Basic Computer Skills
1.87K subscribers
1.22K photos
100 videos
576 files
833 links
#በዚህ የቴሌግራም ቻናል
↪️ Programming
↪️ ቴክኖሎጂ ነክ ትምህርቶችን
↪️ ኮምፒውተር ነክ ትምህርቶችን
↪️Basic Computer Skills
↪️ Software
↪️ AI and AI Skills (Like ChatGPT)

ከላይ የተዘረዘሩትና ሌሎችም ገራሚ ትምህርቶች ይለቀቅበታል!

t.me/BasicComputerSkillsGroup

𝘽𝙮 𝙍𝙚𝙨𝙝𝙖𝙙
Download Telegram
E2PDF_Backup_&_Restore_com_tekxperiastudios_pdfexporter_29_v19_08.apk
26.7 MB
App_name👇

📍 XML backup & restore or
E2pdf backup & restore
App_size 28MB

📍ጥቅሙ ምንድነው

1️⃣ጥቅሙ ስልካችን ላያ ያለን sms ወደ pdf መቀየር
2️⃣ በአንድ አመታት ውስጥ የተደዋወልነውን ስልክ ማን እንደወለ ለስንት ደይቃ እንዳወራን እስከ ስሙ እስከ ቀንና ሰአቱ በpdf ያስቀመጥልናል
3️⃣ contact ላይ የመዘገብነውን ወደ pdf መቀየር .......

መተግበሪያውን እንዴት ልጠቀመው
1️⃣ በመጀመሪያ መተግበሪያውን በማውረድ መክፈት
2️⃣ ከዚያም pdf backup (printable) አሚለው ስር ያለውን CLICK TO CONTINUE ሚለውን በመንካት የሚመጡ ዝርዝሮች ሚፈልጉትን መርጠው ሲነኩ የfile ስም አስገባ ይላል በማስገባት export to pdf ሚለውን በመንካት አለቀ ከዚህ በሁዋላ የስልክወ ፊይል ማናጀር ላይ ገብተው የዚህ app ስም የያዘ ፎልደር ውስጥ ያገኙታል 👍

t.me/TechnologyMasterPage
Data_counter_widget_pro_v4.5.1.658.apk
8.1 MB
Data Usage Manager

👉 ከመጠን በላይ አይጠቀሙ...የኢንተርኔት ዳታ አጠቃቀምዎን ይከታተሉ!

ይህ መተግበሪያ የኢንተርኔት አጠቃቀማችሁን ለመከታተል እንዲሁም የትኛዎቹ አፕሊኬሽኖች ላይ ብዙ ኢንተርኔት access እያረጋችሁ እንዳለ ምታውቁበት እንዲሁም ገደብ ምታበጁበት ነው።

📍 ሌሎች ተጨማሪ አፕሊኬሽኖች ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉ

t.me/TechnologyMasterPage
ብዙ ጊዜ ሞባይል ስንገዛ የምንገዛውን ሞባይል ጥራት ለመለየት ስለምንቸገር በቅርብ ያገኘነውን ሰው በመጠየቅ በምስክርነት እንወስናለን ፡፡
የስሞች መብዛትም አንዱ ችግር ነው፡፡ሳምሰንግ ፣ኖኪያ፣ ኤልጂ፣አፕል፣ወዘተ ወዘተ እየተባለ ይሄ ያ ይበልጣል ሙግትም አለ፡፡
እስቲ ለዛሬ ከሞባይል ቀፎ መሰረታዊ ማወዳደሪያ መስፈርቶች ውስጥ ጥቂቶቹን እንይ፡፡


የመጀመሪያው

የሞባይል ቀፎ ማወዳደሪያ ኦፕሬቲንግ ሲስተሙ ነው። ለምሳሌ ሳምሰንግ አንድሮይድን ና ቴክኖ አንድሮይድን ይጠቀማሉ እንበል፡፡ ኦፕሬቲንግ ሲስተማቸው አንድሮይድ መሆኑ በሞባይል ቀፎዎች መሀል ያለውን ያገልግሎት ጥራት፣ ከዘመነው
(አፕዴት ቴክ ) ጋር ያለውን መግባባትና ችሎታ፣ለቫይረስ ያለመጋለጥ ብቃትን ጨምሮ ከከባድ ድረ ገጽና አፕሊኬሽን ጋር ተጣጥሞ የመስራት አቅሙን ማሳየቱ ጥቂቶቹ መገለጫዎቹ ናቸው፡፡
ባጠቃላይ የሞባይል ቀፎን ባሕርይ ወሳኝ ምዕራፍ ኦፕሬቲንግ ሲስተሙ ነው፡፡ ከሞባይል ቀፎ አንፃር አንድሮይድ ባሁኑ ወቅት ከዊንዶው እና ማክ የተሻለ የኪስን አቅም ባማከለ መልኩ ተቀባይነት እያገኘ ነው፡፡


ሁለተኛው

ማነፃፀሪያ ደግሞ ዋይ ፋይ፣ ብሉቱዝ፣ ዩኤስቢ፣ ጂፒኤስ፣፣ ቱጂ፣ ስሪጂ፣ ፎር ጂ
የመሳሰሉትን መያዙና በተጨማሪም
ሁለትና ከዚያ በላይ ሲም መቀበሉ ሲሆን ከዚህም በላይ ኖርማል ሲም ጂ ኤስ ኤም እና ruim (cdma sim ) ባንድ ላይ መያዙ ነው፡፡
የፋይል አደረጃጀት ስርአታቸው ለአጠቃቀም ቀላል መሆንና እንደፈለግነው መቀየር መቻሉና ምቹ መሆናቸው ደግሞ ሌላው መለኪያ ነው ፡፡

ለምሳሌ ተች ስክሪን፣ ስክሪን ጋድጌትስን መቀይር መቻሉና በፋይል ማናጀር በምንፈልገው መንገድ መቆጣጠር በሚያስችል መንገድ ‘እንደዚህ ሁንልኝ’ ስንለው የሚሆንልን ስማርት ፎን ደስ አይልም ?

