Basic Computer Skills
Photo
የወደፊቱ የአለማችን የኢንተርኔት አብዮት Starlink ምንድን ነው?
Starlink በኤለን መስክ ድርጅት SpaceX የተመሰረተ የሳተላይት ኢንተርኔት project ነው።
የዚህ ፕሮጀክት ተቀዳሚ ተልዕኮው በዓለም ዙሪያ ላሉ የኢንተርኔት አገልግሎት ለማያገኙ ገጠራማና ሩቅ የአለም ክፍሎች ከፍተኛ ፍጥነት ያለው የኢንተርኔት አገልግሎት እንዲያገኙ ማድረግ ነው።
ብዙ ቁጥር ያላቸው Low Earth Orbit (LEO) ሳተላይቶችን በጋራ በማሰማራት የፋይበር ኦፕቲክና የሞባይል ኔትዎርክ ግንኙነት የማያገኙ አካባቢዎችን አስተማማኝና ፈጣን የኢንተርኔት አገልግሎቶችን ለማቅረብ አልሞ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል።
ዋና ዋና ባህሪያቶች
⚫ Global Coverage: የስታርሊንክ የሳተላይት ኢንተርኔት መላው ፕላኔት የሚሸፍን ሲሆን ይህም ቀደም ሲል የኢንተርኔት ግንኙነት የማያገኙ የአለማችን ክልሎችን ተደራሽ ያደርጋል።
⚫ High-Speed Internet: ስታርሊንክ ከባህላዊ የኢንተርኔት አገልግሎት አቅራቢዎች ጋር የሚወዳደር የብሮድባንድ ፍጥነትን የሚያቀርብ ሲሆን Online Gaming, Video Conferencingና የመሳሰሉ real-time online ስራዎችን በጥሩ ፍጥነት መከወን ያስችላል።
⚫ Easy Installation:
StarLink ለመጠቀም በጣም ቀላል የሆነችና በቀላሉ ከታ ቦታ ማንቀሳቀስ የምትቻል Dish ሲኖረው ማንኛውም ቦታ ላይ በማስቀመጥ እራሷን ከሳተላይት ጋር ማስተካከል ትችላለች። ከዚህ በተጨማሪ LTE connection ላላቸው የሞባይል ቀፎዎች የፅሁፍና የድምጽ መልዕክት እንዲሁም የኢንተርኔት አገልግሎት ያገኛሉ ተብሏል።
⚫ Constant Updates: ስታርሊንክ ተጨማሪ ሳተላይቶችን በማምጠቅ እና ሶፍትዌሩን በማዘመን ኔትወርኩን በየጊዜው እያሰፋ እና እያሻሻለ ይገኛል። አገልግሎቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ ብዙ የአለም ክፍሎችን እያካለለ ነው።
⚫ Disaster Response: አሁን የምንጠቀምባቸውን የኢንተርኔት አቅራቢ ድርጅቶችን infrastructure በተለያዩ ተፈጥሯዊና ሰው ሰራሽ አደጋዎች ቢወድሙ communication ይቋረጣል። የስታርሊንክ ሳተላይት ከዚህ ነገር ነጻ ሲሆኑ ለድንገተኛ አገልግሎቶች እና እርዳታ የሚፈልጉ የተጎዱ ሰዎችን በቀላሉ ማግኘት ያስችላል።
በአሁኑ ሰአት በተወሰኑ የአለማችን ሃገራት ስራ የጀመረው StarLink ከአፍሪካ ሃገራት ናይጀርያ፣ ጋና፣ ሴራሊዮን፣ ማላዊ፣ ዛምብያ፣ ቦቶስዋና፣ ማዳጋስካር፣ ሩዋንዳ፣ ኬንያና ደቡብ ሱዳን የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ናቸው።
ይህን አገልግሎት ለመጠቀም ክፍያው ያን ያክል ውድ የሚባል አይደለም። ከሃገራት ሃገራት ልዩነት ቢኖረውም ለግለሰብ unlimited high-speed ዳታ ለመጠቀም በወር 120 ዶላር መክፈል ይጠይቃል። ለBusiness plan ደግሞ በወር ከ140 እስከ 5000 ዶላር ድረስ ያስከፍላል።
ጎረቤቶቻችን ኬንያና ሶማልያ የstarlink service ካላቸው ሃገሮች መካከል ናቸው።
✍️ በሀገራችን በተለይ በገጠሪቱ የሀገራችን ክፍል ብዙ ሰው የኢንተርኔት አገልግሎት አያገኝም። ይህ ነገር በሃገራችን ቢጀመር ብዙ ሰው የሚጠቀም ይመስላችኋል? ሀሳባችሁን አካፍሉን።
©️ bighabesha
════════════════
📍 ለተጨማሪ የቴክኖሎጂ ምክሮች ቻናሉን ይቀላቀሉ
🌐 ዘመኑ #የቴክኖሎጂ ነው 📲 ከዘመኑ ጋር አብረው ይዘምኑ💻
Telegram: t.me/BasicComputer_Skills
Tiktok: tiktok.com/@basiccomputerskills
Instagram: instagram.com/basiccomputerskills
Umma Life: ummalife.com/ReshadMuzemil

👍3❤1
Belkin የተሰኘ የቴክኖሎጂ ድርጅት Wireless HDMI አስተዋወቀ።
በLas Vegas ከተማ እየተካሄደ ባለው አመታዊው የCES(Consumer electronics show) ፕሮግራም ላይ የቀረበው ይህ wireless HDMI ላፕቶፕ፣ ታብሌት ወይም ስማርትፎን ወደ ሌላ ስክሪን ያለ Wi-Fi ወይም Bluetooth ማጋራት የሚያስችል plug-and-play casting system አስተዋውቋል።
ይስ ሲስተም USB-C ዶንግል transmitterና USB-A to HDMI receiver የያዘ ሲሆን ዶንግሉን ስክሪኑን share ማድረግ የፈለግነው device ላይ ሰክተን USB-A to HDMI ሪሲቨሩን ደግሞ ቲቪ፣ ሞኒተር ወይም ፕሮጀክተር ላይ በመሰካት ያለምንም ችግር screen share ማድረግ ያስችለናል።
ሲስተሙን ለመጠቀም ምንም አይነት ዋይፋይ፣ ብሉቱዝ፣ አፕሊኬሽን ወይም ድራይቨር መጫን ሳያስፈልግ በ40 ሜትር ክልል ውስጥ ይሰራል ተብሏል። በተጨማሪም እስከ 1080P በ60Hzና ከ80ms ባነሰ latency እንደሚያስተላልፍ ተገልጿል።
ይህ ቴክኖሎጂ የ150 ዶላር ዋጋ የተለጠፈበት ሲሆን በሚቀጥለው አመት ለገበያ ይቀርባል ተብሎ ይጠበቃል።
©️bighabesha

❤3
#safety
ስልካችሁ ላይ እናንተም ሆናችሁ ታዳጊ እህት ወንድሞቻችሁ ወይም ልጆቻችሁ explicit የሆኑ ዌብሳይቶችን እንዳይከፍቱ በዚህ መሰረት መዝጋት ትችላላችሁ።
1. አጠቃላይ ስልካችሁ ላይ
የስልካችሁ settings ላይ ትገቡና connections የሚለውን ትመርጣላችሁ።
ከዛ more connection settings የሚል አማራጭ ታገኛላችሁ።
private DNS የሚለውን ከፍታችሁ Private DNS provider hostname ውስጥ Adult-filter-dns.cleanbrowsing.org ወይም family.adguard-dns.com የሚሉትን አማራጮች ሞልታችሁ Save አድርጉት።
2. Chrome Browser ላይ
በመጀመሪያ google chrome browser ከከፈታችሁ በኋላ ሶስት ነጥብጣቡን ነክታችሁ ወደ setting ውስጥ ግቡ።
⚫Privacy and security የሚለውን ምረጡ።
⚫በመቀጠል ትንሽ scroll እንዳደረጋችሁ የምታገኙትን "use secure DNS" የሚለውን ምረጡ።
⚫"use your current service provider" የሚል በdefault ተመርጦ የምታገኙ ሲሆን እኛም ከታች ያለውን "choose another provider" የሚለውን እንመርጣለን።
⚫በመጨረሻም ከስር የሚመጣልንን "custom" የሚለውን ነክተን "clean browsing (family filter)" የሚለውን መምረጥ።
ከዚህ በኋላ ምንም አይነት adult content በየትኛውም browser ላይ አይመጣም።

ወደ ስኬት ማማ የሚወስደው ወርቃማው ድልድይ! (የሞዴል ፈተና ሚስጥር)
════════════════
አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱህ!
