➡️ ዛሬ የምናየው ሀርድ ዲስክን Hard Disk እንዴት ለሁለት ወይም ከዚያ በላይ መክፈል እንችላለን የምለውን ነው Step by step:-
ለምሳሌ Local disk C: ካለን ለሁለት ለመክፈል ለምሳሌ
👉 1 right click on My computer
👉 2 ከዛ Manage የሚለውን እንነካለን
👉 3 ከዛ ከሚመጡት ምርጫዎች ውስጥ disk management የሚለውን እንመርጣለን
👉 4 ከዛ ለመክፈል የምንፈልገውን ዲስክ C:
በመምረጥ right click እናደርጋለን
👉 5 ከዛ shrink volume የሚለውን እንመርጣለን ትንሽ ሰከንድ ይቆያል
👉 6 ከዛ የምንፈልገውን መጠን በመፃፍ shrink የሚለውን click አድርጎ መጠበቅ
መጠንቀቅ ያለብን ነገር:- ቁጥሩ በሜጋ ባይት ነው የሚገባው ለምሳሌ 50GB መክፈክ ብትፈልጉ 1GB ማለት 1024 MB ነው ይህ ማለት 50*1024=51,200 ይሆናል ስለዚህ 51,200 ብለን ማስገባት ይጠበቅብናል።
👉7 ከዛ በጥቁር ቀለም ከታች (unlocated) የሚለው ላይ right click ማድረግ
👉 8 click on "new simple volume
ከዛ next next next እያሉ እስከመጨረሻው መቀጠል::
➡️ ይሄን ስናደርግ ምንም አይነት መረጃ አይጠፋብንም።
t.me/TechnologyMasterPage

የሞባይል ባትሪን እድሜ ለማስረዘም እነዚህን 5 ነጥቦች ይተግብሩ
1 👉 Original ( ትክክለኛ ) ሳይሆኑ ለገንዘብ ተብለው በርካሽ ዋጋ ለገበያ የሚቀርቡ ኦርጅናል ያልሆኑ ቻርጀሮች ዋጋቸው ሪካሽ ብሆንም ጥራታቸው ዝቅተኛ በመሆናቸው ቻርጅ በምናደርግበት ጊዜ ለሞባይል ባትሪው ያልተመጣጠነ የኤሌትሪክ ሀይል በመስጠት ይጎደዋል ወይም የሞባይሉን ባትሪ እድሜ ያሳጥራል፡፡
2 👉 ሞባይላችንን ቻርጅ እያደረግን አለመጠቀም
ሞባይል ስልኮች ቻርጅ በሚደረጉበት ጊዜ ስልክ መደወል፣ ጌም መጫወት፣ ኢንተርኔት መጠቀም የባትሪውን እድሜ ከማሳጠሩ ባለፈ ለተጠቃሚዎቹ አደጋ ሊያስከትል ይችላል በተጨማሪም ሞባይላችንን ራሱ ሊፈነዳብን ይችላል።
3 👉 ሞባይሎቻችንን ቻርጅ ሰክቶ አለማሳደር ( ሌሊቱን ሙሉ ቻርጅ አለማድረግ ) ሌሊቱን ሙሉ ቻርጅ ማድረግ አንዱ ባትሪን ከሚገድሉ ችግሮች መካከል አንዱ ነው፡፡ ባትሪው ከምሽት ጀምሮ ሌሊት ሙሉ ቻርጅ ሲያደርግ 100 ፐርሰንት መሙላቱ የማይቀር ሲሆን ከሞላ በኋላ የኤሌክትሪክ ፓወሩ ባትሪውን መደብደቡ የማይቀር ነው፡፡
የሞላ ነገር ሁሉ መፍሰሱ እንደማይቀር ሁሉ ሞልቶ የሚፈስ ነገር ደግሞ እቃው ላይ ጉዳት ያስከትላል፤ በተመሳሳይ ሁኔታ ተሰክቶ ያደረ ባትሪ ከአቅሙ በላይ ስራ ይበዛበታል፡፡
