ቢጠቅሞት ካነበብነው እናካፍሎት
172 subscribers
82 photos
5 links
📖⁣ማንበብ የአስተሳሰብ ልህቀትን ያጎናፅፋል።
📖⁣ማንበብ የእውቀት አድማስን ያሰፋል።
📖⁣ማንበብ የቆሸሸ ስብዕናን ያፀዳል።
📖⁣ማንበብ ምክንያታዊ ፣ጠያቂ እና የሰላ አእምሮን ያጎናጽፋል።
Download Telegram
ቢጠቅሞት ካነበብነው እናካፍሎት pinned «"ስንፍና፣የእውቀትን ዋጋ አሳንሶ መመልከትና የንባብ ባህል ደካማ መሆን በሌሉበት ምንም ሁኔታ ውስጥ ለማንበብ አይገድም። ላለማንበብ ከምንሠጣቸው የተለያዩ አሳማኝ ያልሆኑ ምክንያቶች ሁሉ ጀርባ እውነተኛ ግን የተካደ ደካማ የንባብ ባህል ጠፍሮ እንደያዘን እሙን ነው። ለውጥ እንመኛለን ግን አናነብም፣በትልቁ እንደ ሃገር በግለሰብም ደረጃ ከፍ ያለ ለውጥ አጥብቀን እንሻለን ግና የእውቀትን ዋጋ በቅጡ አላሠላነውም።…»
አታለቃቅሱብን

.

ማህበራዊ ሚዲያው ከቤተመንግስቱ በር ስለተተከለችው ፒኮክ ለሁለት ተከፍሎ እየተነታረከ እየተመለከትን ነው፡፡ ገሚሱ አንበሳው ለምን ወረደ ፒኮክ እኛን ልትወክለን አትችልም የሚል ሲሆን ገሚሱ ደግሞ የፒኮኳ ደጋፊ ሁነው እያየን ነው፡፡

-

እኔን ግርም ያለኝ ነገር ብሄራዊ ጀግና የሌለን ትውልዶች ብሄራዊ እንስሳ ፍለጋ መኳተናችን ነው፡፡ እረ ባሸዮ ከፈረሱ ጋሪውን እያስቀደምክ ነው! አጼ ሚኒሊክን፤ አጼ ዩሀንስን፤አጼ ቴዎድሮስን፤ጃግማ ኬሎን፤አሉላ አባነጋን፤ሸህ ሆጀሌን፤አባ ጅፋርን ወዘተ በብሄር ተቧድነህ በጎራ ተከፍለህ ስታረካክስ እና ስታዋርድ የምትውል ሰው እንዴት ብሄራዊ እንስሳ እንዲኖርህ ፈለግህ?🤔 የሀገር ባለውለታዎችን፤የሀገር ጀግኖችን ፤የሀገር ቅርሶችን፤የሀገር ምልክቶችን በአመለካከትህ ፈርጀህ፤በብሄር መዝነህ፤በቋንቋ ለክተህ ስታበቃና ስታሳንስ ከርመህ ስለምን ፒኮክ ስለምን አንበሳ ነው የምታወራው?🤔 ባሻዮ ከእንስሳቶቹ በፊት ሰው ይቀድማል! መጀመሪያ ያሳነስካቸው ያቃለልካቸው ያዋረድካቸው ጀግኖችህን ከጣልክበት ጭቃ አንሳቸው፡፡ አፋሩ ላይ ያለውን ጀግና ለማሞገስ ቃላት አይጠርህ፤አማራው ላይ ያለውን ጀግና ለማሞገስ አፍህ አይያዝ፤ጉምዙ ላይ ያለውን ጀግና ለማድነቅ ለቃላት አትሰስት፤ኦሮሞው ላይ ያለውን ጀግና ለማወደስ አፍህ አይለጎም፤ሲዳማ ላይ ላለው ጀግና ለማጨብጨብ እጅህን አይሰብሰብ፤ትግራይ ላይ ያለውን ጀግና ለማወደስ ከንፈርህ አይያያዝ፤ሶማሌ ላይ ላለው ጀግና ክብር ለመስጠት አትዘግይ፤ኑዌሩን ጀግና ለማወደስ አታቅማማ፤ሀረሪውንም፤ወላይታውንም ወዘተ፡፡ ይሄን ማድረግ ስትችል ያኔ ስለፒኮክ እና አንበሳ ማውራት ትችላለህ፡፡ አሁን አፍህን አታበላሽ ሰው ይስቅብሀል ባሻዮ! መጀመሪያ ብሄራዊ ጀግኖችህን ፍጠር!

