Basic Computer Skills
1.85K subscribers
1.22K photos
100 videos
575 files
833 links
#በዚህ የቴሌግራም ቻናል
↪️ Programming
↪️ ቴክኖሎጂ ነክ ትምህርቶችን
↪️ ኮምፒውተር ነክ ትምህርቶችን
↪️Basic Computer Skills
↪️ Software
↪️ AI and AI Skills (Like ChatGPT)

ከላይ የተዘረዘሩትና ሌሎችም ገራሚ ትምህርቶች ይለቀቅበታል!

t.me/BasicComputerSkillsGroup

𝘽𝙮 𝙍𝙚𝙨𝙝𝙖𝙙
Download Telegram
Basic Computer Skills
Photo
🎓 የእውቀት ፋና፦ ተማሪነትን ከመከራ ወደ ማህበረሰብ ብርሃንነት

📚 በዚህች ምድር ላይ የምንከፍለው ትልቁ መስዋዕትነት፣ የምናገኘውም ትልቁ ድል በደብተራችንና በብዕራችን መካከል የሚገኝ ነው። ተማሪነት የድካም ሸክም ሳይሆን፣ አላህ ለወደደው ባሪያ የሚሰጠው የብርሃን ቁልፍ ነው።

ክፍል 1፡ የእውቀት ኒዕማ (መለኮታዊ ስጦታ)

ተማሪነት በአላህ የተሰጠን ትልቅ ጸጋ እንጂ እንዲሁ የሚገኝ አጋጣሚ አይደለም። ብዙዎች መማር እየፈለጉ አላገኙትም፤ እናንተ ግን ተመርጣችኋል።
◆ የኢማም ሻፊዒይ ሰይፍ፦ "እውቀት መደብ ላይ የሚቀመጥ ዕቃ ሳይሆን፣ ልብን የሚያበራ ብርሃን ነው" ይላሉ። እውቀት አላህ በልባችሁ ውስጥ የሚያበራው መብራት ከሆነ፣ "አይገባንም" የሚል ጨለማ ቦታ ሊኖረው አይችልም።
◆ የመንፈስ ልዕልና፦ ተማሪነት ከእንስሳዊ ባህሪ ወደ ሰብአዊ ጥበብ የምንሻገርበት ድልድይ ነው። ዛሬ የምታነቡት እያንዳንዱ ገጽ፣ ነገ ለምትገነቡት ታላቅ ማንነት የሚቀመጥ አንድ የመሰረት ድንጋይ ነው።

ክፍል 2፡ የተስፋ-ቢስነትን ሰንሰለት መስበር

⭕️ "አይሳካልንም"፣ "እንግሊዝኛ ይከብደናል" ወይም "ሒሳብ ለኛ አይደለም" የሚሉ ቃላት የነፍስ በሽታ እንጂ የእውነት ነጸብራቅ አይደሉም።
የሼይኩል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያህ ቆራጥነት፦ ሼይኩ በታሰሩበት ወቅት እንዲህ ይሉ ነበር፦ "ጠላቶቼ ምን ሊያደርጉኝ ይችላሉ? ጀነቴና አጸዴ በልቤ ውስጥ ናቸው፤ መታሰሬ ብቸኝነትና ዒባዳ ነው፣ መገደሌ ሸሂድነት ነው፣ ከአገሬ መሰደዴ ደግሞ ቱሪዝም (ጉብኝት) ነው!"።
◆ የእኛ ትምህርት፦ ልክ እንደ ሼይኩ፣ እኛም በትምህርት አለም የሚገጥሙንን መሰናክሎች እንደ እስር ማየት የለብንም። አስቸጋሪ ትምህርት አእምሮን የሚያጎለምስ "ጂምናዚየም" ነው። "አይገባንም" የሚለው ስሜት የሰይጣን እንጂ የአማኝ ቃል አይደለም። እናንተ "አንችልም" ስትሉ፣ ለአእምሮአችሁ እስር ቤት እየገነባችሁለት እንደሆነ እወቁ፤ ቁልፉ ግን እጃችሁ ላይ ነው።

ክፍል 3፡ የወደቁት የጥበብ ማማዎች (የጽናት ዋጋ)

ስኬት የሚለካው ባለመውደቅ ሳይሆን፣ በወደቁ ቁጥር ለመነሳት በሚደረግ ትግል ነው። ዛሬ የምናደንቃቸው ሊቃውንትም ሆኑ ሳይንቲስቶች የውድቀት ተማሪዎች ነበሩ።
◆ የአልበርት አንስታይን ትዕግስት፦ አንስታይን በትምህርት ሥርዓቱ ውስጥ በወቅቱ ባይገነዘቡትም፣ ተስፋ ቆርጦ ቢሆን ኖሮ ዛሬ ስለ አጽናፈ ዓለም ያለን እውቀት ባዶ ይሆን ነበር።
ቶማስ ኤዲሰን፦ አምፖልን ለመፍጠር 1,000 ጊዜ የከሸፈው ሙከራው፣ "አልተሳካልኝም" ሳይሆን "አምፖል የማይሰራባቸውን 1,000 መንገዶች አገኘሁ" በሚል ብሩህ ተስፋ ነው የተጠናቀቀው።
◆ የኢማም አህመድ ቢን ሀንበል ጽናት፦ ለሀቅ ብለው ብዙ ስቃይና ግርፋት ሲደርስባቸው "ይህ የአላህ ፈተና ነው" በማለት ጸንተዋል። ተማሪነትም እንደዚሁ በትዕግስት (ሰብር) እሳት ካልተፈተነ ወርቅ አይሆንም።

