Bank of Abyssinia
183K subscribers
1.67K photos
154 videos
51 files
513 links
Bank of Abyssinia – The Choice for All
Welcome to BoA’s official Telegram channel!

Use @BOA_ATM_bot to access:

ATM locators
Card services & support
Real-time updates
Download Telegram
ለዱዓችሁም ሆነ ለሥራችሁ...
አሚን በእጃችሁ!

ከምንግዜም በላቀ በተለያዩ የዒባዳ ተግባራት የምንደምቅበት ታላቁ ወር ረመዷን፤ መንፈሳዊ ከፍታን ያላብሰናል። እኛም ይህን አስጠብቀንና ውጤታማ ሆነን ለመገኘት በዕለት ተዕለት የህይወት እንቅስቃሴያችን አሚን እንላለን!
አሚን ...
አንድም ለዱዓችን፤ አንድም ለሥራችን!!
ጁሙዐ ሙባረክ!

አቢሲንያ አሚን
ዕሴትዎን ያከበረ!
👍4933😁10
ቀደም ባሉት ጊዜያት የምንፈልገውን ዕቃ ለመግዛት ብዙ ስፍራዎችን ማዳረስ ይጠበቅብን ነበር። አሁን ላይ ግን ባለንበት ስፍራ ሆነን የምንሸምትበት የበይነ መረብ ግብይት ወይም ኢ-ኮሜርስ ፕላትፎርሞች ተፈጥረዋል።
በዚህ ፕላትፎርም ሻጮች ዕቃቸውን በድረ-ገጾቻቸው ላይ የሚያስተዋውቁ ሲሆን ገዢዎችም በሚመቻቸው የክፍያ ስርዓት ተጠቅመው ይከፍላሉ። ባንካችንም ለዚህ የተለያዩ የክፍያ ስርዓቶችን በማስተዋወቅ ፈር-ቀዳጅ እንደሆነ የሚታወቅ ሲሆን በቅርቡም የባንካችን የስራ ሃላፊና ሌሎች ባለሙያዎች በአርትስ ቲቪ ስለጉዳዩ ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል። እኛም እንድትከታተሉት በአክብሮት ጋብዘናችኋል። https://youtu.be/TCaWcQbLk4Q?si=B79DOmOMHMT9Yg-q
👍61👏116
ባንኮክ ላይ ፏ ብትን ይሉ ይሆናል!
ሊያውም ከሚወዱት ተጨማሪ አንድ ሰው ጋር! አሁኑኑ አፖሎን በማውረድ እና በማጋራት ወይም ዲፖዚት በማድረግ የእጣ ቁጥራችሁን ያዙ!

