Basic Computer Skills
1.85K subscribers
1.22K photos
100 videos
575 files
833 links
#በዚህ የቴሌግራም ቻናል
↪️ Programming
↪️ ቴክኖሎጂ ነክ ትምህርቶችን
↪️ ኮምፒውተር ነክ ትምህርቶችን
↪️Basic Computer Skills
↪️ Software
↪️ AI and AI Skills (Like ChatGPT)

ከላይ የተዘረዘሩትና ሌሎችም ገራሚ ትምህርቶች ይለቀቅበታል!

t.me/BasicComputerSkillsGroup

𝘽𝙮 𝙍𝙚𝙨𝙝𝙖𝙙
Download Telegram
Grade 8 1st Sem. ICT and CTE Test 2 Table of Specifications.pdf
189.4 KB
📚 2018 E.C Grade 8 ICT and CTE 
የሙከራ ሁለት የፈተና ቢጋር (Table of Specification for Test 2)



 በተለይም የሙምታዝ ት/ቤት ተማሪዎች Test 2 የተዘጋጀው በዚህ መሠረት ስለሆነ ተጠቀሙበት።

አላህ ይርዳችሁ!!

✍️ ረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል
ከውድቀት_ወደ_ማማ፡_የሙምታዝ_ተማሪዎች_የታሪክ_አዲስ_ምዕራፍ.pdf
14.4 MB
☑️ ለሙምታዝ ትምህርት ቤት ለ7 ክፍል ተማሪዎች የተሰጠ ስልጠና


📚 ርዕስ፡ ከውድቀት ወደ ማማ! - የታሪክ አዲስ ምዕራፍ 🔥


ስላይድ ብዛት: 60 ስላይድ

ስልጠና: በረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል


በስልጠናው ሁሉም እንዲጠቀምበት ታስቦ የተጋራ።
🔥 ከውድቀት ወደ ማማ! - የታሪክ አዲስ ምዕራፍ 🔥
════════════════

ዛሬ በሙምታዝ አካዳሚ ከ7ኛ ክፍል ተማሪዎች ጋር በነበረን ቆይታ፤ በእያንዳንዱ ተማሪ ልብ ውስጥ የህሊና ደወል የሚሆን፣ የተኙትን የሚያነቃ፣ የጠፉትን የሚመልስና አቅጣጫን የሚያስተካክል እውነት ላይ ተወያይተናል። ይህ አብሮ ያያያዝነው የሥልጠና ሰነድ (PDF) ትውልድ ከተቀበለውና ከተገበረው ወደ ታላቅነት ማማ የሚወጣበትን የለውጥ እርምጃዎች ይዟል።

📜 የለውጥ ምዕራፎች

1️⃣ ምዕራፍ 1፡ መስተዋቱ (የነበርንበትና የደረስንበት)
ዛሬ በመስታወት ፊት ቁመን ራሳችንን የምንመረምርበት ቀን ነው። በ2017 የነበረው ትህትና፣ የመማር ጥማትና መከባበር በ2018 ለምን በረብሻና በዝንጋቴ ተተካ? ጌታችን አላህ በተከበረ ቃሉ እንዲህ ይላል፦
"አላህ በሰዎች ዘንድ ያለን (ጸጋ) በነፍሶቻቸው ያለን (ሁኔታ) እስከሚለውጡ ድረስ አይለውጥም።" (ሱረቱ አር-ረዕድ፡ 11)
የዛሬው ወጣት የነገው የኡማው ዋልታ ነው። ዋልታው ከበሰበሰ ቤቱ ይፈርሳል። "አድጌያለሁ፣ ማንም አይነካኝም" የሚል የውሸት ጀግንነት የውድቀት መጀመሪያ መሆኑን ተረድተን ወደ ቀድሞው ወርቃማ ማንነታችን የምንመለስበት ሰዓት አሁን ነው።

2️⃣ ምዕራፍ 2፡ ተማሪነት ከአላህ የተሰጠ ኒዕማ (የፍልስጤም ትምህርት)
ዛሬ እናንተ በሰላም አየር ስር ሆናችሁ፣ ወላጆቻችሁ መጽሐፍና ደብተር አሟልተውላችሁ፣ መምህራን ሊያስተምሯችሁ ቆመው እያለ ጊዜያችሁን ስታባክኑ፤ በሌላው ዓለም በተለይም በጋዛና በፍልስጤም የሚገኙ እኩዮቻችሁን አስቧቸው። እነሱ ትምህርት ቤታቸው በቦምብ ፈርሶ፣ መጽሐፎቻቸው በደም ተለውሰው፣ መምህራኖቻቸው ተሰውተውም እንኳ በድንኳንና በፍርስራሽ መካከል ሆነው እውቀትን ይፈልጋሉ።
እናንተ የተመቻቸላችሁን እድል ስታባክኑ በደምና በእንባ መማር የናፈቃቸውን ትውልዶች እየበደላችሁ ነው። አላህ የሰጣችሁን ይህን የዕውቀት ብርሃን ሸክም ሳይሆን፣ መላእክት ክንፋቸውን የሚያነጥፉለት ልዩ ስጦታ መሆኑን እወቁ። ይህን ጸጋ ማባከን በፈጣሪ ፊት በከፍተኛ ወንጀል ያስጠይቃል።

3️⃣ ምዕራፍ 3፡ አደብ (ስነ-ምግባር) - የእውቀት በር
"እውቀት ሞተር ነው፤ አደብ ደግሞ ብሬክ ነው።" ብሬክ የሌለው መኪና መጨረሻው ገደል እንደሆነ ሁሉ፣ አደብ የሌለው ተማሪም መጨረሻው ጥፋት ነው።
ታላቁ ሊቅ ኢማሙ ማሊክ (ረሂመሁላህ) እንዲህ ይላሉ፡- "ዕውቀትን ከመፈለግህ በፊት አደብን ተማር።" አደብ (ስነ-ምግባር) የሌለው ተማሪ ምንም ቢማር ፍሬ የለውም። መምህርን የሚያላግጥና የሚያቃልል ተማሪ የወደፊቱን ህይወቱን እያጨለመ ነው። በመምህራን ዱዓ እንጂ በቁጣቸው አትታጀቡ።

