Basic Computer Skills
1.87K subscribers
1.22K photos
100 videos
576 files
833 links
#በዚህ የቴሌግራም ቻናል
↪️ Programming
↪️ ቴክኖሎጂ ነክ ትምህርቶችን
↪️ ኮምፒውተር ነክ ትምህርቶችን
↪️Basic Computer Skills
↪️ Software
↪️ AI and AI Skills (Like ChatGPT)

ከላይ የተዘረዘሩትና ሌሎችም ገራሚ ትምህርቶች ይለቀቅበታል!

t.me/BasicComputerSkillsGroup

𝘽𝙮 𝙍𝙚𝙨𝙝𝙖𝙙
Download Telegram
☑️All Mobiles Secret👁‍🗨 Codes AdFree
All Mobiles Secret Codes AdFree v1.3 @ApkManagerBot.apk
2.2 MB
Short Cut-signed.pdf
719.4 KB
Title: All Shortcuts for Students

Page: 27

MB size: 719.4KB

Prepared by: Reshad Muzemil

Pass it on: 🇪🇹 Ethio 🌎Worldwide Students

Telegram:

t.me/TechnologyMasterPage
የሳምሰንግ ስልክ ኦርጅናልና ፎርጅዱን ለመለየት
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇

1) *#9999# ወይም *#0837# - ብለው ፅፈው ሲደውሉ የሶፍትዌሩን አይነት
ያወጣልናል። ካላወጣ ኦርጅናል አይደለም ማለት ነው።

2) #0523# - ብለው ፅፈው ሲደውሉ የስክሪኑን የከለርና የብርሀን አይነት
ለመቀያየር ይረዳናል። ስትጠቀሙ አማራጮችን ካላመጣላቹ፣ ኦርጅናል
አይደለም።

3) *0377# - ስለሜሞሪው መረጃ ይሰጠናል። ካልሰጠን ኦርጅናል አይደለም።

4) *9998*228# - የባትሪውን ሁኔታ ለማየት። ካላወጣ ኦርጅናል አይደለም።

5) *998*289# - አላርሙን መሞከሪያ።

6) *#9987*842# - ቫይብሬቱን ለመሞከር።

7) *2767*3855# - ወደ መጀመሪያው ወደ ተመረተበት (ወደ ፋብሪካው)
ለመመለስ፣ ነው የሚያገለግለው። ይህ ግን አይመከርም፣ ምክኒያቱም ስልካቹ
ላይ ያለው ጠቅላላ መረጃ፣ ፎቶዎች፣ ቪዲዮች፣ ዘፈኖች ይጠፋሉ።

t.me/TechnologyMasterPage
ሪሞት ዴስክቶፕ ኮኔክሽን (Remote Desktop Connection)
ሪሞት ዴስክቶፕ ኮኔክሽን (Remote Desktop Connection) ማለት በአንድ አይነት ኔትወርክ ላይ የሆኑ ኮምፒውተርችን ወይም በኢንተርኔት የተያያዙ ኮምፒውተሮችን ከርቀት ሆኖ ከአንድ ኮምፒውተር ላይ ለመቆጣጠር የምንጠቀምበት የዊንዶ ኦፕሬቲንግ ሲስተም ላይ የምናገኘው ፕሮግራም ሲሆን ባለገመድና ገመድ አልባ ኔትወርክ ላይ እንጠቀምበታለን::
አንድ ሲስተም አድሚኒስትሬተር ሪሞትሊ ሆኖ ሌላ ኮምፒውተር ላይ በሪሞት ዴስክቶፕ በመግባት(በመጠቀም) ፋይሎችን ማዘዋወር፣ ዳውንሎድ ማድረግ፣ ሶፍትዌሮች ሲበላሹ ማስተካከል፣ ኢንስቶል(መጫን)ና ሶፍትዌሮችን ማጥፋት ይችላል፡፡ፕሮግራሙን ለመጠቀም በኔትወርኩ ውስጥ ያሉ ኮምፒውተሮች መከፈት ይኖርባቸዋል እንዲሁም ኔትወርክ ኮኔክሽን(ግንኙነት) መኖር አለበት በተጨማሪ ሪሞት ዴስክቶፕ ፕሮግራም በእያንዳንዱ ኮምፒውተር ላይ መከፈትና ኔትወርክ አክሰስ መፈቀድ ይኖርበታል ይሄን ለማድረግ የአድሚኒስትሬተር አካውንት ተጠቃሚ መሆን ይኖርበታል
ሪሞት ዴስክቶፕ ለመክፈት የምንከተለው ሂደት
1. ማይኮምፒውተር ላይ ራይት ክሊክ ፕሮፐርቲ
2. ሪሞት ዴስክቶፕ (Remote Desktop) ታብ
3. Allows users to connect remotely to this computer የሚለውን ሳጥን እንምረጥ
4. ሪሞትሊ ይህን ኮምፒውተር የሚጠቀሙትን ዩዘሮች(ተጠቃሚዎች) ሴሌክት ሪሞት ዩዘር የሚለውን ቁልፍ በመጫን በኔትወርካችን ውስጥ ያሉ ዩዘሮችን እንምረጥ
5. ኦኬ
ማስታወሻ
ሪሞት ዩዘር ተጠቃሚዎችን መምረጥ የግድ አስፈላጊ አይደለም በፈላጎታችን ለሴኩሪቲ የምነመርጠው ነው
ሪሞት ዴስክቶፕ ለመጠቀም የምንከተለው ሂደት(ስቴፕ)
1. ስታርት - ራን
2. በራን ሳጥን ላይ mstsc ብለን ኦኬ
ወይም
1. ስታርት
2. ኦል ፕሮግራምስ
3. አክሰሰሪስ
4. ኮምኒኬሽን
5. ሪሞት ዴስክቶፕ ኮኔክሽን
🖥🖥🖥🖥🖥🖥🖥🖥🖥
👉👉Click the Start Window

💻👉Type in and enter remote settings into the Cortana search box

💻👉Select Allow Remote PC access to your computer

👉👉Click the Remote tab on the System Properties window

👉👉Click Allow remote desktop connection Manager to this computer

👉👉Make sure the box beside Network Level Authentication is checked. This will ensure that you have a more secure remote access experience.
👉👉👉You can also download and install free remote access software online. 

t.me/TechnologyMasterPage
ለቫይረስ አሪፍ መላ
በቫይረስ የተጠቃ ወይም 'corrupt' የሆነን ፍላሽ ዲስክ እንዴት ያለአንቲ ቫይረስ
እንደምናጸዳውና ስንገዛው እንደነበረው አዲስ እንደምናደርገው እናያለን። አሁኑኑ ሼር
አድርጉት
እባክዎ ከመጀመርዎ በፊት ፍላሹ ላይ ጠቃሚ ፍይል ካለዎት ወደ ሌላ ቦታ ኮፒ ያድርጉ።
በመጀመሪያ ኮምፒዩተራችን ላይ 'command prompt' ወይም 'cmd' እንከፍታለን።
( 'cmd'ን ለመክፈት በመፈለጊያችን ላይ cmd ብለን search እናደርጋለን. Cmd
ሲመጣልን right click አድርገን run as administrator የሚለውን በመጫን cmdን
እንከፍታለን)
Cmd ከከፈትን በኋላ የሚከተሉትን ትእዛዞች በቅደም ተከተል እናስገባለን። እያንዳንዱን
ትእዛዝ ከጻፍን በኋላ ENTER ቁልፍን እንጫናለን
1. DISKPART

