beki_book
72 subscribers
1 file
የስነ ፅሁፍ ስራዎች ለውድ አንባብያን !

> ልቦለድ
> ወግ
> መጣጥፍ
> አጫጭር ታሪኮች
> philosophy idea

በብዙ ይገኙበታል #join

#በረከት_ዘውዱ @Beki_book @bereket_zewdu
Download Telegram
Channel created
ሳልሞት ቅበሩኝ



ለኛም ፀሀይ ወጣ ከድህነት ጨለማ ወጣን ህይወት እጇን ዘረጋች አባዬ ቤቱን ሰርቶ ወደ መጨረሻው ደረሰ ቤቱ የ ውስጥ ስራ ( finishing ) ስራ ሲቀረው ከ አንድ ወር በኋላ ቤቱን ጨርሼው እንገባለን እያለ በስራ በድካም ቀኑን ሲንከራተት እንደዋለ ማታ ላይ ጠራኝ " ብሩኬ ብሩኬ ውሀ ስጠኝ " አለኝ ቤቱ ስለተረባበሸ እስክሰጠው ትንሽ ቆየሁ ውሀውን ይዤ ስመጣ አባቴ አተነፋፈሱ ተቀይሯል ጮህኩኝ እናቴ እህቶቼ ተሰበሰቡ ተረባርበው መኪና መጥቶ ወደ ሆስፒታል መንገድ ጀመሩ ፣ ትንሽ ቆይተው ሲመለሱ አባቴ ተሽሎት መስሎኝ ነበር ለካ አባቴ መንገድ ላይ ህይወቱ አልፏል መኪናው የተመለሰው ለዛ ነበረ ።

ለምን ? ህልሙን ለማሳካት ጫፍ ላይ ደርሶ ከ አንድ ወር በኋላ አዲሱ ቤት እንገባለን እያለ ተስፋውን ጥንካሬውን ህልሙን ሁሉንም አፈር ለምን በላው ? ብሩኬ " እኔ አባትህ ያለ እረፍት ነው ቤቱን ምሰራው አንተ ትምህርትህ ላይ በርታ " እያለኝ " ቤቱ በ አንድ ወር ውስጥ ያልቃል ገናን በአዲሱ ቤታችን ነው ምናከብረው " እያለኝ ሞት ለምን ቀደመው ፈጣሪ እርጅና አይናቸውን የጋረዳቸው የልጃቸውን ደስታ ማየት የሚሹትን እናቱን ለምን አልወሰዳቸውም ልጃቸውን በማጣት ህመም አንጀታቸው እስቲቆስል ማልቀሳቸውን ማዘናቸውን ለምን ፈለገ ።

አባቴ በጣም መልካም ሰው ነበረ ! አቶ አሸናፊ ከተባለ የሰፈር ሰው ሁሉ የሚታየው መልካም ነገር ነው እኔንም ሰፈር ልጫወት ስወጣ ተልኬ ስወጣ ወደ ትምህርትቤት ስሄድ ያዩኝ ሰዎች ሁሉ " የአቶ አሸናፊ ልጅ እደግ የእርግብ እንቁላል እባብ አይሆንም ያሳድግህ " ይሉኛል እህቶቼም በፀባያቸው በጨዋነታቸው ሁሉም ሰው ይስማማበታል እናቴም እስከዳር መልካም ሰው ነች አባቴን በሁሉም ነገር ታግዘው ነበረ ትመክረዋለች ሰላሳ ዓመት በትዳር ሲኖሩ ችግሮቻቸውን በጠብ ለመፍታት ሞክረው አያውቁም ሁሌም እኛ ስንተኛ ሲነጋገሩ እሰማለሁ ከስድስት ወር በኋላ እናቴ አባቴ የጀመረውን ቤት ሰርታ ጨረሰች ።

