ርዕስ፡ 📢 ከጋላክሲ ዊዝደም አሰልጣኝ ፋንታሁን ሀሰን ጋር የተደረገ እጅግ ወሳኝ የህይወት ውይይት!
"ልጆቻችን የጀነት ስጦታዎቻችን ወይስ የቤተሰባችን ህመም ተሸካሚዎች?"
ውድ የሙምታዝ አካዳሚ ቤተሰቦች፣ አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱህ!
ዛሬ በሙምታዝ አካዳሚ፣ በታላቁ አሰልጣኝ ፋንታሁን ሀሰን አማካኝነት እጅግ ዐይን ገላጭ፣ ልብ የሚሰብር እና መልሶ የሚጠግን ድንቅ ስልጠና አግኝተናል። ስልጠናው ስለ ልጆቻችን ብቻ ሳይሆን ወደ እራሳችን እንድንመለከት ያደረገ እውነተኛ መስታወት ነበር።
አላህ (ሱ.ወ) በቅዱስ ቁርአኑ እንዲህ ይላል፡-
“ገንዘብና ልጆች የቅርቢቱ ሕይወት ጌጦች ናቸው...” (አል-ከህፍ፡ 46)
ነገር ግን እነዚህን ጌጦች እንዴት እየያዝናቸው ነው? ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) “ሁላችሁም እረኞች ናችሁ፤ ስለ መንጋችሁም ትጠየቃላችሁ” (ቡኻሪና ሙስሊም) ብለውናልና ቆም ብለን እራሳችንን እንፈትሽ።
ከስልጠናው የቀሰምነውን ወርቃማ እና ህይወት ቀያሪ ሀሳቦች፣ ከእስላማዊ እሴቶች ጋር አዋህደን እነሆ በሁለት ክፍል አቅርበንላችኋል። ይህ ማስታወሻ የውቅያኖስን ያህል ጥልቀት ካለው የስልጠናው ሰነድ በጥቂቱ የተቀዳ ነው። ዋናውን በዝርዝር ለማግኘት ከታች የተያያዘውን PDF ይክፈቱ!
ክፍል 1፡ የልጆችን የተፈጥሮ ፀጋ (Intelligences) መረዳት
አላህ (ሱ.ወ) የሰው ልጆችን ሲፈጥር በአንድ ሻጋታ (Mould) አልቀረጻቸውም። ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) “ሰዎች እንደ ወርቅና ብር ማዕድናት ናቸው...” (ሙስሊም) እንዳሉት፣ ልጆቻችን ውስጥ ያለው ማዕድን የተለያየ ነው።
አሰልጣኝ ፋንታሁን በስልጠናው እንዳብራሩት ልጆች ከሚከተሉት ተሰጥኦዎች አንዱን ወይም ከዚያ በላይ ሊኖራቸው ይችላል። የእኛ ድርሻ ማወቅና መደገፍ ነው፡-
➊ የቋንቋ ብቃት (Linguistic): እንደ ሀሳን ኢብኑ ሳቢት (ረ.ዐ) የመናገርና የመጻፍ ችሎታ ያላቸው። ነገ የዲን ተሟጋች ወይም ታላቅ ጸሃፊ የሚሆኑ።
❷ የሂሳብና አመክንዮ ብቃት (Logical): እንደ ዘይድ ኢብኑ ሳቢት (ረ.ዐ) የመተንተንና የሂሳብ አቅም ያላቸው።
➌ ሰዎችን የመረዳት ተሰጥዖ (Interpersonal Intelligence):
እነዚህ ልጆች የሌሎችን ስሜት፣ ፍላጎትና አመለካከት በቀላሉ የመረዳት ልዩ አቅም አላቸው። በቡድን መስራት ይወዳሉ፣ ችግር ያስታርቃሉ፣ ሰዎችንም የመምራት ተፈጥሯዊ ዝንባሌ አላቸው።
◆ ምሳሌ፦ እንደ አቡበክር አሲዲቅ (ረ.ዐ) የሰዎችን ልብ ማሸነፍ የሚችሉ መሪዎችና ማህበራዊ ጠበብቶች ናቸው።
❹ የአካላዊ ብቃት (Bodily-Kinesthetic): እንደ ኻሊድ ኢብኑል ወሊድ (ረ.ዐ) በስፖርትና እንቅስቃሴ ሜዳ ላይ የሚደምቁ።
❺ የውስጥ ማንነት ብቃት (Intrapersonal): ራሳቸውን የሚያዳምጡና ጠንካራ የውስጥ ማንነት ያላቸው።
❻ የድምፅ ተሰጥኦ (Rhythmic): ለድምፅ ልዩ ትኩረት ያላቸው። ይህንን ጸጋ ቁርአንን በውብ ድምፅ በማነብነብ (እንደ አቡ ሙሳ አል-አሽዓሪ) እንዲጠቀሙበት ልናግዛቸው ይገባል።
❼ የራስን ማንነት የመረዳት ተሰጥዖ (Intrapersonal Intelligence):
እነዚህ ልጆች የራሳቸውን ስሜት፣ ጥንካሬና ድክመት ጠንቅቀው የሚያውቁ ናቸው። ብቻቸውን መሆንና ማሰብ ያስደስታቸዋል። የራሳቸውን ግብ ያስቀምጣሉ፣ በራሳቸውም ይተማመናሉ።
ምሳሌ፦ እንደ ታላቁ የዲን ሊቅ ኢማሙ አል-ጋዛሊ (ረሂመሁላህ) የራሳቸውን ነፍስ መርምረው ለትልቅ ደረጃ የሚበቁ፣ ነገ ጥልቅ አስተላላፊዎች (Philosophers) ወይም የነፍስ ሐኪሞች (Psychologists) የሚሆኑ ናቸው።
❽ ተፈጥሮን የመረዳት ተሰጥዖ (Naturalist Intelligence):
እነዚህ ልጆች ለአካባቢያቸው፣ ለተክሎች፣ ለእንስሳትና ለተፈጥሮ ክስተቶች ልዩ ፍቅርና ትኩረት አላቸው። በተፈጥሮ ውስጥ መሆን ያስደስታቸዋል፣ ነገሮችን የመለየትና የመመደብ አቅማቸው ከፍተኛ ነው።
◆ ምሳሌ፦ አላህ በቁርአኑ "በሰማያትና በምድር ባሉ ተአምራት ላይ አትመለከቱም?" የሚለውን ጥሪ በተግባር የሚተረጉሙ፣ ነገ የአካባቢ ጥበቃ ባለሙያ ወይም ድንቅ የግብርና ሊቃውንት የሚሆኑ ናቸው።
❾ ስዕላዊ ተሰጥዖ (Visual/Spatial Intelligence):
ነገሮችን በምስል የማየት፣ የመቅረጽና የማስታወስ ብቃት። እንደ አርክቴክቶችና ዲዛይነሮች ነገሮችን በአዲስ መልክ የመቅረጽ ችሎታ ያላቸው ልጆች ናቸው።
መልዕክት: ኢማሙ ሻፊዒይ (ረሂመሁላህ) “ጊዜ እንደ ሰይፍ ነው...” እንዳሉት፣ የልጆቻችንን የተፈጥሮ አቅጣጫ በጊዜ ካላወቅንላቸው፣ የተፈጠሩበትን ዓላማ ሳያሳኩ ጊዜው ይቆርጣቸዋል።
ክፍል 2 👇👇👇

❤3
ክፍል 2፡ "የታመመ ቤተሰብ" (Dysfunctional Family) እና ሰለባ የሆኑ ልጆች
ይህ የስልጠናው ክፍል እጅግ ልብ የሚነካ ነው። ቤተሰብ ሲታመም (በግጭት፣ በፍቅር ማነስ፣ ወይም በተሳሳተ አስተዳደግ) ልጆች ያንን ክፍተት ለመሙላት ሳያውቁት 7 አደገኛ ሚናዎችን (Roles) ይጫወታሉ። በስልጠናው ሰነድ ላይ በስፋት እንደተብራራው፣ ልጆቻችንን የትኛው ሳጥን ውስጥ እንደከተትናቸው እንፈትሽ፡-
1. የሜዳሊያ ልጅ (The Hero)
◆ ማንነቱ: ቤተሰቡ የሚወደው ውጤት ሲያመጣ ብቻ ነው። ፍቅርን በውጤት ይለካል።
⭕️ አደጋው: ስህተት መሥራትን እንደ ሞት ይፈራል። ለቤተሰቡ ክብር ሲል የራሱን ማንነት ያጣል።