የመርሃ ግብሩን ዝርዝር መረጃ ከዚህ ያግኙ፡፡
https://t.me/BoAEth/1525
አፖሎን በማውረድ ተሳታፊ ይሁኑ፡
ለአንድሮይድ ስልኮች: https://play.google.com/store/apps/details...
ለአፕል ስልኮች: https://apps.apple.com/eg/app/apollo-digital/id1601224628
ለህዋዌ ስልኮች ፡https://appgallery.huawei.com/app/C108966741
#መጣሁልሽ #አምሮኛል_መጣሁልሽ #ApolloWinBig #DepositAndWin #JoinApolloGetRewarded
👍609😁6😱1
አንድምሽት በባቡል ኸይር ልዩ የኢፍጣር መርሐ ግብር ተከናወነ!
የሸሪዓውን መርሆች መሠረት አድርጎ የተሟላ ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት የሚሰጠው አቢሲንያ አሚን ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት በተለያዩ ከተሞች በመገኘት ለተቸገሩ ወገኖቻችን የረመዳን የኢፍጣር መርሐ ግብሩን እያከናወነ የሚገኝ ሲሆን በትላንትናው ዕለት መጋቢት 10/2017 ምሽት "አንድ ምሽት በባቡል ኸይር" በሚል መሪ ሐሳብ በባቡል ኸይር የበጎ አድራጎት ድርጅት በመገኘት የኢፍጣር መርሐ ግብር አከናውኗል።
በመርሐ ግብሩ አቶ አብዱልቃድር ሪድዋን ዋና ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት ኦፊሰር፣ የአቢሲንያ አሚን ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ የአቢሲንያ አሚን ብራንድ አምባሳደር ሙሐመድ ፈረጅና፤ ሌሎች የባንኩ ሠራተኞች ተገኝተዋል።
የኢፍጣር መርሐ ግብሩን በባቡል ኸይር የበጎ አድራጎት ድርጅት ያደረገው አቢሲንያ አሚን፤ በበርካታ ማኅበረሰብ አቀፍ የበጎ አድራጎት ሥራዎች ላይ በሚያደርገው ተሳትፎና በሚያኖረው አሻራዎቹ የሚታወቅ ሲሆን፤ የትላንትናው የኢፍጣር መርሐ ግብርም የዚሁ አካል መሆኑ በመድረኩ ተወስቷል።
በተለያዩ የአገራችን አካባቢዎች ከተሰማሩ የተራድኦ ተቋማት ጋር በመቀናጀት በንጹህ የመጠጥ ውሃ ቁፋሮ፣ ለአካል ጉዳተኞች የዊልቼር ድጋፍ በማድረግና በተፈጥሮና በሰው ሰራሽ አደጋዎች ተጎጂና ተጋላጭ ለሆኑ ወገኖቻችን ምግብና መሰል አስፈላጊ ግብዓቶችን ድጋፍ ከማድረጉ ባሻገር፤ በስኩል አዋርድ ፕሮግራሙ በትምህርት ውጤታቸው የላቀ ደረጃ ያስመዘገቡ ተማሪዎችን እና መምህራንን በመሸለምና በማበረታታት በትምህርት ልማትና ጥራት ላይም እየሠራ ይገኛል።
በወለድ ነፃ የፋይናንስ ሥርዓት ሰፊ ተደራሽነትና የከበረ ሥም ያለው አቢሲንያ አሚን፤ በሥራ ፈጠራ አቅማቸው ችግሮችን ወደ ዕድል መቀየር ለሚችሉ በርካታ ኢንተርፕሩነሮች በየደረጃው እስከ ብር አንድ ሚሊየን ድረስ የሚያሸልመውን "አሚን አዋርድ የሥራ ፈጠራ ውድድር" በሁለት ዙር በማዘጋጀት፤ ከተለያዩ የሃገራችን አካባቢዎች የተሳተፉ ባለሙያዎችን በቅርበት ሲያግዝና አቅማቸውን መጠቀም እንዲችሉ ሲያነቃቃ ቆይቷል።
በትላንትናው ምሽት መርሐ ግብር አቢሲንያ አሚንን በልዩነት ያመሰገኑት የባቡል ኸይር መሥራችና ሥራ አስኪያጅ ወ/ሮ ሃናን ማህሙድ፤ የአቢሲንያ አሚን ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ካደረጋችሁልን ድጋፍ ባሻገር ዛሬን ከኛ ጋር ውላችሁ ለወገኖቻችሁ ላሳያችሁት አብሮነት ክብር አለን ያሉ ሲሆን፤ ባቡል ኸይር የበጎ አድራጎት ድርጅት የምገባ ተግባሩን ከአምስት ዓመት በፊት ሲጀምር የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ ቀዳሚው የፋይናንስ ተቋም አቢሲንያ አሚን እንደነበረ በማውሳት ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡
👍608👌5🔥4🤩3😁2
👍7218🤩6😱4👏3
ሓጃችሁ መብሩር፣ ሰዕያችሁ መሽኩር እንዲሆን ከልብ የሚመኘው አቢሲንያ አሚን እንኳን ለ1446ኛው (ዓመተ ሂጅራ) የሐጅ እና ዑምራ ጉዞ በሠላም አደረሳችሁ እያለ፤ የሸሪዓ መርህን መሠረት አድርጐ በተዘጋጀው የሐጅና ዑምራ የሙዳራባህ ሂሳብ በመጠቀም፤ አንድም የሐጅና ዑምራ ንያዎን እንዲያሳኩ፣ ሁለትም ከሐላል ኢንቨስትመንት ከሚገኘው ትርፍ ተካፋይ በመሆን ከኛ ጋር በስኬት እንዲጓዙ በአክብሮት ይጋብዝዎታል፡፡
ሐጀን መብሩር፣ ወሰዕየን መሽኩር!

