ℛℯ𝓈𝒽𝒶𝒹 ℳ𝓊𝓏ℯ𝓂𝒾𝓁
Photo
☑ የተፈጠረው ምስል አይነት (Nature of the Image):
☑ ሙሉ እና ህይወት ያለው ምስል፡ ነፍስ ያለው ፍጡርን (ሰው ወይም እንስሳ) ሙሉ አካሉን እና ህይወት ሊኖረው በሚችል መልኩ መፍጠር ከላይ በተጠቀሰው ሐዲሥ መሰረት የተከለከለ ይሆናል። ይህ የአላህን ፈጠራ የማስመሰል ገጽታ ስላለው ነው።
☑ ያልተሟላ ምስል፡ የሰው ወይም የእንስሳ ምስል ነገር ግን ጭንቅላት የሌለው፣ ከወገብ በላይ ብቻ የሆነ፣ ወይም ህይወት ለመቀጠል ወሳኝ የሆነ አካሉ የጎደለው እንዲሆን አድርጎ መፍጠር የተፈቀደ ሊሆን ይችላል።
☑ግዑዝ ነገሮች፡ የህንፃዎች፣ የተፈጥሮ ገጽታዎች፣ መኪናዎች፣ ወይም ምናባዊ ንድፎችን (abstract art) በ AI መፍጠር ሙሉ በሙሉ የተፈቀደ ነው።
☑ የአጠቃቀም አላማ:
ትምህርታዊ እና ሳይንሳዊ ፍላጎቶች፡ ለህክምና፣ ለደህንነት፣ ለትምህርት እና ለሌሎች አስፈላጊ እና ጠቃሚ ለሆኑ ጉዳዮች ምስሎችን መጠቀም በእስልምና (الضرورات تبيح المحظورات) በሚለው መርህ ስር ሊታይ ይችላል።
☑ ለመዝናኛ እና ላልተገባ አላማ፡ ስሜትን የሚቀሰቅሱ፣ ጸያፍ፣ ወይም የሌሎችን ክብር የሚያጎድፉ ምስሎችን መፍጠር በማንኛውም መንገድ የተከለከለ ነው።
☑ ያለውን ምስል ማሻሻል (Modifying Existing Images):
አንድን በካሜራ የተነሳ ፎቶግራፍ ወደ ካርቱን ወይም ስዕል መቀየር፣ ምስሉ ሙሉ እና ህይወት ያለው ከሆነ፣ እንደ አዲስ መሳል ስለሚቆጠር ክልከላው ይመለከተዋል። ነገር ግን ፎቶውን በማሻሻል ያልተሟላ ምስል እንዲሆን ማድረግ (ለምሳሌ: ጭንቅላቱን ማስወገድ ወይም ወደ ረቂቅ ጥበብ መቀየር) ይፈቀዳል።
⬅️ ሲጠቃለል፦
የሰው ሰራሽ የማሰብ ችሎታ (AI) በራሱ ሐላልም ሐራምም አይደለም፤ እሱ መሳሪያ ነው። ብይኑ የሚወሰነው በአጠቃቀማችን ነው። አንዳንድ ሰዎች «ሸሪዓ የቴክኖሎጂን አሠራር ባለመረዳት ይከለክላል!» ብለው ሊያስቡ ይችላሉ። ይህ ስህተት ነው። የእስልምና ህግጋት የተመሰረቱት በማይለወጡ መለኮታዊ መርሆዎች ላይ ነው። ሊቃውንት እነዚህን መርሆዎች በዘመኑ ለሚከሰቱ አዳዲስ ጉዳዮች ላይ እንዴት እንደሚተገበሩ ያመላክታሉ።
ስለዚህ አንድ ሙስሊም የ AI ምስል እና ቪዲዮ ፈጠራ ቴክኖሎጂን ሲጠቀም የሚከተሉትን ነጥቦች ማስታወስ ይገባዋል፡-
☑ ከተከለከሉ ምስሎች መራቅ፡ ነፍስ ያላቸውን ፍጡራን ሙሉ በሙሉ እና ህያው በሚመስል መልኩ ከመፍጠር መቆጠብ።