4️⃣ ምዕራፍ 4፡ የዘመኑ ፈተና (ዲጂታል እስር ቤት)
ስልካችን ውስጥ ያለው ቴሌግራም ጊዜያችንን የሚበላ "የኪስ ውስጥ እስር ቤት" ሊሆንብን አይገባም። በቴሌግራም ግሩፖች የምትጽፉት ስብዕና የጎደለው መልዕክት ነገ ይመሰክርባችኋል። ኢማሙ ሻፊዒ እንዳሉት፡- "ጊዜ ሰይፍ ነው፤ ካልቆረጥከው ይቆርጥሃል።" ዛሬ በከንቱ ወሬ የምታሳልፉት ሰዓት ነገ በፀፀት እሳት ያቃጥላችኋል። "ከመጥፎ ጓደኛ ብቸኝነት ይሻላል"ና የማንነት ሌባ ከሆኑ ጓደኞች ራሳችሁን አርቁ።

5️⃣ ምዕራፍ 5፡ የክብር አርማ (ለሴት ተማሪዎች)
ሂጃብ የአላህ ትዕዛዝ እንጂ የሰው ውሳኔ አይደለም። "አንተ ነቢዩ ሆይ! ለሚስቶቻችሁ፣ ለሴቶች ልጆችህም፣ ለምእምናን ሚስቶችም ከመከናነቢያዎቻቸው በላያቸው ላይ እንዲለቁ ንገራቸው..." (ሱረቱ አል-አህዛብ፡ 59)
ውድ እህታችን! አንቺ የነገዋ የኡማው እናት ነሽ። ሂጃብሽ ውበትሽና አላህ የሰጠሽ ንግስትነትሽ ነው። አርአያሽ እናታችን አይሻ (ረ.ዐ) ትሁን፤ ያለ ቀን ከእስልምና ያፈነገጠ አለባበስ ማንነትን መካድ ነው።

6️⃣ ምዕራፍ 6፡ የታላላቆች አርአያነት
የዛሬዎቹ የዓለማችን ታላላቅ ሊቃውንት እዚህ የደረሱት በተመቸ ህይወት አይደለም። ኢማሙ ቡኻሪ ለአንድ ሀዲስ ብቻ ወራትን በእግር ይጓዙ ነበር። ኢማሙ አህመድ ለእውቀት ሲሉ ግርፋትንና እስርን ታግሰዋል። ስኬት ያለ መስዋዕትነት አይገኝም። ሸይኩል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያህ እንዲህ ይላሉ፡- "ጠላቶቼ ምን ሊያደርጉኝ ይችላሉ? ጀነቴና አፀዴ በልቤ ውስጥ ናቸው፤ ቢገድሉኝ ሸህዳዬ ነው፣ ቢያስሩኝ ከጌታዬ ጋር የምገለልበት (ኸልዋ) ነው፣ ከአገሬ ቢያባርሩኝ ቱሪዝም (ሲያሃ) ነው።" ይህ ነው የዕውቀት ጥንካሬ!

7️⃣ ምዕራፍ 7፡ የመጸጸት ዋጋ (የመጨረሻው ማስጠንቀቂያ)
ዛሬ በትምህርት ማሾፍ፣ ነገ በህይወት መላገጥ ነው። ጊዜው ካለፈ በኋላ "ምነው በሰራሁ" ማለት ለቅሶ እንጂ መፍትሄ አይሆንም። አላህ በቁርአኑ እንዲህ ያስጠነቅቃል፦
"በደለኛ ሰው (በፀፀት) እጆቹን የሚነክስበትን ቀን (አስታውስ)፤ እንዲህም ይላል፡ 'ዋ ምኞቴ! ከመልዕክተኛው ጋር መንገድን በያዝኩ ኖሮ!'" (ሱረቱ አል-ፉርቃን፡ 27)
ዛሬ በስነ-ምግባር ብልሹነት ከትምህርት ቤት መሰናበት በህይወት ዘመን የማይሻር ጠባሳ ይጥላል። ሳይረፍድ ንቁ!

8️⃣ ምዕራፍ 8፡ አዲሱ ውሳኔና ቃልኪዳን
ያለፈው ስህተት ለወደፊቱ ትምህርት ይሁን። አላህ ወደ እርሱ ለሚመለሱ ሩህሩህ ነው። ዛሬ አዲስ ምዕራፍ የምንጀምርበት ቀን ነው። ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- "ከኃጢአቱ የተመለሰ (ተውበት ያደረገ) ሰው ልክ ኃጢአት እንደሌለው ሰው ነው።" (ኢብኑ ማጃህ ዘግበውታል)
በክፍል ውስጥ ጸጥታን በመጠበቅ፣ መምህርን በማክበርና የቤት ስራን በወቅቱ በመስራት ለራሳችን ቃል እንገባለን። "ለውጥ ከእኔ ይጀምራል!" ብለን እንነሳለን።

9️⃣ ምዕራፍ 9፡ የልብ መሳመሪያ (ዱዓ)
በመጨረሻም ይህ ሁሉ ጥረታችን በአላህ እርዳታ ይከናወን ዘንድ እጃችንን ዘርግተናል፡-
"ያ አላህ! በእነዚህ ተማሪዎች ልብ ውስጥ የእውቀትን ብርሃን አንግስ። ከቴክኖሎጂ ወጥመድና ከመጥፎ ጓደኛ ጠብቃቸው። ሴት እህቶቻችንን የክብር ባለቤት፣ ወንድ ልጆቻችንን የዲን ጋሻና የቤተሰብ መከታ አድርጋቸው። ዛሬ በዱዓ እንደሰበሰብከን ሁሉ ነገ በጀነት ይሰብስበን። አሚን!"


የምስጋና መዝጊያ:
ይህ ሥልጠና እውን እንዲሆንና ልጆቻችን የለውጥ ብርሃን እንዲያዩ ሁኔታዎችን ሁሉ በማመቻቸት ለደከሙት ለሙምታዝ አካዳሚ ዳይሬክተር ሚስተር ሙሐመድ ይማም የላቀ ምስጋናዬን አቀርባለሁ። እንዲሁም ለትምህርት ቤቱ አስተዳደር ሰራተኞች፣ ለሙሉ መምህራንና ለትምህርት ቤቱ ማህበረሰብ በሙሉ ለነበራችሁ ያልተቆጠበ ድጋፍና ለሥልጠናው መሳካት ላደረጋችሁት አስተዋጽኦ አላህ ጀዛችሁን ይክፈላችሁ። በኸይር ሥራችሁ ላይ ጽናቱን ይስጣችሁ።

ለለውጥ የተዘጋጃችሁና ቃል የገባችሁ የሙምታዝ የ7ኛ ክፍል ተማሪዎች... እናንተ የነገ የኡማው ኩራት ናችሁ!