2. LIST DISK (አሁን በኮምፒውተሩ ላይ ያሉትን ዲስኮች ይዘረዝርልናል. ለማጽዳት
የፈለግነውን ፍላሽ ቁጥር ከለየን በኋላ ወደ ሶስተኛው ትእዛዝ እንሄዳለን። ምሳሌ.disk 1)

3. SELECT DISK * (በኮከቡ ፋንታ ሁለተኛው ትእዛዝ ላይ የለየነውን የፍላሽ ቁጥር
እናስገባለን)

4. CLEAN (በዚህ ጊዜ ፍላሹ ላይ ያለውን ማንኛውም ነገር ያጠፋዋል)
5. CREATE PARTITION PRIMARY (ለፍላሹ ይዘት ይፈጥራል)

6. SELECT PARTITION 1

7. ACTIVE (ይህ ፍላሹን ዝግጁ ያደርገዋል)

8. FORMAT FS=FAT32 (ይህ ፋላሹን በጥልቀት በመሰረዝ በውስጡ ያሉትን ማንኛውም ቫይረስ ወይም ሌላ ችግር ያጠፋል። ሂደቱ የተወሰነ ጊዜ ስለሚወስድ
እስከሚጨርስ በትዕግስት እንጠብቀዋለን)

9. ASSIGN (አዲስ ለፈጠርነው ፍላሽ የፊደል ስም ይሰጥልናል)

10. EXIT (ፕሮሰሱን ይጨርስልናል)
አሁን አዲሱን ፋላሻችንን መንቀልም ሆነ መጠቀም እንችላለን።

📶 ይህንን መንገድ በመጠቀም ማንኛውንም ችግር ያለበት ፍላሽ ማስተካከል እንችላለን።

t.me/TechnologyMasterPage
#ICT_terms

30 የ ICT ቴክኒካዊ ስያሜዎች

1. #ጥቁር_መዝገብ (Blacklist) - በገዳቢ የክልከላ ፖሊሰ የታገዱ ድረ ገጾች እና ሌሎች የኢንተርኔት አገልግሎቶች ዝርዝር ነው።

2. #ብሉቱዝ (Bluetooth) -ገመድ አልባ ከሞባይል እና
ከባለመስመር ስልኮች በአጭር ርቀት ዳታ ለመላላክ የሚያስችል ገመድ የግንኙነት ደረጃ ነው። ቡሉቱዝ ዳታ ለመለዋወጥ አጭር ሞገዶችን ይጠቀማል

3. #ቡቲንግ (Booting) - ኮምፒውተርን ሥራ
ማስጀመር ወይም ማስነሳት ነው።

4. #አቫስት (Avast) - ጸረ ቫይረስ መሣሪያ

5. #መሠረታዊ _የግብአት/ውጤት ሲስተም ሶፍትዌር (Basic Input/Output System-BIOS) -የኮምፒውተር ሶፍትዌር የመጀመሪያው እና መሠረታዊው ደረጃ ነው። ባዮስ የኮምፒውተራችንን ሐርድዌር ደኅንነት ለማረጋገጥ የሚረዱ የተለያዩ አማራጮችን ይሰጠናል፤ ኮምፒውተራችን ሲከፈት በይለፍ ቃል ብቻ እንዲገባ ማድረግ ከእነዚህ አንዱ ነው።

6. #ሲክሊነር (CCleaner) - በነጻ የሚገኝ ሶፍትዌር ነው። በቅርብ በተጠቀምንባቸው ፕሮግራሞችና በዊንዶውስ ኦፐሬቲንግ ሲሰተም አማካኝነት በሐርድዌራችን ላይ የተተዉ ጊዜያዊ ፋይሎችን ዱካ የሚያሳዩ መረጃዎችን የሚያጸዳ ሶፍትዌር ነው።

7. #ሲዲ_በርነር (CD Burner) - በባዶ ሲዲዎች
ላይ መረጃ ለመጻፍ የሚችል የኮምፒውተር ድራይቭ ነው።
ዲቪዲ በርነር (DVD burners) በተመሳሳይ
መንገድ በባዶ ዲቪዲዎች ላይ ይጽፋል።
ሲዲ-አርደብሊው (CD-RW ) እና ዲቪዲ-አርደብሊው ድራይቮች (DVD-RW drives) ደግሞ በሲዲ/ ዲቪዲ ላይ የተጻፈውን አጥፍተው ከአንድ ጊዜ በላይ መልሰው
መጻፍ ይችላሉ።

8. #ሰርከምቬንሽን (Circumvention) - በኢንተርኔት አፈና የታገዱ ድረ ገጾችን እና
የኢንተርኔት አገልግሎቶችን ለማግኘት እገዳውን ማለፍ።

9. #ክሌም_ዊን (Clam Win) - ለዊንዶውስ የተሠራየኤፍኦኤስኤስ ጸረ ቫይረስ

10. #ኮቢያን_ባክአፕ (Cobian Backup) -
የኤፍኦኤስኤስ የመጠባበቂያ ማከማቻ መሣሪያ ነው።
የቅርብ ጊዜዎቹ የኮቢያን አይነቶች ምንጫቸው
የማይገለጽ ነገር ግን በነጻ የሚገኙ ናቸው፤
የቀድሞዎቹ ግን በኤፍኦኤስኤስ ብቻ የሚለቀቁ ነበሩ።

11. #ኮሞዶ_ፋየርዎል (Comodo Firewall) -
ምንጩ (ውስጣዊ መዋቅሩ) ለምርመራ ክፍት የሆነ፣በነጻ የሚገኝ የፋየርዎል መሣሪያ ነው።

12. #ኩኪ (Cookie) - የኢንተርኔት ማሰሻ
(browser) በኮምፒውተር ላይ የሚተዋቸው የጎበኘነውን ድረ ገጽ እና ተያያዥ መረጃዎችን መዝግቦ የሚይዝ አነስተኛ ፋይል ነው።

13. #ዲጂታል_ፊርማ (Digital signature) -
ኢንክሪፕሽንን በመጠቀም አንድ ፋይል ወይም መልእክት ከትክክለኛው ሰው የተላከ መሆኑን
የማረጋገጫ መንገድ