✅ የሸሪዓው ሚዛን: ይህ አደገኛ ነው። አላህ ሰዎችን የሚመዝነው በ"ተቅዋ" እንጂ በውጤት አይደለም።
2. ተሸካሚው ልጅ (The Scapegoat)
◆ ማንነቱ: የቤተሰቡን ጭንቀት፣ ንዴት እና ውድቀት ማራገፊያ የሆነ ልጅ። ወላጆች ሲጣሉ ጣቱ ወደ እሱ ይቀሰራል።
⭕️ አደጋው: አመፀኛ እንዲሆን ይገደዳል። ጥፋተኝነት ይሰማዋል።
✅ የሸሪዓው ሚዛን: አላህ “ማንኛዋም ነፍስ ኃጢአትን አትሸከምም” (አል-አንዓም 164) ይላል። የቤተሰብን ችግር በልጅ ላይ ማላከክ "ዙልም" (በደል) ነው።
3. የጠፋው ልጅ (The Lost Child)
◆ ማንነቱ: ቤተሰቡ ሲወጠር ይህ ልጅ ትኩረት ላለማጣት ድምፁን ያጠፋል። "ዝምተኛ፣ ጨዋ" ይባላል።
⭕️ አደጋው: በውስጡ ብቸኝነት እየበላው ነው። በስሜት የሞተ ልጅ ይሆናል።
✅ የሸሪዓው ሚዛን: ዝም ያለን ልጅ ችላ ማለት አማናን መብላት ነው።
4. የተቀባው ልጅ (The Golden Child)
◆ ማንነቱ: ሳይጠይቅ ሁሉም የሚሟላለት፣ ከወንድሞቹ ተለይቶ የሚንቀባረር።
⭕️ አደጋው: ሲያድግ ዓለም ሁሉ እንዲንቀጠቀጥለት ይፈልጋል። "ትዕቢተኛ" (Arrogant) ለመሆን የቀርበ ነው።
✅ የሸሪዓው ሚዛን: ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ)፡- “አላህን ፍሩ በልጆቻችሁም መካከል አስተካክሉ (ፍትሃዊ ሁኑ)” ብለው ይህንን ድርጊት አጥብቀው አውግዘዋል።
5. አስታራቂው ልጅ (The Mascot)
◆ ማንነቱ: የቤተሰቡን ግጭት በቀልድ እና በጨዋታ ለማብረድ የሚሞክረው።
⭕️ አደጋው: የቤተሰቡን ሠላም ለመጠበቅ ሲል በውስጡ እያለቀሰ የውሸት ፈገግታ ያሳያል።
6. ሞግዚት ልጅ (The Caretaker)
◆ ማንነቱ: ወላጆቹን ወይም ታናናሾቹን ለመንከባከብ ሲል የራሱን ጨዋታ እና ፍላጎት የገደለ።
⭕️ አደጋው: በልጅነት አካሉ የሽምግልና ጭንቀት ይሸከማል።
7. ብርቅዬው (በወላጅ ቅርጽ የተሰራው) ልጅ
◆ ማንነቱ: የወላጆቹን ያልተሳካ ህልም እንዲኖር የተገደደ። (ለምሳሌ፡ ወላጅ ዶክተር መሆን ፈልጎ ካልሆነ፣ ልጁን በግድ ዶክተር እንዲሆን የሚገፋው)።
⭕️ አደጋው: የራሱን ማንነት አያውቅም። የወላጆቹ "ሮቦት" ነው።
✅ የሸሪዓው ሚዛን: ዐሊይ ኢብኑ አቢ ጣሊብ (ረ.ዐ) “ልጆቻችሁን ለተፈጠሩበት ዘመን አሳድጉ፤ እነሱ የተፈጠሩት ለእናንተ ዘመን አይደለምና” እንዳሉት ልጆቻችንን በራሳችን ሳጥን ውስጥ አንክተታቸው።
📚 ወሳኝ ቀጣይ እርምጃ
ውድ ወላጆች! ይህ አጭር ማጠቃለያ ነው። በስልጠናው ላይ እያንዳንዱ ልጅ የሚያሳያቸው ምልክቶች እና መፍትሄዎች በዝርዝር ተቀምጠዋል።
"እኔ ቤት የትኛው ልጅ አለ?" ብለው እራስዎን ለመጠየቅ እና መፍትሄውን ለማግኘት ከታች የተያያዘውን PDF (የስልጠናውን ሙሉ ሰነድ) አሁኑኑ ይክፈቱ! ለልጆችዎ ሲሉ እባክዎ 10 ደቂቃ በመስጠት ያንብቡት።
ዱዓ 🤲
ያ አላህ!
ልጆቻችንን ለዓይናችን ማረፊያ፣ ለልባችን ደስታ አድርግልን።
ከታመመ አስተዳደግ፣ ከክፉ ነገር ሁሉ ጠብቀህ፤ በሰጠሃቸው ተሰጥኦ (Fitrah) ለአላማህ የምትጠቀምባቸው፣ ለዲናቸውና ለሀገራቸው ጠቃሚዎች አድርግልን።
እንደ ታላቁ ኢብኑል ቀይይም (ረሂመሁላህ) “ልብ እንደ ወፍ ነው፤ ከፍ ባለም ቁጥር ከአደጋ ይርቃል” እንዳሉት፣ የልጆቻችንን ልብ በእውቀትና በፍቅር ወደ አንተ ከፍ የምናደርግበትን ጥበብ ለግሰን። ቤታችንን የሰኪና (የመረጋጋት) እና የራህመት ቤት አድርግልን።
አሚን! 🤲 🤲 🤲
📚 ሙምታዝ አካዳሚ
በአላህ ፍቃድ የነገ መሪዎችን በብቃት እና በእምነት እንቀርፃለን!!
የስልጠናውን PowerPoint ለማግኘት ከታች ያለውን ሊንክ ተጫኑ!! 👇
t.me/MumtazKG/147?single
✍️ በረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል

❤2
Google photos app አዳዲስ ፊቸሮች ተካቶለታል።
Google ሁሉንም እፕሊኬሽኖቹን የGemeni AI ፊቸር integrate እየደረገላቸው ይገኛል።
ከነዚህ ውስጥ አንዱ የሆነው Google photos የተለያዩ የAI ፊቸሮች ተካቶለታል።
ስልካችሁ ላይ ያለ ማንኛውንም ፎቶ በቀላሉ search አድርጋችሁ ማግኘት የምችሉበት ask የሚል አማራጭ ታገኛላችሁ።
Gemini powered የሆነው ይህ ፊቸር ፎቷችሁን በስም፣ በአይነት፣ ወይም በተነሳችሁ ቀን search አድርጋችሁ ማግኘት ትችላላችሁ።
ሌላው create የሚል አማራጭ ያለ ሲሆን ፎቷችሁን ወደ video ወይም ወደ animation መቀየር ትችላላችሁ።
Google photos application Update አድርጋችሁ check አድርጉት።
©️

❤5
SATCOM INSTITUTE OF TECHNOLOG cp hand out - Copy (1).pdf
2.5 MB
Smart phone ጥገና በአማርኛ
ፌስታል ይዛችሁ እንዳትቀጡ!
~
ከነገ ቅዳሜ ጥር 23/2018 ጀምሮ ፌስታል ይዞ የተገኘ ይቀጣል ተብሏል። እገዳው ለአንድ ጊዜ አገልግሎት የሚውሉ (ትንንሽም ይሁን ትልልቅ) ሁሉንም አይነት ፌስታሎች የሚያጠቃልል ሲሆን በእጅ ይዞ ለተገኘ ግለሰብ ከ2,000 እስከ 5,000 ብር ፣ ለአምራቾች፣ አከማቺዎች እና አከፋፋዮች ደግሞ ከ50,000 እስከ 200,000 ብር ቅጣት እና እስከ አምስት አመት የሚደርስ ጽኑ እስራት ያስቀጣል ተብሏል።
ተግባራዊነቱን ወደፊት የምናየው ይሆናል። ዋናው ነገር ህጉን ሰበብ አድርጎ የሚንቀሳቀስ የራበው ጅ - ብ እንዳያገኛችሁ ተጠንቀቁ። "ሰኞን አትሁኑ!"