📚 ውድ የዕውቀት ፈላጊዎች፣ የነገ ሀገር ተስፋዎችና የዚህ ዘመን የለውጥ ፀሐዮች!
ይህ መልዕክት ለዛሬ ወይም ለነገ ብቻ ሳይሆን፣ የሰው ልጅ በትምህርትና በእውቀት ጎዳና ላይ እስካለ ድረስ ዘወትር የሚሰራ እውነተኛ የህይወት ስንቅ ነው። ልባችሁን ሰፋ አድርጋችሁ፣ እንደ ውሃ የሚወርደውን ይህን ሀሳብ አጣጥሙት። (አንባቢዎች ሆይ አላህ ይርዳችሁ 🤲)
✅ 1. ራስን የመመልከቻው "እውነተኛው መስታወት"
ብዙ ተማሪዎች የሚሰናከሉት ባለማወቃቸው ሳይሆን፣ "አውቃለሁ" በሚል ስሜት ውስጥ ስለሚዘናጉ ነው። ሞዴል ፈተና ማለት የውሸት ካባችሁን አውልቆ፣ ትክክለኛውን የእውቀት ደረጃችሁን የሚያሳይ ጥርት ያለ መስታወት ነው።
◆ የድክመት ካርታ፡ ሞዴል ፈተና ማለት የትኛው የእውቀት ክምችትህ ላይ ክፍተት እንዳለ የሚጠቁም ጠቋሚ መሳሪያ (Compass) ነው። ክፍተቱ ሳይንስ ላይ ነው? ወይስ ቋንቋ ላይ? ፈተናው ሳይነግርህ በፊት በሞዴል ፈተና እራስህን መገምገም ትልቁ ጥበብ ነው።
✅ 2. የስነ-ልቦናው "ሰላምና እርጋታ" (Peace of Mind)
ፈተና ማለት እውቀት ብቻ አይደለም፤ ፈተና ማለት የስነ-ልቦና ዝግጅትም ነው። ብዙ ተማሪዎች ጎበዝ ናቸው፤ ነገር ግን የፈተና ክፍል ሲገቡ ይርበተበታሉ።
◆ ድንጋጤን ማራቅ፡ ሞዴል ፈተናን በተደጋጋሚ መውሰድ ማለት፣ አዕምሮን ከ"አዲስ ነገር" ድንጋጤ ማላቀቅ ነው። ልክ ዋናተኛ ውሃ ውስጥ ከመግባቱ በፊት ሰውነቱን እንደሚያላምደው፣ እናንተም የፈተና ወረቀት ሲሰጣችሁ ልባችሁ በተረጋጋና በሰከነ ሁኔታ እንዲመታ ያደርጋል።
✅ 3. ጊዜን የመግራት ጥበብ
ሰዓቱ ሲሮጥ ማየት ያስጨንቃል። ሞዴል ፈተና ግን ከሰዓቱ ጋር አብሮ መጓዝን ያስተምራችኋል። አንድን ጥያቄ ለመመለስ ስንት ደቂቃ እንደሚያስፈልግህ በደመ-ነፍስ (Instinctively) እንድታውቅ ያደርግሃል።
◆ ጊዜ እንደ ወርቅ ነው፡ በአግባቡ ካልተጠቀምንበት ይባክናል። ጊዜን መግደል አይቻልም፤ ጊዜው እራሱ እኛን ይገድለናልና። ሞዴል ፈተና ይህንን ውድ ጊዜ እንዴት በብልሃት እንደምትጠቀሙበት ያስተምራችኋል።
✅ 4. አዕምሮን ማጎልበትና ማነቃቃት
አንድ ስፖርተኛ ለውድድር ከመቅረቡ በፊት ሰውነቱን ያሟሙቃል። ለምን? ብቁ ለመሆን! እናንተስ?
◆ የማስታወስ አቅም፡ ሞዴል ፈተና ስትሰሩ፣ አዕምሮአችሁ በመጋዘኑ ውስጥ ያስቀመጠውን መረጃ በፍጥነት ፈልጎ የማውጣት ልምምድ ያደርጋል። መጽሐፍን ደጋግሞ ከማንበብ ይልቅ፣ እራስን መፈተን የማስታወስ ችሎታንና የመረዳት አቅምን በከፍተኛ ሁኔታ ይጨምራል።
✅ 5. በራስ መተማመን እና የድል መንፈስ
አንድን ተራራ ከመውጣትህ በፊት፣ የመንገዱን ካርታ የሚያውቅ ሰው ልበ-ሙሉነቱ ልዩ ነው።
◆ የአሸናፊነት ስሜት፡ በሞዴል ፈተና ጥሩ ውጤት ስታመጡ፣ ውስጣችሁ "እችለዋለሁ!" የሚል ኃይለኛ ማንነት ይገነባል። ይህ ማንነት በዋናው ፈተና ቀን እንደ ጋሻ ሆኖ ከጭንቀት ይጠብቃችኋል።
◆ መረጋጋት (ሰኪና)፡ በደንብ የተዘጋጀ ተማሪ አይጣደፍም። እርጋታው እራሱ ለሌሎች ተማሪዎች ያስቀናል። ይህ እርጋታ የሚመጣው ከቅድመ-ዝግጅት ነው።
🔥 የልብ መልዕክት
ሞዴል ፈተናን እንደ "ሸክም" አትዩት። እንደ "ወርቃማ እድል" ቁጠሩት። ዛሬ ላይ ተሳሳቱ፣ ዛሬ ላይ ተደናገጡ፣ ዛሬ ላይ ጊዜ ይለቅባችሁ። ምክንያቱም ዛሬ ማረም ይቻላል! በዋናው ፈተና ቀን ግን ስህተትን ማረም አይቻልም፤ የሚቻለው ውጤትን መቀበል ብቻ ነው።
ይህንን እድል ተጠቅማችሁ፣ እራሳችሁን አብቅታችሁ፣ ድክመታችሁን አርማችሁ ለድል ብቁ እንድትሆኑ አደራ። ትምህርት የኢባዳ (የአምልኮ) አካል ነው፤ ጠንክሮ መማር ደግሞ "ኢህሳን" (ምርጥ ስራ) ነው።
🤲 ዱዓ
ያ የዓለማት ጌታ የሆነው አላህ ሆይ! ይህንን ለወገኖቻቸው፣ ለሀገራቸውና ለራሳቸው ብለው ሌት ተቀን የሚደክሙ ተማሪዎችን ልፋት አንተ ባርክላቸው።
ጌታዬ ሆይ! በፈተና ሰዓት የመረጋጋትን መንፈስ አውርድላቸው። የረሱትን አስታውሳቸው፣ የከበዳቸውን አቅልላቸው። እውቀታቸው በወረቀት ላይ ብቻ ሳይሆን በህይወታቸውም ላይ ብርሃን ሆኖ እንዲፈነጥቅ አድርግላቸው።
ለወላጆቻቸው የዓይን ማረፊያ፣ ለሀገራቸው የጀርባ አጥንት፣ ለዲናቸውም ጋሻና መከታ አድርገህ ያማረ ውጤትን ወፍቃቸው። አሚን! 🤲
📖 ማጠቃለያ (መለኮታዊ ቃል)
ንግግሬን የምዘጋው ሁሉን በሚያውቀው ጌታችን በአላህ ቃል ነው። የሰው ልጅ የሚለፋው ለራሱ ነው፤ ውጤቱንም የሚያገኘው እንደ ልፋቱ ልክ ነው።
"ለሰውም ሁሉ የሠራው እንጂ ሌላ የለውም። ሥራውም ወደ ፊት (በቂያማ ቀን) በእርግጥ ይታያል። ከዚያም ሙሉውን ዋጋ ይመነዳል።"
(ሱረቱ አን-ነጅም፡ 39-41)
በልበ ሙሉነት ተዘጋጁ! የስኬት ማማ እጃችሁ ላይ ነው!
