Basic Computer Skills
1.87K subscribers
1.22K photos
100 videos
576 files
833 links
#በዚህ የቴሌግራም ቻናል
↪️ Programming
↪️ ቴክኖሎጂ ነክ ትምህርቶችን
↪️ ኮምፒውተር ነክ ትምህርቶችን
↪️Basic Computer Skills
↪️ Software
↪️ AI and AI Skills (Like ChatGPT)

ከላይ የተዘረዘሩትና ሌሎችም ገራሚ ትምህርቶች ይለቀቅበታል!

t.me/BasicComputerSkillsGroup

𝘽𝙮 𝙍𝙚𝙨𝙝𝙖𝙙
Download Telegram
ዛሬ ይዤላችሁ የመጣሁት በቫይረስ የተጠቃን ፍላሽ ያለ Anti-Virus እንዴት አድርገን ማፅዳት እንችላለን የሚለውን ነው ተከታተሉኝ 👉

በመጀመሪያ የሚናፀዳው ፍላሽ ላይ ያሉትን ፍይሎች ሌላ ፍላሽ ላይ ወይም ኮምፒዩተር ላይ ኮፒ ማድረጋችንን ማረጋገጥ አለብን ፍላሹ ላይ ያለው ፋይላችን እንዳይጠፋብን ለማለት ነው።
በመጀመሪያ ኮምፒዩተራችን ላይ 'command prompt' ወይም 'cmd' እንከፍታለን።
( 'cmd'ን ለመክፈት በመፈለጊያችን ላይ cmd ብለን search እናደርጋለን. Cmd
ሲመጣልን right click አድርገን run as administrator የሚለውን በመጫን cmdን
እንከፍታለን)
Cmd ከከፈትን በኋላ የሚከተሉትን ትእዛዞች እናስገባለን
1. DISKPART ብለን ከፃፍን በኋላ ⏎ click Enter
2. LIST DISK ብለን ከፃፍን በኋላ ⏎ click Enter (አሁን በኮምፒውተሩ ላይ ያሉትን ዲስኮች ይዘረዝርልናል. ለማጽዳት
የፈለግነውን ፍላሽ ቁጥር ከለየን በኋላ ወደ ሶስተኛው ትእዛዝ እንሄዳለን። ምሳሌ.disk 1)
3. SELECT DISK * (በኮከቡ ፋንታ ሁለተኛው ትእዛዝ ላይ የለየነውን የፍላሽ ቁጥር እናስገባለን) በመቀጠልም ⏎ click Enter
4. CLEAN ብለን ከፃፍን በኋላ ⏎ click Enter
5. CREATE PARTITION PRIMARY ብለን ከፃፍን በኋላ ⏎ click Enter
6. SELECT PARTITION 1 ብለን ከፃፍን በኋላ ⏎ click Enter
7. ACTIVE ብለን ከፃፍን በኋላ ⏎ click Enter
8. FORMAT FS=FAT32 ብለን ከፃፍን በኋላ ⏎ click Enter በዚህ ጊዜ ሂደቱ የተወሰነ ይዘገያል በትግስት እንጠብቃ
9. ASSIGN ብለን ከፃፍን በኋላ ⏎ click Enter
10. EXIT ብለን ከፃፍን በኋላ ⏎ click Enter
አሁን ፍላሻችንን አፅድተን ጨርሰናል ማለት ነው በዚህ መንገድ ችግር ያለበትን ፍላሽ (Flash) ማስተካከል ወይም ቫይረሱን ማጥፋት እንችላለን ማለት ነው።
በመጠቀም ማንኛውንም ችግር ያለበት ፍላሽ ማስተካከል እንችላለን።

👉 እባክዎን ይህ መረጃ ለሌሎችም እንዲደርስ ፔጁን LIKE እና SHARE ያድርጉ

t.me/TechnologyMasterPage
1
➡️ ዛሬ የምናየው ሀርድ ዲስክን Hard Disk እንዴት ለሁለት ወይም ከዚያ በላይ መክፈል እንችላለን የምለውን ነው Step by step:-

ለምሳሌ Local disk C: ካለን ለሁለት ለመክፈል ለምሳሌ
👉 1 right click on My computer
👉 2 ከዛ Manage የሚለውን እንነካለን
👉 3 ከዛ ከሚመጡት ምርጫዎች ውስጥ disk management የሚለውን እንመርጣለን
👉 4 ከዛ ለመክፈል የምንፈልገውን ዲስክ C:
በመምረጥ right click እናደርጋለን
👉 5 ከዛ shrink volume የሚለውን እንመርጣለን ትንሽ ሰከንድ ይቆያል
👉 6 ከዛ የምንፈልገውን መጠን በመፃፍ shrink የሚለውን click አድርጎ መጠበቅ
መጠንቀቅ ያለብን ነገር:- ቁጥሩ በሜጋ ባይት ነው የሚገባው ለምሳሌ 50GB መክፈክ ብትፈልጉ 1GB ማለት 1024 MB ነው ይህ ማለት 50*1024=51,200 ይሆናል ስለዚህ 51,200 ብለን ማስገባት ይጠበቅብናል።
👉7 ከዛ በጥቁር ቀለም ከታች (unlocated) የሚለው ላይ right click ማድረግ
👉 8 click on "new simple volume
ከዛ next next next እያሉ እስከመጨረሻው መቀጠል::

