Basic Computer Skills
Photo
◆ 7. የፈተናው ቀን ስነ-ልቦና (Exam Day Mindset)
በፈተናው ቀን ከምንሰራው ጥያቄ እኩል ስነ-ልቦናችን ወሳኝነት አለው። ፈተናው ክፍል ውስጥ ስንገባ የሚኖረውን መደናገጥ ማርገብ ይኖርብናል።
♦️ ተግባራዊ ስልት (Action Step):
● ፈተናው ሲከፋፈል ጥልቅ ትንፋሽ (Deep breath) በመውሰድ እንረጋጋ።
● ጊዜያችንን ለመቆጠብ፣ ከከባድ ጥያቄዎች ይልቅ በቀላሉና በፍጥነት ልንሰራቸው ከምንችላቸው ጥያቄዎች እንጀምር።
⁉️ የነፍስ ጥያቄ: ፈተናውን የምናየው ፍርሃት በሚፈጥር መልኩ ነው ወይስ የዝግጅታችንን ፍሬ የምናሳይበት እድል አድርገን ነው?
◆ 8. የወላጆች ሚና፡ የስኬት ደጀንነት
እኛ ወላጆች የልጆቻችን ውጤት የሚወሰነው በቤት ውስጥ ባለው ሰላም ጭምር መሆኑን ልንገነዘብ ይገባል። ልጆቻችንን አናስጨንቃቸው፣ ይልቁንም እናበረታታቸው።
♦️ ለወላጆች ተግባር (Action Step):
● ፀጥታ መፍጠር፦ በጥናት ሰዓታቸው ረብሻ እንዳይኖር ማድረግ።
● የሞራል ድጋፍ፦ "እንችላለን/ትችላላችሁ" በማለት በራስ መተማመናቸውን መገንባት።
● ጤናን መጠበቅ፦ የተመጣጠነ ምግብና በቂ እረፍት ማግኘታቸውን ማረጋገጥ።
⁉️ የነፍስ ጥያቄ: ለልጆቻችን የፈተና ዝግጅት እንቅፋት እየሆንን ነው ወይስ አጋዥ?
◆ 9. ጥረት፣ ተወኩልና ዱዓ (The Ultimate Shield)
ጥረታችንን ካደረግን በኋላ፣ ከቁጥጥራችን ውጭ የሆነውን የፈተና ውጤት ለጥበብ ባለቤቱ በመተው (በመመካት) ከጭንቀት ነፃ መሆን አለብን። ስኬት የሚገኘው ከባለቤቱ ከአላህ ዘንድ ነው። በአላህ የመመካትና በኢባዳ የመፅናት ሚስጥር የልብ እርጋታን ይሰጠናል።
♦️ ተግባራዊ ስልት (Action Step):
● አምስቱንም ወቅት ሶላት በወቅቱ መስገድ። ሶላት (ፀሎት) አእምሮን ያረጋጋል፣ ትኩረትን ይጨምራል።
● በዱዓችን ላይ "ያ አላህ! ስኬትን ስጠን" ብለን በቅንነት እንጠይቅ።
📚 የጥበብ ጠብታ (ቁርኣን):
✅ "በአላህም ላይ የሚጠጋ ሰው እርሱ በቂው ነው።" (አል-ጠላቅ፡ 3)
🤲 የዱዓ ጥቆማ: "አላሁመ ላ ሳህለ ኢላ ማ ጃዓልተሁ ሳህላ፣ ወአንተ ተጅዓሉል ሐዝነ ኢዛ ሺእተ ሳህላ" (አላህ ሆይ! አንተ ካገራኸው በስተቀር ምንም ቀላል የለም፤ አንተ ከፈለግክ አስቸጋሪውን ነገር ቀላል ታደርገዋለህ)።
⁉️ የነፍስ ጥያቄ: ጥረታችንን ለአላህ ብለን አድርገን፣ እርሱም ስራችንን እንደማያባክንብን ሙሉ እምነት አለን?
🤲 ዱዓ
ያ አላህ! በጥረታችን ላይ በረካህን ጨምርልን። ለፈተና ከሚቀመጡት ተማሪዎቻችን ጋር ሁን፤ የረሱትን አስታውሳቸው፣ ያልገባቸውን ግለፅላቸው። በፈተናው ቀን ትዝታቸውን አድስላቸው፣ ድካማቸውንም በስኬት አብስርላቸው። ለቤተሰቦቻቸውና ለሀገራቸው ኩራት አድርጋቸው። አሚን!
በአላህ እገዛ አሁኑኑ እንነሳ! ለታላቅ ስኬት እንገስግስ!
✍️ በረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል

❤2
#Telegram_update
ቴሌግራም ሰሞኑን ባስተዋወቀው update አንዳንድ features ያካተተ ሲሆን ከነዚህም መካከል፦
AI Text Editor
ይህ feature telegram ላይ ረዘም ያለ መልእክት በምንፅፍበት ጊዜ Translate ማድረግ፣ በተለያዩ Style መፃፍ እና Grammer fix ማድረግ ያስችላል የተባለም ሲሆን የፃፍነውንም text እንደ formal, Short,Tribal,Corp በመሳሰሉ ስታይሎች style ማድረግ እንደሚያስችልም ተገልጿል።
ይህንንም feature ለመጠቀም የቴሌግራም መተግበሪያን Update ካደረግን በኋላ 3 እና ከዚያ በላይ መስመር message bar ላይ ስንፅፍ የሚመጣውን የAi ምልክት መንካት።
New Features for Polls
Pools ላይ እንደ ፎቶ እና ቪድዮ ያሉ medias ወይም location Attach ማድረግ/ማያያዝ፣ Active በሆኑ polls ላይ ምርጫዎችን ሰዎች suggest እንዲያደርጉ ማስቻል፣ምርጫዎቹ ለየሰው random እደምተከተል እንዲኖራቸው ማድረግ የመሳሰሉ features ተካተዋል።
Document Scanner on iOS
የiOS ቴሌግራም ላይ document scan ማድረግ የሚያስችል feature ሲሆን ይህንንም ለማድረግ attachment menu በመክፈት File የሚለውን መንካት ከዚያም Scan Document የሚለውን መንካት።
©

⭐ የነገው ብርሃን ፋናዎች ተስፋዎች፡ የትውልድ ግንባታና የኢኽላስ ጥበብ
✅ መግቢያ:
ትምህርት ማለት መረጃን ከአንድ አእምሮ ወደ ሌላው ማጋዘን ብቻ ሳይሆን፣ የአላህ ስጦታ የሆኑትን የነገ ኮከቦች ማድመቅና የነፍስን ውበት መቅረጽ ነው። እያንዳንዱ የትምህርት ሂደት፣ እያንዳንዱ በክፍል ውስጥ የሚነገር ቃልና እያንዳንዱ የተቋም ውሳኔ በትውልድ ህይወት ላይ የማይረሳ በጎ አሻራ ያሳርፋል።
ዛሬ የምንገነባቸው ትምህርት ቤቶችና የምንሰጣቸው ትምህርቶች የነገዋን አገርና የነገውን ስብዕና የሚወስኑ የጥበብ ማዕከላት ናቸው። መምህርነትና የትምህርት አመራርነት ደግሞ የሰው ልጅ ሊሰማራባቸው ከሚችሉ ታላላቅና ክቡር ተግባራት መካከል በቀዳሚነት ይጠቀሳሉ።
ይህ ጽሑፍ ዓላማው የዚህን ታላቅ ሙያ ክብርና በውስጡ ያለውን መንፈሳዊ በረከት ማስታወስ ነው። ትምህርትን ከግል ስኬት አልፎ ለኡማውና ለትውልድ የሚተርፍ ታላቅ "ዒባዳ" (አምልኮ) የምናደርግበትን የጥበብ መንገድ አብረን እንቃኛለን። ሁላችንም—መምህራን፣ የተቋም መሪዎችና ወላጆች—እጅ ለእጅ ተያይዘን የነገ አበቦችን (ተማሪዎቻችንን) በኢኽላስና በውበት የምናፈካበትን ብሩህ ተስፋ እንሰንቃለን።
የነገው ስኬት ዛሬ በምንዘራው የቅንነትና የጥበብ ዘር ላይ የተመሰረተ ነው!