☑ የተፈቀዱ አማራጮችን መጠቀም፡ ህይወት በሌላቸው ነገሮች (landscapes, objects)፣ ያልተሟሉ ምስሎች እና ረቂቅ ጥበብ (abstract art) ላይ ማተኮር።
☑አላማን ማጥራት: ሥራችን ለአላህ ተቀባይነት ያለው፣ ለሰዎች ጠቃሚ እና ከእስልምና ስነ-ምግባር ጋር የማይጋጭ እንዲሆን መጣር።
☑ ከመጥፎ ነገር መራቅ፡ ቴክኖሎጂውን ለሐሜት፣ ለማጭበርበር (deepfakes)፣ ለብልግና እና ለሌሎች ሐራም ለሆኑ ተግባራት ከመጠቀም ሙሉ በሙሉ መራቅ።
ኢስላም የዕውቀት እና የፈጠራ ኃይማኖት ነው። ቴክኖሎጂን ለኸይር ነገር እስከተጠቀምንበት ድረስ ያበረታታል። AI ትልቅ አቅም ያለው መሳሪያ እንደመሆኑ፣ በእስልምና በተፈቀደው ማዕቀፍ ውስጥ በመቆየት ለዳዕዋ፣ ለትምህርት፣ ለጥበብ እና ለሌሎች በርካታ ጠቃሚ መስኮች ልንጠቀምበት እንችላለን።
ወሏሁ አዕለም – አላህ የበለጠ ያውቃል።
✅ MuradTadesse

❤2
Basic Computer Skills
Photo
📩 የጀግንነት ጉዟችሁ 📩
✅ የእውቀት መንገድ፡ የዛሬው ጥረት የነገው ህይወት!
📚 ውድ ተማሪዎች፣ የትምህርት ጉዟችሁ በራሱ ትልቅ የጀግንነት ታሪክ ነው። ይህ ታሪክ የእያንዳንዳችሁ ልዩ ልምድ፣ የእድገት እና የለውጥ ውብ ሂደት ነው። በእያንዳንዱ ምዕራፍ የምታገኙት እውቀት፣ የምትሰሩት ልምምድ እና የምትደርሱበት ደረጃ የወደፊት ህይወታችሁን የሚቀርጽ የጥንካሬ መሰረት ይጥላል።
📚 ይህ ጉዞ ሁልጊዜ ቀላል ላይሆን ይችላል፤ ፈተናዎች እና እንቅፋቶች ሊያጋጥሟችሁ ይችላሉ። አንዳንድ ጊዜ ነገሮች ከባድ መስለው ይታዩ ይሆናል፣ እናም ድካም ወይም ተስፋ መቁረጥ ሊሰማችሁ ይችላል። ነገር ግን፣ አስታውሱ፣ እነዚህ ሁሉ የሂደቱ አካል ናቸው። እነዚህ መሰናክሎች እንድትጠነክሩ፣ እንድትማሩ እና ይበልጥ እንድታድጉ የሚረዷችሁ ናቸው። "ውድቀት" የስኬት አንዱ አካል ነው።
📚 በእያንዳንዱ ችግር ውስጥ የተደበቀ ትምህርት እንዳለ እወቁ። ዛሬ የምትዘሩት የትጋት ዘር ሁሉ ለነገው ስኬታችሁ ወሳኝ መሠረት ነውና! የትምህርት አጋጣሚያችሁን በአግባቡ ተጠቀሙበት፤ ምክንያቱም እያንዳንዱ የትምህርት ቀን አዲስ ዕድል፣ አዲስ የመማሪያ እና የማደግ አጋጣሚ ነው። እያንዳንዱ ትምህርት ቤት የምትሄዱበት ቀን ለራሳችሁ፣ ለቤተሰባችሁ እና ለአገራችሁ የምታደርጉት ኢንቨስትመንት ነው።
✅ ጥንካሬያችሁ፡ ተስፋን መቼም አለመቁረጥና መሰናክሎችን መግፋት!
