Basic Computer Skills
1.85K subscribers
1.22K photos
100 videos
575 files
833 links
#በዚህ የቴሌግራም ቻናል
↪️ Programming
↪️ ቴክኖሎጂ ነክ ትምህርቶችን
↪️ ኮምፒውተር ነክ ትምህርቶችን
↪️Basic Computer Skills
↪️ Software
↪️ AI and AI Skills (Like ChatGPT)

ከላይ የተዘረዘሩትና ሌሎችም ገራሚ ትምህርቶች ይለቀቅበታል!

t.me/BasicComputerSkillsGroup

𝘽𝙮 𝙍𝙚𝙨𝙝𝙖𝙙
Download Telegram
ℛℯ𝓈𝒽𝒶𝒹 ℳ𝓊𝓏ℯ𝓂𝒾𝓁
Photo
💻 የኮምፒውተር ኪቦርድ ላይ የሚገኙት (F1-F12) ቁልፎች ድብቅ ሚስጥራት

ብዙ ጊዜ የኮምፒውተር ኪቦርድ ላይ ከላይ በኩል የተደረደሩትን (F1-F12) ቁልፎች ለድምፅ መጨመሪያ ወይም ለብሩህነት (Brightness) ማስተካከያ ብቻ ሲያገለግሉ ይስተዋላል። ነገር ግን እነዚህ ቁልፎች "Function Keys" ይባላሉ፤ ስራን በብልሃትና በፍጥነት ለመከወን የተሰሩ አቋራጭ መንገዶች ናቸው።

⚠️ ማሳሰቢያ: አንዳንድ ላፕቶፖች ላይ እነዚህን ቁልፎች ለመጠቀም Fn የሚለውን ቁልፍ ተጭኖ መጠቀም እንደሚያስፈልግ መዘንጋት የለበትም።

ከF1 እስከ F12 ያሉት ቁልፎች የሚሰጡት አገልግሎት በዝርዝር እነሆ፦

➊ F1 (እርዳታና ማስተካከያ)
◆ ከ Windows ቁልፍ ጋር በጋራ ሲጫኑ Help Menu ያመጣል።
◆ Excel እና Word ሲጠቀሙ ከ Ctrl ጋር በጋራ ሲጫኑ የላይኛውን የሪበን ሜኑ (Ribbon Menu) ይደብቃል ወይም መልሶ ያሳያል። ስክሪን ላይ ሰፊ የመጻፊያ ቦታ ለማግኘት ይጠቅማል።

F2 (ስም መቀየርና ማተም)
◆ የተመረጠን ፋይል ወይም ፎልደር ስም (Rename) በፍጥነት ለመቀየር ያገለግላል።
◆ በጣም ጠቃሚ: በ Word ውስጥ Ctrl + F2 ሲጫኑ የጽሁፉን ማተሚያ ቅድመ-እይታ (Print Preview) ያሳያል። ወረቀት ከማበላሸት ያድናል።

F3 (ፍለጋና ፊደል ቅያሪ)
◆ በ Windows Explorer ወይም በብራውዘሮች ላይ የፍለጋ (Search) ሳጥንን ይከፍታል።
◆ ልዩ ጥቅም: በ Word ላይ እንግሊዝኛ ሲጽፉ Shift + F3 በመጫን የፊደላትን ቅርጽ (Capital/Small letter) በፍጥነት ለመቀያየር ይረዳል። መደጋገም አያስፈልግም።

F4 (መዝጋትና መድገም)
Alt + F4 ማንኛውንም የተከፈተ መስኮት ይዘጋል (Shutdown ለማድረግም አማራጭ ያመጣል)።
◆ የባለሙያዎች ሚስጥር: በ Excel እና Word ላይ አንድ የሰሩትን ስራ ለመድገም (Repeat Action) ያገለግላል። ለምሳሌ፡ የአንድን ጽሁፍ ቀለም ቀይረው ቀጣዩንም ለመቀየር F4ን ብቻ መጫን በቂ ነው።