✍️ በረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል

❤2
Grade_7_ICT_&_CTE_T_1st_Sem_Final_Exam_Table_of_Specifications.pdf
217 KB
✅📚 2018 E.C Grade 7 ICT and CTE
የማጠቃለያ ፈተና የፈተና ቢጋር (Table of Specification for Final Exam)
✅ በተለይም የሙምታዝ ት/ቤት ተማሪዎች Final Exam ያዘጋጀሁላችሁ በዚህ መሠረት ስለሆነ ተጠቀሙበት።
✅ አላህ ይርዳችሁ!!
✍️ ረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል

Grade_8_ICT_and_CTE_1st_Sem_Final_Exam_Table_of_Specifications.pdf
226.6 KB
✅📚 2018 E.C Grade 8 ICT and CTE
የማጠቃለያ ፈተና የፈተና ቢጋር (Table of Specification for Final Exam)
✅ በተለይም የሙምታዝ ት/ቤት ተማሪዎች Final Exam ያዘጋጀሁላችሁ በዚህ መሠረት ስለሆነ ተጠቀሙበት።
✅ አላህ ይርዳችሁ!!
✍️ ረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል
የማጠቃለያ ፈተና የፈተና ቢጋር (Table of Specification for Final Exam)
✅ በተለይም የሙምታዝ ት/ቤት ተማሪዎች Final Exam ያዘጋጀሁላችሁ በዚህ መሠረት ስለሆነ ተጠቀሙበት።
✅ አላህ ይርዳችሁ!!
✍️ ረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል
ከጀማሪ እስከ አድቫንስድ ሁሉም ሊያውቃቸው የሚገቡ የWindows shortcuts.
1. Basic & Everyday Shortcuts (Must-Know)
⚫ Ctrl + C = Copy
⚫ Ctrl + V = Paste
⚫ Ctrl + X = Cut
⚫ Ctrl + Z = Undo
⚫ Ctrl + Y = Redo
⚫ Ctrl + A = Select all
⚫ Ctrl + S = Save
⚫ Ctrl + P = Print
⚫ Ctrl + F = Find / Search
⚫ Ctrl + N = New window / document
2. Window & App Control (Power User)
⚫ Alt + Tab = Switch between open apps
⚫ Alt + F4 = Close current app
⚫ Ctrl + Shift + Esc = Open Task Manager
⚫ Windows + D = Show / hide desktop
⚫ Windows + L = Lock your PC
⚫ Windows + E = Open File Explorer
⚫ Windows + I = Open Settings
3. File Explorer Shortcuts
⚫ Ctrl + Shift + N = New folder
Delete Delete file (Recycle Bin)
⚫ Shift + Delete Delete permanently
⚫ Alt + Enter = File properties
F2 Rename file
⚫ Ctrl + Mouse scroll = Zoom icons
4. Screenshot & Recording Shortcuts.
⚫ PrtSc = Screenshot (clipboard)
⚫ Alt + PrtSc = Screenshot active window
⚫ Windows + PrtSc = Save screenshot automatically
⚫ Windows + Shift + S = Snipping Tool (best)
⚫ Windows + Alt + R = Screen recording (Xbox Bar)
5. Browser Shortcuts (Chrome, Edge, Firefox)
⚫ Ctrl + T = New tab
⚫ Ctrl + W = Close tab
⚫ Ctrl + Shift + T = Reopen closed tab
⚫ Ctrl + Tab = Next tab
⚫ Ctrl + L = Focus address bar
⚫ Ctrl + + / - = Zoom in / out
6. Text Editing Shortcuts
⚫ Ctrl + Backspace = Delete whole word
⚫ Shift + Arrow keys = Select text
⚫ Ctrl + Arrow keys = Jump by word
⚫ Ctrl + Shift + Arrow = Select by word
⚫ Ctrl + Home / End Go top / bottom
7. Advanced Windows Shortcuts (Creator Level)
⚫ Windows + X = Power menu (Admin tools)
⚫ Windows + V = Clipboard history
⚫ Windows + . = Emoji panel 😎
⚫ Windows + Tab Task View
⚫ Windows + Ctrl + D = New virtual desktop
⚫ Windows + Ctrl + ← / → = Switch desktops
8. Emergency / Fix Shortcuts
(When something freezes.)
⚫ Ctrl + Alt + Delete = Security options
⚫ Ctrl + Shift + Esc = Force open Task Manager
⚫ Alt + Space → M = Move stuck window
✍️የወደዳችሁት shortcut የቱ ነው?

👏2❤1
ርዕስ፡ 📢 ከጋላክሲ ዊዝደም አሰልጣኝ ፋንታሁን ሀሰን ጋር የተደረገ እጅግ ወሳኝ የህይወት ውይይት!
"ልጆቻችን የጀነት ስጦታዎቻችን ወይስ የቤተሰባችን ህመም ተሸካሚዎች?"
ውድ የሙምታዝ አካዳሚ ቤተሰቦች፣ አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱህ!
ዛሬ በሙምታዝ አካዳሚ፣ በታላቁ አሰልጣኝ ፋንታሁን ሀሰን አማካኝነት እጅግ ዐይን ገላጭ፣ ልብ የሚሰብር እና መልሶ የሚጠግን ድንቅ ስልጠና አግኝተናል። ስልጠናው ስለ ልጆቻችን ብቻ ሳይሆን ወደ እራሳችን እንድንመለከት ያደረገ እውነተኛ መስታወት ነበር።
አላህ (ሱ.ወ) በቅዱስ ቁርአኑ እንዲህ ይላል፡-
“ገንዘብና ልጆች የቅርቢቱ ሕይወት ጌጦች ናቸው...” (አል-ከህፍ፡ 46)
ነገር ግን እነዚህን ጌጦች እንዴት እየያዝናቸው ነው? ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) “ሁላችሁም እረኞች ናችሁ፤ ስለ መንጋችሁም ትጠየቃላችሁ” (ቡኻሪና ሙስሊም) ብለውናልና ቆም ብለን እራሳችንን እንፈትሽ።
ከስልጠናው የቀሰምነውን ወርቃማ እና ህይወት ቀያሪ ሀሳቦች፣ ከእስላማዊ እሴቶች ጋር አዋህደን እነሆ በሁለት ክፍል አቅርበንላችኋል። ይህ ማስታወሻ የውቅያኖስን ያህል ጥልቀት ካለው የስልጠናው ሰነድ በጥቂቱ የተቀዳ ነው። ዋናውን በዝርዝር ለማግኘት ከታች የተያያዘውን PDF ይክፈቱ!