♦️ ክፍል አንድ፦ የኒያ (ዓላማ) ኢኽላስ—ስራን ከልማድ ወደ አምልኮ መቀየር
ትምህርት መስጠትም ሆነ የትምህርት ተቋም ማቋቋም ተራ የንግድ ስራ ወይም የዕለት ተዕለት ልማድ አይደለም። የሰው ልጅን አእምሮ መቅረጽ ታላቅ የዒባዳ (አምልኮ) ዘርፍ ነው። ስራው ውጤታማ የሚሆነውና በረከት የሚኖረው ደግሞ "ኒያ" (ዓላማ) ሲስተካከል ነው። ብዙዎች ስራውን የገቢ ምንጭ ብቻ ሲያደርጉት፣ ጥቂቶች ግን አላህ ዘንድ የሚከፈልበት ታላቅ ንግድ ያደርጉታል።
ኒያህን ስታስተካክል ድካምህ ሁሉ አጅር ይሆንልሃል። መምህሩ ወደ ክፍል ሲገባ "ትውልድን ከጨለማ አወጣለሁ" ብሎ ካሰበ እያንዳንዱ ንግግሩ ተስቢህ ይሆንለታል። ተቋሙም "ለኡማው የሚጠቅም ዜጋ አመርታለሁ" ካለ የህንፃው ኪራይና የሰራተኛው ደመወዝ ሁሉ የአላህ መንገድ ወጪ (ፊ ሰቢሊላህ) ይሆንለታል።
ነቢዩ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦
"(ተግባራት ሁሉ የሚለኩት በውሳጣዊ ዓላማቸው (ኒያ) ነው።)" [ቡኻሪና ሙስሊም]
🎤 ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያህ (رحمه الله) እንዲህ ይላሉ፦ "ልብ በትክክለኛ አምልኮና በንጹህ ዓላማ ካልተሞላች፣ በስሜትና በዱንያ ፍቅር ትሞላለች።"
⁉️ የልብ ምርመራ፦ ዛሬ ወደ ስራ ስሰማራ ወይም ተቋሜን ስከፍት ትኩረቴ በፈጣሪ ዘንድ የምሰራው ስራ ላይ ነበር ወይስ በሚገባኝ ገቢ ላይ ብቻ?
📍ተግባራዊ እርምጃ፦ ዛሬ ስራ ከመጀመርህ በፊት "ጌታዬ ሆይ! ስራዬን ለአንተ ብዬ የሰራሁት አድርግልኝ" የሚል ኒያህን በልብህ አድስ።
♦️ክፍል ሁለት፦ የነገ አበቦች አጸድ — የተማሪዎች ክብርና የነፍስ ዋጋ
ተማሪዎቻችን በጃችን ያሉ አደራዎች (አማናህ) ናቸው። እንደ አትክልተኛ አበቦቹን እንደሚንከባከብ ሁሉ፣ መምህርና ተቋምም ተማሪዎቹን በስስት ሊያያቸው ይገባል። ተማሪን እንደ "ደንበኛ" ብቻ ማየት ለነፍሱ የሚገባውን ስብዕና መንፈግ ነው። እያንዳንዱ ልጅ በውስጡ ዓለምን ሊቀይር የሚችል ታላቅ አቅም አላህ አስቀምጦበታል።
ተማሪው በትምህርት ቤቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ ሲገኝ አካላዊ ደህንነቱ ብቻ ሳይሆን ስነ-ልቦናዊ ክብሩ ሊጠበቅ ይገባል። ስድብ፣ ዝቅ አድርጎ ማየትና ተስፋን መስለብ የአላህን ስጦታ ማቃለል ነው።
🎤 ኢብኑል ቀይም (رحمه الله) እንዲህ ይላሉ፦ "አስተማሪ ለተማሪው እንደ አባት ነው። ይልቁንም ከመካከለኛው አባት በላይ የነፍስ አባት ነው። ምክንያቱም አባት ለዚህች ዓለም ህይወት ሰበብ ሲሆን፣ መምህር ግን ለዘላለም ህይወት ስኬት ሰበብ ነው።"
⁉️ የልብ ምርመራ፦ ዛሬ ተማሪዎቼን ሳያቸው የአላህ አደራዎች መሆናቸውን አስታውሻለሁ ወይስ የክፍያ መታወቂያቸውን?
📍ተግባራዊ እርምጃ፦ ዛሬ በክፍልህ ውስጥ ዝቅ ተደርጎ የሚታይ ወይም ተስፋ የቆረጠ ተማሪ ካለ ለብቻው አግኝተህ አበረታታው።
♦️ክፍል ሶስት፦ ከብር ጩኸት በላይ የነፍስ ጸጥታ — የቁሳዊነትን ሰንሰለት መስበር
ሀብት መፈለግ በራሱ ክፋት የለውም፤ ነገር ግን ሀብት "ብቸኛ ዓላማ" ሲሆንና ትውልድን "መሸቀጫ" ሲያደርገው አደጋው ይጀምራል። የትምህርት ጥራትና የተማሪዎች ስኬት በገቢ ስሌት ውስጥ ሲጨፈለቁ፣ የምንገነባው ህንፃ እንጂ ስብዕና አይሆንም። ቁሳዊነት ሲነግስ መምህሩ ለደመወዙ ብቻ፣ ተቋሙ ለትርፉ ብቻ የሚሮጡ ከሆነ ትምህርቱ በረከቱን ያጣል።
ቁርዓን እንዲህ ያስጠነቅቃል፡
"ገንዘብና ልጆች የቅርቢቱ ሕይወት ጌጦች ናቸው፤ ቀሪዎቹ መልካም ሥራዎች ግን ጌታህ ዘንድ በምንዳ በላጭ ናቸው።" (አል-ካህፍ፡ 46)
🎤 ኢማሙ አሻፊዒይ (رحمه الله) እንዲህ ይላሉ፦ "ዕውቀትን ለዱንያ ጥቅም ብሎ የፈለገ ሰው ዕውቀቱ አይባረክለትም። ዕውቀትን ነፍሱን ለማነጽና ሰዎችን ለመጥቀም የፈለገ ግን ስኬታማ ይሆናል።"
⁉️ የልብ ምርመራ፦ ዛሬ ያገኘሁት ትርፍ ነገ አላህ ፊት የሚያስጠይቀኝ ይሆን ወይስ የሚያስመሰግነኝ?
📍 ተግባራዊ እርምጃ፦ ዛሬ ለትርፍ ስትል ጥራት ልታጓድል የምትችልባቸውን አጋጣሚዎች በታማኝነት እለፋቸው።
♦️ክፍል አራት፦ የነቢያት ተተኪዎች — የመምህርነት ልዕልናና የአደራው ክብደት
መምህርነት ተራ ስራ አይደለም። ነቢያት ወርቅና ብርን አላወረሱም፤ ዕውቀትንና ስነ-ምግባርን እንጂ። መምህራንና የትምህርት ተቋማት መሪዎች የዚህ ታላቅ ውርስ ተረካቢዎች ናቸው። መምህር በክፍል ውስጥ ሲቆም የነቢያትን ስራ እየሰራ መሆኑን ማሰብ አለበት። ይህ ክብር ደግሞ ትልቅ አደራን ይጭናል።
ተቋማትም ለመምህራን የሚገባቸውን ክብርና ማበረታቻ ሊሰጡ ይገባል። መምህር ሲከበር እውቀት ይከበራል፤ እውቀት ሲከበር ደግሞ ትውልድ ይከበራል።
🎤 ኢማሙ አህመድ ቢን ሀንበል (رحمه الله) እንዲህ ይላሉ፦ "ዕውቀትን መፈለግ ለሚችል ሰው ከላቁ ስራዎች አንዱ ነው። ይህም ዓላማው ትክክል ሲሆን ነው፤ ማለትም ካለማወቅ ራሱንና ሌላውን ነጻ ለማውጣት ሲያስብ።"
⁉️ የልብ ምርመራ፦ ራሴን የምመለከተው እንደ ተራ ሰራተኛ ነው ወይስ የነቢያት ውርስ ተረካቢና አስተላላፊ?
📍 ተግባራዊ እርምጃ፦ ዛሬ ስታስተምር ተማሪዎችህ እውቀቱን ብቻ ሳይሆን ካንተ ስነ-ምግባርህን እንዲማሩ ምሳሌ ሁን።
♦️ክፍል አምስት፦ ስውሩ ግድያ — ተስፋንና ስብዕናን የመግደል አደጋ
ትውልድን መግደል ሲባል በስለት ማረድ ብቻ አይደለም። የተማሪን ህልም ማጨለም፣ ለገንዘብ ሲባል ጥራትን ማጓደልና ስነ-ምግባርን ችላ ማለት ትውልድን በቁም መግደል ነው። ተቋማት የገንዘብ ማሽን ብቻ ሲሆኑ፣ የተማሪው ነፍስ ትራባለች። መምህር ተማሪውን "አትረባም" ሲለው አንድን ትልቅ ተስፋ እየገደለ መሆኑን ሊያውቅ ይገባል።
🎤 ኢማሙ ማሊክ (رحمه الله) እንዲህ ይላሉ፦ "ዕውቀት ብርሃን ነው፤ አላህ በሚወደው ልብ ውስጥ ብቻ የሚያስቀምጠው።" ይህ ብርሃን እንዳይጠፋ ጥንቃቄ ማድረግ የአደራ ጠባቂነት ግዴታ ነው።
⁉️ የልብ ምርመራ፦ ዛሬ የምሰራው ስራ የተማሪዬን ተስፋ የሚያለመልም ነው ወይስ የሚያከስም?