❺ F5 (ማደስ)
◆ የኢንተርኔት ገጽን ወይም የኮምፒውተር ፍጥነትን ለማደስ (Refresh) ያገለግላል።
◆ በ PowerPoint Slideshow ለማስጀመር ይጠቅማል።
◆ በ Microsoft Office ውስጥ አንድን ቃል ፈልጎ ለመቀየር (Find and Replace) ያመጣል።

F6 (ፈጣን ሽግግር)
◆ ኢንተርኔት ሲጠቀሙ ማውዝ ሳይነኩ ጠቋሚውን (Cursor) በቀጥታ ወደ አድራሻ መጻፊያው (Address bar) ይወስዳል።
Ctrl + F6 በ Word ላይ የተከፈቱ የተለያዩ ሰነዶች መካከል በፍጥነት ለመሸጋገር ይጠቅማል።

❼ F7 (የፊደል እርማት)
◆ በ Microsoft Word ላይ የፊደልና የሰዋሰው ስህተት (Spelling and Grammar check) ያደርጋል።
Shift + F7 ሲጫኑ ተመሳሳይ ትርጉም ያላቸውን ቃላት (Thesaurus) ይፈልጋል።

❽ F8 (Safe Mode)
◆ ኮምፒውተር ሲነሳ ችግር ካጋጠመ ወደ Safe Mode ለመግባት ያገለግላል።
◆ በ Excel ውስጥ የሴሎችን ምርጫ (Selection) ለማስፋት ይጠቅማል።

F9 (ማዘመን)
◆ በ Word ውስጥ ያሉ ፎርሙላዎችንና መረጃዎችን ያዘምናል።
◆ በ Outlook ውስጥ ኢሜይሎችን ለመላክና ለመቀበል (Send and Receive) ያገለግላል።

F10 (ራይት ክሊክ)
◆ የፕሮግራሞችን የሜኑ ባር (Menu bar) ለመክፈት ይጠቅማል።
◆ ልዩ ጥቅም: Shift + F10 ሲጫኑ ልክ ማውዙን "Right Click" እንዳደረጉ ይቆጠራል። ማውዝ በሌለበት ጊዜ ትልቅ አማራጭ ነው።

F11 (ሙሉ ስክሪን)
◆ ብራውዘር ሲጠቀሙ ምስሉን ሙሉ ስክሪን (Full Screen) ለማድረግና ለመመለስ ያገለግላል።
◆ በ Excel ላይ Shift + F11 ሲጫኑ አዲስ የስራ ወረቀት (New Sheet) ይጨምራል።

F12 (Save As)
◆ በ Word እና Excel ላይ የሰሩትን ፋይል በአዲስ ስም ወይም ቦታ ለመቆጠብ Save As የሚለውን ሳጥን በቀጥታ ያመጣል።
Ctrl + F12 የተቀመጠ ፋይል ለመክፈት (Open) ይረዳል።
እነዚህን አቋራጮች መልመድ የስራ ፍጥነትን ከመጨመሩም በላይ የኮምፒውተር አጠቃቀምን ዘመናዊ ያደርጋል። መረጃው ለሌሎችም እንዲደርስ ሼር በማድረግ እንተባበር!

✍️ በረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል
════════════════
📍 ለተጨማሪ የቴክኖሎጂ ምክሮች ቻናሉን ይቀላቀሉ