ክፍል 1፡ የልጆችን የተፈጥሮ ፀጋ (Intelligences) መረዳት
አላህ (ሱ.ወ) የሰው ልጆችን ሲፈጥር በአንድ ሻጋታ (Mould) አልቀረጻቸውም። ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) “ሰዎች እንደ ወርቅና ብር ማዕድናት ናቸው...” (ሙስሊም) እንዳሉት፣ ልጆቻችን ውስጥ ያለው ማዕድን የተለያየ ነው።
አሰልጣኝ ፋንታሁን በስልጠናው እንዳብራሩት ልጆች ከሚከተሉት ተሰጥኦዎች አንዱን ወይም ከዚያ በላይ ሊኖራቸው ይችላል። የእኛ ድርሻ ማወቅና መደገፍ ነው፡-
➊ የቋንቋ ብቃት (Linguistic): እንደ ሀሳን ኢብኑ ሳቢት (ረ.ዐ) የመናገርና የመጻፍ ችሎታ ያላቸው። ነገ የዲን ተሟጋች ወይም ታላቅ ጸሃፊ የሚሆኑ።
❷ የሂሳብና አመክንዮ ብቃት (Logical): እንደ ዘይድ ኢብኑ ሳቢት (ረ.ዐ) የመተንተንና የሂሳብ አቅም ያላቸው።
➌ ሰዎችን የመረዳት ተሰጥዖ (Interpersonal Intelligence):
እነዚህ ልጆች የሌሎችን ስሜት፣ ፍላጎትና አመለካከት በቀላሉ የመረዳት ልዩ አቅም አላቸው። በቡድን መስራት ይወዳሉ፣ ችግር ያስታርቃሉ፣ ሰዎችንም የመምራት ተፈጥሯዊ ዝንባሌ አላቸው።
◆ ምሳሌ፦ እንደ አቡበክር አሲዲቅ (ረ.ዐ) የሰዎችን ልብ ማሸነፍ የሚችሉ መሪዎችና ማህበራዊ ጠበብቶች ናቸው።
❹ የአካላዊ ብቃት (Bodily-Kinesthetic): እንደ ኻሊድ ኢብኑል ወሊድ (ረ.ዐ) በስፖርትና እንቅስቃሴ ሜዳ ላይ የሚደምቁ።
❺ የውስጥ ማንነት ብቃት (Intrapersonal): ራሳቸውን የሚያዳምጡና ጠንካራ የውስጥ ማንነት ያላቸው።
❻ የድምፅ ተሰጥኦ (Rhythmic): ለድምፅ ልዩ ትኩረት ያላቸው። ይህንን ጸጋ ቁርአንን በውብ ድምፅ በማነብነብ (እንደ አቡ ሙሳ አል-አሽዓሪ) እንዲጠቀሙበት ልናግዛቸው ይገባል።
❼ የራስን ማንነት የመረዳት ተሰጥዖ (Intrapersonal Intelligence):
እነዚህ ልጆች የራሳቸውን ስሜት፣ ጥንካሬና ድክመት ጠንቅቀው የሚያውቁ ናቸው። ብቻቸውን መሆንና ማሰብ ያስደስታቸዋል። የራሳቸውን ግብ ያስቀምጣሉ፣ በራሳቸውም ይተማመናሉ።
ምሳሌ፦ እንደ ታላቁ የዲን ሊቅ ኢማሙ አል-ጋዛሊ (ረሂመሁላህ) የራሳቸውን ነፍስ መርምረው ለትልቅ ደረጃ የሚበቁ፣ ነገ ጥልቅ አስተላላፊዎች (Philosophers) ወይም የነፍስ ሐኪሞች (Psychologists) የሚሆኑ ናቸው።
❽ ተፈጥሮን የመረዳት ተሰጥዖ (Naturalist Intelligence):
እነዚህ ልጆች ለአካባቢያቸው፣ ለተክሎች፣ ለእንስሳትና ለተፈጥሮ ክስተቶች ልዩ ፍቅርና ትኩረት አላቸው። በተፈጥሮ ውስጥ መሆን ያስደስታቸዋል፣ ነገሮችን የመለየትና የመመደብ አቅማቸው ከፍተኛ ነው።
◆ ምሳሌ፦ አላህ በቁርአኑ "በሰማያትና በምድር ባሉ ተአምራት ላይ አትመለከቱም?" የሚለውን ጥሪ በተግባር የሚተረጉሙ፣ ነገ የአካባቢ ጥበቃ ባለሙያ ወይም ድንቅ የግብርና ሊቃውንት የሚሆኑ ናቸው።
❾ ስዕላዊ ተሰጥዖ (Visual/Spatial Intelligence):
ነገሮችን በምስል የማየት፣ የመቅረጽና የማስታወስ ብቃት። እንደ አርክቴክቶችና ዲዛይነሮች ነገሮችን በአዲስ መልክ የመቅረጽ ችሎታ ያላቸው ልጆች ናቸው።
መልዕክት: ኢማሙ ሻፊዒይ (ረሂመሁላህ) “ጊዜ እንደ ሰይፍ ነው...” እንዳሉት፣ የልጆቻችንን የተፈጥሮ አቅጣጫ በጊዜ ካላወቅንላቸው፣ የተፈጠሩበትን ዓላማ ሳያሳኩ ጊዜው ይቆርጣቸዋል።
ክፍል 2 👇👇👇

ክፍል 2፡ "የታመመ ቤተሰብ" (Dysfunctional Family) እና ሰለባ የሆኑ ልጆች
ይህ የስልጠናው ክፍል እጅግ ልብ የሚነካ ነው። ቤተሰብ ሲታመም (በግጭት፣ በፍቅር ማነስ፣ ወይም በተሳሳተ አስተዳደግ) ልጆች ያንን ክፍተት ለመሙላት ሳያውቁት 7 አደገኛ ሚናዎችን (Roles) ይጫወታሉ። በስልጠናው ሰነድ ላይ በስፋት እንደተብራራው፣ ልጆቻችንን የትኛው ሳጥን ውስጥ እንደከተትናቸው እንፈትሽ፡-
1. የሜዳሊያ ልጅ (The Hero)
◆ ማንነቱ: ቤተሰቡ የሚወደው ውጤት ሲያመጣ ብቻ ነው። ፍቅርን በውጤት ይለካል።
⭕️ አደጋው: ስህተት መሥራትን እንደ ሞት ይፈራል። ለቤተሰቡ ክብር ሲል የራሱን ማንነት ያጣል።
✅ የሸሪዓው ሚዛን: ይህ አደገኛ ነው። አላህ ሰዎችን የሚመዝነው በ"ተቅዋ" እንጂ በውጤት አይደለም።
2. ተሸካሚው ልጅ (The Scapegoat)
◆ ማንነቱ: የቤተሰቡን ጭንቀት፣ ንዴት እና ውድቀት ማራገፊያ የሆነ ልጅ። ወላጆች ሲጣሉ ጣቱ ወደ እሱ ይቀሰራል።
⭕️ አደጋው: አመፀኛ እንዲሆን ይገደዳል። ጥፋተኝነት ይሰማዋል።
✅ የሸሪዓው ሚዛን: አላህ “ማንኛዋም ነፍስ ኃጢአትን አትሸከምም” (አል-አንዓም 164) ይላል። የቤተሰብን ችግር በልጅ ላይ ማላከክ "ዙልም" (በደል) ነው።
3. የጠፋው ልጅ (The Lost Child)
