Basic Computer Skills
1.87K subscribers
1.22K photos
100 videos
576 files
833 links
#በዚህ የቴሌግራም ቻናል
↪️ Programming
↪️ ቴክኖሎጂ ነክ ትምህርቶችን
↪️ ኮምፒውተር ነክ ትምህርቶችን
↪️Basic Computer Skills
↪️ Software
↪️ AI and AI Skills (Like ChatGPT)

ከላይ የተዘረዘሩትና ሌሎችም ገራሚ ትምህርቶች ይለቀቅበታል!

t.me/BasicComputerSkillsGroup

𝘽𝙮 𝙍𝙚𝙨𝙝𝙖𝙙
Download Telegram
የርስዎ ኮምፒውተር 32 ቢት ውይም 64 ቢት ሲፒዮ ነው? ልዩነት ምንድን ነው?

● 32 ቢት እና 64 ቢት ሲፒዮ መሆኑን ለማወቅ Computer ላይ Right click -> properties -> system type የሚለውን ይመልከቱ!

#እንደምናችሁ ወዳጆቼ ዛሬ በ32ቢት እና በ64 ቢት ፕሮሰሰር መሃል ያለውን ልዩነት ይዘ ቀርቤለሁ።

▮ይህ ጽሁፍ ኮምፒውተር ለምትገዙ፤ የምትጠቀሙበትን ኮምፒውተር/ላፕቶፕ የተጫነበትን ኦፕሬቲንግ ሲስተም ከፍ(አብግሬድ) ለማድረግ እንዲሁም የምትጭኑትን ሶፍትወዌር ለመወሰን ያግዛል፡፡

➝ የኮምፒውተር ሲፒዩ በሁለት አይነት 32 እና 64 ቢት በሚል የሚከፈል ሲሆን፤ የፕሮሰሱ አይነት በኮምፒውተር ላይ ምንም አይነት እክል የማይፈጥር ቢሆንም የምንጭናቸው ኦፕሬቲንግ ሲስተምና ሶፍትዌሮች ይወስኑታል፡፡

➨ 32 ቢት ፕሮሰሰር 32 ቢት ፕሮሰሰር ከ1990 ጀምሮ በሁሉም ኮምፒውተሮች ላይ የምገኘው ሲሆን የፕሮሰሰር አምራች የሆኑት ኢንቴል እና ኤኤምዲ እየሰሩ ለገበያ በማቅረብ ላይ ይገኛሉ ፡፡
➘ኦፕሬቲን ሲስተም እና ሶፍትዌር የሚሰሩ ድርጂቶች 32 ቢት ፕሮሰሰርን መሰረት በማድረግ ሲሰሩ ከነዚህም ውስጥ ማክሮሶፍ ዊንዶ 95፣ 98 እና ኤክስፒን ሁሉም 32 ቢት ኦፕሬቲንግ ሲስተም ተደርገው የተሰሩ ናቸው፡፡

➘32 ቢት ፕሮሰሰር የሆነ ኮምፒውተር 64 ቢት የሆነ ኦፕሬቲንግ ሲስተም መጫን የማንችል ሲሆን፤ ምንጊዜም 32 ቢት ፕሮሰሰር መጫን የሚችለው 32 ቢት የሆነ ኦፕሬቲን ሲስተም እና ሶፍትዌሮች ብቻ ነው፡፡

➨64 ቢት ፕሮሰሰር 64 ቢት ፕሮሰሰር ያለው ኮምፒውተር በ1961አካባቢ አይቢኤም IBM 7030 Stretch supercomputer የሚባል የሰራ ቢሆንም፤ እስከ 2000 ድረስ ለቤት መጠቀሚያ ተብለው በሚሰሩ ኮምፒውተሮች ላይ አልነበረም።

➘በማክሮሶፍት 64 ቢት ፕሮሰሰርን የሚጠቀም 64 ቢት ዊንዶ ኤክስፒ ኦፕሬቲንግ ሲስተም ለገበያ አቀረበ። ▮በመቀጠል ዊንዶ ቪስታ፣ ዊንዶ 7፣ ዊንዶ 8 እና ዊንዶ 10 64 ቢት ፕሮሰሰር የሚጠቀሙ ባለ 64 ቢት ኦፕሬቲንግ ሲስተም ለገበያ ቀርበዋል፡፡

