Basic Computer Skills
1.87K subscribers
1.22K photos
100 videos
576 files
833 links
#በዚህ የቴሌግራም ቻናል
↪️ Programming
↪️ ቴክኖሎጂ ነክ ትምህርቶችን
↪️ ኮምፒውተር ነክ ትምህርቶችን
↪️Basic Computer Skills
↪️ Software
↪️ AI and AI Skills (Like ChatGPT)

ከላይ የተዘረዘሩትና ሌሎችም ገራሚ ትምህርቶች ይለቀቅበታል!

t.me/BasicComputerSkillsGroup

𝘽𝙮 𝙍𝙚𝙨𝙝𝙖𝙙
Download Telegram
እኛም እኮ ሞተናል

የሰው ቁስል ስናክም - የኛው አመርቅዞ፤
ሞታችን *አረዱን* - በወረቀት ይዞ፤
መቋቋም ሲያቅተን - የህይወትን ጠለል፤
የማይድን ስናክም - የማይሞት ገድለናል፤
ሞታችንም አውቀን - ቀናችን ቆጥረናል፤
ይሀው ሟቹ በዛ - እኛም እኮ ሞተናል፤
ይሀው ሟቹ በዛ - እኛም እኮ ሞተናል።

✍️ በረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል


══════════════
አንዳንዴ ግጥም ብጤ ነገር ላጋራችሁ ብየ ነው❗️
👍3
የኮምፒውተር ሀርድ ዲስክን እንዴት መክፈል እንችላለን?
ዛሬ የምናየው እንዴት አድርገን አንድ ሎካል ዲስክን ወደ ሁለት ከዚያ በላይ ክፍልፋዮች እንደምንቀይር ነው።
ለምሳሌ Local disk C: ካለን ከሁለት ለመክፈል ለምሳሌ
#1_right click on My computer
#2_ከዛ Manage የሚለውን እንነካለን
#3_ከዛ ከሚመጡት ምርጫዎች ውስጥ disk management የሚለውን እንመርጣለን
#4_ከዛ ለመክፈል የምንፈልገውን ዲስክ C:
በመምረጥ right click እናደርጋለን
#5_ከዛ shrink volume የሚለውን እንመርጣለን ትንሽ ሰከንድ ይቆያል
#6-ከዛ የምንፈልገውን መጠን በመፃፍ shrink የሚለውን click አድርጎ መጠበቅ
ማስጠንቀቂያ:- ቁጥሩ በሜጋ ባይት ነው የሚገባው ለምሳሌ 50GB መክፈክ ብትፈልጉ 1GB ማለት 1024 MB ነው ይህ ማለት 50*1024=51,200 ይሆናል ስለዚህ 51,200 ብለን ማስገባት ይጠበቅብናል።
#7_ከዛ በጥቁር ቀለም ከታች (unlocated) የሚለው ላይ right click ማድረግ
#8_click on "new simple volume
ከዛ next next next እያሉ እስከመጨረሻው መቀጠል::
ይሄን ስናደርግ ምንም አይነት መረጃ አይጠፋብንም።
እስኪ ለምሳሌ 152 GB ለመክፈል ብንፈልግ ስንት ብለን መጻፍ ይጠበቅብናል? ኮሜንት ላይ ይጻፉልኝ!


🌐 ዘመኑ #የቴክኖሎጂ ነው 📲 ከዘመኑ ጋር አብረው ይዘምኑ💻

Telegram: t.me/BasicComputer_Skills

tiktok.com/@basiccomputerskills

instagram.com/basiccomputerskills

Umma Life: ummalife.com/ReshadMuzemil
╚═══📌Share📌════
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የ12ኛ ክፍል ኦንላይን (የይነመረብ 🌐) ፈተና መለማመጃ

