✅ ጉዳዩ፡- የ2018 ትምህርት ዘመን ለኮተቤ ሳይንስ ሼርድ ካንፓስ የ9ኛ ክፍል የተማሪዎች
ውድድርን ስለማሳወቅ፤
📚 ኮተቤ ትምህርት ዩኒቨርሲቲ የኮተቤ ሳይንስ ሼድ ካንፓስ 9ኛ ክፍልን በ8ኛ ክፍል በከተማ አቀፍ ፈተና ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡትን ተማሪዎች በማወዳደር በማስተማር ላይ ይገኛል፡፡
📚 በ2017 ትምህርት ዘመን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ውስጥ 8ኛ ክፍል ተምረው ከፍተኛ ውጤት በማምጣት ወደ 9ኛ ክፍል የተዘዋወሩ ተማሪዎች የኮተቤ ሳይንስ ሼርድ ካምፓስ አወዳድሮ በ2018 ትምህርት ዘመን ቅበላ ያደርጋል፡፡
⭕️ ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩ መስፈርቶችን የሚያሟሉ ተማሪዎች ሳይንስ ሼርድ ካምፓስ መወዳደር ይችላሉ፡፡
1. በ2017 ትምህርት ዘመን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 8ኛ ክፍል በመንግስትና የግል ት/ቤቶች በመማር ላይ የነበረ/ች፤
2. በ2017 ትምህርት ዘመን በ8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና አማካኝ /Average/ ውጤት 80% እና በላይ ያስመዘገበ/ች፤
3. በ2017 ትምህርት ዘመን በስነምግባሩ/ሯ በትምህርት ቤቱ የተመሰገነ/ች፤
4. የምዝገባ ቀን ሐምሌ 14 ቀን እስከ 18 ቀን 2017 E.C ይካሄዳል፤
5. መመዝገቢያ ቦታ፡- የኮተቤ ሳይንስ ሼርድ ካምፓስ፤
6. የፈተና ቀን ሐምሌ 23 ቀን 2017 E.C የሚሰጥ መሆኑ ታውቆ ይህ ደብዳቤ በሁሉም ትምህርት ቤቶች ተደራሽ እንዲሆን አሳስባለሁ፡፡
⭕️ 📚 ከዚህ ምዝገባና ፈተና ወቅት ቀድሞም እንዲሁም ዘግይቶ የመጣ አይስተናገድም፡፡
https://t.me/Grade8Info

❤2
የተለያዩ ቪዲዮዎችን በAI generate ማድረግ ከፈለጋቸው በዚህ የCapcut Website ላይ መስራት ትችላላችሁ።
https://pippit.capcut.com/
በጣም ደስ የሚለው feature የፈለጋችሁትን ዌብሳይትም ይሁን የsocial media link አስገብታችሁለት የሚገርም video generate ያደርግላችኋል።
🎓 በጣም አሪፍ website ነው ሞክሩት።
©️bighabesha

Samsung የትኛዎቹ AI ፊቸሮችን ነፃ እደሚያደርግ ይፋ አደረገ።
Samsung በ2025 መጨረሻ ሁሉንም Galaxy AI ፊቸሮች ማስከፈል እንደሚጀምር ሲነገር ነበር። ነገር ግን ሰሞኑን ባወጣው መግለጫ የትኞቹ ፊቸሮች ነፃ እንደሚሆኑ ይፋ አድርጓል።
የSamsung Galaxy AI ፊቸሮች በሁለቱ ይከፈላሉ።
የመጀመሪያው በSamsung በራሱ develop የተደረጉ ሲሆን ሌላው በGoogle develop የተደረጉ Gemini powered የሆኑ ናቸው።
📚 Samsung ባወጣው መግለጫ በራሱ develop የተደረጉት በሙሉ ነፃ የሚሆኑ ሲሆን ከእነዚህ መካከል:
✅ Audio Eraser
✅ Object Eraser
✅ Note Assist
✅ Generative Wallpapers
✅ Live Translate
✅ Writing Assist ናቸው።
📚 ሌሎች Gemini powered የሆኑት:
✅ Gemini as Google assistant replacement
✅ Circle to search
✅ Gboard AI features
✅ Gemini nano (on-device AI)
✅ Call & sefety features
የመሳሰሉት ደግሞ በSamsung ብቻ የሚወሰኑ ስላልሆኑ ለጊዜው ነፃ ቢሆኑም ወደፊት ነፃ ሆነው ስለመቆየታቸው የታወቀ ነገር የለም።

