ቢጠቅሞት ካነበብነው እናካፍሎት
174 subscribers
82 photos
4 links
📖⁣ማንበብ የአስተሳሰብ ልህቀትን ያጎናፅፋል።
📖⁣ማንበብ የእውቀት አድማስን ያሰፋል።
📖⁣ማንበብ የቆሸሸ ስብዕናን ያፀዳል።
📖⁣ማንበብ ምክንያታዊ ፣ጠያቂ እና የሰላ አእምሮን ያጎናጽፋል።
Download Telegram
" ዐይነ ሕሊናህን ገልጠህ ወደ ውስጥህና ዙሪያ ገባህን ብታስተውል በሀብት የተከበብክ መሆንህን ትገነዘባለህ። ሕይወትህን አስደሳችና ምሉዕ ለማድረግ የሚያስችል የወርቅ ማዕድን በውስጥህ ይገኛል። ብዙዎቹ ሀብቶችህ በግልፅ ስለማይስተዋሉ የሌሉ ይመስላሉ። ነገር ግን መኖራቸውን ተገንዝበህ አውጥተህ ከተጠቀምክባቸው ተዓምራትን ይሰራሉ። የማግኔት ሞገድ በላዩ ላይ ያረፈበት ቁራጭ ብረት ከራሱ ክብደት 12 እጥፍ ክብደት ያለውን ነገር ይስባል/ያነሳል፤ ያንኑ ቁራጭ ብረት ግን ኢ-ማግኔታዊ ብታደርግም የዶሮ ላባ እንኳን አያነሳም። በተመሳሳይ መልኩ ሁለት ዐይነት ሰዎች ናቸው ያሉት። የማግኔት ሞገድ የሰፈነበት፤ በራሱ ዕምነት ያለው እና የሚተማመን ሰው አለ። ኢ-ማግኔታዊ የሆነ፤ በፍርሃትና በግራ መጋባት የተሞላ ሰው ደግሞ አለ። ኢ-ማግኔታዊ የሆነው ሰው ዕድል ሲያጋጥመው <<ምናልባት ላይሆንልኝ ይችላል፤ ገንዘቤንም ልከስር እችላለሁ። ሰዎች ያንጓጥጡኛል>> ይላል። እንዲህ ያለው ሰው በሕይወት ረዥም ርቀት አይጓዝም። ምክንያቱም ወደ ፊት ለመጓዝ ስለሚፈራ ባለበት ይቀራል። ስለዚህ ከአንተ የሚጠበቀው ማግኔታዊ ሰው ሆነህ የሕይወትን ምስጢር መርምረህ በመረዳት መበልጸግ ነው።"

ምንጭ ፦ ድብቅ አእምሮን መግለጥ
"ነፃነት ማለት የሌሎችን ነፃነት ሳይነኩ ፣ነፃ መሆን ነው።"

ጳውሎስ ኞኞ
"በጊዜ የሚቀልዱ ሰዎችና ህዝቦች ባጠቃላይ የዕድሜያቸው መጠንና ጥራት ጊዜን በአግባቡ ከሚጠቀሙና የጊዜን መርህ ከሚያከብሩ ሰዎች ይልቅ አጭር ለመሆኑ ብዙ እማኝ አያስፈልግም ፡፡ ለምሳሌ በሠለጠኑት አገሮች የአንድ ሰው አማካይ 80: የኃላቀሮቹ ደግሞ 50 ዓመት አካባቢ ነው፡፡ ጊዜ በሚቀልዱበት ይቀልዳል ወይስ ፈጣሪ ዕድሜን ገፋ አርጎ የሚሰጠው ሊሰሩበት ለሚችሉት ብቻ ስለ ሆነ ይሆን? ወይንስ የባከነ ሰዓት በእግር ኳስ ጨዋታ ላይ ሲጨመር፡ ከሰው ሕይወት ደግሞ ስለሚቀንስ ይሆን? ያባከንነውን ጊዜ ያህል ከዕድሜያችን ላይ እንደሚቀነስ ብናውቅስ እንለወጥ ይሆን?"

የተቆለፈበት ቁልፍ ገፅ 405
"ራስ ወዳድነት በጣም መሠረታዊ የሆነ የሰው ልጅ ባህርይ ነው። ለመኖርም አስፈላጊ ነው። ከሌሎች ጋር የምንኖረው ሌሎችን ስለምንወድ ሳይሆን ከሌሎች ጋር አለመኖር ስለማንችል ነው። ከሌላው ማምለጥ የሚባል ነገር በህይወት ውስጥ የለም። በአንድ ወይም በሌላ መልክ አንተ ፈለግህም፣ አልፈለግህም ሌሎች ለአንተ መኖር አስፈላጊ ናቸው።"
``የሌሎችን ስቃይ እንደራስህ ህመም ቆጥረህ የጎደለባቸውን ለመሙላት የምትከፍለው ዋጋ ላቅ ያለ ከሆነ እውነት እልሀለው ህይወትህን በአግባቡ ኖረሀታል!!''