🌐 ዘመኑ #የቴክኖሎጂ ነው 📲 ከዘመኑ ጋር አብረው ይዘምኑ💻

Telegram: t.me/BasicComputer_Skills

Tiktok:
tiktok.com/@basiccomputerskills

Instagram:
instagram.com/basiccomputerskills

Umma Life:
ummalife.com/ReshadMuzemil
🤔1
Basic Computer Skills pinned «💻 የኮምፒውተር ኪቦርድ ላይ የሚገኙት (F1-F12) ቁልፎች ድብቅ ሚስጥራት ብዙ ጊዜ የኮምፒውተር ኪቦርድ ላይ ከላይ በኩል የተደረደሩትን (F1-F12) ቁልፎች ለድምፅ መጨመሪያ ወይም ለብሩህነት (Brightness) ማስተካከያ ብቻ ሲያገለግሉ ይስተዋላል። ነገር ግን እነዚህ ቁልፎች "Function Keys" ይባላሉ፤ ስራን በብልሃትና በፍጥነት ለመከወን የተሰሩ አቋራጭ መንገዶች ናቸው። ⚠️ ማሳሰቢያ:…»
📚 Addis Ababa City Administration Education Bureau 2026 G.C (2018 E.C)

📚 Grade 6 and 8 First Semester Model Exam Schedule


📚 የ6ኛ፣ የ8ኛ እና የ12 ክፍል ሞዴል ፈተና መስጫ የጊዜ ሰሌዳ 📚
════════════════
የ6ኛ ክፍል ሞዴል ፈተና ጥር 04-06/2018 E.C ይሰጣል።

የ8ኛ ክፍል ሞዴል ፈተና ጥር 04-05/2018 E.C ይሰጣል።

የ12ኛ ክፍል ሞዴል ፈተና ደግሞ ጥር 04-06/2018 E.C ይሰጣል።
3
Grade 7 1st Sem ICT & CTE Test 2 Table of Specifications.pdf
171.5 KB
📚 2018 E.C Grade 7 ICT and CTE 
የሙከራ ሁለት የፈተና ቢጋር (Table of Specification for Test 2)



 በተለይም የሙምታዝ ት/ቤት ተማሪዎች Test 2 የተዘጋጀው በዚህ መሠረት ስለሆነ ተጠቀሙበት።

አላህ ይርዳችሁ!!

✍️ ረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል
2
Grade 8 1st Sem. ICT and CTE Test 2 Table of Specifications.pdf
189.4 KB
📚 2018 E.C Grade 8 ICT and CTE 
የሙከራ ሁለት የፈተና ቢጋር (Table of Specification for Test 2)



 በተለይም የሙምታዝ ት/ቤት ተማሪዎች Test 2 የተዘጋጀው በዚህ መሠረት ስለሆነ ተጠቀሙበት።

አላህ ይርዳችሁ!!

✍️ ረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል
ከውድቀት_ወደ_ማማ፡_የሙምታዝ_ተማሪዎች_የታሪክ_አዲስ_ምዕራፍ.pdf
14.4 MB
☑️ ለሙምታዝ ትምህርት ቤት ለ7 ክፍል ተማሪዎች የተሰጠ ስልጠና


📚 ርዕስ፡ ከውድቀት ወደ ማማ! - የታሪክ አዲስ ምዕራፍ 🔥


ስላይድ ብዛት: 60 ስላይድ

ስልጠና: በረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል


በስልጠናው ሁሉም እንዲጠቀምበት ታስቦ የተጋራ።
🔥 ከውድቀት ወደ ማማ! - የታሪክ አዲስ ምዕራፍ 🔥
════════════════

ዛሬ በሙምታዝ አካዳሚ ከ7ኛ ክፍል ተማሪዎች ጋር በነበረን ቆይታ፤ በእያንዳንዱ ተማሪ ልብ ውስጥ የህሊና ደወል የሚሆን፣ የተኙትን የሚያነቃ፣ የጠፉትን የሚመልስና አቅጣጫን የሚያስተካክል እውነት ላይ ተወያይተናል። ይህ አብሮ ያያያዝነው የሥልጠና ሰነድ (PDF) ትውልድ ከተቀበለውና ከተገበረው ወደ ታላቅነት ማማ የሚወጣበትን የለውጥ እርምጃዎች ይዟል።