➨ 64 ቢት ፕሮሰሰር ያለው ኮምፒውተር 64 ቢት እና 32 ቢት ኦፕሬቲንግ ሲስተም መጫን የሚችል ሲሆን 32 ቢት ፕሮሰሰር 64 ቢት የሆነን ኦፕሬቲን ሲስተም መጫን አይችልም፡፡


➽ ማስታወሻ 64 ቢት ፕሮሰሰር ያለው ኮምፒውተር 16 ቢት ተብለው የተሰሩ ፕሮግራሞችን/ሶፍትዌሮች የማይሰራ ሲሆን፤
➽ ብዙ 32 ቢት የሆኑ ፕሮግራሞች/ሶፍትዌሮች 64 ቢት ፕሮሰሰር እና ኦፕሬቲን ሲስተም ላይ የሚሰሩ ሲሆን አንዳንድ የድሮ ወይም የቆዩ 32 ቢት ፕሮግራሞች/ ሶፍትዌሮች በትክክል አይሰሩም (compatibil አይደሉም)።

▮ 32 ቢት እና 64 ቢት ፕሮሰሰር ትልቅ የሆነ ልዩነት ያላቸው ሲሆን፣ አንድን ስራ በኮምፒውተር ላይ ስንሰራ ፕሮሰሰሩ ያለው ፍጥነት አንዱ ልዩነታቸው ሲሆን፤ 64 ቢት ፕሮሰሰር ትልቅ ፍጥነት አለው፡፡

➽ 64 ቢት ፕሮሰሰር ለገበያ ተሰርቶ የሚመጣው በdual core፣ በquad core፣ በsix core እና በeight core ቨርዥን በሆኑ ኮምፒውተሮች ላይ ነው፡፡

➽ 32 ቢት እና 64 ቢት ፕሮሰሰር አንዱ ሌላው ልዩነታቸው በኮምፒውተሩ ላይ የሚያስፈልገው የሚሞሪ(ራም) መጠን ሲሆን፤ 32 ቢት ፕሮሰሰር ያለው ኮምፒውተር በጠቅላላ 4GB የሆነ ራም ብቻ መጠቀም የሚያስችል ሲሆን.....

➘ 64 ቢት የሆነ ፕሮሰሰር ያለው ኮምፒውተር ከ4GB በላይ የሆነ ራም መጠቀም ያስችላል ይሄም ግራፊክስ ዲዛይን፣ ኢንጂነሪንግ እና ቪዲዮ ኤዲቲንግ ለሆኑ ሶፍዌሮች በጣም አስፈላጊ ነው፡፡.

● በአሁን ጊዜ በርካታ ኦፕሬቲንግ ሲስተሞች እና ሶፍትዌሮች 64 ቢት እየሆኑ የመጡ በመሆኑ ተጠቃሚዎች ኮምፒውተሮቻቸው 64 ቢት እንዲሆኑ የተገደዱ ሲሆን ይሄም የፕሮሰሰር አምራቾች 64 ቢት ፕሮሰሰር በስፋት ወደገበያ እያቀረቡ ነው።


t.me/TechnologyMasterPage
1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ሳተላይቶች ወደ ህዋ ሲመጥቁ ዋንኛ ተግባራቸው የምድር ሁኔታ የሚያሳዩ እጅግ ጥራት ያላቸው ፎቶዎችን በማንሳት መላክ ነው፡፡ የዛሬው ጥንቅር የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ግኝት ሳተለያቶች እንዲያስቡ ያደረገ በፈጣን መንገድም የመረጃ መላላኩን በቅጽበት እንዲካሄድ ያደረገ ነው፡፡

#Technology_News

#የቴክኖሎጂ_ዜና

t.me/TechnologyMasterPage
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ይህን ኹጥባ ሳንለቅ ማሳደር አልቻልንም!
--------------
ፕሮፌሰር ሸይኽ ከማል አልጀዛኢሪ ዛሬ የቁርአን ውድድሩ ላይ ስለ ሀበሻ ምድር ያደረጉት ኹጥባ እጅግ ድንቅ ነበር! ሀቂቃ ለመናገር ታሪካዊ ኹጥባ ነበር!! ስለ ሀበሻ በሌሎች አንደበት እንዲህ መስማት ያስደስታል!

