Basic Computer Skills
1.87K subscribers
1.22K photos
100 videos
576 files
833 links
#በዚህ የቴሌግራም ቻናል
↪️ Programming
↪️ ቴክኖሎጂ ነክ ትምህርቶችን
↪️ ኮምፒውተር ነክ ትምህርቶችን
↪️Basic Computer Skills
↪️ Software
↪️ AI and AI Skills (Like ChatGPT)

ከላይ የተዘረዘሩትና ሌሎችም ገራሚ ትምህርቶች ይለቀቅበታል!

t.me/BasicComputerSkillsGroup

𝘽𝙮 𝙍𝙚𝙨𝙝𝙖𝙙
Download Telegram
ዛሬ ይዤላችሁ የመጣሁት በቫይረስ የተጠቃን ፍላሽ ያለ Anti-Virus እንዴት አድርገን ማፅዳት እንችላለን የሚለውን ነው ተከታተሉኝ 👉

በመጀመሪያ የሚናፀዳው ፍላሽ ላይ ያሉትን ፍይሎች ሌላ ፍላሽ ላይ ወይም ኮምፒዩተር ላይ ኮፒ ማድረጋችንን ማረጋገጥ አለብን ፍላሹ ላይ ያለው ፋይላችን እንዳይጠፋብን ለማለት ነው።
በመጀመሪያ ኮምፒዩተራችን ላይ 'command prompt' ወይም 'cmd' እንከፍታለን።
( 'cmd'ን ለመክፈት በመፈለጊያችን ላይ cmd ብለን search እናደርጋለን. Cmd
ሲመጣልን right click አድርገን run as administrator የሚለውን በመጫን cmdን
እንከፍታለን)
Cmd ከከፈትን በኋላ የሚከተሉትን ትእዛዞች እናስገባለን
1. DISKPART ብለን ከፃፍን በኋላ ⏎ click Enter
2. LIST DISK ብለን ከፃፍን በኋላ ⏎ click Enter (አሁን በኮምፒውተሩ ላይ ያሉትን ዲስኮች ይዘረዝርልናል. ለማጽዳት
የፈለግነውን ፍላሽ ቁጥር ከለየን በኋላ ወደ ሶስተኛው ትእዛዝ እንሄዳለን። ምሳሌ.disk 1)
3. SELECT DISK * (በኮከቡ ፋንታ ሁለተኛው ትእዛዝ ላይ የለየነውን የፍላሽ ቁጥር እናስገባለን) በመቀጠልም ⏎ click Enter
4. CLEAN ብለን ከፃፍን በኋላ ⏎ click Enter
5. CREATE PARTITION PRIMARY ብለን ከፃፍን በኋላ ⏎ click Enter
6. SELECT PARTITION 1 ብለን ከፃፍን በኋላ ⏎ click Enter
7. ACTIVE ብለን ከፃፍን በኋላ ⏎ click Enter
8. FORMAT FS=FAT32 ብለን ከፃፍን በኋላ ⏎ click Enter በዚህ ጊዜ ሂደቱ የተወሰነ ይዘገያል በትግስት እንጠብቃ
9. ASSIGN ብለን ከፃፍን በኋላ ⏎ click Enter
10. EXIT ብለን ከፃፍን በኋላ ⏎ click Enter
አሁን ፍላሻችንን አፅድተን ጨርሰናል ማለት ነው በዚህ መንገድ ችግር ያለበትን ፍላሽ (Flash) ማስተካከል ወይም ቫይረሱን ማጥፋት እንችላለን ማለት ነው።
በመጠቀም ማንኛውንም ችግር ያለበት ፍላሽ ማስተካከል እንችላለን።

👉 እባክዎን ይህ መረጃ ለሌሎችም እንዲደርስ ፔጁን LIKE እና SHARE ያድርጉ

t.me/TechnologyMasterPage
1