Part 1


◆ ለ12ኛ ክፍል ተማሪዎች

══════════════
🀄🀄ሉን👇👇👇 share👇

t.me/AndalusGrade7and8

t.me/AcademicEducations

t.me/BasicComputer_Skills

t.me/AndalusGrade5and6
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የ12ኛ ክፍል ኦንላይን (የይነመረብ 🌐) ፈተና መለማመጃ

Part 2


◆ ለ12ኛ ክፍል ተማሪዎች

══════════════
🀄🀄ሉን👇👇👇 share👇

t.me/AndalusGrade7and8

t.me/AcademicEducations

t.me/BasicComputer_Skills

t.me/AndalusGrade5and6
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የ12ኛ ክፍል ኦንላይን (የይነመረብ 🌐) ፈተና መለማመጃ

Part 3


◆ ለ12ኛ ክፍል ተማሪዎች

══════════════
🀄🀄ሉን👇👇👇 share👇

t.me/AndalusGrade7and8

t.me/AcademicEducations

t.me/BasicComputer_Skills

t.me/AndalusGrade5and6
ምርጥ 9 ድረገፆች

📲 Unscreen.com የአንድን video back ground ለማጥፋት እና video quality ለመጨመር።

📲 math.he.net ማንኛውንም የmaths ጥያቄ መስራት የምትችሉቀት website ነው ጅ።

📲 ALLPCWORLD.COM በጣም ብዙ እና አዳዲስ software ታገኙበታላችሁ።

📲 IFIXIT.COM ማንኛውንም ነገር ሲበላሽባችሁ የትም ሳትሄዱ እራሱ GUIDE እያረገ እንድትሰሩት ያስችላችኋል ለምሳሌ ስልክ፣ ላፕቶፕ፣ TV፣ REDIO፣ ሳይክል የመሳሰሉትን።

📲 Accountingcouch.com Accounting የምትማሩ ከሆነ በጣም ይጠቅማችኋል።

📲 bit.ly/learn-eh2 በነፃ ethical hacking (hacking) የምትማሩበት web site ነው ሰርተፍኬትም አለው።

📲 durable.ai በ 5 ደቂቃ ብቻ ገራሚ AI WEB SITE የምትሰሩበት WEB SITE ነው ከናንተ የሚጠበቀው ስለምትፈልጉት website መፃፍ ነው እራሱ ይጨርስላችኋል።

📲 Podcast.adobe.com video record ያደረጋችሁትን Video አላስፈላጊ ድምፅ ያጠፋላችኋል እንዲሁም የvoice quality ይጨምርላችኋል።

📲 https://www.logoai.com/ የተለያዩ logo በነፃ ይሰራላችኋል ከናንተ የሚጠበቀው ስም ማስገባት ብቻ ነው።

🌐 ዘመኑ #የቴክኖሎጂ ነው 📲 ከዘመኑ ጋር አብረው ይዘምኑ💻

Telegram: t.me/BasicComputer_Skills

tiktok.com/@basiccomputerskills

instagram.com/basiccomputerskills

Umma Life: ummalife.com/ReshadMuzemil
╚═══📌Share📌════
1💯1
ጠቃሚና ኢንተርኔት ላይ በነፃ የምታገኟቸው አሪፍ የኮምፒውተር ሶፍትዌሮች

Audacity: Audio recording and editing software
https://www.audacityteam.org/download/windows/
Blender: Best animation maker software
https://www.blender.org/download/
BleachBit:  free and open-source disk space cleaner, privacy manager, and computer system optimizer.
https://www.bleachbit.org/download
Brave browser: Best secure browser other security features are also included.
https://brave.com/download/
CPU-Z: freeware system profiling and monitoring application that detects the CPU, RAM, motherboard chip-set.
https://www.cpuid.com/softwares/cpu-z.html
picasa: Googles free photo viewer software
https://filehippo.com/download_picasa/
FotoSketcher: photo editing software
https://fotosketcher.com/download-fotosketcher/
Davinchi Resolve: Free video editing software
https://www.blackmagicdesign.com/products/davinciresolve/studio
Everything: searching any files and folders on windows
https://www.voidtools.com/downloads/
OBS Studio (Open Broadcaster Software)
Free and open-source software for video recording and live streaming.
https://obsproject.com/download
HandBrake
A tool for converting video from nearly any format to a selection of modern, widely supported codecs.
https://handbrake.fr/downloads.php
KeePass
A free, open-source password manager that helps you to manage your passwords in a secure way.
https://keepass.info/download.html
Glary Utility: system optimization software to improve PC performance and fix crashes, errors, and other issues.
https://www.glarysoft.com/glary-utilities/download/
Notepad++
A free source code editor and Notepad replacement that supports several languages.
https://notepad-plus-plus.org/downloads/