🚀 ሙምታዝ፡ እውቀትን ከአደብ ጋር!

📚 በረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል

════════════════
⭕️ በስልጠናው ሁሉም ተማሪ እንዲጠቀምበት በሚል የተለጠፈ።

👇 የስልጠናውን ሙሉ ሰነድ (PDF) እዚህ ያውርዱ: 👇
👇 👇 👇

t.me/BasicComputer_Skills/2964
4
Truecaller v16.3.5 (Premium).apk
95.1 MB
Truecaller v16.3.5 (Premium).apk
👍2
Basic Computer Skills
Photo
የወደፊቱ የአለማችን የኢንተርኔት አብዮት Starlink ምንድን ነው?

Starlink በኤለን መስክ ድርጅት SpaceX የተመሰረተ የሳተላይት ኢንተርኔት project ነው።
የዚህ ፕሮጀክት ተቀዳሚ ተልዕኮው በዓለም ዙሪያ ላሉ የኢንተርኔት አገልግሎት ለማያገኙ ገጠራማና ሩቅ የአለም ክፍሎች ከፍተኛ ፍጥነት ያለው የኢንተርኔት አገልግሎት እንዲያገኙ ማድረግ ነው።

ብዙ ቁጥር ያላቸው Low Earth Orbit (LEO) ሳተላይቶችን በጋራ በማሰማራት የፋይበር ኦፕቲክና የሞባይል ኔትዎርክ ግንኙነት የማያገኙ አካባቢዎችን አስተማማኝና ፈጣን የኢንተርኔት አገልግሎቶችን ለማቅረብ አልሞ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል።

ዋና ዋና ባህሪያቶች
Global Coverage: የስታርሊንክ የሳተላይት ኢንተርኔት መላው ፕላኔት የሚሸፍን ሲሆን ይህም ቀደም ሲል የኢንተርኔት ግንኙነት የማያገኙ የአለማችን ክልሎችን ተደራሽ ያደርጋል።

High-Speed Internet: ስታርሊንክ ከባህላዊ የኢንተርኔት አገልግሎት አቅራቢዎች ጋር የሚወዳደር የብሮድባንድ ፍጥነትን የሚያቀርብ ሲሆን Online Gaming, Video Conferencingና የመሳሰሉ real-time online ስራዎችን በጥሩ ፍጥነት መከወን ያስችላል።

Easy Installation:
StarLink ለመጠቀም በጣም ቀላል የሆነችና በቀላሉ ከታ ቦታ ማንቀሳቀስ የምትቻል Dish ሲኖረው ማንኛውም ቦታ ላይ በማስቀመጥ እራሷን ከሳተላይት ጋር ማስተካከል ትችላለች። ከዚህ በተጨማሪ LTE connection ላላቸው የሞባይል ቀፎዎች የፅሁፍና የድምጽ መልዕክት እንዲሁም የኢንተርኔት አገልግሎት ያገኛሉ ተብሏል።

Constant Updates: ስታርሊንክ ተጨማሪ ሳተላይቶችን በማምጠቅ እና ሶፍትዌሩን በማዘመን ኔትወርኩን በየጊዜው እያሰፋ እና እያሻሻለ ይገኛል። አገልግሎቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ ብዙ የአለም ክፍሎችን እያካለለ ነው።

Disaster Response: አሁን የምንጠቀምባቸውን የኢንተርኔት አቅራቢ ድርጅቶችን infrastructure በተለያዩ ተፈጥሯዊና ሰው ሰራሽ አደጋዎች ቢወድሙ communication ይቋረጣል። የስታርሊንክ ሳተላይት ከዚህ ነገር ነጻ ሲሆኑ ለድንገተኛ አገልግሎቶች እና እርዳታ የሚፈልጉ የተጎዱ ሰዎችን በቀላሉ ማግኘት ያስችላል።

በአሁኑ ሰአት በተወሰኑ የአለማችን ሃገራት ስራ የጀመረው StarLink ከአፍሪካ ሃገራት ናይጀርያ፣ ጋና፣ ሴራሊዮን፣ ማላዊ፣ ዛምብያ፣ ቦቶስዋና፣ ማዳጋስካር፣ ሩዋንዳ፣ ኬንያና ደቡብ ሱዳን የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ናቸው።

ይህን አገልግሎት ለመጠቀም ክፍያው ያን ያክል ውድ የሚባል አይደለም። ከሃገራት ሃገራት ልዩነት ቢኖረውም ለግለሰብ unlimited high-speed ዳታ ለመጠቀም በወር 120 ዶላር መክፈል ይጠይቃል። ለBusiness plan ደግሞ በወር ከ140 እስከ 5000 ዶላር ድረስ ያስከፍላል።

ጎረቤቶቻችን ኬንያና ሶማልያ የstarlink service ካላቸው ሃገሮች መካከል ናቸው።

✍️ በሀገራችን በተለይ በገጠሪቱ የሀገራችን ክፍል ብዙ ሰው የኢንተርኔት አገልግሎት አያገኝም። ይህ ነገር በሃገራችን ቢጀመር ብዙ ሰው የሚጠቀም ይመስላችኋል? ሀሳባችሁን አካፍሉን።

©️ bighabesha

════════════════
📍 ለተጨማሪ የቴክኖሎጂ ምክሮች ቻናሉን ይቀላቀሉ

🌐 ዘመኑ #የቴክኖሎጂ ነው 📲 ከዘመኑ ጋር አብረው ይዘምኑ💻

Telegram: t.me/BasicComputer_Skills

Tiktok:
tiktok.com/@basiccomputerskills

Instagram:
instagram.com/basiccomputerskills

Umma Life:
ummalife.com/ReshadMuzemil
👍31
Belkin የተሰኘ የቴክኖሎጂ ድርጅት Wireless HDMI አስተዋወቀ።