📜 የለውጥ ምዕራፎች

1️⃣ ምዕራፍ 1፡ መስተዋቱ (የነበርንበትና የደረስንበት)
ዛሬ በመስታወት ፊት ቁመን ራሳችንን የምንመረምርበት ቀን ነው። በ2017 የነበረው ትህትና፣ የመማር ጥማትና መከባበር በ2018 ለምን በረብሻና በዝንጋቴ ተተካ? ጌታችን አላህ በተከበረ ቃሉ እንዲህ ይላል፦
"አላህ በሰዎች ዘንድ ያለን (ጸጋ) በነፍሶቻቸው ያለን (ሁኔታ) እስከሚለውጡ ድረስ አይለውጥም።" (ሱረቱ አር-ረዕድ፡ 11)
የዛሬው ወጣት የነገው የኡማው ዋልታ ነው። ዋልታው ከበሰበሰ ቤቱ ይፈርሳል። "አድጌያለሁ፣ ማንም አይነካኝም" የሚል የውሸት ጀግንነት የውድቀት መጀመሪያ መሆኑን ተረድተን ወደ ቀድሞው ወርቃማ ማንነታችን የምንመለስበት ሰዓት አሁን ነው።

2️⃣ ምዕራፍ 2፡ ተማሪነት ከአላህ የተሰጠ ኒዕማ (የፍልስጤም ትምህርት)
ዛሬ እናንተ በሰላም አየር ስር ሆናችሁ፣ ወላጆቻችሁ መጽሐፍና ደብተር አሟልተውላችሁ፣ መምህራን ሊያስተምሯችሁ ቆመው እያለ ጊዜያችሁን ስታባክኑ፤ በሌላው ዓለም በተለይም በጋዛና በፍልስጤም የሚገኙ እኩዮቻችሁን አስቧቸው። እነሱ ትምህርት ቤታቸው በቦምብ ፈርሶ፣ መጽሐፎቻቸው በደም ተለውሰው፣ መምህራኖቻቸው ተሰውተውም እንኳ በድንኳንና በፍርስራሽ መካከል ሆነው እውቀትን ይፈልጋሉ።
እናንተ የተመቻቸላችሁን እድል ስታባክኑ በደምና በእንባ መማር የናፈቃቸውን ትውልዶች እየበደላችሁ ነው። አላህ የሰጣችሁን ይህን የዕውቀት ብርሃን ሸክም ሳይሆን፣ መላእክት ክንፋቸውን የሚያነጥፉለት ልዩ ስጦታ መሆኑን እወቁ። ይህን ጸጋ ማባከን በፈጣሪ ፊት በከፍተኛ ወንጀል ያስጠይቃል።

3️⃣ ምዕራፍ 3፡ አደብ (ስነ-ምግባር) - የእውቀት በር
"እውቀት ሞተር ነው፤ አደብ ደግሞ ብሬክ ነው።" ብሬክ የሌለው መኪና መጨረሻው ገደል እንደሆነ ሁሉ፣ አደብ የሌለው ተማሪም መጨረሻው ጥፋት ነው።
ታላቁ ሊቅ ኢማሙ ማሊክ (ረሂመሁላህ) እንዲህ ይላሉ፡- "ዕውቀትን ከመፈለግህ በፊት አደብን ተማር።" አደብ (ስነ-ምግባር) የሌለው ተማሪ ምንም ቢማር ፍሬ የለውም። መምህርን የሚያላግጥና የሚያቃልል ተማሪ የወደፊቱን ህይወቱን እያጨለመ ነው። በመምህራን ዱዓ እንጂ በቁጣቸው አትታጀቡ።