"ሼር" ብታደርጉት።
©️ @IbnuMunewor

❤1
Basic Computer Skills
Photo
🚀 THE GRAND COMEBACK: REWRITING DESTINY (ታላቁ ትንሳኤ፡ ታሪክን የመቀየር ጥበብ)
════════════════
▣ መግቢያ፡ የጨዋታው ግማሽ ክፍል (Half-Time Analysis)
ህይወት እንደ እግር ኳስ ጨዋታ ናት። የመጀመሪያው አጋማሽ (First Semester) መጠናቀቅ የጨዋታው ፍጻሜ አይደለም። በመጀመሪያው አጋማሽ ውጤቱ አላማረም ማለት ተሸንፈሃል ማለት አይደለም። አሁን ያለንበት ጊዜ ስልት ቀይረን፣ ጉልበት አድሰን ለሁለተኛው ዙር "የሞት ሽረት" ትግል የምንዘጋጅበት ወሳኝ ምዕራፍ ነው። ትላንትናችሁ የዛሬ ማንነታችሁን አይወስንም፤ ነገን የመወሰን አቅሙ ግን አሁን ባላችሁ እጅ ላይ ነው።
➲ የተስፋ ብርሃን - ከዜሮ መነሳት ይቻላል!
ባለፈው መንፈቀ ዓመት ውጤታችሁ አላማረም? ደረጃችሁ ዝቅ ብሏል? "ተስፋ የለሽ ነኝ" የሚለውን የሰይጣን ሹክሹክታ አትስሙ። በእስልምና ተስፋ መቁረጥ የለም። አንድ ሰው ምን ያህል ወንጀል ቢሰራ በንስሃ (ተውበት) እንደሚመለስ ሁሉ፣ አንድ ተማሪም ምንም ያህል ቢወድቅ በቁርጠኝነት (Azim) ታሪኩን መቀየር ይችላል። ዛሬ ላይ "ዜሮ" ብትሆኑ እንኳን፣ በሁለተኛው መንፈቀ ዓመት በእውነተኛ ተጋድሎ (Jihad of Education) ወደ "ጀግና" መቀየር ትችላላችሁ።
"ሰውም ለርሱ የሠራው እንጂ ሌላ የለውም፡፡ ሥራውም ወደ ፊት ይታያል (ይፋ ይወጣል) ..." (ሱረቱ አን-ነጅም፡ 39-40)
❓ የነፍስ መመርመሪያ፦ ባለፈው ሴሚስተር ውጤቴ እንዲበላሽ ያደረገው ዋናው "ቫይረስ" ምንድን ነው? እንቅልፍ? ስልክ? ወይስ ጓደኛ? ዛሬ ይህንን ቫይረስ ከስሩ ለመንቀል ለአላህ ቃል ትገባለህ?
➲ ለ6ኛ እና ለ8ኛ ክፍል ተማሪዎች
እናንተ በሚኒስትሪ ፈተና አፋፍ ላይ ያላችሁ ተማሪዎች ሆይ! ይህ ሰዓት "የህይወት አቅጣጫ መቀየሪያ ወሳኝ ምዕራፍ" ነው። ጊዜው እየሮጠ ነው፤ ቀልድ ያብቃ! ይህ ፈተና ከክፍል ወደ ክፍል ማለፊያ ብቻ ሳይሆን፣ የነገ ማንነታችሁ መሰረት የሚጣልበት ነው። አሁን የምታፈሱት ላብ፣ ነገ የምታለቅሱትን እንባ ያድናል። እናንተ ልዩ "ሚሳኤል" ሁኑ፤ ኢላማችሁን (ውጤታችሁን) እስክትመቱ ድረስ ወደ ኋላ አትይዩ።
ነብዩ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፡- "አምስት ነገሮች ከመምጣታቸው በፊት በአምስት ነገሮች ተጠቀም፡ ... ሽምግልና ሳይመጣብህ በወጣትነትህ፣ መታመም ሳይመጣብህ በጤንነትህ..." (አል-ሐኪም ዘግበውታል፡ ሶሒሕ)
❓ የነፍስ መመርመሪያ፦ የቀሩት ወራት በጣም ጥቂት ናቸው። በዚህ አጭር ጊዜ ውስጥ ሙሉ መጽሐፍትን ሸፍኖ ለመጨረስ የምትችለው በምን አይነት ፍጥነት ብትጓዝ ነው? እቅድ አለህ ወይስ በዘፈቀደ ነው የምትነጉደው?
➲ ምክንያት ድርደራን መቅበር (No More Excuses)
"መምህሩ አይገባኝም"፣ "መብራት ይጠፋል"፣ "መጽሐፍ የለኝም"... እነዚህ የደካሞች መዝሙር ናቸው። አላህ እርዳታውን የሚልከው ሰበቡን አድርሰው ለሚታገሉ ነው። ጠንካራ አማኝ መብራት ሲጠፋ ሻማ ያበራል፤ መምህሩ ካልገባለት ሌላ መንገድ ይፈልጋል።
ነብዩ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፡- "ጠንካራ አማኝ ከአላህ ዘንድ ይበልጥ የተወደደና ከደካማ አማኝ የተሻለ ነው..." (ሶሒሕ ሙስሊም)
❓ የነፍስ መመርመሪያ፦ እኔን ወደ ኋላ እየጎተተኝ ያለው "ሰበብ" ምንድን ነው? ይህንን ሰበብ ዛሬውኑ አሽቀንጥሬ ለመጣል ዝግጁ ነኝ?
➲ የዲጂታል እስር ቤት (ስልክና ሶሻል ሚዲያ)
ብዙ ተማሪዎችን እየገደለ ያለው "ቲክቶክ" እና "ጌም" ነው። በሁለተኛው ሴሚስተር ስልካችሁን "የሚቆጣጣራችሁ" ሳይሆን "አገልጋያችሁ" አድርጉት። ለትምህርት ካልሆነ በስተቀር ከስልክ ራቁ። የፌስቡክ ላይክ ውጤት አያመጣም፤ የቲክቶክ ቪዲዮ የወደፊቱን ህይወት አይገነባም።
❓ የነፍስ መመርመሪያ፦ በቀን ስንት ሰዓት በስልክ ላይ ታቃጥላለህ? ይህንን ሰዓት ለሂሳብ ወይም ለእንግሊዝኛ ብትሰጠው ኖሮ አሁን የት ትደርስ ነበር?
➲ የክፍተት ትንተና (Gap Analysis)
ሁለተኛው ሴሚስተር አዲስ ቤት ለመሥራት ብቻ ሳይሆን፣ የፈረሰውን ለመጠገን ጭምር ነው። ባለፈው የከበዳችሁ ትምህርት የትኛው ነው? ያንን ሳትጠግኑ ወደ ፊት መሄድ አትችሉም። ድክመታችሁን አውቃችሁ መድፈን የብልህ ተማሪ ምልክት ነው።
➲ ወላጆች - የቤት ውስጥ መሪዎች
ውድ ወላጆች! ልጆቻችሁ የነገ ተስፋዎቻችሁ ናቸው። በዚህ ወሳኝ ሰዓት ቤታችሁ "የፊልም ቤት" ሳይሆን "የንባብና የዱዓ ቤት" መምሰል አለበት። ከቴሌቪዥን ሪሞት ይልቅ የመጽሐፍ ገጾች ይቅረቡ። ልጆቻችሁ ሲያጠኑ አበረታቷቸው፣ ሲደክሙ አበርቱአቸው። የልጆቻችሁ ውጤት የጋራ ፕሮጀክታችሁ ነው። በዱዓ እና በክትትል ከጎናቸው ቁሙ።
➲ ሶላትና ስኬት - የማይነጣጠሉ ቅንጣቶች
ከአላህ ጋር የተጣላ ሰው የትምህርት ቤት ውጤቱ ቢያምርም በህይወቱ ሰላም የለውም። ጥናታችሁን ከሶላት ጋር አጣምሩ። ሶላቱን በወቅቱ የሚሰግድ ተማሪ፣ ጊዜው በረካ ይሆንለታል። የአላህ እርዳታ (ተውፊቅ) የሚገኘው በሱጁድ ውስጥ ነው። ያለ አላህ እርዳታ የሚመጣ ውጤት የለም።
"...አላህ በሕዝቦች ዘንድ ያለን (ጸጋ) በነፍሶቻቸው ያለን (ሁኔታ) እስከሚለውጡ ድረስ አይለውጥም..." (ሱረቱ አር-ረዕድ፡ 11)
❓ የነፍስ መመርመሪያ፦ ለአላህ ሳትሰግድ ለፈተና ብቻ የምታደርገው ጥረት ፍሬ ያፈራል ብለህ ታስባለህ? ስኬትህ ከሰላትህ ጋር እንደተሳሰረ ታውቃለህ?
