ሓጃችሁ መብሩር፣ ሰዕያችሁ መሽኩር እንዲሆን ከልብ የሚመኘው አቢሲንያ አሚን እንኳን ለ1446ኛው (ዓመተ ሂጅራ) የሐጅ እና ዑምራ ጉዞ በሠላም አደረሳችሁ እያለ፤ የሸሪዓ መርህን መሠረት አድርጐ በተዘጋጀው የሐጅና ዑምራ የሙዳራባህ ሂሳብ በመጠቀም፤ አንድም የሐጅና ዑምራ ንያዎን እንዲያሳኩ፣ ሁለትም ከሐላል ኢንቨስትመንት ከሚገኘው ትርፍ ተካፋይ በመሆን ከኛ ጋር በስኬት እንዲጓዙ በአክብሮት ይጋብዝዎታል፡፡
ሐጀን መብሩር፣ ወሰዕየን መሽኩር!
አቢሲንያ አሚን
ዕሴትዎን ያከበረ!
ሐጀን መብሩር፣ ወሰዕየን መሽኩር!
አቢሲንያ አሚን
ዕሴትዎን ያከበረ!
👍59🔥7🤩4
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አንዳንድ አጭበርባሪዎች ከፋይናንስ ተቋም ነው የምደውለው በማለት ለመስመር ብድር እንዲመዘገቡ በተለያዩ የማማለያ ቃላት በማግባባት የኤ.ቲ.ኤም ካርድ ቁጥርዎን ሚስጥራዊ መረጃና የአንድጊዜ የይለፍ ቃልዎን (ኦ.ቲ.ፒ) እየጠየቁ እንደሚገኙ ተደርሶበታል ፡፡ በመሆኑም እነኚህን ሚስጥራዊ መረጃዎችን ለማንም እንዳያጋሩና በጥንቃቄ እንዲይዙ እያሳሰብን ለመስመር ብድርም መመዝገብ ከፈለጉ፣ ህጋዊ መስመሩን ተከትለው ማከናወን እንደሚችሉ እንገልጽልዎታለን፡፡
በተጨማሪም እንዲህ አይነት መረጃዎችን ሲጠየቁ፣ መረጃውን ሳይናግሩ ወደ ባንካችን ነፃ የስልክ መስመር 8397 ይደውሉ፡፡

👍63👌3😁2🤩2❤1
ባንካችን አቢሲንያ ከቶሞካቡና ጋር በጥምረት የጀመረውን ልዩ ካፌ ለአገልግሎት ክፍት አደረገ
ባንካችን አቢሲንያ ደንበኞች እየተዝናኑ የባንክ አገልግሎት ማግኘት ይችሉ ዘንድ ቅርንጫፎችን ከካፌ ጋር በማቀናጀት ሁለተኛውንልዩ ካፌ (Branch with Café) በባንካችን ኤርፖርት ቅርንጫፍ ለአገልግሎት ክፍት አድርጓል፡፡
በዛሬው ይፋዊ የምርቃት ሥነ-ሥርዓት አገልግሎት የጀመረው ይህ ልዩ ካፌ የወቅቱን የባንክ ቴክኖሎጂዎች በማስተዋወቅ የሚታወቀው ባንካችን አቢሲንያ እና በቡና አቅርቦቱ ከግማሽ ክፍለ ዘመን በላይ ከሚታወቀው ቶሞካ ቡና ጋር በጥምረት የከፈተው ነው፡፡
አገልግሎቱ በአሁኑዘመን ሰዎች በቀላሉ ከቴክኖሎጂ የሚያገኙትን ደስታ ከባንክ አገልግሎት ጋር በማጣመር እየተዝናኑ ጎን ለጎን በቴክኖሎጂ የታገዘ የባንክ አገልግሎት የሚያገኙበትን ምቹ ሁኔታን የሚፈጥር ነው፡፡
ዓላማው ቀለል ያለአገልግሎትን መስጠት፣ የደንበኞቻችንን ልምድ ማሻሻል እና የባንክ ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ከፍ ማድረግ ሲሆን በተጨማሪም ደንበኞች ለመገልገል ሲመጡ፦
✔️ በተመቸ ከባቢ ውስጥ የካፌ አገልግሎት እየተጠቀሙ እንደ ሞባይል ባንኪንግ ፣ፖስ ፣አይ ቲ ኤም እና ኤቲ.ኤም ማሽን በመሳሰሉ ራስ አገዝ የባንክ ቴክኖሎጂዎች በቀላሉ አገልግሎት ያገኛሉ፣
✔️ በካፌው ውስጥ ምንም አይነት የጥሬ ገንዘብ ግብይት የማይኖር ሲሆን ሁሉም ግብይቶች ቴክኖሎጂን ማዕከል ባደረገ መልኩ በስፍራው ባሉ ታብሌቶች ፣ኤ.ቲ.ኤም፣ ኪዉ.አር እና በሞባይል ባንክ ያከናውናሉ፣
✔️ በባንካችን ዘመናዊ የክፍያ አማራጮች (ዴቢት እና ክሬዲት ካርዶች) አገልግሎቱን የሚጠቀሙ የባንካችን ደንበኞችም የልዩ ቅናሽ ተጠቃሚይሆናሉ፡፡
በምርቃቱ ሥነ-ሥርዓት ላይም ባንካችን ጥሩ ጣዕም ባለው ቡናውና በአገልግሎቱ ከሚታወቀው ቶሞካቡና ጋር በአጋርነት በመስራቱ ደስተኛ መሆኑንን ገልጾ ይህ ፕሮጀክት የተሳካ እንዲሆን ላደረጉ የባንኩ የሥራ ክፍል ኃላፊዎችና ሠራተኞች እና ለቶሞካ ቡና ባለቤትና ሠራተኞች ምስጋናውን አቅርቧል፡፡

👍56❤16