14. #የዶሜይን_ስም (Domain name) - በቃላት
የሚገለጽ የድረ ገጽ ወይም የኢንተርኔት አገልግሎት አድራሻ

15. #ኢንክሪፕሽን (Encryption) - የተራቀቀ ሒሳባዊ ስሌትን በመጠቀም ኢንክሪፕት (encrypt) ማድረግ፤ ትክከለኛው መረጃ ማለትም ያለው የይለፍ ቃል ወይም የኢንክሪፕሽን ቁልፍ (encryption key) ሰው ብቻ ኢንክሪፕት የተደረገውን መረጃ ዲክሪፕት ማድረግ/መክፈት (decrypted) እንዲችል የሚያደርግ

16. #ኢንጂሜይል (Enigmail) - የታንደርበርድ
የኢሜይል ፕሮግራም አጋዥ መሣሪያ (add-on) ነው፤ ተጠቃሚዎቹ ኢንክሪፕት የተደረገ ወይም
በዲጂታል ፊርማ የታተመ መልእክት ለመላክና ለመቀበል የሚያስችል

17. #ኢሬዘር/መደምሰሻ (Eraser) ከኮምፒውተር
ወይም ከሌሎች ተንቀሳቃሽ የመረጃ ማከማቻዎች ላይ የሚገኝ መረጃን በአስተማማኝ እና በዘላቂነት ከነጭራሹ ለማጥፋት (delete) የሚያከማይክሮሶፍት

18. #ፋየርፎክስ (Firefox) - የታወቀ የኤፍኦኤስኤስ ማሰሻ (FOSS Web browser) ነው፤ ከማይክሮሶፍት ማሰሻ “ከኢንተርኔት ኤክስፕሎረር” የተለየ አማራጭ ነው።

19. #ፋየርዎል (Firewall) - ኮምፒውተርን
አስተማማኝ ካልሆኑ የኢንተርኔት እና የቤት ውስጥ መረቦች ግንኙነት የሚጠብቅ መሣሪያ ነው።

20. #ነጻና_ቀመሩ የሚታይ ሶፍትዌር- ኤፍኦኤስኤስ
(Free and Open Source Software-FOSS) -
ያለክፍያ በነጻ የሚገኙ እንዲሁም ተጠቃሚዎች
የሶፍትዌሮቹን አሠራር እንዲመረምሩ፣ እንዲፈትሹ፣ እንዲያሻሽሉና ለሌሎች አሳልፈው እንዲሰጡ የሚፈቅዱ ሶፍትዌሮች ምድብ

21. #ፍሪዌር (Freeware) - በነጻ የሚገኙ፣ ነገር ግን ተጠቃሚዎች መሠረታዊ የፈጠራ አወቃቀሩን (sourcecode) እንዳያገኙ ሕጋዊና ቴክኒካዊ ክልከላዎችን የሚያደርጉ ሶፍትዌሮች

22. #ጂኤንዩ/ሊኑክስ (GNU/Linux) -
የኤፍኦኤስኤስ ኦፐሬቲንግ ሲስተም ነው፤
ለማይክሮሶፍት ዊንዶውስ አማራጭ ሲስተም ነው።

23. #ጂፒኤስ (Global Positioning System - GPያደረገ በስፔስ/ምህዋር ላይ መሠረት ያደረገ
በሳተላይት በመታገዝ ቦታንና ጊዜን ለመለየት የሚያስችል፤ በማንኛውም የአየር ሁኔታ፣
በየትኛውም የምድራችን ወይም በአቅራቢያዋ ባሉ ቦታዎች የሚሠራ፤ ከሞላ ጎደል በምንም ነገር የማያደናቀፍ ከሰማይ ከፍታ ለመመልከት የሚያስችል የሳተላይት መመልከቻ ነው።

24. #ሐከር/ሰባሪ (Hacker) በዚህ አገባቡ፣ ከርቀት ኮምፒውተራችንን ሙሉ በሙሉ ለመቆጣጠር ወይም ስስ
መረጃዎቻችንን ለመስረቅ አይፒ የሚሞክር ወንጀለኛ

25. #የኢንተርኔት_ፕሮቶኮል_አድራሻ-(
አድራሻ) (Internet Protocol address -IP
address) - ማንኛውምሰጪ ኮምፒውተር ከኢንተርኔት ጋራ ሲገናኝ የሚሰጠው ልዩ መለያ

26. #ኢንተርኔት_አገልግሎት (አይኤስፒ)
(Internet Service Provider-ISP) - የኢንተርኔት ወይም ግንኙነት መስመር አገልግሎት የሚሰጥ ኩባንያ ወይም ድርጅት። የብዙ አገሮች መንግሥታት ኢንተርኔትን በጣም
ይቆጣጠራሉ፤ እነዚህን አገልግሎት ሰጪዎች (አይኤስፒ) በመጠቀምም የኢንተርኔት አሶሲዬሽን ክልከላ፣ ስለላ እና እገዳ ያደርጋሉ።

27. #ኢንፍራሬድ_ዳታ (Infrared Data
Association) (ኢርዳ/IrDAአልባ በአጭር ርቀት
የኢንፍራሬድ ስፔክተረም ጨረሮችን በመጠቀም
መረጃ/ዳታ ለመለዋወጥ የሚያስችል ገመድ አልባ የግንኙነት መንገድ ነው። በዘመናዊ መገልገያዎች ውስጥ ኢርዳ/IrDA በብሉቱዝ ተተክቷል።

28. #ጃቫ_አፕሊኬሽንስ (Java Applications)
(አፕልትስ/Applets) - በብዙ ኦፕሬቲንግ ሲስተሞች ላይ የሚሠሩ አነስተኛ ፕሮግራሞች ናቸው። ብዙውን ጊዜ በድረ ገጾች ውስጥ የተሻሻሉ አገልግሎቶችን (functionalities) ለመስጠት ጥቅም ላይ ይውላሉ።

29. #ኪይሎገር (Keylogger) - ለስለላ ተግባር
የሚውል የስፓይዌር አይነት ነው፤ በኮምፒውተሩ
የመተየቢያ ገበታ (keyboard) ላይ የነካናቸውን/ የተጫንናቸውን ቁልፎች/ፊደሎች በሙሉ መዝግቦ ለሦስተኛ ወገን ይልካል። ኪይሎገሮች የኢሜይሎችን እና የይለፍ ቃሎችን ለመስረቅ በብዛት ጥቅም ላይ ይውላሉ።

30. #ኪፓስ (KeePass) - የአስተማማኝ የይለፍ ቃል ማከማቻ (database) ፍሪዌር ነው።

#Reshad_Muzemil

t.me/EthioWorldwideStudents
​​🔥 ኮምፒውተርዎን ፈጣን የሚያደርጉ 10 ዘዴዎች፡

💻 ኮምፒውተር ሲዘገይ በጣም ያበሳጫል አንዳንዴ ስበሩት ስበሩት ያሰኛል። ስንት ገንዘብ የከሰከሱበትን ኮምፒውተር ከመስበርዎ በፊት ግን እነዚህን ዘዴዎች ይተግብሯቸው። እርስዎን ከብስጭት፣ ኮምፒውተርዎንም
ከመሰበር ይታደግዎታል፡፡

