Basic Computer Skills
1.89K subscribers
1.22K photos
100 videos
576 files
833 links
#በዚህ የቴሌግራም ቻናል
↪️ Programming
↪️ ቴክኖሎጂ ነክ ትምህርቶችን
↪️ ኮምፒውተር ነክ ትምህርቶችን
↪️Basic Computer Skills
↪️ Software
↪️ AI and AI Skills (Like ChatGPT)

ከላይ የተዘረዘሩትና ሌሎችም ገራሚ ትምህርቶች ይለቀቅበታል!

t.me/BasicComputerSkillsGroup

𝘽𝙮 𝙍𝙚𝙨𝙝𝙖𝙙
Download Telegram
Basic Computer Skills
Photo
💬 Alhamdulillah

💫 Hopes are the Wings of Dreams. Never stop hoping, never stop dreaming.
════════════════
ለተማሪዎች የተላለፈ መልዕክት።


የላቀ የወደፊት ዕድል ለመፍጠር!

እያንዳንዱ ጉዞ የሚጀምረው በአንድ እርምጃ ነው። በጋለ ስሜትና በትጋት ደግሞ ያ እርምጃ ታሪክ የሚሰራ ቅርስ ይሆናል። ይህ ሰርተፍኬት እናንተም ታላቅ ደረጃ ላይ መድረስ እንደሚችሉ ማስታወሻ ይሁንልኝ!

📚 ስኬት የዕድል ጉዳይ አይደለም፤ የጥረትን፣ የመማርን እና በየቀኑ ጥረት የማድረግ ውጤት ነው። በጽናት ከሰሩ፣ የማይቻል ነገር የለም!

📚 Artificial Intelligence (AI) / (ሰው ሰራሽ አስተውሎት):  የወደፊት ብቻ አይደለም፤ የእናንተ የዛሬው ዕድል ነው። መማር ጀምሩ፣ የማወቅ ጉጉታችሁን አጧጥፉት፣ እና ለነገ ስኬትን የሙከራ እርምጃ ጀምሩ። ይህ ዘርፍ ገደብ የለሽ ዕድሎችን ይዟል፤ እናንተም የዚህ አካል መሆን ትችላላችሁ።

⭕️ ምናልባት አሁን በጥያቄዎችና በጥርጣሬዎች የተሞሉ ሊሆኑ ይችላሉ። ነገር ግን በትኩረትና በእምነት እነዚያን ጥያቄዎች ወደ ብቃት መቀየር ይቻላል። አሁን የእናንተ ተራ ነው! እያንዳንዱ ጥረታችሁ ፍሬ ያፈራል። ኢንሻአላህ!

ያለፈው ሁኔታችሁ ገደባችሁን አይወስንም፤ የአዕምሮአችሁ ሁኔታ ነው የሚወስነው። ወሰኖችን አፍርሷቸው፣ መሰናክሎችን ጣሷቸው (ሰባብሯቸው)፣ እና ብቃታችሁን ተጠቀሙበት! በውስጣችሁ ያለውን እምቅ ኃይል አውጡት።

📚 እያንዳንዱን ትንሽ ድል አክብሩ። ይህ ሰርተፍኬት መጨረሻው አይደለም። በአላህ ፍቃድ ከእናንተ ጋር በፈጠራ እና በለውጥ ወደተሞላ የወደፊት ጊዜ የሚወስድ ወሳኝ ምዕራፍ ነው። ለበለጠ ስኬት መነሻ ይሁን።

📚 ዕድልን አትጠብቁ። ለዕድል ተዘጋጁ ። ተማሩ፣ እደጉ፣ አሁንም አድጉ! እናም በሩ ሲከፈት፣ በልበ-ሙሉነት ለመግባት ዝግጁ ትሆናላችሁ። የእውቀት ፍለጋችሁ መቼም አታቁሙ።
ይህን አስደናቂ ትምህርት ለመማር እና ህይወታችሁን ለመለወጥ ይህ ትልቅ አጋጣሚ እንደሆነ ተስፋ አደርጋለሁ።

ምን ትጠብቃላችሁ ታዲያ⁉️


════════════════
📚 ጠንካራ ተስፋዎቻችን የህልሞቻችን ክንፎች ናቸው!

📚 የዛሬ እርምጃዎቻችን የነገ ስኬቶቻችን ናቸው!