አዲሱ ቤት ከገባን በ ዓመቱ ሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ለትምህርት ሄድኩኝ ከእናቴ ጋ በስልክ እናወራ ነበረ ለእረፍትም ስሄድ እንገናኛለን ሁለተኛ ዓመት ተማሪ ስሆን ታላቅ እህቴ የቤቱ የመጀመሪያ ልጅ ተሞሸረች አምስተኛ ዓመት ተማሪ ስሆን ታላቅ እህቴ የቤቱ ሁለተኛ ልጅ ተሞሸረች ከ ሁለት ወር በኋላ እኔም electrical mechanical engineering ተመረቅኩ እናቴ ሁሌም " ምን ነበረ አሹ በህይወት ኖሮልኝ ይህንን ወግ ማዕረግ አብረን ብንካፈል ምን ነበር የዘራውን አጭዶ ቢሆን ፈጣሪ ስድስት ዓመት መታገስ አቅቶት ነው " ትላለች አንዳንዴም ደግሞ " ፈጣሪ ትክክል ነው ነገሮች ሁሉ ለመልካም ናቸው " ትላለች ።

አባቴ ተስፋ ነበረው እውነትም የሆነ ሊቀድመው የፈለገ ነገር እንደ ነበረ ተረድቶ ነበር ልቡን ትንሽ ይደክመው ነበር ግና ጥንካሬው ምንም በሽታ እንደማያጠቃው ሰው ነበር ሁሌም ልንተኛ ጊዜ ከመፅሀፍ ቅዱስ ክፍሎች አስር አስር ምዕራፍ ያነብልኛል ረዥም ከሆነ ደግሞ አምስት ምዕራፍ አንብቦልኝ ከመፅሀፍ ቅዱስ ካነበበው ይመክረኝ ነበረ ። አሁን ላይ ሆኜ ምን ነበር አባቴ በህይወት ኖሮ ተመርቄያለሁ ስራ ይዣለው በመንፈሳዊ ህይወቴም ጥሩ ላይ ነኝ አባቴ ይህን ሁሉ አብሮኝ ሆኖ ብናየው ብዬ እመኛለሁ ።

ሰውነት ድክመት ነው አይደል ስንኖር ነገ ወይ ዛሬ መሞታችንን አናስተውልም መኖር ብቻ እንደተፈቀደልን ሳይሆን እንደፈቀድን የምንኖር ይመስለናል እስከፈለግነው ጥግ እንድድምንሄድ እናስባለን መንገዱ ላይ እንቅፋት ወይንም ገደል እንዳለ እንዘነጋለን ሁሉን ነገር ይዘን የምንሄድ ይመስለናል ። ህይወት መወለድ መኖር መሞት ብቻ እንዳልሆነ አባቴ አስተምሮኝ አልፏል ለስጋው መጠለያ እንደደከመው ሁሉ ለነፍሱ ስጋውንም ሲያደክም ተናግሮ ብቻ ሳይሆን ሆኖም አስተምሮኛል ።

#በረከት_ዘውዱ

@Beki_book
10👍1
ተዐምር
"""" "'''''"""""""""

ማርታ ፊት ለፊቷ ጠረጴዛ ላይ ካለው አልበም ፎቶ እያየች እያለ ከአልበሙ ጀርባ ያረጀ ወረቀት አገኘች የተፃፈውን ፅሁፍ ማንበብ ስላልቻለች ልጇን ጠራቻት " ተዐምር ተዐምር ልጄ ነይ እስቲ አንብቢልኝ " አለች ተዐምር ወረቀቱን ተቀብላ ስታየው ከላይ " ልጄ ይህን ወረቀት ካገኘሽው ለእናትሽ ሳትሞት አንብቢላት ለእናንተ ያለኝ ፍቅር ከኖርኩትም በላይ እንደነበረ ትረዱታላችሁ " የሚል ፅሁፍ አለው ፣ ተዐምርም ደብዳቤውን ቁጭ ብላ ማንበብ ጀመረች " ጆሊ ነበርኩኝ የጭነት መኪና ላይ ረዳት ሆኜ ነበር ምሰራው እኔ እና ጭስ ያልወጣንበት ቀዳዳ የለም ከሰማንያውም ብሔረሰብ ሴቶች ጋ ተኝቻለሁ ብል ውሸት ሊመስል ይችላል ልጃ ገረድ የለ ያላያገባች የወለደች የቀረኝ የለም ኤልያስ ከተባለ የጅማ አጋሮ ሰዎች ጆሯቸው ይቆማል ። ተዘመረልኝ ወጣትነቴ እየተጠቀምኩበት ያለፍኩት ይመስለኝ ነበረ ፣ ያልተዝናናሁበት ሪዞርት ካየሁት ሳልጠጣበት የወጣሁበት ባር የለም ፣ ከትግሬዋ ጋ ከመይ ከመይ ፣ ከኦሮሞዋ ጋ ጫልቱ ጫልቱ  ፣ ከአማራዋ ጋ ውቤ ውቤ ፣ ከጉራጌዋ ጋ ገረ ገረ እያልኩ ወጣትነቴን ሴትና አልኮል በማሳደድ አጠፋሁት ።

