👉 ዛሬ Server ማለት ምን ማለት እንደሆነ የምናይ ነው የምሆነው:
➡️ Server(ሰርቨር)
👉 ሰርቨር ማለት በሁለት ይከፈላል እነሱም Hardware Server and Software Server በማለት።
➡️ ሰርቨር ማለት ከስሙ እንደምንረዳው አገልጋይ ማለት ሲሆን ለ Client Devices አገልግሎት የሚሰጥ ማለት ነው። በዚህም የሶፍትዌር ሰርቨር የምንላቸው
ዌብ ሰርቨር፣ ዶሜን ኔም ሰርቨር፣ ሜይል ሰርቨር በጥቂቱ መጥቀስ እንችላለን። ከዚህ በተጨማሪም ስርቨር የሆኑ ኦፕሬቲንግ ሲስተምን መጥቀስ ይቻላል ለምሳሌ ማይክሮሶፍት ዊንዶውስ ሰርቨር፣ ኡቡንቱ ጥቂቶች ናቸው።
➡️ Hardware Server የምንለው የኮምፒውተር አይነት ሲሆን መረጃን ለመያዝ የሚያገለግልና በክሊያንት ኮምፒውተሮች መረጃውን እንዲደርስና ዋና መረጃው የሚቀመጥበት ማለት ነው። ሰርቨር ኮምፒውተር በጣም በጣም ከፍተኛ የሆነ መረጃን የመያዝ አቅም ያለው፣ መረጃን ፕሮሰስ የማድረግ አቅሙ በጣም ከፍተኛ የሆነ የመስራት አቅሙ በጣም ከፍተኛ የሆነ በዋጋ፣ በአካላዊ ከመደበኛው ኮምፒውተር የሚተልቅ እቃ ነው።
➡️ በአንድ ሰርቨር ኮምፒውተር ለብዙ ክሊያንት ኮምፒውቲንግ እቃዎች(ሞባይል፣ ላፕቶፕ፣ ደስክቶፕ፣ ካሜራ፣ ፕሪንተር ወዘተ...) በአንድ ላይ ኔትወርክ በመጠቀም እርስ በራሳቸው እንዲተዋወቁ፣ መረጃ እንዲለዋወጡ፣ መረጃውን እንዲጋሩ ያደርጋል።
➡️ Client Devices የምንለው ማንኛውም የኮምፒውቲንግ እቃዎች ከሰርቨሩ ጋር በመግናኘት መረጃዎችን አሳሾችን(Browsers) በመጠቀም መረጃን የምንጠቀምበት እቃዎችን ያካትታል ለምሳሌ አሁን የምንጠቀምበት ኮምፒውተር፣ ላፕቶፕ፣ ሞባይል ስልክ ስልካችን ክሊያንት ዲቫይስ የሆነበት ምክንያት ለምሳሌ ፌስቡክ፣ ቴሌግራም፣ ዩቱቭ ስንጠቀም መረጃውን ከሰርቨር ኮምፒውተር ላይ ኔትወርክ በመጠቀም የሚያመጣልንና ስለምንጠቀም ነው። በአጠቃላይ ሰርቨር ኮምፒውተር ማለት በጣም ብዙ መረጃዎችን አምቆ የያዘ ለተጠቃሚዎች በክሊያንት ኮምፒውተር አማካኝነት በመጠቀም መረጃን ከሰርቨር ኮምፒውተር በማምጣት ለተጠቃሚዎች የሚያደርስ ነው።
➡️ ክሊያንትና ሰርቨር ኮምፒውተር የሚገናኙበት ፕሮቶኮል TCP/IP ይባላል። TCP/IP በዋናነት መልእክቶች ከሰርቨር ኮምፒውተር ወደ ክሊያንት ኮምፒውተር እንዲለዋወጡ የሚያደርግ ሲሆን በLAN Local Area Network ወይም በWAN Wide Area Network ክሊያንት ኮምፒውተሮችን ከሰርቨር ኮምፒውተሮች ጋር በማስተሳሰር መረጃን መለዋወጥ ያስችላል።
t.me/TechnologyMasterPage

❤4
በጎግል ፕሌይ ስቶር ላይ ብዙ ማስታወሻ የሚወስዱ አፕሊኬሽኖች አሉ ነገርግን ብዙ ሰዎች እንደ Google Keep፣ Evernote ወይም Microsoft OneNote ባሉ ትልልቅ ስሞች ላይ ይሳቡ ይሆናል።
አዲስ ነገር ለመሞከር ከፈለጉ፣ WeNoteን ይመልከቱ።
ልክ እንደሌሎቹ ሁሉ የእርስዎ ማስታወሻዎች፣ የተግባር ዝርዝሮች፣ አስታዋሾች ወዘተ መተግበሪያ ነው፣ ነገር ግን እንደ አዶ ለማስታወሻዎች ማበጀት፣ የይለፍ ቃሎች ጀርባ ማስታወሻዎችን መቆለፍ፣ ማስታወሻዎችን በሁኔታ አሞሌዎ ላይ መጣበቅ እና ሌሎች ብዙ ባህሪያትን የያዘ መተግበሪያ ነው።