🌐 ዘመኑ #የቴክኖሎጂ ነው 📲 ከዘመኑ ጋር አብረው ይዘምኑ💻

Telegram: t.me/BasicComputer_Skills

tiktok.com/@basiccomputerskills

instagram.com/basiccomputerskills

Umma Life: ummalife.com/ReshadMuzemil
╚═══📌Share📌════
👍2
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
Grade 7 ICT

Unit 6: Logic Oriented Graphics Oriented Programming



🌐 ዘመኑ #የቴክኖሎጂ ነው 📲 ከዘመኑ ጋር አብረው ይዘምኑ💻

Telegram: t.me/BasicComputer_Skills

tiktok.com/@basiccomputerskills

instagram.com/basiccomputerskills

Umma Life: ummalife.com/ReshadMuzemil
╚═══📌Share📌════
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
Grade 8 ICT

Unit 6: Logic Oriented Graphics Oriented Programming



🌐 ዘመኑ #የቴክኖሎጂ ነው 📲 ከዘመኑ ጋር አብረው ይዘምኑ💻

Telegram: t.me/BasicComputer_Skills

tiktok.com/@basiccomputerskills

instagram.com/basiccomputerskills

Umma Life: ummalife.com/ReshadMuzemil
╚═══📌Share📌════
👍2
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
Grade 7 ICT

Unit 5: Security and Safety of Computer

Language: Amharic


🌐 ዘመኑ
#የቴክኖሎጂ ነው 📲 ከዘመኑ ጋር አብረው ይዘምኑ💻

Telegram:
t.me/BasicComputer_Skills

tiktok.com/@basiccomputerskills

instagram.com/basiccomputerskills

Umma Life:
ummalife.com/ReshadMuzemil
╚═══📌Share📌════
የበይነ_መረብ_ፈተና_አሰጣጥ_ቴክኒካል_ስልጠና.pptx
4.2 MB
📚የ12ኛ ክፍል ኦን ላይን ፈተናን ተማሪዎች እንዴት አድርገዉ መፈተን እንዳለባቸዉ የሚረዳ የቴክኒካል ስልጠና ማንዋል!

💻Online ለምትፈተኑ ተማሪዎች

━━━━━━━━━━━


🌐 ዘመኑ #የቴክኖሎጂ ነው 📲 ከዘመኑ ጋር አብረው ይዘምኑ💻

Telegram:
t.me/BasicComputer_Skills

tiktok.com/@basiccomputerskills

instagram.com/basiccomputerskills

Umma Life:
ummalife.com/ReshadMuzemil
╚═══📌Share📌════
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
Grade 7 ICT

Unit 5: Internet 📶 🌐

Language: Amharic


🌐 ዘመኑ
#የቴክኖሎጂ ነው 📲 ከዘመኑ ጋር አብረው ይዘምኑ💻

Telegram:
t.me/BasicComputer_Skills

tiktok.com/@basiccomputerskills

instagram.com/basiccomputerskills

Umma Life:
ummalife.com/ReshadMuzemil
╚═══📌Share📌════
👍1
ከቴክኖሎጂ ወጣ ብዬ አንድ ፅሁፍ ላጋራችሁ ነው። አንብቧት❗️
Basic Computer Skills
ከቴክኖሎጂ ወጣ ብዬ አንድ ፅሁፍ ላጋራችሁ ነው። አንብቧት❗️
‌በትናንሽ ስህተቶች ብቻ ለም እንበሻሸቃለን⁉️