በLas Vegas ከተማ እየተካሄደ ባለው አመታዊው የCES(Consumer electronics show) ፕሮግራም ላይ የቀረበው ይህ wireless HDMI ላፕቶፕ፣ ታብሌት ወይም ስማርትፎን ወደ ሌላ ስክሪን ያለ Wi-Fi ወይም Bluetooth ማጋራት የሚያስችል plug-and-play casting system አስተዋውቋል።

ይስ ሲስተም USB-C ዶንግል transmitterና USB-A to HDMI receiver የያዘ ሲሆን ዶንግሉን ስክሪኑን share ማድረግ የፈለግነው device ላይ ሰክተን USB-A to HDMI ሪሲቨሩን ደግሞ ቲቪ፣ ሞኒተር ወይም ፕሮጀክተር ላይ በመሰካት ያለምንም ችግር screen share ማድረግ ያስችለናል።

ሲስተሙን ለመጠቀም ምንም አይነት ዋይፋይ፣ ብሉቱዝ፣ አፕሊኬሽን ወይም ድራይቨር መጫን ሳያስፈልግ በ40 ሜትር ክልል ውስጥ ይሰራል ተብሏል። በተጨማሪም እስከ 1080P በ60Hzና ከ80ms ባነሰ latency እንደሚያስተላልፍ ተገልጿል።
ይህ ቴክኖሎጂ የ150 ዶላር ዋጋ የተለጠፈበት ሲሆን በሚቀጥለው አመት ለገበያ ይቀርባል ተብሎ ይጠበቃል።

©️bighabesha
3
#safety

ስልካችሁ ላይ እናንተም ሆናችሁ ታዳጊ እህት ወንድሞቻችሁ ወይም ልጆቻችሁ explicit የሆኑ ዌብሳይቶችን እንዳይከፍቱ በዚህ መሰረት መዝጋት ትችላላችሁ።

1. አጠቃላይ ስልካችሁ ላይ
የስልካችሁ settings ላይ ትገቡና connections የሚለውን ትመርጣላችሁ።
ከዛ more connection settings የሚል አማራጭ ታገኛላችሁ።
private DNS የሚለውን ከፍታችሁ Private DNS provider hostname ውስጥ Adult-filter-dns.cleanbrowsing.org ወይም family.adguard-dns.com የሚሉትን አማራጮች ሞልታችሁ Save አድርጉት።

2. Chrome Browser ላይ
በመጀመሪያ google chrome browser ከከፈታችሁ በኋላ ሶስት ነጥብጣቡን ነክታችሁ ወደ setting ውስጥ ግቡ።
Privacy and security የሚለውን ምረጡ።
በመቀጠል ትንሽ scroll እንዳደረጋችሁ የምታገኙትን "use secure DNS" የሚለውን ምረጡ።
"use your current service provider" የሚል በdefault ተመርጦ የምታገኙ ሲሆን እኛም ከታች ያለውን "choose another provider" የሚለውን እንመርጣለን።
በመጨረሻም ከስር የሚመጣልንን "custom" የሚለውን ነክተን "clean browsing (family filter)" የሚለውን መምረጥ።

ከዚህ በኋላ ምንም አይነት adult content በየትኛውም browser ላይ አይመጣም።

©️ bighabesha
Basic Computer Skills
Photo
ወደ ስኬት ማማ የሚወስደው ወርቃማው ድልድይ! (የሞዴል ፈተና ሚስጥር)
════════════════

አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱህ!


📚 ውድ የዕውቀት ፈላጊዎች፣ የነገ ሀገር ተስፋዎችና የዚህ ዘመን የለውጥ ፀሐዮች!
ይህ መልዕክት ለዛሬ ወይም ለነገ ብቻ ሳይሆን፣ የሰው ልጅ በትምህርትና በእውቀት ጎዳና ላይ እስካለ ድረስ ዘወትር የሚሰራ እውነተኛ የህይወት ስንቅ ነው። ልባችሁን ሰፋ አድርጋችሁ፣ እንደ ውሃ የሚወርደውን ይህን ሀሳብ አጣጥሙት። (አንባቢዎች ሆይ አላህ ይርዳችሁ 🤲)

1. ራስን የመመልከቻው "እውነተኛው መስታወት"
ብዙ ተማሪዎች የሚሰናከሉት ባለማወቃቸው ሳይሆን፣ "አውቃለሁ" በሚል ስሜት ውስጥ ስለሚዘናጉ ነው። ሞዴል ፈተና ማለት የውሸት ካባችሁን አውልቆ፣ ትክክለኛውን የእውቀት ደረጃችሁን የሚያሳይ ጥርት ያለ መስታወት ነው።
◆ የድክመት ካርታ፡ ሞዴል ፈተና ማለት የትኛው የእውቀት ክምችትህ ላይ ክፍተት እንዳለ የሚጠቁም ጠቋሚ መሳሪያ (Compass) ነው። ክፍተቱ ሳይንስ ላይ ነው? ወይስ ቋንቋ ላይ? ፈተናው ሳይነግርህ በፊት በሞዴል ፈተና እራስህን መገምገም ትልቁ ጥበብ ነው።

2. የስነ-ልቦናው "ሰላምና እርጋታ" (Peace of Mind)
ፈተና ማለት እውቀት ብቻ አይደለም፤ ፈተና ማለት የስነ-ልቦና ዝግጅትም ነው። ብዙ ተማሪዎች ጎበዝ ናቸው፤ ነገር ግን የፈተና ክፍል ሲገቡ ይርበተበታሉ።
◆ ድንጋጤን ማራቅ፡ ሞዴል ፈተናን በተደጋጋሚ መውሰድ ማለት፣ አዕምሮን ከ"አዲስ ነገር" ድንጋጤ ማላቀቅ ነው። ልክ ዋናተኛ ውሃ ውስጥ ከመግባቱ በፊት ሰውነቱን እንደሚያላምደው፣ እናንተም የፈተና ወረቀት ሲሰጣችሁ ልባችሁ በተረጋጋና በሰከነ ሁኔታ እንዲመታ ያደርጋል።

3. ጊዜን የመግራት ጥበብ
ሰዓቱ ሲሮጥ ማየት ያስጨንቃል። ሞዴል ፈተና ግን ከሰዓቱ ጋር አብሮ መጓዝን ያስተምራችኋል። አንድን ጥያቄ ለመመለስ ስንት ደቂቃ እንደሚያስፈልግህ በደመ-ነፍስ (Instinctively) እንድታውቅ ያደርግሃል።
◆ ጊዜ እንደ ወርቅ ነው፡ በአግባቡ ካልተጠቀምንበት ይባክናል። ጊዜን መግደል አይቻልም፤ ጊዜው እራሱ እኛን ይገድለናልና። ሞዴል ፈተና ይህንን ውድ ጊዜ እንዴት በብልሃት እንደምትጠቀሙበት ያስተምራችኋል።