🔰 ትላልቅ መጠን ያላቸውን ፎቶዎች (ዋልፔፐር) አይጠቀሙ፡፡

🔰 ሁሌም ኮምፒዩተሩ ከፍቶ ሳይጨርስ አፕሊኬሽን ለመክፈትም ሆነ ለመነካካት አይሞክሩ፡፡

🔰 አፕሊኬሽን ከዘጉ በሁዋላ ዴስክቶፑን ሪፍሬሽ ያድርጉ፤ ይህም ራም ሜሞሪን ነፃ ያደርጋል፡፡

🔰 የማይጠቀሙበት አፕሊኬሽን ካለ ከኮምፒውተሩ ይሰርዙ (አን-
ኢንስታል) ያድርጉት።

🔰 ዴስክቶፕ ላይ ፋይል አያስቀምጡ፤ ሾርትከትም መብዛት የለበትም፡፡

🔰 ኮምፒዩተሩ ሲከፈት በራሳቸው የሚከፈቱ ለምሳሌ: ስካይፒ አይነት አፕሊኬሽኖች ካሉ disable ያድርጉ

🔰 Recycle binን ሁሌም ባዶ ያድርጉ::

🔰 ሀርድ ዲስኩን ሁለት ፓርቲሽን ይፍጠሩለት፡፡

🔰 ብዙ አፕሊኬሽን ባንዴ አይክፈቱ::

t.me/TechnologyMasterPage
✴️ የኢንተርኔት አጠቃቀማችንን ቀለል የሚያደርጉ አቋራጭ ስልቶች
---------------
📍ማውዝ ማንቀሳቀስ ሳያስፈልገን የኪቦርድ ቁልፎችን ብቻ በመጠቀም የኢንተርኔት አጠቃቀማችን ቀላል እና ፈጣን ማድረግ እንችላለን፡፡

📍1. አዲስ ድረ ገፅ ለመክፈት
በተለምዶ አዲስ የድረ ገፅ አድራሻ ለመክፈት http:// ወይም www አስቀድመን እንፅፋለን፡፡ ይሁን እንጂ የምንፈልገውን ድገ ገፅ ስም ብቻ ፅፈን ብቻ <Ctrl> እና <Enter> በአንድ ጊዜ ስንጫን http:// ወይም www ከፊት እንዲሁም “.com” ከኋላ በራሱ ጨምሮ ወደ ድረ ገፁ በቀላሉ መግባት ያስችለናል፡፡
ለምሳሌ፦ ወደ www.facebook.com ድረ ገፅ ለመግባት ቢፈልጉ የሚጠበቅብዎት በአድራሻ መፃፊያ ስፍራው ላይ facebook ብለን ፅፈን Ctrl እና Enter አከታትለን መጫን ብቻ ነው፡፡ የድረ ገፁ አድራሻ መጨረሻው “.org” ከሆነ የፈለግነውን ድረ ገፅ ፅፈን Ctrl + Shift + Enter፤ በ“.net” የሚልቅ ከሆነ ደግሞ Shift + Enter ወደምንፈልገው ድረ ገፅ እንድንገባ ያግዘናል፡፡

📍2. ከአንድ አምድ ወደ ሌላ አምድ ለመሸጋገር
በኢንተርኔት የተለያዩ ቅፆችን በምንሞላበት ጊዜ ከአንዱ አምድ ወደ ሌላ ለመሸጋገር Tab
ቁልፍን መጠቀም እንችላለን፡፡
ወደ ኋለኛው አምድ ለመመለስ ደግሞ Shift + Tab አቋራጭ ነው፡፡

📍3. አዲስ ታብ ለመክፈት - Ctrl + T
📍4. የተከፈቱ ታቦችን ለመዝጋት - Ctrl + W

📍5. ከአንዱ ታብ ወደ ሌላ ታብ ለመሄድ - Ctrl + Page Up ወይም Ctrl + Page Down

📍6. በቅርቡ የዘጋናቸውን ታቦች እንደገና ለመክፈት - Ctrl + Shift + T

📍7. በድረ ገፆች ላይ የፊደላትን መጠን ለመጨመር Ctrl ከዚያም + ፤ ለመቀነስ Ctrl እና የፊደላቱን መጠን ወደነበረበት ለመመለስ Ctrl ከዚያም 0

📍8. መረጃዎችን በአዲስ ገፅ ለመክፈት (Opening link in a new tab) – ልንከፍተው የፈለግነውን ርዕስ ላይ Ctrl ተጭነን ክሊክ ማድረግ፤ ወርድ ላይ ከሆነም የምንፈልገውን የድረ ገፅ አድራሻ በሙሉ መርጠን Ctrlን ተጭነን በመያዝ በአዲስ ገፅ መክፈት
እንችላለን።

📍9. የተጣራ ፍለጋ ለማድረግ - የምንፈልገውን ጉዳይ በትምህርተ ጥቅስ ውስጥ ማስገባት
ለምሳሌ፦ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ብለን ጎግል ላይ ብንፈልግ ስለ ኢትዮጵያ አልያም ስለ ኢኮኖሚ የተለያዩ ጉዳዮችን በዝርዝር ያመጣልናል። ይሁን እንጂ “የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ” ብለን ብንፈልግ የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ብቻ የተመለከቱ መረጃዎችን ማግኘት እንችላለን።

📍10. የድረ ገፅ አድራሻ መፃፊያ ስፍራን በአጭሩ ለማግኘት - Alt + D ወይም F6

📍11. ጠቃሚ ድረ ገፆችን ለሌላ ጊዜ ለማስቀመጥ ወይም ቡክማርክ ለማድረግ - Ctrl + D + Enter

📍12. ከዚህ ቀደም ያስቀመጥናቸውን የድረ ገጽ አድራሻዎች ለማግኘት - Ctrl + B

📍13. ገፆችን እንደ አዲስ በድጋሚ ለመክፈት (refresh)- Ctrl + Shift + R

📍14. ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማስቆም እና ለማጫወት - K
════❁✿❁ ═══════                                                     
🎯 t.me/EthioWorldwideStudents          
📣ሌላኛወን የ Technology ቻናላችንን ለመቀላቀል👇
t.me/TechnologyMasterPage

facebook.com/Ethio-Worldwide-Students-113133807538863


▭▭ Facebook Group:

facebook.com/groups/916787471774555/

▭▭ YouTube channel:

youtube.com/channel/UCAgflSe6nsrTgZI71rSKOBw


▭▭ Instagram :

instagram.com/ethioworldwide

▭▭ Twitter:

twitter.com/ethio_worldwide

Email:

ethioworldwidestudents@gmail.com

          #ሁሌም_ከኛ_ጋር_ወደ_ፊት 🏃🏃‍♀
══════❁✿❁════════
◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦
✳️ይህን ያውቁ ኖሯል?