❤1
የቀድሞው የTwitter co-founder እና CEO የነበረው Jack Dorsey ያለምንም sim card እና internet network በBluetooth ብቻ text message መላላክ የሚያስችላችሁ አፕሊኬሽን ይፋ አድርጓል።
⚫አፕሊኬሽኑ Bitchat ይባላል።
⚫ከPlaystore ላይ አውርዳችሁ መጠቀም ትችላላችሁ።
https://play.google.com/store/apps/details?id=dev.hostingduty.bitchat
⚫አፕሊኬሽኑን ለመጠቀም አካዉንት መክፈት አይጠይቅም።
⚫ምንም አይነት Server ስለሌለው end-to-end encrypted ነው። ያ ማለት 3ኛ ወገን የምንፃፃፈውን ሊያይ አይችልም።
Bluetooth በ10 ሜትር ርቀት ስለሚሰራ text መላላክ የምንችለው በ10 ሜትር ርቀት ብቻ ነዉ ? የሚል ጥያቄ መነሳቱ አይቀርም።
ነገር ግን ከዛም በላይ መላላክ እንችላለን። ምክንያቱም በአካባቢያችን ብዙ ተጠቃሚዎች ካሉ የሚፈጠሩት ትንንሽ ኔትዎርኮች ሌላ ትልቅ mesh network እየፈጠሩ ሰፊ ክልል እንዲያካልሉ ያስችላሉ።
ይህ ቴክኖሎጂ በጣም ብዙ አይነት ጠቀሜታዎች አሉት።
⚫የስልክ ኔትዎርክ በሌለባቸውና አደጋ በሚያጋጥማቸው አካባቢዎች communication እንዲኖር ያስችላል።
⚫Security ለሚያሳስባቸው ሰዎች ከፍተኛ ጠቀሜታ አለዉ።

❤1👍1
Open Ai አዲስ Chatgpt Agent አስተዋወቀ።
እያደር ብዙ ነገሮችን እየጨመረ የመጣው OpenAi አዲስ የchat gpt agent አስተዋወቀ። ይህም የተለያዩ ስራዎችን እኛን ተክቶ መስራት ይችላል።
የራሱን ኮምፒውተር በመጠቀም የተለያዩ ውስብስብ ተግባራትን መከወን ይችላል ሲል ካምፓኒው አትቷል።
ተጠቃሚዎች ይህንን Agent እንደ browsing ማለትም ድረገፆች ላይ የተለያዩ ስራዎችን እንዲሰራ፣ code run እንዲያደርግ፣ እንደ gmail እና calander ያሉ መተግበሪያዎች ላይ login አድርጎ በርካታ ስራዎችን እንዲሰራ እንዲሁም ውስብስብ የሆኑ ስራዎችን እንዲከውን ማዘዝ ይችላሉ።
ይህ Agent ግዢ ከመፈፀምና email ከማድረጉ በፊት የናንተን permission/ፍቃድ ይጠይቃል። እንዲሁም እንደ financial ያሉ ተግባራት ላይ እናንተ የሱን ተግባር የምትቆጣጠሩት ይሆናል። ይሁንና ያዘዛችሁት ተግባር እንዲቋረጥ ከፈለጋችሁ ማቋረጥ ትችላላችሁ ተብሏል።
©bighabesha

👍4❤2
📱Instagram ላይ ሌሎች ሰዎችን invite በማድረግ አካውንታችሁን control እንዲያደርጉላችሁ ማድረግ ትችላላችሁ።
ይህን ለማድረግ አካውንታችሁ ላይ Login ማድረግ አይጠበቅባቸውም።
⚫Instagram ከፍታችሁ ፕሮፋይላችሁ ላይ ከገባችሁ በኋላ 3 ሰረዙን ትነካላችሁ።
⚫ታች ላይ shared access የሚል ምርጫ ታገኛላችሁ።
⚫invite new people የሚለውን መርጣችሁ የፈለጋችሁትን ሰው instagram account search አድርጋችሁ invitation ትልኩለታላችሁ።
✔️ይህን invitation ከተቀበላችሁ በእናንተ አካውንት Post ማድረግ፣ Like ማድረግ እንዲሁም comment መፃፍ ይችላል።
✔️አካውንታችሁን disable ማድረግ ወይም account information (username, Display name) መቀየር ግን አይችልም።
✔️የinbox እና የstory access enable/disable ማድረግ ትችላላችሁ።

❤4
Basic Computer Skills
Photo
💬 Alhamdulillah
💫 Hopes are the Wings of Dreams. Never stop hoping, never stop dreaming.