4 👉 ሞባይል ስልክን አልፎ አልፎ ማጥፋት ሞባይል ስልክን አለማጥፋት ሌላው የባትሪን እድሜ ከሚቀንሱ ውስጥ አንዱ ሲሆን ሞባይል ስልኮች እንደማንኛውም ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች እና ማሽን እረፍት ያስፈልጋቸዋል፡፡ ቢቻል በምሽት ወደ መኝታ ስንሄድ አልፎ አልፎ ስልኮቻችንን ብናጠፋ ይመከራል፡፡ ብዙዎቻችን የሞባይል ስልካችን በስራ ላይ የሚመስለን ስንደውል፣
ሲደወልልን፣ አንዳንድ ነገሮችን በስልኮቻችን ስንጠቀም ብቻ ባትሪ የሚጠቀም ይመስለናል፤ ሆኖም ግን የባትሪው የመጠቀም መጠን ይለያያል እንጂ ሞባይሉ ሲከፈት በላዩ ላይ ያሉት ክፍት የተደረጉ ሰርቪሶች ማለትም ብሉቱዝ፣ጂፒኤስ፣ ዳታ ወዘተ ባትሪውን ይጠቀማሉ፡፡
5 👉 ባትሪው 0% እስኪሆን ድረስ አለመጠበቅ 0% እስክሆን ጠብቀን ቻርጅ ማድረግ ይህም የባትሪውን እድሜ የሚያሳጥሩት አንዱ ነው ባትሪው ግማሽ ወይም ሩብ ሲቀረው ቻርጅ ብናደርግ የተሻለ የባሪውን እድሜ ይጨምርልናል።
Like Share Follow Invite በማድረግ ለሌሎች ያድርሱ !!

❤5
“አግራሞቴን በብዕር” ከተሰኘው የፅሑፍ ማህደሬ የተወሰዱ የድንቅ መስመሮች ሀሳብ ▼▼
➝የእይታን አድማስ የሚያሰፉበት፣
➝የጥሩነት ጥሩነት የሚያውቁበት፣
➝የመጥፎነትን መጥፎነት የሚያውቁበት፣
➝ለነገሮች ያሎትን ምልከታ የሚያሳድግ።
➝ጊዜ ሮጦ እንዲያመልጦት ሳይሆን ጊዜን ሮጠው እንዲያመልጡ የሚያግዝ።
➝ደግነትን የሚዘክሩ፤ ክፋትን የሚያወግዙ ብሎም የሚጠሉ።
➝አንዳንዴ ደስታ፤ አንዳንዴ ደግሞ ሀዘን የሚቦርቅበት።
➝ሰውና ሰብዓዊነት የሚፋረዱበት፤ ሰብዓዊነት የሚረታበት።
➝የአቅሙን ያህል ለሞከረ የሚያጨበጭብ፤
➝የአቅሙን ያህል ያልሞከረን፤ የአቅሙን እንዲሞክር የሚያነሳሱ።
➝ለውጥን የሚፈሩ ሰዎች ለውጥን የሚያለማምድ፤ ለውጥን የለመዱ ሰዎች ደግሞ ትክክለኛ መለወጥን እንዲለወጡ የሚያደርግ።
➝ዘረኝነት የሚባለውን የካንሰር በሽታ መድሃኒት የሚያቅጣጭ።
➝ፍርሃት የሚባለውን ተራራ የሚደረምስ፤
➝ድፍረት የሚባለውን ግንብ በአግባቡ የሚገነባ።
➝ፍትህን ለማስፈን አስተዋጽኦ የሚዶግም፤
➝ኢፍትሃዊነትን ለማስቀረት የራሱን ጥረት የሚያደርግ።
➝መፃፍ ስለቻልን ብቻ መፃፍ እንደሌለብን የሚያቅጣጭ፤ መናገር ስለቻልን ብቻ መናገር እንደሌለብን ጠቆም የሚያደርግ።
➝የሰው ቁስል ስናክም የኛው ማመርቀዙን፤
የማይድን ስናክም የማይሞት መግደላችንን የሚነግረን።
➝መንገዱ ረጅም ነውና መፍጠን እንዳለብን የሚነግረን፤ ስንፈጥንም ተጠንቅቀን ምናረገውን ክንዋኔ ማከናወን እንዳለብን የሚጦቅምም።
➝የትግል ውጤትና ደረጃን የሚያቅጣጭ።
➝የውሸትን ውሸትነት፤ የእውነትን እውነትነት የሚጦቅም።
➝ህልማችንን ለማሯሯጥ የሚያነሳሳ ልብ ሲያዝን ብዕር ሲያነባ የሚገልፅ፤
● ልብ ሲደሰት፤ ብዕር እየሳቀ የሚያሳይ።
➝ብዕር የተባለን የሳለ ሰይፍ የሚያሞግስና የሚያበረታታ....