ቀን:- ሐምሌ 14/2017 ዓ.ል [ሙሐረም 27/1447 አ.ሒ]

✍️ በረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል
2
የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) እና የምስል ፈጠራው
============================
✍️ በዘመናችን የቴክኖሎጂ እድገት ውስጥ፣ ሰው ሰራሽ የማሰብ ችሎታ (Artificial Intelligence - AI) ግንባር ቀደም ሆኖ ብቅ ብሏል። በተለይም ምስሎችን እና ቪዲዮዎችን ከመፍጠር፣ ከማሻሻል እና ወደ ተለያዩ አይነቶች ከመቀያየር ጋር ተያይዞ የሚያቀርባቸው አስደናቂ ችሎታዎች ብዙ ጥያቄዎችን አስነስተዋል። እንደ ሙስሊም የእነዚህን መሳሪያዎች አጠቃቀም ኢስላማዊ ብይን መረዳት እጅግ አስፈላጊ ነው።

1⃣) AI ምስሎችን እና ቪዲዮዎችን እንዴት ይፈጥራል?

ስለ ሐራም ሐላልነቱ ከመናገራችን በፊት AI እንደት ፎቶዎችንና ቪድዮዎችን እንደሚያቀናብርና እንደሚፈጥር እንመልከት።

የ AI ምስል አመንጪ መሳሪያዎች (AI Image Generators) ግልፅ ያልሆኑ ብላክ ቦክሶች "ጥቁር ሳጥን" ወይም ምትሃቶች አይደሉም። እነሱ የተገነቡት ውስብስብ በሆኑ የሒሳብ ሞዴሎች እና ስልተ ቀመሮች (algorithms) ላይ ነው። አሠራራቸውን በቀላሉ ለመረዳት በሁለት ዋና ዋና ሞዴሎች እንከፍላቸዋለን፡-

1⃣Generative Adversarial Networks (GANs): ይህ ሞዴል ሁለት ክፍሎችን ያቀፈ ነው፤ "ጄነሬተር" (the Generator) እና "ዲስክሪሚኔተር" (the Discriminator)።

ጄነሬተሩ (The Forger): ልክ እንደ ሰዓሊ ወይም አታላይ፣ ከስልጠና መረጃው (dataset) የተማረውን መሰረት በማድረግ አዲስ ምስል ለመፍጠር ይሞክራል።

ዲስክሪሚኔተሩ (The Detective): ልክ እንደ መርማሪ፣ ጄነሬተሩ የፈጠረው ምስል እውነተኛ (ከስልጠና መረጃው ውስጥ ያለ) ነው ወይስ የውሸት (በጄነሬተሩ የተፈጠረ) መሆኑን ለመለየት ይሞክራል።

ይህ "የፉክክር" ሂደት በሚሊዮን ጊዜያት ይደጋገማል (በተደጋጋሚ train ይደረጋል!)። ጄነሬተሩ ዲስክሪሚኔተሩን ለማታለል እየተሻሻለ ሲሄድ፣ ዲስክሪሚኔተሩ ደግሞ የውሸት ምስሎችን በመለየት እየተሻሻለ ይሄዳል። የVAE አሠራርን የተማራችሁ የኤአይ ሪሰርቸሮች ካላችሁ በቀላሉ ትረዱኛላችሁ። በመጨረሻም ጄነሬተሩ በጣም ከፍተኛ ጥራት ያላቸው እና እውነተኛ የሚመስሉ ምስሎችን መፍጠር ይጀምራል።

ይህ ቴክኖሎጂ ቀደም ባሉት የ AI ሞዴሎች ውስጥ በስፋት ጥቅም ላይ የዋለ ሲሆን፣ ለምሳሌ እንደ NVIDIA's StyleGAN (በጣም እውነተኛ የሚመስሉ የሰው ፊት ምስሎችን በመፍጠር የሚታወቀው) እና Artbreeder (ያሉትን ምስሎች በማቀላቀል አዲስ ለመፍጠር የሚያስችለው) ያሉ መሳሪያዎች በዚህ መርህ ላይ የተመሰረቱ ናቸው።

2⃣Diffusion Models: ይህ በአሁኑ ጊዜ በጣም ተወዳጅ እና ከፍተኛ አቅም ያለው ዘዴ ነው። አሠራሩም፡
🔗ስልጠና (training)፡ ሞዴሉ በሚሊዮን የሚቆጠሩ እውነተኛ ምስሎችን ይመለከታል። በእያንዳንዱ ምስል ላይ ቀስ በቀስ visual noise በመጨመር ምስሉ ሙሉ በሙሉ ወደ ኖይዝነት እስኪቀየር ድረስ ያለውን ሂደት ይማራል።