ሶሰተኛው

ማነፃፀሪያ የራሱ የሞባይሉ ሜሞሪ ( ፎን ወይም ኢንተርናል ሜሞሪ) ምንለው
ነው፡፡ ይህ ሜሞሪ አቅሙ በጨመረ
ቁጥር ዋጋውም አብሮ መጨመሩ እሙን ሲሆን ለቀፎዎች የዋጋ ልዩነት መሰረትም አንዱ
ምክንያት ነው፡፡

ቀፎዎች የምንከትላቸውን የውጭ ሜሞሪዎችና አብሮአቸው የተሰራውን ሜሞሪ ባንድ
አይነት ስለማይጠቀሙ በፍጥነት፣ በጥራትና
በአቅማቸው ላይ የሚያመጣው ልዩነት ትልቅ ነው፡፡ ቀፎዎች (TIF card)ቲፍ ካርድና
ኤስዲ(SD card) ካርድን(ሞባይላችን ላይ
ምንከታቸው ሜሞሪዎች ማለቴ ነው) ሲጠቀሙ ፍጥነታቸው ዝቅተኛ ከመሆኑም በላይ
የሚጭኑት አፕሊኬሽን ውስንና ቀጥታ ፍሰት
(Real Time access) ነው፡፡
➛ስለዚህ ቀፎ ስንገዛ የራሱን ሜሞሪ አቅም ማስተዋል ግድ
ይላል፡፡


አራተኛው

የሞባይል ቀፎ ማወዳደሪያ ‘ፎን ክሎክ’ የሞባይል ቀፎውን ሲስተም ሃርድዌር
ፍጥነት ሚወስን ነው።

➝ ለምሳሌ ድረ ገፅ ለይ አንድ ሞባይል ያለምንም መቆራረጥ ከዩቱብ ወይንም ከኛው ድሬትዩባችን ላይ ቪዲዮ
ቢያጫውት የክሎክ ፍጥነቱንና
የቢዩልት ኢን ሜሞሪን(phone memory) ጥራት ያሳያል፡፡
በተጨማሪ ቪዲዮ ኮሊንግ ያለችግርና (ፍሪዝ) በእስካይፒ መጠቀም ከቻልን በርግጥም
የቀፎዎችን ግሩም ጥራት ያሳየናል፡፡

➝እዚህ ጋር ከግንዛቤ ውስጥ እንዲገባልኝ ምፈልገው አሁን ያለው የአገራችን የኔትዎርክ ችግር
በቀፎው እንዳይሳበብ የኔትዎርኩን ሁኔታም
ማየት መልካም መሆኑን ነው፡፡
አምስተኛ የባትሪ ጥራትና ቆይታ ነው ፡፡ አንዳንድ ሞባይሎች ባትሪ ሙጥጥ አያረጉ ‘‘እረ
የቻርጀር ያለህ!’’ እያሰኙ ስንቱን
አስጨንቀዋል፡፡ በርግጥ የሞባይል አቅምና ያገልግሎት ጥራት በጨመረ ቁጥር ባትሪ
አጠቃቀምም አብሮ ቢጨምርም ብዙ
ሞባይል አምራቾች የሞባይል ባትሪ ጥራትን በማሻሻል እነዚህ ቀፎዎች ለ18 ሰኣት
አንዲያገለግሉ አርገው ሰርተውልናል፡፡
ሌላው ባትሪን በተመለከተ ማየት ያለብን የተሻለ ሞባይል ለመግዛት የባትሪ ማኔጅመንት
ፕሮቶኮል አውቶማቲክና ማኑዋል አማራጭ
እንዳለው ማጣራት ነው፡፡

የባትሪ ቀበኛ ከሆኑት ስክሪን ብራይትነስና ቫይብሬት ቴክኖሎጂን ጨምሮ ከጀርባ ሳናያቸው
የሚስሩ አፕሊኬሽኖች መኖር፣ ቫይረስና
አንቲ ቫይረስ ማኔጅ ማድረግና የመሳሰሉትን መቆጣጠሪያ ሶፍት ዌር መጫን የባትሪን
ቀይታ ለማራዘም የምጠቁመው ተጨማሪ
መፍተሄ ነው።

በመጨረሻም

የተሻለ ሞባይል ለመያዝ ከላይ ከጠቀስኳቸው በተጨማሪ ኢሜይል፣ የጽሑፍ
መልዕክት፣ ካሜራ ጥራት፣ ምቾት፣ ሰክሪን
ስፋትና የተመረተበትን ቀን ማረጋገጡ ጠቃሚ ነው!!

t.me/TechnologyMasterPage
✳️ የሰዎችን ድምጽ በማዳመጥ በልብ ድካም የመጠቃት እድልን የሚያሰላው የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ሥርዓት

🚩በተዘጉ የደም ቧንቧዎች ምክንያት ከፍ ያለ ቀጭን ድምጽ ያላቸው ሰዎች የልብ ችግሮች ሊገጥሟቸው እንደሚችል የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ሥርዓትን ተመስርተው ተመራማሪዎች አሳወቁ፡፡

🚩ተመራማሪዎቹ የልብ ደም ስሮቻቸውን ሁኔታ ለመገንዘብ ኤክስ ሬይ የታዘዘላቸውን መቶ ስምንት ታማሚዎች በመመልመል ቮካሊስ ሄልዝ በተባለው የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የስልክ መተግበሪያ ላይ የሰላሳ ሰከንድ የድመጽ ናሙና እንዲሰጡ አድርገዋል፡፡

🚩በሦስት የተለያዩ ደረጃዎች ወደመተግበሪያው የሚቀዱት የድምጽ ናሙናዎች በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ሥርዓቱ ተተንትነው ከውጤት አመላካች ጋር ይቀርባሉ፡፡

🚩አስር ሺህ የድምጽ ቅጂዎች ሥርዓቱን ለማሰልጠን አገልግሎት ላይ መዋላቸውን ዘ ኢንዲፔንደንት በዘገባው አመላክቷል፡፡

🚩ሥርዓቱ ሰማንያ አይነት የድምጽ ሁኔታዎችን መገንዘብ እንደሚችልና ከእነዚህም ውስጥ ስድስቱ የልብ ደም ስር መዘጋት ችግርን አመላካች መሆናቸው ተገልጿል፡፡

🚩በተመራማሪዎቹ ገለጻ የሰው ልጆች ጆሮ እና አዕምሮ የማይለይለዩትን የድምጽ ሁኔታ ቴክኖሎጂው በማሽን ለርኒንግ አማካኝነት ሊቆጠሩ ወደሚችሉ የውጤት መግለጫዎች በመቀየር ማስቀመጥ እንደቻለ አብራርተዋል፡፡

🚩በአሜሪካ የማዮ ክሊኒክ ባልደረባ እና ምርምሩን የመሩት ዶ/ር ጃስክንዊል ሳራ እንደተናገሩት ምርምሩ ሐኪሞችንም ሆነ በተግባር ላይ ያሉ የልብ ምርመራ መንገዶችን ለመተካት ያሰበ አይደለም፡፡ ይልቁንም ከተለመዱት መንገዶች ጋር አጣምሮ ለመጠቀም ትልቅ እድል ይዞ የመጣ ነው፡፡