ፕለይስቶር ላይ በመግባት ወደ ስልካችን መጫን እንችላለን።
ይህች አፕልኬሽን ፌስቡክ፣ ቴሌግራም፣ እንዲሁም በማንኛውም የሶሻል ሚዲያ ላይ የምናገኛቸውን ማስታወሻዎችን ለመያዝ ያገለግላል።
ማስታወሻ ለመያዝና መጻፍ ብትፈልጉ ይህችንን አፕልኬሽን በመጠቀም ኖት መያዝ እንችላለን።
ይህ አፕልኬሽን ከጎግል ድራይቭ ጋር በማገናኘት አፕልኬሽኑ ላይ የተቀመጡት ማስታዎሻዎች በየግዜው ባክአፕ መያዝ ትችላላችሁ። ይህ ጥቅም(ባክአፕ) ለምሳሌ አፕልኬሽኑ ቢጠፋ፣ ዲሌት ቢሆን፣ ስልኩ ቢጠፋ፣ ስልኩ ቢበላሽ፣ በሌላ ስልክ ከፍተን ማስታወሻውን እንደገና ማግኘት ያስችለናል።
ባክአፕ ለማድረግ ኢሜይል የሚጠይቅ ሲሆን ኢሜይል አድራሻ በማስገባት መረጃውን መያዝ ያስችለናል።
ሌላው ጥቅም
በፈለግነው ካታጎሪ ስያሜ በመስጠት ማዘጋጀት ያስችለናል።
ℹ️ ካላንደር የተዘጋጀለት ነው።
ℹ️ በፈለግነው View style ለእይታ ምቹ በሚሆን መልኩ እንድናዘጋጅ ያደርገናል።
ℹ️ በፍጥነት የገለግነውን መረጃ ጽሁፍ በመጻፍ ከኖታችን ላይ እንድንፈልግ ያስችለናል።
ℹ️ በፈለግነው አይነት Sorting type ሶርት ማድረግ ያስችለናል።
እንዲሁም የተለየ መተግበሪያ ሳያስፈልግዎት አስታዋሾችን ለመከታተል አብሮ የተሰራ የቀን መቁጠሪያ አለው፣ እና እንዲሁም በጭራሽ መረጃዎትን እንዳያጡ ከ Google Drive ጋር ማስተሳሰር ይችላል።
መተግበሪያው እንደ ፕሌይ ስቶር መግለጫው የሚያቀርባቸው ባህሪያት ዝርዝር ይኸውና።
✅ የቀለም ማስታወሻዎችን እና የተግባር ዝርዝሮችን መፍጠር ይችላሉ።
✅ ስዕሎችን፣ ስዕሎችን፣ ወይም የእጅ ጽሑፍን እንደ አባሪ በመጨመር መረጃ እንድንይዝ ያደርገናል።
✅ ማስታወሻዎችን፣ የተግባር ዝርዝሮችን ወይም መተግበሪያውን በራሱ በፒን ፣ በይለፍ ቃል ወይም በጣት አሻራ መቆልፍ እንችላለን።
✅ ከ2 የተለያዩ የቅርጸ አይነቶች፣ 5 የተለያዩ የቅርጸ መጠኖች፣ 4 የተለያዩ ገጽታዎች (ጨለማ ሞድ)፣ 5 የተለያዩ እይታዎች፣ 6 የተለያዩ የመደርደር ሁነታዎች እና 12 ምርጫዎችን ቀለም መቀባት እንድትችሉ ተደርጎ የተሰራ ነው።
✅ አስታዋሾች (ሊበጁ የሚችሉ እና በየቀኑ፣ ሳምንታዊ፣ ወርሃዊ ወይም አመታዊ) እና የቀን መቁጠሪያ (ከጨረቃ ቀን መቁጠሪያ ድጋፍ ጋር፣ ግን ምንም የGoogle Calendar ውህደት የለም)
✅ የምትፈልጉትን ማስታወሻ ፒን ማድረግ ያስችላችኋል።
✅ ደህንነቱ በተጠበቀ ሁኔታ ከ Google Drive ጋር ማገናኘት ይችላሉ ስለዚህ ማስታወሻዎችን ባክአፕ ያድርጉ
✅ ማስታወሻዎችን እና አባሪዎችን ለኢሜል፣ ኤስኤምኤስ፣ ማህበራዊ አውታረ መረብ እና የመልእክት መላላኪያ መተግበሪያዎች ማጋራት ይችላሉ።
✅ ከሌሎች መተግበሪያዎች የተጋሩ ማስታወሻዎችን እና አባሪዎችን መቀበል ይችላሉ።
✅ ፈጣን የሆነ ፍለጋ
t.me/TechnologyMasterPage
#Source:- Muhammed Computer Technology

❤3
✳️የሳይበር ጥቃት SMS Phishing
🔻ይህን Method በመጠቀም የATM ፤ የEmail ፤ የfacebook ወ.ዘ.ተ የሚስጥር ቁጥሮች በቀላሉ ይሰረቃሉ።
🔻SMS Phishing በቀላሉ ወደናንተ Fake የሆኑ SMS በመላክ ሊያጠቋችሁ ይችላሉ።
〽️ለምሳሌ፦ Facebook Account እንዴት ሊሰርቁ እንደሚችሉ እንመልከት...