➲ ማጠቃለያ - ብዕሩ በእጅህ ነው!
ታሪክህ ገና አልተጻፈም፤ ብዕሩ በእጅህ ነው። ሁለተኛው ሴሚስተር ባዶ ነጭ ወረቀት ነው። በዚህ ወረቀት ላይ የውድቀት ታሪክ ትጽፋለህ ወይስ የድል አድራጊነት ዜና? ምርጫው ያንተ ነው። ተነሳ! አቧራህን አራግፍ! አንተ ከተቀየርክ ዓለም አብራህ ትቀየራለች።
በቀጣዩ ሴሚስተር በደረጃ ሰንጠረዥ አናት ላይ እንገናኝ! አላህ ጥረታችሁን ይባርክ፤ ልፋታችሁን በስኬት ያክልላችሁ (ያብቃላችሁ)! 🚀

የባንክ ሒሳብን ከፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ጋር አላጣመሩም? ጊዜው እየሄደ ስለሆነ በቀጥታ ካሉበት ሆነው ኦንላይን ያጣምሩ።
💸 እናት ባንክ:
https://kyc.enatbanksc.com/bank-account-entry
💸 የኢትዮጵያ ልማት ባንክ:
https://fayda.dbe.com.et
💸 ፀሀይ ባንክ፡
https://fayda.tsehaybank.com.et/FAYDA/home
💸 አባይ ባንክ:-
https://faydaabaybank.com.et/
💸 ንብ ባንክ:-
https://fayda.nibbank.com.et
💸 ቡና ባንክ:-
https://verifayda.bunnabanksc.com
💸 ዳሽን ባንክ:
https://dashensuperapp.com/dashen-fayda
💸 ዘመን ባንክ:
https://fayda.zemenbank.com
💸 ሒጅራ ባንክ:
https://apps.hijradigital.com/fayda/v2
💸 ሕብረት ባንክ :
https://services.hibretbank.com.et/fayda
💸 ብርሀን ባንክ:
https://nationalidharmonization.berhanonline.et:9095/fayda-login
💸 አዲስ ባንክ:
https://fayda.addisbank.com.et
💸 አቢሲኒያ ባንክ:
https://cs.bankofabyssinia.com/fayda_connect
💸 አዋሽ ባንክ :
https://fayda.awashbank.com
💸 የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ:
https://my.coopbankoromiasc.com/harmonization
💸 የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፡
https://cbefayda.cbe.com.et/
💸 ኦሮሚያ ባንክ ፡
https://obfayda.oromiabank.com/

የነገ_ሰው_አናፅያን_የKG_መምህራን_የሙያ_ስነ_ምግባርና.pdf
16.1 MB
🚀 የነገ ሰው አናፅያን፦ ከዘመን የተሻገረ፣ ትውልድን የሚቀይር የነፍስ ጥሪ!
ስላይድ ብዛት: 81
ዝግጅት: በረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል
ስላይድ ብዛት: 81
ዝግጅት: በረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል
Basic Computer Skills
የነገ_ሰው_አናፅያን_የKG_መምህራን_የሙያ_ስነ_ምግባርና.pdf
🚀 የነገ ሰው አናፅያን፦ ከዘመን የተሻገረ፣ ትውልድን የሚቀይር የነፍስ ጥሪ!
(ለወላጆች፣ ለመምህራንና ማህበረሰብን ለሚያንፁ ሁሉ የተበረከተ ድንቅ ስንቅ)
"ይህ ዝም ብሎ የንባብ ሰነድ አይደለም፤ ይህ በአላህ ፈቃድ የነገውን ዓለም የሚቀይሩ ጀግኖችን የማፍሪያ ጥበብ ነው!"
ምዕራፍ 1፦ የክብር ጥሪ - አንተ ማን ነህ? (The Awakening)
✨ "የነገው ታሪክ ዛሬ ያንተ ክፍል/ቤት ውስጥ ነው የሚጻፈው!"
ወዳጄ ሆይ! አንተ የምትሰራው ፋብሪካ ውስጥ አይደለም፤ የሰው ልብ ውስጥ ነው። ፋብሪካ ቢበላሽ "እቃ" ይበላሻል፤ አንተ ጋር ከተበላሸ ግን "ትውልድ" ይበላሻል። ጌታችን አላህ (ሱ.ወ) ለሰው ልጅ የሰጠው ትልቁ ክብር ማስተማር ነው፤ በቁርኣኑ እንዲህ ይላል፡-
"አላህም ለአደም ስሞችን ሁሉንም አስተማረው..." (አል-በቀራህ፡ 31)።
የአላህ መልክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- "አላህ፣ መላእክቱ፣ የሰማይና የምድር ነዋሪዎች፣ በጉድጓዷ ያለች ጉንዳንና በባህር ውስጥ ያለ አሳ ሳይቀሩ ለሰዎች መልካምን ነገር ለሚያስተምር ሰው ዱዓ ያደርጉለታል።" አንተ የነብያት ውርስ ተሸካሚ ነህ። አሳዎች በባህር ውስጥ ሆነው ዱዓ የሚያደርጉልህ ታላቅ ባለሙያ ነህ!
🌊 ለመሆኑ ይህን ክብር ጠብቆ ለመጓዝ የሚያስፈልገው 'የልብ ትርታ' ምንድነው? ወደ ቀጣዩ ክፍል እንለፍ...
ምዕራፍ 2፦ ስነ-ምግባር - የሙያው የልብ ትርታ
✨ "እውቀት ጌጥ ነው፤ ስነ-ምግባር ግን የሕይወት እስትንፋስ ነው!"
ትክክለኛው ማንነትህ ማለት፣ ማንም ሳያይህ የምታደርገው ነገር ነው። ኢስላም ይህንን "ኢሕሳን" ይለዋል። ታላቁ ኢማሙ ማሊክ (ረሒመሁላህ) እንዲህ ይላሉ፡- "ዕውቀትን ከመማርህ በፊት ስነ-ምግባርን (አደብን) ተማር።" ስነ-ምግባር የሌለው ዕውቀት ልክ እንደሌለው ዛፍ ነው። እናንተ የልጆች የህሊና ካሜራዎች ናችሁ፤ ልጆች የሚሰሙትን ሳይሆን፣ የሚያዩትን ነው የሚደግሙት።
ኢማሙ አል-ሻፊዒይ ደግሞ እንዲህ ይላሉ፡- "ዕውቀት ማለት የሸመደድከው ሳይሆን በተግባር የገለጽከውና የጠቀመህ ነው"። አንተ መሪ ነህ፤ መሪ ደግሞ በባህሪው ይሰብካል!
💎 ይህን ድንቅ ባህሪ ይዘህ የምታንጻቸው "ውድ እንቁዎች" እነማን ናቸው? ምዕራፍ 3 ላይ እናገኘዋለን...
ምዕራፍ 3፦ ተማሪዎቻችን - የአማና ውድ ስጦታዎች
✨ "ለአምስት ዓመት የዘራኸው ፍቅር፣ ለሃምሳ ዓመት የሚቆይ ፅናት ይፈጥራል!"
ሳይንስ እንደሚያረጋግጠው የሰው ልጅ 90% የአዕምሮ እድገት የሚጠናቀቀው እስከ 5 ዓመት ባለው ጊዜ ነው። በዚህ ወሳኝ ሰዓት እጃችሁ ላይ ያሉት ህፃናት ከአላህ የተሰጡ "አማናዎች" ናቸው። ኢማሙ አህመድ (ረሒመሁላህ) እንዳሉት፡- "ሰዎች ለዕውቀት ያላቸው ፍላጎት ከምግብና ከመጠጥ በላይ ነው።"
ልጆችን በዱላ ሳይሆን በፍቅር ቅረጹት። ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) "ልጆቻችሁ መካከል በስጦታ (በመሳምም ቢሆን) አስተካክሉ" በማለት ፍትሃዊነትን አስተምረውናል። ይህ ፍትህና ፍቅር ደግሞ በአንደበትህ በሚወጡ ቃላት ይገለጻሉ...