ክፍል 4፡ ሰብር እና አደብ (ስነ-ምግባር)

እውቀት ያለ ትዕግስት አይገኝም፤ ያለ ስነ-ምግባርም ብርሃን አይሆንም።
◆ የኢማም ማሊክ አባባል፦ "እውቀት ሁሉንም ነገራችሁን ካልሰጣችሁት፣ ከፊሉን እንኳን አይሰጣችሁም" ይላሉ። ግማሽ ልብ ይዛችሁ ሙሉ ስኬት አትጠብቁ።
◆ የስነ-ምግባር ሚዛን፦ እውቀት በትህትና ካላስዋባችሁ፣ ተምራችሁ ሳይሆን ደንዝዛችሁ ቀርታችኋል። እውነተኛ ተማሪ በትምህርቱ ከፍ ሲል፣ በትህትናው ወደ መሬት ዝቅ የሚል ነው። ጊዜያችሁን በሰብር ከገነባችሁ ግን፣ እውቀት የክብር ዘውድ ያቀዳጃችኋል።

ክፍል 5፡ ተማሪነት ለሀገርና ለማህበረሰብ

እኛ የምንማረው ለራሳችን ሰርተን ለመብላት ብቻ አይደለም። እኛ የምንማረው የታመሙትን ለመፈወስ፣ የተቸገሩትን ለመርዳትና ሀገራችንን ከድህነት ጨለማ ለማውጣት ነው።
◆ አማና (አደራ)፦ ተማሪነት ድጋፍ የሚሹ ወገኖቻችንን የምንደግፍበት ኃይል ነው። እውቀት ኖሯችሁ ማህበረሰባችሁን ካልቀየራችሁ፣ እናንተ እንደተሸከመ አህያ ናችሁ።
◆ የለውጥ አርክቴክቶች፦ ዓለምን ለመቀየር መጀመሪያ ራስን መለወጥ ግድ ነው። በትምህርታችሁ የምታመጡት እያንዳንዱ ለውጥ በቤተሰባችሁና በሀገራችሁ ላይ የሚበራ ትልቅ ፋኖስ ነው።

ክፍል 6፡ የመጨረሻው ጥሪ - ተነሱና ታሪካችሁን ጽፉ!

ውድ ተማሪዎች! ውስጣችሁ ያለው አቅም ከማንኛውም ፈተና ይበልጣል። ቱርኮች "ከፈለጋችሁ ህይወታችሁን እጡ እንጂ ተስፋ እንዳታጡ" ይላሉ። ተስፋ የቆረጠ ሰው በቁሙ የሞተ ነው።
◆ ውሳኔያችን፦ ዛሬውኑ ከስንፍና ጋር ያለንን ውል እናፍርስ። ለውድቀታችን ሰበብ አንደርድር። በአላህ ስም እንነሳ! ዛሬ የምታባክኑት እያንዳንዱ ደቂቃ ነገ የምትከፍሉት ዋጋ መሆኑን አትዘንጉ።
◆ የመጨረሻ መልዕክት፦ እናንተ የሁኔታዎች ሰለባ አይደላችሁም፤ እናንተ በብዕራችሁና በጥረታችሁ የራሳችሁንና የሀገራችሁን እጣ ፈንታ የምትቀይሩ "የህይወት አርክቴክቶች" ናችሁ። የዛሬው ድካም የነገው የድል አክሊል ነው።

ዛሬውኑ ጀምሩ! ምክንያቱም ነገ ለሰነፎች የቀጠሮ ቀን ነው።

✍️ በረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል
4
Forwarded from Grade 8 Info & Materials
Grade 8 Info & Materials
Photo
🎓 NotebookLM
══════════════
🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟

🎓 በኖትቡክኤልኤም (NotebookLM) ትምህርታችሁን ቀይሩ

አዲስ የብልህ፣ የፈጠራ ባለቤት እና ባራሳችሁ በጣም በቀላል መንገድ ትምርታችሁ፣ ጥናታችሁ፣ ክለሳችሁ ላይ ውጤታማ የምትሆኑበት ዘመን

🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟

💭 ይህን አስቡት...
የእናንተ ማስታወሻዎች፣ የትምህርት መጻሕፍት እና የምርምር ጽሑፎች ሕያው ሆነው የናግራችኋል፣ ያብራራልላችኋል፣ ያጠቃልላልላችኋል እንዲሁም በጥልቀት እንድታስቡ ይረዳችኋል!

ይህ የNotebookLM አስገራሚ ኃይል ነው። ይህ ጉግል በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ኃይል ያጎናጸፈው እና ለጠያቂ፣ ፈጠራ ላላቸውና ቆራጥ ተማሪዎች የተዘጋጀው ዲጂታል ማስታወሻ ደብተር ነው። 💡

💫 ለምን ጠቃሚ ነው?