Buzie Z Gilgel Beles ቡዜ ዘ ግልገል በለስ🤔
ልጄ ሆይ ለሰዎች ደግ ስትሆን እንደወንዝ ሁን– ወንዝ መርጦ አያጠጣም። አጎንብሶ ሊጠጣ ለወደደ ሁሉ ሳይሰስት ያጠጣል። ደግነታችን እንደወንዝ ይሁን ፤ ሳንመርጥ፣ ለለመነን ሁሉ እጃችንን እንዘርጋ ። ወንዝ ወደፊት ብቻ የሚሄድ ወደኋላ የማይመለስ ሲሆን ቀጣይነቱን ይመሰክራል፤ የኛም ደግነት እንዲሁ ዛሬ ተጀምሮ ነገ የማያበቃ፤ ሁል ጊዜ እንደወንዝ የሚፈስ መልካምነት በጎነት ይኑርህ። ሌላው የወንዝ ውበቱ ዝቅ ብሎ ሳይጮህ መፍሰሱ ነው። ዝቅ ብሎ ሌሎችን ከፍ እንደማድረግ ምን ውብ ነገር አለ? ይህንን አደረግኩኝ፤ እንዲህ ደግ ሰራው እያሉ መጮህ የደግነትን ክብር ይነካል፤ እንደወንዝ በዝምታ፤ ለሌሎች መልካም መሆን ነው እውነተኛው ደግነት ነው ።
የደግነት ተግባር አፈጻጸም ሦስት ወገን ነው፡፡ይለናል ጥንታዊው አንጋረ ፈላስፋ መጽሐፍ ይህም
1ኛ. ዋል እደር ሳይሉ ፈጥኖ መስጠት፡፡
2ኛ. ይህን ብሰጠው ምን ይጠቅመዋል? ሳይሉ ያለውን መስጠት፡፡
3ኛ. ሲሰጡ ሰውሮ መስጠት ናቸው፡፡
ምክንያቱ ፈጥኖ መስጠቱም ያስደስተዋል፤ተቸግሮ ሳለ ጥቂቱንም ሲሰጡት እንደ ብዙ ያየዋል ፡፡ ሰውሮ መስጠቱ ገንዘቡን ያበረክተዋልና ነው፡፡
የሌሊት ወፍ

“የሌሊት ወፍ በቀን የመኖር ስልጣን የላትም” ይላል ምንጩ ያልታወቀ የጥንት አፈ-ታሪክ፡፡ “ለዚህ ነው ሌሊቱን እየጠበቀች ከመሸ ተደብቃ ወጥታ ሳይነጋ ተደብቃ የምትገባው”፡፡

በጥንት ጊዜ በሰማይ አእዋፍና በምድር አራዊት መካከል ውጊያ ነበር ይባላል፡፡ የአሁኗ የሌሊት ወፍ ያን ጊዜ እንደማንኛውም የወፍ ዝርያ ነበረች፡፡ ይህቺ ወፍ (የአሁኗ የሌሊት ወፍ) በውጊያው ጊዜ የምድር አራዊት ሲያሸነፍ ለእነሱ ታግዝ ነበር፤ የሰማዩ ሲያሸነፍ ደግሞ ተገልብጣ ለእነሱ ታግዝ ነበር፡፡

አንድ ጊዜ ግን እነዚህ ሁለት ጸበኞች ታረቁና የጦርነቱ ሁኔታና ትውስታ ሲነሳ ምን ስታደርግ እንደነበረ ታወቀባት፡፡ ከዚያ ቀን ጀምሮ በሁሉም የተጠላችና የተገፋች ወደመሆን ስለመጣች በቀን የመኖር ስልጣኗን አጣችና ሌሊት መኖር ጀመረች ይባላል፡፡

አስመሳይነት፣ ሁለት መልክ ያለው ሕይወት፣ አቋም የለሽነት፣ ውሸተኛነት፣ አታላይነት፣ መስሎ አዳሪነት፣ ባለ ሁለት ምላስነት፣ ሸንጋይነት፣ ለሆድ አዳሪነት . . . የዘመኑ ችግር!