📍 ተግባራዊ እርምጃ፦ ዛሬ ለተማሪዎችህ በምትናገረው ቃል ውስጥ "ትችትን" ቀንሰህ "ተስፋን" የሚዘሩ ቃላትን አብዛ።

❤1
Basic Computer Skills
Photo
♦️ ክፍል ስድስት፦ የበረከት ሚስጥር— ጥቂት በቅንነት ሲሰራ እንዴት ይበዛል?
ሰዎች ወደ ብር የሚያደሉት "ብዙ ካላገኘሁ አይበቃኝም" በሚል ስጋት ነው። ነገር ግን በረከት (Barakah) ማለት ጥቂቱ ነገር የብዙውን ስራ መስራት መቻሉ ነው። በአሻጥርና ትውልድን ችላ በማለት የሚገኝ ብዙ ሀብት መጨረሻው ውድመትና የልብ መረበሽ ነው። መምህሩ በቅንነት ሲያስተምር የሚሰጠው ጥቂት ደመወዝ ለቤቱ በረከት ይሆንለታል።
ሀብት የሚለካው በቁጥሩ ሳይሆን በውጤቱ (በረከቱ) ነው! በሀላል የሚገኝ ጥቂት ገቢ፣ ሀቅ ተበልቶ ከሚገኝ ብዙ ክምችት ይበልጣል።
⁉️ የልብ ምርመራ፦ በረከት የሌለው ሺህ ብር ይሻለኛል ወይስ በረከት ያለው መቶ ብር? የቤተሰቤንና የነፍሴን ሰላም በየትኛው እፈልገዋለሁ?
📍 ተግባራዊ እርምጃ፦ ዛሬ በገቢህ ውስጥ ላሉ ጥቂት ብሮች ምስጋና (ሹክር) አቅርብ፤ አላህ በረከቱን እንዲጨምርልህም ለምነው።
♦️ ክፍል ሰባት፦ የትውልድ ድልድዮች — የተቋማትና የወላጆች የጋራ አደራ
የትምህርት ተቋም ማለት የህዝብ ተስፋ የሚገነባበት ድልድይ ነው። ይህ ድልድይ ጠንካራ ካልሆነ ማህበረሰቡ ይወድቃል። አመራሮች የትርፍ ስሌታቸውን ከአላህ ውዴታ ስር ሊያደርጉት ይገባል።
ትምህርት ቤት ብቻውን ትውልድ አይቀርጽም። ወላጆች የዚህ ሂደት 50% ባለቤትና ቀዳሚ መምህራን ናቸው። ወላጅ ልጁን ትምህርት ቤት ሲልክ ኒያውን በትክክል ካልቀረጸና ቤቱ ውስጥ የእውቀት ፍቅር ካልዘራ፣ የተቋሙ ጥረት ብቻውን አያዋጣም። ትምህርት ቤትና ቤት የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታዎች መሆን አለባቸው።
🎤 ኢብኑ ባዝ (رحمه الله) እንዲህ ይላሉ፦ "ትውልድን ማረም ማለት ሀገርንና ሃይማኖትን ማረም ነው። ይህ ደግሞ የሚጀምረው ከቁሳዊ ጥቅም በላቀ መልኩ የአላህን ውዴታ ከማስቀደም ነው።"
⁉️ የልብ ምርመራ፦ እንደ ወላጅ ወይም እንደ ተቋም መሪ፣ የተማሪውን ስኬት ከገቢ ስሌት በላይ አድርጌዋለሁ?
📍 ተግባራዊ እርምጃ፦
➤ ዛሬ ለተማሪህ/ለልጅህ ስነ-ምግባር ማማር ከአላህ ፊት ዱዓ አድርግ።
► ዛሬ ልጃችሁ ከትምህርት ቤት ሲመለስ ስለ ውጤቱ ብቻ ሳይሆን፣ "ዛሬ ምን ጥሩ ነገር ሰራህ?" ብላችሁ በመጠየቅ ለስነ-ምግባር ትኩረት ስጡ።
♦️ክፍል ስምንት፦ የአደብ (ስነ-ምግባር) ቀዳሚነት — የዘመኑን ፈተና ማሸነፍ
ትምህርት ያለ አደብ ስልጣን ያለ ፍትህ እንደማለት ነው። ዛሬ መምህራን በተማሪዎች ስነ-ምግባር መበላሸትና በሶሻል ሚዲያ ተጽዕኖ ከፍተኛ ፈተና ውስጥ ይገኛሉ። ተማሪው በትምህርቱ ላይ ትኩረት እንዳያደርግ የቴክኖሎጂ ሱስና የተሳሳቱ የባህል ተጽዕኖዎች ልቡን ሰርቀውታል። ስለዚህ ዛሬ ከመረጃው በፊት "አደብን" ማስቀደም የግድ የሚልበት ወቅት ላይ ነን።
🎤 ኢማሙ ማሊክ (رحمه الله) ለአንድ ወጣት የመከሩት፦ "እውቀትን ከመማርህ በፊት አደብን (ስነ-ምግባርን) ተማር።"
⁉️ የልብ ምርመራ፦ በተማሪዎቼ ውጤት ላይ እንደምጨነቀው ሁሉ በሶሻል ሚዲያ በሚሰረቀው ስነ-ምግባራቸው እጨነቃለሁ?
📍 ተግባራዊ እርምጃ፦ ዛሬ በክፍልህ ውስጥ ተማሪዎች ቴክኖሎጂን ለጥፋት ሳይሆን ለበጎ ተግባር እንዴት እንደሚጠቀሙበት አጭር ምክር ስጥ።
♦️ክፍል ዘጠኝ፦ የማይደርቀው ምንጭ — ሰደቀተል ጃሪያህ ስሌት
ዛሬ በትምህርት ዘርፍ ላይ የምናሳርፈው ማንኛውም በጎ አሻራ እኛ ከሞትን በኋላም የሚከተለን "ሰደቀተል ጃሪያህ" (ተቋራጭ የሌለው ምንዳ) ነው። በአንድ ተማሪ ውስጥ የምንዘራው መልካም ነገር፣ ያ ተማሪ ነገ ለሚሰራው መልካም ስራ ሁሉ እኛም ድርሻ አለን። ይህ ትልቁና ትርፋማው "ቢዝነስ" ነው።
ተቋም ያቋቋመ ሰው ከዚያ ተቋም ተምረው የሚወጡት ተማሪዎች የሚያደርጉት መልካም ስራ ሁሉ በሞተበት ይደርሰዋል። መምህሩም ያስተማረው እውቀት ትውልድ በተሻገረ ቁጥር አጅሩ ይጎርፍለታል።
🎤 አቡ ሃኒፋ (رحمه الله) እንዲህ ይላሉ፦ "መምህርነትና ትምህርት የዱንያ ጌጥ መፈለጊያ ሳይሆን፣ የነፍስ ሐሴትና የተቋረጠውን መልካም ስራ የመቀጠያ መንገድ ነው።"
⁉️ የልብ ምርመራ፦ ከሞትኩ በኋላም የሚከተለኝ ስንቅ ዛሬ እያዘጋጀሁ ነው?
📍 ተግባራዊ እርምጃ፦ ዛሬ ስትሰራ "ይህ ስራ ለነገው ቀብሬ ስንቅ ይሆነኛል" የሚል ፅኑ ተስፋ ይኑርህ።
♦️ክፍል አስር፦ የንጋት ጥሪ — ተስፋ፣ ዱዓና የለውጥ ጅምር
ለውጥ የሚጀምረው ከእኔና ከእናንተ ነው። ዛሬ የምናደርገው ዱዓና የምንወስነው ውሳኔ ለነገው ትውልድ ስኬት መሰረት ነው። ይህ መልዕክት ለማንም ግለሰብ የተሰነዘረ ጦር ሳይሆን፣ ለሁላችንም የቀረበ የፍቅርና የአደራ ጥሪ ነው። አላህ በጎ ሰበቦች ያድርገን።
ማጠቃለያ:
ከኒያ ማስተካከል ጀምሮ እስከ ሰደቀተል ጃሪያህ ድረስ ያለውን ጉዞ ስንመለከት፣ ትምህርት ማለት ተራ ስራ ሳይሆን ዘላለማዊ ትርፍ የሚገኝበት ንግድ መሆኑን እንረዳለን። ዛሬ ከነዚህ አሥር ክፍሎች መካከል አንዲቷን ነጥብ ብቻ በተግባር ላይ ብናውላት፣ በትውልዳችን ላይ ትልቅ ለውጥ እናመጣለን። የነገው ብርሃን ዛሬ በምንዘራው ዘር ውስጥ ነውና ለዘሩ ጥራት እንትጋ።
ዱዓ
አላህ ሆይ! ከንቱና ትውልድን ከሚገድል፣ ተስፋን ከሚያጨልም ስራ ጠብቀን። 🤲
ጌታችን ሆይ! የነገ አበቦችን፣ አንፀባራቂ ኮከቦችን የሚገድል ስራ ከመስራት አላህ ይጠብቀን! 🤲
ትኩረታችንን ዱንያ ሳይሆን ያንተን ፊት ፈልገን ለእነዚያ አበቦችና አንፀባራቂ ኮከቦች (ለተማሪዎቻችን) ስኬትና እድገት የምንተጋ አድርገን። 🤲
የነገው የህይወት ጉዟቸው በስኬት እንዲበሽበሽና እንዲሞላ እኛን በጎ ሰበቦች አድርገን። 🤲
ልባችንን ከቁሳዊ ጥቅም ጥማት አጽዳው፤ ስራችንንም ለሁለቱም ዓለም ስኬት የሚበቃ አድርገው። 🤲
አሚን!