ወይ ኤልያስ ዘመን ሲቀየር ነገሮች አብረው ተቀየሩ ፣ ህይወት ለኔ ዋዛ እንደሆነች መስላ ጠልፋኝ ነበረ የሚያውቁኝ ሰዎች " ኤልያስ ቆሞ መቅረቱ ነው " ብለው ያሙኝ ነበረ ፈጣሪ ወደ ህይወቴ ማርታ የምትባል መልአከ ህይወት ላከ ፣ ማርታን ያወቅኳት ፓስታ ቤት እየሰራች ነበረ ፣ ውብ ነበረች ሌላ ጊዜ እንደምቀርባቸው ሴቶች ልቀርባት ያልሞከርኩት ነገር የለም ግን የዋዛ አልነበረችም ቀኖች በሄዱ ቁጥር ለሷ ያለኝ ስሜት ተቀየረ  ተቀራረብን የሆነ ቀን ስለ ህይወቷ በትንሹ አጫወተችኝ አግብታ እንደፈታች እና የአንድ ልጅ እናት እንደሆነች ልጇ የባሏ እናት ጋ እንደሚኖር እሷ ብቻዋን ተከራይታ እንደምትኖር ባሏም ሰካራም እንደሆነ እና ሰካራም እንደምትጠላ ነገረችኝ ። የበፊት ህይወቴን ነገርኳት እናም ከዚህ ህይወት መውጣት እንደምፈልግ ነገርኳት ማርቲ ቀስ በቀስ ለወጠችኝ እሷን ለማስደሰት ስል አልጠጣም አልቅምም አላጨስም ገንዘብም መያዝ ጀመርኩ ከማርቲ ጋ በጣም ስንግባባ ጊዜ ስናሳልፍ አብሮ የመኖር ሀሳብ መጣ  አዲስ ቤት ተከራይተን መኖር ጀመርን የድሮ ጓደኞቼ የሚያውቁኝ ሰዎች " ኤልያስ ቫይረስ ሳይዘው አይቀርም ይሄኔ ከእሷም ጋ ሚኖረው ሁለቱም ታማሚ ሆነው ነው  " እያሉ እንደሚያሙኝ ሰማሁ ፣ በርሜል ሙሉ ሀሜት አንድ እንጀራ አይጋግርም ብዬ ጆሮዬን ደፍኜ ህይወቴን ቀጠልኩ እገባባቸው የነበሩ ባሮች ፣ እተኛቸው የነበሩ ሴቶች በሙሉ አስጠሉኝ ፣ የድለላውንም ስራ ቤት ሆኜ መሥራት ጀመርኩ ።

ማርቲ ከእኔም ከእሷም ብር አጠራቅማ ትንሽዬ ሸቀጣ ሸቀጥ ሱቅ ከፈትን ፣ ትንሽ እንደሰራች ሴት ልጅ ወለድን  ስሟንም ተዐምር አልነው ልጃችን ህይወታችንን ይበልጥ አሳመረችው ፣ ፈጣሪ እንደ ሀጥያቱ የከፈለው ሰው ላለመኖሩ ምስክር ነኝ ማርታን ከሞት ህይወት መውጫ በትር አድርጎ ሰጠኝ ፣ አንዳንዴ ያለምንም ስራ ያለምንም ድካም ያለምንም እቅድ በህይወታችን የሚመጣ የፈጣሪ በረከት አለ ፣ አምላክ በማርታ በኩል ለኔ ቸርነቱን ገለጠ ፣ ከብኩነንት ከበድንነት ህይወቴን ለመለሰችው ማርታ ህይወቴን ሰጥቼ ላፈቅራት ወሰንኩ ልጄንም በንፁህ ልቤ ወደድኳት በህይወት እስከነበርኩበት ጊዜ ሁሉ በሙሉ ልቤ እወዳችሁ ነበረ " አልያስ ይላል ።

