Bank of Abyssinia
183K subscribers
1.67K photos
154 videos
51 files
513 links
Bank of Abyssinia – The Choice for All
Welcome to BoA’s official Telegram channel!

Use @BOA_ATM_bot to access:

ATM locators
Card services & support
Real-time updates
Download Telegram
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አንዳንድ አጭበርባሪዎች ከፋይናንስ ተቋም ነው የምደውለው በማለት ለመስመር ብድር እንዲመዘገቡ በተለያዩ የማማለያ ቃላት በማግባባት የኤ.ቲ.ኤም ካርድ ቁጥርዎን ሚስጥራዊ መረጃና የአንድጊዜ የይለፍ ቃልዎን (ኦ.ቲ.ፒ) እየጠየቁ እንደሚገኙ ተደርሶበታል ፡፡ በመሆኑም እነኚህን ሚስጥራዊ መረጃዎችን ለማንም እንዳያጋሩና በጥንቃቄ እንዲይዙ እያሳሰብን ለመስመር ብድርም መመዝገብ ከፈለጉ፣ ህጋዊ መስመሩን ተከትለው ማከናወን እንደሚችሉ እንገልጽልዎታለን፡፡
በተጨማሪም እንዲህ አይነት መረጃዎችን ሲጠየቁ፣ መረጃውን ሳይናግሩ ወደ ባንካችን ነፃ የስልክ መስመር 8397 ይደውሉ፡፡
👍63👌3😁2🤩21
ባንካችን አቢሲንያ ከቶሞካቡና ጋር በጥምረት የጀመረውን ልዩ ካፌ ለአገልግሎት ክፍት አደረገ

ባንካችን አቢሲንያ ደንበኞች እየተዝናኑ የባንክ አገልግሎት ማግኘት ይችሉ ዘንድ ቅርንጫፎችን ከካፌ ጋር በማቀናጀት ሁለተኛውንልዩ ካፌ (Branch with Café) በባንካችን ኤርፖርት ቅርንጫፍ ለአገልግሎት ክፍት አድርጓል፡፡
በዛሬው ይፋዊ የምርቃት ሥነ-ሥርዓት አገልግሎት የጀመረው ይህ ልዩ ካፌ የወቅቱን የባንክ ቴክኖሎጂዎች በማስተዋወቅ የሚታወቀው ባንካችን አቢሲንያ እና በቡና አቅርቦቱ ከግማሽ ክፍለ ዘመን በላይ ከሚታወቀው ቶሞካ ቡና ጋር በጥምረት የከፈተው ነው፡፡
አገልግሎቱ በአሁኑዘመን ሰዎች በቀላሉ ከቴክኖሎጂ የሚያገኙትን ደስታ ከባንክ አገልግሎት ጋር በማጣመር እየተዝናኑ ጎን ለጎን በቴክኖሎጂ የታገዘ የባንክ አገልግሎት የሚያገኙበትን ምቹ ሁኔታን የሚፈጥር ነው፡፡
ዓላማው ቀለል ያለአገልግሎትን መስጠት፣ የደንበኞቻችንን ልምድ ማሻሻል እና የባንክ ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ከፍ ማድረግ ሲሆን በተጨማሪም ደንበኞች ለመገልገል ሲመጡ፦
✔️ በተመቸ ከባቢ ውስጥ የካፌ አገልግሎት እየተጠቀሙ እንደ ሞባይል ባንኪንግ ፣ፖስ ፣አይ ቲ ኤም እና ኤቲ.ኤም ማሽን በመሳሰሉ ራስ አገዝ የባንክ ቴክኖሎጂዎች በቀላሉ አገልግሎት ያገኛሉ፣
✔️ በካፌው ውስጥ ምንም አይነት የጥሬ ገንዘብ ግብይት የማይኖር ሲሆን ሁሉም ግብይቶች ቴክኖሎጂን ማዕከል ባደረገ መልኩ በስፍራው ባሉ ታብሌቶች ፣ኤ.ቲ.ኤም፣ ኪዉ.አር እና በሞባይል ባንክ ያከናውናሉ፣
✔️ በባንካችን ዘመናዊ የክፍያ አማራጮች (ዴቢት እና ክሬዲት ካርዶች) አገልግሎቱን የሚጠቀሙ የባንካችን ደንበኞችም የልዩ ቅናሽ ተጠቃሚይሆናሉ፡፡
በምርቃቱ ሥነ-ሥርዓት ላይም ባንካችን ጥሩ ጣዕም ባለው ቡናውና በአገልግሎቱ ከሚታወቀው ቶሞካቡና ጋር በአጋርነት በመስራቱ ደስተኛ መሆኑንን ገልጾ ይህ ፕሮጀክት የተሳካ እንዲሆን ላደረጉ የባንኩ የሥራ ክፍል ኃላፊዎችና ሠራተኞች እና ለቶሞካ ቡና ባለቤትና ሠራተኞች ምስጋናውን አቅርቧል፡፡
👍5616
👍436🤩5👏2😱1
👍57👏10🤩6🔥41
ባንካችን አቢሲንያ የአእምሮ ዕድገት ውስንነት ለገጠማቸው ሕጻናት የትምህርት እና ሥልጠና ማዕከል በማቋቋም ከ2,000 በላይ ሕጻናትን እያገዘ ያለው ዲቦራ ፋውንዴሽን “መጋቢትን ከዲቦራ ጋር” በሚል ዛሬ ለ5ኛ ጊዜ የሚያከብረውን ዓለም አቀፍ የዳውን ሲንድረም ክብረ በዓል  የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ አጋር ሆነ፡፡