▮እነዚህንና ሌሎችንም ድንቅ የሚያነቃቁ አስተማሪ የሆኑ ሐሳቦችን የያዘ....
▮“አግራሞቴን በብዕር” የተሰኘ
● ▮በትንሽ በስመሮች ብዙ ሐሳብን የሚዳስስ
▮የሚያነቃቁና በድንቅ የስነ-ፅሑፍ ዘይቤ የቀረቡ መልዕክቶችን የያዘ ፅሑፍ የሚቀርብበት የናተው መድረክ።
↪️ “አግራሞቴን በብዕር” (“My Marveled with pen”)
↪️ #ስለታማ ሰይፎች (The sharp swords) ብየ የሰየምኳቸውን ፅሑፎች ይዤ መጥቻለሁ!!
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
📚 የቻናሉ ማስፈንጠሪያ (Link) ከታች አለላችቹ!!
● ከኛ ጋር በመሆን፣ አብረን የእይታችንን አድማስ እናስፋው፣
●የመነፅራችን መስታወት እንቀይረው፤
● የእይታችን መነፅሩ ቁጥሩ አንሶ ከሆነም ከፍ እናድርገው!!
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
#በረሻድ_ዒብኑ_ሙዘሚል
t.me/SharpSwords

✅ ደንበኞቹ ከአጭበርባሪዎች ራሳቸውን እንዲጠብቁ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አሳሰበ።
📍ደንበኞች የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሚያዘጋጃቸውን የሽልማት ፕሮግራሞች በመንተራስ የሌብነት ተግባር ከሚፈፅሙ አጭበርባሪዎች ራሳቸውን እንዲጠብቁ የባንኩ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ አሳሰቡ፡፡
📍ወደ ደንበኞች ስልክ ደውለው ሽልማት እንደደረሳቸው በመንገርና ገንዘብ እንዲያስገቡ በመጠየቅ ሌብነት የሚፈጽሙ አጭበርባሪዎች መበራከታቸውን አቶ አቤ ገልፀዋል፡፡
📍ባንኩ ወደ ደንበኞች ስልክ የሚደውልበት አጋጣሚ መኖሩን የተናገሩት አቶ አቤ፣ ነገር ግን ደንበኞቹ ወደ ባንኩ በአካል እንዲቀርቡ ወይም ሰነድ እንዲያቀርቡ እንጂ በስልክ ይህን አስገቡ ያን አስወጡ የሚለው ነገር እንደሌለ አስረድተዋል፡፡
📍ደንበኞች ከባንክ ነው በሚል ስልክ ሲደወልላቸው ከሞባይል ባንኪንግ አገልግሎት ጋር በተያያዘ ምንም አይነት እርምጃ መውሰድ እንደሌለባቸው እና በስልክ መረጃ እንዳይሰጡ ያሳሰቡት አቶ አቤ፣ ይልቁንስ በአቅራቢያቸው ወደሚገኝ ቅርንጫፍ በመሄድ ወይም 951 ላይ በመደወል የመረጃውን ትክክለኛነት ማጣራት እንዳለባቸው ገልፀዋል፡፡
📍የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለሚሰጠው አገልግሎት ስልክ ደውሎ ምንም አይነት ክፍያ እንደማይጠይቅም ነው አቶ አቤ ያስገነዘቡት፡፡
📍በተጨማሪም ደንበኞች ሞባይላቸው ሲጠፋባቸው ወደ ባንኩ ቅርንጫፍ በመሄድ የሞባይል ባንኪንግ አገልግሎታቸው እንዲቋረጥ ማስደረግ እንዳለባቸው አቶ አቤ አሳስበዋል፡፡
@TechnologyMasterPage