◆ ማንነቱ: ቤተሰቡ ሲወጠር ይህ ልጅ ትኩረት ላለማጣት ድምፁን ያጠፋል። "ዝምተኛ፣ ጨዋ" ይባላል።
⭕️ አደጋው: በውስጡ ብቸኝነት እየበላው ነው። በስሜት የሞተ ልጅ ይሆናል።
✅ የሸሪዓው ሚዛን: ዝም ያለን ልጅ ችላ ማለት አማናን መብላት ነው።
4. የተቀባው ልጅ (The Golden Child)
◆ ማንነቱ: ሳይጠይቅ ሁሉም የሚሟላለት፣ ከወንድሞቹ ተለይቶ የሚንቀባረር።
⭕️ አደጋው: ሲያድግ ዓለም ሁሉ እንዲንቀጠቀጥለት ይፈልጋል። "ትዕቢተኛ" (Arrogant) ለመሆን የቀርበ ነው።
✅ የሸሪዓው ሚዛን: ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ)፡- “አላህን ፍሩ በልጆቻችሁም መካከል አስተካክሉ (ፍትሃዊ ሁኑ)” ብለው ይህንን ድርጊት አጥብቀው አውግዘዋል።
5. አስታራቂው ልጅ (The Mascot)
◆ ማንነቱ: የቤተሰቡን ግጭት በቀልድ እና በጨዋታ ለማብረድ የሚሞክረው።
⭕️ አደጋው: የቤተሰቡን ሠላም ለመጠበቅ ሲል በውስጡ እያለቀሰ የውሸት ፈገግታ ያሳያል።
6. ሞግዚት ልጅ (The Caretaker)
◆ ማንነቱ: ወላጆቹን ወይም ታናናሾቹን ለመንከባከብ ሲል የራሱን ጨዋታ እና ፍላጎት የገደለ።
⭕️ አደጋው: በልጅነት አካሉ የሽምግልና ጭንቀት ይሸከማል።
7. ብርቅዬው (በወላጅ ቅርጽ የተሰራው) ልጅ
◆ ማንነቱ: የወላጆቹን ያልተሳካ ህልም እንዲኖር የተገደደ። (ለምሳሌ፡ ወላጅ ዶክተር መሆን ፈልጎ ካልሆነ፣ ልጁን በግድ ዶክተር እንዲሆን የሚገፋው)።
⭕️ አደጋው: የራሱን ማንነት አያውቅም። የወላጆቹ "ሮቦት" ነው።
✅ የሸሪዓው ሚዛን: ዐሊይ ኢብኑ አቢ ጣሊብ (ረ.ዐ) “ልጆቻችሁን ለተፈጠሩበት ዘመን አሳድጉ፤ እነሱ የተፈጠሩት ለእናንተ ዘመን አይደለምና” እንዳሉት ልጆቻችንን በራሳችን ሳጥን ውስጥ አንክተታቸው።
📚 ወሳኝ ቀጣይ እርምጃ
ውድ ወላጆች! ይህ አጭር ማጠቃለያ ነው። በስልጠናው ላይ እያንዳንዱ ልጅ የሚያሳያቸው ምልክቶች እና መፍትሄዎች በዝርዝር ተቀምጠዋል።
"እኔ ቤት የትኛው ልጅ አለ?" ብለው እራስዎን ለመጠየቅ እና መፍትሄውን ለማግኘት ከታች የተያያዘውን PDF (የስልጠናውን ሙሉ ሰነድ) አሁኑኑ ይክፈቱ! ለልጆችዎ ሲሉ እባክዎ 10 ደቂቃ በመስጠት ያንብቡት።
ዱዓ 🤲
ያ አላህ!
ልጆቻችንን ለዓይናችን ማረፊያ፣ ለልባችን ደስታ አድርግልን።
ከታመመ አስተዳደግ፣ ከክፉ ነገር ሁሉ ጠብቀህ፤ በሰጠሃቸው ተሰጥኦ (Fitrah) ለአላማህ የምትጠቀምባቸው፣ ለዲናቸውና ለሀገራቸው ጠቃሚዎች አድርግልን።
እንደ ታላቁ ኢብኑል ቀይይም (ረሂመሁላህ) “ልብ እንደ ወፍ ነው፤ ከፍ ባለም ቁጥር ከአደጋ ይርቃል” እንዳሉት፣ የልጆቻችንን ልብ በእውቀትና በፍቅር ወደ አንተ ከፍ የምናደርግበትን ጥበብ ለግሰን። ቤታችንን የሰኪና (የመረጋጋት) እና የራህመት ቤት አድርግልን።
አሚን! 🤲 🤲 🤲
📚 ሙምታዝ አካዳሚ
በአላህ ፍቃድ የነገ መሪዎችን በብቃት እና በእምነት እንቀርፃለን!!
የስልጠናውን PowerPoint ለማግኘት ከታች ያለውን ሊንክ ተጫኑ!! 👇
t.me/MumtazKG/147?single

Google photos app አዳዲስ ፊቸሮች ተካቶለታል።
Google ሁሉንም እፕሊኬሽኖቹን የGemeni AI ፊቸር integrate እየደረገላቸው ይገኛል።
ከነዚህ ውስጥ አንዱ የሆነው Google photos የተለያዩ የAI ፊቸሮች ተካቶለታል።
ስልካችሁ ላይ ያለ ማንኛውንም ፎቶ በቀላሉ search አድርጋችሁ ማግኘት የምችሉበት ask የሚል አማራጭ ታገኛላችሁ።
Gemini powered የሆነው ይህ ፊቸር ፎቷችሁን በስም፣ በአይነት፣ ወይም በተነሳችሁ ቀን search አድርጋችሁ ማግኘት ትችላላችሁ።
ሌላው create የሚል አማራጭ ያለ ሲሆን ፎቷችሁን ወደ video ወይም ወደ animation መቀየር ትችላላችሁ።
Google photos application Update አድርጋችሁ check አድርጉት።
©️

❤5
SATCOM INSTITUTE OF TECHNOLOG cp hand out - Copy (1).pdf
2.5 MB
Smart phone ጥገና በአማርኛ
ፌስታል ይዛችሁ እንዳትቀጡ!
~
ከነገ ቅዳሜ ጥር 23/2018 ጀምሮ ፌስታል ይዞ የተገኘ ይቀጣል ተብሏል። እገዳው ለአንድ ጊዜ አገልግሎት የሚውሉ (ትንንሽም ይሁን ትልልቅ) ሁሉንም አይነት ፌስታሎች የሚያጠቃልል ሲሆን በእጅ ይዞ ለተገኘ ግለሰብ ከ2,000 እስከ 5,000 ብር ፣ ለአምራቾች፣ አከማቺዎች እና አከፋፋዮች ደግሞ ከ50,000 እስከ 200,000 ብር ቅጣት እና እስከ አምስት አመት የሚደርስ ጽኑ እስራት ያስቀጣል ተብሏል።
ተግባራዊነቱን ወደፊት የምናየው ይሆናል። ዋናው ነገር ህጉን ሰበብ አድርጎ የሚንቀሳቀስ የራበው ጅ - ብ እንዳያገኛችሁ ተጠንቀቁ። "ሰኞን አትሁኑ!"