════════════════
✅ ለተማሪዎች የተላለፈ መልዕክት። ✅
የላቀ የወደፊት ዕድል ለመፍጠር!
እያንዳንዱ ጉዞ የሚጀምረው በአንድ እርምጃ ነው። በጋለ ስሜትና በትጋት ደግሞ ያ እርምጃ ታሪክ የሚሰራ ቅርስ ይሆናል። ይህ ሰርተፍኬት እናንተም ታላቅ ደረጃ ላይ መድረስ እንደሚችሉ ማስታወሻ ይሁንልኝ!
📚 ስኬት የዕድል ጉዳይ አይደለም፤ የጥረትን፣ የመማርን እና በየቀኑ ጥረት የማድረግ ውጤት ነው። በጽናት ከሰሩ፣ የማይቻል ነገር የለም!
📚 Artificial Intelligence (AI) / (ሰው ሰራሽ አስተውሎት): የወደፊት ብቻ አይደለም፤ የእናንተ የዛሬው ዕድል ነው። መማር ጀምሩ፣ የማወቅ ጉጉታችሁን አጧጥፉት፣ እና ለነገ ስኬትን የሙከራ እርምጃ ጀምሩ። ይህ ዘርፍ ገደብ የለሽ ዕድሎችን ይዟል፤ እናንተም የዚህ አካል መሆን ትችላላችሁ።
⭕️ ምናልባት አሁን በጥያቄዎችና በጥርጣሬዎች የተሞሉ ሊሆኑ ይችላሉ። ነገር ግን በትኩረትና በእምነት እነዚያን ጥያቄዎች ወደ ብቃት መቀየር ይቻላል። አሁን የእናንተ ተራ ነው! እያንዳንዱ ጥረታችሁ ፍሬ ያፈራል። ኢንሻአላህ!
ያለፈው ሁኔታችሁ ገደባችሁን አይወስንም፤ የአዕምሮአችሁ ሁኔታ ነው የሚወስነው። ወሰኖችን አፍርሷቸው፣ መሰናክሎችን ጣሷቸው (ሰባብሯቸው)፣ እና ብቃታችሁን ተጠቀሙበት! በውስጣችሁ ያለውን እምቅ ኃይል አውጡት።
📚 እያንዳንዱን ትንሽ ድል አክብሩ። ይህ ሰርተፍኬት መጨረሻው አይደለም። በአላህ ፍቃድ ከእናንተ ጋር በፈጠራ እና በለውጥ ወደተሞላ የወደፊት ጊዜ የሚወስድ ወሳኝ ምዕራፍ ነው። ለበለጠ ስኬት መነሻ ይሁን።
📚 ዕድልን አትጠብቁ። ለዕድል ተዘጋጁ ። ተማሩ፣ እደጉ፣ አሁንም አድጉ! እናም በሩ ሲከፈት፣ በልበ-ሙሉነት ለመግባት ዝግጁ ትሆናላችሁ። የእውቀት ፍለጋችሁ መቼም አታቁሙ።
ይህን አስደናቂ ትምህርት ለመማር እና ህይወታችሁን ለመለወጥ ይህ ትልቅ አጋጣሚ እንደሆነ ተስፋ አደርጋለሁ።
ምን ትጠብቃላችሁ ታዲያ⁉️
════════════════
📚 ጠንካራ ተስፋዎቻችን የህልሞቻችን ክንፎች ናቸው!
📚 የዛሬ እርምጃዎቻችን የነገ ስኬቶቻችን ናቸው!
