Basic Computer Skills
1.89K subscribers
1.22K photos
100 videos
576 files
833 links
#በዚህ የቴሌግራም ቻናል
↪️ Programming
↪️ ቴክኖሎጂ ነክ ትምህርቶችን
↪️ ኮምፒውተር ነክ ትምህርቶችን
↪️Basic Computer Skills
↪️ Software
↪️ AI and AI Skills (Like ChatGPT)

ከላይ የተዘረዘሩትና ሌሎችም ገራሚ ትምህርቶች ይለቀቅበታል!

t.me/BasicComputerSkillsGroup

𝘽𝙮 𝙍𝙚𝙨𝙝𝙖𝙙
Download Telegram
Python ለመማር አስባችሁ ከሆነ አልያም ገና እየጀመራችሁ ከሆነ እነዚህን ድረገጾች ሞክሯቸው።

https://www.programiz.com/python-programming
በቀላል አገላለፅ እና በቀላል ምሳሌ python መማር ያስችላል።

https://www.w3schools.com/python/
አብዛኞቻችሁ ታውቁታላችሁ ለጀማሪ የሚሆን ትምህርት በሚገባ ታገኙበታላችሁ። ከpython በተጨማሪም ሌሎች programming languages መማር ትችላላችሁ።

https://docs.python.org/3/tutorial/
የpython official documentation የምታገኙበት ሲሆን። አገላለፁ ትንሽ ጠጠር ስለሚል ቅድሚያ የpythone basic ብታጠኑ ይመረጣል።

https://www.geeksforgeeks.org/python/python-lists/
ከቀላል እስከ ከባድ የpython tutorial የምታገኙበት ድረገጽ ነው።

©bighabesha
4👍2
📩 Ethiocoders ማማር የጀመራችሁ እስቲ እጃችሁን አንሱ!

1. አልተማርኩም 👎

2. ተምሬ ሰርተፊኬት አግቻለሁ ❤️

3. እየተማርኩ ነው 👍

4. ስለምትለው Ethiocoders ምንም አላውቅም 😭
#ChatGpt

ChatGpt study and learn (study mode) የተሰኘና ተማሪዎችን ይበልጥ ተጠቃሚ የሚያደርግ feature አስተዋወቀ።

ይህም ጥያቄ ሲጠየቅ ቀጥታ መልሱን ከመስጠት ይልቅ step by step እኛንም በመሃል እየጠየቀን explain ያደርግልናል።

ተማሪዎች study modeን የቤት ስራ በሚሰሩበት ጊዜ፣ ለፈተና በሚዘጋጁበት ጊዜ እና ስለ አዳዲስ ነገሮች ማወቅ ሲሹ ቢጠቀሙ ውጤታማ እንደሚሆኑ ተመላክቷል።

study mode አሁን ላይ ለ free, pro እና ለplus ተጠቃሚዎች Available ነው። ተጠቃሚዎችም website ላይ tools የሚለውን ከነኩ በኋላ study and learn የሚለውን በመምረጥ እና በአፕሊኬሽን ደግሞ የፎቶ icon ከነኩ በኋላ study and learn የሚለውን በመምረጥ ይህንን feature መጠቀም ይችላሉ።

©bighabesha
6👍1
🎓 A Fearless Mind and Heart can Communicate Fearlessly!
════════════════
🎓 ፍርሃት የሌለበት አዕምሮ እና ልብ ያለ ፍርሃት ይግባባሉ!!
════════════════
⭕️ ለዚህ ደግሞ:- ሁሌም አዲስ ነገር መማር፣ ተስፋ አለመቁረጥ፤ ሁሌም መሞከር... በጣም አስፈላጊ ነው።

✍️ Reshad Ibnu Muzemil
#እንድታውቁት

ethiocoders (udacity) ላይ ተምራችሁ ሰርተፍኬስ ልትቀበሉ ስትሉ ሰርተፍኬት ካልሰጣትሁ የትምህርት ማጠናቀቂያው ቀነ ገደቡ አልፏል ማለት ነው።