🔗ምስል መፍጠር፡ ተጠቃሚው የጽሑፍ ትዕዛዝ (prompt) ሲሰጥ (ለምሳሌ "A horse running on a beach during sunset")፣ ሞዴሉ ከኖይዝ ይጀምርና በስልጠናው የተማረውን ተቃራኒ ሂደት በመጠቀም ኖይዙን ደረጃ በደረጃ እያስወገደ የተሰጠውን ትዕዛዝ የሚያሟላ አዲስ ምስል ይፈጥራል።

ይህ ቴክኖሎጂ በአሁኑ ጊዜ ገበያውን የሚመሩት የ AI መሳሪያዎች የሚጠቀሙበት ነው። ለምሳሌ፦ ለምስል ፈጠራ የምናውቃቸው እንደ OpenAI's DALL-E 3, Midjourney, እና Stable Diffusion ያሉ መሳሪያዎች በሙሉ በዚህ ሞዴል ላይ የተገነቡ ናቸው። ያው ቻትጅፒቲ ራሱ ይሄ ተገጥሞለት ነው።

በተመሳሳይ፣ ለቪድዮ ፈጠራ ግንባር ቀደም የሆኑት እንደ OpenAI's Sora, Runway Gen-2, እና Pika Labs እንዲሁም የጎግል Veo ያሉ መተግበሪያዎችም የ Diffusion ሞዴልን ወይም የእሱን variants ይጠቀማሉ።

🎙ዋናው ነገር በሁለቱም አጋጣሚዎች AI "በራሱ ፈቃድ" አይፈጥርም። ይልቁንም፣ ከግዙፍ የመረጃ ቋት (database) የተማራቸውን ስልቶች (patterns) በመጠቀም፣ በተጠቃሚው ትዕዛዝ እና ቁጥጥር ስር ሆኖ እንደ አንድ እጅግ የላቀ መሳሪያ ሆኖ ያገለግላል።

ስለዚህ አንድ ሰው በብሩሽ ወይም በእርሳስ እንደሚስለው ሁሉ፣ AI ን በመጠቀም ምስል «እንዲፈጠር ማዘዝ» የሰውየው ድርጊት አካል ነው።


2⃣ በኢስላም የምስል ፈጠራ መሰረታዊ መርሆዎች

ወደ AI ከመግባታችን በፊት፣ ኢስላም በአጠቃላይ ስለ ምስል ፈጠራ (التصوير) ያለውን አቋም መረዳት አለብን። ዋናው መነሻ ነጥብ የአላህን የፈጠራ ባህሪ ለመጋፋት ወይም ለመምሰል (مشابهة بخلق الله) መሞከርን የሚከለክሉ ነብያዊ ሐዲሶች ናቸው።

ውዱ ነቢይ (ሶለዋቱ ረቢ ዓለይሂ ሰላሙ) እንዲህ ብለዋል፡-
«እነዚህን ምስሎች የሚሠሩ ሰዎች በትንሳኤ ቀን ይቀጣሉ። 'የፈጠራችሁትን ሕያው አድርጉ!' ይባላሉ።»


ይህ ክልከላ በዋነኝነት የሚያተኩረው ነፍስ ባላቸው ነገሮች (ذوات الأرواح) ማለትም በሰው፣ በእንስሳት እና በአዕዋፍ ምስሎች ላይ ነው። የዚህ ክልከላ ጥበብ ከጣዖት አምልኮ መራቅ እና የአላህን ብቸኛ የፈጣሪነት ባህሪ ማክበር ነው።

ሆኖም እስልምና ተራማጅ እና ተግባራዊ መፍትሄዎችን የሚያቀርብ ኃይማኖት እንደመሆኑ፣ የዲኑ ሊቃውንት ከእነዚህ መርሆዎች በመነሳት የተለያዩ ዝርዝር ህጎችን አስቀምጠዋል፡-

⬇️ ያልተሟላ ምስል፡ ምስሉ ህይወት ያለው ነገርን የሚወክል ቢሆንም፣ ህይወት ሊኖረው የማይችልበት ወሳኝ አካሉ ከጎደለ (ለምሳሌ ጭንቅላት ከሌለው ወይም የሰውነት ግማሽ ብቻ ከሆነ) ክልከላው አይመለከተውም። ኢማም ኢብኑ ቁዳማህ እንደገለጹት፣ «ምስል ማለት ጭንቅላቱ ነው። ጭንቅላቱ ከተቆረጠ ምስል አይደለም።!»
ይህ አቡ ሁረይራ ካስተላለፉት የጂብሪል ታሪክ የተወሰደ ነው።

