Basic Computer Skills
1.85K subscribers
1.22K photos
100 videos
575 files
833 links
#በዚህ የቴሌግራም ቻናል
↪️ Programming
↪️ ቴክኖሎጂ ነክ ትምህርቶችን
↪️ ኮምፒውተር ነክ ትምህርቶችን
↪️Basic Computer Skills
↪️ Software
↪️ AI and AI Skills (Like ChatGPT)

ከላይ የተዘረዘሩትና ሌሎችም ገራሚ ትምህርቶች ይለቀቅበታል!

t.me/BasicComputerSkillsGroup

𝘽𝙮 𝙍𝙚𝙨𝙝𝙖𝙙
Download Telegram
#Update

የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ነገ ይፋ ይደረጋል።

የትምህርት ሚኒስቴር የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ነገ ይፋ እንደሚደረግ አሳውቋል።

የፈተና ውጤቱን አስመልክቶ ነገ ከቀኑ 10 ሰዓት ጀምሮ መግለጫ ይሰጣል።

#MoE
ከፍተኛ የተማሪ ቁጥር የት አለፈ ?

" ዘንድሮ 8.4 በመቶ ተማሪ ከ 50 በመቶ በላይ በማስመዝገብ ፈተናውን አልፏል " - ትምህርት ሚኒስቴር

የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ውጤት እየተገለጸ ይገኛል።

በዘንድሮ አመት ፈተናውን ከወሰዱ ተማሪዎች ውስጥ 8.4 በመቶ ተማሪ ከ 50 በመቶ በላይ በማስመዝገብ ፈተናውን አልፏል ተብሏል።

ከፍተኛ ተማሪዎችን ያሳለፉ ክልሎች ፦
- አዲስ አበባ፣
- ሐረሪ
- አማራ ክልል ናቸው።

ዘንድሮ " የተፈታኙ ቁጥር ቀንሷል ያለፈው ተማሪ ቁጥር ግን ጨምሯል " ያሉት ትምህርት ሚኒስትሩ ዘንድሮ በአጠቃላይ 48,929 ተማሪዎች ማለፋቸውን ገልጸዋል።

ባለፈው አመት ያለፈው ተማሪ ቁጥር 36,409 ነበር።

በጾታ ስብጥር
30,451 ወንድ ተማሪዎች አልፈዋል።
18,478 ሴት ተማሪ አልፏል።

በተፈጥሮ ሳይንስ ከፍተኛ ውጤት

ወንድ 591/600 ዶዶላ ኢፋ ቦሩ ትምህርት ቤት
ሴት 579/600 ብስራተ ገብርኤል ትምህርት ቤት

በማህበራዊ ሳይንስ
ወንድ 562/600 አምቦ አምቦ ቦርዲንግ ስኩል።
548 /600 ሴንት ጆሴፍ ትምህርት ቤት።

አማካይ ውጤት
87 በመቶ የአዳሪ ትምህርት ቤቶች
86 በመቶ ዓለማቀፍ ትምህርት ቤቶች
5.4 በመቶ የመንግስት ትምህርት ቤቶች
51 በመቶ የግል ትምህርት ቤት ውጤት

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
4
Grade 8 ICT Short PPT(2018 E.C Updated).pdf
34.7 MB
📚 Grade 8 ICT PPT (2018 E.C Updated)

📚 From Unit 1 through Unit 6 (Full)

Prepared by: Reshad Ibnu Muzemil
Slides:
313
Grade 8th CTE PPT (2018 E.C Updated).pdf
29.7 MB
📚 Grade 8 ICT Ppt (2018 E.C Updated)
From Unit 1 through Unit 7 (Full)
Slide: 281 Slides
Prepared by: Reshad Ibnu Muzemil
1
Grade 7 ICT PPT(2018 E.C Updated).pdf
27.4 MB
📚 Grade 7 ICT PPT (2018 E.C Updated)

📚 From Unit 1 through Unit 6 (Full)

Prepared by: Reshad Ibnu Muzemil
Slides:
248
Grade 7th CTE PPT (2018 E.C Updated).pdf
31.6 MB
📚 Grade 7 CTE PPT (2018 E.C Updated)

📚 From Unit 1 through Unit 8 (Full)

Prepared by: Reshad Ibnu Muzemil
Slides:
284

══════════════
🀄🀄ሉን👇👇👇 share👇

Join our channel

t.me/Grade1_4Info

t.me/Grade5and6Info

t.me/Grade7Info

t.me/Grade8Info

t.me/Grade9Info

t.me/Grade10Info

t.me/BasicComputer_Skills
2
Basic Computer Skills
Grade 7th CTE PPT (2018 E.C Updated).pdf
📚 ለ7ኛ እና ለ8ኛ ክፍሎች 📚

● የኮምፒውተርንና የሙያ ትምህርትን (CTE) ዓለምን እንቃኛለን!