✍️ረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል

2018_E_C_2nd_Semester_ICT_&_CTE_Mid_Exam_Table_of_Specifications.pdf
264.7 KB
📚 2018 E.C የአጋማሽ ፈተና የፈተና ቢጋር (Table of Specification for Mid Exam)
✅ Grade 7 and 8: ICT and CTE
♦️ Paper size: A3
══════════════
✅ በተለይም የሙምታዝ ት/ቤት ተማሪዎች Mid Exam ያዘጋጀሁላችሁ በዚህ መሠረት ስለሆነ ተጠቀሙበት።
✅ አላህ ይርዳችሁ!!
✍️ ረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል
✅ Grade 7 and 8: ICT and CTE
♦️ Paper size: A3
══════════════
✅ በተለይም የሙምታዝ ት/ቤት ተማሪዎች Mid Exam ያዘጋጀሁላችሁ በዚህ መሠረት ስለሆነ ተጠቀሙበት።
✅ አላህ ይርዳችሁ!!
✍️ ረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል
Basic Computer Skills
Photo
✅ Telegram Passkey
ቴሌግራም አካውንታችን ላይ login ለማድረግ የሚያገለግለን የpasskey feature እንዳስተዋወቀ ታውቃላችሁ።
♦️Passkey password-less የsign in መንገድ ሲሆን ባህላዊ የፊደልና የቁጥር የይለፍ ቃሎችን የሚተካ ደህንነቱ የተጠበቀ፣ ፈጣንና ቀላል login መንገድ ነው።
Passkey Public-key cryptographic መንገድ ስለሚጠቀም ከጣትና ከፊት አሻራችን እንዲሁም የscreen ፒንና ፓተርን የተያያዘ private key የቀፏችን ሃርድዌር ላይ ይቀመጣል።
ስለዚህ ማንኛውንም የPasskey feature ያለው አፕሊኬሽን ስልካችን android ከሆነ ከGoogle password manager ጋር iphone ከሆነ ደግሞ ከiCloud Keychain ጋር በማገናኘት መጠቀም ይቻላል።
♦️Passkey መጠቀም ብዙ ጥቅም አለው።
✔️ፊደል ወይም ቁጥር ስላልሆነ ልንረሳው አንችልም።
✔️ለፊሺንግ ጥቃት የተጋለጠ አይደለም።
✔️ሰርቨር ላይ አይቀመጥም።
አዲስ ስልክ ስንቀይርስ እንዴት login ማድረግ እንችላለን?
አዲስ ስልክ ቀይረን በGoogle አካውንታችን login ስናደርግ ፓስኪን ጨምሮ ሁሉም ከgoogle አካውንታችን ጋር የተገናኙ አካውንቶችን መጠቀም እንችላለን።
ስለዚህ የGoogle አካውንታችንን(Gmail) እንደ አይን ብሌን መጠበቅ ይኖርብናል። እዚጋ መታወቅ ያለበት google አካውንታችን ሃክ ቢደረግ ራሱ የሞላነው Passkey ግን safe ነው።
♦️ይህ የPasskey feature በአዲስም ሆነ በነባር የስልክ ቀፏቸን ላይ ስልክ ቁጥር ማስገባት ሳይጠበቅብን ቴሌግራም አካውንታችን ላይ login ለማድረግ ይጠቅመናል።
ነገር ግን ብዙ ሰው passkey እና 2-step verification ትዝ የሚለው አካውንቱ ሃክ ከተደረገ በኋላ ነው።
ስለዚህ አሁኑኑ ቴሌግራም አካውንታችንን passkey register ማድረግ አለብን።
ይህን ለማድረግ
⚫ Settings -- Privacy and Security -- Passkey
አሁኑኑ አስተካክሉት።
©️

❤3
📚 የ8ኛ ክፍል በቪድዮ የተለቀቁ የትምህርት አይነቶች (ምዕራፎች)
✅ ማስፈንጠሪያዎቹን (ሊንኮቹን) በመንካት ቪድዮዎቹን በቻናሉ ማግኘት ትችላላችሁ!!
📚 Grade 8 General Science: Unit 2 (6 ቪድዮዎች)
https://t.me/Grade8Info/1398?single
📚 Grade 8 General Science: Unit 3 (2 ቪድዮዎች)
https://t.me/Grade8Info/1535?single
📚 Grade 8 General Science Unit 4 (11 ቪድዮዎች)
https://t.me/Grade8Info/1440
📚 Grade 8 General Science Unit 5, 6 and 7 (ሶስቱም ምዕራፎች በአንድ ቪድዮ)
https://t.me/Grade8Info/1901
📚 Grade 8 Social Studies Unit 1 (2 ቪድዮዎች)
https://t.me/Grade8Info/1480
📚 Grade 8 Social Studies Unit 4 (6 ቪድዮዎች)
https://t.me/Grade8Info/1895?single
📚 Grade 8 Social Studies Unit 5 (6 ቪድዮዎች)
https://t.me/Grade8Info/1453
📚 Grade 8 Social Studies Unit 6 (8 ቪድዮዎች)
https://t.me/Grade8Info/1453
📚 Grade 8 Social Studies Unit 7 (3 ቪድዮዎች)
https://t.me/Grade8Info/1453
📚 Grade 8 Mathematics Unit 4 (11 ቪድዮዎች)
https://t.me/Grade8Info/1542
📚 Grade 8 Mathematics Unit 1 - 4 Review Exercise with Explanation (አራቱም ምዕራፎች በአንድ ቪድዮ)
https://t.me/Grade8Info/1908
📚 Grade 8 Citizenship Unit 2 (4 ቪድዮዎች)
https://t.me/Grade8Info/1480
📚 Grade 7 English All Review Questions
t.me/Grade8Info/2120
📚 Review English Questions from Grade 6, 7 and 8
✅ Part 1
https://t.me/Grade8Info/2121

✅ Part 2
https://t.me/Grade8Info/2123

✅ Part 3
https://t.me/Grade8Info/2124
══════════════
🌟 ውድ ተማሪዎቻችን፣ የልፋታችሁን ፍሬ የምታጭዱበት ወርቃማው ወቅት ቀርቧል! 🌟
ትኩረታችሁን ሙሉ በሙሉ በንባብ ላይ አድርጉ፤ ጊዜያችሁንም በአግባቡ ተጠቀሙ። አላህ መንገዱን እንዲያገራላችሁና የጣራችሁለትን ስኬት እንዲሰጣችሁ ዱዓችን ነው። 🤲📖

❤3🤔1
ለቴሌግራም ተጠቃሚዎች በሙሉ፤ ጥብቅ ማሳሰቢያ‼
==============================
(አካውንታችሁ ሀክ ተደርጎ አጸያፊ ነገሮች ከመላካቸው በፊት አሁኑኑ አንብቡት)
||
✍️ ሰሞኑን የብዙ ወንድምና እህቶች የቴሌግራም አካውንት እየተጠለፈ (Hack እየተደረገ) በተለያዩ ግሩፖች፣ ቻናሎች እና በውስጥ መስመር Inbox ላይ አጸያፊ እና ሐራም የሆኑ ሊንኮች በስማቸው እየተላኩ ነው። ይህ ድርጊት የሰዎችን ክብር ከማጉደፍም ባለፈ፣ ወዳጅ ዘመድን ለማያስፈልግ ፈተና እና ለሐራም እይታ እያጋለጠ ይገኛል።
✅ ይህ ሁሉ ችግር ከየት መጣ⁉️
ዋናው የችግሩ ምንጭ ብዙዎቻችን ኦፊሴላዊውን የቴሌግራም መተግበሪያ ትተን ሌሎች ቴሌግራም መሰል የዘ
ሦስተኛ ወገን (Unofficial) አፖችን መጠቀም መጀመራችን ነው። እነዚህ አፖች (ለምሳሌ፦ Nicegram, Mobogram, Vidogram, Plus, Huligram, Telega ወዘተ) የእናንተን የግል መረጃ አሳልፈው ለሌቦች የሚሰጡ አደገኛ መተግበሪያዎች ናቸው።
➤ ቴሌግራም ኩባንያም ይህን በመረዳት እነዚህን አፖች በሚጠቀሙ ሰዎች ፕሮፋይል ላይ "Warning Label" (የማስጠንቀቂያ ምልክት) ማሳየት ጀምሯል። እርምጃ ካልወሰዳችሁ አካውንታችሁ በዘላቂነት ሊዘጋ ይችላል!