"ሼር" ብታደርጉት።
©️ @IbnuMunewor

❤1
Basic Computer Skills
Photo
🚀 THE GRAND COMEBACK: REWRITING DESTINY (ታላቁ ትንሳኤ፡ ታሪክን የመቀየር ጥበብ)
════════════════
▣ መግቢያ፡ የጨዋታው ግማሽ ክፍል (Half-Time Analysis)
ህይወት እንደ እግር ኳስ ጨዋታ ናት። የመጀመሪያው አጋማሽ (First Semester) መጠናቀቅ የጨዋታው ፍጻሜ አይደለም። በመጀመሪያው አጋማሽ ውጤቱ አላማረም ማለት ተሸንፈሃል ማለት አይደለም። አሁን ያለንበት ጊዜ ስልት ቀይረን፣ ጉልበት አድሰን ለሁለተኛው ዙር "የሞት ሽረት" ትግል የምንዘጋጅበት ወሳኝ ምዕራፍ ነው። ትላንትናችሁ የዛሬ ማንነታችሁን አይወስንም፤ ነገን የመወሰን አቅሙ ግን አሁን ባላችሁ እጅ ላይ ነው።
➲ የተስፋ ብርሃን - ከዜሮ መነሳት ይቻላል!
ባለፈው መንፈቀ ዓመት ውጤታችሁ አላማረም? ደረጃችሁ ዝቅ ብሏል? "ተስፋ የለሽ ነኝ" የሚለውን የሰይጣን ሹክሹክታ አትስሙ። በእስልምና ተስፋ መቁረጥ የለም። አንድ ሰው ምን ያህል ወንጀል ቢሰራ በንስሃ (ተውበት) እንደሚመለስ ሁሉ፣ አንድ ተማሪም ምንም ያህል ቢወድቅ በቁርጠኝነት (Azim) ታሪኩን መቀየር ይችላል። ዛሬ ላይ "ዜሮ" ብትሆኑ እንኳን፣ በሁለተኛው መንፈቀ ዓመት በእውነተኛ ተጋድሎ (Jihad of Education) ወደ "ጀግና" መቀየር ትችላላችሁ።
"ሰውም ለርሱ የሠራው እንጂ ሌላ የለውም፡፡ ሥራውም ወደ ፊት ይታያል (ይፋ ይወጣል) ..." (ሱረቱ አን-ነጅም፡ 39-40)
❓ የነፍስ መመርመሪያ፦ ባለፈው ሴሚስተር ውጤቴ እንዲበላሽ ያደረገው ዋናው "ቫይረስ" ምንድን ነው? እንቅልፍ? ስልክ? ወይስ ጓደኛ? ዛሬ ይህንን ቫይረስ ከስሩ ለመንቀል ለአላህ ቃል ትገባለህ?
➲ ለ6ኛ እና ለ8ኛ ክፍል ተማሪዎች
እናንተ በሚኒስትሪ ፈተና አፋፍ ላይ ያላችሁ ተማሪዎች ሆይ! ይህ ሰዓት "የህይወት አቅጣጫ መቀየሪያ ወሳኝ ምዕራፍ" ነው። ጊዜው እየሮጠ ነው፤ ቀልድ ያብቃ! ይህ ፈተና ከክፍል ወደ ክፍል ማለፊያ ብቻ ሳይሆን፣ የነገ ማንነታችሁ መሰረት የሚጣልበት ነው። አሁን የምታፈሱት ላብ፣ ነገ የምታለቅሱትን እንባ ያድናል። እናንተ ልዩ "ሚሳኤል" ሁኑ፤ ኢላማችሁን (ውጤታችሁን) እስክትመቱ ድረስ ወደ ኋላ አትይዩ።
ነብዩ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፡- "አምስት ነገሮች ከመምጣታቸው በፊት በአምስት ነገሮች ተጠቀም፡ ... ሽምግልና ሳይመጣብህ በወጣትነትህ፣ መታመም ሳይመጣብህ በጤንነትህ..." (አል-ሐኪም ዘግበውታል፡ ሶሒሕ)
❓ የነፍስ መመርመሪያ፦ የቀሩት ወራት በጣም ጥቂት ናቸው። በዚህ አጭር ጊዜ ውስጥ ሙሉ መጽሐፍትን ሸፍኖ ለመጨረስ የምትችለው በምን አይነት ፍጥነት ብትጓዝ ነው? እቅድ አለህ ወይስ በዘፈቀደ ነው የምትነጉደው?
➲ ምክንያት ድርደራን መቅበር (No More Excuses)
"መምህሩ አይገባኝም"፣ "መብራት ይጠፋል"፣ "መጽሐፍ የለኝም"... እነዚህ የደካሞች መዝሙር ናቸው። አላህ እርዳታውን የሚልከው ሰበቡን አድርሰው ለሚታገሉ ነው። ጠንካራ አማኝ መብራት ሲጠፋ ሻማ ያበራል፤ መምህሩ ካልገባለት ሌላ መንገድ ይፈልጋል።
ነብዩ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፡- "ጠንካራ አማኝ ከአላህ ዘንድ ይበልጥ የተወደደና ከደካማ አማኝ የተሻለ ነው..." (ሶሒሕ ሙስሊም)
❓ የነፍስ መመርመሪያ፦ እኔን ወደ ኋላ እየጎተተኝ ያለው "ሰበብ" ምንድን ነው? ይህንን ሰበብ ዛሬውኑ አሽቀንጥሬ ለመጣል ዝግጁ ነኝ?
➲ የዲጂታል እስር ቤት (ስልክና ሶሻል ሚዲያ)
ብዙ ተማሪዎችን እየገደለ ያለው "ቲክቶክ" እና "ጌም" ነው። በሁለተኛው ሴሚስተር ስልካችሁን "የሚቆጣጣራችሁ" ሳይሆን "አገልጋያችሁ" አድርጉት። ለትምህርት ካልሆነ በስተቀር ከስልክ ራቁ። የፌስቡክ ላይክ ውጤት አያመጣም፤ የቲክቶክ ቪዲዮ የወደፊቱን ህይወት አይገነባም።
❓ የነፍስ መመርመሪያ፦ በቀን ስንት ሰዓት በስልክ ላይ ታቃጥላለህ? ይህንን ሰዓት ለሂሳብ ወይም ለእንግሊዝኛ ብትሰጠው ኖሮ አሁን የት ትደርስ ነበር?
➲ የክፍተት ትንተና (Gap Analysis)
ሁለተኛው ሴሚስተር አዲስ ቤት ለመሥራት ብቻ ሳይሆን፣ የፈረሰውን ለመጠገን ጭምር ነው። ባለፈው የከበዳችሁ ትምህርት የትኛው ነው? ያንን ሳትጠግኑ ወደ ፊት መሄድ አትችሉም። ድክመታችሁን አውቃችሁ መድፈን የብልህ ተማሪ ምልክት ነው።
➲ ወላጆች - የቤት ውስጥ መሪዎች
ውድ ወላጆች! ልጆቻችሁ የነገ ተስፋዎቻችሁ ናቸው። በዚህ ወሳኝ ሰዓት ቤታችሁ "የፊልም ቤት" ሳይሆን "የንባብና የዱዓ ቤት" መምሰል አለበት። ከቴሌቪዥን ሪሞት ይልቅ የመጽሐፍ ገጾች ይቅረቡ። ልጆቻችሁ ሲያጠኑ አበረታቷቸው፣ ሲደክሙ አበርቱአቸው። የልጆቻችሁ ውጤት የጋራ ፕሮጀክታችሁ ነው። በዱዓ እና በክትትል ከጎናቸው ቁሙ።
➲ ሶላትና ስኬት - የማይነጣጠሉ ቅንጣቶች
ከአላህ ጋር የተጣላ ሰው የትምህርት ቤት ውጤቱ ቢያምርም በህይወቱ ሰላም የለውም። ጥናታችሁን ከሶላት ጋር አጣምሩ። ሶላቱን በወቅቱ የሚሰግድ ተማሪ፣ ጊዜው በረካ ይሆንለታል። የአላህ እርዳታ (ተውፊቅ) የሚገኘው በሱጁድ ውስጥ ነው። ያለ አላህ እርዳታ የሚመጣ ውጤት የለም።
"...አላህ በሕዝቦች ዘንድ ያለን (ጸጋ) በነፍሶቻቸው ያለን (ሁኔታ) እስከሚለውጡ ድረስ አይለውጥም..." (ሱረቱ አር-ረዕድ፡ 11)
❓ የነፍስ መመርመሪያ፦ ለአላህ ሳትሰግድ ለፈተና ብቻ የምታደርገው ጥረት ፍሬ ያፈራል ብለህ ታስባለህ? ስኬትህ ከሰላትህ ጋር እንደተሳሰረ ታውቃለህ?