4️⃣ ምዕራፍ 4፡ የዘመኑ ፈተና (ዲጂታል እስር ቤት)
ስልካችን ውስጥ ያለው ቴሌግራም ጊዜያችንን የሚበላ "የኪስ ውስጥ እስር ቤት" ሊሆንብን አይገባም። በቴሌግራም ግሩፖች የምትጽፉት ስብዕና የጎደለው መልዕክት ነገ ይመሰክርባችኋል። ኢማሙ ሻፊዒ እንዳሉት፡- "ጊዜ ሰይፍ ነው፤ ካልቆረጥከው ይቆርጥሃል።" ዛሬ በከንቱ ወሬ የምታሳልፉት ሰዓት ነገ በፀፀት እሳት ያቃጥላችኋል። "ከመጥፎ ጓደኛ ብቸኝነት ይሻላል"ና የማንነት ሌባ ከሆኑ ጓደኞች ራሳችሁን አርቁ።

5️⃣ ምዕራፍ 5፡ የክብር አርማ (ለሴት ተማሪዎች)
ሂጃብ የአላህ ትዕዛዝ እንጂ የሰው ውሳኔ አይደለም። "አንተ ነቢዩ ሆይ! ለሚስቶቻችሁ፣ ለሴቶች ልጆችህም፣ ለምእምናን ሚስቶችም ከመከናነቢያዎቻቸው በላያቸው ላይ እንዲለቁ ንገራቸው..." (ሱረቱ አል-አህዛብ፡ 59)
ውድ እህታችን! አንቺ የነገዋ የኡማው እናት ነሽ። ሂጃብሽ ውበትሽና አላህ የሰጠሽ ንግስትነትሽ ነው። አርአያሽ እናታችን አይሻ (ረ.ዐ) ትሁን፤ ያለ ቀን ከእስልምና ያፈነገጠ አለባበስ ማንነትን መካድ ነው።

6️⃣ ምዕራፍ 6፡ የታላላቆች አርአያነት
የዛሬዎቹ የዓለማችን ታላላቅ ሊቃውንት እዚህ የደረሱት በተመቸ ህይወት አይደለም። ኢማሙ ቡኻሪ ለአንድ ሀዲስ ብቻ ወራትን በእግር ይጓዙ ነበር። ኢማሙ አህመድ ለእውቀት ሲሉ ግርፋትንና እስርን ታግሰዋል። ስኬት ያለ መስዋዕትነት አይገኝም። ሸይኩል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያህ እንዲህ ይላሉ፡- "ጠላቶቼ ምን ሊያደርጉኝ ይችላሉ? ጀነቴና አፀዴ በልቤ ውስጥ ናቸው፤ ቢገድሉኝ ሸህዳዬ ነው፣ ቢያስሩኝ ከጌታዬ ጋር የምገለልበት (ኸልዋ) ነው፣ ከአገሬ ቢያባርሩኝ ቱሪዝም (ሲያሃ) ነው።" ይህ ነው የዕውቀት ጥንካሬ!

7️⃣ ምዕራፍ 7፡ የመጸጸት ዋጋ (የመጨረሻው ማስጠንቀቂያ)
ዛሬ በትምህርት ማሾፍ፣ ነገ በህይወት መላገጥ ነው። ጊዜው ካለፈ በኋላ "ምነው በሰራሁ" ማለት ለቅሶ እንጂ መፍትሄ አይሆንም። አላህ በቁርአኑ እንዲህ ያስጠነቅቃል፦
"በደለኛ ሰው (በፀፀት) እጆቹን የሚነክስበትን ቀን (አስታውስ)፤ እንዲህም ይላል፡ 'ዋ ምኞቴ! ከመልዕክተኛው ጋር መንገድን በያዝኩ ኖሮ!'" (ሱረቱ አል-ፉርቃን፡ 27)
ዛሬ በስነ-ምግባር ብልሹነት ከትምህርት ቤት መሰናበት በህይወት ዘመን የማይሻር ጠባሳ ይጥላል። ሳይረፍድ ንቁ!