📚 በውስጣችሁ ያለውን ታላቅ ጥንካሬ አውጡ! እያንዳንዱ ውድቀት የመማሪያ ትምህርት እንደሆነ አስቡት፣ እናም ወደፊት ለመራመድ የሚያስችል አዲስ መንገድ እንደሚያሳያችሁ እመኑ። ስህተት መስራት የሰውነት ባህሪ ቢሆንም ከስህተት መማር ግን ብልህነት ነው። ሁሌም ሞክሩ! ደጋግሞ መሞከር ለስኬት ወሳኝ ነው። ብዙ ታላላቅ ፈጠራዎች እና ግኝቶች የተገኙት ከተደጋጋሚ ሙከራዎች እና ውድቀቶች በኋላ ነው።
➡ አዎ! ደጋግሞ ወድቆ ደጋግሞ ሳይነሳ፤ ከፍ ብሎ የሚበር የለም!!
📚 ታዋቂው ሳይንቲስት ቶማስ ኤዲሰን የኤሌክትሪክ አምፖልን ከመፍጠሩ በፊት በሺዎች የሚቆጠሩ ጊዜያት ሳይሳካለት ቀርቷል፤ ነገር ግን ተስፋ ባለመቁረጡ፣ ዓለም የምታበራውን መብራት አበረከተላት። እናንተም እንደዛው ተስፋ የማትቆርጡ ከሆነ የሆነ ሙከራችሁ መሳካቱ አይቀሬ ነው!!
⭕️ አዎ! ተስፋ አትቁረጡ! በጽናት ከቀጠላችሁ፣ ምንም ያህል ከባድ ቢሆንም የምትፈልጉትን ግብ ማሳካት እንደምትችሉ እወቁ። አስታውሱ፡ "ወንዝ የሚሻገረው በድፍረት እንጂ በመቆም አይሆንም!" ድፍረት ይኑራችሁ፣ ወደፊት ሂዱ! መሰናክሎች ሲያጋጥሟችሁ እንደ መጨረሻ አትዩዋቸው፤ ይልቁንም እንደ ፈተና እና ጥንካሬያችሁን የምታሳዩበት አጋጣሚ ተመልከቷቸው።
➡ ብሩህ ተስፋ፡
📚 የእውቀት ኃይል ተጠቀሙበት እና የወደፊት ብሩህ ተስፋ ይኑራችሁ! በጥረታችሁ እና በትጋታችሁ ታላቅ ነገር መፍጠር እንደምትችሉ እመኑ።
✅ የዛሬው ጥረታችሁ የነገ ህይወታችሁን ይመሰርታል። ስለዚህ፣ በትጋት አጥኑ፣ አዳዲስ ነገሮችን ለመማር ጓጉ፣ እና እርስ በርስ ተጋገዙ። የቡድን ስራ እና መረዳዳት የትምህርት ጉዞአችሁን የበለጠ ፍሬያማ ያደርገዋል። እርስ በርሳችሁ ተደጋገፉ፣ እውቀትን ተለዋወጡ፣ እና አብራችሁ ማደግን ተማሩ። እውቀት ሃይል ብቻ ሳይሆን መጨለማ ጉዞ መንገድን የሚያቅጣጭ ብርሃን ነውም ጭምር!፣ እናም በአላህ እርዳታ እናንተ የዚህ ሃይልና ብርሃን ባለቤቶች ናችሁ። ይህ ኃይልና ብርኃን የወደፊት ህይወታችሁን ብቻ ሳይሆን፣ ቤተሰባችሁን፣ ማኅበረሰባችሁን እና አገራችሁን የመለወጥ አቅም አለው።
✅ እውቀታችሁን ለበጎ ነገር ተጠቀሙበት። ዓለም የእናንተን አስተዋጽኦ ትፈልጋለች። እያንዳንዱ ያገኛችሁት ዕውቀት ለእናንተም ሆነ ለሌሎች በጎ ነገሮችን ለመፍጠር የሚያስችል ብርሃን ይሁን። በዓለም ላይ መልካም ለውጥ ለማምጣት የእናንተ ብቃት እና ትጋት ወሳኝ ነው።
✅ መትጋትና በራስ መተማመን፡ ገደብ የለሽ አቅም እና ታላቅነት