ቀን:- ሐምሌ 14/2017 ዓ.ል [ሙሐረም 27/1447 አ.ሒ]
✍️ በረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል

የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) እና የምስል ፈጠራው‼
============================
✍️ በዘመናችን የቴክኖሎጂ እድገት ውስጥ፣ ሰው ሰራሽ የማሰብ ችሎታ (Artificial Intelligence - AI) ግንባር ቀደም ሆኖ ብቅ ብሏል። በተለይም ምስሎችን እና ቪዲዮዎችን ከመፍጠር፣ ከማሻሻል እና ወደ ተለያዩ አይነቶች ከመቀያየር ጋር ተያይዞ የሚያቀርባቸው አስደናቂ ችሎታዎች ብዙ ጥያቄዎችን አስነስተዋል። እንደ ሙስሊም የእነዚህን መሳሪያዎች አጠቃቀም ኢስላማዊ ብይን መረዳት እጅግ አስፈላጊ ነው።
1⃣) AI ምስሎችን እና ቪዲዮዎችን እንዴት ይፈጥራል?
ስለ ሐራም ሐላልነቱ ከመናገራችን በፊት AI እንደት ፎቶዎችንና ቪድዮዎችን እንደሚያቀናብርና እንደሚፈጥር እንመልከት።
የ AI ምስል አመንጪ መሳሪያዎች (AI Image Generators) ግልፅ ያልሆኑ ብላክ ቦክሶች "ጥቁር ሳጥን" ወይም ምትሃቶች አይደሉም። እነሱ የተገነቡት ውስብስብ በሆኑ የሒሳብ ሞዴሎች እና ስልተ ቀመሮች (algorithms) ላይ ነው። አሠራራቸውን በቀላሉ ለመረዳት በሁለት ዋና ዋና ሞዴሎች እንከፍላቸዋለን፡-
1⃣Generative Adversarial Networks (GANs): ይህ ሞዴል ሁለት ክፍሎችን ያቀፈ ነው፤ "ጄነሬተር" (the Generator) እና "ዲስክሪሚኔተር" (the Discriminator)።
☑ ጄነሬተሩ (The Forger): ልክ እንደ ሰዓሊ ወይም አታላይ፣ ከስልጠና መረጃው (dataset) የተማረውን መሰረት በማድረግ አዲስ ምስል ለመፍጠር ይሞክራል።
☑ዲስክሪሚኔተሩ (The Detective): ልክ እንደ መርማሪ፣ ጄነሬተሩ የፈጠረው ምስል እውነተኛ (ከስልጠና መረጃው ውስጥ ያለ) ነው ወይስ የውሸት (በጄነሬተሩ የተፈጠረ) መሆኑን ለመለየት ይሞክራል።
ይህ "የፉክክር" ሂደት በሚሊዮን ጊዜያት ይደጋገማል (በተደጋጋሚ train ይደረጋል!)። ጄነሬተሩ ዲስክሪሚኔተሩን ለማታለል እየተሻሻለ ሲሄድ፣ ዲስክሪሚኔተሩ ደግሞ የውሸት ምስሎችን በመለየት እየተሻሻለ ይሄዳል። የVAE አሠራርን የተማራችሁ የኤአይ ሪሰርቸሮች ካላችሁ በቀላሉ ትረዱኛላችሁ። በመጨረሻም ጄነሬተሩ በጣም ከፍተኛ ጥራት ያላቸው እና እውነተኛ የሚመስሉ ምስሎችን መፍጠር ይጀምራል።
ይህ ቴክኖሎጂ ቀደም ባሉት የ AI ሞዴሎች ውስጥ በስፋት ጥቅም ላይ የዋለ ሲሆን፣ ለምሳሌ እንደ NVIDIA's StyleGAN (በጣም እውነተኛ የሚመስሉ የሰው ፊት ምስሎችን በመፍጠር የሚታወቀው) እና Artbreeder (ያሉትን ምስሎች በማቀላቀል አዲስ ለመፍጠር የሚያስችለው) ያሉ መሳሪያዎች በዚህ መርህ ላይ የተመሰረቱ ናቸው።
2⃣Diffusion Models: ይህ በአሁኑ ጊዜ በጣም ተወዳጅ እና ከፍተኛ አቅም ያለው ዘዴ ነው። አሠራሩም፡
