Basic Computer Skills
1.89K subscribers
1.22K photos
100 videos
576 files
833 links
#በዚህ የቴሌግራም ቻናል
↪️ Programming
↪️ ቴክኖሎጂ ነክ ትምህርቶችን
↪️ ኮምፒውተር ነክ ትምህርቶችን
↪️Basic Computer Skills
↪️ Software
↪️ AI and AI Skills (Like ChatGPT)

ከላይ የተዘረዘሩትና ሌሎችም ገራሚ ትምህርቶች ይለቀቅበታል!

t.me/BasicComputerSkillsGroup

𝘽𝙮 𝙍𝙚𝙨𝙝𝙖𝙙
Download Telegram
📌Programming language📌

Programming language ማለት ከ ኮምፒዉተር ጋር ሊያግባባን የሚችል program ለመፃፍ የሚጠቅም ቋንቋ ማለት ነው: :


👨‍💻Computer ላይ የምንጭናቸው ማንኛውም አይነት የ ዳታ አይነቶች ለምሳሌ:  photo, video , software....ሌሎችም የሚቀመጡት  Mechine language በሚባል 0 እና 1 ቁጥሮች በያዘ የኮምፒውተር ቋንቋ ነው: : ለምሳሌ 10 ቁጥርን ከ keyboard ብናስገባ ኮምፒዉተራችን የሚረዳውና የሚያስቀምጠው ወደ እንደዚህ አይነት ቁጥሮች ቀይሮ ነው  👉 010001010...እነዚህ አይነት ቁጥሮች Machine language በመባል ይጠራሉ: : 

Machine Language
━━━━━━━━━━━━━
Machine language ማለት computer 💻 ሊረዳው የሚችል የኮምፒውተር ቋንቋ ነው: : የሚጠቀመውም 0 እና 1'ን ብቻ ነው: : ለምሳሌ 33 በ Machine language 00100001 ነው: :

➠ ነገር ግን ለኛ ለሰዎች Machine language'ን ለማንበብና ለመረዳት ከባድም አሰልቺም በመሆኑ ምክንያት በ Machine language program መፃፍ የማይታሰብ ነው: :

➠ በዚም ምክንያት ሰዎች አንብበው ሊረዱት የሚችል program መፃፊያ ቋንቋ(programming language) ለመፍጠር ጥረት መደረግ ተጀመረ: :
ይህ ጥረትም ለ Assembly language መፈጠር ምክንያት ሆነ: :

Assembly Language
━━━━━━━━━━━━━━
Assembly language  ሰዎችንና computer'ን በመጠኑም ቢሆን ያቀራረበ ቋንቋ ነው: :

Assembly language ከ Machine language አንፃር ለማነበብና ለመረዳት በመጠኑም ቢሆን ቀለል ያለ programming language ነው: :

Assembly language የእንግሊዝኛ ፊደላትን የያዙ አጫጭር ቃላቶችን ይጠቀማል። ለምሳሌ: ADD, MUL, MOV, INC, POP, PUSH, SUB, DEC,....,e.t.c

እነዚህ Assembly language ላይ ያሉ አጫጭር ቃላት(instructions) mnemonic( ሜሞኒክ) ተብለው ይጠራሉ።

Assembly language እና Machine language ባንድ ላይ low-level programming language በመባል ይጠራሉ: :

Assembly language ከ Machine language አንፃር ለ ሰው ልጅ ቋንቋ ቀረብ ያለ ነው አልን እንጂ እሱም ቢሆን ለ መማንበብ እና ለመረዳት ያን ያህል የቀለለ አልነበረም: :

በዚህም ምክንያት እስካሁን ካየናቸው የተሻለና ለማንበብ ለመፃፍ የበለጠ የቀለለ አዲስ programming  language አስፈለገ: :

High-level Programming language
━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━
➻ በፈረንጆቹ ወደ 1950ዓ.ም ላይ ለ ሰውልጅ ቋንቋ እጅግ የቀረበ, እንግሊዘኛ ቋንቋ መሳይ ለማንበብ , ለመረዳት እና ለመፃፍ ቀላል የሆኑ programming language'ኦች መሰራትና ወደ ገበያ መውጣት ጀመሩ: : እነዚህ programming language'ኦች high-level programming language በመባል ይታወቃሉ: :

➻ አሁን ባለንበት ዘመን ከ 100 በላይ High-level programming language'ኦች ይገኛሉ: : ከነዚህ ውስጥ ታዋቂዎቹ:
C, C++, C#, Java, COBOL, FORTRAN, Python, PHP …ይገኙበታል: :


t.me/TechnologyMasterPage
3