* * *
አልበርት አንስታይን
"እዉነተኛ ነጻነት የኅሊና ነጻነት ነው::የኅሊና ነጻነት ደግሞ እውነትን በማወቅና በመኖር ነጻ ከወጣ አእምሮ ብቻ የሚገኝ ጸጋ ነው::"
"እውነተኛ ሐብት በአክሲዮን ብዛት አሊያም ባንክ ውስጥ ባለው ተቀማጭ ገንዘብ አይወሰንም። እነርሱ የሐብት ምልክቶች ብቻ ናቸው። እውነተኛ የሐብት ምንጭ፤ በራሱም ሐብት የሆነው አስተሳሰብ ነው። በችግር ውስጥ ያሉ ሰዎች ዘወትር የተሳካላቸው ሰዎች እንዳብጠለጠሉ ናቸው። የአንዱን ሥም እያነሱ <<እርሱ አጭበርባሪ ነው>> ማለታቸው የተለመደ ነው። የሚፈልጉትን መልሰው ስለሚኮንኑ ነው የማይሳካላቸው። ሐብት በእኛ ደጅ እንዳይደርስ ለማድረግ ቀላሉ መንገድ ከእኛ የበለጠ ሐብት ያላቸውን ሰዎች መኮነን ነው።

ከኹሉ በላይ ቅናት የድህነት ምንጭ ነው። ቅናትን ማሸነፍ ቀላል ነው፤ በሰዎች ስኬት ደስ መሰኘትና ከትልቅ ደረጃም እንዲደርሱ መመኘት ብቻ ነው።
ቅናተኛ መሆን በጣም አደገኛ ነገር ነው ምክንያቱም አዕምሮን በአሉታዊ ሐሳቦች ይሞላልና። ስለዚህም ሐብት ወደ አንተ ሳይሆን የሚመጣው ከአንተ ነው የሚሸሸው። በሰዎች ስኬት ደስ መሰኘት አሉታዊ ሐሳቦችን ከማጥፋቱ ባሻገር በውስጥህ መልካም ስሜት የሚፈጥር በመሆኑ ስኬትን እንድትጎናፅፍ ያስችልሃል።"
"ሰዎች በጠረጠሩህ ጊዜ ልብህ አይሸበር። በራስህ ተማመን እንጂ ለምን ተጠረጠርሁ ብለህ ቅሬታ አይግባህ።
ምኞትን ተመኘው እንጂ የምኞትህ ባሪያ አትሁን።
ሀሳብን አስበው እንጂ ነገርህ ሁሉ ሀሳብ ብቻ ሆኖ አይቅር።
ሰው ሁሉ ይመንህ እንጂ ማንም ቢሆን እጅግ አድርጐ አለመጠን አይተማመንብህ።
ሰዎች በጠሉህ ጊዜ ቂም አታድርግባቸው። እንዲሁም ደግሞ ደግነት አታብዛ፤ ወይም
በመለማመጥ ራስህን አታዋርደው።
በዙሪያህ የሚገኙ ሰዎች ናላቸው ተናውጦ ኃላፊነቱን ሁሉም በአንተ ላይ ሲጥሉብህ አንተ
ግን ሳትደነግጥ ነገሩን ሁሉ በርጋታ ተቀበለው።"
"አእምሮ ማለት በእግዚዓብሄር አርዓያ ከተፈጠረች ከነፍስ ባህሪይ የሚገኝ እጅግ ታላቅ ነገር ነውና አዕምሮህን በማይረባው ቦታ አትበትን ፣ አእምሮህን ለከንቱ ስራ የጨረስከው እንደሆነ ጌታው አምኖ የሰጠውን ወርቅ ላዝማሪ ለዘዋሪ፣ ለመሸታ ፣ ለጨዋታ፣ እያደረገ ጨርሶ እንደሚቀጣ እብድ ተቆጥረህ ወደ እግዚዓብሄር ቅጣት እንዳታልፍ ፤ አእምሮህን ለከንቱ ስራ እንዳታባክን ተጠንቀቅ። "
"ከሰዎች ኹሉ ያለብህ ዕዳ ፍቅር ነው። ፍቅር ደግሞ ለራስህ እንደምትመኘው ጤንነትን፣ ደስታን እና በረከትን ኹሉ ለሰዎች መመኘት ነው።"