እነሆ እናነተም ትመለከቱትና ታጣጥሙት ዘንድ ለቀነዋል!!!

خطبة الشيخ البروفيسور كمال الجزائري في حفل المسابقة لحفظ القرأن الكريم شارك فيها الحفاظ من دول متنوعة في العالم
تم القاؤه في نادي اديس ابابا في الدولة اثيوبيا يونيو 13 عام 2022
الحمد لله الذي بنعمته تتم الصالحات
𒊹︎︎︎አጫጭርና ጠቃሚ መልዕክቶች ለማግኘት ይቀላቀሉን☟︎︎︎ ☟︎︎︎
𑁍𑁍𑁍𑁍𑁍𑁍𑁍𑁍𑁍𑁍𑁍𑁍
❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀
☀️ሁዳ መልቲሚዲያ

ቴሌግራም 👇
t.me/huda4eth

ፌስቡክ👇
fb.com/huda4eth

ዩትዩብ👇
http://www.youtube.com/c/HudaMultimedia
👍1
ስልኮቻችንን ከጥቃት ለመከላከል የሚረዱ 10 መንገዶች
❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖ ❖❖
በስማርት ስልኮች ላይ እየደረሰ ያለው የመረጃ ጥቃት ከቀን ቀን እያደገ ይገኛል፡፡
ይህን የላላ ደህንነት ክፍተት በመጠቀም የመረጃ በርባሪዎች በስልካችን ውስጥ ያሉትን እንደ ኢ-ሜይል
፣ማህበራዊ ሚዲያ አካውንቶች እና የባንክ አካውንታችንን በቀላሉ እንደሚመዘብሩ ጥሩ አጋጣሚን
ይፈጥራል፡፡
ሊያደርሱብን የሚችሉትን የመረጃ ጥቃቶች ለመከላከል እንዲያግዘን እነዚህን መንገዶች ብንጠቀም
ይመከራል፡-
1. ➳➳ሁልጌዜ ስማርት ስልኩን ሶፍትዌር ማሻሻል፡- የሶፍትዌር ማሻሻዎች ለስልኮች በሚለቀቁበት ጊዜ
በወቅቱ ማሻሻያውን ኢንስቶል( install) ማድረግና፡፡
2.➳➳ ስማርት ስልኩን በይለፍ-ቃል( passcode) መቆለፍ
3.➳➳ በስማርት ስልኩ በህዝብ ዋይፋይ( Wi-Fi) ኔትዎርክ ከመጠቀም መቆጠብ
4. ➳➳ሁልጊዜ ብልቱዙ( Bluetooth) መዘጋቱን ማረጋገጥ እና መዝጋት
5.➳➳ ስልኩ ላይ የተለየ ነገር ሲከሰት የሚያሳውቅ ማሳወቂያ ማስቀመጥ፡- ይህ ሁኔታም ስልኩ
በሶስተኛ ወገን እጅ መግባቱን የሚጠቁም ሲሆን በአስቸኳይ ስልኩ ውስጥ ያሉትን ኢ-ሜይል ፣ማህበራዊ
ሚዲያ አካውንቶች እና የባንክ አካውንታችንን ለመሰወር ያግዛል፡፡
6.➳➳ ህጋዊ እና ደህንነታቸው ከተጠበቁ ሶፍትዌር አቅራቢዎች ብቻ አፕሊኬሽኖችን ኢንስቶል( Install)
ማድረግ፡፡ ለምሳሌ ከጉግል እና አፕል ስቶር
7.➳➳ ሁልጊዜ የኦንላይን አገልግሎቱ የተቆለፈ እና ደህንነቱ የተጠበቀ መሆኑን ማረጋገጥ
8.➳➳ እያንዳንዱን በስልካችን ውስጥ ያሉትን አፕሊኬሽኖችን በይለፍ-ቃል መቆለፍ
9.➳➳ በስውር ከእኛ እውቅና ውጪ በስልካችን ውስጥ አጥፊ ሶፍትዌሮች ዳውንሎድ(download)
መሆናቸውን መፈተሸ እና ማስወገድ
10.➳➳ በስልኮቻችን ውስጥ ያሉ እና ኢንስቶል ያደረግናቸውን አፕሊኬሽኖችን መፈተሸ እና መሻሻል
ያለባቸውን ማሻሻል፡፡