◽️ በየወሩ ከ6000 በላይ የኮምፒዩተር ቫይረሶች ተሰርተው ይለቀቃሉ።

◽️ 123456 ፣ 12345 እና Password በአለማችን ሰዎች በብዛት የሚጠቀሟቸው የይለፍ ቃላት ናቸው።

◽️ 340000 የሚሆኑ የTwitter ትዊቶች (tweets) በየደቂቃው ይላካሉ።

◽️ ቴክኖሎጂን መፍራት በህክምና አጠራሩ ቴክኖፎቢያ (Technophobia) በመባል ይታወቃል። ሁኔታው በኢንዱስትሪ አብዮት ጊዜ ሰራተኞች በማሽኖች ተተክተው ከስራቸው እንዳይፈናቀሉ ከነበራቸው ስጋት የመነጨ ነው።

◽️ የፌስቡክ መስራች የሆነው ማርክ ዘከርበርግ ቀለሞችን የመለየት ችግር ወይም በእንግሊዘኛው “Color Blindness” ተጠቂ ነው። ማርክ ቀይና አረንጓዴ ቀለሞችን በቅጡ መለየት ስለማይችል የፌስቡክንም የከለር አጠቃቀም ሰማያዊ እንዲሆን አድርጓል።

◽️ በአለማችን የመጀመሪያው ዌብፔጅ እንስካሁን ድረስ እየሰራ እንደሚገኝ ያውቁ ኖራል? ፔጁ መሰረታዊ የኢንተርኔት አጠቃቀምን ብቻ ለመሞከሪያነት የተሰራ በመሆኑ ምንም አይነት ግራፊክስ የለውም። info.cern.ch ላይ በመግባት ፔጁን መሞከር ይቻላል።

◽️ አሁን ባለንበት በ2020 ከ8 ቢሊዮን በላይ የሚሆኑ መሳሪያዎች በኢንተርኔት አማካኝነት እርስ በእርስ ይገናኛሉ።

◽️ በዚህ ሰዓት ከ3.8 ቢሊዮን በላይ ሰዎች ኢንተርኔት ይጠቀማሉ። ይህም ከአለም አጠቃላይ የህዝብ ብዛት 40% የሚሆነውን ይይዛል።

◽️ “Robot” የሚለው ቃል “robota” ከሚለው የቼክ ቋንቋ የመጣ ሲሆን ትርጉሙም የጉልበት ወይም አስገዳጅ ስራ (Forced labor or work) የሚል ነው። ቃሉ ለመጀመሪያ ጊዜ በጥቅም ላይ የዋለው እ.ኤ.አ በ1920 ለልብወለዳዊ ተውኔት ነው።

📢: t.me/TechnologyMasterPage

#Technology_News

#የቴክኖሎጂ_ዜና
✳️ቫይረሶች ወደ ኮምፒውተሮች እንዴት ነው የሚገቡት?

✴️በዚህ የቴክኖሎጅ ዘመን ኮምፒውተራችን አልያም ስማርት ስልኮቻችን ሁነኛ የመረጃ ማግኛ እና መዝናኛ ከሆኑ ሰነባብተዋል።

✴️ይሁን እንጂ የሰዎችን መረጃ አላስፈላጊ በሆነ መልኩ ለመጠቀም ብሎም መረጃ እና ንብረትን ወደ ግል ለማዞር የሚሞክሩ ሰዎች ስጋት ከሆኑም ቆይተዋል።

✴️ቫይረሶች በማወቅም ይሁን ባለማወቅ ወደ ኮምፒውተራችን ሲገቡ ሙሉ በሙሉ አልያም በከፊል ከጥቅም ውጭ ሊያደርገው ይችላል፤
የተለያዩ ጠቃሚ መረጃዎቻችንም ለሌሎች አሳልፈው የመስጠት እድልም አላቸው።

✴️እናም በተቻለ መጠን ቫይረሶች ወደ ኮምፒውተራችን ገብተው ጉዳት እንዳያደርሱብን ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል።

🔰ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ነጥቦችም የኮምፒውተር ቫይረሶች ወደ ኮምፒውተሮች የሚገቡበትን መንገድ ያስገነዝባሉ።

✴️የማንቂያ መልዕክቶችን (ኖቲፊኬሽን) ሳናነብ መቀበል
ቫይረስ ወደ ኮምፒውተራችን ከሚገባባቸው መንገዶች ዋነኛው የማንቂያ መልዕክቶችን ሳንረዳ መክፈት ነው።
♻️ለምሳሌ፦♻️
✴️1. በኢንተርኔት መረጃዎችን ስናፈላልግ a unique plugin is necessary is required የሚል ማስታወቂያ ሲመጣ ምንም አይነት የደህንነት ስጋት ይኑረው አይኑረው ሳናውቅ እንዲከፍትልት የሚያዘንን ቅደም ተከተል መከተል፤

✴️2. በነፃ የሚለቀቁ ፕሮግራሞችን ከጫንን በኋላ በተደጋጋሚ እንድንጭናቸው የምንጠየቀውንና እያንዳንዱን የኢንተርኔት እንቅስቃሴያችንን ለመረጃ በርባሪዎች አሳልፈው የሚሰጡ ፕሮግራሞችን ማውረድ
የተበከለ ሶፍትዌር መጫን
ከኢንተርኔት
የምናወርዳቸው ነገሮች ከታማኝ ምንጮች የተገኙ መሆናቸውን ማረጋገጥ ይኖርብናል።

✴️ካወረድን በኋላ ወደ ኮምፒውተራቸን ስንጭን (install ስናደርግም አንቲቫይረስ ሶስትዌር ሊኖረን ይገባል።

✴️ላኪያቸው የማይታወቁ የኢሜል መልዕክቶችን መክፈት
ማንኛውንም ላኪያቸውን የማናውቃቸውን የኢሜል መልዕክቶች ከመክፈታችን በፊት በኦንላይን አንቲቫይረስ ሶፍትዌሮች ስካን ማድረግ ይኖርብናል።

✴️በኢሜል መልዕክቶች አማካኝነት የተለያዩ ቫይረሶች ስለሚላኩ ጥንቃቄ ማድረግ ተገቢ ነው።

✴️የተበከሉ ውጫዊ ስቶሬጅ መሳሪያዎች (ሚሞሪ፣ ፍላሽ ዲስክ፣ ሀርድ ዲስክ ወዘተ ኮምፒውተራችን ላይ መሰካትም ሌላኛው ቫይረስ ወደ ኮምፒውተራችን የሚገባበት መንገድ ነው።