የብዙዎችን በነጻነትና ቀና ብሎ በድፍረት የመኖር አቅም ያሳጣ የዘመኑ ወረርሽኝ!
አስመሳይ ሆነህ ወዳጅህ ከሚበዛ፣ እውነተኛ ሆነህ ጠላትህ ቢበዛ ይሻላል፡፡ ሁለት መልክ ይዘህ ትርፋማ ከምትሆን፣ አንድ መልክ ይዘህ ባለህ ነገር መኖር ይሻልሃል፡፡"

ዶክተር እዮብ
ራስን መሆን

"ራስን መሆን ማለት፣ ማንነትን ተቀብሎ፣ ሳይደባብቁና ሌላውን ሰው ለመሆን ሳይሞክሩ በነጻነት መኖር ማለት ነው፡፡ ራስን የመሆን ጉልበት የሚመነጨው ከፈጣሪ የተሰጠኝን ማንነቴን ከመቀበል ነው፡፡ አንዳንድ ሰዎች ራሳቸውን ስለማይቀበሉ ራሳቸውን ሆነው መኖር አይችሉም፡፡

ራሱን መቀበል ያስቸገረው ሰው ላይ የሚታየው የመጀመሪያው ምልክት ራስን አለመሆን ነው የማይቀበሉትን ማንነታቸውን ለውጠው ለመታየት ሲሞክሩ ራሳቸውን ያገኙታል፡፡ ልንለውጥ በማንችለው ማንነታችን ስንደላደልና ስንቀበለው መለወጥ የምንችለውን ሁኔታችንን ለመለወጥ መሞከራችንን እደቀጠልን ማንነታችንን ግን በመቀበልና ቀና ብለን መኖር እንጀምራለን፡፡ ራስህን ለመሆን መውሰድ የምትችላቸው እርምጃዎች፡-

1. መለወጥ ወይም ማሻሻል የምችለውን መለወጥና ማሻሻል፡፡
በማንነቴ ላይ የማልቀበለውን ነገር ለማሻሻል ጤናማ መንገዶችን መሞከሩ ክፋት አይኖረውም፤ ከተሳካልኝ፡፡ ቁም ነገሩ፣ አሻሻልኩትም አላሻሻልኩት ራሴን ወደ መቀበል መምጣቴና ጤናማ የሕብረተሰቡ አካል ሆኜ መኖሬ ነው፡፡

2.መለወጥ ወይም ማሻሻል የማልችለውን መቀበል፡፡
ዘሬን፣ መልኬን፣ አወላለዴንና የመሳሰሉትን ከፈጣሪ የተቀበልኩትን አሁን የሆንኩትን ማንነት ለመቀየር አስቸጋሪ እንደሆነ ግልጽ ነው፡፡ ምርጫዬ አንድ ነው፣ ራሴን ተቀብዬ፣ በተረጋጋ ስሜት በሰላምና በመደላደል መኖር፡፡