4. አዕምሮን ማጎልበትና ማነቃቃት
አንድ ስፖርተኛ ለውድድር ከመቅረቡ በፊት ሰውነቱን ያሟሙቃል። ለምን? ብቁ ለመሆን! እናንተስ?
◆ የማስታወስ አቅም፡ ሞዴል ፈተና ስትሰሩ፣ አዕምሮአችሁ በመጋዘኑ ውስጥ ያስቀመጠውን መረጃ በፍጥነት ፈልጎ የማውጣት ልምምድ ያደርጋል። መጽሐፍን ደጋግሞ ከማንበብ ይልቅ፣ እራስን መፈተን የማስታወስ ችሎታንና የመረዳት አቅምን በከፍተኛ ሁኔታ ይጨምራል።

5. በራስ መተማመን እና የድል መንፈስ
አንድን ተራራ ከመውጣትህ በፊት፣ የመንገዱን ካርታ የሚያውቅ ሰው ልበ-ሙሉነቱ ልዩ ነው።
◆ የአሸናፊነት ስሜት፡ በሞዴል ፈተና ጥሩ ውጤት ስታመጡ፣ ውስጣችሁ "እችለዋለሁ!" የሚል ኃይለኛ ማንነት ይገነባል። ይህ ማንነት በዋናው ፈተና ቀን እንደ ጋሻ ሆኖ ከጭንቀት ይጠብቃችኋል።
◆ መረጋጋት (ሰኪና)፡ በደንብ የተዘጋጀ ተማሪ አይጣደፍም። እርጋታው እራሱ ለሌሎች ተማሪዎች ያስቀናል። ይህ እርጋታ የሚመጣው ከቅድመ-ዝግጅት ነው።

🔥 የልብ መልዕክት
ሞዴል ፈተናን እንደ "ሸክም" አትዩት። እንደ "ወርቃማ እድል" ቁጠሩት። ዛሬ ላይ ተሳሳቱ፣ ዛሬ ላይ ተደናገጡ፣ ዛሬ ላይ ጊዜ ይለቅባችሁ። ምክንያቱም ዛሬ ማረም ይቻላል! በዋናው ፈተና ቀን ግን ስህተትን ማረም አይቻልም፤ የሚቻለው ውጤትን መቀበል ብቻ ነው።
ይህንን እድል ተጠቅማችሁ፣ እራሳችሁን አብቅታችሁ፣ ድክመታችሁን አርማችሁ ለድል ብቁ እንድትሆኑ አደራ። ትምህርት የኢባዳ (የአምልኮ) አካል ነው፤ ጠንክሮ መማር ደግሞ "ኢህሳን" (ምርጥ ስራ) ነው።

🤲 ዱዓ
ያ የዓለማት ጌታ የሆነው አላህ ሆይ! ይህንን ለወገኖቻቸው፣ ለሀገራቸውና ለራሳቸው ብለው ሌት ተቀን የሚደክሙ ተማሪዎችን ልፋት አንተ ባርክላቸው።
ጌታዬ ሆይ! በፈተና ሰዓት የመረጋጋትን መንፈስ አውርድላቸው። የረሱትን አስታውሳቸው፣ የከበዳቸውን አቅልላቸው። እውቀታቸው በወረቀት ላይ ብቻ ሳይሆን በህይወታቸውም ላይ ብርሃን ሆኖ እንዲፈነጥቅ አድርግላቸው።
ለወላጆቻቸው የዓይን ማረፊያ፣ ለሀገራቸው የጀርባ አጥንት፣ ለዲናቸውም ጋሻና መከታ አድርገህ ያማረ ውጤትን ወፍቃቸው። አሚን! 🤲

📖 ማጠቃለያ (መለኮታዊ ቃል)
ንግግሬን የምዘጋው ሁሉን በሚያውቀው ጌታችን በአላህ ቃል ነው። የሰው ልጅ የሚለፋው ለራሱ ነው፤ ውጤቱንም የሚያገኘው እንደ ልፋቱ ልክ ነው።

"ለሰውም ሁሉ የሠራው እንጂ ሌላ የለውም። ሥራውም ወደ ፊት (በቂያማ ቀን) በእርግጥ ይታያል። ከዚያም ሙሉውን ዋጋ ይመነዳል።"
(ሱረቱ አን-ነጅም፡ 39-41)

በልበ ሙሉነት ተዘጋጁ! የስኬት ማማ እጃችሁ ላይ ነው!

✍️ በረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል
2
Grade_7_ICT_&_CTE_T_1st_Sem_Final_Exam_Table_of_Specifications.pdf
217 KB
📚 2018 E.C Grade 7 ICT and CTE 
የማጠቃለያ ፈተና የፈተና ቢጋር (Table of Specification for Final Exam)



 በተለይም የሙምታዝ ት/ቤት ተማሪዎች Final Exam ያዘጋጀሁላችሁ በዚህ መሠረት ስለሆነ ተጠቀሙበት።

አላህ ይርዳችሁ!!

✍️ ረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል
3
Grade_8_ICT_and_CTE_1st_Sem_Final_Exam_Table_of_Specifications.pdf
226.6 KB
📚 2018 E.C Grade 8 ICT and CTE 
የማጠቃለያ ፈተና የፈተና ቢጋር (Table of Specification for Final Exam)



 በተለይም የሙምታዝ ት/ቤት ተማሪዎች Final Exam ያዘጋጀሁላችሁ በዚህ መሠረት ስለሆነ ተጠቀሙበት።

አላህ ይርዳችሁ!!

✍️ ረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል
ከጀማሪ እስከ አድቫንስድ ሁሉም ሊያውቃቸው የሚገቡ የWindows shortcuts.