1⃣. Facebook page በመግባት Forget Account የሚለውን ይጫናሉ
2⃣. የናንተን User Name በመጠቀም Verification Number እንዲላክ ያደርጋሉ Fbookም ወደናንተ Verification Number ይልካል
3⃣. Fake Phone Number በመጠቀም የራሳቸውን Phishing SMS ወደናንተ ይልካሉ። የሚልኩት SMS ለምሳሌ ፦ የFacebook አካውንታችሁን በተሻለ Secure ለማድረግ የደረሳችሁን 6 digit Verification Number መልሰው ይላኩ
⚠️From Facebook Company
‼️Notes ፦ የሚደርሳችሁ በEnglish language ሊሆን ይችላል በተጨማሪም በጣም እውነት የመሰሉ SMS ነው የሚጠቀሙት እና የሞባይል ቁጥርም የሚፈልጉትን ሀገር መርጠው ሊጠቀሙ ስለሚችል በቀላሉ ልንሸወድ እንችላለን።
4⃣. 6 digit Verification Number ለነሱ ላክን ማለት BOOM Facebook አካውንታችንን በድጋሜ ልናገኘው አንችልም ማለት ነው።
‼️ ማስጠንቀቂያ ‼️
🔻በምንም አይነት ስልክ ቁጥር ይሁን ከየትኛውም አይነት ሀገር... ከላይ እንደገለፅኩት አይነት ጥያቄ ቢያቀርቡላችሁ የትኛውንም አይነት SMS እንዳትልኩ።
Source :- Muhammad Computer Technology

📍 መረጃ ቴክኖሎጂ 📍
#ፓስዋርድ_ሲጠፋን_ኮምፒውተራችንን_መክፈቻ_ዘዴ
የኮምፒውተርዎ ፓስዋርድ ከነአካቴው ቢጠፋብዎት ብዙም አይጭነቅዎ መፍትሄ አለው ።
የሚያስፈልገው ሶፍትዌር “Spotmou Bootsuite.iso” ወይም "isee password Windows password Recovery pro" ሲሆኑ ሁለትም ከ internet ላይ ማውረድ ትችላላችሁ ነገር ግን isee password windows password recovery pro የሚለውን ገዝታችሁ የምታገኙት ስለሆነ እኛ የገዛንውን ለውድ የቻናላችን ተከታታዮች sofrwarun ከላይ ለቀንላችኋል።
በ "Spotmou Bootsuit.iso ሶፍትዌር ፓስዎርዳችሁን መክፈት ለምትፈልጉ:- ቀጣዮቹን 10 ስቴፖች ተከትለው ኮምፒውተርዎን መክፈትና መጠቀም ይችላሉ፡፡
#Step 1: መጀመረያ ሶፍትዌሩን በፍላሽ ወይም CD ላይ እንጭናላን።
#Step 2: ኮምፒዩተራችንን Turn OFF ማድረግ፡፡
#Step 3: ፍላሹን /ሲዲውን/ ኮመፒዩተሩን ጋር አገናኝተን Turn ON ማድረግ፣ ከዛ F12 (Boot key) (ለHp ላፕቶፕ F9) መንካት፡፡
#Step 4: “Boot Sequence” የሚል ሲመጣልን “USB” የሚለውን መርጠን “Enter”ን መንካት ከዛ ትዕዛዙን መከተል፡፡
#Step 5: ኮምፒዩተሩ ከተከፈተ በኋላ “Spotmou Bootsuite 2012 Application” ይከፈትልናል፡፡
#Step 6: ከአፕልኬሽኑ ላይ “Password and Key Finder” የሚለውን “Menu” እንመርጣለን፡፡
#Step 7: “Admin Password Resetter” የሚል መንካት፡፡
#Step 8: “Please select the target widows” ከሚለው ሥር የኮምፒዩተሩን “Window Version (XP/7/8/8.1/ 10)” ይመርጣሉ፡፡ ቀጥሎ “please select the target user” ከሚለዉ ሥር ደግሞ መክፈት የሚፈልጉትን “User Account” መርጠዉ “Reset” የሚለውን መጫን፣ ከዛ “OK” ከዛ “YES” የሚለውን እንጫናለን፡፡
#Step 9: መጨረሻ ላይ “Password is reset successfully” የሚል መልዕክት ይደርሶታል፡፡
#Step 10: ኮምፒዩተሩን ዘግተው ይክፈቱት (Reboot). በትክክል 100% ይሰራል።
በ "iSee password windows password recovery Pro" ፓስዎርዳችሁን መክፈት ለምትፈልጉ ሶፍትዌሩን ቻናላችን ላይ ለቀንዋል Registered የሆነውን የሚከተለውን step ይከተሉ። ሶፍትዌሩን Download ያድርጉ ።
ሌላ Computer ላይ install ያደርጉት ሶፍትዌሩን ስከፍቱት ከላይ በምስል እንደምታዩት ያመጣላችኋል። ባዶ Flash or CD ትከቱና ፍላሽ ከሆነ የከተታችሁት Create password Reset Usb Flash drive ከሚለው ስር የፍላሹን ስም መርጣችሁ "Burn Usb" የሚለውን ስነኩት Burn አድጎ ሲጨርስ flashun ትነቅላላችሁ።
ከዛ በፓስዎርድ የተዘጋብንን ኮምፒዩትራችንን Turn OFF ማድረግ ፍላሹን/ሲዲውን/ ከኮምፒዩተራችን ጋር አገናኝተን Turn On ማድረግ ከዛም (F12 ለቶሽባ/ዴል) F9 ለHp Computer (Boot key) መንካት " Boot sequence" የሚል ሲመጣልን " USB" የሚለውን መርጠን "Enter"ን በመንካት ትዕዛዙን መከተል።
ኮምፒዩተራችን ከተከፈተ ብኋላ "isee password Windows recover pro" ይከፍትልናል ከአፕልኬሽኑ ላይ ካሉት አማራጭች(Option) ውስጥ "Admin Password Resetter" የሚለውን መንካት ከዛም "yes" የሚለውን እንጫናለን።