3.ደስተኛነትን መለማመድ
ደስተኛነት ከፈቃድ ጋር የተያያዘ ጉዳይ ነው፡፡ ከላይ እንደጠቀስነው አንድ ሰው መቀየርና ማሻሻል የሚችለውልን ነገር ለመቀየርና ለማሻሻል የተቻለውን ካደረገ በኋላ በሁኔታው ደስተኛ ለመሆን በመወሰን አለበት፡፡"
"የመልካምነት መሠረቱ ዕውቀት ፣ የክፋት መሠረቱ ደግሞ አለማወቅ ናቸው ፤ የእውቀት መጀመሪያ አለማወቅን ማወቅ ሲሆን ማወቅ ደግሞ ከማሰብ ይጀምራል" ሶቅራጠስ ።
፨ ለማወቅ ስናነብ የበለጠ አለማወቃችን ይገለጥልናል ፤ አለማወቃችን ሲገለጥልን ያኔ በውስጣችን ያጨቅነውን ያላዋቂነትና ባዶ መመፃደቃችንን አራግፈን በእውቀትና በመልካምነት እንጠመቃለን ።
"ልጄ ሆይ የሆነውን ነገር ተናገር እንጂ ገና የሚሆነውን ነገር አትናገር። ሌሎችም ሰዎች ገና የሚሆነውን ቢነግሩህ አትመናቸው።ክፉ የሚሰራ እንደሚጎዳ ደግ የሚሰራ ግን እንዲጠቀም የሚታውቅ ነውና፤ደግ ስራ እየሰራህ ብቻ ወደ ፊት የሚሆነውን ነገር ጠብቅ። ነገር ሁሉ ጊዜ ሲደርስ በግድ ይፈፀማል እንጂ ጊዜው ሳይደርስ አይፈፀምምና ለማንኛውም ነገር አትቸኩል።"ይሉናል ፀሐፊው
ስለዚህ ባለፈው እንጂ በሚመጣው ምንም ታህል አናውቅምና በአንደበታችን ስለማናውቀው ነገር አውርተን ሰውንም ከማስደንገጥም እራሳችንን ከማስፈራራት እንቆጠብ። በወቅታዊ ነገር ጥሩ እይታ ስለሌለን ማለቴ ነው። በነገሮች ላይ አንቸኩል በመቸኮላችን የእኛ ሊሆን የሚገባውን እንዳናጣው።
"ሽልማት የሚባለው በሰዎች በኩል ተዘጋጅቶ ለተሸላሚዎች የሚሰጥ ገንዘብ አይደለም። ሽልማት ማለት ራሳችን ለራሳችን የምንሸልመው ሰላም ነው! ሰላምና ገንዘብ ደግሞ መንገዳቸው ለየቅል ነው። ፍቅርና ገንዘብም መንገዳቸው ለየቅል ነው። ታማኝነትና ገንዘብም እንደዚያው! ከገንዘብ እና ከህሊና ህሊናቸው የበለጠባቸው ሰዎች በማጣቷ ነው ኢትዮጵያ እንዲህ ሆና የቀረችው።"

የሳጥናኤል ጎል ኢትዮጵያ
"ቀላሉን ነገር አለማካበድ ስትጀምር ሕይወት በአንዴ ወደ ሙሉና ፍፁም አይቀየርም። ነገር ግን በሕይወት ውስጥ የሚያጋጥሙህን ነገሮችን ያለ ትግል መቀበል ትችላለህ። ይሄ ፍልስፍና እንደሚያስተምረው ነገሮች ጋር ባለ በሌለ ኀይል ከመላተም ይልቅ ተወት ስታደርጋቸው ሕይወት ቀለል ያለ ይሆናል። " የሴሬኒቲ ፀሎት" እንደሚለው መለወጥ የሚችሉትን ነገሮች በድፍረት መለወጥ፣ መለወጥ የማይችሉትን በፀጋ መቀበልና ሁለቱን ለመለያየት ደግሞ ጥበብ ይኖርሀል።"

ቀላሉን ነገር አታካብድ መቅድም
"እኔና አንተ አንድ ቦታ ላይ በተለያየ አቅጣጫ ፊታችንን አዙረን ብንቆም የእኔ ቀኝ ያንተ ግራ ነው። ያንተ ግራ የኔ ቀኝ ነው። 'ቀኝ ይሄ ነው ወይም ግራ ይሄ ነው' ብዬ ብከራከርህ ቂል ነኝ። እንዳንተ አቋቋም ያንተ እውነት ይሆናል። እንደ እኔ አቋቋም ደግሞ የእኔ እውነት ይሆናል። ባንተ እውነት ለማመን ያንተን ጫማ መዋስ አለብኝ። የቆምኩበት ሆኜ ለስህተትህ ሒሳብ እየሰራሁ ስዳኝህ እቀሽማለሁ።"


ጠበኛ እውነቶች በሜሪ ፈለቀ
"የሰው ልጅ ራቁቱን የሚሆነው ልብሱን ሲያወልቅ አይደለም ፍርድ ቤት ሲቆም እንጂ። ፍርድ ቤት ውስጥ አካል ሳይሆን ህሊና ራቁቷን ትቆማለች።