1. Basic & Everyday Shortcuts (Must-Know)
Ctrl + C = Copy
Ctrl + V = Paste
Ctrl + X = Cut
Ctrl + Z = Undo
Ctrl + Y = Redo
Ctrl + A = Select all
Ctrl + S = Save
Ctrl + P = Print
Ctrl + F = Find / Search
Ctrl + N = New window / document

2. Window & App Control (Power User)
Alt + Tab = Switch between open apps
Alt + F4 = Close current app
Ctrl + Shift + Esc = Open Task Manager
Windows + D = Show / hide desktop
Windows + L = Lock your PC
Windows + E = Open File Explorer
Windows + I = Open Settings

3. File Explorer Shortcuts
Ctrl + Shift + N = New folder
Delete Delete file (Recycle Bin)
Shift + Delete Delete permanently
Alt + Enter = File properties
F2 Rename file
Ctrl + Mouse scroll = Zoom icons

4. Screenshot & Recording Shortcuts.
PrtSc = Screenshot (clipboard)
Alt + PrtSc = Screenshot active window
Windows + PrtSc = Save screenshot automatically
Windows + Shift + S = Snipping Tool (best)
Windows + Alt + R = Screen recording (Xbox Bar)

5. Browser Shortcuts (Chrome, Edge, Firefox)
Ctrl + T = New tab
Ctrl + W = Close tab
Ctrl + Shift + T = Reopen closed tab
Ctrl + Tab = Next tab
Ctrl + L = Focus address bar
Ctrl + + / - = Zoom in / out

6. Text Editing Shortcuts
Ctrl + Backspace = Delete whole word
Shift + Arrow keys = Select text
Ctrl + Arrow keys = Jump by word
Ctrl + Shift + Arrow = Select by word
Ctrl + Home / End Go top / bottom

7. Advanced Windows Shortcuts (Creator Level)
Windows + X = Power menu (Admin tools)
Windows + V = Clipboard history
Windows + . = Emoji panel 😎
Windows + Tab Task View
Windows + Ctrl + D = New virtual desktop
Windows + Ctrl + ← / → = Switch desktops

8. Emergency / Fix Shortcuts
(When something freezes.)
Ctrl + Alt + Delete = Security options
Ctrl + Shift + Esc = Force open Task Manager
Alt + Space → M = Move stuck window

✍️የወደዳችሁት shortcut የቱ ነው?

©️ bighabesha
👏21
ርዕስ፡ 📢 ከጋላክሲ ዊዝደም አሰልጣኝ ፋንታሁን ሀሰን ጋር የተደረገ እጅግ ወሳኝ የህይወት ውይይት!

"ልጆቻችን የጀነት ስጦታዎቻችን ወይስ የቤተሰባችን ህመም ተሸካሚዎች?"
ውድ የሙምታዝ አካዳሚ ቤተሰቦች፣ አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱህ!
ዛሬ በሙምታዝ አካዳሚ፣ በታላቁ አሰልጣኝ ፋንታሁን ሀሰን አማካኝነት እጅግ ዐይን ገላጭ፣ ልብ የሚሰብር እና መልሶ የሚጠግን ድንቅ ስልጠና አግኝተናል። ስልጠናው ስለ ልጆቻችን ብቻ ሳይሆን ወደ እራሳችን እንድንመለከት ያደረገ እውነተኛ መስታወት ነበር።
አላህ (ሱ.ወ) በቅዱስ ቁርአኑ እንዲህ ይላል፡-

“ገንዘብና ልጆች የቅርቢቱ ሕይወት ጌጦች ናቸው...” (አል-ከህፍ፡ 46)

ነገር ግን እነዚህን ጌጦች እንዴት እየያዝናቸው ነው? ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) “ሁላችሁም እረኞች ናችሁ፤ ስለ መንጋችሁም ትጠየቃላችሁ” (ቡኻሪና ሙስሊም) ብለውናልና ቆም ብለን እራሳችንን እንፈትሽ።
ከስልጠናው የቀሰምነውን ወርቃማ እና ህይወት ቀያሪ ሀሳቦች፣ ከእስላማዊ እሴቶች ጋር አዋህደን እነሆ በሁለት ክፍል አቅርበንላችኋል። ይህ ማስታወሻ የውቅያኖስን ያህል ጥልቀት ካለው የስልጠናው ሰነድ በጥቂቱ የተቀዳ ነው። ዋናውን በዝርዝር ለማግኘት ከታች የተያያዘውን PDF ይክፈቱ!

ክፍል 1፡ የልጆችን የተፈጥሮ ፀጋ (Intelligences) መረዳት
አላህ (ሱ.ወ) የሰው ልጆችን ሲፈጥር በአንድ ሻጋታ (Mould) አልቀረጻቸውም። ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) “ሰዎች እንደ ወርቅና ብር ማዕድናት ናቸው...” (ሙስሊም) እንዳሉት፣ ልጆቻችን ውስጥ ያለው ማዕድን የተለያየ ነው።
አሰልጣኝ ፋንታሁን በስልጠናው እንዳብራሩት ልጆች ከሚከተሉት ተሰጥኦዎች አንዱን ወይም ከዚያ በላይ ሊኖራቸው ይችላል። የእኛ ድርሻ ማወቅና መደገፍ ነው፡-

➊ የቋንቋ ብቃት (Linguistic): እንደ ሀሳን ኢብኑ ሳቢት (ረ.ዐ) የመናገርና የመጻፍ ችሎታ ያላቸው። ነገ የዲን ተሟጋች ወይም ታላቅ ጸሃፊ የሚሆኑ።

የሂሳብና አመክንዮ ብቃት (Logical): እንደ ዘይድ ኢብኑ ሳቢት (ረ.ዐ) የመተንተንና የሂሳብ አቅም ያላቸው።

➌ ሰዎችን የመረዳት ተሰጥዖ (Interpersonal Intelligence):
እነዚህ ልጆች የሌሎችን ስሜት፣ ፍላጎትና አመለካከት በቀላሉ የመረዳት ልዩ አቅም አላቸው። በቡድን መስራት ይወዳሉ፣ ችግር ያስታርቃሉ፣ ሰዎችንም የመምራት ተፈጥሯዊ ዝንባሌ አላቸው።
◆ ምሳሌ፦ እንደ አቡበክር አሲዲቅ (ረ.ዐ) የሰዎችን ልብ ማሸነፍ የሚችሉ መሪዎችና ማህበራዊ ጠበብቶች ናቸው።