ትንሽ ከቆየ በኋላ(max. 2mint) "password is reset እናደርጋለን።

✳️ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ሶፍትዌሮች
🚩 የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ሁለገብነትን ተከትሎ ዘርፉን ለማበልፀግና ብዙኃንን ተሳታፊ ለማድረግ ተቋማት እና ግለሰቦች የቴክኖሎጂውን ሶፍትዌሮችን በነጻ ያቀርባሉ፡፡ በስፋት ጥቅም ላይ እየዋሉ ከሚገኙት መካከል ሁለቱን ለዛሬ እናስተዋውቃችሁ፡፡
▫️1.ቴንሰርፍሎው/ TensorFlow
ይህ ሶፍትዌር የማሽን ለርኒንግ ሞዴሎችን ለማሰልጠን እና ለማበልፀግ በስፋት ግልጋሎት ላይ ይውላል፡፡ በተጨማሪም ዳታዎችን በማጠናቀር የትንበያ መላምቶችን ለማዘጋጀት የላቀ አቅም ያላቸው ቁጥርን ማስላት የሚያስችሉ ክምችቶችን ይዟል፡፡
🚩ቴንሰርፍሎው ድምፅን እና ምስሎችን ለሚለዩ የተለያዩ መተግበሪያዎች የጀርባ አጥንት መሆኑ ይነገራል፡፡
ድሮፕቦክስ፣ ኢቤይ፣ ትዊተር፣ ኡበር እና ኢንቴልን የመሳሰሉ ትላልቅ ተቋማት ሳይቀሩ ይህንን ሶፍትዌር ጥቅም ላይ በማዋል ይታወቃሉ፡፡
▫️2. አይ.ቢ.ኤም ዋትሰን / IBM Watson
አይ.ቢ.ኤም ዋትሰን በተቋማት የሚደረጉ ጥናት እና ምርምሮችን እንዲሁም ግኝቶችን ለማፋጠን የተሻለ አቅምን መፍጠር እንደሚችል ይነገርለታል፡፡ ብዙ ተቋማት ሶፍትዌሩ የሚሰጠውን እድል በመጠቀም ዳታቸውን ለማጥናት፣ የፈጠራ ስራዎቻቸውን ለማሰባሰብ፣ ስለ ስራቸው ጥልቅ እይታን ለማግኘት እና ቀጣይ የስራ አፈጻጸማቸውን በቀላሉ ለመተንበይ አገልግሎት ላይ ያውሉታል፡፡
🚩በትምህርት፣ በጤና ጥበቃ፣ በፋይናንስ፣ በትራንስፖርት እንዲሁም በኃይል ዘርፍ የተሰማሩ ተቋማት ሶፍትዌሩን አገልግሎት ላይ በማዋል ውጤት አግኝተውበታል፡፡ በተጨማሪም ይህንን ሶፍትዌር በመጠቀም ምርታማነትን ማሳደግ እንደሚቻል የዘርፉ ምሁራን ይጠቁማሉ፡፡
● For Computer and Technology 👇👇👇
t.me/TechnologyMasterPage
● For Motivational Texts 👇👇
t.me/InspiresWorld
● For English Grammar 👇👇
t.me/Worldwide_Students

❤3👍1
▬▬▬ በሰው ሲተላለፍ
ፍርዳቸው እነደሆነ - እንደ ሰምበሌጥ ደካማ
ከህሊናቸው ተጣልተው - እውነትን የቀማ
ከሰይጣን ወዳጅ - የሐጢያት ጓደኛ
እጅና ጓንት ሆኖ - ውሸት ፈራጅ ዳኛ
እኔ የሚል በዛ - ከማስቀደም እኛ
እስቲ እንወቃቀስ - ጥፋቱ የነሱ ወይስ የኛ
ውለታዋን የከፈለ - ወይስ ያስያዛት በእዳ
እሷን የጎዳት ወይስ - ለሷ የተጎዳ
መፃሐፍ ስለቻለ የፃፈ - ወይስ አውጥቶ ያወረደ
ውሸት የተናገረ - ወይ ሀቅን የወደደ
እንደ ውሃ የፈሰሰ - ወይስ ለእውነት የተሰደደ
እስቲ እነወቃቀስ - መነው እውነተኛ
እኮ ንገሩኛ - ማነው ሀሰተኛ
ዘረኝነት ሰባኪው - እሱ ወይስ እኛ
እኔ ልኑር የሚል - ሌላውን የቀደደ
በሰው ማንነት - በብዕሩ የቀለደ
እንዴት ደጋፊው በዛ!? - እንዴትስ ተወደደ
ቆይ ሰው ይደግፈዋል - ሰው እያሽመደመደ
እንዲህ አይነት ቅልነት - ዛሬነው የተለመደ!?
ወይስ ድሮም አለ - በአባቶታችን ጊዜ!?
ግን ታሪክ ሲነበብ - ሲደመጥ ኑዛዜ
እነሱ ዘንድ አነበረም - የዘረኝነት አባዜ
ወይስ ማናውቀው አለ!? - ውሸት ነው ታሪኩ?
አአዕምሯቸው ጥግ - ይል ነበር ልኩ!?
በሰው ሲተላለፍ
በቀላሉ ምናልፍ መስሎን - የህይወትን ምዘና
ከዘረኝነት ተጋብተን - ብዙ ተዋልደናልና
እኮ አበጣበጡን - እነ እገሌ መጡና
አታስቡ ይሉናል - ምን ሞልቶልን አናስብ
ልጅ እቅፋት ሲመታው - በዕውቀት ሲያብብ
አልፈልግም እያለ - የዘረኝነትን ቀለብ
የሱ ልብ ታጥቦ - የኛን ልብ ሚያጥብ
........ ግን ምን ዋጋ አለው!
ዘረኝነትን ለመዝራት - እኛ አለንላቸው
ልባቸውን በርዘን - ወደ ጥቁር ቀየርነባቸው
በቃ እነሱ ይገሱ - እኛን ያሳላቸው
የሚጣፍጥ አንደበት - ደሞም ሲያምርባቸው።
.........ግን ምን ዋጋ አለው!
ከኛ እየተማሩ - ትልቅን ማሳነስ
ከኛ እየተማሩ - የወንድም ደም ማፍሰስ
በዘረኝነት ተባልተን - ስንቦጫጨቅ እርሰበርስ
ፍቅርንና ሰላምን አባረን - ሁኸትን ስንከልስ
እኮ ከኛ እያዩ ማሸነፍን - በውሸት ማስረጃ
ወደመሬት እየቀበርነው - የሀቅ ደረጃ
ይህን ከኛ ካዩ - የወደፊታቸውን እንጃ
በሀገሬ ዶክተር - በውጭ ሰርተፊኬት
ወንድምነትን በጎሳ - ያቀያየርን ለት
ብሄርህ ምንድነው!? - እንደ ድግሪ ወረቀት
በዘረኝነትነው የምንቀጥረው - አደለም በዕውቀት
ሰርስረን እያጣራን - የወንድማችንን ማንነት
ልጅም እኮ ያያል - ይህንን ውድቀት
ቆይ..! ማንነቱን - ሰርስረን ብናጣራስ
የገኘን ሰው አለ - የሆነ ከማርስ!?