⬇️ህይወት የሌላቸው ነገሮች፡ እንደ መልክዓ ምድር (landscape)፣ ህንፃዎች፣ ዛፎች እና ሌሎች ግዑዝ ነገሮች ያሉ ምስሎችን መፍጠር ሙሉ በሙሉ የተፈቀደ ነው።

⬇️ዲጂታል እና ፊዚካል ምስሎች፡ ብዙ የዘመናችን ሊቃውንት በካሜራ የሚነሱ ፎቶግራፎች እና በስክሪን ላይ የሚታዩ ዲጂታል ምስሎች "ምስል መፍጠር" (ተስዊር) ሳይሆን "የጥላ ነፀብራቅን ማቆየት" (حبس الظل) በሚለው ስር እንደሚወድቁ ይገልጻሉ።

እነዚህ ምስሎች በወረቀት፣ በግድግዳ ወይም በሌላ ቋሚ ነገር ላይ እስካልታተሙ ድረስ፣ እንደ ጊዜያዊ የብርሃን ቅንጅት ስለሚቆጠሩ ክልከላው እንደማይጠናከርባቸው ያስረዳሉ።


3⃣ የ AI ምስል ፈጠራን ከኢስላማዊ መርሆዎች ጋር ማገናዘብ

ከላይ የተገለጹትን የቴክኖሎጂ አሠራር እና የሸሪዓ መርሆዎችን መሰረት በማድረግ፣ የAI ምስል ፈጠራን ብይን በሚከተሉት ነጥቦች መተንተን እንችላለን።

የድርጊቱ ባለቤትነት (Attribution of the Act):
አንድ ሰው ለ AI ስርዓት «የአንበሳ ምስል ሳልልኝ!» ብሎ ሲያዝ፣ ምንም እንኳን ሥራውን የሚሰራው ማሽኑ ቢሆንም፣ ድርጊቱ የታዘዘው እና የተጀመረው በሰውየው ነው። AI እዚህ ላይ እንደ ብዕር፣ እንደ ኮምፒውተር ወይም እንደ ቀለም አይነት መሳሪያ ነው። ስለዚህ የድርጊቱ ሐላል ወይም ሐራምነት በትዕዛዙ እና በውጤቱ ላይ ይመሰረታል። ሰውየው መሳሪያውን አንድ ነገር እንዲስል ሲያዝ እና እሱ እንዳዘዘው ሲፈጽም፣ ይህ የስዕልን ህግ ሊይዝ ይችላል።
2
ℛℯ𝓈𝒽𝒶𝒹 ℳ𝓊𝓏ℯ𝓂𝒾𝓁
Photo
የተፈጠረው ምስል አይነት (Nature of the Image):
ሙሉ እና ህይወት ያለው ምስል፡ ነፍስ ያለው ፍጡርን (ሰው ወይም እንስሳ) ሙሉ አካሉን እና ህይወት ሊኖረው በሚችል መልኩ መፍጠር ከላይ በተጠቀሰው ሐዲሥ መሰረት የተከለከለ ይሆናል። ይህ የአላህን ፈጠራ የማስመሰል ገጽታ ስላለው ነው።

ያልተሟላ ምስል፡ የሰው ወይም የእንስሳ ምስል ነገር ግን ጭንቅላት የሌለው፣ ከወገብ በላይ ብቻ የሆነ፣ ወይም ህይወት ለመቀጠል ወሳኝ የሆነ አካሉ የጎደለው እንዲሆን አድርጎ መፍጠር የተፈቀደ ሊሆን ይችላል።

ግዑዝ ነገሮች፡ የህንፃዎች፣ የተፈጥሮ ገጽታዎች፣ መኪናዎች፣ ወይም ምናባዊ ንድፎችን (abstract art) በ AI መፍጠር ሙሉ በሙሉ የተፈቀደ ነው።

የአጠቃቀም አላማ:
ትምህርታዊ እና ሳይንሳዊ ፍላጎቶች፡ ለህክምና፣ ለደህንነት፣ ለትምህርት እና ለሌሎች አስፈላጊ እና ጠቃሚ ለሆኑ ጉዳዮች ምስሎችን መጠቀም በእስልምና (الضرورات تبيح المحظورات) በሚለው መርህ ስር ሊታይ ይችላል።