እናት እና ልጅ ተቃቅፈው አለቀሱ ተዐምር " እናቴ አንቺስ አባቴን ሳታውቂው ህይወትሽ እንዴት ነበረ ? " ብላ ጠየቀቻት ማርታ ፊቷ ላይ ያለውን እንባ እየጠረገች " ልጅ እያለሁ እናቴ ለአንድ ሀብታም ሰው ዳረችኝ ሰካራም ነበረ ይማታል ሰውን ከጥፍሩ ቆሻሻ አይቆጥርም አንድ ልጅ ወለድኩ ፣ ስወልድ ይበልጥ አስጠላሁት ምቱ ስካሩ ስድቡ ጨመረ ይህን መቋቋም ሲያቅተኝ ባለቤቴን በህግ ፈታሁት ያለምንም ንብረት ክፍፍል ልጄን ጥዬ ቤቱን ለቅቄ ወጣሁ ፣  ያኔ የህይወት መንገዶች ተዘግተውብኝ ነበረ የወንድምሽን አባት ፈትቼ ወደ ውጭ ሀገር ለስራ ሄድኩ ግን የምኖርለት ነገር ስላልነበረኝ ብዙ መልፋቱ መስሎ አልታየኝም ትንሽ ብር ይዤ ሀገሬ ተመለስኩ ከዚያም ፖስታ ቤት ተቀጥሬ እየሰራሁ ብቻዬን ተከራይቼ መኖር ጀመርኩ አባትሽ መልእክት ለመላክ ይመላለስ ነበረ በዚህ ተዋወቅን በብዙ ፈተንኩት ፣ ከበፊት ህይወቱ እኔን እንደመረጠ ራሱን በመግዛት አሳየኝ ፣ እንክብካቤው ለሴት ያለው ክብር ለመኖር ያለው ፍላጎት አብሬው እንድኖር አስገደደኝ በፈጣሪ እገዛ ጎጆ ወጣን ፣ ህይወታችን ቀስ በቀስ ተቀየረ አንቺ ስትወለጂ አባትሽ ተዐምር ብሎ አወጣልሽ ፣ ልጄ ህይወት ላይ ለመኖር ዳግም እድል እንደማግኘት ያለ ተዐምር ያንን ደግሞ እንደመጠቀም ያለ ጥበብ የለም " እያለች ወረቀቱን አልበሙ ውስጥ ከተተችው ።


#በረከት_ዘውዱ

@beki_book
👍4👏1
የሟች ሚዜ


ሳሚን ያወቅኩት ሀይ ስኩል ዘጠነኛ ክፍል ተማሪ እያለሁ ነው ወንድሜ እንደሞተ ከለገጣፎ አዲስ አበባ አክስቴ ጋ መጣሁ አክስቴ ባሏን ፈታ ከልጇ ጋ ብቻዋን ነው ምትኖረው ጠዋት አስራ ሁለት ሰዓት ወጥታ ማታ አስራ ሁለት ሰዓት ትመጣለች ፣ የቤቱን ስራዎች መስራት እና ልጇን መንከባከብ የኔ ሀላፊነት ነበር አክስቴ ቅዳሜ እና እሁድ ታግዘኝ ነበረ ፣ ለአዲስ አበባ አዲስ ስለነበርኩ ጓደኛ ለማፍራት ብዙ ጊዜ ወሰደብኝ ወደ ትምህርትና ቤት ብቻዬን ነበር ምመላለሰው የአክስቴን ልጅ ከትምህርት ቤት ለማምጣት እንዳይረፍድብኝ እየቸኮልኩ እራመዳለሁ ፣ አብዛኛውን ጊዜ ትምህርት ቤት ስለ ወንድሜ እና እናቴ ሞት እያሰብኩ ብቻዬን እሆናለሁ ፣ ሳሚን ያን ጊዜ ነበር ያወቅኩት ፣ ከትምህርት ቤት ስወጣ ልሸኝሽ አለኝ እንደምቸኩል ብነግረውም ከኔ እኩል መፍጠን እንደሚችል ነግሮኝ ሸኘኝ ተዋወቅን ፣ ነገሮች ሲደጋገሙ ጓደኞች ሆንን ብቸኝነት ተሽቀነጠረ በጓደኝነት ከነፍን አክስቴ ፊልድ ከሆነች አልፎ አልፎ ፓርቲ ደይ በሚል ሰበብ እንጠጣለን አስራ ሁለት ስንደርስ እንደሚያፈቅረኝ ነገረኝ እኔም ስለማፈቅረው ጥያቄውን ተቀበልኩ ።