ሁላችንም የአደም ልጅ ነን - በዘር አንኮፈስ
ወንድማችን እንጂ - ሌላ አካል አደለም
የአብራካችን ክፋይ - የራሳችን ወንድም
እኛው ነን እንጂ - ሌላ ወገን ዬለም
በሰው ሲተላለፍ
የእውነት ጎተራ - የፍህተኞች መንደር
ጠባቦች መጡና - ያጨዱብሽ አቃቂር
አሳምራለሁ የሚሉ - በዘረኝነት ዲኮር
ልብ እኮ ንጉስ ነው - ሌላው አካል ወታደር
ስሚኝ እትዮጵያ - አንቺነው ማናግር
ንጉሱ አስተሳሰብ ነው - ወታደሩማ ህዝብሽ
ንጉስ ሲመረዝ - ወታደሩ የሚያፈርስሽ
በገዛ ልጆችሽ - ቁልቁል የወረድሽ
በዘረኝነት ሰባኪዎች - ተበላሸ ምድርሽ
ምድርሽ እኮ ነበር - የሐቅ መጠሊያ
የእወነተኞች እናት - ፀሎትሽ መሣሪያ
ለሰው ፈጡር በሙሉ - የሆንሽ መከለያ
የደግነት ተምሳሌት - የፍቅር ማሳያ
የእቁ ሀበሾች እናት - የሌለሽ አምሳያ
አሷማ አደለም - እኛ አገት እንድፋ
እኛ ስንቀዳት - እሷ ግን ስትሰፋ
ለኛ ባለችበት - ለም በደሏ ይክፋ!?
ኮትኩታ ለማሳደግ - ሌተቀን ስትለፋ
ግን ዘረኝነት - ኬት መጥቶ አካፋ?
በሰው ሲተላለፍ
ዛሬስ ምን ተገኘ - እኮ ምን ነካሽ
ጥሩ አላበቅልም አለ - ያ! ለምለም ምድርሽ
በጥንብ ዘረኝነት - አገትሽን ደፋሽ
እኛነን ጥፋተኛው - አንቺስ ምን አጠፋሽ
ኑ! ልጆቼ አልሽ እንጂ - መች ክፉ ወጣሽ
እንግዲያው ስሚኝ - አንድ አሳዛኝ ዜና
እኔም በጣም ከፍቶኛል - ሚያስደነግጥ ነውና
በቃ ለቅሶ ያዢ - ልጆቼ አልቋል ብለሽ
በቁማቸው ሞቷል - እውነቱን ልገርሽ
ዘረኝነት የሚባል ጥንብ - ልጆችሽን ነጠቀሽ።
ግን ብዙ አደንግጪ - አትጪብኝ ሰላም
የሞተው አስተሳሰባቸው እንጂ - አካላቸው አይደለም
የፍትህ ጅማሮ - አንቺ እናት-አለም
ብዕር እንኳን የለ - ሚገልፅሽ ቀለም
ሰው በዛብሽ እንጂ - ዘረኝነትን የሚያልም
ማሽላ ጠባቂ - ለያድር ያመሻል
ፈርተን ነው እንጂ - እግራችን ልሂድ ብሏል
በዘረኝነት እሾህ - ውስጥ ውስጡ ቆስሎዋል።
በሰው ሲተላለፍ
ሀገር እንደ ሸንኮራ - ቆራርጠን የሸጥን
ያን ደግ ሰላም - በክፋት የለወጥን
ያ! ግዙፍ አባይ - ሚያልቅ የመሰለን
ስጡኝ ብሎ ሲለምን - አኛ የከለከልን
በረሃብና ጥም - ህዝባችንን ጨረስን
እቺ ናት እትዮጵያ - ቀደን የሰፋናት
የሳቅ አባሳደር - ለቅሶ ያስለመድናት
የድሃ እናት - ንፍግ ያደረግናት
የሰላም ወጀብ - ጥሩ አትውለጂ ያልናት
ኑ! ወደኔ እያለች - እኛ የሄድንባት
እስቲ እንተወው - የትላንቱን ዱላ
ተፈጥሮ የመሰለን - ከታጨቀ አተላ
የኛ ሆኖ አረፈ - የወቃነው ሁላ
እኮ የኛ ወገን - ዬለም የሚጠላ
ግን! ምን አይነት ጊዜ ነው - እንደው ወገኖቼ!?
ደምሬ ብቀንስ - ህሳቡን ሰርቼ
አካፌዬ ባባዛ - ምድሩን ለክቼ
ለሁሉም ይበቃል ልል አልኩና - ዝም አልኩኝ ፈርቼ
ግን ምን አይነት ዘመነው - እንደው ወገኖቼ
አረመኔነት ከፍ ብሎ - ተዋርዶ ደግነት
አዋቂነት ቀሎ - አላዋቂነት የሚሞገስበት
አውነተኝነት - እንደ ውሸተኝነት
ታማኝነት - እንደ አሰመሳይነት
ዶንቆሮ ብቻ - እኔ አወቅኩ የሚልበት
ትንሽነት ከፍ ብሎ - ዝቅ የሚል ትልቅነት
ምን አይነት ጊዜ ነው - እንደው ወገኖቼ
ምን አይነት ዓለም ናት - እንደው ዘመዶቼ
በሰው ሲተላለፍ
ፀሀይም እንደሆነች - ምድርን በኢዳ አላያዘቻትም
እስካሁን ላበራሁልሽ - ክፈይ አላለቻትም
ፀሀይ እያበራችልን - በምድር ስንቦርቅ
አቤት ውለታዋ - ወይ ብርሃኗ ማያልቅ
እናም እስከዛሬ - ፀሃይ በብርሃን
ክፍያ ሳትጠይቅ - ኖራለች በርታልን
ብርሃኗ ይቀጥላል - ወደፊትም እንደሆን
እኛ ግን ለአረመኔነትታችን - አበል ጠየቅን።
ከሰባት ቀን አይዘልም - የዚህ የሳምንቱ
ከአራት ሳምንት አይበልጥም - እድሜው የወራቱ
365 ቀን - አንድነው ዓመቱ
ሳይዛባ ይቆጥራል - ካልሰከረ ሰዓቱ
እኛ ማየት ከቻልን - መሽቶ ይነጋል ወቅቱ
ታዲያ ምን ቀየረ - የሰው ዘረኝነቱ!?
