡
ባንካችን አቢሲንያ የኢትዮጵያ ቅርስ ባለአደራ ማኅበር፣ የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር፣ ሜሪ ጆይ፣ ፓርኪንሰንስ ፔሸንት ሳፖርት ኦርጋናይዜሽን የንግድና አሠሪዎች ምክር ቤት የክብር አባል በመሆን በተጨማሪ ማኅበራዊ ኃላፊቱን እየተወጣ ይገኛል፡፡
እንዲሁም ባንካችን ዲቦራ ፋውንዴሽንንም ከምስረታ ጀምሮ አጋርነት በሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች አጋርነቱን ሲያሳይ ቆይቷል፡፡
ብዙ ቤተሰቦች ከአእምሮ ዕድገት ውስንነት ያለባቸውን ሕፃናት ከማሳደግ ጋር ተያይዞ ከባድ ፈተና ይገጥማቸዋል፡፡ ዲቦራ ፋውንዴሽን እነዚህን ወገኖች ለማገዝ ታስቦ የተቋቋመ እንደመሆኑ ከዚህ ጋር ተያይዞ እየሠራቸው ያሉትን የትምህርት፣ ጤና እና ማኅበረሰብ አቀፍ የሆኑ ሥራዎችን አጠናክሮ እንዲቀጥል በማበረታታት የሀገር የወገን አለኝታነቱን በቀጣይም አጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል።

👍71❤14🔥3🤩2🥰1😁1