8️⃣ ምዕራፍ 8፡ አዲሱ ውሳኔና ቃልኪዳን
ያለፈው ስህተት ለወደፊቱ ትምህርት ይሁን። አላህ ወደ እርሱ ለሚመለሱ ሩህሩህ ነው። ዛሬ አዲስ ምዕራፍ የምንጀምርበት ቀን ነው። ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- "ከኃጢአቱ የተመለሰ (ተውበት ያደረገ) ሰው ልክ ኃጢአት እንደሌለው ሰው ነው።" (ኢብኑ ማጃህ ዘግበውታል)
በክፍል ውስጥ ጸጥታን በመጠበቅ፣ መምህርን በማክበርና የቤት ስራን በወቅቱ በመስራት ለራሳችን ቃል እንገባለን። "ለውጥ ከእኔ ይጀምራል!" ብለን እንነሳለን።

9️⃣ ምዕራፍ 9፡ የልብ መሳመሪያ (ዱዓ)
በመጨረሻም ይህ ሁሉ ጥረታችን በአላህ እርዳታ ይከናወን ዘንድ እጃችንን ዘርግተናል፡-
"ያ አላህ! በእነዚህ ተማሪዎች ልብ ውስጥ የእውቀትን ብርሃን አንግስ። ከቴክኖሎጂ ወጥመድና ከመጥፎ ጓደኛ ጠብቃቸው። ሴት እህቶቻችንን የክብር ባለቤት፣ ወንድ ልጆቻችንን የዲን ጋሻና የቤተሰብ መከታ አድርጋቸው። ዛሬ በዱዓ እንደሰበሰብከን ሁሉ ነገ በጀነት ይሰብስበን። አሚን!"


የምስጋና መዝጊያ:
ይህ ሥልጠና እውን እንዲሆንና ልጆቻችን የለውጥ ብርሃን እንዲያዩ ሁኔታዎችን ሁሉ በማመቻቸት ለደከሙት ለሙምታዝ አካዳሚ ዳይሬክተር ሚስተር ሙሐመድ ይማም የላቀ ምስጋናዬን አቀርባለሁ። እንዲሁም ለትምህርት ቤቱ አስተዳደር ሰራተኞች፣ ለሙሉ መምህራንና ለትምህርት ቤቱ ማህበረሰብ በሙሉ ለነበራችሁ ያልተቆጠበ ድጋፍና ለሥልጠናው መሳካት ላደረጋችሁት አስተዋጽኦ አላህ ጀዛችሁን ይክፈላችሁ። በኸይር ሥራችሁ ላይ ጽናቱን ይስጣችሁ።

ለለውጥ የተዘጋጃችሁና ቃል የገባችሁ የሙምታዝ የ7ኛ ክፍል ተማሪዎች... እናንተ የነገ የኡማው ኩራት ናችሁ!

🚀 ሙምታዝ፡ እውቀትን ከአደብ ጋር!

📚 በረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል

════════════════
⭕️ በስልጠናው ሁሉም ተማሪ እንዲጠቀምበት በሚል የተለጠፈ።

👇 የስልጠናውን ሙሉ ሰነድ (PDF) እዚህ ያውርዱ: 👇
👇 👇 👇

t.me/BasicComputer_Skills/2964
4
Truecaller v16.3.5 (Premium).apk
95.1 MB
Truecaller v16.3.5 (Premium).apk
👍2
Basic Computer Skills
Photo
የወደፊቱ የአለማችን የኢንተርኔት አብዮት Starlink ምንድን ነው?

Starlink በኤለን መስክ ድርጅት SpaceX የተመሰረተ የሳተላይት ኢንተርኔት project ነው።
የዚህ ፕሮጀክት ተቀዳሚ ተልዕኮው በዓለም ዙሪያ ላሉ የኢንተርኔት አገልግሎት ለማያገኙ ገጠራማና ሩቅ የአለም ክፍሎች ከፍተኛ ፍጥነት ያለው የኢንተርኔት አገልግሎት እንዲያገኙ ማድረግ ነው።