"በስሜት በስለህ ሌሎች ሰዎች ከአንተ የተለየ ሐሳብ እንዲይዙ ፍቀድላቸው። ማንኛውም ሰው ከአንተ ተቃራኒ የመሆን መብት እንዳለው ዕወቅ። ያለ ጥላቻ መቃረን ትችላላችሁ።"
"በተፈጥሮ በውስጥህ ይዘህ የተወለድከው ሁለት ፍርሐቶች ብቻ ነው፤ የመውደቅ እና የድምፅ/የሁካታ ፍርሐት። ሌላው ኹሉ ከማሕበረሰቡ የተጋባብህ ነው ከአንተ ዘንድ አስወግደው።

ልክ ያልሆነውን ፍርሐትህን የውስጥ ሕሊናህን ኅይል ስትገነዘብ ማሸነፍ ትችላለህ። ከዚያም በላይ ያለህበትን ኹኔታ ትለውጣለህ፤ የልብህን መሻት ዕውን ታደርጋለህ። ሙሉ ትኩረትህን ከፍርሐትህ በተቃራኒ በሆነ ሐሳብ ላይ አድርገው። ይህ ነው ፍርሐትህን በሙሉ የሚደመስስልህ ፍቅር።

የምትፈራቸው ነገሮች በሙሉ በአዕምሮህ ውስጥ ካልሆነ በቀር በዕውኑ የሉም። መልካም ስታስብ መልካም ኹሉ ይሆንልሀል። ፍርሐቶችህን ተመልከታቸው የምክንያታዊነትን ብርሐንም አውጣባቸው። በፍርሐትህ ላይ ሳቅ። ፍቱን መድኀኒቱ እርሱ ነው።"
"የሕይወት ግብ ከሞት፣ ከስቃይ ወይም ከመከራ ማምለጥ አይደለም። ነገር ግን ከመጥፎ ተግባር
ማምለጥና ከሌሎች ጋር በመልካም መኖር ነው።"

ሶቅራጥስ
"ራስህን ስለሆንክና ትክክል ስለሆንክ ብዙ ሠዎች በተለይም አላዋቂ የሆኑ ሠዎች ሊቀጡህ ወይም ሊጠሉህ ይፈልጋሉ፡፡ ለትክክለኛነትህ ይቅርታ አታድርግለት፡፡ ትክክል ከሆንክና ትክክል መሆንህን ካወቅክ ለአዕምሮህ ንገረው፡፡
#ምንም እንኳን ከታናናሾቹ አንዱ ብትሆንም እውነት አሁንም እውነት ነው፡፡"

ማህተመ ጋንዲ
"በቀኖችህ ውስጥ ለምታደርገው ትግል ጥያቄው መሸነፍህ አይደለም። መዋጋትህ እንጂ። ካልታገልክ ውጤቱ ተሸናፊነት መሆኑ የታወቀ ነው። በትግልህ ውስጥ ዉጤቱ ከሁለቱ አንዱ ነው።"
"የሰዎችን ስቃይ እንደራስህ ህመም አድርገህ ቆጥረህ የጎደለባቸውን ለመሙላት የምትከፍለው ዋጋ ላቅ ያለ ከሆነ-እውነት እልሃለሁ ሕይወትን በአግባቡ ኖረሃታል።"
አልበርት አንስታይን
"ሰውየው እንዲህ አሉ ፤ ወጣት ሳለው አለምን መለወጥ ፈለኩኝ ፤ አለምን መለወጥ አስቸጋሪ መሆኑን ስላወኩኝ ሀገሬን መለወጥ ፈለኩኝ፤ ሀገሬን መለወጥ እንደማልችል ሲገባኝ ከተማዬን መለወጥ ፈለኩኝ ፤ ከተማዬን መለወጥ እንደማልችል ሲገባኝ እድሜዬም እየገፋ ቤተሰቤን መለወጥ ሞከርኩኝ ፤ አሁን እድሜዬ በገፋበት ዘመን የገባኝ ነገር መለወጥ የምችለው ነገር እራሴን ብቻ መሆኑን ነው ። ገና ድሮውኑ እራሴን መለወጥ ብችል ኖሮ ቤተሰቤ ላይ ለውጥ ማምጣት እችል ነበር ፤ እኔና ቤተሰቤ ከተማችን ላይ ለውጥ ማምጣት እንችል ነበር ፤ ከተማችን ደግሞ ሀገርን መለወጥ ትችል ነበር ፤ እና እኔም ዓለምን መለወጥ እችል ነበር ብሏል ።