ውድ ተማሪዎች (እህትና ወንድሞቼ)

ለወደፊት ህይወታችሁ ትልቅ ስንቅ የሚሆን እጅግ በጣም ጠቃሚ እውቀትን እንድታገኙ በሚል ። የኮምፒውተር ክህሎቶችን እና የሙያ ትምህርትን (CTE) ከነሙሉ ዝርዝራቸው የምትማሩበት አጭር እና ግልጽ የPowerPoint አቀራረብ ይዘን ቀርበናል።


🎯 የምታገኙት ጥቅም:

እያንዳንዱ ክፍል "Easy Tips" በሚል ርዕሱን በቀላሉ ለመረዳት የሚያስችሉ ጠቃሚ እና አጫጭር ነጥቦችን ያካትታል።
ከእያንዳንዱ ርዕስ ጋር ተያይዘው የሚቀርቡት ማራኪ ምስሎች ትምህርቱን የበለጠ ሳቢ እና በቀላሉ ለመረዳት የሚያስችል ነው።
በዚህ አቀራረብ ላይ የሚገኙት አብዛኛዎቹ ምስሎች በዘመናዊው የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) መሳሪያ በሆነው ChatGPT የተፈጠሩ ናቸው። ይህም የቴክኖሎጂን እድገት እንድትረዱና የወደፊቱን ዓለም እንድታዩት ያግዛችኋል።

ወደፊት ለመራመድ ጊዜው አሁን ነው!

🎯 ይህ PowerPoint ለእናንተ የተዘጋጀ ጠቃሚ የመማሪያ መሳሪያ ነው።
📚 የዛሬው ጠንካራ ጥረታችሁ እና እርምጃችሁ ነገ ትልቅ ስኬት እንድታስመዘግቡ ያግዛችኋል።
📚 የኮምፒውተር እውቀት ለወደፊት ህልማችሁ ክንፍ እንደሚሰጥ አስታውሱ።
════════════════
📚 ጠንካራ ተስፋዎቻችን የህልሞቻችን ክንፎች ናቸው!
📚 የዛሬ እርምጃዎቻችን የነገ ስኬቶቻችን ናቸው!

✍️ በረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል
2
#Tech_tip

ከዚህ ቀደም ስልክ ላይ ለምታዘወትሩ ሰዎች eye care/eye protection mode እንድታበሩ ስለዚህ feature አንዳንድ ነገሮችን አጋርተናችሁ ነበር። ታዲያ ይህንን feature window computer ላይ መጠቀም እንችላለን።

ወደ windows + i በመጫን አልያም በሌላ መንገድ setting ከከፈትን በኋላ system>display >Night light settings እዚህ ላይ Turn on now የሚለውን በመንካት ይህንን on ማድረግ፤ strength ከሚለው ስር ያለውን የሚለውን በመጨር እና በመቀነስ ድምቀቱን መጨመር እና መቀነስ እንችላለን።

ይህ feature ላፕቶፓችሁ ላይ ብዙ ሰዓት ለምታሳልፉ ሊጠቅማችሁ ይችላል።

©bighabesha
3
Grade 3 and 4 ICT (2018 E.C).pdf
1 MB
ICT Reference Book

📚 Grade 3 and 4 // and 1-6 Students
Page: 117 Pages
✍️ Prepared by: Reshad Ibnu Muzemil
Basic Computer Skills
Grade 3 and 4 ICT (2018 E.C).pdf
🌎 ወደ አስደናቂው የቴክኖሎጂ ዓለም እንኳን በደህና መጣችሁ!

📚 ውድ ተማሪዎች፣

ይህ ያዘጋጀሁላችሁ የICT የመማሪያ መጽሐፍ፣ የነገውን ዓለም ቋንቋ በቀላሉና በደስታ እንድትማሩበት የተዘጋጀ ልዩ ቁልፍ ነው!

መጽሐፉ በዋናነት ለ3ኛ እና 4ኛ ክፍል ተማሪዎች ታስቦ የተዘጋጀ ቢሆንም፣ አስደናቂ ብቃቱ ከ1ኛ እስከ 6ኛ ክፍል ያሉትን ሁሉንም የቴክኖሎጂ ጀግኖች ያካትታል!