ትምህርት ማለት መርሳት የሌለብንን ነገር መያዝ ብቻ አይደለም—መረዳት፣ ማሰስ እና ትርጉም መፍጠር ነው። 🌱

📚 NotebookLM የሚከተሉትን ለማድረግ ይረዳችኋል፦

በፍጥነት መማር፣
በብልህነት ማጥናት፣
ጥልቅ አስተሳሰብ መፍጠር፣
እና ትምህርትን እንደገና መውደድ 💖

⭕️ ይህ መሣሪያ መምህራንን ወይም ተማሪዎችን ለመተካት አልመጣም ይልቁንም ሁለቱንም ለማጎልበት ነው። 🌍

📘 NotebookLM ምንድነው?

🧠 NotebookLM = የእናንተ የኤአይ (AI) የጥናት አጋር ነው።

የሚከተሉትን ጫኑበት (Upload):
📄 ፒዲኤፎች (PDFs)
📝 ጉግል ዶክስ (Google Docs)
🖼️ ስላይዶች (Slides)
🔗 የድር አገናኞች (Web links)
ከዚያም እንዲህ እንዲያደርግ ፍቀዱለት፦
💬 ቁልፍ ነጥቦችን ያጠቃልላል
🎯 ለጥያቄዎቻችሁ መልስ ይሰጣል
🗂️ የጥናት መመሪያዎችን፣ የክስተቶች ቅደም ተከተል እና በተደጋጋሚ የሚጠየቁ ጥያቄዎችን ይፈጥራል
🎧 ማስታወሻዎቻችሁን ወደ በድምጽ የሚቀርብ ትምህርት/ታሪክ (ፖድካስት) ይቀይራቸዋል።

የእናንተ የጥናት ቁሳቁሶች—አሁን ተግባቢ፣ ሕያው (የእናንተ አጋዥ) እና አነቃቂ ይሆናሉ! 💥

🚀 እንዴት መጀመር ይቻላል?

1️⃣ 👉 notebooklm.google.com  ጎብኙ
2️⃣ የራስ ማስታወሻ ደብተር ፍጠሩ 🗂️
3️⃣ የትምህርት ቁሳቁሶቻችሁን ጫኑ 📚
4️⃣ እንደነዚህ ያሉ ጥያቄዎችን ጠይቁ፦
💬 “ይህን በቀላል ቃላት አብራራልኝ።”
💬 “አንድ የፈተና ጥያቄ (Quiz) ፍጠርልኝ።”
💬 “እነዚህን ሁለት ሐሳቦች አወዳድር።”
💬 “ከእውነተኛ ሕይወት ጋር የሚሄዱ ምሳሌዎችን ስጠኝ።” // Real-World-Example

በሰከንዶች ውስጥ ትምህርታችሁ መስተጋብራዊ የመማር ጉዞ ይሆናል! 🌈

🎒 ለተማሪዎች

🎯 ማስታወሻዎቻችሁን ወደ አጭር ማጠቃለያ ቀይሩ
🎧 እየተራመዳችሁ ከሆነ የኦዲዮ ማጠቃለያ እይታዎችን (Audio Overviews) አዳምጡ
💬 የራስ ጥያቄዎችን ጠይቁ እና አስሱ
📝 በጠያቂነት በመነሳት ግንዛቤያችሁን ገንቡ


ጠቃሚ ምክር:

⭕️ NotebookLM እንዲረዳችሁ ፍቀዱ፣ ነገር ግን ሁልጊዜ በራስ አሰቡ። የትምህርቱ ኃይል እናንተ ናችሁ!

🧑‍🏫 ለመምህራን

🌍 የትምህርት ማጠቃለያዎችን በደቂቃዎች ውስጥ አዘጋጁ
📚 የፈተና ጥያቄዎችን፣ በተደጋጋሚ የሚጠየቁ ጥያቄዎችን ወይም መከለሻ ወረቀቶችን ፍጠሩ
💬 ለቡድን ሥራ እና ለፕሮጀክቶች ማስታወሻ ደብተሮችን አጋሩ
💖 የቢሮ ሥራን በመቀነስ፣ አእምሮን በማነሳሳት ላይ የበለጠ ጊዜ አጥፉ

ለመምህራን የሚሆን ግንዛቤ፡

NotebookLM ትምህርትን አይተካም — ያጎላዋል እንጂ።
🏫 ለትምህርት ቤቶች ማኅበረሰቦች
🌺 የዲጂታል ዕውቀትን አበረታቱ
💡 አሳታፊ ትምህርትን ደግፉ
🎯 ፈጠራንና ትብብርን አነሳሱ
🌍 የፈጠራና የጠያቂነት ባህልን ገንቡ

💻 በእውነተኛው ክፍል ውስጥ አጠቃቀሙ
🧮 ሂሳብ፦ የመፍትሄያ ዘዴዎችን የያዙ ልምምድ ጥያቄዎችን ይፍጠሩ
📖 ሥነ ጽሑፍ፦ ታሪኮችን ያጠቃልሉባቸው እና ጭብጦችን ይወያዩ
🧬 ሳይንስ፦ ንድፈ ሐሳቦችን ያነጻጽሩ፣ ሥዕላዊ መግለጫዎችን ይፍጠሩ
.
.
.
.

📚 እያንዳንዱ የትምህርት ዓይነት መስተጋብራዊ የመማር ልምድ ይሆናል!