#የቴክኖሎጂ_ዜና

#Technology_News

©Technology Master Page
════❁✿❁ ═══════

t.me/TechnologyMasterPage
በጽሁፍ ውስጥ የተደበቁ ስሜቶችን በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የመግለጽ ብልሀት

የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂ እና የስልተ-ቀመሮች ዕውን መሆን በሰዎች ይሰሩ የነበሩ አድካሚ የዳታ ትንተና ሂደቶችን በመቅረፍ ረገድ ብዙ ርቀት ተጉዘዋል፡፡

ከእነዚህም መካከል ሴንቲሜንት አናሊስስ #SentimentAnalysis ይጠቀሳል፡፡ ይህ ሥርዓት በአገልግሎት እና ምርት አቅራቢነት ወይም ከደምበኞች ጋር በተለያየ ምክንያት የሚያገናኝ ሥራ ያላቸው ተቋማት የደምበኞቻቸውን ግብረ-መልስ እውነተኛ ትርጉም ወይም ስሜት የሚረዱበት አንዱ መንገድ ነው፡፡

ሥርዓቱ ናቹራል ላንጉዌጅ ፕሮሰሲንግን ከማሽን ለርኒንግ ጋር አሰባጥሮ በመጠቀም በጽሁፍ የሰፈረ ግብረ-መልስ በትክክል ምን ማለት እንደሆነ ይተነትናል፡፡

ሴንቲሜንት አናሊስስ በሦስት መንገዶች ይከወናል፡፡ አንደኛው ቀድመው በተቀመጡ ሕግጋት ወይም የቋንቋው መዝገበ ቃላት መሠረት የሚተገበር ነው (Rule or Lexicon based approach) ፡፡ ሌላኛው በጊዜ ሂደት ከዳታ በሚማር የማሽን ለርኒንግ ስልት ይከወናል (Automated or Machine Learning approach)፡፡ ሦስተኛውና ተመራጩ እንዲሁም በስፋት ጥቅም ላይ እየዋለ የሚገኘው ሁለቱን በጥምረት የሚጠቀመው ነው (Hybrid approach)፡፡

በዚህም መሠረት በኢሜል፣ በማሕበራዊ ትስስር ገጾች፣ በተለያዩ ድረ-ገጾች እና መሰል መድረኮች ደንበኞች ካሰፈሯቸው ተቋሙን የተመለከቱ ያልተደራጁ ጽሁፎች ውስጥ ጠቃሚ እይታዎች ይጠናቀራሉ፡፡

እንደ ቴክታርጌት ትንተና ይህ ሥርዓት በዓረፍተ ነገር፣ በሐረግ፣ በአንቀፅ እና ከዛም ደረጃ በላይ በሚገኙ ጽሁፎች ላይ መተግበር ይችላል፡፡

#Technology_News

#የቴክኖሎጂ_ዜና

t.mr/TechnologymasterPage
✳️ ብዙ ሰዎች የማያዉቋቸው የGSM ሞባይል ሚስጥራዊ ኮዶች!

1. ስልክዎ ሲደወልሎት ይህ ቁጥር አገልግሎት አልዋለም እንዲልላቹ ከፈለጋቹ! ወደ *21*900# ይደውሉ ወይም 1 ዲጂት በመቀነስ ወደ ራስዎ ስልክ ማድረግ! ለምሳሌ ስልክ ቁጥርዎ 0902 ከሆነ ወደ *21*090215# ደውሉ ለማጥፋት ሲፈልጉ #21# ብለው ይደውሉ! ከላይ የተገለጸው በ900 ቦታ የፈለጉት ሌላ ትክክለኛ የስልክ ቁጥር ያልሆነም ማድረግ ይችላሉ!

➜ሁሉም ጥሪዎችና መልእክች ወደ ሌላ ቁጥር ዳይቨርት ለማድረግ ሲልጉ
*21*0144# በ0144 ቦታ የፈጉትን የሞባይል ወይም መደበኛ
ስልክ ቁጥር ያስገቡ ቀድሞ ወደ ነበረበት ለመመለስ ከፈለጉ #21# ብለው ይደውሉ ማለትም ስልክዎ ዳይቨርት ከተደረገ #21# ሲደውሉ ወደ ኖርማል ይመለሳል ዳይቨርቱ ይጠፋል *#21#
ከሆነ ስልኩ ዳይቨርት ተደርገዋል ወይስ አልተደረገም የሚል መረጃ ይሰጠናል

2. ስልክዎ ቢዚ ብቻ ሲሆን ዳይቨርት ለማድረግ *67*የፈለጉትቁጥር# ብለው
ይደውሉ! ይህንን ዳይቨርት ለማጥፋት #67# ይደውሉ

3. ስልክዎ ካልተነሳ ብቻ ዳይቨርት ለማደረግ *61*የፈለጉትቁጥር# ይደውሉ! ይህንን ዳይቨርት ለማጥፋት #61# ይደውሉ

4. ስልክዎ ከኔትዎርክ ዉጪ ብቻ ሲሆን ዳይቨርት ለማድረግ *62*የፈለጉትቁጥር# ይደውሉ! ይህንን ለማጥፋት ሲፈልጉ #62# ብለው ይደውሉ!

5. ኮል ወይቲንግ አክቲቭ ለማደረግ ሲፈልጉ *43# ብለው ይደውሉ! ኮል ወይቲንግ ለማጥፋት ሲፈልጉ #43# ብለው ይደውሉ! ኮልወይቲንግ አክቲቬት መደረጉ ወይም አለመደረጉ ለማወቅ *#43# መደወል

6. ሲደውሉ ስልክ ቁጥርዎ እንዳይታይ ወይም በሌላ ቁጥር ተክተው ለመደወል
ሲፈልጉ #31#የሚደውሉት ቁጥር ከዛ መደወል
▫️አንዳንድ ስልኮች #31# ከተደወለ በኀላ የምንደውለውን ቁጥር እናስገባለን በእኛ አገር ኔትዎርክ ላይሰራ ይችላል

➥ሁላቹም ብትሞክሯቸው ጥሩ ነው

➲Forward , Like , Comment

#መረጃዎችን ለወዳጅዎ ያጋሩ።

t.me/TechnologyMasterPage


Fb.com/TechnologyMasterPage
በፓርኪንሰንስ በሽታ የተጠቁ ሴሎችን ድብቅ ባሕርያት በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ አማካኝነት መለየት ተቻለ፡፡

ተመራማሪዎች ከፓርኪንሰንስ ተጠቂዎች የተወሰዱ የቆዳ ሕዋስ ናሙናዎችን አዳዲስ ባሕርያት አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ እና ሮቦቲክስ ቴክኖሎጂን በማጣመር መለየት መቻላቸው ተገልጿል፡፡