እነዚህን አፖች መጠቀም ምን አደጋ አለው?
♦️ የመረጃ ስርቆት፦ የግል ሚስጥራችሁ፣ ፎቶዎቻችሁ እና መልዕክቶቻችሁ በሌሎች እጅ ይወድቃሉ።
♦️ አካውንት መነጠቅ፦ የይለፍ ቃል (OTP Code) በመስረቅ አካውንታችሁን ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥረው፣ በናንተ ስም ወንጀልና ማጭበርበር ይሰራሉ።
♦️ ያለፍቃድ ግሩፕ መግባት፦ ሳታውቁት የተለያዩ የክሪፕቶ፣ የፕሮፖጋንዳ እና የብልግና ግሩፖች ውስጥ ያስገቧችኋል።
✅ መፍትሄው ምንድን ነው? አሁኑኑ ማድረግ ያለባችሁ 3 ወሳኝ እርምጃዎች፦
❶ ትክክለኛውን ቴሌግራም ብቻ ተጠቀሙ:
አሁኑኑ ስልካችሁ ላይ ያሉትን ኦፊሴላዊ ያልሆኑ አፖች (Nicegram, Mobogram...) አጥፉና (Uninstall አድርጉና)፣ ትክክለኛውን በሰማያዊ ምልክት የሚታወቀውን "Telegram" ከፕሌይስቶር ወይም ከአፕስቶር ላይ ብቻ አውርዳችሁ ተጠቀሙ።
❷ አሁኑኑ ሌቦችን ከአካውንታችሁ አስወጡ (Terminate Sessions)
አካውንታችሁ ሀክ መደረጉን ለማወቅ እና ለማስወጣት ይህንን ተከተሉ፦
ወደ ቴሌግራም Settings ግቡ።
Devices (ወይም Privacy and Security ገብታችሁ Active Sessions) የሚለውን ተጫኑ።
እዛ ላይ ከእናንተ ስልክ ውጪ የገቡ ሌሎች መሳሪያዎች (ኮምፒዩተርም ሆነ ሌላ ስልክ) ካያችሁ ወዲያውኑ "Terminate All Other Sessions" የሚለውን ቀይ ጽሑፍ ተጭናችሁ ሁሉንም አስወጡ!
❸ Two-Step Verification አብሩ:
አካውንታችሁን ማንም ሰው እንዳይገባበት በፓስዎርድ ቆልፉት። (Settings > Privacy and Security > Two-Step Verification ገብታችሁ ፓስዎርድ አስገቡ)።
➤ ያላወቀው እንዲያውቅ፣ የተዘናጋውም እንዲነቃ ይህንን ወሳኝ መልዕክት ለወዳጅ ዘመድዎ Share በማድረግ ከስርቆት እና ከሐራም ድርጊቶች እንታደጋቸው!
©️ Murad Tadesse

📢 የልጆቻችን ስኬት "ሁለገብ" ቀመር
መግቢያ፦
ውድና የተከበራችሁ ወላጆች፤ ልጆቻችንን ወደ ትምህርት ቤት ስንልካቸው አእምሯቸውን ለዕውቀት፣ ልባቸውን ለሥነ-ምግባር አሳልፈን እየሰጠን ነው። ነገር ግን ትምህርት ቤት ዘሩን የሚዘራበት "ማሳ" እንጂ፣ ፍሬው እንዲበቅል የሚያደርገው ብቸኛው "ዝናብ" አይደለም። እውነተኛው ለውጥ የሚመጣው በትምህርት ቤት የተጀመረው ብርሃን በቤት ውስጥ ባለው የጥናት ሥርዓትና በወላጆች ጥበብ የታከለበት ክትትል ሲታጀብ ከሁሉ በላይ ደግሞ በጌታችን አላህ (ሱ.ወ) እገዛና በረካ ሲባረክ ብቻ ነው።
ይህ መልዕክት ውጤት ላይ ብቻ ያተኮረውን ጭንቀት ገሸሽ አድርጎ፣ በአላህ ፈቃድ ለልጆቻችን ስኬት መሠረት የሚሆንና የልብ ለልብ ጥሪን የሚያስተላልፍ መመሪያ ነው።
ክፍል 1፦ የትምህርት ቤትና የቤት "ቅንጅታዊ ሚስጥር"
ትምህርት ቤት መሄድና ወርሃዊ ክፍያን መክፈል የተማሪን ሕይወት ለመቀየር የመጀመርያው እርምጃ እንጂ የመጨረሻው ግብ አይደለም። ብዙዎቻችን "ውድ ትምህርት ቤት አስገብተን ለምን ለውጥ የለም?" ብለን እንጠይቃለን። እውነታው ግን፤ እውቀት በትምህርት ቤት ተቀምሮ ቤት ውስጥ ካልተከለሰ፣ ልክ እንደ ውሃ ላይ ምስል ቶሎ ይረሳል። ትምህርት ቤት ግብዓትን (Information) ይሰጣል፤ ቤት ደግሞ ያንን መረጃ ወደ እውቀት (Knowledge) እና ወደ ስብዕና (Character) የሚቀይርበት ማብሰያ ኩሽና ነው።
ያለ ቤት እገዛ ትምህርት ቤት ብቻውን እንዲለወጥ መጠበቅ፣ ያለ ውሃ መሬት ላይ ዘር ጥሎ ፍሬ እንደመጠበቅ ነው። እውቀት በክፍል ውስጥ ይዘራል፣ በቤት ውስጥ ይኮተኮታል፣ በፈተና ወቅት ደግሞ ይታጨዳል። ኮተኮታው (ቤት ውስጥ ያለው ክትትል) ከሌለ ግን አዝመራው እንክርዳድ የመሆን ዕድሉ ሰፊ ነው።
♦️ ከዚህም ባለፈ ወላጆች በዓመት አንዴ የካርድ ቀን ብቻ ሳይሆን፣ አልፎ አልፎ ትምህርት ቤት ብቅ እያሉ ከመምህራን ጋር አጫጭር ውይይት በማድረግ የልጆቻቸውን ጠንካራና ደካማ ጎን በትብብር መከታተል አለባቸው።
🎤 ታላቁ ሊቅ ሼይኩል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያህ (ረሂመሁላህ) እንዲህ ይላሉ፦ "እውቀት ማለት መረጃን መደርደር ሳይሆን፣ አላህ በልብ ውስጥ የሚጥለውና ወደ ተግባር የሚመራ ብርሃን ነው።" ይህ ብርሃን ደግሞ በወላጅ ፍቅርና ክትትል ካልታጀበ በስተቀር በትምህርት ቤቱ ድካም ብቻ አይመጣም።
⁉️ የነፍስ ጥያቄ፦ እኔ ለልጄ "ወላጅ" ነኝ ወይስ "ባንክ"? ልጄ ከትምህርት ቤት ሲመጣ የምጠይቀው ስለደኅንነቱ ነው ወይስ ስለ ውጤቱ?
🔶 የተግባር እርምጃ፦ ዛሬ ማታ ልጃችሁ ሲመጣ ቢያንስ ለ 15 ደቂቃ ስለ ውጤት ሳታነሱ፣ ትምህርት ቤት ውስጥ ስላሳለፈው ስሜትና ስለገጠመው አዲስ ነገር ብቻ በጥሞና አዳምጡት።
ክፍል 2፦ የ"በረካማ ወቅቶች" እና የአእምሮ ፊዚዮሎጂ
በትምህርት ቤቱ በኩል በኮሙኒኬሽን ደብተራቸው ላይ የተዘጋጀው የጥናት ፕሮግራም ሁለት ወሳኝ ወቅቶችን ታሳቢ ያደረገ ነው። ከሱብሂ በኋላ (ጧት) አእምሮ አዲስ መረጃን ለመቅዳት ንጹሕ ነው፤ ከኢሻዕ በኋላ (ማታ) ደግሞ የዋለበትን ትምህርት በአእምሮው ውስጥ ለማደራጀት (Memory Consolidation) ወሳኝ ሰዓት ነው። አእምሮአችን እንደ ባትሪ ነው። ጧት ላይ ሙሉ ኃይል አለው፤ ማታ ላይ ደግሞ ተሞልቶ (በእንቅልፍ) ራሱን እንዲያድስ ይፈልጋል።
ሳይንሱ እንደሚነግረን በጧት ክፍለ ጊዜ የአእምሮ ንቃት ደረጃ (Alertness) እጅግ ከፍተኛ ነው። በዚህ ሰዓት የሚጠና ትምህርት በቀላሉ የመያዝ ዕድሉ ሰፊ ነው። ማታ ላይ ደግሞ አእምሮ ወደ ጥልቅ እንቅልፍ ከመሄዱ በፊት ያነበበውን ነገር እንደ ፋይል የማደራጀት ተፈጥሮ አለው። ልጆቻችን ጧት ተኝተው የሚረፍዱ ከሆነ፣ ቀኑን ሙሉ የዛለና ያልተነቃቃ አእምሮ ይዘው ነው የሚውሉት።
▶ የአላህ መልክተኛ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦
❝አላህ ሆይ! ለኡመቴ በጧት ጊዜያቸው ላይ በረካን አድርግላቸው።❞ [አቡ ዳውድና ቲርሚዚ ዘግበውታል]
⁉️ የነፍስ ጥያቄ፦ የቤቴ ድባብ ለበረካማው የጧት ጊዜ ምቹ ነው? ወይስ ልጆቼ በእንቅልፍ እጦት እየዛሉ ነው የሚነቁት?