እስቲ ትላንት አብረን ያሳለፍነውን ጊዜ እናስበው!
እስቲ ትላንት በጥሩ ሁኔታ ተጎራብተን የኖርነባቸውን አመታቶች ቆም ብለን እናስባቸው።

ለምን በትንሽ ስህተቱ ወንድማችንን እንራቀው!?
ለምን በትንሽ ስህተቷ እህታችንን እንራቃት!?

የራቅናቸውን ሰዎች እንደ ነጭ ወረቀት ብናስባቸው፤ ይህ ነጭ ወረቀት መሬት ወደቀ እንበል። ወረቀቱ ይዞ የተነሳው አቧራ ትንሽ ነው (የቆሸሸው የወረቀቱ ክፍል ኢምንት ነው)።
ያ! የቀረው ወይም አቧራ ያልነካው ቦታ ሁሉ እኛ የጠላነው ሰው ጥሩ ጎኑ ነው። የሱ ስህተት ደግሞ ያቺ ትንሿ አቧራ የነካት ቦታ ብቻ ናት።
ታዲያ ለዚህች ኢምንት ነገር ብለን ያሳለፍናቸውን በጎ ነገራቶችን በሙሉ ለምን እንርሳቸው⁉️

ለምንስ በዚህች ትንሽ ስህተቱ ብቻ እንበሻሸቅ?
ለምንስ እዚህ ግባ በማይባል ስህተት እንገፋፋለን፣ እንባላለን፣ እንጎሻሸማለን⁉️

ያን ትንሽ አቧራ ከማየት አቧራ ያልነካውን ትልቁን ቦታ ብናይስ? ግዴላችሁም በቃ ለሰው ልጅ ፍቅር እንስጥ፤ በማይረባ ነገር አንበሻሸቅ።

ለሰው ልጅ ፍቅርህንና አክብሮትህን የምትሰጠው ደግሞ ከገንዘብህ ወይም ከዕድሜህ ሳይሆን ከንፁህ ልብህ ነው!!

ግን ብዙዎቻችን ፍቅርን ከገነዘባችንና ከዕድሜያችን ቀንሰን የምንሰጥ ይመስለንና ለሰው ልጅ.......
ፍቅርን፣ አክብሮትን፣ ታማኝነትን፣ ሐቀኝነትን፣ ይቅር ባይነትን፣ መርዳትንና መደገፍን፣ መቻቻልን፣ ምክርንና ተግሳፅን እንሰስታለን፤ አረ አንደውም ይባስ ብለን እንደ አውሬ ለብቻችን መኖርን እንመርጣለን።

⇒ የተገላቢጦሽ ሆኖ ጭካኔ እና እራስ ወዳድነት የጥንካሬ ምልክቶች፤ የዋህነትና ይቅርባይነት የሞኝነት ባህሪ ይመስሉናል። እንደ መልካም ስራ ጥንካሬን የሚፈትን ምን ነገር አለ?
-  እየተጠሉ መወደድ፤
- እየተዋረዱ ክብር መስጠት፤
- በጥላቻ መንፈስ እየታዩ ፍቅርን መስጠት
- እየተገፉ አለሁኝ ማለት፤ ጠንካራ ማንነትን ይጠይቃል።
ትዕግስት እንደ ፍርሃት፤ ይቅር ባይነት እንደ ውርደት፤ አክብሮት እንደ ማስመሰል እየተቆጠረ መልካምነት ከዘመኑ ጋር የማይሄድ ባህሪ እየመሰለን እየሸሸነው ነው።
⇒ ብዙዎቻችን ደግነትን እንደ ደካማ ጎን አድረገን እናየዋለን።
ደግነት ማለት ማየት ለማይችሉ አይን፤ መስማት ለማይችሉ ጆሮ ሆኖ የሚያገለግል መሣሪያ መሆኑን ማን በነገረን!!!
ደግነት የሚጀመረው ደግሞ በልባችን ስንመራ፣
o እንደራሳችን ቆጥረን ስለሌሎች ስንጨነቅ፣
o ዉለታን ሳንፈልግ ስናገለግል፣
o ሰው ስንቀን እኛ ግን ስናከብር
o ምላሽ ሳንጠብቅ መስጠት ስንጀምር ነው።