✴️የኮምፒውተር ሶፍትዌሮችን በየጊዜው አለማሳደግ አፕዴት አለማድረግ ችግር ላይ እንደሚጥል ይታመናል።

📢: t.me/TechnologyMasterPage


#ከቴክኖሎጂ_ማህደር
💢ኮምፒውተር💻 ማለት በሰውም ይሁን በፕሮግራም በታዘዘው የተለያዩ #ትእዛዞች መሰረት ስራ የሚያከናውን #ማሽን ነው፡፡ ይህ ስራ ለምሳሌ #ሰነድ ለመጻፍ፣ #ሂሳብ ለማሰል፣ #ኢንተርኔት ለመጠቀም፣ #ለመጫወት#ፎቶና ቪዲዮ ለማዘጋጀት ወዘተ ሊሆን ይችላል፡፡ ይህንን የስራ ክንውን ለመፈጸም #ኮምፕዩተር #በሶስት ዋና ዋና ክፍሎች ይከፈላል፡፡ ከታች የቀረቡት ሶስቱ መሰረታዊ ክፍሎች ኮምፕዩተሩ እንደ #ኮምፕዩተር እንዲሆንና #ትእዛዞቹም እንዲፈጸሙ ያስችሉታል፡፡ በአይነትም ሆነ በትልቅነት የተለያዩ ኮምፕዩተሮች አሉ፡፡ ለምሳሌ የጭን፣ የቤት፣ የመስሪያ ቤት ኮምፕዩተሮች አሉ፡፡ ከአካል #መጠናቸው፣ ከፍጥነታቸውና ከአቅማቸው ልዩነት በስተቀር መሰረታዊ #አሰራራቸው ይመሳሰላል፡፡

1⃣. አንደኛው 

#የውስጥ አካላዊ ክፍሎቹ ለምሳሌ Harddrive HD ፣ #RAM#Motherboard#Sound card ፣ #Video card፣ #CPU ይገኙበታል፡፡ እና #የውጭ አካላዊ ክፍሎቹ ደግሞ #Display#Keyboard#CD/DVD-rom ፣ #Printer#Mouse ፣ ይገኙበታል፡፡ የሁሉም የውስጥና የውጭ አካል የጋራ ስም ደግሞ #ሃርድዌር ይባላል፡፡ ይህ ሃርድዌር #በአካል የሚታይና የሚነካ ነው፡፡

2⃣. ሁለተኛው

#አካላዊ ያልሆኑ ፕሮግራም ተብለው የሚጠሩ ናቸው፡፡ እነዚህም ለምሳሌ #ሰነድ መጻፊያዎች፣ #ሂሳብ ማስሊያወች፣ #ኢንተርኔት መጠቀሚያዎ ፣ #ስእል መሳሊያወች፣ #ፎቶና ቪዲዮ ማቀናበሪያወች ወዘተ የሚያገለግሉ ፕሮግራሞች ናቸው፡፡ እንደተጠቃሚው ፍላጎትና ስራ #በመቶና በሺህ የሚቆጠሩ ፕሮግራሞች አሉ፡፡ የሁሉም ፕሮግራሞች አጭር የጋራ ስም #software ሊባል ይችላል፡፡ ሶፍትዌር ልክ እንደ #ሃርድዌር የሚነካና #የሚጨበጥ አይደለም፡፡ 


3⃣.ሶስተኛው

# Operating System ዋና ዋና ሚና ካላቸው አንዱ ክፍል ነው፡፡ ባጭሩ ዋናው የ #Operating System ስራ ግን #;የኮምፕዩተር የውስጥና #የውጭ አካል እና #ሶፍትዌሮች በአንድ ላይ ተጣጥመው ወይም #እጅና ጓንት ሆነው እንዲሰሩ የሚያስችል ነው፡፡ ለምሳሌ #Windows#Mac#Linux የመሳሰሉት #Operating System #አይነቶች ናቸው፡፡

#ኮምፕዩተሩ እንዲሰራ ሶስቱም ክፍሉች ማለትም #አካላዊ ክፍሎቹ፣ #ፕሮግራሞቹና Operating System በአንድ ላይ ተቀናጅተውና #ተስማምተው መስራት አለባቸው፡፡ 

#Reshad_Muzemil

t.me/TechnologyMasterPage
ኮምፒውተራችሁን በምትከፍቱት እና በምትጠቀሙበት ሰአት እየተንቀራፈፈ አማሯችዋል? እንግዲያውስ ፍጥነቱን ሊጨምሩ የሚችሉ ነገሮችን እናያለን።

1. Power option
Start menu ላይ power option ብላችሁ ፈልጉ ከሚመጣላችሁ window ውስጥ high performance የሚለውን ምረጡ

2.Disable unwanted start up programs

ይሄ ኮምፒዩተራችንን በምንከፍትበት ጊዜ ያለ እኛ ፍቃድ ፕሮግራሞችን እየከፈተ ፍጥነቱን ከሚቀንሱ ነገሮች አንዱ ነው። ይሄን ለመከላከል

Task manager ላይ መግባት (ይሄን ለማግኘት start menu ላይ right click አድርጎ ማግኘት ይቻላል አልያም Ctrl Alt እና delete የሚለውን አንድ ላይ መጫን) ከሚመጣው window ውስጥ start up ላይ በማድረግ የማትፈልጉትን ፕሮግራሞች disable ማድረግ።

እዚህ ጋር impact የሚለው high ከሆነ disable ባታረጉት ይመረጣል።

3.Defragment and optimize drive Start menu search bar ላይ defragment ብሎ መፈለግ
Window ሲመጣላችሁ የምትፈልጉትን driver መርጣችሁ optimize ማድረግ

4. Delete unnecessary temporary file Start menu ላይ right click አድርጎ run የሚለውን መምረጥ አልያም window key እና R ን ከ ኪቦርዳችን ላይ አንድ ላይ መጫን
%temp% ብሎ ጽፎ enter መጫን የሚመጣላችሁ folder ላይ ያሉ ፋይሎችንctrl + A ተጭነን ሁሉንም ሲመርጥልን ማጥፋት
ድጋሚ run ቦክሱን ከፍታቹ temp ብሎ መጻፍ ከሚመጣላችሁ folder ውስጥ ያሉ ፋይሎችን ሁሉ ማጥፋት አሁንም ለ ሶስተኛ ጊዜ run ቦክስ ላይ prefetch ብሎ መጻፍ የሚመጣላችሁ folder ውስጥ የሚገኙ ፋይሎችን ማጥፋት።

እነዚህን የምናጠፋበት ምክንያት ጊዜያዊ እና space የያዙ ፋይሎች ስለሆኑ ነው። ምንም አይነት ችግር አያመጡም።

5. Clean up Memory
This pc ውስጥ ገብታችሁ የምፈልጉት local ዲስክ ላይ right click በማድረግ property መምረጥ Disk clean up የምትለውን icon click ማድረግ
የሚመጣውን የ warning box ok ማድረግ እዚህ ጋ recycle bin ውስጥ ያሉ ፋይሎች ሳይቀሩ ነው የሚጠፉት

6. Reduce run time service
Run box ከፍታችሁ msconfig ብሎ መጻፍ ቀጥሎ ከሚመጣው window service የሚለውን መጫን በመቀጠል hide all microsoft service የሚለውን tick ማድረግ በመቀጠል disable የምትለዋን icon click ማድረግ