ለመዝናኛ እና ላልተገባ አላማ፡ ስሜትን የሚቀሰቅሱ፣ ጸያፍ፣ ወይም የሌሎችን ክብር የሚያጎድፉ ምስሎችን መፍጠር በማንኛውም መንገድ የተከለከለ ነው።

ያለውን ምስል ማሻሻል (Modifying Existing Images):
አንድን በካሜራ የተነሳ ፎቶግራፍ ወደ ካርቱን ወይም ስዕል መቀየር፣ ምስሉ ሙሉ እና ህይወት ያለው ከሆነ፣ እንደ አዲስ መሳል ስለሚቆጠር ክልከላው ይመለከተዋል። ነገር ግን ፎቶውን በማሻሻል ያልተሟላ ምስል እንዲሆን ማድረግ (ለምሳሌ: ጭንቅላቱን ማስወገድ ወይም ወደ ረቂቅ ጥበብ መቀየር) ይፈቀዳል።

⬅️ ሲጠቃለል፦
የሰው ሰራሽ የማሰብ ችሎታ (AI) በራሱ ሐላልም ሐራምም አይደለም፤ እሱ መሳሪያ ነው። ብይኑ የሚወሰነው በአጠቃቀማችን ነው። አንዳንድ ሰዎች «ሸሪዓ የቴክኖሎጂን አሠራር ባለመረዳት ይከለክላል!» ብለው ሊያስቡ ይችላሉ። ይህ ስህተት ነው። የእስልምና ህግጋት የተመሰረቱት በማይለወጡ መለኮታዊ መርሆዎች ላይ ነው። ሊቃውንት እነዚህን መርሆዎች በዘመኑ ለሚከሰቱ አዳዲስ ጉዳዮች ላይ እንዴት እንደሚተገበሩ ያመላክታሉ።

ስለዚህ አንድ ሙስሊም የ AI ምስል እና ቪዲዮ ፈጠራ ቴክኖሎጂን ሲጠቀም የሚከተሉትን ነጥቦች ማስታወስ ይገባዋል፡-

ከተከለከሉ ምስሎች መራቅ፡ ነፍስ ያላቸውን ፍጡራን ሙሉ በሙሉ እና ህያው በሚመስል መልኩ ከመፍጠር መቆጠብ።

የተፈቀዱ አማራጮችን መጠቀም፡ ህይወት በሌላቸው ነገሮች (landscapes, objects)፣ ያልተሟሉ ምስሎች እና ረቂቅ ጥበብ (abstract art) ላይ ማተኮር።

አላማን ማጥራት: ሥራችን ለአላህ ተቀባይነት ያለው፣ ለሰዎች ጠቃሚ እና ከእስልምና ስነ-ምግባር ጋር የማይጋጭ እንዲሆን መጣር።

ከመጥፎ ነገር መራቅ፡ ቴክኖሎጂውን ለሐሜት፣ ለማጭበርበር (deepfakes)፣ ለብልግና እና ለሌሎች ሐራም ለሆኑ ተግባራት ከመጠቀም ሙሉ በሙሉ መራቅ።

ኢስላም የዕውቀት እና የፈጠራ ኃይማኖት ነው። ቴክኖሎጂን ለኸይር ነገር እስከተጠቀምንበት ድረስ ያበረታታል። AI ትልቅ አቅም ያለው መሳሪያ እንደመሆኑ፣ በእስልምና በተፈቀደው ማዕቀፍ ውስጥ በመቆየት ለዳዕዋ፣ ለትምህርት፣ ለጥበብ እና ለሌሎች በርካታ ጠቃሚ መስኮች ልንጠቀምበት እንችላለን።

ወሏሁ አዕለም – አላህ የበለጠ ያውቃል።

MuradTadesse
2
Introduction_to_ChatGPT Videos.zip
26.6 MB
Artificial Intelligence Fundamentals

Video: Part 1

#Source: Udacity (Ethiocoders)
Discovering_Ethical_AI Videos.zip
64.5 MB
Artificial Intelligence Fundamentals

Video: Part 2

#Source: Udacity (Ethiocoders)

#For International Certification
Basic Computer Skills
Photo
📩 የጀግንነት ጉዟችሁ 📩

የእውቀት መንገድ፡ የዛሬው ጥረት የነገው ህይወት!