🔒 ሥነ ምግባርና ኃላፊነት ያለው የኤአይ (AI) አጠቃቀም
💡 NotebookLMን በቅንነትና በታማኝነት ተጠቀሙ።
አጋር ነው፣ የአቋራጭ መንገድ አይደለም።
ሁልጊዜ በጥልቀት አስቡ።
እውነታዎችን ሁለቴ አረጋግጡ።
ግላዊነትንና የቅጂ መብትን አክብሩ።
በኤአይ ተማሩ፣ በዓይነ ስውርነት አትመኑበት [ምንም አይነት ጥያቄ ሳትጠይቁ ወይም ሳታረጋግጡ (Blindly) አትመኑት]።

🌟 እውነተኛ ብልህነት ሰብአዊም ሥነ ምግባራዊም ነው።

🌈 ፈጠራ እና ለሥራ ዝግጁነት
NotebookLM የወደፊቱ ጊዜ የሚጠይቃቸውን ችሎታዎች እንድትለማመዱ ያግዛችኋል፦
💭 ወሳኝ አስተሳሰብ
💡 ፈጠራ
🗣️ መግባባት
🤝 ትብብር
እነዚህ የ21ኛው ክፍለ ዘመን ልዕለ ኃይሎች ናቸው፤ ለሁሉም የህልም ሥራዎች በሮችን ይከፍታሉ!

🤝 ትብብር እና መጋራት
ማስታወሻ ደብተሮቻችሁን ከክፍል ጓደኞቻችሁ ወይም ከመምህራን ጋር አጋሩ።
👩‍💻 በፕሮጀክቶች ላይ በጋራ ስሩ።
🧩 ሐሳቦቻችሁን በኤአይ (AI) ከተፈጠሩ ግንዛቤዎች ጋር አጣምሩ።
💖 ውድድርን ሳይሆን የቡድን ሥራን ገንቡ።
ትምህርት ሲገራ ያድጋል 🌻

🌍 የትምህርት የወደፊት ሁኔታ
ትምህርት ከአሁን በኋላ በመጻሕፍትና በትምህርት ክፍሎች ብቻ አይወሰንም።
🌟 ኤአይ (AI) ትምህርትን ግላዊ፣ ፈጠራ ያለው እና የዕድሜ ልክ ያደርገዋል።

📚 NotebookLM የወደፊቱ የትምህርት ክፍል የሚከተለው እንደሆነ ያሳያችኋል፡
በሰው ላይ ያተኮረ
በቴክኖሎጂ የጎለበተ
በጠያቂነት የሚመራ
እያንዳንዱ ተማሪ አሁን የራሱን የመማሪያ መንገድ መገንባት ይችላል። 🚀


🧩 ይህን ፈተና ሞክሩት!

🎯 የመጀመሪያውን የኤአይ ማስታወሻ ደብተራችሁን ፍጠሩ!
1️⃣ አንድ የትምህርት ዓይነት ምረጡ።
2️⃣ 2–3 የጥናት ቁሳቁሶችን ጫኑ (ለምሳሌ: General Science)።
3️⃣ 5 የማወቅ ጉጉት የሞላባቸው ጥያቄዎችን ጠይቁ።

4️⃣ የጥናት መመሪያ እና በድምጽ የሚቀርብ ማጠቃለያ ፍጠሩ።
5️⃣ ለጓደኛችሁ ወይም ለመምህራችሁ አጋሩ።
6️⃣ አስቡና ገምግሙ፦ ምን አዲስ ሐሳብ አገኛችሁ? 🌟
══════════════

❤️ ለመምህራንና ለተማሪዎች የተላለፈ መልዕክት
ውድ ተማሪዎችና መምህራን፣
ትምህርት እየተለወጠ ነው። እናም ይህን ለውጥ እየመራችሁ ያላችሁት እናንተ ናችሁ። 🌍

🌟 ኤአይን (AI) ከፍላጎት ጋር ተጠቀሙበት።
💫 ልፋትን ሳይሆን ጠያቂነትን እንዲያነሳሳ ፍቀዱለት።
🌈 በዓላማ ተማሩ።
🔥 በድፍረት አልሙ።
🧠 ጥልቅ አስተሳሰብ ይኑራችሁ።
ትምህርት ሕያው፣ አስደሳች እና ሰብአዊነት የሰፈነበት እንዲሆን የሚያደርጉ ትምህርት ቤቶችን እንገንባ። 💖
የወደፊቱ ጊዜ ደርሷል
NotebookLM የመማሪያ መተግበሪያ ብቻ አይደለም፤ የትምህርት አብዮት ነው።
📚 መረጃን ወደ ምናብ፣ እና 💡 እውቀትን ወደ ጥበብ ይለውጣል።

🚀 መማር ቀጥሉ።
💪 መፍጠር ቀጥሉ።
💫 ማብራት ቀጥሉ።
ምክንያቱም የወደፊቱ ጊዜ የጠያቂ አእምሮዎች ነውና።


የNootebookLM አጠቃቀምን በቪድዮ ከታች እለቅላችኋለሁ።
══════════════
✍️ በረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል
ℛℯ𝓈𝒽𝒶𝒹 ℳ𝓊𝓏ℯ𝓂𝒾𝓁
Photo
💻 የኮምፒውተር ኪቦርድ ላይ የሚገኙት (F1-F12) ቁልፎች ድብቅ ሚስጥራት