ክፍል 3፦ የጥናት ቀመር፦ ጥራት ከሰዓት ይበልጣል
ልጆቻችን እንዲያጠኑ ስንነግራቸው "ለሰዓታት ተቀመጡ" ማለት ሳይሆን "በትኩረት ስሩ" ማለት ነው። በትምህርት ቤቱ የተዘጋጀው የጥናት ቀመር ሳይንሳዊ መሠረት አለው። የአንድ ተማሪ ትኩረት (Attention Span) ውሱን ነው። አእምሮ ልክ እንደ ጡንቻ ነው፤ ለረጅም ሰዓት ያለ እረፍት ሲሠራ ይዝላል።
◉ በፕሮግራሙ መሠረት ልጆች ማታ ላይ ብቻ ሊያጠኑ የሚገባው የጊዜ እርዝማኔ፦
♦️ 1ኛ እና 2ኛ ክፍል፦ለማታ ጥናት 1፡30 ሰዓት
♦️ 3ኛ እና 4ኛ ክፍል፦ ለማታ ጥናት 2፡15 ሰዓት
♦️ 5ኛ እና 6ኛ ክፍል፦ ለማታ ጥናት 2፡30 ሰዓት
♦️ 7ኛ እና 8ኛ ክፍል፦ለማታ ጥናት 2፡45 ሰዓት
የፖሞዶሮ (Pomodoro) ቴክኒክ እንደሚያረጋግጠው፣ አእምሮ ለረጅም ሰዓት ካለእረፍት እንዲያጠና ከተገደደ፣ መረጃን ከመቀበል ይልቅ ራሱን መከላከል (Shut down) ይጀምራል። አጫጭር እረፍቶች አእምሮን እንደገና ለማነቃቃት (Brain Reboot) ይረዳሉ። ታዋቂው የፈጠራ ሰው ቶማስ ኤዲሰን እንኳ ለረጅም ሰዓት ከመሥራት ይልቅ አጫጭር እረፍቶችን በመውሰድ ለፈጠራ አእምሮውን ያድስ ነበር። ጥራት ያለው ጥናት ማለት የተቀመጡበት ሰዓት ሳይሆን፣ አእምሮ የተቀበለው እውቀት ነው።
⁉️ የነፍስ ጥያቄ፦ ልጄ መጽሐፍ ከፍቶ ስለታየኝ ብቻ እያጠና ነው ብዬ አምናለሁ? ወይስ የጥናቱን ጥራት እከታተላለሁ?
🔶 የተግባር እርምጃ፦ በቤታችሁ ውስጥ የጥናት ሰዓት ሲጀምር በሰዓት (Timer) በመታገዝ ልጁ ትኩረት አድርጎ እንዲሠራና በፕሮግራሙ መሠረት እረፍት እንዲያደርግ አበረታቱት።
♦️ የማታ ጥናቱ እስከ ሦስት ትምህርቶችን ሊያካትት ስለሚችል፣ ልጆች ከላይ የተጠቀሰውን የጊዜ ገደብ አሟልተው ጧት በንቃት እንዲነሱ፤ 1ኛ እና 2ኛ ክፍል ቢበዛ 3:00 ሰዓት ላይ፣ 3ኛ እና 4ኛ ክፍል እስከ 3:30-4:00 ሰዓት ባለው፣ እንዲሁም ከ5ኛ ክፍል በላይ ያሉ ተማሪዎች ከ4:00 - 5: 00 ሰዓት ባለው እንዲተኙ ቋሚ ሥርዓት ይዘርጉ።
ክፍል 4፦ "የአቅም ልክ" እና ቁርኣናዊው ፍትሕ
አንዱ ልጅ በሒሳብ ጎበዝ ሲሆን፣ ሌላው በቋንቋ ወይም በስነ-ጥበብ ድንቅ ይሆናል። ሁሉም ልጅ 100/100 እንዲያመጣ መጠበቅ፣ የተፈጥሮን ሕግ እንደመጋፋት ይቆጠራል። እያንዳንዱ ልጅ የተሰጠው አቅም የተወሰነ ነው። አላህ ሰዎችን የፈጠረው በተለያዩ ችሎታዎችና አቅሞች ነው።
አንድ ተማሪ ሒሳብ ላይ 60 አምጥቶ ስነ-ጽሁፍ ላይ 95 ካመጣ፣ ያ ልጅ ደካማ ሳይሆን ተሰጥኦው ሌላ ቦታ ነው ማለት ነው። አቅሙን ያላገናዘበ ጫና መፍጠር ልጁ በትምህርቱ ላይ ጥላቻ እንዲያድርበትና በራስ መተማመኑ እንዲጠፋ ያደርጋል። ወላጅ መሆን ማለት የልጁን "ጣሪያ" ማወቅና ከዚያ በላይ አለመጫን ማለት ነው።
ጌታችን በቅዱስ ቁርኣን እንዲህ ይላል፦
❝አላህ ማንኛይቱንንም ነፍስ ከችሎታዋ በላይ አያስገድዳትም (አይጭንባትም)።❞ [አል-በቀራህ 2፡286]
⁉️ የነፍስ ጥያቄ፦ እኔ ልጄን የምመዝነው በራሱ አቅም ነው ወይስ ጎረቤት ካለው ተማሪ ጋር በማወዳደር?

🔶 የተግባር እርምጃ፦ ባለፉት ሦስት ወራት ልጃችሁ የትኛው ትምህርት ላይ የተሻለ ዝንባሌ እንዳለው መዝግቡ። ደካማ በሆነበት ላይ ድጋፍ አድርጉ እንጂ ወቀሳ አታውርዱበት።
ክፍል 5፦ የተሰጥኦ ሚስጥር፦ "እያንዳንዱ ለተፈጠረለት ይገራል"
እያንዳንዱ ልጅ ለተፈጠረለት አላማ የተመቻቸ ነው። ወላጅ የልጁን ደካማ ጎን ብቻ ከመመልከት ይልቅ፣ ጠንካራ ተሰጥኦውን መፈለግ አለበት። የአላህ መልክተኛ (ﷺ) ሶሐባዎቻቸውን የገመገሙት በተለያየ መስክ ነበር። አቡበክር (ረ.ዐ) በለገስነታቸው፣ ዑመር (ረ.ዐ) በጥንካሬያቸው፣ ኻሊድ ኢብኑል ወሊድ በጦር መሪነታቸው እንደተመሰገኑት ሁሉ፤ የእናንተም ልጅ ነገ ለዓለም የሚተርፍበት የራሱ መስክ ይኖረዋል።
ሳይንቲስቱ አልበርት አንስታይን እንዲህ ይላል፦ "ሁሉም ሰው ሊቅ ነው፤ ነገር ግን አንዲትን አሳ ዛፍ ላይ የመውጣት ችሎታዋን መለኪያ አድርገህ ብትመዝናት፣ እድሜዋን ሙሉ ጅል እንደሆነች አስባ ትኖራለች።" የልጃችሁን የ"ዋናተኛነት" ተፈጥሮ ሳታዩ ለምን እንደ ዝንጀሮ ዛፍ ላይ አልወጣህም ብላችሁ አትውቀሱት።
▶ የአላህ መልክተኛ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦
❝ስሩ፤ እያንዳንዱ ሰው ለተፈጠረለት ነገር የተገራ/የተመቻቸለት ነው።❞ [ቡኻሪና ሙስሊም]
⁉️ የነፍስ ጥያቄ፦ የልጄ "የተገራለት" (ተፈጥሯዊ) ዝንባሌ ምንድነው? እኔስ እሱን ለማሳደግ ምን አድርጌያለሁ?