በኢትዮጵያ ከአእምሮ ዕድገት ውስንነት ሕመም ጋር የሚኖሩ ከ600,000 በላይ ሕጻናት አሉ የሚል ግምት አለ፡፡ እነዚህን ሕፃናት እና ወላጆቻቸውን የማገዝ ዓላማን አንግበው የተቋቋሙ ሌሎች የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ያሉ ሲሆን፣ ከዚህ አኳያም የምስረታ ጊዜው ከአምስት ዓመት በላይ የሆነው ዲቦራ ፋውንዴሽን ያቀደው ግዙፍ ፕሮጀክት ወደ መሬት ሲወርድ ጎዶሎ የሚሞላ፣ አገራችን ያለባትን ትልቅ ክፍተት የሚደፍን እና በየቤቱ ተዘግቶባቸው ያሉ የብዙ ሕጻናትንና መኖር ስቃይ የሆነባቸውን እናቶች ችግር የሚያቀል ነው። 

ባንካችን አቢሲንያ ከመንግሥት፣ ከግብረ ሠናይ ድርጅቶችና ሌሎች ተቋማት ለተጠየቁ የድጋፍ ጥያቄዎችና ሀገራችን እና ሕዝቧ የገጠሟቸውን ችግሮች በተቻለ ለመቅረፍ ያለስስት እጆቹን በመዘርጋት ማኅበራዊ ኃላፊነቱን በሚገባ ሲወጣ ቆይቷል፡፡
ባንካችን አቢሲንያ የኢትዮጵያ ቅርስ ባለአደራ ማኅበር፣ የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር፣ ሜሪ ጆይ፣ ፓርኪንሰንስ ፔሸንት ሳፖርት ኦርጋናይዜሽን የንግድና አሠሪዎች ምክር ቤት የክብር አባል በመሆን በተጨማሪ ማኅበራዊ ኃላፊቱን እየተወጣ ይገኛል፡፡

እንዲሁም ባንካችን ዲቦራ ፋውንዴሽንንም ከምስረታ ጀምሮ አጋርነት በሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች  አጋርነቱን ሲያሳይ ቆይቷል፡፡

ብዙ ቤተሰቦች ከአእምሮ ዕድገት ውስንነት ያለባቸውን ሕፃናት ከማሳደግ ጋር ተያይዞ ከባድ ፈተና ይገጥማቸዋል፡፡ ዲቦራ ፋውንዴሽን እነዚህን ወገኖች ለማገዝ ታስቦ የተቋቋመ እንደመሆኑ ከዚህ ጋር ተያይዞ እየሠራቸው ያሉትን የትምህርት፣ ጤና እና ማኅበረሰብ አቀፍ የሆኑ ሥራዎችን አጠናክሮ እንዲቀጥል በማበረታታት የሀገር የወገን አለኝታነቱን በቀጣይም አጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል።
👍7114🔥3🤩2🥰1😁1
👍5516😁3🤩2