ከዘጠና አንድ የበሽታው ተጠቂዎች እና ጤናማ ሰዎች የተወሰዱ ከሚሊዮን የተሻገሩ የቆዳ ሕዋስ ምስሎችን በመጠቀም ውጤቱ እንደተገኘ ተዘግቧል፡፡

በኒው ዮርክ ስቴም ሴል ፋውንዴሽን በበለፀገው የሮቦቲክ ቴክኖሎጂ አማካኝነት ከሕመምተኞቹ የተወሰደውን ናሙና በመተንነተን እስካሁን ያልታወቁ አዳዲስ ባሕርያት መገኘታቸው ታውቋል፡፡

NYSCF Global Stem Cell Array ተብሎ የሚታወቀው የፋውንዴሽኑ እጅግ ዘመናዊ የሮቦት ሥርዓት ብዛት ያላቸውን የሕዋስ ምስሎች ለመለየት አገልግሎት ላይ ውሏል፡፡ በውጤቱ የተገኙ የሕዋስ ምስሎችን ለዚሁ ወደተዘጋጀ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ሥርዓት በማስገባት የጋራ ባሕርያቸውን ለመለየት ጥቅም ላይ ውሏል፡፡

የፋውንዴሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሱዛን ኤል. ሶሎሞን እንደተናገሩት እንደ ፓርኪንሰንስ ላሉ ውስብስብ በሽታዎች በተለመደው መንገድ መድኃኒት ለማግኘት የሚደረገው ጥረት አመርቂ አይደለም፡፡ ነገር ግን በምርምሩ የተደረገው ጥረት ውጤታማ የሆነ አዲስ መድኃኒት ለማግኘት መሠረት እንደሚሆን አመላክተዋል፡፡

ኔቸር ኮምዩኒኬሽንስ ተብሎ በሚታወቀው ጆርናል ላይ ለሕትመት የበቃው ምርምር የኒው ዮርክ ስቴም ሴል ፋውንዴሽን እና የጉግል የምርምር ክፍል ውጤት መሆኑን ኒውሮሳይንስ ኒውስ ድረ-ገጽ ዘገቧል፡፡



#Technology_News

#የቴክኖሎጂ_ዜና

t.me/TechnologyMasterPage
Power Ge'ez 2017 Kanna.zip
8.8 MB
🔆Power Geez 2017

🦋#Share🦋
@TechnologyMasterPage
Power Geez 2010.exe
3.8 MB
በ ኮምፒውተራኝን አማርኛ ለመፃፍ ሚያገለግል👍

#share
@TechnologyMasterPage
Windows_MsOffice_Activator_Collections1-aiosetup.exe
101.9 MB
💻All Windows and Microsoft Office Activator Collections 1.0

Activate your Windows and Ms. Office

❖Includes :
KMS Tools, KMSpico, Microsoft Toolkit, ReLoader, RemoveWAT, Windows Loader and more.

🦋#Share🦋

#Tech: t.me/TechnologyMasterPage
Microsoft_Office_2021_Pro_Plus_16_0_14332_20216_x64_VL_LTSC_with.zip
1.8 GB
💻 Microsoft Office 2021 Pro Plus [16.0.14332.20216] [x64] [VL] [LTSC] with Activator

🦋#Share🦋
#Tech: @TechnologyMasterPage
#Academic : @EthioWorldwideStudents
Dear College and University students
We have come up with a special STUDENT PACKAGE with attractive gifts.
#Studentpackage


#Ethio_telecom_news_for_Students

#የኢቲዮ_ቴሌ_አዲስ_ዜና_ለተማሪዎች
#EthioTelecom

ኢትዮ ቴሌኮም ለተማሪዎች ልዩ ጥቅል ማቅረቡን ገለፀ።

➝ ኢትዮ ቴሌኮም ለኮሌጅ እና ለዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ልዩ የሆነ የተማሪ ጥቅል ማቅረቡን አሳውቋል።
በዚህም :
ወርሃዊ ፦
➨ ዋጋ ↪️ 34 ብር ፤ ጥቅል 👉 180 ደቂቃ (ጥሪ) ፤ ስጦታ 90 ደቂቃ (ጥሪ) + 100 መልዕክት ፤
➨ ዋጋ 👉 64 ብር ፤ ጥቅል 👉 360 ደቂቃ (ጥሪ) ፤ ስጦታ 200 ደቂቃ (ጥሪ) + 150 መልዕክት ፤
➨ ዋጋ 👉 42 ብር ፤ ጥቅል 👉 1 GB (ዳታ) ፤ ስጦታ 512 MB (ዳታ) + 100 መልዕክት ፤
➨ ዋጋ 👉 82 ብር ፤ ጥቅል 👉 2 GB (ዳታ) ፤ ስጦታ 1.1 GB (ዳታ) + 150 መልዕክት ፤
ሳምንታዊ ፦
➨ ዋጋ 👉29 ብር ፤ 3 GB (ዳታ) መሆኑ ተገልጿል።
ኢትዮ ቴሌኮም ፤ ሳምንታዊው የዳታ ጥቅል እና ለደንበኞች የቀረቡት ስጦታዎች የሚያገለግሉት ከለሊቱ 6 ሰዓት እስከ ንጋት 12 ሰዓት መሆኑን አሳውቋል።
ተማሪዎች ተማሪነታቸውን የሚገልፅ " መታወቂያ " በመያዝ በኢትዮ ቴሌኮም ሽያጭ ማዕከሎች በመቅረብ ጥቅሎቹን መግዛት ይችላሉ ተብሏል።

@TechnologyMasterPage

#ethiotelecom_News
አግራሞቴን በጥያቄ እና መልስ

#ጥ:- እንዴ ወዴት ነው የምትሄደው!?
#መ:- እኔ መቆም አልችልም፤ ከቆምኩ እሞታለሁ!
#ጥ: እሞታለሁ!?
መ:- አዎ!፤ እኔ ውድድር ላይ እየሮጥኩ ነው!
ጥ:- እንዴ! እሺ፤ ይሄ የትኛው ውድድር ነው!?
መ:- የትኛው ውድድር እንደሆነ እኔም አላውቀውም!
ጥ:- የትኛው ውድድር እንደሆነ አንተም አታውቀውም!?፤ ታዲያ ለምን ትርጣለህ!?

መ:- ምክንያቱም ሁሉም እየሮጠ ነው፤ ስለዚህ እኔም እየሮጥኩ ነው!

ጥ፦ እንዴ ለምን ይሮጣል ሁሉም!?፤ ቆሞ የሚጠይቅ የለም!?
መ:- ለምን ይጠይቃሉ!?
ጥ:- ለምን ደግሞ ምንድነው እሱ!?