🔶 የተግባር እርምጃ፦ ልጁ ከትምህርት ውጪ የሚያሳያቸውን የፈጠራ ስራዎች በጥሞና ተከታተሉና አድናቆት ስጡ።
ክፍል 6፦ የኢብኑል ቀይም (ረሂመሁላህ) የትምህርት ፍልስፍና
የልጆቻችንን አቅም እንዴት መገምገም እንዳለብን ሊቃውንት ትልቅ ጥቆማ ሰጥተውናል። ትምህርት ማለት የመረጃ ጭነት ሳይሆን የተሰጥኦ ጥበቃ ነው። የልጁን ተፈጥሯዊ ዝንባሌ ማስተዋልና እሱን ማሳደግ ከሁሉ በላይ ዋጋ አለው።
ሳይንቲስቱ ሃዋርድ ጋርድነር "የብዝሃ-እውቀት" ቲዎሪውን ሲያቀርብ፣ ሰው በስምንት የተለያዩ መንገዶች ሊቅ ሊሆን እንደሚችል አረጋግጧል። ሒሳብ ላይ 100 ያላመጣ ልጅ በንግግር፣ ከሰው ጋር በመግባባት ወይም በቴክኖሎጂ አቻ የሌለው ሊቅ ሊሆን ይችላል።
🎤 ኢብኑል ቀይም (ረሂመሁላህ) እንዲህ ይላሉ፦ "ወላጅ የልጁን የተፈጥሮ ዝንባሌ ማስተዋል አለበት። ልጁ ዝንባሌ በሌለው ትምህርት በግድ እንዲወጠር ማድረግ የለበትም። ዝንባሌውን ያገኘ ልጅ በዚያ መስክ የላቀ ይሆናል፤ የማይወደውን የተጫነ ግን ሁለቱንም ያጣል (አዲሱንም አያውቅም፣ የራሱንም ተሰጥኦ ይገድላል)።"
⁉️ የነፍስ ጥያቄ፦ እኔ የምገነባው የልጄን ስብዕና ነው ወይስ የእኔን ያልተሳካ ህልም በእሱ ላይ ለመጫን እየሞከርኩ ነው?
🔶 የተግባር እርምጃ፦ ልጃችሁ የማይወደውን ትምህርት ለምን እንደማይወደው በረጋ መንፈስ ጠይቁት። ችግሩ ከተፈጥሮ ዝንባሌ ከሆነ አማራጭ መንገዶችን ፈልጉ።
ክፍል 7፦ "ጥረት" ከ "ውጤት" ይበልጣል
እንደ ወላጅ ትኩረታችን መሆን ያለበት ልጆቻችን ባመጡት "ቁጥር" ላይ ሳይሆን፣ ባሳዩት "ጥረት" ላይ ነው። ውጤት በብዙ ነገሮች ሊለዋወጥ ይችላል፤ ጥረት ግን ቋሚ ስብዕና ነው። ቶማስ ኤዲሰን መብራትን ከመፍጠሩ በፊት 10,000 ጊዜ ወድቆ ነበር። እናቱ ግን "ውድቀት" ብላ አልጠራችውም፤ "ለመስራት የማይችሉ 10,000 መንገዶችን አገኘህ" ብላ አበረታታችው እንጂ። ዛሬ በጥረት ያገኘው 80፣ ነገ ወደ 100 ያደርሰዋል። ጥረትን ማድነቅ ተማሪው ተስፋ እንዳይቆርጥ ያደርገዋል።
🎤 ኢማም አሽ-ሻፊዒ (ረሂመሁላህ) እንዲህ ይላሉ፦ "እውቀት ማለት መረጃን በቃል መያዝ ሳይሆን፣ ለተግባር የሚጠቅመውና ሰውን የሚቀይረው ነው።"
⁉️ የነፍስ ጥያቄ፦ ልጄ ዛሬ ቢለፋም ውጤቱ ባይመጣ፣ ጥረቱን አይቼ "አይዞህ" እለዋለሁ? ወይስ "ጊዜዬን አባከንክ" ብዬ እገስጻለሁ?
🔶 የተግባር እርምጃ፦ "100 ስላመጣህ ጎበዝ ነህ" ከማለት ይልቅ "ዛሬ 40 ደቂቃ ሙሉ በጥሞና ስላጠናህ ኩራት ይሰማኛል" የሚለውን አገላለጽ ተጠቀሙ።
ክፍል 8፦ የቤት ድባብ፦ የዕውቀት ቤተ-ሙከራ
ቤት የዕውቀት ድባብ ከሌለው ትምህርት ቤት የሰጠው እውቀት ይከስማል። እናንተ ስልካችሁን እያያችሁ ልጁን "አጥና" ብትሉት ውጤት የለውም። የልጁ አርአያ እናንተ ናችሁ። ልጁ በሚያጠናበት 40 ደቂቃ ውስጥ እናንተም መጽሐፍ ወይም ቁርኣን በመያዝ የንባብ ድባብ ፍጠሩ። ቤቱ የቲቪና የስልክ ጫጫታ ከሆነ፣ የልጁ አእምሮ በትምህርቱ ላይ ሊያተኩር አይችልም።
♦️ በተጨማሪም የጥናት ቦታው አካላዊ ዝግጅት ወሳኝ ነው። ልጆች አልጋ ላይ ተኝተው እንዳያጠኑ ማሳሰብ ይገባል፤ አእምሮ አልጋን ከእንቅልፍ ጋር ስለሚያያይዘው ትኩረት ይበተናል። ጸጥታ ያለበት፣ በቂ ብርሃንና ንጹህ አየር ያለው ማዕዘን ለጥናት ሊመደብላቸው ይገባል።
🎤 ኢብኑ ኡሰይሚን (ረሂመሁላህ) እንዲህ ይላሉ፦ "ወላጅ ለልጁ ምሳሌ የሚሆን ተግባር ካላሳየ ምክሩ ብቻውን ፍሬ አያፈራም።"
⁉️ የነፍስ ጥያቄ፦ ቤቴ የዕውቀት ማዕከል ነው ወይስ የመዝናኛ ስፍራ? ልጆቼ ሲያጠኑ እኔ ምን እያደረግኩ ነው?
🔶 የተግባር እርምጃ፦ የጥናት ሰዓት ሲጀምር በቤቱ ውስጥ ያሉ የኤሌክትሮኒክስ መሣሪያዎችን (ቲቪ፣ ስልክ) በሙሉ ለተወሰነ ሰዓት የመዝጋት ልማድ አዳብሩ።
ክፍል 9፦ ስሜታዊ ደኅንነት፦ የመማር ቁልፍ
አእምሮ ስጋትና ጭንቀት ውስጥ ሲሆን የመማር አቅሙ ይዘጋል። ልጆች በትምህርታቸው ውጤት ካላመጡ ምናልባት ውስጣቸው ሰላም አጥቶ ሊሆን ይችላል። የአላህ መልክተኛ (ﷺ) ለልጆች የነበራቸው ርህራሄና ፍቅር ልባቸውን እንዲከፍቱ ያደርጋቸው ነበር። ፍቅርና መረጋጋት ባለበት ቤት ውስጥ ተማሪው የትምህርት ቤት ፕሮግራሙን ለመተግበር አይቸገርም።
♦️ ልጆች ውጤት ሲቀንስባቸው ቤት ውስጥ የሚኖረው መሸማቀቅ (ፍርሃት) ለቀጣይ ውድቀት ይዳርጋቸዋል። ከስህተት መማር እንደሚቻል ማሳየት ያስፈልጋል። በተለይም ከ1ኛ-8ኛ ክፍል ባለው የዕድሜ እርከን (በተለይ ወደ 7ኛ እና 8ኛ ክፍል ሲጠጉ) የራሳቸው የሆነ ስሜታዊ ሽግግርና የጓደኛ ግፊት ውስጥ ስለሚገቡ፣ ወላጅ "አዛዥ" ከመሆን ይልቅ "አማካሪ እና ጓደኛ" መሆን አለበት። ልጆቻችሁን "ለምን አልመጣህም?" ብላችሁ ከመውቀሳችሁ በፊት፣ "ለማጥናት ምን ጎደለህ/ሽ? ምን የሚያስጨንቅሽ ነገር አለ?" ብላችሁ በጥበብ ጠይቁ።
⁉️ የነፍስ ጥያቄ፦ ልጄ እኔን የሚያየኝ እንደ "አስፈሪ ዳኛ" ነው ወይስ እንደ "አጋዥ ደጋፊ"?