➡️ ይሄን ስናደርግ ምንም አይነት መረጃ አይጠፋብንም።

t.me/TechnologyMasterPage
የሞባይል ባትሪን እድሜ ለማስረዘም እነዚህን 5 ነጥቦች ይተግብሩ

1 👉 Original ( ትክክለኛ ) ሳይሆኑ ለገንዘብ ተብለው በርካሽ ዋጋ ለገበያ የሚቀርቡ ኦርጅናል ያልሆኑ ቻርጀሮች ዋጋቸው ሪካሽ ብሆንም ጥራታቸው ዝቅተኛ በመሆናቸው ቻርጅ በምናደርግበት ጊዜ ለሞባይል ባትሪው ያልተመጣጠነ የኤሌትሪክ ሀይል በመስጠት ይጎደዋል ወይም የሞባይሉን ባትሪ እድሜ ያሳጥራል፡፡
2 👉 ሞባይላችንን ቻርጅ እያደረግን አለመጠቀም
ሞባይል ስልኮች ቻርጅ በሚደረጉበት ጊዜ ስልክ መደወል፣ ጌም መጫወት፣ ኢንተርኔት መጠቀም የባትሪውን እድሜ ከማሳጠሩ ባለፈ ለተጠቃሚዎቹ አደጋ ሊያስከትል ይችላል በተጨማሪም ሞባይላችንን ራሱ ሊፈነዳብን ይችላል።
3 👉 ሞባይሎቻችንን ቻርጅ ሰክቶ አለማሳደር ( ሌሊቱን ሙሉ ቻርጅ አለማድረግ ) ሌሊቱን ሙሉ ቻርጅ ማድረግ አንዱ ባትሪን ከሚገድሉ ችግሮች መካከል አንዱ ነው፡፡ ባትሪው ከምሽት ጀምሮ ሌሊት ሙሉ ቻርጅ ሲያደርግ 100 ፐርሰንት መሙላቱ የማይቀር ሲሆን ከሞላ በኋላ የኤሌክትሪክ ፓወሩ ባትሪውን መደብደቡ የማይቀር ነው፡፡
የሞላ ነገር ሁሉ መፍሰሱ እንደማይቀር ሁሉ ሞልቶ የሚፈስ ነገር ደግሞ እቃው ላይ ጉዳት ያስከትላል፤ በተመሳሳይ ሁኔታ ተሰክቶ ያደረ ባትሪ ከአቅሙ በላይ ስራ ይበዛበታል፡፡
4 👉 ሞባይል ስልክን አልፎ አልፎ ማጥፋት ሞባይል ስልክን አለማጥፋት ሌላው የባትሪን እድሜ ከሚቀንሱ ውስጥ አንዱ ሲሆን ሞባይል ስልኮች እንደማንኛውም ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች እና ማሽን እረፍት ያስፈልጋቸዋል፡፡ ቢቻል በምሽት ወደ መኝታ ስንሄድ አልፎ አልፎ ስልኮቻችንን ብናጠፋ ይመከራል፡፡ ብዙዎቻችን የሞባይል ስልካችን በስራ ላይ የሚመስለን ስንደውል፣
ሲደወልልን፣ አንዳንድ ነገሮችን በስልኮቻችን ስንጠቀም ብቻ ባትሪ የሚጠቀም ይመስለናል፤ ሆኖም ግን የባትሪው የመጠቀም መጠን ይለያያል እንጂ ሞባይሉ ሲከፈት በላዩ ላይ ያሉት ክፍት የተደረጉ ሰርቪሶች ማለትም ብሉቱዝ፣ጂፒኤስ፣ ዳታ ወዘተ ባትሪውን ይጠቀማሉ፡፡
5 👉 ባትሪው 0% እስኪሆን ድረስ አለመጠበቅ 0% እስክሆን ጠብቀን ቻርጅ ማድረግ ይህም የባትሪውን እድሜ የሚያሳጥሩት አንዱ ነው ባትሪው ግማሽ ወይም ሩብ ሲቀረው ቻርጅ ብናደርግ የተሻለ የባሪውን እድሜ ይጨምርልናል።

Like Share Follow Invite በማድረግ ለሌሎች ያድርሱ !!

t.me/TechnologyMasterPage
5