🔗ስልጠና (training)፡ ሞዴሉ በሚሊዮን የሚቆጠሩ እውነተኛ ምስሎችን ይመለከታል። በእያንዳንዱ ምስል ላይ ቀስ በቀስ visual noise በመጨመር ምስሉ ሙሉ በሙሉ ወደ ኖይዝነት እስኪቀየር ድረስ ያለውን ሂደት ይማራል።
🔗ምስል መፍጠር፡ ተጠቃሚው የጽሑፍ ትዕዛዝ (prompt) ሲሰጥ (ለምሳሌ "A horse running on a beach during sunset")፣ ሞዴሉ ከኖይዝ ይጀምርና በስልጠናው የተማረውን ተቃራኒ ሂደት በመጠቀም ኖይዙን ደረጃ በደረጃ እያስወገደ የተሰጠውን ትዕዛዝ የሚያሟላ አዲስ ምስል ይፈጥራል።
ይህ ቴክኖሎጂ በአሁኑ ጊዜ ገበያውን የሚመሩት የ AI መሳሪያዎች የሚጠቀሙበት ነው። ለምሳሌ፦ ለምስል ፈጠራ የምናውቃቸው እንደ OpenAI's DALL-E 3, Midjourney, እና Stable Diffusion ያሉ መሳሪያዎች በሙሉ በዚህ ሞዴል ላይ የተገነቡ ናቸው። ያው ቻትጅፒቲ ራሱ ይሄ ተገጥሞለት ነው።
በተመሳሳይ፣ ለቪድዮ ፈጠራ ግንባር ቀደም የሆኑት እንደ OpenAI's Sora, Runway Gen-2, እና Pika Labs እንዲሁም የጎግል Veo ያሉ መተግበሪያዎችም የ Diffusion ሞዴልን ወይም የእሱን variants ይጠቀማሉ።
🎙ዋናው ነገር በሁለቱም አጋጣሚዎች AI "በራሱ ፈቃድ" አይፈጥርም። ይልቁንም፣ ከግዙፍ የመረጃ ቋት (database) የተማራቸውን ስልቶች (patterns) በመጠቀም፣ በተጠቃሚው ትዕዛዝ እና ቁጥጥር ስር ሆኖ እንደ አንድ እጅግ የላቀ መሳሪያ ሆኖ ያገለግላል።
ስለዚህ አንድ ሰው በብሩሽ ወይም በእርሳስ እንደሚስለው ሁሉ፣ AI ን በመጠቀም ምስል «እንዲፈጠር ማዘዝ» የሰውየው ድርጊት አካል ነው።
2⃣ በኢስላም የምስል ፈጠራ መሰረታዊ መርሆዎች፦
ወደ AI ከመግባታችን በፊት፣ ኢስላም በአጠቃላይ ስለ ምስል ፈጠራ (التصوير) ያለውን አቋም መረዳት አለብን። ዋናው መነሻ ነጥብ የአላህን የፈጠራ ባህሪ ለመጋፋት ወይም ለመምሰል (مشابهة بخلق الله) መሞከርን የሚከለክሉ ነብያዊ ሐዲሶች ናቸው።
ውዱ ነቢይ (ሶለዋቱ ረቢ ዓለይሂ ሰላሙ) እንዲህ ብለዋል፡-
«እነዚህን ምስሎች የሚሠሩ ሰዎች በትንሳኤ ቀን ይቀጣሉ። 'የፈጠራችሁትን ሕያው አድርጉ!' ይባላሉ።»
ይህ ክልከላ በዋነኝነት የሚያተኩረው ነፍስ ባላቸው ነገሮች (ذوات الأرواح) ማለትም በሰው፣ በእንስሳት እና በአዕዋፍ ምስሎች ላይ ነው። የዚህ ክልከላ ጥበብ ከጣዖት አምልኮ መራቅ እና የአላህን ብቸኛ የፈጣሪነት ባህሪ ማክበር ነው።
ሆኖም እስልምና ተራማጅ እና ተግባራዊ መፍትሄዎችን የሚያቀርብ ኃይማኖት እንደመሆኑ፣ የዲኑ ሊቃውንት ከእነዚህ መርሆዎች በመነሳት የተለያዩ ዝርዝር ህጎችን አስቀምጠዋል፡-
⬇️ ያልተሟላ ምስል፡ ምስሉ ህይወት ያለው ነገርን የሚወክል ቢሆንም፣ ህይወት ሊኖረው የማይችልበት ወሳኝ አካሉ ከጎደለ (ለምሳሌ ጭንቅላት ከሌለው ወይም የሰውነት ግማሽ ብቻ ከሆነ) ክልከላው አይመለከተውም። ኢማም ኢብኑ ቁዳማህ እንደገለጹት፣ «ምስል ማለት ጭንቅላቱ ነው። ጭንቅላቱ ከተቆረጠ ምስል አይደለም።!»