📚 ያለማቋረጥ በመትጋትና በራስ በመተማመን፣ ህልሞቻችሁን እውን ማድረግ ብቻ ሳይሆን፣ ለአገራችሁ እና ለዓለም ትልቅ አስተዋጽኦ ማድረግ ትችላላችሁ። ስኬት የፅናት ውጤት ነው፤ ተስፋ እስካልቆረጣችሁ ድረስ መማር፣ ማደግ እና ማሸነፍ ትችላላችሁ።
📚 በራሳችሁ ተማመኑ፣ አቅማችሁን እወቁ። ወሰኖችን የሚያስቀምጠው የራሳችሁ አስተሳሰብ እንጂ ውጫዊ ሁኔታ አይደለም። ውስጣችሁ ያለውን እምቅ ኃይል አውጡት። እያንዳንዳችሁ ልዩ የሆነ ተሰጥኦ እና አቅም አላችሁ። ያንን አቅም ለማውጣት አትፍሩ።
📚 ከዚህ በፊት ማንም ያላሰበውን ነገር ለማሰብ፣ ማንም ያልሰራውን ለመስራት ድፈሩ። የዓለምን ታሪክ የቀየሩ ታላላቅ ሰዎች የተለዩ ስላልሆኑ ሳይሆን፣ በራሳቸው ስላመኑ እና ተስፋ ስላልቆረጡ ነው። እናንተም ያን ማድረግ ትችላላችሁ። የዛሬው ጥረታችሁ፣ ትጋታችሁ እና ጽናታችሁ ለታላቅ የወደፊት ሕይወት መሠረት ይሆናል። ህልሞቻችሁን እውን ለማድረግ የማትታክቱ ከሆነ፣ ዓለም በእርምጃችሁ ወደ መልካም ትሸጋገራለች።
⭕️ አስታውሱ፣ የትምህርት ጉዞአችሁ የእድሜ ልክ የመማር ሂደት መጀመሪያ እንጂ መጨረሻ አይደለም። ሁልጊዜ አዳዲስ ነገሮችን ለመማር ዝግጁ ሁኑ፣ የማወቅ ጉጉታችሁን አትግደሉ። ራሳችሁን አዳዲስ ፈተናዎች ላይ ጣሉ፣ እና ከመጽናናት ፈጥናችሁ ለመውጣት አትፍሩ። ይህን ስታደርጉ፣ የምትችሉት ነገር ወሰን እንደሌለው ትገነዘባላችሁ።
መልካም የትምህርት ጊዜ! በጉዟችሁ ሁሉ መልካም ዕድል እመኛለሁ።
════════════════
📚 ጠንካራ ተስፋዎቻችን የህልሞቻችን ክንፎች ናቸው!
📚 የዛሬ እርምጃዎቻችን የነገ ስኬቶቻችን ናቸው!
════════════════
ቀን:- ሐምሌ 23/2017 ዓ.ል [ሰፈር 05/1447 አ.ሒ]
✍️ በረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል

👍2
Basic Computer Skills
📩 የጀግንነት ጉዟችሁ 📩 ✅ የእውቀት መንገድ፡ የዛሬው ጥረት የነገው ህይወት! 📚 ውድ ተማሪዎች፣ የትምህርት ጉዟችሁ በራሱ ትልቅ የጀግንነት ታሪክ ነው። ይህ ታሪክ የእያንዳንዳችሁ ልዩ ልምድ፣ የእድገት እና የለውጥ ውብ ሂደት ነው። በእያንዳንዱ ምዕራፍ የምታገኙት እውቀት፣ የምትሰሩት ልምምድ እና የምትደርሱበት ደረጃ የወደፊት ህይወታችሁን የሚቀርጽ የጥንካሬ መሰረት ይጥላል። 📚 ይህ ጉዞ ሁልጊዜ ቀላል…
#ከEthiocoders በተጨማሪ
#UniAthena ከ-Cambridge International Qualification, United Kingdom (UK🇬🇧) ጋር በመሆን የሚሰጡ 12 የሚሆኑ ነፃ የOnline ትምህርቶች ከሰርተፊኬትና ከትራንስክሪፕት ጋር!!