7. Registry tweaks
Run box መክፈት(window key + R) regedit ብሎ መጻፍ
Hkey -current user Control panel Mouse Mouse hover time valueን ወደ 10 መቀየር
እዛው folder ላይ desktop መምረጥ Menu show delay
Valueን ወደ 10 መቀየር

8. visual effects
Start menu ላይ System ብሎ መፈለግ Advanced system setting መምረጥ
Advance ውስጥ በመግባት setting መምረጥ Adjust for best performance መምረጥ
ቀጥሎ የምትፈልጉት ነገር ካለ ቲክ በማድረግ መምረጥ በመጨረሻም ከላይ ያሉትን ከጨረስን በኋላ ኮምፒዩተራችንን Restart ማድረግ

ሌሎችንም ወደቻናላችን ይጋብዙ JOIN⬇️

📢:
t.me/TechnologyMasterPage
ኦርጅናሉን ስልክ ከፌኩ በቀላሉ እንዴት መለየት ይቻላል። እነዚን መንገዶች በመጠቀም ፌክ ሳምሰንግ ስልኮችን መለየት ይችላሉ።

📂የስልኩን ቀፎ አካላዊ ገጽታዎች በመገምገም
ፌክ ሳምሰንግ ስልክ

1. የስክሪኑ መስታወት ጥራት የለዉም
2. ስክሪኑ ከቀፎዉ ጠርዝ በጣም ይርቃል
3. ስክሪኑ ድምቀት ይጎድለዋል
4. የሳምሰንግ ሎጎ (ሳምሰንግ የሚለዉ ጽሁፍ) ሲነካ
ይሻክራል፣ በደንብ ከተጫኑት ይለቃል
5. ከኦርጂናል ስልኮች ጋር ሲያስተያዩት፤ የባትሪ መክደኛዉን ሲከፍቱ የሚታዩ ትንንሽ አካሎች እና ባትሪዉ ላይ የሚገኙት መረጃዎች የተለያዩ መሆናቸዉን
ይመለከታሉ፡፡

📂የስልኩን ፍጥነት እና ትእዛዞችን አፈጻፀም በመገምገም

1. በስልኩ ፎቶዎችን ለማንሳት ይሞክሩ፣ በፌክ ሳምሰንግ
ስልኮች የሚያነሱት ፎቶ ጥራት የወረደ ይሆናል
2. በተመሳሳይ ጊዜ በርካታ ጌሞች እና አፕሊኬሽኖችን
ለመክፈት ይሞክሩ፣ ፌክ ስልኮች ስታክ(ቀጥ) የማለት ባህሪይ ያሳያሉ፡፡
3. ስልኩን አጥፍተዉ ያብሩት፣ ፌክ ስልኮች ቶሎ አይከፍቱም

📂የስልኩን የምርት መረጃዎች በመገምገም

1. ከአፕሊኬሽን ማዉጫዉ ላይ፣ Settings የሚለዉን ይጫኑ
3. ከ Settings ላይ More የሚለዉን ይጫኑ እና storage የሚለዉን በመጫን ስልኩ ላይ መጫን ሚችሉትን የዳታ መጠን ይመልከቱ፤ ከኦርጂናሎቹ ስልኮች በጣም ያነሰ ከሆነ ፌክ መሆኑን ያረጋግጣሉ፡፡

እንዲሁም About device የሚለዉን ይጫኑ እና
የስልኩን ሞዴል ቁጥር እና baseband, build number
ጉግል ላይ ይፈልጉት፣ የሚያገኙት መልስ ፌክ ወይም ኦርጅናል መሆኑን ይነግሮታል፡፡

የሳምሰንግ ኮዶችን በመጠቀም ወደ ስልክ መደወያዉ በመሄድ፣ ከዚህ በታች የተጠቀሱትን ኮዶች ያስገቡ እና Call የሚለዉን ይጫኑ፤ ስልኩ
ያስገቡትን ኮድ አዉቆ መልስ መስጠት ከቻለ ኦርጅናል
መሆኑን ያረጋግጣሉ፡፡ ካልሆነ ግን ፌክ ስልክ ነዉ፡፡

🗂 *#0*# አጠቃላይ መገምገሚያ
🗂 *#1234# or *#9999# ስልኩ የሚጠቀመዉን
ሶፍትዌር እና ሞደም ማወቂያ
🗂 *#12580*369# ስለ ስልኩ ሶፍትዌር እና ሀርድዌር ማወቂያ
🗂 *#06# የስልኩን ኢንተርናሽናል መለያ ቁጥር ማወቂያ
🗂 *#9998*246# የስልኩን የባትሪ እና ሚሞሪ መረጃዎች ማወቂያ
ሳምሰንግ ኪይ(Samsung Kies) ሶፍትዌርን በመጠቀም ከላይ በተጠቀሱት መንገዶች ፌክ ሳምሰንግ ስልክን መለየት ካልቻሉ ይህን ሶፍትዌር ይጠቀሙት፡፡

1. Samsung Kies ሶፍትዌርን ኮምፒዉተሮት ላይ
ይጫኑት
2. ለማረጋገጥ የፈለጉትን ስልክ ከኮምፒዉተሮት ጋር ያገኛኙት
3. ሶፍትዌሩ ስልኩን ያነበዉ እና የስልኩን ስም ፣ የሚጠቀመዉን ሶፍትዌር እና ሀርድዌር ያሳያል፤
ሶፍትዌሩ ስልኩን ማንበብ ካልቻለ በድጋሚ ይሞክሩት በድጋሚ ማንበብ ካልቻለ ሰልኩ ፌክ መሆኑን ያረጋግጣሉ፡፡

▒▓⇨→መረጃዎች ቶሎ ቶሎ እንዲደርሶት ስልኮቻችሁ ላይ ላሉ
❖ Contact
❖ Group and Channel share አድርጉለን ከምስጋና ጋር።

📝 ለተሻለ ለውጥ እንተጋለን!!
━━━━━━━━━━━━━━━
📢:
t.me/TechnologyMasterPage
━━━━━━━━━━━━━━━
▬▬▬▬▬📌Share📌▬▬▬▬
🤔ይህንን ያውቃሉ

👉ከ 3.8 ቢሊዮን በላይ ሰዎች ዛሬ በይነመረብ ይጠቀማሉ ፣ ይህም ከዓለም ህዝብ 40% ነው፡፡

👉8 ቢሊዮን መሳሪያዎች በ 2020 ከበይነመረቡ ጋር ይገናኛሉ ፡፡

👉በየደቂቃው ከ 570 በላይ አዳዲስ ድርጣቢያዎች ይፈጠራሉ ፡፡

👉Google ላይ በየቀኑ ከ 3.5 ቢሊዮን በላይ ፍለጋዎች አሉ።

👉በየደቂቃው የ 24 ሰዓታት ቪዲዮ ወደ YouTube ይሰቀላል። በ 60 ዓመታት ውስጥ ከተፈጠሩ ሶስት ዋና የአሜሪካ የቴሌቪዥን አውታረ መረቦች በበለጠ የበለጠ የቪዲዮ ይዘት በ 60 ቀናት ውስጥ ወደ YouTube ይሰቀላል ፡፡