❹ የአካላዊ ብቃት (Bodily-Kinesthetic): እንደ ኻሊድ ኢብኑል ወሊድ (ረ.ዐ) በስፖርትና እንቅስቃሴ ሜዳ ላይ የሚደምቁ።

❺ የውስጥ ማንነት ብቃት (Intrapersonal): ራሳቸውን የሚያዳምጡና ጠንካራ የውስጥ ማንነት ያላቸው።

❻ የድምፅ ተሰጥኦ (Rhythmic): ለድምፅ ልዩ ትኩረት ያላቸው። ይህንን ጸጋ ቁርአንን በውብ ድምፅ በማነብነብ (እንደ አቡ ሙሳ አል-አሽዓሪ) እንዲጠቀሙበት ልናግዛቸው ይገባል።

​❼ የራስን ማንነት የመረዳት ተሰጥዖ (Intrapersonal Intelligence):
እነዚህ ልጆች የራሳቸውን ስሜት፣ ጥንካሬና ድክመት ጠንቅቀው የሚያውቁ ናቸው። ብቻቸውን መሆንና ማሰብ ያስደስታቸዋል። የራሳቸውን ግብ ያስቀምጣሉ፣ በራሳቸውም ይተማመናሉ።

​ምሳሌ፦ እንደ ታላቁ የዲን ሊቅ ኢማሙ አል-ጋዛሊ (ረሂመሁላህ) የራሳቸውን ነፍስ መርምረው ለትልቅ ደረጃ የሚበቁ፣ ነገ ጥልቅ አስተላላፊዎች (Philosophers) ወይም የነፍስ ሐኪሞች (Psychologists) የሚሆኑ ናቸው።

❽  ተፈጥሮን የመረዳት ተሰጥዖ (Naturalist Intelligence):
እነዚህ ልጆች ለአካባቢያቸው፣ ለተክሎች፣ ለእንስሳትና ለተፈጥሮ ክስተቶች ልዩ ፍቅርና ትኩረት አላቸው። በተፈጥሮ ውስጥ መሆን ያስደስታቸዋል፣ ነገሮችን የመለየትና የመመደብ አቅማቸው ከፍተኛ ነው።
◆ ምሳሌ፦ አላህ በቁርአኑ "በሰማያትና በምድር ባሉ ተአምራት ላይ አትመለከቱም?" የሚለውን ጥሪ በተግባር የሚተረጉሙ፣ ነገ የአካባቢ ጥበቃ ባለሙያ ወይም ድንቅ የግብርና ሊቃውንት የሚሆኑ ናቸው።

❾ ስዕላዊ ተሰጥዖ (Visual/Spatial Intelligence):
ነገሮችን በምስል የማየት፣ የመቅረጽና የማስታወስ ብቃት። እንደ አርክቴክቶችና ዲዛይነሮች ነገሮችን በአዲስ መልክ የመቅረጽ ችሎታ ያላቸው ልጆች ናቸው።


መልዕክት: ኢማሙ ሻፊዒይ (ረሂመሁላህ) “ጊዜ እንደ ሰይፍ ነው...” እንዳሉት፣ የልጆቻችንን የተፈጥሮ አቅጣጫ በጊዜ ካላወቅንላቸው፣ የተፈጠሩበትን ዓላማ ሳያሳኩ ጊዜው ይቆርጣቸዋል።

ክፍል 2 👇👇👇
3
ክፍል 2፡ "የታመመ ቤተሰብ" (Dysfunctional Family) እና ሰለባ የሆኑ ልጆች

ይህ የስልጠናው ክፍል እጅግ ልብ የሚነካ ነው። ቤተሰብ ሲታመም (በግጭት፣ በፍቅር ማነስ፣ ወይም በተሳሳተ አስተዳደግ) ልጆች ያንን ክፍተት ለመሙላት ሳያውቁት 7 አደገኛ ሚናዎችን (Roles) ይጫወታሉ። በስልጠናው ሰነድ ላይ በስፋት እንደተብራራው፣ ልጆቻችንን የትኛው ሳጥን ውስጥ እንደከተትናቸው እንፈትሽ፡-

1. የሜዳሊያ ልጅ (The Hero)

◆ ማንነቱ: ቤተሰቡ የሚወደው ውጤት ሲያመጣ ብቻ ነው። ፍቅርን በውጤት ይለካል።
⭕️ አደጋው: ስህተት መሥራትን እንደ ሞት ይፈራል። ለቤተሰቡ ክብር ሲል የራሱን ማንነት ያጣል።
የሸሪዓው ሚዛን: ይህ አደገኛ ነው። አላህ ሰዎችን የሚመዝነው በ"ተቅዋ" እንጂ በውጤት አይደለም።

2. ተሸካሚው ልጅ (The Scapegoat)
◆ ማንነቱ: የቤተሰቡን ጭንቀት፣ ንዴት እና ውድቀት ማራገፊያ የሆነ ልጅ። ወላጆች ሲጣሉ ጣቱ ወደ እሱ ይቀሰራል።
⭕️ አደጋው: አመፀኛ እንዲሆን ይገደዳል። ጥፋተኝነት ይሰማዋል።
የሸሪዓው ሚዛን: አላህ “ማንኛዋም ነፍስ ኃጢአትን አትሸከምም” (አል-አንዓም 164) ይላል። የቤተሰብን ችግር በልጅ ላይ ማላከክ "ዙልም" (በደል) ነው።

3. የጠፋው ልጅ (The Lost Child)
◆ ማንነቱ: ቤተሰቡ ሲወጠር ይህ ልጅ ትኩረት ላለማጣት ድምፁን ያጠፋል። "ዝምተኛ፣ ጨዋ" ይባላል።
⭕️ አደጋው: በውስጡ ብቸኝነት እየበላው ነው። በስሜት የሞተ ልጅ ይሆናል።
የሸሪዓው ሚዛን: ዝም ያለን ልጅ ችላ ማለት አማናን መብላት ነው።

4. የተቀባው ልጅ (The Golden Child)
◆ ማንነቱ: ሳይጠይቅ ሁሉም የሚሟላለት፣ ከወንድሞቹ ተለይቶ የሚንቀባረር።
⭕️ አደጋው: ሲያድግ ዓለም ሁሉ እንዲንቀጠቀጥለት ይፈልጋል። "ትዕቢተኛ" (Arrogant) ለመሆን የቀርበ ነው።
የሸሪዓው ሚዛን: ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ)፡- “አላህን ፍሩ በልጆቻችሁም መካከል አስተካክሉ (ፍትሃዊ ሁኑ)” ብለው ይህንን ድርጊት አጥብቀው አውግዘዋል።