ይህ አቡ ሁረይራ ካስተላለፉት የጂብሪል ታሪክ የተወሰደ ነው።
⬇️ህይወት የሌላቸው ነገሮች፡ እንደ መልክዓ ምድር (landscape)፣ ህንፃዎች፣ ዛፎች እና ሌሎች ግዑዝ ነገሮች ያሉ ምስሎችን መፍጠር ሙሉ በሙሉ የተፈቀደ ነው።
⬇️ዲጂታል እና ፊዚካል ምስሎች፡ ብዙ የዘመናችን ሊቃውንት በካሜራ የሚነሱ ፎቶግራፎች እና በስክሪን ላይ የሚታዩ ዲጂታል ምስሎች "ምስል መፍጠር" (ተስዊር) ሳይሆን "የጥላ ነፀብራቅን ማቆየት" (حبس الظل) በሚለው ስር እንደሚወድቁ ይገልጻሉ።
እነዚህ ምስሎች በወረቀት፣ በግድግዳ ወይም በሌላ ቋሚ ነገር ላይ እስካልታተሙ ድረስ፣ እንደ ጊዜያዊ የብርሃን ቅንጅት ስለሚቆጠሩ ክልከላው እንደማይጠናከርባቸው ያስረዳሉ።
3⃣ የ AI ምስል ፈጠራን ከኢስላማዊ መርሆዎች ጋር ማገናዘብ፦
ከላይ የተገለጹትን የቴክኖሎጂ አሠራር እና የሸሪዓ መርሆዎችን መሰረት በማድረግ፣ የAI ምስል ፈጠራን ብይን በሚከተሉት ነጥቦች መተንተን እንችላለን።
☑የድርጊቱ ባለቤትነት (Attribution of the Act):
አንድ ሰው ለ AI ስርዓት «የአንበሳ ምስል ሳልልኝ!» ብሎ ሲያዝ፣ ምንም እንኳን ሥራውን የሚሰራው ማሽኑ ቢሆንም፣ ድርጊቱ የታዘዘው እና የተጀመረው በሰውየው ነው። AI እዚህ ላይ እንደ ብዕር፣ እንደ ኮምፒውተር ወይም እንደ ቀለም አይነት መሳሪያ ነው። ስለዚህ የድርጊቱ ሐላል ወይም ሐራምነት በትዕዛዙ እና በውጤቱ ላይ ይመሰረታል። ሰውየው መሳሪያውን አንድ ነገር እንዲስል ሲያዝ እና እሱ እንዳዘዘው ሲፈጽም፣ ይህ የስዕልን ህግ ሊይዝ ይችላል።

ℛℯ𝓈𝒽𝒶𝒹 ℳ𝓊𝓏ℯ𝓂𝒾𝓁
Photo
☑ የተፈጠረው ምስል አይነት (Nature of the Image):
☑ ሙሉ እና ህይወት ያለው ምስል፡ ነፍስ ያለው ፍጡርን (ሰው ወይም እንስሳ) ሙሉ አካሉን እና ህይወት ሊኖረው በሚችል መልኩ መፍጠር ከላይ በተጠቀሰው ሐዲሥ መሰረት የተከለከለ ይሆናል። ይህ የአላህን ፈጠራ የማስመሰል ገጽታ ስላለው ነው።
☑ ያልተሟላ ምስል፡ የሰው ወይም የእንስሳ ምስል ነገር ግን ጭንቅላት የሌለው፣ ከወገብ በላይ ብቻ የሆነ፣ ወይም ህይወት ለመቀጠል ወሳኝ የሆነ አካሉ የጎደለው እንዲሆን አድርጎ መፍጠር የተፈቀደ ሊሆን ይችላል።
☑ግዑዝ ነገሮች፡ የህንፃዎች፣ የተፈጥሮ ገጽታዎች፣ መኪናዎች፣ ወይም ምናባዊ ንድፎችን (abstract art) በ AI መፍጠር ሙሉ በሙሉ የተፈቀደ ነው።
☑ የአጠቃቀም አላማ:
ትምህርታዊ እና ሳይንሳዊ ፍላጎቶች፡ ለህክምና፣ ለደህንነት፣ ለትምህርት እና ለሌሎች አስፈላጊ እና ጠቃሚ ለሆኑ ጉዳዮች ምስሎችን መጠቀም በእስልምና (الضرورات تبيح المحظورات) በሚለው መርህ ስር ሊታይ ይችላል።
☑ ለመዝናኛ እና ላልተገባ አላማ፡ ስሜትን የሚቀሰቅሱ፣ ጸያፍ፣ ወይም የሌሎችን ክብር የሚያጎድፉ ምስሎችን መፍጠር በማንኛውም መንገድ የተከለከለ ነው።
☑ ያለውን ምስል ማሻሻል (Modifying Existing Images):
አንድን በካሜራ የተነሳ ፎቶግራፍ ወደ ካርቱን ወይም ስዕል መቀየር፣ ምስሉ ሙሉ እና ህይወት ያለው ከሆነ፣ እንደ አዲስ መሳል ስለሚቆጠር ክልከላው ይመለከተዋል። ነገር ግን ፎቶውን በማሻሻል ያልተሟላ ምስል እንዲሆን ማድረግ (ለምሳሌ: ጭንቅላቱን ማስወገድ ወይም ወደ ረቂቅ ጥበብ መቀየር) ይፈቀዳል።
⬅️ ሲጠቃለል፦
የሰው ሰራሽ የማሰብ ችሎታ (AI) በራሱ ሐላልም ሐራምም አይደለም፤ እሱ መሳሪያ ነው። ብይኑ የሚወሰነው በአጠቃቀማችን ነው። አንዳንድ ሰዎች «ሸሪዓ የቴክኖሎጂን አሠራር ባለመረዳት ይከለክላል!» ብለው ሊያስቡ ይችላሉ። ይህ ስህተት ነው። የእስልምና ህግጋት የተመሰረቱት በማይለወጡ መለኮታዊ መርሆዎች ላይ ነው። ሊቃውንት እነዚህን መርሆዎች በዘመኑ ለሚከሰቱ አዳዲስ ጉዳዮች ላይ እንዴት እንደሚተገበሩ ያመላክታሉ።
ስለዚህ አንድ ሙስሊም የ AI ምስል እና ቪዲዮ ፈጠራ ቴክኖሎጂን ሲጠቀም የሚከተሉትን ነጥቦች ማስታወስ ይገባዋል፡-
☑ ከተከለከሉ ምስሎች መራቅ፡ ነፍስ ያላቸውን ፍጡራን ሙሉ በሙሉ እና ህያው በሚመስል መልኩ ከመፍጠር መቆጠብ።
☑ የተፈቀዱ አማራጮችን መጠቀም፡ ህይወት በሌላቸው ነገሮች (landscapes, objects)፣ ያልተሟሉ ምስሎች እና ረቂቅ ጥበብ (abstract art) ላይ ማተኮር።
☑አላማን ማጥራት: ሥራችን ለአላህ ተቀባይነት ያለው፣ ለሰዎች ጠቃሚ እና ከእስልምና ስነ-ምግባር ጋር የማይጋጭ እንዲሆን መጣር።
☑ ከመጥፎ ነገር መራቅ፡ ቴክኖሎጂውን ለሐሜት፣ ለማጭበርበር (deepfakes)፣ ለብልግና እና ለሌሎች ሐራም ለሆኑ ተግባራት ከመጠቀም ሙሉ በሙሉ መራቅ።
ኢስላም የዕውቀት እና የፈጠራ ኃይማኖት ነው። ቴክኖሎጂን ለኸይር ነገር እስከተጠቀምንበት ድረስ ያበረታታል። AI ትልቅ አቅም ያለው መሳሪያ እንደመሆኑ፣ በእስልምና በተፈቀደው ማዕቀፍ ውስጥ በመቆየት ለዳዕዋ፣ ለትምህርት፣ ለጥበብ እና ለሌሎች በርካታ ጠቃሚ መስኮች ልንጠቀምበት እንችላለን።
ወሏሁ አዕለም – አላህ የበለጠ ያውቃል።
✅ MuradTadesse