እኔ ENTRANCE ውጤት መጥቶልኝ ደብረ ብርሀን ዩኒቨርስቲ ተመደብኩ ከ አራት ዓመት በኋላ በ አካውንቲንግ ተመረቅኩ ፣ ሳሚ ከዱርዬዎች ጋ እንደገጠመ እና በጣም አደገኛ ሱሶች እንደጀመረ እናቱ ነገረችኝ ፣ ትላንት ፊቴ ላይ ድቅን አለ ፣ ኩርፊያዬን አይቶ ቀኑ ሚረበሸውን ፣ ከእኔጋ ጊዜ ለማሳለፍ ጓደኞቹን የገፋውን ፣ እንዝናና ካልኩት ብር ከየትም ተበዳድሮ የሚያመጣው ሳሚ ፣ አራት አመት ስንቆይ ከንፈሩን እንኳ ስስመው ደንግጦ ሳምንት ያኮረፈኝ እኔ ላይ ስሜቱን መወጣት ያልፈለገው ጓደኞቹ ፋራ እያሉት ስሜቱን ገዝቶ በፍቅር ያነገሰኝ ሳሚ ዛሬ በቁሙ እንዳጣሁት ተሰማኝ ፣ ካለበት ፈልጌ ሳገኘው በአፉ ተርዚና ይዟል በአንድ እጁ ሲጋራ በአንድ እጁ ጫቱን አቅፎታል ሲያየኝ ምንም አልመሰለውም ፣ ምንም እንዳልተፈጠረ ተነስቶ በአጠገቤ አለፈ ተከተልኩት ሳሚ ሳሚ አንድ ጊዜ እናውራ አልኩት " ሀና እኔ አልሆንሽም በቃ እኔ ላንቺ አልመጥንሽም " ብሎኝ መልሴን ሳይጠብቅ ሄደ ።

ጥዬው ስለሄድኩ ይሆን ምናለ ከሱጋ ፍቅር ባልጀምር ምን ነበር ባንገናኝ እያልኩ ሳስበው አመሸሁ ጠዋት እንደ ነጋ ወደ ቤቱ ሄድኩ ፣ እናቱ ሲቀሰቅሱት ስካሩ አለቀቀውም " ኤጭ አንቺ ለምን መጣሽ ለምን አተይኝም " አለኝ እንደማልተወው እና ነገሮች መስተካከል እንደሚችሉ ነገርኩት ፣ ግን ሊያደምጠኝ ፍቃደኛ አልነበረም ፣ ከእናቱ ጋ ተማከርኩ ፀበል እንድወስደው ተነጋግረን ለሳምንት ቀጠሮ ያዝን እህቱ በመሐል ደወለች ድምጿ እየተቆራረጠ እያለቀሰች " ሳሚ ሞተ ተለየን " አለችኝ የሰማሁትን ማመን አልቻልኩም እየበረርኩ ቤታቸው ስደርስ ድንኳን ተጥሏል እናት እና እህቱ ሳጥኑን አቅፈው ያለቅሳሉ ፣ የማላውቀው ስሜት ወረረኝ እየተንደፋደፍኩ አለቀስኩ ፣ ሳሚ የጫት ብር ለመሙላት ሰርቆ ሲሮጥ መኪና ገጭቶት ህይወቱ አለፈ ፣ ወደ ራሱ ተመልሶ ተጋብተን አንድ ላይ እንኖራለን ያልኩት ተስፋ ነፋስ እንደበዛበት ሻማ ጠፋ ፣ ህይወት የምወዳቸውን ሰዎች ልትነጥቀኝ የቆመች የሰርግ ሳይሆን የሞት ሚዜ ምታደርገኝ እስክትመስለኝ ድረስ አዘንኩ ።