📩 ለመመዝገብና ለመማር ከታች ያለውን Website ነክታችሁ መግባት ትችላላችሁ። 📩
https://uniathena.com

Python ለመማር አስባችሁ ከሆነ አልያም ገና እየጀመራችሁ ከሆነ እነዚህን ድረገጾች ሞክሯቸው።
https://www.programiz.com/python-programming
በቀላል አገላለፅ እና በቀላል ምሳሌ python መማር ያስችላል።
https://www.w3schools.com/python/
አብዛኞቻችሁ ታውቁታላችሁ ለጀማሪ የሚሆን ትምህርት በሚገባ ታገኙበታላችሁ። ከpython በተጨማሪም ሌሎች programming languages መማር ትችላላችሁ።
https://docs.python.org/3/tutorial/
የpython official documentation የምታገኙበት ሲሆን። አገላለፁ ትንሽ ጠጠር ስለሚል ቅድሚያ የpythone basic ብታጠኑ ይመረጣል።
https://www.geeksforgeeks.org/python/python-lists/
ከቀላል እስከ ከባድ የpython tutorial የምታገኙበት ድረገጽ ነው።
©bighabesha

❤4👍2
#ChatGpt
ChatGpt study and learn (study mode) የተሰኘና ተማሪዎችን ይበልጥ ተጠቃሚ የሚያደርግ feature አስተዋወቀ።
ይህም ጥያቄ ሲጠየቅ ቀጥታ መልሱን ከመስጠት ይልቅ step by step እኛንም በመሃል እየጠየቀን explain ያደርግልናል።
ተማሪዎች study modeን የቤት ስራ በሚሰሩበት ጊዜ፣ ለፈተና በሚዘጋጁበት ጊዜ እና ስለ አዳዲስ ነገሮች ማወቅ ሲሹ ቢጠቀሙ ውጤታማ እንደሚሆኑ ተመላክቷል።
study mode አሁን ላይ ለ free, pro እና ለplus ተጠቃሚዎች Available ነው። ተጠቃሚዎችም website ላይ tools የሚለውን ከነኩ በኋላ study and learn የሚለውን በመምረጥ እና በአፕሊኬሽን ደግሞ የፎቶ icon ከነኩ በኋላ study and learn የሚለውን በመምረጥ ይህንን feature መጠቀም ይችላሉ።

❤6👍1
🎓 A Fearless Mind and Heart can Communicate Fearlessly!
════════════════
🎓 ፍርሃት የሌለበት አዕምሮ እና ልብ ያለ ፍርሃት ይግባባሉ!!
════════════════
⭕️ ለዚህ ደግሞ:- ሁሌም አዲስ ነገር መማር፣ ተስፋ አለመቁረጥ፤ ሁሌም መሞከር... በጣም አስፈላጊ ነው።
✍️ Reshad Ibnu Muzemil

#እንድታውቁት
ethiocoders (udacity) ላይ ተምራችሁ ሰርተፍኬስ ልትቀበሉ ስትሉ ሰርተፍኬት ካልሰጣትሁ የትምህርት ማጠናቀቂያው ቀነ ገደቡ አልፏል ማለት ነው።
ለአንድ course 8 ሳምንት ሲሆን የሚሰጣችሁ። በዚህ ጊዜ ውስጥ ካላጠናቀቃችሁ ሰርተፍኬት ላታገኙ ትችላላችሁ። ነገር ግን 8 ሳምንት ሳይሞላ ትምህርታችሁን መጨረስ ትችላላችሁ።
ትምህርቱን የጀመራችሁበትን ቀን ለማወቅ ከፈለጋችሁ በምስሉ ላይ እንደምትመለከቱት ወደ transcript በመግባት Enrolled on ከሚለው አጠገብ መመልከት ትችላላችሁ።

👍4
OpenAI በጣም ፈጣንና powerful ነው የተባለለትን GPT 5 ማስተዋወቁ ይታወቃል።
ድረገፆችን እና መተግበሪያዎችን በአንድ prompt መስራት የሚችለው ይህ ሞዴል ከበድ ያሉ ጥያቄዎችን ማሰላሰል እና መመለስ ይችላል።
ይህ ሞዴል እንደ Gpt 4o ካሉት ሞዴሎች ጋር ሲነፃፀር እጅግ የተሻለ ሲሆን ከዚህ በፊት ያደረገውን ምልልስ የማስታወስ ችሎታውም ከሌሎቹ አንፃር የተሻለ ነው።
ይህን ሞዴል በነፃ መጠቀም ትችላላችሁ ነገር ግን የ5 ሰዐት ገደብ አለው።
አፕሊኬሽኑን update አድርጋችሁ መሞከር ትችላላችሁ።

📚 ጠንካራ ተስፋዎች የህልሞቻችን ክንፎች ናቸው!