➲ ማጠቃለያ - ብዕሩ በእጅህ ነው!
ታሪክህ ገና አልተጻፈም፤ ብዕሩ በእጅህ ነው። ሁለተኛው ሴሚስተር ባዶ ነጭ ወረቀት ነው። በዚህ ወረቀት ላይ የውድቀት ታሪክ ትጽፋለህ ወይስ የድል አድራጊነት ዜና? ምርጫው ያንተ ነው። ተነሳ! አቧራህን አራግፍ! አንተ ከተቀየርክ ዓለም አብራህ ትቀየራለች።
በቀጣዩ ሴሚስተር በደረጃ ሰንጠረዥ አናት ላይ እንገናኝ! አላህ ጥረታችሁን ይባርክ፤ ልፋታችሁን በስኬት ያክልላችሁ (ያብቃላችሁ)! 🚀

የባንክ ሒሳብን ከፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ጋር አላጣመሩም? ጊዜው እየሄደ ስለሆነ በቀጥታ ካሉበት ሆነው ኦንላይን ያጣምሩ።
💸 እናት ባንክ:
https://kyc.enatbanksc.com/bank-account-entry
💸 የኢትዮጵያ ልማት ባንክ:
https://fayda.dbe.com.et
💸 ፀሀይ ባንክ፡
https://fayda.tsehaybank.com.et/FAYDA/home
💸 አባይ ባንክ:-
https://faydaabaybank.com.et/
💸 ንብ ባንክ:-
https://fayda.nibbank.com.et
💸 ቡና ባንክ:-
https://verifayda.bunnabanksc.com
💸 ዳሽን ባንክ:
https://dashensuperapp.com/dashen-fayda
💸 ዘመን ባንክ:
https://fayda.zemenbank.com
💸 ሒጅራ ባንክ:
https://apps.hijradigital.com/fayda/v2
💸 ሕብረት ባንክ :
https://services.hibretbank.com.et/fayda
💸 ብርሀን ባንክ:
https://nationalidharmonization.berhanonline.et:9095/fayda-login
💸 አዲስ ባንክ:
https://fayda.addisbank.com.et
💸 አቢሲኒያ ባንክ:
https://cs.bankofabyssinia.com/fayda_connect
💸 አዋሽ ባንክ :
https://fayda.awashbank.com
💸 የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ:
https://my.coopbankoromiasc.com/harmonization
💸 የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፡
https://cbefayda.cbe.com.et/
💸 ኦሮሚያ ባንክ ፡
https://obfayda.oromiabank.com/

የነገ_ሰው_አናፅያን_የKG_መምህራን_የሙያ_ስነ_ምግባርና.pdf
16.1 MB
🚀 የነገ ሰው አናፅያን፦ ከዘመን የተሻገረ፣ ትውልድን የሚቀይር የነፍስ ጥሪ!
ስላይድ ብዛት: 81
ዝግጅት: በረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል
ስላይድ ብዛት: 81
ዝግጅት: በረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል
Basic Computer Skills
የነገ_ሰው_አናፅያን_የKG_መምህራን_የሙያ_ስነ_ምግባርና.pdf
🚀 የነገ ሰው አናፅያን፦ ከዘመን የተሻገረ፣ ትውልድን የሚቀይር የነፍስ ጥሪ!
(ለወላጆች፣ ለመምህራንና ማህበረሰብን ለሚያንፁ ሁሉ የተበረከተ ድንቅ ስንቅ)
"ይህ ዝም ብሎ የንባብ ሰነድ አይደለም፤ ይህ በአላህ ፈቃድ የነገውን ዓለም የሚቀይሩ ጀግኖችን የማፍሪያ ጥበብ ነው!"
ምዕራፍ 1፦ የክብር ጥሪ - አንተ ማን ነህ? (The Awakening)
✨ "የነገው ታሪክ ዛሬ ያንተ ክፍል/ቤት ውስጥ ነው የሚጻፈው!"
ወዳጄ ሆይ! አንተ የምትሰራው ፋብሪካ ውስጥ አይደለም፤ የሰው ልብ ውስጥ ነው። ፋብሪካ ቢበላሽ "እቃ" ይበላሻል፤ አንተ ጋር ከተበላሸ ግን "ትውልድ" ይበላሻል። ጌታችን አላህ (ሱ.ወ) ለሰው ልጅ የሰጠው ትልቁ ክብር ማስተማር ነው፤ በቁርኣኑ እንዲህ ይላል፡-
"አላህም ለአደም ስሞችን ሁሉንም አስተማረው..." (አል-በቀራህ፡ 31)።
የአላህ መልክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- "አላህ፣ መላእክቱ፣ የሰማይና የምድር ነዋሪዎች፣ በጉድጓዷ ያለች ጉንዳንና በባህር ውስጥ ያለ አሳ ሳይቀሩ ለሰዎች መልካምን ነገር ለሚያስተምር ሰው ዱዓ ያደርጉለታል።" አንተ የነብያት ውርስ ተሸካሚ ነህ። አሳዎች በባህር ውስጥ ሆነው ዱዓ የሚያደርጉልህ ታላቅ ባለሙያ ነህ!
🌊 ለመሆኑ ይህን ክብር ጠብቆ ለመጓዝ የሚያስፈልገው 'የልብ ትርታ' ምንድነው? ወደ ቀጣዩ ክፍል እንለፍ...
ምዕራፍ 2፦ ስነ-ምግባር - የሙያው የልብ ትርታ
✨ "እውቀት ጌጥ ነው፤ ስነ-ምግባር ግን የሕይወት እስትንፋስ ነው!"
ትክክለኛው ማንነትህ ማለት፣ ማንም ሳያይህ የምታደርገው ነገር ነው። ኢስላም ይህንን "ኢሕሳን" ይለዋል። ታላቁ ኢማሙ ማሊክ (ረሒመሁላህ) እንዲህ ይላሉ፡- "ዕውቀትን ከመማርህ በፊት ስነ-ምግባርን (አደብን) ተማር።" ስነ-ምግባር የሌለው ዕውቀት ልክ እንደሌለው ዛፍ ነው። እናንተ የልጆች የህሊና ካሜራዎች ናችሁ፤ ልጆች የሚሰሙትን ሳይሆን፣ የሚያዩትን ነው የሚደግሙት።
ኢማሙ አል-ሻፊዒይ ደግሞ እንዲህ ይላሉ፡- "ዕውቀት ማለት የሸመደድከው ሳይሆን በተግባር የገለጽከውና የጠቀመህ ነው"። አንተ መሪ ነህ፤ መሪ ደግሞ በባህሪው ይሰብካል!
💎 ይህን ድንቅ ባህሪ ይዘህ የምታንጻቸው "ውድ እንቁዎች" እነማን ናቸው? ምዕራፍ 3 ላይ እናገኘዋለን...
ምዕራፍ 3፦ ተማሪዎቻችን - የአማና ውድ ስጦታዎች
✨ "ለአምስት ዓመት የዘራኸው ፍቅር፣ ለሃምሳ ዓመት የሚቆይ ፅናት ይፈጥራል!"