🔶 የተግባር እርምጃ፦ በሳምንት አንድ ቀን ከትምህርት ውጪ በሆነ ጉዳይ ላይ ከልጃችሁ ጋር ብቻችሁን ጊዜ አሳልፉ።
ክፍል 10፦ የቴክኖሎጂ እና የስክሪን አስተዳደር
በአሁኑ ዘመን የወላጆች ትልቁ ፈተና ቴክኖሎጂ ነው። ስልክ፣ ጌም እና ቴሌቪዥን የልጆችን ጊዜና ትኩረት በከፍተኛ ሁኔታ ይሰርቃሉ። ነገር ግን ቴክኖሎጂን ከማጥፊያነት ወደ ማሳደጊያ መሣሪያነት መቀየር ይቻላል። ለምሳሌ ለጥናት የሚረዱ ትምህርታዊ ቪዲዮዎችን እንዲያዩ በማድረግ በሥርዓት እንዲጠቀሙ መምራት ያስፈልጋል። ቴክኖሎጂን ያለ ገደብ መልቀቅ የልጆችን ተፈጥሯዊ የመማር ፍላጎት ያደነዝዛል።
⁉️ የነፍስ ጥያቄ፦ የቤቴ ቴክኖሎጂ ልጆቼን እያሳደጋቸው ነው ወይስ ትኩረታቸውን እየሰረቀ?
🔶 የተግባር እርምጃ፦ ልጆች ስክሪን የሚያዩበትን ሰዓት ገደብ በማውጣት፣ ከትምህርት ጋር የተገናኙ ጠቃሚ ይዘቶችን ብቻ እንዲከታተሉ መምራት።

ክፍል 11፦ ማጠቃለያና የነፍስ ቃል
ውድ ወላጆች፤ ልጆቻችን የአላህ አማናዎች ናቸው። በትምህርት ቤታችን የተሰጠው የጥናት መርሐ ግብር (Schedule) እናንተን ለማገዝ የተዘጋጀ "ካርታ" ነው። ይህን ካርታ በፍቅር፣ በትዕግስትና በእምነት ተጠቀሙበት። የልጆቻችሁን ልዩ ተሰጥኦ እዩላቸው፣ ጥረታቸውን አድንቁላቸው። ዛሬ የምታሳዩአቸው ርህራሄና የምትሰጧቸው ማበረታቻ፣ ነገ ለሚገነቡት ታላቅ ስብዕና ዋነኛው ግብዓት ነው።
➤ የድርጊት ቃል ኪዳን፦ ይህን መልዕክት ካነበባችሁ በኋላ፣ ዛሬውኑ ማታ ከልጆቻችሁ ጋር አዲስ የፍቅርና የክትትል ምዕራፍ ጀምሩ።
🌸 አላህ ይርዳችሁ እና ትምህርታችሁንም ይባርክላችሁ። ዛሬ የምታደርጉት እያንዳንዱ ትንሽ ጥረት ነገ ብሩህ ስኬት ይሆናል! 🌸 🤲 🤲
━━━━━━━━━━━━━━
📢 ለልጆቻችን ስኬትና ብሩህ ተስፋ!
✅ ይህ መመሪያ በአላህ ፈቃድና እገዛ የልጆቻችንን ሁለገብ ስኬት ለማገዝ የቀረበ አነስተኛ ጥረት ነው። ሁሉም ስኬት የሚገኘው በአላህ ፈቃድ ነውና፣ ይህ መልዕክትም ለልጆቻችን እድገት ሰበብ እንዲሆንልን እንመኛለን።
➡ መልዕክቱ 11 ወሳኝ ክፍሎችን የያዘ በመሆኑ ረዘም ሊል ይችላል፤ ሆኖም እያንዳንዱ ነጥብ ለልጆቻችን ስኬትና ሥነ-ምግባር ትልቅ ፋይዳ ይኖረዋል ተብሎ የታሰበ ነው። ኢንሻአላህ!!
💡 ትኩረት ለልጆቻችን ስኬት፦ እነዚህን ነጥቦች በአግባቡ ለማደራጀትና ጠቃሚ መረጃዎችን ለማሰባሰብ ረጅም ሰዓታት ቢፈጁም፤ እናንተ ለልጆቻችሁ ስኬት ሲባል ጥቂት ደቂቃዎችን ሰጥታችሁ አስራ አንዱንም ክፍሎች ብታነቧቸው፣ በአላህ ፈቃድ ለትልቅ ለውጥ መነሻ ይሆናል።
መልካም ንባብ!
✨━━━━━━━━━━━━✨
🌈 ꧂ ✍️ ረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል ꧁ 🌈

ለተማሪዎች ምርጥ PDF ማንበቢያ App
FLEX PDF READER
🔶 Group PDF files together
🔶 Table of contents
🔶 Merge multiple PDFs
🔶 Split PDF
🔶 Add watermark
🔶 Images to PDF
🔶 PDF to Image
🔶 Lock PDF
🔓 PDF
🔶 Create Bookmarks
🔶 Search PDFs
🔶 Dark and light mode
Install 👇
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.smartpdf.reader

❤4
ጥቆማ‼
=====
✍️ ነቃ በሉ፣ አታንቀላፉ! ማለፍ የሌለባችሁ ወርቃማ የስታርታፕ ዕድል!
የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት (EAII) በአይነቱ ልዩ የሆነውን የስታርታፕ (Startup) ድጋፍ 2ኛ ዙር ምዝገባ ይፋ አድርጓል።
ባለፈው በመጀመሪያው ዙር የገቡት ከ200 በላይ ልጆች ምን ያህል ተጠቃሚ እንደሆኑና በወረቀት ላይ የነበረ ሃሳባቸውን ወደ ተጨባጭ ቢዝነስ እንደቀየሩ አይተናል። አሁን ደግሞ ይበልጥ ሰፍቶ እና አዳዲስ ድጋፎችን አካቶ መጥቷል።
እንደ ወንድም ልምከራችሁ፡- ምናልባት "ገና እኮ ሞዴል ትሬይን (Train) አድርጌ አልጨረስኩም" ብላችሁ ወደኋላ እንዳትሉ። ማቅረብ ያለባችሁ ፕሮጀክት ከኤአይ (AI) ጋር የተያያዘ መሆን አለበት እንጂ፣ የግድ የተጠናቀቀ ሞዴል
ይዛችሁ ቅረቡ አይባልም። ከሃሳብ እና ከፕሮቶታይፕ (Prototype) ጀምሮ ይዛችሁ መግባትና መወዳደር ትችላላችሁ።
መድረኩን ካገኛችሁ በራስ መተማመን ሃሳባችሁን በሚገባ አስረዱት (Pitch it well)፤ በደስታ ነው የሚቀበሏችሁ።
ይሄ ፕሮግራም ዝም ብሎ ማዳመጥ ብቻ አይደለም፤ ከሃሳብ ጀምሮ፣ እውን አድርጋችሁት፣ ከዛ ጋር የተያያዘ ፈንድ (Funding) አግኝታችሁ፣ ተግባር ላይ የሚውል ፕሮዳክት እስኪሆን ድረስ አብረዋችሁ ሆነው ያግዟችኋል።
በተለይ ይሄ እድል ለነማን ነው አሪፍ? በኤአይ (AI) ዘርፍ ላይ ፈጠራ አስባችሁ ነገር ግን መስሪያ ቦታ (Workspace)
ላጣችሁ ስታርታፖች፣ የኤአይ ሞዴሎችን ትሬይን የምታደርጉበት አቅም ያለው ኮምፒውተር/ጂፒዩ (GPU) ለሌላችሁ፣ እንዲሁም
ለዲፕሎይመንት (Deployment) ለተቸገራችሁ ወጣቶች... ይሄ እድል ፈፅሞ ሊያመልጣችሁ አይገባም!
🎯 የትኞቹ ዘርፎች ላይ መሳተፍ ይቻላል? በግብርና፣ በጤና፣ በደህንነት፣ በትምህርት፣ በፋይናንስ፣ በሮቦቲክስ፣ በኤ.አይ ኤጀንት
(AI Agent)፣ እንዲሁም በቨርችዋል እና ኦግመንትድ ሪያሊቲ (VR/AR) ዘርፎች ላይ የፈጠራ ሀሳብ ያላችሁ ሁሉ መሳተፍ ትችላላችሁ።
⏰ የምዝገባ ጊዜ፡- ከሚያዚያ 15፣ 2018 እስከ ግንቦት 06፣ 2018 ብቻ! (ቀኑ እየሄደ ነው ቶሎ በሉ)
🔗 ለማመልከት፡- ይህን ድረ-ገፅ ይጠቀሙ ▶️ aistartup.aii.et
የፈጠራ ሃሳብዎን ወደ ተጨባጭ ምርት፣ ህልምዎን ወደ እውነታ የሚቀይሩበት ጊዜ አሁን ነው። በድጋሚ እላለሁ ነቃ በሉ፣ አታንቀላፉ!
ለሌሎች ጓደኞቻችሁም እንዲደርሳቸው ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ!
||
©️ STEMwithMurad

Claude AI ያለVPN መስራት ጀምሯል መጠቀም ትችላላችሁ።
አፕሊኬሽኑ play store ላይ የለም።
Claude.ai ላይ አካውንት በመክፈት መጠቀም ትችላላችሁ።
አፕሊኬሽኑ play store ላይ የለም።
Claude.ai ላይ አካውንት በመክፈት መጠቀም ትችላላችሁ።