ለአንድ course 8 ሳምንት ሲሆን የሚሰጣችሁ። በዚህ ጊዜ ውስጥ ካላጠናቀቃችሁ ሰርተፍኬት ላታገኙ ትችላላችሁ። ነገር ግን 8 ሳምንት ሳይሞላ ትምህርታችሁን መጨረስ ትችላላችሁ።

ትምህርቱን የጀመራችሁበትን ቀን ለማወቅ ከፈለጋችሁ በምስሉ ላይ እንደምትመለከቱት ወደ transcript በመግባት Enrolled on ከሚለው አጠገብ መመልከት ትችላላችሁ።

©bighabesha
👍4
OpenAI በጣም ፈጣንና powerful ነው የተባለለትን GPT 5 ማስተዋወቁ ይታወቃል።

ድረገፆችን እና መተግበሪያዎችን በአንድ prompt መስራት የሚችለው ይህ ሞዴል ከበድ ያሉ ጥያቄዎችን ማሰላሰል እና መመለስ ይችላል።

ይህ ሞዴል እንደ Gpt 4o ካሉት ሞዴሎች ጋር ሲነፃፀር እጅግ የተሻለ ሲሆን ከዚህ በፊት ያደረገውን ምልልስ የማስታወስ ችሎታውም ከሌሎቹ አንፃር የተሻለ ነው።

ይህን ሞዴል በነፃ መጠቀም ትችላላችሁ ነገር ግን የ5 ሰዐት ገደብ አለው።
አፕሊኬሽኑን update አድርጋችሁ መሞከር ትችላላችሁ።
Basic Computer Skills
Photo
📚 ጠንካራ ተስፋዎች የህልሞቻችን ክንፎች ናቸው!

ተስፋ የሰው ልብ ውስጥ ሲበቅል እንደ ትንንሽ ዘር ይጀምራል። ነገር ግን ይህ ትንንሽ ዘር እንዲበቅል በግንባር ጠንካራ እና በትክክል እንክብካቤ ያስፈልገዋል። ተስፋ ያለው ሰው ምን ያህል ችግር ቢያጋጥመው እንኳን በህልም መንገዱ አይቆምም።

ተስፋ ህልምን ለማሳካት የሚረዳን ኃይል ነው፣ እና ያለ ተስፋ ህልም እንደ ቀላል ብናኝ በግድግዳ ላይ የተቀረ ነው፤ ያለ እንቅስቃሴ እና እድገት ደግሞ ዝም ብሎ በባድ መኖር በቁም መሞት ነው።

ውድ ተማሪዎች ሆይ፣ ዛሬ ያላችሁን ትንሽ ህልም አትናቁት። ትንሹ ህልማችሁ በሰው ልብ ውስጥ ከተሰወረ፤ ትክክለኛ አቅጣጫ እምነት እና ትጋት በተሞላበት ሙከራ በጊዜ የማይታመን አስደናቂ ውጤት ያመጣል።

📚 የዛሬ እርምጃዎቻችን የነገ ስኬቶቻችን ናቸው!

እኛ በዛሬ የምናደርገው ነገር እንደ መጀመሪያ ዘር ነው። በሙሉ ልብ የምንተክለው "ዛሬ" ነገ ደግሞ ታላቅ ዛፍ ይሆናል። በዛሬ ላይ ያለን ጥረት (የምናደርገው ሙከራ) ለኛም ሆነ ለሌሎች ላይታይ ይችላል፣ ግን ጊዜው እየነጎደ ጥረታችንም እየፏፏ ይመጣና በቅፅበት የስኬታችን እርሻ ፍሬ ያፈራል፣ ያብባል።