👉በ 2020 ቪዲዮ ከሁሉም የበይነመረብ ትራፊክ 80% ገደማ የሚሆነው ተጠያቂ ይሆናል።

👉በደቂቃ 340,000 ትዊቶች ይላካሉ ፡፡

👉በቀን 500 ሚሊዮን ትዊቶች ይላካሉ ፡፡

👉ፌስቡክ በአማካይ 155 ጓደኞች ያሏቸው ከ 2 ቢሊዮን በላይ ንቁ ተጠቃሚዎች አሉት ፡፡

👉በየቀኑ ከ 300 ሚሊዮን በላይ ፎቶዎች በፌስቡክ ይሰቀላሉ ፣ በየቀኑ 800 ሚሊዮን መውደዶች እና በቀን 175 ሚሊዮን ፍቅራዊ ግብረመልሶች።

𝐒𝐇𝐀𝐑𝐄 || ሼር 👇


t.me/TechnologyMasterPage

#Technology_Facts

#የቴክኖሎጂ_እውነታዎች
☑️All Mobiles Secret👁‍🗨 Codes AdFree
All Mobiles Secret Codes AdFree v1.3 @ApkManagerBot.apk
2.2 MB
#ምናልባት የአንደሉስ ተማሪዎች ካላችሁ ዛሬ የነገርኳችሁ አፕ ይቺህ ናት!

#በጣም ብዙ የሆኑ Codes(ኮዶችን) ይዛለች!

●የያንዳንዱ ኮድ ስልካችንን ኦርጂናል ነው ወይስ ፎርጂት የሚለውን ነገር እንድናውቅ ይረዳናል!!

#ረሻድ_ሙዘሚል
​​💥 እንዴት አድርገን የተበላሸ ሚሞሪ ካርድን እንደገና ጥቅም ላይ ማዋል እንችላለን⁉️

💥 እነዚህን 12 ስቴፓች ይጠቀሙግን ሚሞሪ ካርዱ ውስጥ የነበሩት ፋይሎች መጥፋታቸው የማይቀር ነገር ነው።
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈

◉step 1➹
ሚሞሪ ካርዱን የኮምፒውተርዎ “USB port” ላይ ይሰኩት።
♡┈┈┈••✦

◉step 2➹
ከዚያም “my computer” ውስጥ ገብተው ኮምፒውተሩ ሚሞሪ
ካርዱን እንዳነበበው ቼክ ያድርጉ።
♡┈┈┈••✦

◉step 3 ➹
ከዚያም “Start” በተኑን በመጫን “cmd” ብለው በመፃፍ
“Enter”ን ይጫኑ።
♡┈┈┈••✦

◉step 4 ➹
ከዚያም “Command prompt” ውስጥ ብለው “DISKPART”
ይፃፋና “Ok”ን ይጫኑ።
♡┈┈┈••✦

◉step 5 ➹
ከዚያም “list disk there” ብለው ይፃፋና የሚቀርቡ
አማራጮችን ይዩ።
♡┈┈┈••✦

◉step 6➹
ከሚመጡት አማራጮች ውስጥ ሚሞሪ ካርዱን ከነ ቁጥሩ
ያገኛሉ።
♡┈┈┈••✦

◉step 7➹
ከዚያም “select disk (disknumber)” ብለው ይፃፋና
“Enter”ን ይጫኑ።
♡┈┈┈••✦


◉step 8 ➹
ከዚያም “clear” ብለው ይፃፋና Enterን ይጫኑ።
♡┈┈┈••✦


◉step 9➹
ከዚያም “create partition primary” ብለው ይፃፋና
“Enter”ን ይጫኑ።
♡┈┈┈••✦


◉step 10➹
ከዚያም “active” ብለው ይፃፋና “Enter” ይጫኑ።
♡┈┈┈••✦


◉step 11➹
ከዚያም “format fs=fat32” ብለው ይፃፋና “Enter” ይጫኑ።
♡┈┈┈••✦

◉step 12➹
ከዚያም ኮምፒውተሩ ሚሞሪ ካርዱን ፎርማት ያደርገዋል።
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈

        🗣➹share &Join Us
                     👇🏾👇🏾👇🏾
t.me/TechnologyMasterPage
      ┗━ ••• ━ ••• ━━•••━━━┛

#Reshad_Muzemil
የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ።

በ2013 ዓ/ም የትምህርት ዘመን ሊሰጥ የነበረው የ12ኛ ክፍል ፈተና በተለያዩ ሀገራዊ ምክንያቶች ወደ 2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ተሸጋግሮ በሁለት ዙር መሰጠቱ ይታወቃል።

የመጀመሪያው ዙር የሲቪክስ ፈተና በሁሉም ትምህርት ቤቶች በሚባል ደረጃ የውጤት መመሳሰልና ግሽበት ታይቶበታል። ስለሆነም የሲቪክስ የፈተና ውጤት ለዩኒቨርስቲ መግቢያ መወዳደሪያነት #እንዳያገለግል ተወስኗል።

በሌሎቹ የትምህርት ዓይነቶች የተገኘው የውጤት ትንተና ሲታይ ምንም ዓይነት ችግር የሌለበት በመሆኑ እንዲመዘገብ ተደርጓል።

ለከፍተኛ ትምህርት ገብተው ለመማር ብቁ የሚሆኑ ሁሉም ተማሪዎች ለመግቢያነት የሚያገለግሉ የትምህርት ዓይነቶችን አጠቃላይ አማካይ ነጥብ 50% እና በላይ ያመጡ ተማሪዎች ይሆናሉ።

ለምሳሌ በሰባት የትምህርት ዓይነት ተፈትነው ከ600 ለሚያዝላቸው ተማሪዎች አማካይ ውጤት 300 እና በላይ ማምጣት ይጠበቅባቸዋል።

ይህ በዲህ እንዳለ በመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ገብተው ለሚማሩ ተማሪዎች የዩኒቨርስቲዎችን የመቀበል አቅም በማገናዘብ ዝርዝር የመግቢያ ነጥብ ወደፊት ይገለፃል።

ተማሪዎች የሚከተሉትን አማራጮች በመጠቀም ውጤታቸውን ማወቅ ይችላሉ።

1) በትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዌብሳይት፡- result.neaea.gov.et

2) በትምህርት ሚኒስቴር ዌብሳይት፡- result.ethernet.edu.et

3) በቴሌግራም ቦት (Telegram Bot):- @moestudentbot

4) በ9444 SMS ፡- በመልክት ማስተላለፊያ መጻፊያ ላይ የመለያ ቁጥራቸውን በማስገባት ወደ 9444 በመላክ ውጤታቸውን ማየት ይችላሉ።

(የአገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ)

#Pass_it_on:- tikvahethiopia