⚔️ ቃላትህ ሰይፍ መሆናቸውን ያውቃሉ? ወደ ምዕራፍ 4 እንዝለቅ...
ምዕራፍ 4፦ አርአያነትና የቃላት ኃይል - የኤድሰን ምስጢር
✨ "አንደበታችሁ ወይ የትውልድ ብርሃን ወይ የነፍስ ጨለማ ይፈጥራል!"
ቶማስ ኤድሰን በትምህርት ቤቱ "ዘገምተኛ" ተብሎ ሲባረር፣ እናቱ ግን ደብዳቤውን ቀይራ "አንተ በጣም ብልህ ስለሆንክ ትምህርት ቤቱ አይመጥንህም" አለችው። ያቺ መልካም ቃል ዓለምን በኤሌክትሪክ ያበራ ታላቅ ሰው ፈጠረች።
ሸይኽ ኢብኑ ኡሰይሚን እንዲህ ይላሉ፡- "አስተማሪነት ማለት በተማሪዎችህ ልብ ውስጥ ፍቅርን መትከል ነው።" አላህ እንዲህ ይላል፡-
"መልካም ቃል ልክ እንደ መልካም ዛፍ ናት፤ ስሯ የጠነከረ ቅርንጫፎቿም ወደ ሰማይ የረዘሙ..." (ኢብራሂም፡ 24)። ዛሬ የምትናገረው ቃል የነገውን አገር ሰሪ ይተክላል!
🤝 ይህን ትልቅ ኃላፊነት ግን ብቻህን አትሸከመውም!
ምዕራፍ 5 አጋርህን ያስተዋውቅሃል...
ምዕራፍ 5፦ አብሮነት - ድልድይ መሆን
✨ "ትውልድ የሚገነባው በመምህር፣ በወላጅና በማህበረሰብ ህብረት ነው!"
መማር ማስተማር የአንድ ወገን ሩጫ አይደለም። ኢብኑል ቀይም እንደሚሉት፡- "ልጅን ማሳደግ ልክ እንደ መስታወት ነው፤ የሰጠኸውን ምስል መልሶ ያሳይሃል"። መምህርና ወላጅ በአንድ ልብ ካልቆሙ ትውልዱ ይሰነጠቃል። ማህበረሰቡ እናንተን ሲያከብር ሙያችሁን ያከብራል።
📈 ይህንን ድልድይ ለመገንባት ግን ያንተ "ብቃት" የት ላይ ነው? ምዕራፍ 6 ይገርምሃል...
ምዕራፍ 6፦ የላቀ ብቃትና ፅናት (Growth)
✨ "ለዘጠኝ ሴኮንድ ስኬት፣ ዘጠኝ ዓመት በትዕግስት መዝራት ግድ ነው!"
ሸይኩል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያህ እንዲህ ይላሉ፡- "ትዕግስት (ሶብር) ለዕውቀት ልክ እንደ ጭንቅላት ለሰውነት ነው።"
የዓለማችን ፈጣኑ ሯጭ ዩሴይን ቦልት እንዲህ ይላል፡-
"እኔ ለዘጠኝ (9) ሴኮንድ ውድድር፣ ለዘጠኝ (9) ዓመታት ሰልጥኛለሁ። አንዳንድ ሰዎች ግን በሁለት ወር ውስጥ ለውጥ ካላዩ ተስፋ ይቆርጣሉ!!"።
ልጅን መቅረጽ የ9 ሴኮንድ ስራ አይደለም። ዛሬ የዘራኸው ነገ ላይበቅል ይችላል፤ ግን መዝራትህን አታቁም! ፍሬው የትውልድ ስኬት ነው። ይህ ስኬት ደግሞ ከዘመኑ ጋር መራመድን ይፈልጋል...
💻 ዘመኑን የማይቀድም መምህር፣ ትውልድን መምራት ይችላል? ምዕራፍ 7 መልሱን ይዟል...
ምዕራፍ 7፦ መምህሩና ቴክኖሎጂ (The Modern Teacher)
"በድንጋይ ዘመን አስተሳሰብ፣ የዲጂታሉን ትውልድ መቅረጽ አይቻልም!"
በ21ኛው ክፍለ ዘመን እየኖርን፣ በ20ኛው ክፍለ ዘመን አስተሳሰብ መጓዝ አይቻልም። ቴክኖሎጂ ስራችሁን ያቀላል እንጂ አይተካችሁም። ራሳችሁን አዘምኑ። ዛሬ መምህሩ ኦንላይን በመስራት፣ በZoom በማስተማርና እውቀቱን በማጋራት ገቢውንም እውቀቱንም ማሳደግ ይችላል።
"ሰነፍን አላህም ሰውም አይወደውም! እውቀታችሁን ሽጡት፤ የህፃናት መጽሐፍ ጻፉ"። ዘመኑ የብዙ አማራጮች ነው። ይህ ሁሉ ልፋት መጨረሻው ምን ይሆን?
🌈 የመጨረሻው ግብና የነፍስ እርካታ... ምዕራፍ 8 ላይ!
ምዕራፍ 8፦ የነገው ብሩህ ህይወታችን (Life Mastery)
✨ "ዛሬ የምትዘራው ኸይር፣ ነገ በጀነት ውስጥ ጥላ ይሆንሃል!"
አንድ ቀን ይህን አለም ትሰናበታላችሁ። ያኔ ምንድነው የሚቀረው? ገንዘብ? ህንፃ? አይደለም! የሚቀረው እናንተ የቀረጻችሁት የሰው አዕምሮ እና ንጹህ ልብ ነው። ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) "ሰው ሲሞት ስራው ይቋረጣል፤ ከሶስት ነገሮች በስተቀር" አሉና አንዱ "ለእርሱ ዱዓ የሚያደርግለት መልካም ልጅ" መሆኑን ጠቅሰዋል። ዛሬ የምትቀርጹት ልጅ ነገ ዶክተር ሆኖ ሰውን ሲያድን፣ እናንተም አብራችሁ እያዳናችሁ ነው።
🌟 መደምደሚያ፦ የጥበብ ማጠቃለያ
✨ "ዕውቀት፦ የመንፈስ ዝናብ፣ የተግባር ምንጭ!"
"እውቀት እንደ ውሃ ነው፤ ካልፈሰሰ ይሸታል። አነበብን ብቻ ሳይሆን ተገበርን የምንባል ያድርገን!" ይህ ሰነድ በውስጣችሁ እንዲፈስ ፍቀዱለት። ካልተገበረ ዕውቀት የተገበረች አንዲት ጠብታ ትበልጣለች።
🏔️ Mumtaz Academy፦ የልህቀት ማማ፣ የትውልድ ቀራጭ!
✨ "የላቀ እውቀት ለላቀ ትውልድ!"

🤲 የዱዓ ማሳረጊያ
ያ አላህ! ትውልድን ለማነጽ የሚደክሙትን መምህራኖቻችንን ዕውቀታቸውን ጨምርላቸው፤ ልባቸውን በኑር አብራው። ለወላጆቻችን ትዕግስቱንና ጥበቡን ስጣቸው። ማህበረሰባችንን የሚያንፁትን ጀግኖቻችንን በክብር ጠብቅልን።
ያ አላህ! የምናስተምራቸውን ልጆች የአይን ማረፊያ፣ የአገር ኩራት፣ የዲን አለኝታ አድርግልን። ይህን ስራችንን ለፊትህ ጥራት ብቻ የተሰራ አድርግልን። በዱንያ የድል ባለቤት፣ በአኺራ ደግሞ የጀነት ወራሾች አድርገን። አሚን!!