የሰው ልጅ ምን ያህል እንደሚዘቅጥ ለማየት ትክክለኛው ቦታ ፍርድ ቤት ነው። ሌባው፣ ነፍሰገዳዩ ፣ አመንዝራው፣ አጭበርባሪው ሁሉም ጭምብላቸውን አውልቀው ራቁታቸውን ይቆማሉ። ሁሉም ገመናቸውን ያያል። የሰው ልጅ አስቀያሚ መልክ ሌጣውን ይገለጣል፤ መለመላውን ይቆማል። የሰውን ልጅ ስነልቡና ለመረዳት ከፍርድቤት የተሻለ ቦታ የለም።

"የሰው ልጅ ቀረብ ብለው ሲያዩት አስቀያሚ ፍጡር ነው" ብሏል አንዱ ፈላስፋ። የሰውን ልጅ ቀረብ ብሎ ለማየት ደግሞ ከፍርድ ቤት የተሻለ ቦታ የለም።

ሱፉን ግጥም አድርጎ የለበሰው ጠበቃ ደንበኛውን ነፃ ለማድረግ የማይፈነቅለው ድንጋይ የለም። አቃቤ ህጉም ተከሳሹ እንዲፈረድበት መላ ጉልበቱን ይጠቀማል። ፍርድ ቤት ውስጥ ቁምነገሩ ፍትህ ሳይሆን ማሸነፍ ነው። ለማሸነፍ ደግሞ ጣልቃ የሚገቡ ሌሎች ነገሮችም አሉ―የፖለቲካ ስልጣን፣ ገንዘብ ወይም ጉቦ ወዘተ።

ፍርድ ቤት ውስጥ ልብ ቦታ የለውም። አቃቤ ህግና ጠበቃ የሚጫወቱበት ሜዳ ነው። ይኸው ነው በቃ―ለነሱ ጨዋታ ነው። እውነት የያዘ ሳይሆን ጥሩ የተጫወተ ያሸንፋል። ፍርድ ቤት ውስጥ በማስረጃ ሊረጋገጥ ያልቻለ እውነት ምንም ነው። እውነትን ፍርድ ቤት ውስጥ አትፈልጓት። እውነት ሆይ ከወዴት ነሽ?!"

ምንጭ፦ Book for All
መጋፈጥ ያለብህን ነገር ለይ!

"አንዳንድ ሰዎች ምንም ነገር መጋፈጥ (Confrontation) አይወዱም፡፡ እንደዚህ አይነት ሰዎች ከመጋፈጥ ይልቅ መታገስና መሸከም ይሻላቸዋል፡፡

ለምሳሌ፣ ሰዎች እያታለሏቸውና ወይም ደግሞ አንዳንዴ የእነሱ የሆነውን ነገር ካለማቋረጥ በድብቅ እየወሰዱ እንደሆነ ያውቃሉ፣ ሰዎቹን ቁጭ አድርጎ እያደረጉት ያለውን ስርቆት እንደሚያውቁ፣ ትክክል እንዳልሆነና መታረም እንደሚገባው ለመናገር ግን ድፍረቱ የላቸውም፡፡

እንደዚህ አይነት ሰዎች ምግባረ ብልሹ የሆኑ ሰዎችን “ሲቀልቡ” ይኖራሉ፡፡

በማንኛውም ማሕበራዊ ግንኙነት ውስጥ አብሮን ያለ ሰው ለዚያ ግንኙነት የማይመጥን ባህሪን ሲያሳይ ነገሩ እንዲታረም ከፈለግን ፊት ለፊት መጋፈጥ የግድ ነው፡፡ ከዚህ ሌላ ያለን ምርጫ ዝም ብለን እንደፈለጉ ሲያደርጉን ማየት ነው፡፡

አንዳንድ ጊዜ ሰዎችን መጋፈጥ ማለት ጸብ፣ ጩኸት፣ ልክ ልክ መነጋገር እንደሆነ ስለምናስብ ነው የማንፈልገው፡፡ ሆኖም፣ በለስላሳ ድምጽና በተረጋጋ ስሜት ሰዎቹ መስማት ያለባቸውን መንገር እንደሚቻል ማሰታወስ አለብን፡፡