↪️ እንተወው እሺ ለምን መሆኑ ምን ለውጥ ያመጣል!?

ጥ:- #ያው ውድድሩ ላይ ከሮጥክ አንደኛ ትወጣለህ!?
መ:- አይ
ጥ:- እሺ ሁለተኛ!?
መ:- አይ
ጥ:- እሺ! እሺ ሶስተኛ!?
መ:- አይ
ጥ:- 4, 5, 6, 7, 8, 9, 10 ትወጣለህ!?
መ:- አይ
ጥ:- በቃ በዚህ ውድድር መሃል ላይ ትወጣለሃ!?
መ:- አዎ እኔ መሃል ላይ እወጣለሁ፣ መሃል ላይ ያለሁ ሰው፣ ተራ ጨዋ ሰው ነኝ!!
ጥ፦ ግን እኮ ስህተት እየሰራህ ነው!
➝ አንተ ራስህ ውድድርህን ምረጥ!
➝ በምታውቀውን ውድድር ተወዳዳር!
➝ ለምን እንደ ምትወዳደር እወቅ፤ ያኔ ታያለህ አንደኛ ካልወጣህ፡ ምን አለ በለኝ!!

እኮ፣ ቆም ብለንማ መጠየቅ ይኖርብናል፤ ሰው ለምን እየሮጠ እንዳለና ወዴት እየሮጠ እንዳለ፣ ከነ አላማውና የውድድሩን ምንነት ማወቅ ያስፈልገናል። ካልሆነ ግን የውድድሩ አጨራረስ፣ የኛ መጨረሻ እና የህልማችን አወዳደቅና አነሳስ አያምርም። ማማሩንስ እንተወው በሉ እንደውም የስኬት መዳረሻ ጎዳናው(መንገዱ) ላይ ራሱ አንኖርም!!

እኮ ታዲያ እኛው አደለን!?፣ ውድድሩን አውቀነውና ለኛ የሚሆነውን መርጠን፤ የውድድሩን አጨራረስ እናሳምረዋ!?

በረሻድ ሙዘሚል
💢ስልክዎ ላይ #Application's ሲጭኑ "There was a Problem Parsing The Package" እያላችሁ ለተቸገራችሁ #መፍትሔ ⬇️⬇️⬇️

1⃣.USB Debugging On አድርጉት።

⚠️Settings➡️ About Phone➡️ Build Number (7ጊዜ ይንኩት)➡️ ወደ Setting ይመለሱና➡️ Developer Options➡️ USB debugging የሚለውን #ON ያድርጉት።

2⃣. የጫኑት Antivirus ወይም Cleaner ካለ ለጊዜው #Disable ያድርጉት።

3⃣. ያለዎት አፕ #Corrupted ወይም Download ተደርጎ ያላለቀ ሊሆን ስለሚችል ከእንደገና Download📥 ያድርጉት።

⚠️አፖችን #ከPlaystore ብቻ ቢያወርዱ📥 ተመራጭ ነው።👍

4⃣. የPlay Storeን Cache Cookies Clear ያድርጉት።

⚠️Settings➡️ Apps➡️ Playstore ➡️ Clear Cache Cookies

5⃣. ሊጭኑት ያሰቡት አፕ ካለዎት Operating System ጋር #Compatible ሳይሆን ሲቀር።

⚠️በተጨማሪም ሌላ የሚፈልገው Hardware Requirements ካለ የአፑን #description በደንብ ያንብቡ።



⚠️መረጃዎች ቶሎ ቶሎ እንዲደርሳችሁ ቻናላችንን #muteያደረጋችሁት #UNMUTE በማድረግ ተባበሩን🙏🙏🙏"መረጃዎች በፍጥነት ይደርሶታለል

⚠️መረጃዎችን ለወዳጅዎ 👥 ያጋሩ።


︎●●●◇●●●◇●●●◇●●●◇●●●◇●●●
🌐ዘመኑ #የቴክኖሎጂ ነው 📲 ከዘመኑ ጋር አብረው ይዘምኑ💻

t.me/TechnologyMasterPage
ስማርት ስልክዎን ለበሽታ ምርመራ የማዋል ሂደት

ጉግል በጤናው ዘርፍ ያሉ መሰናክሎችን ለመቅረፍ ስማርት ስልኮች እና አርቲፊሻል ኢንተለጀንስን በመሰሉ ጉዳዮች ዙሪያ ምርምሮችን እያካሄደ መሆኑን አስታወቀ፡፡

ምርምሩ የስልኮቹን የድምጽ ማዳመጫ እና ካሜራ በመጠቀም የሕመም ምልክቶች መኖር አለመኖራቸውን ለማረጋገጥ እንደሚረዳ የዩሮ ኒውስ መረጃ አመላክቷል፡፡

ለአብነትም የስልኮቹን የድምጽ ማዳመጫ እና መነጋገሪያ (ማይክሮፎን) ደረት ላይ በማስቀመጥ የልብ ምት እንዲሁም ተያያዥ ድምጾችን በማዳመጥ የሕመም ምልክቶችን አስቀድሞ ለመለየት ያገለግላል፡፡

በሌላ በኩል የስልኮቹን ካሜራ በመጠቀም የተወሰዱ የዓይን ምስሎችን መሠረት አድርጎ የስኳር በሽታ ምልክቶችን ሳይረፍድ ለመለየት እንደሚያስችል ተጠቁሟል፡፡

በአዋቂዎች ዘንድ ለአይነ ስውርነት አንዱ ምክንያት የሆነው ይህ በሽታ ሬቲና ተብሎ በሚታወቀው የዓይን ክፍል የደም ስሮች ላይ ከፍተኛ ጉዳት በማድረስ ይታወቃል፡፡

የጉግል የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ሥርዓትን በመጠቀም በሕንድ እና ታይላንድ የሚገኙ የጤና ባለሞያዎች ዳያቤቲክ ሬቲኖፓቲ በተባለው በዚህ በሽታ ተጠቂ የሆኑ መቶ ሺህ የሚጠጉ ሰዎችን መለየት እንደቻሉ በዘገባው ተጠቅሷል፡፡

ሆኖም እስካሁን ባለው ሂደት ጥቅም ላይ የዋሉት በጤና አገልግሎት ተቋማት የሚገኙ ሌሎች ካሜራዎች እንደሆኑ ተጠቁሟል፡፡ ይህን ሂደት በስማርት ስልኮች ለመተካት እየተሰራ ያለው ምርምር ከጅምሩ አመርቂ ውጤት እያሳየ መሆኑ ተመላክቷል፡፡