ብዙ ጊዜ የኮምፒውተር ኪቦርድ ላይ ከላይ በኩል የተደረደሩትን (F1-F12) ቁልፎች ለድምፅ መጨመሪያ ወይም ለብሩህነት (Brightness) ማስተካከያ ብቻ ሲያገለግሉ ይስተዋላል። ነገር ግን እነዚህ ቁልፎች "Function Keys" ይባላሉ፤ ስራን በብልሃትና በፍጥነት ለመከወን የተሰሩ አቋራጭ መንገዶች ናቸው።

⚠️ ማሳሰቢያ: አንዳንድ ላፕቶፖች ላይ እነዚህን ቁልፎች ለመጠቀም Fn የሚለውን ቁልፍ ተጭኖ መጠቀም እንደሚያስፈልግ መዘንጋት የለበትም።

ከF1 እስከ F12 ያሉት ቁልፎች የሚሰጡት አገልግሎት በዝርዝር እነሆ፦

➊ F1 (እርዳታና ማስተካከያ)
◆ ከ Windows ቁልፍ ጋር በጋራ ሲጫኑ Help Menu ያመጣል።
◆ Excel እና Word ሲጠቀሙ ከ Ctrl ጋር በጋራ ሲጫኑ የላይኛውን የሪበን ሜኑ (Ribbon Menu) ይደብቃል ወይም መልሶ ያሳያል። ስክሪን ላይ ሰፊ የመጻፊያ ቦታ ለማግኘት ይጠቅማል።

F2 (ስም መቀየርና ማተም)
◆ የተመረጠን ፋይል ወይም ፎልደር ስም (Rename) በፍጥነት ለመቀየር ያገለግላል።
◆ በጣም ጠቃሚ: በ Word ውስጥ Ctrl + F2 ሲጫኑ የጽሁፉን ማተሚያ ቅድመ-እይታ (Print Preview) ያሳያል። ወረቀት ከማበላሸት ያድናል።

F3 (ፍለጋና ፊደል ቅያሪ)
◆ በ Windows Explorer ወይም በብራውዘሮች ላይ የፍለጋ (Search) ሳጥንን ይከፍታል።
◆ ልዩ ጥቅም: በ Word ላይ እንግሊዝኛ ሲጽፉ Shift + F3 በመጫን የፊደላትን ቅርጽ (Capital/Small letter) በፍጥነት ለመቀያየር ይረዳል። መደጋገም አያስፈልግም።

F4 (መዝጋትና መድገም)
Alt + F4 ማንኛውንም የተከፈተ መስኮት ይዘጋል (Shutdown ለማድረግም አማራጭ ያመጣል)።
◆ የባለሙያዎች ሚስጥር: በ Excel እና Word ላይ አንድ የሰሩትን ስራ ለመድገም (Repeat Action) ያገለግላል። ለምሳሌ፡ የአንድን ጽሁፍ ቀለም ቀይረው ቀጣዩንም ለመቀየር F4ን ብቻ መጫን በቂ ነው።

❺ F5 (ማደስ)
◆ የኢንተርኔት ገጽን ወይም የኮምፒውተር ፍጥነትን ለማደስ (Refresh) ያገለግላል።
◆ በ PowerPoint Slideshow ለማስጀመር ይጠቅማል።
◆ በ Microsoft Office ውስጥ አንድን ቃል ፈልጎ ለመቀየር (Find and Replace) ያመጣል።

F6 (ፈጣን ሽግግር)
◆ ኢንተርኔት ሲጠቀሙ ማውዝ ሳይነኩ ጠቋሚውን (Cursor) በቀጥታ ወደ አድራሻ መጻፊያው (Address bar) ይወስዳል።
Ctrl + F6 በ Word ላይ የተከፈቱ የተለያዩ ሰነዶች መካከል በፍጥነት ለመሸጋገር ይጠቅማል።

❼ F7 (የፊደል እርማት)
◆ በ Microsoft Word ላይ የፊደልና የሰዋሰው ስህተት (Spelling and Grammar check) ያደርጋል።
Shift + F7 ሲጫኑ ተመሳሳይ ትርጉም ያላቸውን ቃላት (Thesaurus) ይፈልጋል።

❽ F8 (Safe Mode)
◆ ኮምፒውተር ሲነሳ ችግር ካጋጠመ ወደ Safe Mode ለመግባት ያገለግላል።
◆ በ Excel ውስጥ የሴሎችን ምርጫ (Selection) ለማስፋት ይጠቅማል።

F9 (ማዘመን)
◆ በ Word ውስጥ ያሉ ፎርሙላዎችንና መረጃዎችን ያዘምናል።
◆ በ Outlook ውስጥ ኢሜይሎችን ለመላክና ለመቀበል (Send and Receive) ያገለግላል።

F10 (ራይት ክሊክ)
◆ የፕሮግራሞችን የሜኑ ባር (Menu bar) ለመክፈት ይጠቅማል።
◆ ልዩ ጥቅም: Shift + F10 ሲጫኑ ልክ ማውዙን "Right Click" እንዳደረጉ ይቆጠራል። ማውዝ በሌለበት ጊዜ ትልቅ አማራጭ ነው።

F11 (ሙሉ ስክሪን)
◆ ብራውዘር ሲጠቀሙ ምስሉን ሙሉ ስክሪን (Full Screen) ለማድረግና ለመመለስ ያገለግላል።
◆ በ Excel ላይ Shift + F11 ሲጫኑ አዲስ የስራ ወረቀት (New Sheet) ይጨምራል።

F12 (Save As)
◆ በ Word እና Excel ላይ የሰሩትን ፋይል በአዲስ ስም ወይም ቦታ ለመቆጠብ Save As የሚለውን ሳጥን በቀጥታ ያመጣል።
Ctrl + F12 የተቀመጠ ፋይል ለመክፈት (Open) ይረዳል።
እነዚህን አቋራጮች መልመድ የስራ ፍጥነትን ከመጨመሩም በላይ የኮምፒውተር አጠቃቀምን ዘመናዊ ያደርጋል። መረጃው ለሌሎችም እንዲደርስ ሼር በማድረግ እንተባበር!