እስቲ እንተማመን - ሀገራችን እቺ ናት
የአንድነት መድረክ - የኛ የበተናት
የፍቅር ተምሳሌት - ክፋት የዘራንባት
ገለባውን ከእንክርዳድ - በአንድ ያማሰልንባት
ቢሆንም ግን ወገኖቼ! - አሁንም የኛው ናት
ሰላም እንዝራበት - በትላቱ ክፋት
ስድቡን ተወት እናርገው - እንደ ወትሮው ምርቃት
እያወራን ያለነው - ስለ ሙሉ ጎጆ
አይደለም ስለኔ ቤት - የስልጣን ኮሮጆ
እየፃፍን ያለነው - ስለኛዋ ሀገር
ለምን እንባላ - ለምን እንሸበር
ሀገርን በቁና - ለመንስ እንስፈር
ራሳችን ሊወጋን - ለም እሾህ እንጠር
የዕይታችን አድማስ - ለምስ ይጠር
ለምንስ አናስተውል - ክፋት ከመቀመር
መፅፍ ስለቻልን ብቻ - ለምን እንፃፍ
ህዝብን ለማጋጨት - በሚዲያ እለፍፍ!?
ነገ እኮ ይደርሳል - የዘሬው ቀን ሲያልፍ!
ድፍን ሙሉ ሀገር - በሽታ ሲሰለፍ
እኛንም ዪዘናል - በሰው ሲተላለፍ
እኛንም ዪዘናል - በሰው ሲተላለፍ።
በረሻድ ሙዘሚል
t.me/InspiresWorld
ፍርዳቸው እነደሆነ - እንደ ሰምበሌጥ ደካማ
ከህሊናቸው ተጣልተው - እውነትን የቀማ
ከሰይጣን ወዳጅ - የሐጢያት ጓደኛ
እጅና ጓንት ሆኖ - ውሸት ፈራጅ ዳኛ
እኔ የሚል በዛ - ከማስቀደም እኛ
እስቲ እንወቃቀስ - ጥፋቱ የነሱ ወይስ የኛ
ውለታዋን የከፈለ - ወይስ ያስያዛት በእዳ
እሷን የጎዳት ወይስ - ለሷ የተጎዳ
መፃሐፍ ስለቻለ የፃፈ - ወይስ አውጥቶ ያወረደ
ውሸት የተናገረ - ወይ ሀቅን የወደደ
እንደ ውሃ የፈሰሰ - ወይስ ለእውነት የተሰደደ
እስቲ እነወቃቀስ - መነው እውነተኛ
እኮ ንገሩኛ - ማነው ሀሰተኛ
ዘረኝነት ሰባኪው - እሱ ወይስ እኛ
እኔ ልኑር የሚል - ሌላውን የቀደደ
በሰው ማንነት - በብዕሩ የቀለደ
እንዴት ደጋፊው በዛ!? - እንዴትስ ተወደደ
ቆይ ሰው ይደግፈዋል - ሰው እያሽመደመደ
እንዲህ አይነት ቅልነት - ዛሬነው የተለመደ!?
ወይስ ድሮም አለ - በአባቶታችን ጊዜ!?
ግን ታሪክ ሲነበብ - ሲደመጥ ኑዛዜ
እነሱ ዘንድ አነበረም - የዘረኝነት አባዜ
ወይስ ማናውቀው አለ!? - ውሸት ነው ታሪኩ?
አአዕምሯቸው ጥግ - ይል ነበር ልኩ!?
በሰው ሲተላለፍ
በቀላሉ ምናልፍ መስሎን - የህይወትን ምዘና
ከዘረኝነት ተጋብተን - ብዙ ተዋልደናልና
እኮ አበጣበጡን - እነ እገሌ መጡና
አታስቡ ይሉናል - ምን ሞልቶልን አናስብ
ልጅ እቅፋት ሲመታው - በዕውቀት ሲያብብ
አልፈልግም እያለ - የዘረኝነትን ቀለብ
የሱ ልብ ታጥቦ - የኛን ልብ ሚያጥብ
........ ግን ምን ዋጋ አለው!
ዘረኝነትን ለመዝራት - እኛ አለንላቸው
ልባቸውን በርዘን - ወደ ጥቁር ቀየርነባቸው
በቃ እነሱ ይገሱ - እኛን ያሳላቸው
የሚጣፍጥ አንደበት - ደሞም ሲያምርባቸው።
.........ግን ምን ዋጋ አለው!
ከኛ እየተማሩ - ትልቅን ማሳነስ
ከኛ እየተማሩ - የወንድም ደም ማፍሰስ
በዘረኝነት ተባልተን - ስንቦጫጨቅ እርሰበርስ
ፍቅርንና ሰላምን አባረን - ሁኸትን ስንከልስ
እኮ ከኛ እያዩ ማሸነፍን - በውሸት ማስረጃ
ወደመሬት እየቀበርነው - የሀቅ ደረጃ
ይህን ከኛ ካዩ - የወደፊታቸውን እንጃ
በሀገሬ ዶክተር - በውጭ ሰርተፊኬት
ወንድምነትን በጎሳ - ያቀያየርን ለት
ብሄርህ ምንድነው!? - እንደ ድግሪ ወረቀት
በዘረኝነትነው የምንቀጥረው - አደለም በዕውቀት
ሰርስረን እያጣራን - የወንድማችንን ማንነት
ልጅም እኮ ያያል - ይህንን ውድቀት
ቆይ..! ማንነቱን - ሰርስረን ብናጣራስ
የገኘን ሰው አለ - የሆነ ከማርስ!?
ሁላችንም የአደም ልጅ ነን - በዘር አንኮፈስ
ወንድማችን እንጂ - ሌላ አካል አደለም
የአብራካችን ክፋይ - የራሳችን ወንድም
እኛው ነን እንጂ - ሌላ ወገን ዬለም
በሰው ሲተላለፍ
የእውነት ጎተራ - የፍህተኞች መንደር
ጠባቦች መጡና - ያጨዱብሽ አቃቂር
አሳምራለሁ የሚሉ - በዘረኝነት ዲኮር
ልብ እኮ ንጉስ ነው - ሌላው አካል ወታደር
ስሚኝ እትዮጵያ - አንቺነው ማናግር
ንጉሱ አስተሳሰብ ነው - ወታደሩማ ህዝብሽ
ንጉስ ሲመረዝ - ወታደሩ የሚያፈርስሽ
በገዛ ልጆችሽ - ቁልቁል የወረድሽ
በዘረኝነት ሰባኪዎች - ተበላሸ ምድርሽ
ምድርሽ እኮ ነበር - የሐቅ መጠሊያ
የእወነተኞች እናት - ፀሎትሽ መሣሪያ
ለሰው ፈጡር በሙሉ - የሆንሽ መከለያ
የደግነት ተምሳሌት - የፍቅር ማሳያ
የእቁ ሀበሾች እናት - የሌለሽ አምሳያ
አሷማ አደለም - እኛ አገት እንድፋ
እኛ ስንቀዳት - እሷ ግን ስትሰፋ
ለኛ ባለችበት - ለም በደሏ ይክፋ!?