ዋሽተን ማሳመን ብልጠት፤ እራሳችንን ማስቀደም ብልህንት፤ ሌሎችን ማዋረድ ክብር የሚያስገኝልን እየመሰለን ከሰብዓዊው ማንነታችን ቀስ በቀስ እንሸሻለን። እውነታው ግን ይቅር እንደማለት፤ ሌሎችን እደማክበር፤
ፍቅር ለሚገባው ፍቅር እንደመስጠት ፈታኝ እና ጥንካሬን የሚጠይቁ ምን ነገሮች አሉ

⇒ ግዴላችሁም ወንድምና እህቶቼ እስቲ ብንበደልም ይቅርታ እንጠይቅ ምክንያቱም ይቅርታ ለአዕምሮ ነፃነትን፣ ለልብ እርካታን፣ ለመላው ሰውነታችን ደግሞ ደስታን ይሰጣል።
ታዲያ ነፃነት፣ እርካታንና ደስታን ማይፈልግ አለን

▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂

⭕️ በመጨረሻም የምላችሁ ነገር ቢኖር፦

❝ጊዜ የሳለ ጎራዴ ነው❞ ይላሉ አረቦች❗️

አዎ! ጊዜ የሳለ ጎራዴ ነው፤ ካልተጠቀምንበት ይቆርጠናል!!
እናም በዚህ ጎራዴ በሆነው ጊዜያችን ከመባላትና ከመጠላላት ይልቅ አብረን ተዋደን፣ ተከባብረን፣ ተደጋግፈን፣ አንዳችን አንዳችንን መክረን ወይም ገስፀን በሰላምና በፍቅር እንኑር። ካልሆነ ግን በጥላቻና በተንኮል ያሳለፍነው ጊዜ እራሳችንን ቆርጦ ይጥለናል።

✍️ ረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል

✍️ ለአስታያየት: t.me/ReshadMuzemil
👍52
🔴 ታዋቂው የማይክሮሶፍት Copilot Generative AI በቴሌግራም ቦት መጥቷል❗️

➡️ Microsoft Copilot OpenAI ከGitHub ጋር በመቀናጀት ያበለፅጉት AI Chatbot ሲሆን ጽሑፍን የሚያመነጭ እና ጥያቄዎችን የሚመልስ እንዲሁም በማንኛውም አይነት ሀሳብ ላይ ከተጠቃሚዎች ጋር Real Time መነጋገር የሚችል ቦት ነው።

➡️ በአሁኑ ጊዜ ይህ ቦት በቴሌግራም BETA ቨርዥን ላይ ሲሆን ማንኛውም የቴሌግራም ተጠቃሚ በስልክ ቁጥሩ አማካኝነት በነፃ በመመዝገብ ይህን ቦት መጠቀም ይችላል፤ በተጨማሪም ቦቱ ከኢንተርኔት ጋር ስለተገናኘ አሁናዊ ወይም Real Time መረጃዎችን መስጠት ይችላል።

ቦቱን ለመጠቀም @CopilotOfficialBot
👍3
Microsoft ለWindows 10 የonline support እና security update ቀጣይ አመት October 2025 ጀምሮ ያቆማል።
እንደሚታወቀው Microsoft ኮምፒውተራችን ለሳይበር ተጋላጭ እንዳይሆንና በየጊዜው የሚወጡ ዘመናዊ ፊቸሮችን እንድንጠቀም ሁሌም የመጨረሻውን ዊንዶውስ እንድንጭ ይመክራል።
ከዚህ በተጨማሪ የonline support እና በየጊዜው የሴኩሪቲ ማዘመኛውችን ይለቃል።ነገር ግን አዲስ ዊንዶውስ በለቀቁ ቂጥር ከዛ በፊት ለነበሩ ዊንዶሶች ሲሰጥ የነበረው እገዛ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ይቋረጣል።