#ethiotelecom_News

#የቴክኖሎጂ_ዜና


t.me/TechnologyMasterPage

Fb.com/TechnologyMasterPage
💻 ኮምፒዉተር የሚዘጋበት ወይም ክራሽ የሚያደርግበት ምክንያቶች 💻

💽📀የሀርድዌር መቃረን📀🔌

ለ Windows ክራሽ የማድረግ ዋነኛው ምክንያት የ Hardware መቃረን ነው፡፡እያንዳንዱ Hardware ክፍሎች ለመግባባት IRQ(interrupt request channel) ያስፈልጋቸዋል፡፡ እነዚህ IRQ ለየሀርድዌሩ የተለዩ ወይም የተነጠሉ መሆን አለባቸው፡፡ ለምሳሌ አንድ ፕሪንተር IRQ 7 ሲኖረው ኪቦርድ ደግሞ IRQ 1፡፡እያንዳንዱ ሀርድዌር የራሱ የሆን IRQ ለመያዝ ጥረት ያደርጋል፡፡ ግን ብዙ የሀርድዌር እቃዎች ስንጠቀም ወይም የሀርድዌሩ ሶፍትዌር በስርዓት ካልተጫነ ሁለት ሀርድዌሮች ተመሳሳይ IRQ ሊጋሩ ይችላሉ፡፡ በዚህም ሰዓት ሁለት የሀርድዌር ዕቃዎች በተመሳሳይ ሰዓት ለመጠቀም ስንሞክር ክራሽ ሊከሰት ይችላል፡፡

📼የተበላሸ ራም📼

ራም Ram (random-access memory) ችግሮች ዋናው የብሉ እስክሪን ኦፍ ዴዝ (blue screen of death) ዋና መንስኤ ሲሆን የሚያሳየው መልእክት ፋታል ኤክሰብሽን ኢረር( Fatal Exception Error) የሚል ነው፡፡ ፋታል ኢረር የሚነግረን አሳሳቢ የሀርድዌር ችግር አለ ማለት ነው፡፡ አንዳንዴ የሀርድዌር ክፍል ስለተጎዳ መቀየር እንዳለበት ይናገራል፡፡ በራም የሚመጡ ችግሮች ብዙ ግዜ የራሙ ከኮምፒዉተሩ ጋር ሳይጣጣም ሲቀር ነው፡፡ ይህም ማለት ለኮምፒዉተር የራም ስሎት ጋር ሳይመጣጠን ሲቀር ፤ የራሱ ያልሆነ ሞዴል ስንጠቀም እና የተለያየ አይነት ራም በአንድ Computer ውስጥ ስንጠቀም ነው፡፡ለምሳሌ 70ns ለይ 60ns ራም ስንጠቀም ኮምፒተሩን ፍጥነት ይቀንሳል፡፡ይሄ ደግሞ ራሙን ከአቅሙ በላይ ይጫነዋል በዚህ ግዜ window ክራሽ ያደርጋል፡፡

📟ባዮስ ሴቲንግ( BIOS settings)📟

እያንዳንዱ ማዘር ቦርድ ሲመረት የራሱ የሆነ የተለያዩ ቺፕሴት ሴቲንግ አብሮት ይጫናል፡፡ እነዚህን ሴቲንግ ለመጠቀም በኮምፒውተራችን ኪቦርድ ላይ F2 ወይም F10 (እንደ ኮምፒዉተሩ ይለያያል) ኮምፒዉተሩ ስንከፍት ከጥቂት ሰከንድ በኻላ በመንካት ሴቲንጉን አክሰስ ማድረግ ይቻላል፡፡ ነገር ግን አንዴ ባዮስ ዉስጥ ከገባን ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ አለብን፡፡ ማንኛውንም ሴቲንግ ከመቀየራችን በፊት ፎቶ ወይም ወረቀት ለይ ሴቲንጎቹን ማኖር አንድ ያበላሸነው ነገር ካለ በቀላሉ መቀየር ያስችለናል፡፡ብዙን ግዜ የባዮስ ችግር የራም ላተንሲ ችግር ነው፡፡ የድሮ ኮምፒዉተር ራም ላተንሲ 3 ሲሆን የቅርብ ግዜ ራሞች ደግሞ ላተንሲ 2 ናቸው፡፡ ይሄንን ሴቲንግ በምንቀይርበት ጊዜ ኮምፒዉተሩ ክራሽ ያደርጋል ወይም ፍሪዝ ይሆናል፡፡
 
🐞ቫይረስ🐞
ቫይረሶች የኮምፒዉተር ፕሮግራም ሲሆኑ እራሳችውን በማብዝት ወይም ኮምፒዉተር ፋይሎች ላይ በማጣበቅ ከፍተኛ ጉዳት ሊያደርሱ ይችላሉ፡፡ ቫይረሶች የትእዛዞች ስብስብ ሆኖ እራሱን በሌላ የኮምፒዉተር ፕሮግራም ያጣብቃሉ(ብዙ ግዜ ኦፕሬቲንግ ሲስተሙን)፡፡ ኮምፒዉተራችን ውስጥ ቫይረስ ሲያጠቃ የኦፕሬቲንግ ሲስተሙን ፋይል የመቀየር ሀይል ስላለው ኮምፒዉተሩን ክራሽ ወይም ፍሪዚ ሊያረግ ይችላል፡፡

መጋል
በኮምፒዉተራችን ዉስጥ ካሉ ሀርድዌሮች በጣም አስፈላጊው እና ዋናው ሲፒዩ ነው፡፡ ሲፒዩ በኤሌትሪክ ሃይል የሚሰራ ሲሆን ካለው ውስብስብ የትራዚስተር ብዛት አማካኝነት የሚፈጥረው ከፍተኛ ሙቀት ሲፒዩን ሊያበላሸው ወይም ከጥቅም ውጪ ሊያደርገው ይችላል፡፡ ሲፒዩ ብዙ ጊዜ ከማቀዝቀዣ ቬንትሌተር ከኮምፒዉተራችን አንድ ላይ ይመጣል፡፡ እነዚህ ቬንትሌተር ከተበላሹ ወይም ሲፒዩ ካረጀ የኮምፒዉተራችን ሲፒዩ መጋል ይጀምራል፡፡ ይህ ደግሞ በኮምፒዉተራችን ላይ የከርንል ኢረር ያስከትላል፡፡ ይሄ ችግር ብዙ ጊዜ የሚታየው በኦቩር ክሎኪንግ ጊዜ ነው፡፡ ይህ ማለት ሲፒዩን ከሚገባው በላይ በማሰራት ወይም ከፍተኛ ፍጥነት እንዲገባ በማድረግ ነው፡፡ሲፒዩ በጣም ሲግል ኮምፒዉተራችን ሳናስበው እራሱን ይዘጋል ወይም ክራሽ ያደርጋል፡፡

▒▓⇨→መረጃዎች ቶሎ ቶሎ እንዲደርሶት ስልኮቻችሁ ላይ ላሉ
❖ Contact
❖ Group and Channel share አድርጉለን ከምስጋና ጋር።
━━━━━━━━━━━━━━━
📢: t.me/TechnologyMasterPage
👥: @EthioWorldwideStudents
━━━━━━━━━━━━━━━
▬▬▬▬▬📌Share📌▬▬▬▬▬
👏1
ትዝብቴን በብዕር

በድስት ያለ ውሃ በእሳት ወይም በእስትቭ ተጥዶ በሚተከተክ ወቅት ቀዝቃዛ የሆነ ውኃ እላይ-ላዩ ስንጨምርበት፣ ልክ መብራት ድንገት ጠፍቶ ብዙ ነገሮች ሰጥ ረጭ እንደ ሚሉት፤ የጣድነው ውኃም መንተክተኩን ያቆማል!!