ኮትኩታ ለማሳደግ - ሌተቀን ስትለፋ
ግን ዘረኝነት - ኬት መጥቶ አካፋ?
በሰው ሲተላለፍ
ዛሬስ ምን ተገኘ - እኮ ምን ነካሽ
ጥሩ አላበቅልም አለ - ያ! ለምለም ምድርሽ
በጥንብ ዘረኝነት - አገትሽን ደፋሽ
እኛነን ጥፋተኛው - አንቺስ ምን አጠፋሽ
ኑ! ልጆቼ አልሽ እንጂ - መች ክፉ ወጣሽ
እንግዲያው ስሚኝ - አንድ አሳዛኝ ዜና
እኔም በጣም ከፍቶኛል - ሚያስደነግጥ ነውና
በቃ ለቅሶ ያዢ - ልጆቼ አልቋል ብለሽ
በቁማቸው ሞቷል - እውነቱን ልገርሽ
ዘረኝነት የሚባል ጥንብ - ልጆችሽን ነጠቀሽ።
ግን ብዙ አደንግጪ - አትጪብኝ ሰላም
የሞተው አስተሳሰባቸው እንጂ - አካላቸው አይደለም
የፍትህ ጅማሮ - አንቺ እናት-አለም
ብዕር እንኳን የለ - ሚገልፅሽ ቀለም
ሰው በዛብሽ እንጂ - ዘረኝነትን የሚያልም
ማሽላ ጠባቂ - ለያድር ያመሻል
ፈርተን ነው እንጂ - እግራችን ልሂድ ብሏል
በዘረኝነት እሾህ - ውስጥ ውስጡ ቆስሎዋል።
በሰው ሲተላለፍ
ሀገር እንደ ሸንኮራ - ቆራርጠን የሸጥን
ያን ደግ ሰላም - በክፋት የለወጥን
ያ! ግዙፍ አባይ - ሚያልቅ የመሰለን
ስጡኝ ብሎ ሲለምን - አኛ የከለከልን
በረሃብና ጥም - ህዝባችንን ጨረስን
እቺ ናት እትዮጵያ - ቀደን የሰፋናት
የሳቅ አባሳደር - ለቅሶ ያስለመድናት
የድሃ እናት - ንፍግ ያደረግናት
የሰላም ወጀብ - ጥሩ አትውለጂ ያልናት
ኑ! ወደኔ እያለች - እኛ የሄድንባት
እስቲ እንተወው - የትላንቱን ዱላ
ተፈጥሮ የመሰለን - ከታጨቀ አተላ
የኛ ሆኖ አረፈ - የወቃነው ሁላ
እኮ የኛ ወገን - ዬለም የሚጠላ
ግን! ምን አይነት ጊዜ ነው - እንደው ወገኖቼ!?
ደምሬ ብቀንስ - ህሳቡን ሰርቼ
አካፌዬ ባባዛ - ምድሩን ለክቼ
ለሁሉም ይበቃል ልል አልኩና - ዝም አልኩኝ ፈርቼ
ግን ምን አይነት ዘመነው - እንደው ወገኖቼ
አረመኔነት ከፍ ብሎ - ተዋርዶ ደግነት
አዋቂነት ቀሎ - አላዋቂነት የሚሞገስበት
አውነተኝነት - እንደ ውሸተኝነት
ታማኝነት - እንደ አሰመሳይነት
ዶንቆሮ ብቻ - እኔ አወቅኩ የሚልበት
ትንሽነት ከፍ ብሎ - ዝቅ የሚል ትልቅነት
ምን አይነት ጊዜ ነው - እንደው ወገኖቼ
ምን አይነት ዓለም ናት - እንደው ዘመዶቼ
በሰው ሲተላለፍ
ፀሀይም እንደሆነች - ምድርን በኢዳ አላያዘቻትም
እስካሁን ላበራሁልሽ - ክፈይ አላለቻትም
ፀሀይ እያበራችልን - በምድር ስንቦርቅ
አቤት ውለታዋ - ወይ ብርሃኗ ማያልቅ
እናም እስከዛሬ - ፀሃይ በብርሃን
ክፍያ ሳትጠይቅ - ኖራለች በርታልን
ብርሃኗ ይቀጥላል - ወደፊትም እንደሆን
እኛ ግን ለአረመኔነትታችን - አበል ጠየቅን።
ከሰባት ቀን አይዘልም - የዚህ የሳምንቱ
ከአራት ሳምንት አይበልጥም - እድሜው የወራቱ
365 ቀን - አንድነው ዓመቱ
ሳይዛባ ይቆጥራል - ካልሰከረ ሰዓቱ
እኛ ማየት ከቻልን - መሽቶ ይነጋል ወቅቱ
ታዲያ ምን ቀየረ - የሰው ዘረኝነቱ!?
እስቲ እንተማመን - ሀገራችን እቺ ናት
የአንድነት መድረክ - የኛ የበተናት
የፍቅር ተምሳሌት - ክፋት የዘራንባት
ገለባውን ከእንክርዳድ - በአንድ ያማሰልንባት
ቢሆንም ግን ወገኖቼ! - አሁንም የኛው ናት
ሰላም እንዝራበት - በትላቱ ክፋት
ስድቡን ተወት እናርገው - እንደ ወትሮው ምርቃት
እያወራን ያለነው - ስለ ሙሉ ጎጆ
አይደለም ስለኔ ቤት - የስልጣን ኮሮጆ
እየፃፍን ያለነው - ስለኛዋ ሀገር
ለምን እንባላ - ለምን እንሸበር
ሀገርን በቁና - ለመንስ እንስፈር
ራሳችን ሊወጋን - ለም እሾህ እንጠር
የዕይታችን አድማስ - ለምስ ይጠር
ለምንስ አናስተውል - ክፋት ከመቀመር
መፅፍ ስለቻልን ብቻ - ለምን እንፃፍ
ህዝብን ለማጋጨት - በሚዲያ እለፍፍ!?