✅ ተስፋ የሰው ልብ ውስጥ ሲበቅል እንደ ትንንሽ ዘር ይጀምራል። ነገር ግን ይህ ትንንሽ ዘር እንዲበቅል በግንባር ጠንካራ እና በትክክል እንክብካቤ ያስፈልገዋል። ተስፋ ያለው ሰው ምን ያህል ችግር ቢያጋጥመው እንኳን በህልም መንገዱ አይቆምም።
✅ ተስፋ ህልምን ለማሳካት የሚረዳን ኃይል ነው፣ እና ያለ ተስፋ ህልም እንደ ቀላል ብናኝ በግድግዳ ላይ የተቀረ ነው፤ ያለ እንቅስቃሴ እና እድገት ደግሞ ዝም ብሎ በባድ መኖር በቁም መሞት ነው።
✅ ውድ ተማሪዎች ሆይ፣ ዛሬ ያላችሁን ትንሽ ህልም አትናቁት። ትንሹ ህልማችሁ በሰው ልብ ውስጥ ከተሰወረ፤ ትክክለኛ አቅጣጫ እምነት እና ትጋት በተሞላበት ሙከራ በጊዜ የማይታመን አስደናቂ ውጤት ያመጣል።
📚 የዛሬ እርምጃዎቻችን የነገ ስኬቶቻችን ናቸው!
እኛ በዛሬ የምናደርገው ነገር እንደ መጀመሪያ ዘር ነው። በሙሉ ልብ የምንተክለው "ዛሬ" ነገ ደግሞ ታላቅ ዛፍ ይሆናል። በዛሬ ላይ ያለን ጥረት (የምናደርገው ሙከራ) ለኛም ሆነ ለሌሎች ላይታይ ይችላል፣ ግን ጊዜው እየነጎደ ጥረታችንም እየፏፏ ይመጣና በቅፅበት የስኬታችን እርሻ ፍሬ ያፈራል፣ ያብባል።
✅ እናንተ ተማሪዎች፣ ዛሬ በትምህርታችሁ ላይ በምታደርጉት ጥረት በቀጣዩ ዓመት ከአምላካችሁ እርዳታ ጋር ምን ያህል ለውጥና ስኬት ሊያመጣ እንደሚችል አስቡ። የአሁኑን ጥረታችሁን አሁኑኑ አይታይም፣ እናንተም ጥረታችሁን አጧጡፉ እንጂ አትቸኩሉ። ነነገ የምታዩት ስኬት "ዛሬ" በትክክል የተወሰደ እርምጃ ነው (በአላህ እርዳታ ተስፋ-አለመቁረጥ የታከለበት የልፋታችሁ ውጤት ነው።
✨ እናም ውድ ወንድምና እህቶቼ (ተማሪዎቼ)
➊ ትኩረት አድርጉ:– በምትማሩት ትምህርት ላይ ትኩረታችሁ እየጨመረ ሲሄድ ወደ ስኬት ጉዞአችሁ መራመድ ትጀምራላችሁ። በዚህ ስኬት ጉዞ ሌሎችንም አብሯችሁ እንዲራመዱ እድሉን ታመቻቻላችሁ።
❷ ጊዜን በአግባቡ ተጠቀሙ – የዛሬውን ጊዜናችሁን ለነገ ስኬታችሁ ምክንያት እንዲሆን አድርጋችሁ ተጠቀሙበት።
➌ በትዕግሥት ጠብቁ:– ሁሉም ነገር በአላህ እርዳታ በጊዜው ይሆናል! የሆነ ዘርን ዘርተን እስከሚያፈራ ድረስ በትዕግስት እንደምንጠብቀው ሁሉ ዛሬ የምታደርጉት ጥረት ውጤቱ ለምን በቅፅበት አልታየንም አትበሉ።
❹ ተስፋን አትቁረጡ:– የምትችሉትን ከጣራችሁ በኋላም፣ ደጋግማችሁ ከሞከራችሁም በኋላ የሆነ ነገር ላይሳካ ይችላል ነገር ግን ተስፋ ፈፅሞ አትቁረጡ፤ ተስፋ ያለው ሰው መንገድ ያገኛል። "ህይወትህን እጣ እንጂ ተስፋ እንዳታጣ" ይላሉ ቱርኮች!!