➝ ታዲያ እኛ በንዴታችን ላይ የመረጋጋትንና የማስተዋልን «ውኃ አንደፋበትም!?»

በረሻድ ሙዘሚል

ትዝብቴን በብዕር

በድስት ያለ ውሃ በእሳት ወይም በእስትቭ ተጥዶ በሚተከተክ ወቅት ቀዝቃዛ የሆነ ውኃ እላይ-ላዩ ስንጨምርበት፣ ልክ መብራት ድንገት ጠፍቶ ብዙ ነገሮች ሰጥ ረጭ እንደ ሚሉት፤ የጣድነው ውኃም መንተክተኩን ያቆማል!!

➝ ታዲያ እኛ በንዴታችን ላይ የመረጋጋትንና የማስተዋልን «ውኃ አንደፋበትም!?»

በረሻድ ሙዘሚል

● ሙሉውን ለማንበብ ▼

t.me/EthioWorldwideStudents/5622
📱 የስልክዎት ፍጥነት እየዘገየ አስቸገረዎት?
የስልክዎን ፍጥነት ወደቀድመው ለመመለስ እነዚህን ቀላል የሆኑ ዘዴዎችን ይጠቀሙ፡፡

1. ችግሩን ለመለየት ይሞክሩ
የስልክ ፍጥነት ችግር በበርካታ ምክንያቶች ሊመጣ ይችላል፡፡
እነዚህን ችግሮች ምናልባት የተከሰቱት ኮራብት በሆኑ አፕልከሽኖችና ፋይሎች፤በRAMና በstorage መጣበብ ወይም በቫይረስ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ እነዚህን ችግሮች በተለያዩ አፕሊኬሽኖች ማወቅ ስንችል የቅርብ ግዜ(latest) የሆኑ ስልኮች እራሳቸው cleaner አላቸው።
በነዚህ አፕልኬሽኖች ታግዘው የስልክዎን ብቃት
(performance) ሪፖርት ማየት ይችላሉ፡፡ ቀጥሎም የሚከተሉትን ዘዴዎችን ይሞክሩ፡፡

2. አላስፈላጊ የሆኑ አፕልከሽኖችን ያጥፉ
ተጠቅመው የማያውቅትን አፕልከሽኖችን ያጥፉ ወይም freeze ያርጓቸው(ለ latest ስልኮች)

3. የአፕልከሽኖችን cach data ያጥፉ ካች ዳታ ማለት አፕልከሽኖች ለሌላ ጊዜ ለፍጥነት እንዲረዳቸው
በራሳቸው የሚያስቀምጡት ዳታ ነው ነገር ግን ይህ ዳታ እየበዛ ስሄድ የስልኩን የውስጥ storage ቦታ በከፍተኛ ሁኔታ ሊይዝ ይችላል።
ካች ዳታ ለማጥፋት setting =>apps(all application) ውስጥ ገብተን በየአንዳንዱ አፕልኬሽን ውስጥ እየገባን "clear cache" የምለውን በመምረጥ ካች ዳታ ማጥፋት ይቻላል፡፡

4. የስልክዎን ስቶረጅ( storage ) ያጽዱ
የስልክዎ storage አላስፈላጊ በሆኑ ፋይሎች ተጣቦ ሊሆን ይችላል። እነዚህን ፋይሎች ማጥፋት በተለይም የስልኩን የውስጥ ስቶሬጅ(internal storage) ማጥፋት ለስልክዎ ስራ ጥሩ የመተንፈሻ ቦታ ይሰጣል፡፡

5. (widgets), በአንመሽን የተሞሉ launcher እና(animated launchers and live wallpapers ) አይጠቀሙ። ውድጌቶች(widgets), በአንመሽን የተሞሉ ላውንቸረችንና ዋልፔፐሮች(animated launchers and live wallpapers ) የስልካችንን ራምና ፕሮሰሰር ሊያጣብቡና ሊያጨናንቁ ስለሚችሉ ውድጌቶችን ያለመጠቀም ይምረጣል፡፡ በተጨማሪም ውድጌቶች(widgets), በአንመሽን የተሞሉ
ላውንቸረችንና ዋልፐፐሮች(animated launchers and live wallpapers ) የባትሪ ጠላቶች ናቸው፡፡

6. በአንዴ ብዙ አፕልከሽኖችን አይጠቀሙ
በአንዴ ብዙ አፕልከሽኖችን መክፈት ከስልካችን አቅም በላይ ሆኖ የስልኩን ፕሮሰሰርና ራም ልያጨናንቅና ልያስቸግር ይችላል፡፡ስለዚህ በአንዴ ብዙ አፕልከሽኖችን አይጠቀሙ፡፡

7. ፎርማት(format) ያድርጉ (ፋክተሪ ሪሲት)
ከላይ የተጠቀሱት መፍትሄዎች አንድሮይድ ስልክዎን ፍጥነት ልያሻሽሉ ይችላሉ ነገር ግን ሙሉ በሙሉ ልያጠፉ አይችሉም፡፡
ፎርማት(format) ማድረግ ግን ወደ ቀድመው ፍጥንት ልመልስ ይችላል፡፡ ነገር ግን ስልከዎን ፎርማት ከማድረገዎ በፊት ባክአፕ
(backup) ማድረግ የግድ ነው።

t.me/EthioWorldwideStudents

t.me/TechnologyMasterPage
💢 ሞባይል ባትሪና ቻርጀር ስንገዛ ኦርጅናልና ፌክ ኮፒ
መሆኑን እንዴት ማወቅ (መለየት) እንደምንችል እነሆ...⬇️⬇️⬇️