ማይክሮሶፍትም ለwindows 7 January 14, 2020 ለwindows 8.1 January 10, 2023 ሙሉ በሙሉ አቋርጧል። የwindows 10 ደግሞ በቀጣይ አመት October 2025 ይቋረጣል። ስለዚህ ኮምፒውተራችሁን ወደ windows 11 ማሳደግ ይኖርባችኋል።
👍5
🇵🇸 ንፅዎችን አደራ

I love you ብየ - አላበዛም ጣጣ፤
በጣም እወዳችኋለሁ - ነብሴ እስኪወጣ፤
ውስጤ ቢያመኝም - አይኔ ቢመረቅዝ፤
ለእናንተ ያለኝ ፍቅር - መቼም አይቀዘቅዝ፤
ባገኝም እበላለሁ - ባጣም ተበድሬ፤
ክፉ አይካችሁ - ሞቼም ተቀብሬ፤
ወሰላሙ አለይኩም - ፍቅሬን በስንኝ፤
እስቲ ልጀምር - ኢብኑ ሙዘሚል ነኝ።

የረህማን የአላህ - እውቀት ለግሳቸው፤
ለማህበረሰቡ የሚጠቅም - ለሀገር የሚተርፋቸው፤
ጀባሩ ያአዚዝ - ሲሳይ ለግሳቸው፤
የድሆችን ሀዘን - እንባ የሚያብስላቸው፤
በተውሒዱም ቀጥ - በሱና አፅናቸው፤
በሀቁ ጎዳና እንጂ - እባክህ አትግደላቸው።

እነሱ ናቸው - ምሳሌ የፍቅር፤
ባለ ንፁህ ልብ - ሰውን የሚቀይር፤
እውነት ነው ልባቸው - ሐቅን የሚያፈቅር፤
በቃ ፍቅር ነው - የንፁህነታቸው ሚስጥር
ዝግ ሆኖ አያውቅም - የመልካምነታቸው በር፤

የወንድምነት ቁጣ - ክፋት መስሏችሁ
ተቀይማችሁም እንደሆን - እኔ አስከፍቻችሁ፤
ሰብሬው ከሆነ - መልካሙን ልባችሁ፤
አውፍ በሉኝ እንደው - ለአላህ ብላችሁ፤
ይቅር በሉኝ እንደው - ለአላህ ብላችሁ።

ምኞቴ ብዙ ነበር - ጊዜም አልፈቅድ አለ፤
ሰዓቱ ጉድ ሰራኝ - ገና ነኝ እያለ፤
እሁድን ስጠብቅ - ሰኞ ከተፍ አለ፤
ማክሰኞ ብትዘገይስ - አረ እንደው ምን አለ⁉️
ለካ! ሞዴል እየጠበቅኩ - ሚኒስትሪ ደረሰ፤
ቀን ተፈራረቀ - ወሩ ተጋመሰ፤
ወር ቀረን ስንል - ሳምንቱ ተደረመሰ፤
ጊዜም እንደ ቤት - ተሰርቶ ፈረሰ፤
እናም ይህ ጊዜ - ፈረሰና ሊለያየን፤
ሚኒስትሪ ደርሶ - ሰኔ 4 ነው አሉን፤
በሩ ተንኳኳ - ደርሶ የቁርጡ ቀን፤
ቀኑም አልቆም አለ - መያዝም አልቻልን፤
እባክህ ብንለው - እሱም ዝም አለን፤
ብዙ እናወጋ ነበር - ትንሽ ቢጠብቀን፤
ምን እናድርግ ታዲያ - አማራጭ አልሰጠን⁉️