▒▓⇨→መረጃዎች ቶሎ ቶሎ እንዲደርሶት ስልኮቻችሁ ላይ ላሉ
❖ Contact
❖ Group and Channel share አድርጉለን ከምስጋና ጋር።


━━━━━━━━━━━━━━━
📢: t.me/TechnologyMasterPage
━━━━━━━━━━━━━━━
▬▬▬▬▬📌Share📌▬▬▬▬▬
✳️ላፕቶፓችን ያለኛ ፍቃድ ፍላሽ ዲሰክ እንዳይቀበል ማድረግ እንዴት እንደ ሚቻል ላሳያችሁ።

⚡️ፍላሽ ዲሰክ ፋይሎችን የምናስቀምጥበትና በቀላሉ ይዘነው የምንቀሳቀሰውማሽን ነው፡፡ በስራ ምክንያትም ይሁን በሌላ ፋይሎችን ላማስተላለፍና ኮፒ ለማድረግ ሰዎች የሚጠቀሙበት ፍላሽ ዲሰኮች ላፕቶፓችን ላይ እንሰካል፡፡

⚡️ላፕቶፓችን ላይ ያገኘነውን ፍላሽ ዲሰክ የምንሰካ ከሆነ ደሞ ላፕቶፓችን አደጋ ውስጥ ይገባል፡፡
ምክንያቱም ፍለሽ ዲሰክ ፋይሎችን ብቻ ሳይሆን ቫይረሶችንም ስለሚያስቀምጥ ያገኘነውን ፍላሽ ላፕቶፓችን ላይ የምንሰካ ከሆነ በፍላሽ ዲሰኮች አማካኝነት ቫይረሶች ወደ ኮፒውተራችን በመግባት ላፕቶፓችን ላይ አደጋ ሊያደርሱ ይችላል፡፡

⚡️ከኛ ፍቃድም ውጪ ሳናውቀው አንድ ሰው ተደብቆ ላፕቶፓችን ላይ ፍለሽ ዲሰክ በመሰካት ላፕቶፓችንን ክጥቅም ውጪ ሊያደርገው ይችላል፡፡

⚡️ስለዚህ በተለይ ያለኛ ፍቃድና እውቀት ላፕቶፓችን ፍላሽ ዲሰክ እንዳይቀበል ለማድረግ የሚከተሉትን ስቴፖች መከተል ነው፡፡

1ኛ፡-መጀመሪያ Start በተንን ክሊክ እናደርግና gpedit.msc ብለን እንፅፍና ኢንተር እንጫናል፣

2ኘ፡- የተለያዩ አማራጮች የያዘ ሊስት ይመጣል፤ ሊስቱ ውስጥ “Local Group Policy Editor” የሚለውን ምረጡ፣

3ኛ፡-ከዚያ የሚከተለውን መንግድ ተከተሉ ፤ computer configuration>administrative templates>system>Removable storage access

4ኛ፡-አሁን በቀኝ በኩል ከሚመጡ አማራጮች ውስጥ “All Removable Storage Classes: Deny all access” የሚለውን ክሊክ ማድረግ፣

5ኛ፡- “Enable” የሚል አለ እሱን መምረጥ፣

6ኛ፡- “Apply”> “Ok” ሁለቱንም ተራ በተራ ክሊክ ማድረግ፡፡

⚡️አለቀ፡፡ ካሁን በኋላ ማንም ሰው ፍላሽ ዲስኩን ላፕቶፓችሁ ላይ መሰካት አይችልም፡፡

⚡️ምናልባት ይህንን የከለከላችሁትን አክሰስ መመለስ ስትፈልግ ከላይ ከ1 እስከ 4 ስቴፖችን እንዳሉ ተከተሉ እና፣

5ኛ፡- “Not Configure” የሚል አለ እሱን መምረጥ፣

6ኛ፡- “Apply”> “Ok” ሁለቱንም ተራ በተራ ክሊክ ማድረግ፡፡

════❁✿❁ ═══════
📣የ Technology ቻናላችንን ለመቀላቀል👇👇
t.me/TechnologyMasterPage
5