5. አስታራቂው ልጅ (The Mascot)
◆ ማንነቱ: የቤተሰቡን ግጭት በቀልድ እና በጨዋታ ለማብረድ የሚሞክረው።
⭕️ አደጋው: የቤተሰቡን ሠላም ለመጠበቅ ሲል በውስጡ እያለቀሰ የውሸት ፈገግታ ያሳያል።

6. ሞግዚት ልጅ (The Caretaker)
◆ ማንነቱ: ወላጆቹን ወይም ታናናሾቹን ለመንከባከብ ሲል የራሱን ጨዋታ እና ፍላጎት የገደለ።
⭕️ አደጋው: በልጅነት አካሉ የሽምግልና ጭንቀት ይሸከማል።

7. ብርቅዬው (በወላጅ ቅርጽ የተሰራው) ልጅ
◆ ማንነቱ: የወላጆቹን ያልተሳካ ህልም እንዲኖር የተገደደ። (ለምሳሌ፡ ወላጅ ዶክተር መሆን ፈልጎ ካልሆነ፣ ልጁን በግድ ዶክተር እንዲሆን የሚገፋው)።
⭕️ አደጋው: የራሱን ማንነት አያውቅም። የወላጆቹ "ሮቦት" ነው።
የሸሪዓው ሚዛን: ዐሊይ ኢብኑ አቢ ጣሊብ (ረ.ዐ) “ልጆቻችሁን ለተፈጠሩበት ዘመን አሳድጉ፤ እነሱ የተፈጠሩት ለእናንተ ዘመን አይደለምና” እንዳሉት ልጆቻችንን በራሳችን ሳጥን ውስጥ አንክተታቸው።

📚 ወሳኝ ቀጣይ እርምጃ
ውድ ወላጆች! ይህ አጭር ማጠቃለያ ነው። በስልጠናው ላይ እያንዳንዱ ልጅ የሚያሳያቸው ምልክቶች እና መፍትሄዎች በዝርዝር ተቀምጠዋል።
"እኔ ቤት የትኛው ልጅ አለ?" ብለው እራስዎን ለመጠየቅ እና መፍትሄውን ለማግኘት ከታች የተያያዘውን PDF (የስልጠናውን ሙሉ ሰነድ) አሁኑኑ ይክፈቱ! ለልጆችዎ ሲሉ እባክዎ 10 ደቂቃ በመስጠት ያንብቡት።

ዱዓ 🤲
ያ አላህ!
ልጆቻችንን ለዓይናችን ማረፊያ፣ ለልባችን ደስታ አድርግልን።
ከታመመ አስተዳደግ፣ ከክፉ ነገር ሁሉ ጠብቀህ፤ በሰጠሃቸው ተሰጥኦ (Fitrah) ለአላማህ የምትጠቀምባቸው፣ ለዲናቸውና ለሀገራቸው ጠቃሚዎች አድርግልን።
እንደ ታላቁ ኢብኑል ቀይይም (ረሂመሁላህ) “ልብ እንደ ወፍ ነው፤ ከፍ ባለም ቁጥር ከአደጋ ይርቃል” እንዳሉት፣ የልጆቻችንን ልብ በእውቀትና በፍቅር ወደ አንተ ከፍ የምናደርግበትን ጥበብ ለግሰን። ቤታችንን የሰኪና (የመረጋጋት) እና የራህመት ቤት አድርግልን።

አሚን! 🤲 🤲 🤲

📚 ሙምታዝ አካዳሚ

በአላህ ፍቃድ የነገ መሪዎችን በብቃት እና በእምነት እንቀርፃለን!!

የስልጠናውን PowerPoint ለማግኘት ከታች ያለውን ሊንክ ተጫኑ!! 👇

t.me/MumtazKG/147?single

✍️ በረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል
2
Google photos app አዳዲስ ፊቸሮች ተካቶለታል።

Google ሁሉንም እፕሊኬሽኖቹን የGemeni AI ፊቸር integrate እየደረገላቸው ይገኛል።

ከነዚህ ውስጥ አንዱ የሆነው Google photos የተለያዩ የAI ፊቸሮች ተካቶለታል።

ስልካችሁ ላይ ያለ ማንኛውንም ፎቶ በቀላሉ search አድርጋችሁ ማግኘት የምችሉበት ask የሚል አማራጭ ታገኛላችሁ።

Gemini powered የሆነው ይህ ፊቸር ፎቷችሁን በስም፣ በአይነት፣ ወይም በተነሳችሁ ቀን search አድርጋችሁ ማግኘት ትችላላችሁ።

ሌላው create የሚል አማራጭ ያለ ሲሆን ፎቷችሁን ወደ video ወይም ወደ animation መቀየር ትችላላችሁ።

Google photos application Update አድርጋችሁ check አድርጉት።

©️
5
SATCOM INSTITUTE OF TECHNOLOG cp hand out - Copy (1).pdf
2.5 MB
Smart phone ጥገና በአማርኛ
ፌስታል ይዛችሁ እንዳትቀጡ!
~
ከነገ ቅዳሜ ጥር 23/2018 ጀምሮ ፌስታል ይዞ የተገኘ ይቀጣል ተብሏል። እገዳው ለአንድ ጊዜ አገልግሎት የሚውሉ (ትንንሽም ይሁን ትልልቅ) ሁሉንም አይነት ፌስታሎች የሚያጠቃልል ሲሆን በእጅ ይዞ ለተገኘ ግለሰብ ከ2,000 እስከ 5,000 ብር ፣ ለአምራቾች፣ አከማቺዎች እና አከፋፋዮች ደግሞ ከ50,000 እስከ 200,000 ብር ቅጣት እና እስከ አምስት አመት የሚደርስ ጽኑ እስራት ያስቀጣል ተብሏል።

ተግባራዊነቱን ወደፊት የምናየው ይሆናል። ዋናው ነገር ህጉን ሰበብ አድርጎ የሚንቀሳቀስ የራበው ጅ - ብ እንዳያገኛችሁ ተጠንቀቁ። "ሰኞን አትሁኑ!"

"ሼር" ብታደርጉት።

©️ @IbnuMunewor
1