✍️ በረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል
════════════════
📍 ለተጨማሪ የቴክኖሎጂ ምክሮች ቻናሉን ይቀላቀሉ

🌐 ዘመኑ #የቴክኖሎጂ ነው 📲 ከዘመኑ ጋር አብረው ይዘምኑ💻

Telegram: t.me/BasicComputer_Skills

Tiktok:
tiktok.com/@basiccomputerskills

Instagram:
instagram.com/basiccomputerskills

Umma Life:
ummalife.com/ReshadMuzemil
🤔1
Basic Computer Skills pinned «💻 የኮምፒውተር ኪቦርድ ላይ የሚገኙት (F1-F12) ቁልፎች ድብቅ ሚስጥራት ብዙ ጊዜ የኮምፒውተር ኪቦርድ ላይ ከላይ በኩል የተደረደሩትን (F1-F12) ቁልፎች ለድምፅ መጨመሪያ ወይም ለብሩህነት (Brightness) ማስተካከያ ብቻ ሲያገለግሉ ይስተዋላል። ነገር ግን እነዚህ ቁልፎች "Function Keys" ይባላሉ፤ ስራን በብልሃትና በፍጥነት ለመከወን የተሰሩ አቋራጭ መንገዶች ናቸው። ⚠️ ማሳሰቢያ:…»
📚 Addis Ababa City Administration Education Bureau 2026 G.C (2018 E.C)

📚 Grade 6 and 8 First Semester Model Exam Schedule


📚 የ6ኛ፣ የ8ኛ እና የ12 ክፍል ሞዴል ፈተና መስጫ የጊዜ ሰሌዳ 📚
════════════════
የ6ኛ ክፍል ሞዴል ፈተና ጥር 04-06/2018 E.C ይሰጣል።

የ8ኛ ክፍል ሞዴል ፈተና ጥር 04-05/2018 E.C ይሰጣል።

የ12ኛ ክፍል ሞዴል ፈተና ደግሞ ጥር 04-06/2018 E.C ይሰጣል።
3
Grade 7 1st Sem ICT & CTE Test 2 Table of Specifications.pdf
171.5 KB
📚 2018 E.C Grade 7 ICT and CTE 
የሙከራ ሁለት የፈተና ቢጋር (Table of Specification for Test 2)



 በተለይም የሙምታዝ ት/ቤት ተማሪዎች Test 2 የተዘጋጀው በዚህ መሠረት ስለሆነ ተጠቀሙበት።

አላህ ይርዳችሁ!!

✍️ ረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል
2
Grade 8 1st Sem. ICT and CTE Test 2 Table of Specifications.pdf
189.4 KB
📚 2018 E.C Grade 8 ICT and CTE 
የሙከራ ሁለት የፈተና ቢጋር (Table of Specification for Test 2)



 በተለይም የሙምታዝ ት/ቤት ተማሪዎች Test 2 የተዘጋጀው በዚህ መሠረት ስለሆነ ተጠቀሙበት።

አላህ ይርዳችሁ!!

✍️ ረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል
ከውድቀት_ወደ_ማማ፡_የሙምታዝ_ተማሪዎች_የታሪክ_አዲስ_ምዕራፍ.pdf
14.4 MB
☑️ ለሙምታዝ ትምህርት ቤት ለ7 ክፍል ተማሪዎች የተሰጠ ስልጠና


📚 ርዕስ፡ ከውድቀት ወደ ማማ! - የታሪክ አዲስ ምዕራፍ 🔥


ስላይድ ብዛት: 60 ስላይድ

ስልጠና: በረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል


በስልጠናው ሁሉም እንዲጠቀምበት ታስቦ የተጋራ።
🔥 ከውድቀት ወደ ማማ! - የታሪክ አዲስ ምዕራፍ 🔥
════════════════

ዛሬ በሙምታዝ አካዳሚ ከ7ኛ ክፍል ተማሪዎች ጋር በነበረን ቆይታ፤ በእያንዳንዱ ተማሪ ልብ ውስጥ የህሊና ደወል የሚሆን፣ የተኙትን የሚያነቃ፣ የጠፉትን የሚመልስና አቅጣጫን የሚያስተካክል እውነት ላይ ተወያይተናል። ይህ አብሮ ያያያዝነው የሥልጠና ሰነድ (PDF) ትውልድ ከተቀበለውና ከተገበረው ወደ ታላቅነት ማማ የሚወጣበትን የለውጥ እርምጃዎች ይዟል።