እናንተ ተማሪዎች፣ ዛሬ በትምህርታችሁ ላይ በምታደርጉት ጥረት በቀጣዩ ዓመት ከአምላካችሁ እርዳታ ጋር ምን ያህል ለውጥና ስኬት ሊያመጣ እንደሚችል አስቡ። የአሁኑን ጥረታችሁን አሁኑኑ አይታይም፣ እናንተም ጥረታችሁን አጧጡፉ እንጂ አትቸኩሉ። ነነገ የምታዩት ስኬት "ዛሬ" በትክክል የተወሰደ እርምጃ ነው (በአላህ እርዳታ ተስፋ-አለመቁረጥ የታከለበት የልፋታችሁ ውጤት ነው።


እናም ውድ ወንድምና እህቶቼ (ተማሪዎቼ)

➊ ትኩረት አድርጉ:– በምትማሩት ትምህርት ላይ ትኩረታችሁ እየጨመረ ሲሄድ ወደ ስኬት ጉዞአችሁ መራመድ ትጀምራላችሁ። በዚህ ስኬት ጉዞ ሌሎችንም አብሯችሁ እንዲራመዱ እድሉን ታመቻቻላችሁ።

❷ ጊዜን በአግባቡ ተጠቀሙ – የዛሬውን ጊዜናችሁን ለነገ ስኬታችሁ ምክንያት እንዲሆን አድርጋችሁ ተጠቀሙበት።

➌ በትዕግሥት ጠብቁ:– ሁሉም ነገር በአላህ እርዳታ በጊዜው ይሆናል! የሆነ ዘርን ዘርተን እስከሚያፈራ ድረስ በትዕግስት እንደምንጠብቀው ሁሉ ዛሬ የምታደርጉት ጥረት ውጤቱ ለምን በቅፅበት አልታየንም አትበሉ።

❹ ተስፋን አትቁረጡ:– የምትችሉትን ከጣራችሁ በኋላም፣ ደጋግማችሁ ከሞከራችሁም በኋላ የሆነ ነገር ላይሳካ ይችላል ነገር ግን ተስፋ ፈፅሞ አትቁረጡ፤ ተስፋ ያለው ሰው መንገድ ያገኛል። "ህይወትህን እጣ እንጂ ተስፋ እንዳታጣ" ይላሉ ቱርኮች!!

📚 ደጋግሞ ወድቆ ደጋግሞ ሳይነሳ ከፍ ብሎ የሚበር የለም!

🌱 በመጨረሻም:

በህይወት መንገድ ላይ የምንወስዳቸው እርምጃዎች ሁሉ ለወደፊታችን መሠረት ናቸው። ዛሬ የምንተክለው ትንንሽ ዘሮች ትክክለኛውን እንክብካቤ ካገኙ በአላህ እርዳታ ነገ ብዙ ጣፋጭ ፍሬዎችን የያዘ ትልቅ የፍራፍሬ ዛፍ መሆናቸው አይቀሬ ነው። ህልምና ተስፋ እንዲሁም "በዛሬ" ላይ በምናደርገው ጥረት ነገ የምንፈልገውን ህልም ሁሉ ማሳካት እንችላለን።

⭕️ አዎ! ጠንካራ ተስፋዎች የህልሞቻችን ክንፎች ናቸው! የዛሬ እርምጃዎቻችን ደግሞ የነገ ስኬቶቻችን ናቸው!

✍️ በረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል
👍2
#telegram_update

ቴሌግራም ሰሞኑን አዳዲስ ማሻሻያዎችን ያደረገ ሲሆን ከነዚህም መካከል፦

Public post search
search tab ላይ አዲስ posts የሚል tab የተጨመረ ሲሆን ይህም public channel ላይ የሚገኙ ነገሮችን search ማድረግ ያስችለናል። ከዚህ በፊት አንድን መረጃ search በምናደርግበት ጊዜ የቻናሉ ስም አልያም እኛ join ካደረግናቸው ቻናሎች ያለን መረጃ ነበር የሚያሳየን ነገር ግን posts ላይ search ስናደርግ አለም አቀፍ ካሉ ቻናሎች ላይ search results/ውጤቶችን ያሳየናል።
ይህ feature አሁን ላይ ክፍት የሆነው ለቴሌግራም ፕሪሚየም ተጠቃሚዎች ነው።