ብዙ ቁጥር ያላቸው Low Earth Orbit (LEO) ሳተላይቶችን በጋራ በማሰማራት የፋይበር ኦፕቲክና የሞባይል ኔትዎርክ ግንኙነት የማያገኙ አካባቢዎችን አስተማማኝና ፈጣን የኢንተርኔት አገልግሎቶችን ለማቅረብ አልሞ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል።

ዋና ዋና ባህሪያቶች
Global Coverage: የስታርሊንክ የሳተላይት ኢንተርኔት መላው ፕላኔት የሚሸፍን ሲሆን ይህም ቀደም ሲል የኢንተርኔት ግንኙነት የማያገኙ የአለማችን ክልሎችን ተደራሽ ያደርጋል።

High-Speed Internet: ስታርሊንክ ከባህላዊ የኢንተርኔት አገልግሎት አቅራቢዎች ጋር የሚወዳደር የብሮድባንድ ፍጥነትን የሚያቀርብ ሲሆን Online Gaming, Video Conferencingና የመሳሰሉ real-time online ስራዎችን በጥሩ ፍጥነት መከወን ያስችላል።

Easy Installation:
StarLink ለመጠቀም በጣም ቀላል የሆነችና በቀላሉ ከታ ቦታ ማንቀሳቀስ የምትቻል Dish ሲኖረው ማንኛውም ቦታ ላይ በማስቀመጥ እራሷን ከሳተላይት ጋር ማስተካከል ትችላለች። ከዚህ በተጨማሪ LTE connection ላላቸው የሞባይል ቀፎዎች የፅሁፍና የድምጽ መልዕክት እንዲሁም የኢንተርኔት አገልግሎት ያገኛሉ ተብሏል።

Constant Updates: ስታርሊንክ ተጨማሪ ሳተላይቶችን በማምጠቅ እና ሶፍትዌሩን በማዘመን ኔትወርኩን በየጊዜው እያሰፋ እና እያሻሻለ ይገኛል። አገልግሎቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ ብዙ የአለም ክፍሎችን እያካለለ ነው።

Disaster Response: አሁን የምንጠቀምባቸውን የኢንተርኔት አቅራቢ ድርጅቶችን infrastructure በተለያዩ ተፈጥሯዊና ሰው ሰራሽ አደጋዎች ቢወድሙ communication ይቋረጣል። የስታርሊንክ ሳተላይት ከዚህ ነገር ነጻ ሲሆኑ ለድንገተኛ አገልግሎቶች እና እርዳታ የሚፈልጉ የተጎዱ ሰዎችን በቀላሉ ማግኘት ያስችላል።

በአሁኑ ሰአት በተወሰኑ የአለማችን ሃገራት ስራ የጀመረው StarLink ከአፍሪካ ሃገራት ናይጀርያ፣ ጋና፣ ሴራሊዮን፣ ማላዊ፣ ዛምብያ፣ ቦቶስዋና፣ ማዳጋስካር፣ ሩዋንዳ፣ ኬንያና ደቡብ ሱዳን የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ናቸው።

ይህን አገልግሎት ለመጠቀም ክፍያው ያን ያክል ውድ የሚባል አይደለም። ከሃገራት ሃገራት ልዩነት ቢኖረውም ለግለሰብ unlimited high-speed ዳታ ለመጠቀም በወር 120 ዶላር መክፈል ይጠይቃል። ለBusiness plan ደግሞ በወር ከ140 እስከ 5000 ዶላር ድረስ ያስከፍላል።

ጎረቤቶቻችን ኬንያና ሶማልያ የstarlink service ካላቸው ሃገሮች መካከል ናቸው።

✍️ በሀገራችን በተለይ በገጠሪቱ የሀገራችን ክፍል ብዙ ሰው የኢንተርኔት አገልግሎት አያገኝም። ይህ ነገር በሃገራችን ቢጀመር ብዙ ሰው የሚጠቀም ይመስላችኋል? ሀሳባችሁን አካፍሉን።