#በረከት_ዘውዱ

@beki_book
4
አክስቴና ገጠመኞቿ

#sit_down_tragedy

ክፍል አንድ

አክስቴ በጣም ከሚያናዱኝ እና ከሚያዝናኑኝ ሰዎች አንዷና ብቸኛዋ ናት ማለት እችላለሁ ፣ እድሜዋ ወደ ሀምሳዎቹ ይደርሳል ትዳር የላትም ሳታገባ ቀርታ አይደለም ግን ከባሏ ጋ ሊስማሙ ባለመቻላቸው አንድ ልጅ አፍርተው ተለያይተዋል ።

ሁል ጊዜም በጠዋት ለነገሩ ለኔ ነው ጠዋት ማለዳ ሶስት ሰዐት አካባቢ ገና ከእንቅልፌ ሳልነቃ ወደ ቤት ትመጣለች ፣ " ደጃፉ ዛሬም ተኝተሀል " ፣ ደጃፉ የምትለኝ ማታ ማታ አምሽቼ ስለምገባ ነው ፣ " በል ተነስ ታጠብና እህል ቅመስ እስቲ...አፍህ ራሱ ምን ምንድነው ሚለው አንተ አፍ ላይ ነው እንዴ ቢራውን ሚጠምቁት ወይኔ ብርቄ አሳድጌ አስተምሬህ ተመርቀሀል....ታድያ ወግ ማዕረግ አሳይተህ ትጦረኛለህ ስል ጦር ሆነህ ትወጋኝ በል ተነስ ታጠብ "

ይኸውልሽ አክስቴ ብርቅዬ የኔ ብርቅ ብርቅርቅታ " ምነው ምን ልትጠይቀኝ ነው " ኧረ ምንም አክስቴ ሁሌ ሳሞግስሽ ምፈልገው ነገር አለ ማለት ነው አክስቴ " ታድያ አንተ መች በጤና ታቆላምጠኛለህ " አይይ አይደለም አክስቴ ያው የምስራች ልነግርሽ ነው " ምስር ብላ በላ ንገረኝ " እየበላሁ ነው አክስቴ ይልቅ አንቺ ለምን አትበይም ? " እኔ ቤት በልቼ ነው የመጣሁት በል ምስራቹ ምንድነው ? " ስራ አጊኝቻለው " አንተ መቼ ስራ አጣህ " ታድያ ምድንድነው ያጣሁት ? " ሚስት ሰብሰብ ምታደርግህ ሴት ነዋ " አይይ አክስቴ መቼ ተበትኜ ነው ምሰበሰበው " ከዚህ በላይ የፓርላማው ድክመት ነው እንጂ እኮ ተኝተሀል " አይይ አክስቴ ተጫዋች ነሽ እኮ " አንተ ነህ እንጂ ምትጫወተው በእድሜህ እና በወጣትነትህ ! እየተጫወትክ አይደል¡......በል በላ በላ አርግና ተነስ ስራ እንዳይረፍድብህ " ።

መዝገብ 1

አክስቴ እና እኔን አንድ ሚያደርግን እኔ እናቴን በሞት ሳጣ አክስቴ ልጇን በሞት አጣች እናም እንደ አክስት ሳይሆን እንደ እናት አሳደገችኝ ሁሌም እንዳገባ ትፈልጋለች እኔም እፈልጋለሁ ግን የኔን ግራ ጎን ፈጣሪ አልፈጠራትም ይሆን ወይስ አኙአክ ብሄረሰብ ውስጥ የጦላጳቂንቂ ጎሳ ተወላጅ ናት ጦላጳቂንቂ ይህንን ቃል ደሞ ከየት አመጣሁት ።

በረከት_ዘውዱ

#ክፍል_ሁለት .....


@beki_book
@beki_book
@beki_book
👍4