📚 ደጋግሞ ወድቆ ደጋግሞ ሳይነሳ ከፍ ብሎ የሚበር የለም!
🌱 በመጨረሻም:
በህይወት መንገድ ላይ የምንወስዳቸው እርምጃዎች ሁሉ ለወደፊታችን መሠረት ናቸው። ዛሬ የምንተክለው ትንንሽ ዘሮች ትክክለኛውን እንክብካቤ ካገኙ በአላህ እርዳታ ነገ ብዙ ጣፋጭ ፍሬዎችን የያዘ ትልቅ የፍራፍሬ ዛፍ መሆናቸው አይቀሬ ነው። ህልምና ተስፋ እንዲሁም "በዛሬ" ላይ በምናደርገው ጥረት ነገ የምንፈልገውን ህልም ሁሉ ማሳካት እንችላለን።
⭕️ አዎ! ጠንካራ ተስፋዎች የህልሞቻችን ክንፎች ናቸው! የዛሬ እርምጃዎቻችን ደግሞ የነገ ስኬቶቻችን ናቸው!

#telegram_update
ቴሌግራም ሰሞኑን አዳዲስ ማሻሻያዎችን ያደረገ ሲሆን ከነዚህም መካከል፦
⚫ Public post search
search tab ላይ አዲስ posts የሚል tab የተጨመረ ሲሆን ይህም public channel ላይ የሚገኙ ነገሮችን search ማድረግ ያስችለናል። ከዚህ በፊት አንድን መረጃ search በምናደርግበት ጊዜ የቻናሉ ስም አልያም እኛ join ካደረግናቸው ቻናሎች ያለን መረጃ ነበር የሚያሳየን ነገር ግን posts ላይ search ስናደርግ አለም አቀፍ ካሉ ቻናሎች ላይ search results/ውጤቶችን ያሳየናል።
ይህ feature አሁን ላይ ክፍት የሆነው ለቴሌግራም ፕሪሚየም ተጠቃሚዎች ነው።
⚫ Story Albums
የቴሌግራም ቻቶቻችንን channel, group, bots እያልን እንደምንከፋፍለው post ያደረግናቸውንም stories በአልበም መሰነድ የሚያስችለን feature ነው። ይህንንም ለማድረግ ጥግ ጋር ያለውን ሶስት ነጥብ ነክተን ወደ my profile መግባት> album ውስጥ ማስገባት የምንፈልገውን story ጫን አድርገን መያዝ > add to folder> new folder> የፈለጋችሁት ስም መሰየም።
⚫ Profile Rating
ቴሌግራም ፕሮፋይል ላይ ቁጥር(ደረጃ) የሚያሳይ አዲስ badge የተጨመረ ሲሆን ይህም የቴሌግራም starን በመጠቀም የተደረገውን transaction የሚያሳይ ይሆናል። በተጨማሪም telegram ሌሎች ማሻሻያዎችን የጨመረ ሲሆን telegram መተግበሪያችሁን update በማድረግ መጠቀም ትችላላችሁ።

❤4