✔️ከሌሎች በይበልጥ ሳምሰንግ ስልኮች ተፈላጊነታቸዉ እየጨመረ በመጣ ቁጥር፣ ከኦርጂናሉ ጋር ተመሳስለዉ በቻይና የሚመረቱ ፌክ ሳምሰንግ ስልኮችም📱 በዛዉ መጠን ይጨምራሉ፡፡

🔆ሳምሰንግ የጉግልን አንድሮይድ ኦፐሬቲንግ ሲስተም ይጠቃማል፣ የአንድሮይድ ሲስተም ኮድ ደግሞ ማንኛዉም ፍላጎት ያለዉ አካል ኮዱን እንዲጠቀም የሚያስችል
ፍቃድ ስለሚሰጥ፣ አጭበርባሪ ድርጅቶች ከኦርጂናሉ ስልክ ከፍተኛ ቅናሽ ያለዉን ተመሳሳይ ፌክ ሳምሰንግ ስልክ በማምረት ገበያዉን ያጥለቀልቁታል፡፡

⚠️ኦርጂናሉን ስልክ ከፌኩ በቀላሉ መለየት ያስቸግራል፣ ነገር ግን እነዚህን 👇 መንገዶች በመጠቀም ፌክ ሳምሰንግ
ስልኮችን መለየት ይችላሉ...

የስልኩን ቀፎ አካላዊ ገጽታዎች በመገምገም 👇

💢
#ፌክ ሳምሰንግ ስልክ፡

1⃣. የስክሪኑ መስታወት ጥራት የለዉም‼️

2⃣. ስክሪኑ ከቀፎዉ ጠርዝ በጣም ይርቃል‼️

3⃣. ስክሪኑ ድምቀት ይጎድለዋል‼️

4⃣. የሳምሰንግ ሎጎ (ሳምሰንግ የሚለዉ ጽሁፍ) ሲነካ
ይሻክራል፣ በደንብ ከተጫኑት ይለቃል‼️

5⃣. ከኦርጂናል ስልኮች ጋር ሲያስተያዩት፤ የባትሪ መክደኛዉን ሲከፍቱ የሚታዩ ትንንሽ አካሎች እና ባትሪዉ ላይ የሚገኙት መረጃዎች የተለያዩ መሆናቸዉን ይመለከታሉ‼️

የስልኩን ፍጥነት እና የትእዞች አፈጻፀም በመገምገም *

1⃣. በስልኩ ፎቶዎችን ለማንሳት ይሞክሩ፣ በፌክ ሳምሰንግ
ስልኮች የሚያነሱት ፎቶ ጥራት የወረደ ይሆናል 😡

2⃣. በተመሳሳይ ጊዜ በርካታ ጌሞች 🎮 እና አፕሊኬሽኖችን
ለመክፈት ይሞክሩ፣ ፌክ ስልኮች ስታክ(ቀጥ) የማለት ባህሪይ ያሳያሉ፡፡ 😡😡

3⃣. ስልኩን አጥፍተዉ ያብሩት፣ ፌክ ስልኮች ቶሎ አይከፍቱም😡😡😡

የስልኩን የምርት መረጃዎች በመገምገም *

1⃣. ወደ ዋናዉ ማዉጫ ይሂዱ እና አፕስ(Apps) የሚለዉን ቁልፍ ይጫኑ...

2⃣. ከአፕሊኬሽን ማዉጫዉ ላይ፣ Settings የሚለዉን ይጫኑ...

3⃣. ከ Settings ላይ More የሚለዉን ይጫኑ እና Storage የሚለዉን በመጫን ስልኩ ላይ መጫን ሚችሉትን የዳታ መጠን ይመልከቱ፤ ከኦርጂናሎቹ ስልኮች በጣም ያነሰ ከሆነ ፌክ መሆኑን ያረጋግጣሉ፡፡

4⃣. እንዲሁም About device የሚለዉን ይጫኑ እና
የስልኩን ሞዴል ቁጥር እና baseband, build number
ጉግል ላይ ይፈልጉት፣ የሚያገኙት መልስ ፌክ ወይም ኦርጅናል መሆኑን ይነግሮታል፡፡

የሳምሰንግ ኮዶችን በመጠቀም *

💢ወደ ስልክ📱 መደወያዉ በመሄድ፣ ከዚህ በታች የተጠቀሱትን ኮዶች ያስገቡ እና Call የሚለዉን ይጫኑ፤ ስልኩ
ያስገቡትን ኮድ አዉቆ መልስ መስጠት ከቻለ ኦርጅናል ✔️
መሆኑን ያረጋግጣሉ፡፡ ካልሆነ ግን 😭 ፌክ ስልክ ነዉ፡፡

1⃣. *#0*# 👉 አጠቃላይ መገምገሚያ

2⃣. *#1234# or *#9999# 👉 ስልኩ የሚጠቀመዉን
ሶፍትዌር እና ሞደም ማወቂያ

3⃣. *#12580*369# 👉 ስለ ስልኩ ሶፍትዌር እና ሀርድዌር ማወቂያ

4⃣. *#06# 👉 የስልኩን ኢንተርናሽናል መለያ ቁጥር
ማወቂያ

5⃣. *#9998*246# 👉 የስልኩን የባትሪ እና ሚሞሪ መረጃዎች ማወቂያ

ሳምሰንግ ኪይስ(Samsung Kies) ሶፍትዌርን በመጠቀም *

💢ከላይ 👆 በተጠቀሱት መንገዶች ፌክ ሳምሰንግ ስልክን መለየት ካልቻሉ ይህን ሶፍትዌር ይጠቀሙት፡፡

1⃣. Samsung Kies ሶፍትዌርን ኮምፒዉተሮት💻 ላይ
ይጫኑት...

2⃣. ለማረጋገጥ የፈለጉትን ስልክ ከኮምፒዉተሮት ጋር ያገኛኙት

3⃣. ሶፍትዌሩ ስልኩን 📱ያነበዉ እና የስልኩን ስም ፣የሚጠቀመዉን ሶፍትዌር እና ሀርድዌር ያሳያል
ሶፍትዌሩ ስልኩን ማንበብ ካልቻለ በድጋሚ ይሞክሩት በድጋሚ ማንበብ ካልቻለ ሰልኩ ፌክ መሆኑን ያረጋግጣሉ፡፡😭😭

▒▓⇨→መረጃዎች ቶሎ ቶሎ እንዲደርሶት ስልኮቻችሁ ላይ ላሉ
❖ Contact
❖ Group and Channel share አድርጉለን ከምስጋና ጋር።
━━━━━━━━━━━━━━━
📢:
t.me/EthioWorldwideStudents
👥:
t.me/TechnologyMasterPage
━━━
━━━━━━━━━━━
▬▬▬▬▬📌Share
📌▬▬▬▬▬
3