አቢሲንያ አሚን
ዕሴትዎን ያከበረ!
👍59🔥7🤩4
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አንዳንድ አጭበርባሪዎች ከፋይናንስ ተቋም ነው የምደውለው በማለት ለመስመር ብድር እንዲመዘገቡ በተለያዩ የማማለያ ቃላት በማግባባት የኤ.ቲ.ኤም ካርድ ቁጥርዎን ሚስጥራዊ መረጃና የአንድጊዜ የይለፍ ቃልዎን (ኦ.ቲ.ፒ) እየጠየቁ እንደሚገኙ ተደርሶበታል ፡፡ በመሆኑም እነኚህን ሚስጥራዊ መረጃዎችን ለማንም እንዳያጋሩና በጥንቃቄ እንዲይዙ እያሳሰብን ለመስመር ብድርም መመዝገብ ከፈለጉ፣ ህጋዊ መስመሩን ተከትለው ማከናወን እንደሚችሉ እንገልጽልዎታለን፡፡
በተጨማሪም እንዲህ አይነት መረጃዎችን ሲጠየቁ፣ መረጃውን ሳይናግሩ ወደ ባንካችን ነፃ የስልክ መስመር 8397 ይደውሉ፡፡
👍63👌3😁2🤩21
ባንካችን አቢሲንያ ከቶሞካቡና ጋር በጥምረት የጀመረውን ልዩ ካፌ ለአገልግሎት ክፍት አደረገ

ባንካችን አቢሲንያ ደንበኞች እየተዝናኑ የባንክ አገልግሎት ማግኘት ይችሉ ዘንድ ቅርንጫፎችን ከካፌ ጋር በማቀናጀት ሁለተኛውንልዩ ካፌ (Branch with Café) በባንካችን ኤርፖርት ቅርንጫፍ ለአገልግሎት ክፍት አድርጓል፡፡
በዛሬው ይፋዊ የምርቃት ሥነ-ሥርዓት አገልግሎት የጀመረው ይህ ልዩ ካፌ የወቅቱን የባንክ ቴክኖሎጂዎች በማስተዋወቅ የሚታወቀው ባንካችን አቢሲንያ እና በቡና አቅርቦቱ ከግማሽ ክፍለ ዘመን በላይ ከሚታወቀው ቶሞካ ቡና ጋር በጥምረት የከፈተው ነው፡፡
አገልግሎቱ በአሁኑዘመን ሰዎች በቀላሉ ከቴክኖሎጂ የሚያገኙትን ደስታ ከባንክ አገልግሎት ጋር በማጣመር እየተዝናኑ ጎን ለጎን በቴክኖሎጂ የታገዘ የባንክ አገልግሎት የሚያገኙበትን ምቹ ሁኔታን የሚፈጥር ነው፡፡
ዓላማው ቀለል ያለአገልግሎትን መስጠት፣ የደንበኞቻችንን ልምድ ማሻሻል እና የባንክ ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ከፍ ማድረግ ሲሆን በተጨማሪም ደንበኞች ለመገልገል ሲመጡ፦
✔️ በተመቸ ከባቢ ውስጥ የካፌ አገልግሎት እየተጠቀሙ እንደ ሞባይል ባንኪንግ ፣ፖስ ፣አይ ቲ ኤም እና ኤቲ.ኤም ማሽን በመሳሰሉ ራስ አገዝ የባንክ ቴክኖሎጂዎች በቀላሉ አገልግሎት ያገኛሉ፣
✔️ በካፌው ውስጥ ምንም አይነት የጥሬ ገንዘብ ግብይት የማይኖር ሲሆን ሁሉም ግብይቶች ቴክኖሎጂን ማዕከል ባደረገ መልኩ በስፍራው ባሉ ታብሌቶች ፣ኤ.ቲ.ኤም፣ ኪዉ.አር እና በሞባይል ባንክ ያከናውናሉ፣
✔️ በባንካችን ዘመናዊ የክፍያ አማራጮች (ዴቢት እና ክሬዲት ካርዶች) አገልግሎቱን የሚጠቀሙ የባንካችን ደንበኞችም የልዩ ቅናሽ ተጠቃሚይሆናሉ፡፡
በምርቃቱ ሥነ-ሥርዓት ላይም ባንካችን ጥሩ ጣዕም ባለው ቡናውና በአገልግሎቱ ከሚታወቀው ቶሞካቡና ጋር በአጋርነት በመስራቱ ደስተኛ መሆኑንን ገልጾ ይህ ፕሮጀክት የተሳካ እንዲሆን ላደረጉ የባንኩ የሥራ ክፍል ኃላፊዎችና ሠራተኞች እና ለቶሞካ ቡና ባለቤትና ሠራተኞች ምስጋናውን አቅርቧል፡፡
👍5616
👍436🤩5👏2😱1