Story Albums
የቴሌግራም ቻቶቻችንን channel, group, bots እያልን እንደምንከፋፍለው post ያደረግናቸውንም stories በአልበም መሰነድ የሚያስችለን feature ነው። ይህንንም ለማድረግ ጥግ ጋር ያለውን ሶስት ነጥብ ነክተን ወደ my profile መግባት>  album ውስጥ ማስገባት የምንፈልገውን story ጫን አድርገን መያዝ > add to folder>  new folder> የፈለጋችሁት ስም መሰየም።

Profile Rating
ቴሌግራም ፕሮፋይል ላይ ቁጥር(ደረጃ) የሚያሳይ አዲስ badge የተጨመረ ሲሆን ይህም የቴሌግራም starን በመጠቀም የተደረገውን transaction የሚያሳይ ይሆናል። በተጨማሪም telegram ሌሎች ማሻሻያዎችን የጨመረ ሲሆን telegram መተግበሪያችሁን update በማድረግ መጠቀም ትችላላችሁ።

©bighabesha
4
#tech_tip

Instagram ላይ ሳታስቡት ብዙ ጊዜያችሁን የምታጠፉ ከሆነ ይህንን setting ሞክሩት።

ፕሮፋይላችሁ ላይ ከገባችሁ በኋላ ሶስት ሰረዙን በመንካት Your activity ውስጥ ትገባላችሁ። ታች ላይ time spent የሚል ታገኛላችሁ። ይህም ዛሬ instagram ላይ ያጠፋችሁን ሰዓት ያሳያችኋል።

በተጨማሪም daily limit የሚለውን በመንካት ሰዓት መሙላትና የሞላችሁት ሰዓት ሲደርስ እንዲያስታውሳችሁ ማድረግ እንዲሁም sleeep mode on በማድረግ ሰዓትና ቀን በመሙላት በዛ ሰዓት notification እንዳይደርሳችሁ ማድረግ ትችላላችሁ።

©bighabesha
══════════════

🀄🀄ሉን👇👇👇 share👇

Join our channel

t.me/Grade1_4Info

t.me/Grade5and6Info

t.me/Grade7Info

t.me/Grade8Info

t.me/Grade9Info

t.me/Grade10Info

t.me/BasicComputer_Skills
#እንድታውቁት

⭕️ ከዚህ በፊት ቴሌግራም አካውንታችንን ካልተጠቀምን በራሱ አካውንቱን የሚያጠፋበት የጊዜ ገደብ ከፍተኛው 12 ወር (1 አመት) የነበረ ሲሆን አሁን ላይ ግን ወደ 24 ወር (2 አመት) ከፍ ብሏል።

ይህም እስከ 2 አመት ድረስ ወደ አካውንታችሁ ካልተመለሳችሁ ወይም አካውንታችሁን ካልተጠቀማችሁት አካውንታችሁን ሳይጠፋ ልታገኙት ትችላላችሁ።

📚 ይህንንም ለማድረግ <setting> privacy and security> if away for የሚለውን በመንካት እናንተ የፈለጋችሁትን የወር መጠን መምረጥ።


══════════════

🀄🀄ሉን👇👇👇 share👇

Join our channel

t.me/Grade1_4Info

t.me/Grade5and6Info

t.me/Grade7Info

t.me/Grade8Info

t.me/Grade9Info

t.me/Grade10Info

t.me/BasicComputer_Skills
5
══════════════
🀄🀄ሉን👇👇👇 share👇

Join our channel

t.me/Grade1_4Info

t.me/Grade5and6Info

t.me/Grade7Info

t.me/Grade8Info

t.me/Grade9Info

t.me/Grade10Info

t.me/BasicComputer_Skills
3
Hardware Components' Tips
2
Easy Tips

Input Devices

══════════════
🀄🀄ሉን👇👇👇 share👇

Join our channel

t.me/Grade1_4Info

t.me/Grade5and6Info

t.me/Grade7Info

t.me/Grade8Info

t.me/Grade9Info

t.me/Grade10Info

t.me/BasicComputer_Skills