📚 ውድ ተማሪዎች፣ የትምህርት ጉዟችሁ በራሱ ትልቅ የጀግንነት ታሪክ ነው። ይህ ታሪክ የእያንዳንዳችሁ ልዩ ልምድ፣ የእድገት እና የለውጥ ውብ ሂደት ነው። በእያንዳንዱ ምዕራፍ የምታገኙት እውቀት፣ የምትሰሩት ልምምድ እና የምትደርሱበት ደረጃ የወደፊት ህይወታችሁን የሚቀርጽ የጥንካሬ መሰረት ይጥላል።

📚 ይህ ጉዞ ሁልጊዜ ቀላል ላይሆን ይችላል፤ ፈተናዎች እና እንቅፋቶች ሊያጋጥሟችሁ ይችላሉ። አንዳንድ ጊዜ ነገሮች ከባድ መስለው ይታዩ ይሆናል፣ እናም ድካም ወይም ተስፋ መቁረጥ ሊሰማችሁ ይችላል። ነገር ግን፣ አስታውሱ፣ እነዚህ ሁሉ የሂደቱ አካል ናቸው። እነዚህ መሰናክሎች እንድትጠነክሩ፣ እንድትማሩ እና ይበልጥ እንድታድጉ የሚረዷችሁ ናቸው። "ውድቀት" የስኬት አንዱ አካል ነው።

📚 በእያንዳንዱ ችግር ውስጥ የተደበቀ ትምህርት እንዳለ እወቁ። ዛሬ የምትዘሩት የትጋት ዘር ሁሉ ለነገው ስኬታችሁ ወሳኝ መሠረት ነውና! የትምህርት አጋጣሚያችሁን በአግባቡ ተጠቀሙበት፤ ምክንያቱም እያንዳንዱ የትምህርት ቀን አዲስ ዕድል፣ አዲስ የመማሪያ እና የማደግ አጋጣሚ ነው። እያንዳንዱ ትምህርት ቤት የምትሄዱበት ቀን ለራሳችሁ፣ ለቤተሰባችሁ እና ለአገራችሁ የምታደርጉት ኢንቨስትመንት ነው።

ጥንካሬያችሁ፡ ተስፋን መቼም አለመቁረጥና መሰናክሎችን መግፋት!

📚 በውስጣችሁ ያለውን ታላቅ ጥንካሬ አውጡ! እያንዳንዱ ውድቀት የመማሪያ ትምህርት እንደሆነ አስቡት፣ እናም ወደፊት ለመራመድ የሚያስችል አዲስ መንገድ እንደሚያሳያችሁ እመኑ። ስህተት መስራት የሰውነት ባህሪ ቢሆንም ከስህተት መማር ግን ብልህነት ነው። ሁሌም ሞክሩ! ደጋግሞ መሞከር ለስኬት ወሳኝ ነው። ብዙ ታላላቅ ፈጠራዎች እና ግኝቶች የተገኙት ከተደጋጋሚ ሙከራዎች እና ውድቀቶች በኋላ ነው።

አዎ! ደጋግሞ ወድቆ ደጋግሞ ሳይነሳ፤ ከፍ ብሎ የሚበር የለም!!

📚 ታዋቂው ሳይንቲስት ቶማስ ኤዲሰን የኤሌክትሪክ አምፖልን ከመፍጠሩ በፊት በሺዎች የሚቆጠሩ ጊዜያት ሳይሳካለት ቀርቷል፤ ነገር ግን ተስፋ ባለመቁረጡ፣ ዓለም የምታበራውን መብራት አበረከተላት። እናንተም እንደዛው ተስፋ የማትቆርጡ ከሆነ የሆነ ሙከራችሁ መሳካቱ አይቀሬ ነው!!

⭕️ አዎ! ተስፋ አትቁረጡ! በጽናት ከቀጠላችሁ፣ ምንም ያህል ከባድ ቢሆንም የምትፈልጉትን ግብ ማሳካት እንደምትችሉ እወቁ። አስታውሱ፡ "ወንዝ የሚሻገረው በድፍረት እንጂ በመቆም አይሆንም!" ድፍረት ይኑራችሁ፣ ወደፊት ሂዱ! መሰናክሎች ሲያጋጥሟችሁ እንደ መጨረሻ አትዩዋቸው፤ ይልቁንም እንደ ፈተና እና ጥንካሬያችሁን የምታሳዩበት አጋጣሚ ተመልከቷቸው።