በቀ❗️ እመካከራለሁ - ከጌታዬ ጋራ
መጥፎን አርቅላቸው - ከሚቀማመጡበት ስፍራ
ወዳጅ አበርክትላቸው - አላህን የሚፈራ፤
ሰውን የሚያከብር - የማያውቅ ጎራ፤
ህይወቷቸው ይመር - ኑሮአቸውም ይብራ፤
እባክህ የአላህ - ተማሪዎቼን አደራ፤
እባክህ የአላህ - ንፁዎችን አደራ።

✍️ በረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል
▭▬▬▭▭▬▬▭▭▬▭▬▭▬▭▬
⭕️ ማስታወሻነቱ: ለ2016 ዓ.ል ለ8ኛ ክፍል ተማሪዎቼ (ለወንድም እህቶቼ) ይሁን❗️

══════════════
🀄🀄ሉን👇👇👇 share👇

t.me/AndalusGrade7and8

t.me/AcademicEducations

t.me/BasicComputer_Skills

t.me/AndalusGrade5and6
👍3
ፕሮግራሚንግ ቋንቋ ምንድነው?

ፕሮግራሚንግ ቋንቋ ሰዎችና ኮምፒዩተሮች እንዲግባቡ የሚያስችሉ እና ሶፍትዌሮችን ለማበልፀግ የሚያገለግሉ የመመሪያ እና ደንቦች ስብስብ ነው። የሰው ልጅ ቋንቋዎች በሰዋሰው ሕግጋት እንደሚመሩት ሁሉ የፕሮግራሚንግ ቋንቋዎችም የራሳቸው ሕግጋት አሏቸው፡፡

ፕሮግራሚንግ ቋንቋዎች ሰዎች ኮምፒዩተሮች እንዲከውኑላቸው ለሚፈልጓቸው ተግባራት ትዕዛዛትን መስጠት በማስቻል በሰው እና በማሽኖች መካከል ቁልፍ ድልድይ መሆን መቻላቸውን የሳይንስ ዳይሬክት ድረ-ገጽ መረጃ ያመላክታል፡፡

የፕሮግራሚንግ ቋንቋዎች ሃይ ሌቭል እና ሎው ሌቭል ተብለው በሁለት ይከፈላሉ፡፡ እንደ ፓይተን፣ ጃቫ እና C++ የሚመደቡበት ሃይ ሌቭል የፕሮግራሚንግ ቋንቋ ለሰው ልጆች ተፈጥሯዊ ቋንቋ የቀረበ እና ለመረዳትም ቀላል ነው፡፡ በሌላ በኩል ሎው ሌቭል የፕሮግራሚንግ ቋንቋ የምንላቸው ውስብስብ የኮምፒዩተር ሥርዓቶችን ለማበልጸግ የሚያገለግሉ የፕሮግራሚንግ ቋንቋዎችን ያመለክታሉ፡፡ 

የፕሮግራሚንግ ቋንቋዎች የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ሥርዓቶችን ዕውን በማድረግ ሂደት ጉልህ ሚና አላቸው፡፡ ቋንቋዎቹ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ስልተቀመሮችን ለማርቀቅ፣ ዳታ ለማሰባሰብ እና ለመተንተን፣ ሞዴሎችን ለማሰልጠን እና ለሌሎችም አገልግሎቶች ይውላሉ፡፡

በዚህ ረገድ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ሞዴሎች እና መተግበሪያዎችን ለማዳበር እንደ Python፣ R፣ Java፣ C++ እና Lisp የመሳሰሉ የፕሮግራሚንግ ቋንቋዎች በስፋት ጥቅም ላይ ይውላሉ፡፡