ሳይንስ እንደሚያረጋግጠው የሰው ልጅ 90% የአዕምሮ እድገት የሚጠናቀቀው እስከ 5 ዓመት ባለው ጊዜ ነው። በዚህ ወሳኝ ሰዓት እጃችሁ ላይ ያሉት ህፃናት ከአላህ የተሰጡ "አማናዎች" ናቸው። ኢማሙ አህመድ (ረሒመሁላህ) እንዳሉት፡- "ሰዎች ለዕውቀት ያላቸው ፍላጎት ከምግብና ከመጠጥ በላይ ነው።"
ልጆችን በዱላ ሳይሆን በፍቅር ቅረጹት። ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) "ልጆቻችሁ መካከል በስጦታ (በመሳምም ቢሆን) አስተካክሉ" በማለት ፍትሃዊነትን አስተምረውናል። ይህ ፍትህና ፍቅር ደግሞ በአንደበትህ በሚወጡ ቃላት ይገለጻሉ...
⚔️ ቃላትህ ሰይፍ መሆናቸውን ያውቃሉ? ወደ ምዕራፍ 4 እንዝለቅ...
ምዕራፍ 4፦ አርአያነትና የቃላት ኃይል - የኤድሰን ምስጢር
✨ "አንደበታችሁ ወይ የትውልድ ብርሃን ወይ የነፍስ ጨለማ ይፈጥራል!"
ቶማስ ኤድሰን በትምህርት ቤቱ "ዘገምተኛ" ተብሎ ሲባረር፣ እናቱ ግን ደብዳቤውን ቀይራ "አንተ በጣም ብልህ ስለሆንክ ትምህርት ቤቱ አይመጥንህም" አለችው። ያቺ መልካም ቃል ዓለምን በኤሌክትሪክ ያበራ ታላቅ ሰው ፈጠረች።
ሸይኽ ኢብኑ ኡሰይሚን እንዲህ ይላሉ፡- "አስተማሪነት ማለት በተማሪዎችህ ልብ ውስጥ ፍቅርን መትከል ነው።" አላህ እንዲህ ይላል፡-
"መልካም ቃል ልክ እንደ መልካም ዛፍ ናት፤ ስሯ የጠነከረ ቅርንጫፎቿም ወደ ሰማይ የረዘሙ..." (ኢብራሂም፡ 24)። ዛሬ የምትናገረው ቃል የነገውን አገር ሰሪ ይተክላል!
🤝 ይህን ትልቅ ኃላፊነት ግን ብቻህን አትሸከመውም!
ምዕራፍ 5 አጋርህን ያስተዋውቅሃል...
ምዕራፍ 5፦ አብሮነት - ድልድይ መሆን
✨ "ትውልድ የሚገነባው በመምህር፣ በወላጅና በማህበረሰብ ህብረት ነው!"
መማር ማስተማር የአንድ ወገን ሩጫ አይደለም። ኢብኑል ቀይም እንደሚሉት፡- "ልጅን ማሳደግ ልክ እንደ መስታወት ነው፤ የሰጠኸውን ምስል መልሶ ያሳይሃል"። መምህርና ወላጅ በአንድ ልብ ካልቆሙ ትውልዱ ይሰነጠቃል። ማህበረሰቡ እናንተን ሲያከብር ሙያችሁን ያከብራል።
📈 ይህንን ድልድይ ለመገንባት ግን ያንተ "ብቃት" የት ላይ ነው? ምዕራፍ 6 ይገርምሃል...
ምዕራፍ 6፦ የላቀ ብቃትና ፅናት (Growth)
✨ "ለዘጠኝ ሴኮንድ ስኬት፣ ዘጠኝ ዓመት በትዕግስት መዝራት ግድ ነው!"
ሸይኩል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያህ እንዲህ ይላሉ፡- "ትዕግስት (ሶብር) ለዕውቀት ልክ እንደ ጭንቅላት ለሰውነት ነው።"
የዓለማችን ፈጣኑ ሯጭ ዩሴይን ቦልት እንዲህ ይላል፡-
"እኔ ለዘጠኝ (9) ሴኮንድ ውድድር፣ ለዘጠኝ (9) ዓመታት ሰልጥኛለሁ። አንዳንድ ሰዎች ግን በሁለት ወር ውስጥ ለውጥ ካላዩ ተስፋ ይቆርጣሉ!!"።
ልጅን መቅረጽ የ9 ሴኮንድ ስራ አይደለም። ዛሬ የዘራኸው ነገ ላይበቅል ይችላል፤ ግን መዝራትህን አታቁም! ፍሬው የትውልድ ስኬት ነው። ይህ ስኬት ደግሞ ከዘመኑ ጋር መራመድን ይፈልጋል...
💻 ዘመኑን የማይቀድም መምህር፣ ትውልድን መምራት ይችላል? ምዕራፍ 7 መልሱን ይዟል...
ምዕራፍ 7፦ መምህሩና ቴክኖሎጂ (The Modern Teacher)
"በድንጋይ ዘመን አስተሳሰብ፣ የዲጂታሉን ትውልድ መቅረጽ አይቻልም!"
በ21ኛው ክፍለ ዘመን እየኖርን፣ በ20ኛው ክፍለ ዘመን አስተሳሰብ መጓዝ አይቻልም። ቴክኖሎጂ ስራችሁን ያቀላል እንጂ አይተካችሁም። ራሳችሁን አዘምኑ። ዛሬ መምህሩ ኦንላይን በመስራት፣ በZoom በማስተማርና እውቀቱን በማጋራት ገቢውንም እውቀቱንም ማሳደግ ይችላል።
"ሰነፍን አላህም ሰውም አይወደውም! እውቀታችሁን ሽጡት፤ የህፃናት መጽሐፍ ጻፉ"። ዘመኑ የብዙ አማራጮች ነው። ይህ ሁሉ ልፋት መጨረሻው ምን ይሆን?
🌈 የመጨረሻው ግብና የነፍስ እርካታ... ምዕራፍ 8 ላይ!
ምዕራፍ 8፦ የነገው ብሩህ ህይወታችን (Life Mastery)
✨ "ዛሬ የምትዘራው ኸይር፣ ነገ በጀነት ውስጥ ጥላ ይሆንሃል!"
አንድ ቀን ይህን አለም ትሰናበታላችሁ። ያኔ ምንድነው የሚቀረው? ገንዘብ? ህንፃ? አይደለም! የሚቀረው እናንተ የቀረጻችሁት የሰው አዕምሮ እና ንጹህ ልብ ነው። ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) "ሰው ሲሞት ስራው ይቋረጣል፤ ከሶስት ነገሮች በስተቀር" አሉና አንዱ "ለእርሱ ዱዓ የሚያደርግለት መልካም ልጅ" መሆኑን ጠቅሰዋል። ዛሬ የምትቀርጹት ልጅ ነገ ዶክተር ሆኖ ሰውን ሲያድን፣ እናንተም አብራችሁ እያዳናችሁ ነው።
🌟 መደምደሚያ፦ የጥበብ ማጠቃለያ
✨ "ዕውቀት፦ የመንፈስ ዝናብ፣ የተግባር ምንጭ!"
"እውቀት እንደ ውሃ ነው፤ ካልፈሰሰ ይሸታል። አነበብን ብቻ ሳይሆን ተገበርን የምንባል ያድርገን!" ይህ ሰነድ በውስጣችሁ እንዲፈስ ፍቀዱለት። ካልተገበረ ዕውቀት የተገበረች አንዲት ጠብታ ትበልጣለች።
🏔️ Mumtaz Academy፦ የልህቀት ማማ፣ የትውልድ ቀራጭ!
✨ "የላቀ እውቀት ለላቀ ትውልድ!"