ብሩህ ተስፋ፡
📚 የእውቀት ኃይል ተጠቀሙበት እና የወደፊት ብሩህ ተስፋ ይኑራችሁ! በጥረታችሁ እና በትጋታችሁ ታላቅ ነገር መፍጠር እንደምትችሉ እመኑ።

የዛሬው ጥረታችሁ የነገ ህይወታችሁን ይመሰርታል። ስለዚህ፣ በትጋት አጥኑ፣ አዳዲስ ነገሮችን ለመማር ጓጉ፣ እና እርስ በርስ ተጋገዙ። የቡድን ስራ እና መረዳዳት የትምህርት ጉዞአችሁን የበለጠ ፍሬያማ ያደርገዋል። እርስ በርሳችሁ ተደጋገፉ፣ እውቀትን ተለዋወጡ፣ እና አብራችሁ ማደግን ተማሩ። እውቀት ሃይል ብቻ ሳይሆን መጨለማ ጉዞ መንገድን የሚያቅጣጭ ብርሃን ነውም ጭምር!፣ እናም በአላህ እርዳታ እናንተ የዚህ ሃይልና ብርሃን ባለቤቶች ናችሁ። ይህ ኃይልና ብርኃን የወደፊት ህይወታችሁን ብቻ ሳይሆን፣ ቤተሰባችሁን፣ ማኅበረሰባችሁን እና አገራችሁን የመለወጥ አቅም አለው።

እውቀታችሁን ለበጎ ነገር ተጠቀሙበት። ዓለም የእናንተን አስተዋጽኦ ትፈልጋለች። እያንዳንዱ ያገኛችሁት ዕውቀት ለእናንተም ሆነ ለሌሎች በጎ ነገሮችን ለመፍጠር የሚያስችል ብርሃን ይሁን። በዓለም ላይ መልካም ለውጥ ለማምጣት የእናንተ ብቃት እና ትጋት ወሳኝ ነው።

መትጋትና በራስ መተማመን፡ ገደብ የለሽ አቅም እና ታላቅነት

📚 ያለማቋረጥ በመትጋትና በራስ በመተማመን፣ ህልሞቻችሁን እውን ማድረግ ብቻ ሳይሆን፣ ለአገራችሁ እና ለዓለም ትልቅ አስተዋጽኦ ማድረግ ትችላላችሁ። ስኬት የፅናት ውጤት ነው፤ ተስፋ እስካልቆረጣችሁ ድረስ መማር፣ ማደግ እና ማሸነፍ ትችላላችሁ።

📚 በራሳችሁ ተማመኑ፣ አቅማችሁን እወቁ። ወሰኖችን የሚያስቀምጠው የራሳችሁ አስተሳሰብ እንጂ ውጫዊ ሁኔታ አይደለም። ውስጣችሁ ያለውን እምቅ ኃይል አውጡት። እያንዳንዳችሁ ልዩ የሆነ ተሰጥኦ እና አቅም አላችሁ። ያንን አቅም ለማውጣት አትፍሩ።

📚 ከዚህ በፊት ማንም ያላሰበውን ነገር ለማሰብ፣ ማንም ያልሰራውን ለመስራት ድፈሩ። የዓለምን ታሪክ የቀየሩ ታላላቅ ሰዎች የተለዩ ስላልሆኑ ሳይሆን፣ በራሳቸው ስላመኑ እና ተስፋ ስላልቆረጡ ነው። እናንተም ያን ማድረግ ትችላላችሁ። የዛሬው ጥረታችሁ፣ ትጋታችሁ እና ጽናታችሁ ለታላቅ የወደፊት ሕይወት መሠረት ይሆናል። ህልሞቻችሁን እውን ለማድረግ የማትታክቱ ከሆነ፣ ዓለም በእርምጃችሁ ወደ መልካም ትሸጋገራለች።

⭕️ አስታውሱ፣ የትምህርት ጉዞአችሁ የእድሜ ልክ የመማር ሂደት መጀመሪያ እንጂ መጨረሻ አይደለም። ሁልጊዜ አዳዲስ ነገሮችን ለመማር ዝግጁ ሁኑ፣ የማወቅ ጉጉታችሁን አትግደሉ። ራሳችሁን አዳዲስ ፈተናዎች ላይ ጣሉ፣ እና ከመጽናናት ፈጥናችሁ ለመውጣት አትፍሩ። ይህን ስታደርጉ፣ የምትችሉት ነገር ወሰን እንደሌለው ትገነዘባላችሁ።

መልካም የትምህርት ጊዜ! በጉዟችሁ ሁሉ መልካም ዕድል እመኛለሁ።

════════════════
📚 ጠንካራ ተስፋዎቻችን የህልሞቻችን ክንፎች ናቸው!