🌐 ዘመኑ #የቴክኖሎጂ ነው 📲 ከዘመኑ ጋር አብረው ይዘምኑ💻

Telegram:
t.me/BasicComputer_Skills

tiktok.com/@basiccomputerskills

instagram.com/basiccomputerskills

Umma Life:
ummalife.com/ReshadMuzemil
╚═══📌Share📌════
ልዩ የክረምት ኮርስ ሴቶች በሴቶች የሚሰጥ እና ከ12 አመት በታች ለሆኑ ልጆች Riseup tech solution ቀለል ባለ መልኩ በአማርኛ ቋንቋ የፕሮግራሚንግ ትምህርትን በማስተማር ብቁ እናደርጋለን።

ስለ ልጅዎስ ይህን ክረምት ምን ቢማር፣ በምንስ ቢያሳልፍ ይሻላል ብለው ተጨንቀዋል? በአልባሌ በጨዋታ ግዜያቸው እንዳይባክን እና  ለወደፊቱም ዘላቂ በሆኑ የቴክኖሎጂ መስኮች ላይ ቢያሳልፉ ብለው አልጓጉም?
የሀይስኩል ተማሪዎችስ ለቀጣይ ትምህርት ብቁ እንዲያደርገኝ ይህንን ክረምት ምን ብማር፣ በምን ባሳልፍ ይሻላል የሚለው አሳስቧቹሀል?

Riseup የቴክኖሎጂ ማዕከል እንኳን ደስ አላችሁ እያልን!

ለሴቶች እንዲሁም ከ12 አመት በታች ለሆኑ ህፃናት ከቴክኖሎጂው ጋር ፈጥነው እንዲቀላቀሉ የሚያስችላቸውን ልዩ የክረምት ፕሮግራም በonline እና በአካል ለማስተማር ዝግጅታችንን አጠናቀን በምዝገባ ላይ ነን።
ቦታ ሳይገድቦ ያሉበት ቦታ ሆነው በonline አልያም በአካል መማር ይችላሉ።

የሚሰጡ ኮርሶች:-
front end website development
ለ3 ወራት የሚቆይ ኮርስ ሲሆን፤ ኮርሱ HTML, CSS, Media Query,Bootstrap, Java Script (JS) እና ሎሎችንም  የሚያካትት ይሆናል።
መሰረታዊ የኮምፒውተር እውቀት
ለ2 ወራት የሚቆይ ኮርስ ሲሆን፤ ኮርሱ Microsoft Word, Microsoft Excel, Microsoft PowerPoint, Microsoft publisher እና ሌሎችንም ያካትታል

እንዲሁም ለ Full stack web development (MERN) course በምዝገባ ላይ እንገኛለን። ኮርሱ 8 ወራት የሚቆይ ሲሆን ከcomputer አከፋፈት ጀምሮ የተዋጣለት ዌብሳይት አበልፃጊ እና ችግር ፈቺ የሆኑ ሲስተሞችን መስራት የሚያስችሎትን ፕሮግራሞች ያካተተ ነው።

አላማችን ጥራት ያለው ትምህርት በጥራት መስጠት በመሆኑ የምንቀበለው ውስን ተማሪ ነው። ስለሆነም ፈጥነው ይመዝገቡ።

በዌብሳይታችን http://www.riseuptechsolution.com በመግባት signup የሚለውን ነክተው  የሚጠይቆትን መስፈርት በማሟላት ይመዝገቡ።

          
            ለበለጠ መረጃ አድራሻችን
ቤተል ወደ ዌራ መሄጃ አዲስ ኢንተርናሽናል
ባንክ ያለበት ህንፃ 3ኛ ፎቅ

Mobile +251907667777
           +251936775727
Telegram @riseuptechsolution


⭕️ 👆በጣም ምርጥ እድል ነው ተጠቀሙበት❗️

🌐 ዘመኑ #የቴክኖሎጂ ነው 📲 ከዘመኑ ጋር አብረው ይዘምኑ💻

Telegram:
t.me/BasicComputer_Skills

tiktok.com/@basiccomputerskills

instagram.com/basiccomputerskills

Umma Life:
ummalife.com/ReshadMuzemil
╚═══📌Share📌════
👍5