ጉዳዩን ወደራሳችን ስናዞረው፣ የራሳችንንም ድካምና ችግርም ቢሆን ካልተጋፈጥነው በስተቀር ልናርመው አንችልም፡፡ የራስን ሁኔታ መጋፈጥ ማለት ስላለብን ሁኔታ ምክር መፈለግ፣ እርዳታን መጠየቅ፣ ችግርን አምኖ መቀበል . . . ሊሆን ይችላል፡፡

ያም ሆነ ይህ ወሳኝ ለሆኑ ነገሮች ዝምታው ቆም ሊልና መጋፈጥ ያለብንን ነገር በረጋ መንፈስ መጋፈጥ የጨዋዎችና የብልሆች መንገድ ነው፡፡"

ዶክተር እዮብ
"እውነታው ሰዎች ሊያወድሱህ ከፈለጉ ከፈጣሪ ታናሽ ያደርጉሃል። ሊዘልፉህ ከፈለጉ ደግሞ ሳጥናኤል የሚቀናበት ክፉ ያደርጉሃል። ከሰማሃቸው ደግሞ ራስህን የመሆን እድል አይሰጡህም። ሁሉም በፈለጉት መንገድ ሊቀርፁህ መጥረቢያ ይስላሉ። ልብህን ከከፈትክላቸው የየድርሻቸውን ጠርበውህ ቅርፅ አልባ ያደርጉሃል።"

ምንጭ ፦ ጠበኛ እውነቶች
"አብዛኞቻችን እኮ ግብዝ ነን:: ለሚሰማን እውነተኛ ስሜት ሳይሆን ሰዎች በሚሰጡን የውዳሴ ምላሽ ቃርሚያ እናጎባድዳለን:: ጥሩ ስናደርግ እንኳ ግብዝ ነን:: ደግ ለመሆን ከምናደርግ ይልቅ በሌሎች ዘንድ ደግ ለመባል ነው:: ደግነት ለቅድስና ደግ ከመሆን ይልቅ ለእውቅና ደግ እንሆናል:: ...አነሰም በዛም ደግነታችን ዓይንና ልብ እንዲስብ እንፈልጋለን::.."
"ህይወት የሂሳብ ቀመር ይመስል የሁለት ተመሳሳይ ነገር ድምር ወይም ብዜት ሁሌ መልሱ አንድ ዓይነት አይመጣባትም። ውጤቱን የሚወስኑት ሰዎች ናቸው"
"ኢትዮጵያውያን በዓለም ልዩ የሚያደርጋቸው ነገር ቢኖር በጦር ሜዳ ውሏቸው ጤነኛ መሆናቸው እስኪያጠራጥር ድረስ እንደ እብድ መድፉን መትረየሱን ታንኩንና የአውሮፕላን ቦምቦችን ከመጤፍ ሳይቆጥሩ እየፎከሩና እየሸለሉ የጠላትን ጉሮሮ አንቀው ይወድቃሉ..."

የሃበሻ ጀብዱ
"ሁሌም ዛሬ ላይ ቆመህ ሁለት ምርጫ አለህ። ትናንት ወይም ነገ፤ ትዝታ ወይም ተስፋ!"
★ "ማንኛውም ሀሳብ መንስኤ ነው፤ እያንዳንዱ ሁኔታ ደግሞ ውጤት ነው።"

★ "አስተሳሰብህን በመለወጥ እጣ ፈንታህን ለውጥ/ቀይስ"

★ "ትልቁ ሐብት ያለው በውስጥህ ነው። ለነፍስህ መሻት መልስ ለማግኘት ዙሪያህን አስተውል"
የቆሸሸ ልብስ የለበሰን እብድ ብለህ ከምትሸሸው ይልቅ ንጹህ ልብስ ለብሶ አዕምሮው የቆሸሸን ጥላቻን የሚሰብክ ሰውን ሸሸው ! !
/ አነስታይን/
"ሕይወት በመርሳትንና በማስታወስ...በመሸለምና በመቅጣት...አንዱን ስታነግስ ሌላውን ስታኮስስ...የምትቀጥል የትዝታና የትውስታ...የመርሳትና የመዘንጋት...ማህደር ናት።"

በዶ/ር ምህረት ደበበ