📜 የለውጥ ምዕራፎች

1️⃣ ምዕራፍ 1፡ መስተዋቱ (የነበርንበትና የደረስንበት)
ዛሬ በመስታወት ፊት ቁመን ራሳችንን የምንመረምርበት ቀን ነው። በ2017 የነበረው ትህትና፣ የመማር ጥማትና መከባበር በ2018 ለምን በረብሻና በዝንጋቴ ተተካ? ጌታችን አላህ በተከበረ ቃሉ እንዲህ ይላል፦
"አላህ በሰዎች ዘንድ ያለን (ጸጋ) በነፍሶቻቸው ያለን (ሁኔታ) እስከሚለውጡ ድረስ አይለውጥም።" (ሱረቱ አር-ረዕድ፡ 11)
የዛሬው ወጣት የነገው የኡማው ዋልታ ነው። ዋልታው ከበሰበሰ ቤቱ ይፈርሳል። "አድጌያለሁ፣ ማንም አይነካኝም" የሚል የውሸት ጀግንነት የውድቀት መጀመሪያ መሆኑን ተረድተን ወደ ቀድሞው ወርቃማ ማንነታችን የምንመለስበት ሰዓት አሁን ነው።

2️⃣ ምዕራፍ 2፡ ተማሪነት ከአላህ የተሰጠ ኒዕማ (የፍልስጤም ትምህርት)
ዛሬ እናንተ በሰላም አየር ስር ሆናችሁ፣ ወላጆቻችሁ መጽሐፍና ደብተር አሟልተውላችሁ፣ መምህራን ሊያስተምሯችሁ ቆመው እያለ ጊዜያችሁን ስታባክኑ፤ በሌላው ዓለም በተለይም በጋዛና በፍልስጤም የሚገኙ እኩዮቻችሁን አስቧቸው። እነሱ ትምህርት ቤታቸው በቦምብ ፈርሶ፣ መጽሐፎቻቸው በደም ተለውሰው፣ መምህራኖቻቸው ተሰውተውም እንኳ በድንኳንና በፍርስራሽ መካከል ሆነው እውቀትን ይፈልጋሉ።
እናንተ የተመቻቸላችሁን እድል ስታባክኑ በደምና በእንባ መማር የናፈቃቸውን ትውልዶች እየበደላችሁ ነው። አላህ የሰጣችሁን ይህን የዕውቀት ብርሃን ሸክም ሳይሆን፣ መላእክት ክንፋቸውን የሚያነጥፉለት ልዩ ስጦታ መሆኑን እወቁ። ይህን ጸጋ ማባከን በፈጣሪ ፊት በከፍተኛ ወንጀል ያስጠይቃል።

3️⃣ ምዕራፍ 3፡ አደብ (ስነ-ምግባር) - የእውቀት በር
"እውቀት ሞተር ነው፤ አደብ ደግሞ ብሬክ ነው።" ብሬክ የሌለው መኪና መጨረሻው ገደል እንደሆነ ሁሉ፣ አደብ የሌለው ተማሪም መጨረሻው ጥፋት ነው።
ታላቁ ሊቅ ኢማሙ ማሊክ (ረሂመሁላህ) እንዲህ ይላሉ፡- "ዕውቀትን ከመፈለግህ በፊት አደብን ተማር።" አደብ (ስነ-ምግባር) የሌለው ተማሪ ምንም ቢማር ፍሬ የለውም። መምህርን የሚያላግጥና የሚያቃልል ተማሪ የወደፊቱን ህይወቱን እያጨለመ ነው። በመምህራን ዱዓ እንጂ በቁጣቸው አትታጀቡ።

4️⃣ ምዕራፍ 4፡ የዘመኑ ፈተና (ዲጂታል እስር ቤት)
ስልካችን ውስጥ ያለው ቴሌግራም ጊዜያችንን የሚበላ "የኪስ ውስጥ እስር ቤት" ሊሆንብን አይገባም። በቴሌግራም ግሩፖች የምትጽፉት ስብዕና የጎደለው መልዕክት ነገ ይመሰክርባችኋል። ኢማሙ ሻፊዒ እንዳሉት፡- "ጊዜ ሰይፍ ነው፤ ካልቆረጥከው ይቆርጥሃል።" ዛሬ በከንቱ ወሬ የምታሳልፉት ሰዓት ነገ በፀፀት እሳት ያቃጥላችኋል። "ከመጥፎ ጓደኛ ብቸኝነት ይሻላል"ና የማንነት ሌባ ከሆኑ ጓደኞች ራሳችሁን አርቁ።

5️⃣ ምዕራፍ 5፡ የክብር አርማ (ለሴት ተማሪዎች)
ሂጃብ የአላህ ትዕዛዝ እንጂ የሰው ውሳኔ አይደለም። "አንተ ነቢዩ ሆይ! ለሚስቶቻችሁ፣ ለሴቶች ልጆችህም፣ ለምእምናን ሚስቶችም ከመከናነቢያዎቻቸው በላያቸው ላይ እንዲለቁ ንገራቸው..." (ሱረቱ አል-አህዛብ፡ 59)
ውድ እህታችን! አንቺ የነገዋ የኡማው እናት ነሽ። ሂጃብሽ ውበትሽና አላህ የሰጠሽ ንግስትነትሽ ነው። አርአያሽ እናታችን አይሻ (ረ.ዐ) ትሁን፤ ያለ ቀን ከእስልምና ያፈነገጠ አለባበስ ማንነትን መካድ ነው።