ለታናናሾች (1ኛ እና 2ኛ ክፍል) ይህ መጽሐፍ ወደ ቴክኖሎጂ የምትገቡበት የመጀመሪያውና አስደሳች በር ይሆናችኋል።
ለ3ኛ እና 4ኛ ክፍል ተማሪዎች ደግሞ ፍቱን መመሪያችሁ ነው።
ትልልቆቹ (5ኛ እና 6ኛ ክፍል) ደግሞ መሰረታችሁን ይበልጥ የምታጠነክሩበትና እውቀታችሁን የምታሳድጉበት ምርጥ አጋር ይሆንላችኋል።

በዚህ መጽሐፍ ውስጥ በምናደርገው አስደሳች ጉዞ፡
➊ ከኮምፒውተር ጋር ትተዋወቃላችሁ፦ ኮምፒውተር ምንድን ነው? ለምን ይጠቅማል? ከየት መጣ? ምን አይነት አይነቶች አሉት? እንዴትስ በጥንቃቄ መያዝ አለብን? የሚሉትን መሰረታዊ ጥያቄዎች እየተዝናናችሁ ትማራላችሁ።

❷ የኮምፒውተርን አካላት ትለያላችሁ፦ ልክ እንደ ሰውነት ክፍሎች ሁሉ፣ ኮምፒውተርም የተለያዩ ክፍሎች አሉት። መረጃ የምናስገባባቸውን (Input)፣ የምናይባቸውንና የምንሰማባቸውን (Output) እንዲሁም መረጃ የምናስቀምጥባቸውን (Storage) መሳሪያዎች በቀላሉ ትለያላችሁ። በተጨማሪም ኮምፒውተርን እንዴት በአስተማማኝ ሁኔታ ማስነሳትና መዝጋት እንደምትችሉ ትለማመዳላችሁ።

➌ የኮምፒውተርን አለም ትቆጣጠራላችሁ፦ ዴስክቶፕን፣ ኪቦርድን እና ማውዝን በመጠቀም ኮምፒውተርን እንደፈለጋችሁ ማዘዝ ትጀምራላችሁ። ከዚያም ቀስ በቀስ እንደ ማይክሮሶፍት ወርድ (Microsoft Word) ያሉ መተግበሪያዎችን ተጠቅማችሁ መጻፍ፣ በፓወርፖይንት (PowerPoint) አስደሳች የዝግጅት ስራዎችን መስራት፣ እንዲሁም በኤክሴል (Excel) ቁጥሮችን ማደራጀት ትማራላችሁ።

❹ ከኮምፒውተርም ባሻገር ትጓዛላችሁ፦ ፋይሎችን እንዴት ማደራጀትና ማግኘት እንደምትችሉ፣ ስለ ኢንተርኔትና ኢሜይል መሰረታዊ እውቀት፣ ስለ መልቲሚዲያ (ምስልና ድምጽ) እንዲሁም በMSW-LOGO የመጀመሪያ የፕሮግራሚንግ ትዕዛዞችን መጻፍ ትጀምራላችሁ።

❺ የወደፊቱን ቴክኖሎጂ ትቀምሳላችሁ፦ በመጨረሻም፣ እንደ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) እና ቻትጂፒቲ (ChatGPT) ያሉትን አዳዲስና አስገራሚ ቴክኖሎጂዎች እናስተዋውቃችኋለን። እነዚህ ቴክኖሎጂዎች ምን ያህል ጠቃሚ እንደሆኑ እና እንዴት በጥንቃቄ ልንጠቀምባቸው እንደሚገባ እንማራለን።

📚 ይህ አስደናቂ ጉዟችን በ15 አጓጊ ምዕራፎች ተከፋፍሎ የቀረበ ሲሆን፣ እያንዳንዱን ምዕራፍ በሁለት ሳምንታት ጊዜ ውስጥ እየተዝናናችሁና በደንብ እየተረዳችሁ ትጨርሳላችሁ። ይህ አደረጃጀት ትምህርቱን ሳትሰላቹና ጫና ሳይበዛባችሁ፣ እውቀታችሁን ደረጃ በደረጃ እንድትገነቡ ታስቦ የተዘጋጀ ነው!

📧 ከዚህም በተጨማሪ፣ መጽሐፉ በውስጡ ከእውነተኛው ዓለም የተወሰዱ ምሳሌዎችን፣ አዝናኝ የተግባር ልምምዶችን፣ የተማራችሁትን የምትፈትሹባቸው ጥያቄዎችን እና የፈጠራ ችሎታችሁን የምታሳዩባቸው የፕሮጀክት ስራዎችን ይዟል። ይህም ትምህርቱን ተግባራዊ፣ አሳታፊ እና ለሁሉም ዕድሜ ተስማሚ ያደርገዋል።

አስታውሱ! ይህ መጽሐፍ የመማሪያ ብቻ ሳይሆን፣ ወደፊት ለምትፈጥሩት አስደናቂ ነገር ሁሉ የመጀመሪያው እርምጃችሁ ነው። በድፍረት ገጾቹን ግለጡ፣ አዲስ ነገር ለመማር ሁሌም ዝግጁ ሁኑ፣ እናም በቴክኖሎጂው ዓለም የራሳችሁን አሻራ ለማሳረፍ ተዘጋጁ!
መልካም የትምህርት ዘመን!