📚 የዛሬ እርምጃዎቻችን የነገ ስኬቶቻችን ናቸው!

════════════════
ቀን:- ሐምሌ 23/2017 ዓ.ል [ሰፈር 05/1447 አ.ሒ]

✍️ በረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል
👍2
Python ለመማር አስባችሁ ከሆነ አልያም ገና እየጀመራችሁ ከሆነ እነዚህን ድረገጾች ሞክሯቸው።

https://www.programiz.com/python-programming
በቀላል አገላለፅ እና በቀላል ምሳሌ python መማር ያስችላል።

https://www.w3schools.com/python/
አብዛኞቻችሁ ታውቁታላችሁ ለጀማሪ የሚሆን ትምህርት በሚገባ ታገኙበታላችሁ። ከpython በተጨማሪም ሌሎች programming languages መማር ትችላላችሁ።

https://docs.python.org/3/tutorial/
የpython official documentation የምታገኙበት ሲሆን። አገላለፁ ትንሽ ጠጠር ስለሚል ቅድሚያ የpythone basic ብታጠኑ ይመረጣል።

https://www.geeksforgeeks.org/python/python-lists/
ከቀላል እስከ ከባድ የpython tutorial የምታገኙበት ድረገጽ ነው።

©bighabesha
4👍2
📩 Ethiocoders ማማር የጀመራችሁ እስቲ እጃችሁን አንሱ!

1. አልተማርኩም 👎

2. ተምሬ ሰርተፊኬት አግቻለሁ ❤️

3. እየተማርኩ ነው 👍

4. ስለምትለው Ethiocoders ምንም አላውቅም 😭
#ChatGpt

ChatGpt study and learn (study mode) የተሰኘና ተማሪዎችን ይበልጥ ተጠቃሚ የሚያደርግ feature አስተዋወቀ።

ይህም ጥያቄ ሲጠየቅ ቀጥታ መልሱን ከመስጠት ይልቅ step by step እኛንም በመሃል እየጠየቀን explain ያደርግልናል።

ተማሪዎች study modeን የቤት ስራ በሚሰሩበት ጊዜ፣ ለፈተና በሚዘጋጁበት ጊዜ እና ስለ አዳዲስ ነገሮች ማወቅ ሲሹ ቢጠቀሙ ውጤታማ እንደሚሆኑ ተመላክቷል።

study mode አሁን ላይ ለ free, pro እና ለplus ተጠቃሚዎች Available ነው። ተጠቃሚዎችም website ላይ tools የሚለውን ከነኩ በኋላ study and learn የሚለውን በመምረጥ እና በአፕሊኬሽን ደግሞ የፎቶ icon ከነኩ በኋላ study and learn የሚለውን በመምረጥ ይህንን feature መጠቀም ይችላሉ።

©bighabesha
6👍1
🎓 A Fearless Mind and Heart can Communicate Fearlessly!
════════════════
🎓 ፍርሃት የሌለበት አዕምሮ እና ልብ ያለ ፍርሃት ይግባባሉ!!
════════════════
⭕️ ለዚህ ደግሞ:- ሁሌም አዲስ ነገር መማር፣ ተስፋ አለመቁረጥ፤ ሁሌም መሞከር... በጣም አስፈላጊ ነው።

✍️ Reshad Ibnu Muzemil
#እንድታውቁት

ethiocoders (udacity) ላይ ተምራችሁ ሰርተፍኬስ ልትቀበሉ ስትሉ ሰርተፍኬት ካልሰጣትሁ የትምህርት ማጠናቀቂያው ቀነ ገደቡ አልፏል ማለት ነው።

ለአንድ course 8 ሳምንት ሲሆን የሚሰጣችሁ። በዚህ ጊዜ ውስጥ ካላጠናቀቃችሁ ሰርተፍኬት ላታገኙ ትችላላችሁ። ነገር ግን 8 ሳምንት ሳይሞላ ትምህርታችሁን መጨረስ ትችላላችሁ።

ትምህርቱን የጀመራችሁበትን ቀን ለማወቅ ከፈለጋችሁ በምስሉ ላይ እንደምትመለከቱት ወደ transcript በመግባት Enrolled on ከሚለው አጠገብ መመልከት ትችላላችሁ።

©bighabesha
👍4