6️⃣ ምዕራፍ 6፡ የታላላቆች አርአያነት
የዛሬዎቹ የዓለማችን ታላላቅ ሊቃውንት እዚህ የደረሱት በተመቸ ህይወት አይደለም። ኢማሙ ቡኻሪ ለአንድ ሀዲስ ብቻ ወራትን በእግር ይጓዙ ነበር። ኢማሙ አህመድ ለእውቀት ሲሉ ግርፋትንና እስርን ታግሰዋል። ስኬት ያለ መስዋዕትነት አይገኝም። ሸይኩል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያህ እንዲህ ይላሉ፡- "ጠላቶቼ ምን ሊያደርጉኝ ይችላሉ? ጀነቴና አፀዴ በልቤ ውስጥ ናቸው፤ ቢገድሉኝ ሸህዳዬ ነው፣ ቢያስሩኝ ከጌታዬ ጋር የምገለልበት (ኸልዋ) ነው፣ ከአገሬ ቢያባርሩኝ ቱሪዝም (ሲያሃ) ነው።" ይህ ነው የዕውቀት ጥንካሬ!

7️⃣ ምዕራፍ 7፡ የመጸጸት ዋጋ (የመጨረሻው ማስጠንቀቂያ)
ዛሬ በትምህርት ማሾፍ፣ ነገ በህይወት መላገጥ ነው። ጊዜው ካለፈ በኋላ "ምነው በሰራሁ" ማለት ለቅሶ እንጂ መፍትሄ አይሆንም። አላህ በቁርአኑ እንዲህ ያስጠነቅቃል፦
"በደለኛ ሰው (በፀፀት) እጆቹን የሚነክስበትን ቀን (አስታውስ)፤ እንዲህም ይላል፡ 'ዋ ምኞቴ! ከመልዕክተኛው ጋር መንገድን በያዝኩ ኖሮ!'" (ሱረቱ አል-ፉርቃን፡ 27)
ዛሬ በስነ-ምግባር ብልሹነት ከትምህርት ቤት መሰናበት በህይወት ዘመን የማይሻር ጠባሳ ይጥላል። ሳይረፍድ ንቁ!

8️⃣ ምዕራፍ 8፡ አዲሱ ውሳኔና ቃልኪዳን
ያለፈው ስህተት ለወደፊቱ ትምህርት ይሁን። አላህ ወደ እርሱ ለሚመለሱ ሩህሩህ ነው። ዛሬ አዲስ ምዕራፍ የምንጀምርበት ቀን ነው። ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- "ከኃጢአቱ የተመለሰ (ተውበት ያደረገ) ሰው ልክ ኃጢአት እንደሌለው ሰው ነው።" (ኢብኑ ማጃህ ዘግበውታል)
በክፍል ውስጥ ጸጥታን በመጠበቅ፣ መምህርን በማክበርና የቤት ስራን በወቅቱ በመስራት ለራሳችን ቃል እንገባለን። "ለውጥ ከእኔ ይጀምራል!" ብለን እንነሳለን።

9️⃣ ምዕራፍ 9፡ የልብ መሳመሪያ (ዱዓ)
በመጨረሻም ይህ ሁሉ ጥረታችን በአላህ እርዳታ ይከናወን ዘንድ እጃችንን ዘርግተናል፡-
"ያ አላህ! በእነዚህ ተማሪዎች ልብ ውስጥ የእውቀትን ብርሃን አንግስ። ከቴክኖሎጂ ወጥመድና ከመጥፎ ጓደኛ ጠብቃቸው። ሴት እህቶቻችንን የክብር ባለቤት፣ ወንድ ልጆቻችንን የዲን ጋሻና የቤተሰብ መከታ አድርጋቸው። ዛሬ በዱዓ እንደሰበሰብከን ሁሉ ነገ በጀነት ይሰብስበን። አሚን!"


የምስጋና መዝጊያ:
ይህ ሥልጠና እውን እንዲሆንና ልጆቻችን የለውጥ ብርሃን እንዲያዩ ሁኔታዎችን ሁሉ በማመቻቸት ለደከሙት ለሙምታዝ አካዳሚ ዳይሬክተር ሚስተር ሙሐመድ ይማም የላቀ ምስጋናዬን አቀርባለሁ። እንዲሁም ለትምህርት ቤቱ አስተዳደር ሰራተኞች፣ ለሙሉ መምህራንና ለትምህርት ቤቱ ማህበረሰብ በሙሉ ለነበራችሁ ያልተቆጠበ ድጋፍና ለሥልጠናው መሳካት ላደረጋችሁት አስተዋጽኦ አላህ ጀዛችሁን ይክፈላችሁ። በኸይር ሥራችሁ ላይ ጽናቱን ይስጣችሁ።

ለለውጥ የተዘጋጃችሁና ቃል የገባችሁ የሙምታዝ የ7ኛ ክፍል ተማሪዎች... እናንተ የነገ የኡማው ኩራት ናችሁ!

🚀 ሙምታዝ፡ እውቀትን ከአደብ ጋር!

📚 በረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል

════════════════
⭕️ በስልጠናው ሁሉም ተማሪ እንዲጠቀምበት በሚል የተለጠፈ።

👇 የስልጠናውን ሙሉ ሰነድ (PDF) እዚህ ያውርዱ: 👇
👇 👇 👇

t.me/BasicComputer_Skills/2964
4
Truecaller v16.3.5 (Premium).apk
95.1 MB
Truecaller v16.3.5 (Premium).apk
👍2