════════════════
ትውልዱን አንውቀሰው፤ ይልቁንስ ለወደፊቱ እናስታጥቀው። የዛሬ ዝግጅት የነገው ማንነቱ መሰረት ነው።

አዎ! ትውልዱ ላይ የትችት ድንጋይ ከመወርወር፣ የነገ ህይወቱን የሚሻገርበትን የእውቀት ድልድይ እንገንባለት።
════════════════

📚 ✍️ አዘጋጅ: ረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል

════════════════
📚 ጠንካራ ተስፋዎቻችን የህልሞቻችን ክንፎች ናቸው!
📚 የዛሬ እርምጃዎቻችን የነገ ስኬቶቻችን ናቸው!
4
ከ1ኛ ክፍል ክስከ 10ኛ ክፍል ያሉ የተማሪ መፅሀፎችን ፈልጋችሁ ያጣችሁ ካላችሁ፡ ከታች የለውን #የቴሌግራም_ማስፈንጠሪያ (Link) በመንካት ማግኘት ትችላላችሁ።

📚 Grade 1 Students Textbook 👇👇

https://t.me/Grade1_4Info/431?single

📚 Grade 2 Students Textbook 👇👇

https://t.me/Grade1_4Info/437?single

📚 Grade 3 Students Textbook  👇👇

https://t.me/Grade1_4Info/409?single

📚 Grade 4 Students Textbook  👇👇

https://t.me/Grade1_4Info/401?single

📚 Grade 5 Students Textbook 👇👇

https://t.me/Grade5and6Info/689?single

📚 Grade 6 Students Textbook  👇👇

https://t.me/Grade5and6Info/838?single

📚 Grade 7 Students Textbook 👇👇

https://t.me/Grade7Info/783?single

Grade 8 Students Textbook 👇👇

https://t.me/Grade8Info/2032?single

📚 Grade 9 Students Textbook 👇👇

https://t.me/Grade9Info/528?single

📚 Grade 10 Students Textbook 👇👇

https://t.me/Grade10Info/8
════════════════
ትውልዱን አንውቀሰው፤ ይልቁንስ ለወደፊቱ እናስታጥቀው። የዛሬ ዝግጅት የነገው ማንነቱ መሰረት ነው።

አዎ! ትውልዱ ላይ የትችት ድንጋይ ከመወርወር፣ የነገ ህይወቱን የሚሻገርበትን የእውቀት ድልድይ እንገንባለት።
════════════════
📚 ጠንካራ ተስፋዎቻችን የህልሞቻችን ክንፎች ናቸው!
📚 የዛሬ እርምጃዎቻችን የነገ ስኬቶቻችን ናቸው!
════════════════
✍️ በረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል
👍3
📚 Study Time Table for Grade 6 Students


Evening = Grade 6
Morning = Grade 5

ከ5ኛ እና ከ6ኛ ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ርዕሶች አብራችሁ አንድ ላይ አንብቧቸው።

▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
አላህ ይርዳችሁ!! 🤲🤲


አዘጋጅ: ረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል
3
📚 Study Time Table for Grade 8 Students

Evening = Grade 8
Morning = Grade 7


ከ7ኛ እና ከ8ኛ ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ርዕሶች አብራችሁ አንድ ላይ አንብቧቸው
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
አላህ ይርዳችሁ!! 🤲🤲

አዘጋጅ: ረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል
4
ተማሪዎች እየበረታችሁ ነው?

በርቱ አላህ ያግዛችሁ። ወደፊት ብዙ እድል ይጠብቃችኋል። ከእናንተ ብዙ መልካም ነገር ይጠበቃል!

አላህ ይርዳችሁ! 🤲 🤲 🤲
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
ከዚህ ጋር በተያያዘ አጠር ያለች አነቃቂ፣ አበረታች፣ ለወደፊት ስኬት ለመዘጋጀት ሰበብ የምትሆን ፅሁፍ ይዤላችሁ እመጣለሁ።

ዝግጁ የሆናችሁ ❤️ ወይ 👍 ተጫኑ!!
7👍2