©️ bighabesha

════════════════
📍 ለተጨማሪ የቴክኖሎጂ ምክሮች ቻናሉን ይቀላቀሉ

🌐 ዘመኑ #የቴክኖሎጂ ነው 📲 ከዘመኑ ጋር አብረው ይዘምኑ💻

Telegram: t.me/BasicComputer_Skills

Tiktok:
tiktok.com/@basiccomputerskills

Instagram:
instagram.com/basiccomputerskills

Umma Life:
ummalife.com/ReshadMuzemil
👍31
Belkin የተሰኘ የቴክኖሎጂ ድርጅት Wireless HDMI አስተዋወቀ።

በLas Vegas ከተማ እየተካሄደ ባለው አመታዊው የCES(Consumer electronics show) ፕሮግራም ላይ የቀረበው ይህ wireless HDMI ላፕቶፕ፣ ታብሌት ወይም ስማርትፎን ወደ ሌላ ስክሪን ያለ Wi-Fi ወይም Bluetooth ማጋራት የሚያስችል plug-and-play casting system አስተዋውቋል።

ይስ ሲስተም USB-C ዶንግል transmitterና USB-A to HDMI receiver የያዘ ሲሆን ዶንግሉን ስክሪኑን share ማድረግ የፈለግነው device ላይ ሰክተን USB-A to HDMI ሪሲቨሩን ደግሞ ቲቪ፣ ሞኒተር ወይም ፕሮጀክተር ላይ በመሰካት ያለምንም ችግር screen share ማድረግ ያስችለናል።

ሲስተሙን ለመጠቀም ምንም አይነት ዋይፋይ፣ ብሉቱዝ፣ አፕሊኬሽን ወይም ድራይቨር መጫን ሳያስፈልግ በ40 ሜትር ክልል ውስጥ ይሰራል ተብሏል። በተጨማሪም እስከ 1080P በ60Hzና ከ80ms ባነሰ latency እንደሚያስተላልፍ ተገልጿል።
ይህ ቴክኖሎጂ የ150 ዶላር ዋጋ የተለጠፈበት ሲሆን በሚቀጥለው አመት ለገበያ ይቀርባል ተብሎ ይጠበቃል።

©️bighabesha
3
#safety

ስልካችሁ ላይ እናንተም ሆናችሁ ታዳጊ እህት ወንድሞቻችሁ ወይም ልጆቻችሁ explicit የሆኑ ዌብሳይቶችን እንዳይከፍቱ በዚህ መሰረት መዝጋት ትችላላችሁ።

1. አጠቃላይ ስልካችሁ ላይ
የስልካችሁ settings ላይ ትገቡና connections የሚለውን ትመርጣላችሁ።
ከዛ more connection settings የሚል አማራጭ ታገኛላችሁ።
private DNS የሚለውን ከፍታችሁ Private DNS provider hostname ውስጥ Adult-filter-dns.cleanbrowsing.org ወይም family.adguard-dns.com የሚሉትን አማራጮች ሞልታችሁ Save አድርጉት።

2. Chrome Browser ላይ
በመጀመሪያ google chrome browser ከከፈታችሁ በኋላ ሶስት ነጥብጣቡን ነክታችሁ ወደ setting ውስጥ ግቡ።
Privacy and security የሚለውን ምረጡ።
በመቀጠል ትንሽ scroll እንዳደረጋችሁ የምታገኙትን "use secure DNS" የሚለውን ምረጡ።
"use your current service provider" የሚል በdefault ተመርጦ የምታገኙ ሲሆን እኛም ከታች ያለውን "choose another provider" የሚለውን እንመርጣለን።
በመጨረሻም ከስር የሚመጣልንን "custom" የሚለውን ነክተን "clean browsing (family filter)" የሚለውን መምረጥ።

ከዚህ በኋላ ምንም አይነት adult content በየትኛውም browser ላይ አይመጣም።

©️ bighabesha