ለውጥ ከራስ ይጀምራል ፤ እራሳችንን መለወጥ ሳንችል ቤተሰብን ፣ ሀገርን ፣ ዓለምን መለወጥ ከቶ አንችልምና እራሳችን ላይ ተግተን እንስራ።"
"ከልብ የሚወድህን ወዳጅህን ለማስቀየም አትቸኩል ቀን ይጥልህና የልብ ወዳጅ ያጣህ
ቀን ይቆጭሃል::"
"ሰውን የምናውቀው ስለራሱ የነገረን እንደሆነ ነው። ግን ከጠየቅነው አይናገርም፣ ቢናገርም እውነቷን ፍርጥ አድርጎ አይደለም። ስለዚህ መታገስ ያሻል፣ ጊዜን መጠበቅ። አንዲት ሰአት ትመጣለች፣ ሰውየው መናገር የሚፈልግበት ሰአት። መቼ እንደምትመጣ ለማወቅ አይቻልም፣ ግን መምጣቷ አይቀርም። ስለዚህ ዘወትር ዝግጁ መሆን ያሻል።"
ወይ መፍቀድህን አቁም ወይም ንጭንጭህን አቁም!

"አንድን ነገር መቆጣጠር ስትችል እንዲሆንብህ እየፈቀድክ ከዚያ ደግሞ በሁኔታውና በውጤቱ መነጫነጭ ታላቅ አባካኝነት ነው፡፡ አንድ ነገር እንዲሆን የምትፈቅድ ከሆነ በዚያ ምክንያት ስለሆነብህ ነገር መነጫነጭ ማቆም አለብህ፡፡ በአጭሩ፣ እንዲሆን ስለፈቀድከው ነገር አትነጫነጭ፡፡ በኋላ እንድትነጫነጭ የሚያደርግህን ነገር ደግሞ መጀመሪያውኑ መፍቀድን አቁም፡፡

አንድ ነገር እንዲሆንብህ አንተው እየፈቀድክ በኋላ ስትነጫነጭ ሁለት ነገር ነው የምትከስረው፡- የሆነብህ ነገር ያመጣው ክስረትና ከዚያም በመነጫነጭህ ምክንያት የምታባክነው የጊዜና የስሜት ብክነት፡፡

ለምሳሌ፣ “ሁል ጊዜ ገንዘብ ተበድሮኝ አይመልስም” . . . “ሁል ጊዜ እቃ እየወሰደ አያመጣም” . . . “ሁል ጊዜ ሚስጥሬን ስነግራት ለሌላ ሰው ትናገርብኛለች” . . . “ሁል ጊዜ ይቅርታ ትጠይቀኝና መልሼ ሳምናት ያንኑ ጥፋት ትደጋግማለች” እና እነዚህን መሰል ንጭንጮች ካሉበህ ወይ ተግባርህን አቁም፣ ወይም ደግሞ በተግባርህ ቀጥልና ንጭንጩን አቁም፡፡

አንዳንድ ጊዜ ከአቅማችን በላይ በሆነ መልኩ ነገሮች እንዲሆኑ የመፍቀዳችን እውነታ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ አንድን ነገር እየፈቀድን ስንነጫነጭ ግን ወይ አስመሳይነት ነው ወይም ደግሞ አጠቃላይ የሕይወት ሂደት ግንዛቤ የጎደለን አይነት ሰዎች ነን፡፡

የሆነብህን ወይም ሰው አደረገብኝ ብለህ የምታስበውን ነገር በሚገባ አጢነው፡፡ ሁኔታው ወደመሆን እንዲመጣ ፈቃድ የሰጠኸው አንተ ከሆንክ ያለህ ምርጫ ከሁለቱ አንዱ ነው፤ ወይ መፍቀድን ማቆም ወይም ደግሞ መነጫነጭን ማቆም፡፡"

ዶክተር እዮብ
"ማወዳደር ትልቅ በሽታ ነው፡፡የራስህን ሂወት በፍፁም ከሌላ ሠዉ ጋ አታወዳድር፡፡ምክንያቱም የምታገኘዉ ዉጤት ከዛ ሰዉ የተሻልክ ከሆነ 'ኩራት'ሲሆን ከዛ ሰዉ የምታንስ ከሆነ ደግሞ 'ቅናት' ነው ሚሆነዉ፡፡ ሁለቱም መጥፎ ዉጤቶች ናቸው፡፡ጨረቃና ፀሀይ አይወዳደሩም ሁለቱም በጊዜያቸው ደምቀዉ ያበራሉና፡፡"
" የምትወደው ሁልጊዜ ሲለይህ የሚያስረሳህ እንጂ የሚያስታውስህ ነገር አትፈልግ ያለዚያ
ህይወትህ የስቃይ ህይወት ይሆናል።"

ፍቅር እስከ መቃብር