ነገ እኮ ይደርሳል - የዘሬው ቀን ሲያልፍ!
ድፍን ሙሉ ሀገር - በሽታ ሲሰለፍ
እኛንም ዪዘናል - በሰው ሲተላለፍ
እኛንም ዪዘናል - በሰው ሲተላለፍ።
በረሻድ ሙዘሚል
t.me/InspiresWorld
❤3
#ላፕቶፓችን_ያለኛ_ፍቃድ_ፍላሽ_ዲሰክ_እንዳይቀበል_ማድረግ_እንዴት_እንደ_ሚቻል_ላሳያችሁ
ፍላሽ ዲሰክ ፋይሎችን የምናስቀምጥበትና በቀላሉ ይዘነው የምንቀሳቀሰውማሽን ነው፡፡ በስራ ምክንያትም ይሁን በሌላ ፋይሎችን ላማስተላለፍና ኮፒ ለማድረግ ሰዎች የሚጠቀሙበት ፍላሽ ዲሰኮች ላፕቶፓችን ላይ እንሰካል፡፡
ላፕቶፓችን ላይ ያገኘነውን ፍላሽ ዲሰክ የምንሰካ ከሆነ ደሞ ላፕቶፓችን አደጋ ውስጥ ይገባል፡፡
ምክንያቱም ፍለሽ ዲሰክ ፋይሎችን ብቻ ሳይሆን ቫይረሶችንም ስለሚያስቀምጥ ያገኘነውን ፍላሽ ላፕቶፓችን ላይ የምንሰካ ከሆነ በፍላሽ ዲሰኮች አማካኝነት ቫይረሶች ወደ ኮፒውተራችን በመግባት ላፕቶፓችን ላይ አደጋ ሊያደርሱ ይችላል፡፡
ከኛ ፍቃድም ውጪ ሳናውቀው አንድ ሰው ተደብቆ ላፕቶፓችን ላይ ፍለሽ ዲሰክ በመሰካት ላፕቶፓችንን ክጥቅም ውጪ ሊያደርገው ይችላል፡፡
ስለዚህ በተለይ ያለኛ ፍቃድና እውቀት ላፕቶፓችን ፍላሽ ዲሰክ እንዳይቀበል ለማድረግ የሚከተሉትን ስቴፖች መከተል ነው፡፡
1ኛ፡-መጀመሪያ Start በተንን ክሊክ እናደርግና gpedit.msc ብለን እንፅፍና ኢንተር እንጫናል፣
2ኘ፡- የተለያዩ አማራጮች የያዘ ሊስት ይመጣል፤ ሊስቱ ውስጥ “Local Group Policy Editor” የሚለውን ምረጡ፣
3ኛ፡-ከዚያ የሚከተለውን መንግድ ተከተሉ ፤ computer configuration>administrative templates>system>Removable storage access
4ኛ፡-አሁን በቀኝ በኩል ከሚመጡ አማራጮች ውስጥ “All Removable Storage Classes: Deny all access” የሚለውን ክሊክ ማድረግ፣
5ኛ፡- “Enable” የሚል አለ እሱን መምረጥ፣
6ኛ፡- “Apply”> “Ok” ሁለቱንም ተራ በተራ ክሊክ ማድረግ፡፡
አለቀ፡፡ ካሁን በኋላ ማንም ሰው ፍላሽ ዲስኩን ላፕቶፓችሁ ላይ መሰካት አይችልም፡፡
ምናልባት ይህንን የከለከላችሁትን አክሰስ መመለስ ስትፈልግ ከላይ ከ1 እስከ 4 ስቴፖችን እንዳሉ ተከተሉ እና፣
5ኛ፡- “Not Configure” የሚል አለ እሱን መምረጥ፣
6ኛ፡- “Apply”> “Ok” ሁለቱንም ተራ በተራ ክሊክ ማድረግ፡፡
#ሼር_ይደረግ
➤ እግረመንገዳችሁን አነቃቂፅሑፎችን የምለቅበት የቴሌግራም ገፄን በመቀላቀል አብሮነታችሁ አይለየኝ👇

Document Formatting.Mp4
58.8 MB
#Document_formatting
በቪድዮ
➞ Bold, Italic, Underlie
➞ Insert Column, Picture, clip art/Smart art, Table and Tible design, Watermarks, shapes, Page border and
#ከላይ ያሉትን ነገሮች እንዴት እንደምንሰራ የምታሳይ ቪድዮ!!
#Title: Document formatting
#MB Size:
#Time:
#Sound:
#Prepared by: #Reshad_Muzemil
#ትንሽም ቢሆን ያግዛችኋል አውርዱና ኢዩት!!
#ለኮሌጅ ተማሪዎች ያዘጋጀሁት ቪድዮ ነው፤ ለናተም ይጠቅማችኋል!
t.me/TechnologyMasterPage
በቪድዮ
➞ Bold, Italic, Underlie
➞ Insert Column, Picture, clip art/Smart art, Table and Tible design, Watermarks, shapes, Page border and
Word art#ከላይ ያሉትን ነገሮች እንዴት እንደምንሰራ የምታሳይ ቪድዮ!!
#Title: Document formatting
#MB Size:
58.8MB#Time:
26 minutes#Sound:
Reshad Muzemil#Prepared by: #Reshad_Muzemil
#ትንሽም ቢሆን ያግዛችኋል አውርዱና ኢዩት!!
#ለኮሌጅ ተማሪዎች ያዘጋጀሁት ቪድዮ ነው፤ ለናተም ይጠቅማችኋል!
t.me/TechnologyMasterPage
❤3