📚 የስልጠናውን ሙሉ ሰነድ እዚህ ያውርዱ
👇👇 👇👇👇
t.me/BasicComputer_Skills/2992
✍️ አዘጋጅ፦ ረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል

❤4
«የቻነል ፕሮፋይል ፎቶ አጥፉ፣ ሪፖርት ተደርጎ ይሰረቃል!» የምትለዋን አሉባልታ አታሰራጯት።
ቴሌግራም ሴኩሪቲው እንደበፊቱ አይደለም፣ በየጊዜው ብዙ አሻሽሏል። በቀላሉ መሰል ተራ ሪፖርትን አያስተናግድም።
በሆነ አጋጣሚ አፕደት ሲሠሩ ልክ ባለፈ ክላውድፍሌር እንዳጋጣመው ችግር ቢፈጠር እንኳ (ይህ ተራ ነገር ከመሆኑ ጋር)፤ ድጋሜ ለትክክለኛ ባለቤቱ የሚመለስበትን አማራጭ ያመቻቻሉ።
ይሄ የሚሰራጨው hoax እና engagement farming አይጠቅማችሁም፤ በዚህ አትሸበሩ። ተጨንቃችሁ እኔንም አጥፋ ያላችሁኝ አላጠፋም።
ቴሌግራም ዝም ብሎ በነ ጃቫ ስክሪፕት የተሠራ አታስመስሉት¡
ያንን አሉባልታ ከምታሰራጩ፤ ተደነባብረው ቻነላቸውን የሚያጠፉ ሰዎችን ለመታደግ፤ ይህንን መልዕክት በየቦታው አሰራጩላቸው።
|| Murad Tadesse

👌3
Google የWindows software ተለቋል።
በቀላሉ search ማድረግ ስትፈልጉ browser መክፈት ሳይጠበቅባችሁ ALT+Space በመንካት search ማድረግ ያስችላችኋል።
ከዚህ በተጨማሪ የኮምፒውተራችሁ screen ላይ ያለ ማንኛውንም ነግር በቀላሉ crop እያደረጋችሁ search ማድረግ ትችላላችሁ።
ከዚህ ማወረድ ትችላላችሁ።
◆ https://labs.google.com/search?source=hp&authuser=0
◆ t.me/BasicComputer_Skills/2998

🌟 የነገው ብርሃን ስንቅ፡ ለተማሪዎችና ለወላጆች የቀረበ የሕይወት ጥሪ!
♦️[በተማሪዎች ወቅታዊ ሁኔታ የተከተበ]
══════════════
መግቢያ:
እናንተ ተማሪዎች ሆይ! ሕይወት በምኞት ብቻ የምትገነባ አይደለችም። ዛሬ የምታሳዩት ትጋት፣ የምትላበሱት ስነ-ምግባር እና ለወላጆቻችሁ የምታሳዩት ክብር ነገ የምትሆኑትን ሰው ይወስናል። ይህ መልዕክት ከቁርኣን፣ ከሐዲሥ እና ከታላላቅ ዑለሞች ጥበብ የተቀዳ ስንቅ ነው። ወላጆች ሆይ! ይህንን መመሪያ ከልጆቻችሁ ጋር ሆናችሁ አንብቡት፤ ምክንያቱም የነገው ውጤታማ ትውልድ የሚገነባው በዛሬው ጠንካራ ውይይትና መግባባት ላይ ነውና።
ክፍል 1፡ ስነ-ምግባር (አደብ) — የዕውቀት መጀመሪያና መድረሻ
እናንተ ተማሪዎች ሆይ! ዕውቀት ማለት መረጃዎችን መሸምደድ ብቻ አይደለም። ዕውቀት ያለ ስነ-ምግባር (አደብ) እንደ ቆሻሻ ላይ የተቀመጠ አልማዝ ነው። ብልጭታው ውበት ቢኖረውም ጠረኑ ግን ሰውን ያርቃል። መምህራኖቻችሁን ስታከብሩ፣ ለታላላቆቻችሁ ስትታዘዙና ለባልንጀሮቻችሁ መልካም ስትሆኑ አላህ በዕውቀታችሁ ላይ በረካን ያፈስላችኋል።
አላህ እንዲህ ይላል፦
“በእርግጥም አንተ (ሙሐመድ ሆይ) በታላቅ ስነ-ምግባር ላይ ነህ።” (ሱረቱ አል-ቀለም፡ 4)
ይህ መለኮታዊ ምስክርነት የሚያረጋግጥልን ታላቁ ነቢይ (ﷺ) የተወደሱት በላቀ ስነ-ምግባራቸው መሆኑን ነው። እናንተም ይህን ፈለግ መከተል አለባችሁ። ታላቁ ኢማሙ ሻፊዒይ እንዲህ ይላሉ፦ "አደብ (ስነ-ምግባር) የሌለው ሰው እውቀት የለውም፤ ትዕግስት የሌለው ሰው ሃይማኖት የለውም።" ስለዚህ እወቁ! ስነ-ምግባር ለዕውቀት መሰረት ነው። ስነ-ምግባር የሌለው ተማሪ የቱንም ያህል ቢማር ለሰዎች የሚጠቅም ብርሃን ሊሆን አይችልም፤ ይልቁንም ትዕቢቱ የዕውቀቱን ጣዕም ያጠፋዋል።
ክፍል 2፡ ወላጆች — የጀነት በሮችና የድል ቁልፎች
ወላጆች ሆይ! እናንተ ለልጆቻችሁ የምትከፍሉት መስዋዕትነት የሚመነጨው ከጥልቅ ፍቅር ነው። እናንተ ተማሪዎች ሆይ! ወላጆቻችሁ እናንተን ወደ ትምህርት ቤት ሲልኳችሁ፣ ከቤቱ ጫጫታ ለመገላገል እንዳይመስላችሁ። እነሱ ራሳቸውን እያቃጠሉ ለእናንተ ብርሃን የሚሆኑት፣ ነገ በኩራት "ልጆቼ ናቸው" ብለው የሚጠሩበት ደረጃ ላይ እንድትደርሱ በማለም ነው።
አላህ እንዲህ ይላል፦
“ጌታህም (እንዲህ ሲል) አዘዘ፦ እርሱን እንጂ ሌላን አትገዙ፤ ለወላጆቻችሁም መልካምን ውሉ...” (ሱረቱ አል-ኢስራእ፡ 23)
ይህ ትእዛዝ የሚያሳየን ለወላጆች ዝቅ ማለት ለአላህ ከፍ ማለት መሆኑን ነው። ኢማሙ አህመድ እንዲህ ይላሉ፦ "ወላጆችን መታዘዝ ለአላህ ከሚቀርቡባቸው የሱና ስራዎች ሁሉ የላቀ ነው።" እናንተ ተማሪዎች ሆይ! ወላጆቻችሁ የሚለፉት ለእናንተ ደስታ ነው። የእነሱን ውለታ ለመመለስ የዛሬው ትጋታችሁ እና የምታመጡት ውጤት ትልቁ የድካም ካሳቸው ነው። እነሱን ማስደሰት የጀነት መክፈቻ መሆኑን አውቃችሁ ለውጤት ተጋደሉ።
ክፍል 3፡ የጊዜ ሰይፍ — ዛሬን ካልቆረጣችሁት ነገ ይቆርጣችኋል
እናንተ ተማሪዎች ሆይ! ጊዜ የሚሮጥ ደመና ነው። ዛሬ የምታሳልፏት እያንዳንዷ ደቂቃ ነገ የሕይወታችሁ መሠረት ናት። ዛሬ ላይ ጊዜያችሁን በማይጠቅም ፊልም፣ በሶሻል ሚዲያና በከንቱ ወሬ ማሳለፍ ማለት የነገ ህይወታችሁ ላይ ትልቅ መሰናክል መገንባት ማለት ነው።
ነቢዩ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦
“ሁለት ጸጋዎች አሉ። ብዙ ሰዎች በእነሱ ይሸወዳሉ (ዋጋቸውን አያውቁም)፡- ጤንነት እና ክፍት ጊዜ።” (ቡኻሪ ዘግበውታል)
ይህ ማስጠንቀቂያ ዛሬ ጊዜያችሁን በከንቱ እያባከናችሁ መሆኑን ይነግራችኋል። ታላቁ ዓሊም ኢብኑል ቀይም እንዲህ ይላሉ፦ "ጊዜን ማባከን ከሞት ይከፋል፤ ምክንያቱም ሞት ከሰዎችና ከዱንያ ይለይሃል፤ ጊዜን ማባከን ግን ከአላህና ከአኼራ ይለይሃልና።" ይህ ንግግር እንደ ሰይፍ የሳለ ነው! ዛሬ የምታጠፉት ጊዜ ነገ በቁጭትና በእንባ ሊመለስ አይችልም። ዛሬ ስነፍ መሆን ማለት ነገ ዋጋ መክፈል ማለት መሆኑን አውቃችሁ ጊዜያችሁን በቁም ነገር ላይ አውሉት።
ክፍል 4፡ ለ6ኛ እና ለ8ኛ ክፍል ተፈታኞች — የጥንቃቄ ደወል
እናንተ የሚኒስትሪ ተፈታኞች ሆይ! ደወሉ እየጮኸ ነው! ለፈተና የቀረው ወቅት በጣም ጥባብና አጭር በመሆኑ፣ አላህን በመያዝ ጥረታችሁን ከየትኛውም ጊዜ በላይ መጨመር አለባችሁ። ይህ ወቅት የመጫወቻ ሳይሆን የውሳኔ ወቅት ነው።
ሼይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያ እንዲህ ይላሉ፦ "በትዕግስትና በጽናት እንጂ ታላቅነት (ስኬት) አይገኝም።"
ስኬት በአጋጣሚ የሚመጣ ሳይሆን በጽናት የሚገነባ ነው። በዚህች ጠባብ ወቅት የምታደርጉት ትግል ለዓመታት የምትደሰቱበትን ውጤት ያመጣላችኋል። አሁን መተኛት ወይም ቸልተኛ መሆን ነገ ለምታፍሩበት ውጤት ምክንያት ይሆናል። ስለዚህ የዛሬውን ጥረት አጥፉት!
ክፍል 5፡ ከስህተት መመለስ — የሕይወት አዲስ ምዕራፍ
ሰው ስህተተኛ ነው፤ እናንተም ትላንት አጥፍታችሁ፣ ጊዜያችሁን አባክናችሁ ወይም መጥፎ ጓደኛ ይዟችሁ ሄዶ ሊሆን ይችላል። ነገር ግን በስህተት ላይ መጽናት ነው ውድቀቱ። የዛሬ ስህተታችሁ ላይ መጽናት ነገ ህይወታችሁን ይቀጥፍባችኋል።
ነቢዩ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦
“የአደም ልጆች ሁሉ ስህተተኞች ናቸው፤ ከስህተተኞች ሁሉ በላጮቹ ግን (ከስህተታቸው) ተመላሾቹ ናቸው።” (ቲርሚዚ ዘግበውታል)
አላህ የመመለሻውን በር ሁልጊዜ ክፍት አድርጓል። ዛሬውኑ ተመለሱ፣ ተውበት አድርጉ። ሼይኽ ኢብኑ ባዝ እንዲህ ይላሉ፦ "እውነተኛ ለውጥ የሚጀምረው ስህተትን አምኖ ወደ አላህ በመመለስና አዲስ ጥረት በመጀመር ነው።" ትላንት ላይ አትቆዝሙ፤ ከዛሬ ጀምሮ አዲስ ተማሪ፣ አዲስ ታጋይ ሆናችሁ ተነሱ።
ክፍል 6፡ ለኡማው መዘጋጀት — የትልቅ ራዕይ ባለቤትነት
የምትማሩት ለራሳችሁ ሆድ ብቻ አይደለም። እናንተ የዚህ ኡማ የጀርባ አጥንት ናችሁ። ይህ ኡማ የሚታደገው፣ ከድንቁርና የሚያወጣውና በልህቀት የሚመራው ትውልድ ይፈልጋል።
አላህ እንዲህ ይላል፦
“ለሰዎች ከተገለጸች ህዝብ ሁሉ በላጭ ሆናችሁ፤ በደግ ነገር ታዛላችሁ፣ ከክፉም ትከለክላላችሁ...” (ሱረቱ አሊ-ዒምራን፡ 110)
ሐኪም ስትሆኑ ህሙማንን ለመርዳት፣ መሀንዲስ ስትሆኑ ሀገርን ለመገንባት፣ አዋቂ ስትሆኑ ጨለማን ለማብራት መዘጋጀት አለባችሁ። ነቢዩ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦ “ጠንካራ አማኝ ከአላህ ዘንድ ከደካማ አማኝ ይበልጥ በላጭና ተወዳጅ ነው።” (ሙስሊም ዘግበውታል)። ይህ ጥንካሬ በዕውቀትም ጭምር መሆኑን አውቃችሁ ለኡማው ኩራት ለመሆን ተጋደሉ።
ክፍል 7፡ ጥረትና ዱዓ — የማይነጣጠሉ ክንፎች
እናንተ ተማሪዎች ሆይ! ከጥረት በፊትም ሆነ ከጥረት በኋላ ዱዓ ማድረግ የአላህ ባሪያ መገለጫ ነው። በጥናት ብቻ አትመኩ፣ አላህ ካልረዳችሁ ጥረታችሁ ፍሬ አይኖረውም። ነገር ግን ሳታጠኑ "አላህ ያሳልፈኝ" ማለት ስንፍና ነው።
ኢማሙ አህመድ እንዲህ ይላሉ፦ "ሰበቡን (ምክንያቱን) ሳያደርስ 'በአላህ እመካለሁ' የሚል ሰው የአላህን ህግ ያልተረዳ ሰው ነው።" ይህ የሚያስገነዝበን ስኬት የጥረትና የዱዓ ውህደት መሆኑን ነው። ታላቁ ሰሃባ ዐሊይ ኢብኑ አቢ ጣሊብ (ረ.ዐ) እንዲህ ይላሉ፦ "ጥረት የሌለው ዱዓ ልክ ያለ ክር ቀስት እንደሚወረውር ሰው ነው።" ልክ ያለ ክር ቀስት መወርወር እንደማይቻለው ሁሉ፣ ያለ ጥረትም ዱዓ ብቻውን ውጤት አያመጣም። ስለዚህ አጥኑ፣ ተጋደሉ፣ ከዚያም ውጤቱን በአላህ ላይ ጣሉ። አላህ የለፋውን ሰው ድካም አያባክንም።

ክፍል 8፡ ተስፋና ጽናት — ትግላችሁ ነገ ይከፍላችኋል
ተማሪዎች ሆይ! መንገዱ አድካሚ ሊሆን ይችላል፣ ፈተናው ሊከብድ ይችላል። ነገር ግን ተስፋ አትቁረጡ። የአላህ እዝነት ሰፊ ነው።
አላህ እንዲህ ይላል፦
“በእርግጥም ከችግር ጋር ምቾት አለ።”(ሱረቱ አል-ኢንሺራህ፡ 5-6)
ዛሬ መራራ የሆነው ጥናት፣ ነገ ጣፋጭ የሆነ ስኬት ይዞላችሁ ይመጣል። ሼይኽ ኢብኑ ኡሰይሚን እንዲህ ይላሉ፦ "የዕውቀት መንገድ መጀመሪያው ድካም፣ መጨረሻው ግን የዱንያና የአኼራ ደስታ ነው።" የዛሬ ሙከራችሁ ነገ እጥፍ ድርብ ሆኖ በመልካም ይጠብቃችኋልና እስከመጨረሻው ድረስ ጽኑ።
መደምደሚያ (የመልዕክት ማሰሪያ)
✅ ለእናንተ ለውድ ተማሪዎች፡
ዛሬ የምታፈሱት ላብ ነገ የደስታ እንባ ሆኖ እንደሚመለስላችሁ አትጠራጠሩ። ስነ-ምግባራችሁ የዕውቀታችሁ ውበት፣ ጥረታችሁ ደግሞ የድላችሁ መመሪያ ይሁን። ሰዓታችሁን አትግደሉ፤ ምክንያቱም ጊዜያችሁ ሕይወታችሁ ነውና። ከስህተታችሁ የምትመለሱበት፣ ወደ ስራ የምትገቡበትና ተስፋን ሰንቃችሁ የምትቆሙበት ወቅት አሁን ነው። ዛሬ የምታሳዩት ጥንካሬ ነገ በታሪክ የሚነገር ታላቅ ማንነታችሁ ይሆናል። አላህን ያዙ፣ ጠንክሩ፣ ኡማውን ለመጥቀም ዝግጁ ሁኑ!
✅ ለእናንተ ለተከበራችሁ ወላጆች፡
ልጆቻችሁ ላይ የምትዘሩት ትዕግስትና የምታፈሱት ጥረት መቼም ቢሆን አይባክንም። እናንተ የነገውን ትውልድ ቀራጺዎች፣ የጀግና አምራቾች ናችሁ። ልጆቻችሁ ለውጤት ሲታገሉ እናንተ በዱዓና በምክር ከጎናቸው አትራቁ። የእነሱ ስኬት የእናንተ የዓይን ማረፊያ፣ በዱንያም በአኼራም ትልቁ የድካማችሁ ካሳ ነው። አላህ ጥረታችሁን ይባርከው፣ ልጆቻችሁንም ለቁም ነገር ያብቃልን።
🤲 የዱዓ ስብስብ
እናንተ ተማሪዎች ሆይ! እነዚህን ዱዓዎች በየቀኑ ደጋግሟቸው፦
► አላሁመ ረበና አቲና ፊ ዱንያ ሐሰና ወፊል አኺረቲ ሐሰና ወቂና ዐዛበ ናር
(ጌታችን ሆይ! በዱንያም መልካምን፣ በአኼራም መልካምን ስጠን፤ ከእሳት ቅጣትም ጠብቀን።)
► አላሁመ አዒና ዐላ ዚክሪከ ወሹክሪከ ወሑስኒ ዒባደቲክ
(አላህ ሆይ! አንተን በማውሳት፣ አንተን በማመስገን እና አንተን በሚያምር ሁኔታ በመገዛት ላይ አግዘኝ።)
► አላሁመ ኢኒ አዑዙቢከ ሚን ሙንከራቲል አኽላቅ ወልአዕማል ወልአህዋእ
(አላህ ሆይ! እኔ ከተጠሉ/መጥፎ ስነ-ምግባራት፣ ከክፉ ስራዎች እና ከማይጠቅሙ ምኞቶች በአንተ እጠበቃለሁ።)
► አላሁመ ኢንፈዕኒ ቢማ ዐለምተኒ ወዐሊምኒ ማ የንፈዑኒ ወርዙቅኒ ዒልመን ተንፈዑኒ ቢሂ
(አላህ ሆይ! በስተማርከኝ ነገር ጥቀመኝ፣ የሚጠቅመኝንም ነገር አስተምረኝ፣ የምትጠቅመኝንም እውቀት ለግሰኝ።)
► አላሁመ ኢኒ አስአሉከ ዒልመን ናፊዓ ወሪዝቀን ጠዪባ ወዐመለን ሙተቀበላ
(አላህ ሆይ! እኔ ጠቃሚ እውቀትን፣ መልካም ሲሳይን እና ተቀባይነት ያለውን ስራ እጠይቅሃለሁ።)
══════════════
📅 የሳምንቱ የትግልና የለውጥ እቅድ (ለተማሪዎች)
ይህ እቅድ እናንተን ከስንፍና አውጥቶ ወደ ስኬት ጎዳና የሚያስገባ የተግባር መመሪያ ነው። በየቀኑ ራሳችሁን እየገመገማችሁ ተግባራዊ አድርጉት።
ቀን 1፡ የውሳኔና የንጽህና ቀን
◆ ተግባር፦ ትላንት ያባከናችሁትን ጊዜ በመጸጸት ለአላህ ቃል ግቡ። ትምህርታችሁን ለማንበብ የሚያስተጓጉሉ ሶሻል ሚዲያዎችንና መጥፎ ጓደኞችን ዛሬውኑ አቁሙ።
➼ የቀኑ መሪ ቃል፦ "ለውጥ የሚጀምረው ከእኔ ውሳኔ ነው!"
ቀን 2፡ የወላጆች ምርቃት ቀን
◆ ተግባር፦ ዛሬ ወላጆቻችሁን ዝቅ ብላችሁ አገልግሉ። ድካማቸውን ተረድታችሁ "ዱዓ አድርጉልኝ" በሏቸው። የእነሱ ደስታ የጭንቅላታችሁን መከፈትና የዕውቀታችሁን በረካ ይወስነዋል።
➼ የቀኑ መሪ ቃል፦ "የወላጆቼ ደስታ የስኬቴ ቁልፍ ነው!"
ቀን 3፡ የጊዜ ሰሌዳ (Schedule) የማውጫ ቀን
◆ ተግባር፦ የቀረውን ጊዜ በደቂቃ አስሉ (ለ6ኛ እና 8ኛ ክፍል ተፈታኞች)። የትኛውን ትምህርት በየትኛው ሰዓት እንደምታጠኑ ግልጽ እቅድ አውጡ። ያላጠናችሁትን ምዕራፍ ለይታችሁ ጀምሩ።
➼ የቀኑ መሪ ቃል፦ "ጊዜዬን ካልመራሁት ይመራኛል!"
ቀን 4፡ የጽናትና የትግል ቀን
◆ ተግባር፦ ዛሬ የከበዳችሁን ትምህርት ፊት ለፊት ተጋጠሙት። "አይገባኝም" የሚለውን የሰይጣን ወሬ አቁማችሁ ደጋግማችሁ አንብቡ። ቢያንስ ለ 4 ሰዓታት ጥልቅ ጥናት (Deep Study) አድርጉ።
➼ የቀኑ መሪ ቃል፦ "ትዕግስት የድል ድልድይ ናት!"
ቀን 5፡ የስነ-ምግባርና የጥያቄ ቀን
◆ ተግባር፦ መምህራኖቻችሁን በትህትና ጠይቁ። ያልገባችሁን ነገር ለመጠየቅ አትፈሩ። በክፍል ውስጥ ያላችሁን አደብ ፈትሹ። የጓደኛችሁን ውጤት ሳይሆን የራሳችሁን እድገት ተከታተሉ።
➼ የቀኑ መሪ ቃል፦ "አደብ ያለው ዕውቀት ብርሃን ነው!"
ቀን 6፡ የራስን የመፈተኛ ቀን
◆ ተግባር፦ በዚህ ሳምንት ያጠናችሁትን ነገር ለመገምገም ያለፉ የፈተና ጥያቄዎችን (Old Exams) ስሩ። የት ጋ እንደምትሳሳቱ ለዩ። ስህተታችሁ ላይ በደንብ ስሩ።
➼ የቀኑ መሪ ቃል፦ "ራሱን የገመገመ አይወድቅም!"
ቀን 7፡ የዱዓና የዝግጅት ቀን
◆ ተግባር፦ ለሰራችሁት ስራ አላህን አመስግኑ። ለቀጣዩ ሳምንት ብርታት እንዲሰጣችሁ ዱዓ አድርጉ። ድካማችሁን በአላህ እዝነት እንዲተካላችሁ ለምኑት።
➼ የቀኑ መሪ ቃል፦ "ጥረት ከእኔ - ውጤት ከአላህ!"
ልዩ ማሳሰቢያ፦
ይህ እቅድ ሰይፍ ነው። ካልተጠቀማችሁበት ዝገት ይበላዋል። እናንተ ተማሪዎች ዛሬ የምትከፍሉት ዋጋ ነገ በኩራት የምትቀበሉት የድል ውጤት ነው። ዛሬውኑ ጀምሩ!
══════════════
🔰 አላህ ይርዳችሁ!
🔰 አላህ ውጤቱን ያማረ ያድርግላችሁ!
🔰 አላህ በእናንተ ጥረት ብቻ ሳይሆን በሱ (በአላህ) እዝነት መልካም የሆነ ውጤትን ይስጣችሁ!!
ይህ መልዕክት ለተማሪዎች እንዲደርስ በማድረግ የኸይር ስራ ተካፋይ ይሁኑ።
✍️በረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል

❤6👎1
Aptoide
በAptoide application እንደ Gemini AI እና Notebooklm የመሳሰሉ ስልካችሁ ላይ ካልጫናችሁ ይህን application store በመጫን ከሱ ላይ ማውረድ ትችላላችሁ።
Aptoide "This Item is not available in your country" እያለ የሚያስቸግሯችሁን Play store ላይ የሌሉ አፕሊኬሽኖች በቀላሉ ማውረድ ትችላላችሁ።
Download link Link
t.me/BasicComputer_Skills/3003