Basic Computer Skills
1.86K subscribers
1.22K photos
100 videos
575 files
833 links
#በዚህ የቴሌግራም ቻናል
↪️ Programming
↪️ ቴክኖሎጂ ነክ ትምህርቶችን
↪️ ኮምፒውተር ነክ ትምህርቶችን
↪️Basic Computer Skills
↪️ Software
↪️ AI and AI Skills (Like ChatGPT)

ከላይ የተዘረዘሩትና ሌሎችም ገራሚ ትምህርቶች ይለቀቅበታል!

t.me/BasicComputerSkillsGroup

𝘽𝙮 𝙍𝙚𝙨𝙝𝙖𝙙
Download Telegram
የ2017 የትምህርት ዘመን የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ከተማ አቀፍ ፈተና ውጤት ዛሬ ከሰዓት ይፋ ይሆናል፡፡

(ሰኔ 25/2017 E.C) የ2017 የትምህርት ዘመን የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ከተማ አቀፍ ፈተና ውጤት ዛሬ ከሰዓት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአጠቃላይ ካውንስል አባላት በማለፊያ ነጥቡ ላይ ውይይት ካደረጉ በሃላ ይፋ ይደረጋል።

የ2017 E.C የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ከተማ አቀፍ ፈተና በአጭር ጊዜ ታርሞ ይፋ መደረጉ ተማሪዎች ለቀጣዩ የትምህርት አመት ከወዲሁ በቂ ዝግጅት እንዲያደርጉ የሚያስችል ሲሆን የ2017 የትምህርት ዘመን የ6ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ከሰኔ 10-12/2017 E.C ድረስ በከተማ አስተዳደሩ በሚገኙ 192 የመፈተኛ ጣቢያዎች ለተከታታይ ሶስት ቀናት መሰጠቱ ይታወሳል፡፡ ።
የሙምታዝ ት/ቤት የ6ኛ ክፍል ተማሪዎች (ወንድምና እህቶቻችን) ሙሉ በሙሉ ስላለፉ እንኳን ደስ አላችሁ፤ ደስ ብሎናል።

🎉 🎉 Congratulation 🎉 🎉   🎆

አላህ ከፍ ያለ ደረጃ ያድርሳችሁ። 🤲
አላህ ማህበረሰቡን የምትጠቅሙበትን አቅምና እውቀት ይስጣችሁ። 🤲

✍️ ረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል
3
#Telegram_update
Telegram ሰሞኑን አዳዲስ updates የለቀቀ ሲሆን ከነዚህም መካከል፦

Checklists
Telegram Premium ያላቸው ተጠቃሚዎች የተለያዩ ስራዎችን ለመለየትና ለመቆጣጠር የሚያግዛቸውን checklist መስራት እና በቻቶች ውስጥ ማጋራት ይችላሉ። በተጨማሪም checklists በውስጡ 2 permission ያሉት ሲሆን እነሱም mark tasks as done እና add more items ናቸው። checklist ለመፍጠር መልዕክት መፃፊያ አጠገብ ያለውን የሚድያ እና የፋይል ምልክት በመንካትና checklist የሚለውን በመንካት በቀላሉ ማዘጋጀት ይቻላል።

Suggest Posts in Channels
የቻናል ተከታዮች በሚመቻቸው ቻናል ላይ ከፍያ በመክፈል ማስታወቂያ እንዲነገርላቸው የሚያስችላቸው feature ሲሆን ፖስቱን ያዘጋጁት ሰዎችም ቻናሉ ላይ የሚለቀቅበትን ሰዓት መምረጥ ይችላሉ። ይህም ፖስት እንደ ማስታወቂያና እንኳን ደስ አላችሁ ያሉ መልዕክቶች ሊኖሩት ይችላሉ። ይህንንም ለማድረግ ከቻናሉ mute/unmute button አጠገብ ያለውን የdirect message button በመንካትና የ$ ምልክቱን በመንካት post እንዲደረግላችሁ መጠየቅ ትችላላችሁ።
ክፍያ የሚፈፀመው በstar ሲሆን 35% Telegram ይቆርጣል።

እንዲሁም እናንተ የቻናል ባለቤቶች ከሆናችሁ suggest የተደረገላችሁን post እንዲቀይር መጠየቅ፣ መቀበል እና ውድቅ ማድረግ ትችላላችሁ።

©bighabesha
ai-edge-gallery.apk
115 MB
Google AI edge gallery.apk

የGoogle official app
🔰Google ያልምንም ኔትዎርክ offline የምንጠቀምበት አዲስ AI አስተዋውቋል።
Google edge gallery ይባላል።

ልክ እንደChatGPTና Gemini  የፈለግነውን ነገር መጠየቅ እንችላለን።
ይህን ነገር ለማድረግ መጀመርያ ውስጡ ካሉት ሞዴሎች ውስጥ አንዱን መርጥን ማውረድ ይጠበቅብናል።
ውስጡ 4 አይነት ሞዴሎች አሉት።
Gemma-3n-E2B-it-int4
Gemma-3n-E4B-it-int4
Gemma3-1B-IT q4
Qwen2.5 -instruct q8

ለመሞከር 1.6GB size ያለውን Qwen2.5 -instruct q8 ሞደል አውርዳችሁ መሞከር ትችላላችሁ። ሌሎችን ለመጠቀም Hugging face አካውንት ሊኖራችሁ ይገባል።

አፕሊኬሽኑን ከዚ አውርዱት👇

t.me/BasicComputer_Skills/2692
📚 Basic Computer Skills Training

Introduction
MS-Word (All skills
MS-Excel (All skills)
MS-PowerPoint (Presentation and All skills)
MS-Publisher (Business Card, Brochures, Certificate and etc Designing)
MSW-LOGO Programming
AI Tools skills
LOGO or Profile Designing

⭕️ ስልጠናው ለሁሉም ክፍት ነው (የሙምታዝ ተማሪ ለሆነም ላልሆነም)

ስልጠናው ሲያበቃ Certificate ይኖረዋል!

════════════════
📚 ጠንካራ ተስፋዎቻችን የህልሞቻችን ክንፎች ናቸው!
📚 የዛሬ እርምጃዎቻችን የነገ ስኬቶቻችን ናቸው!


ለበለጠ መረጃ
@ReshadMuzemil


የት/ቤቱ ዳይሬክተር 👇
+251913412926
5
የ2018 የትምህርት ዘመን ዓመታዊ የትምህርት ካላንደር ፡፡


(ሰኔ 30/2017 E.C)


══════════════
🀄🀄ሉን👇👇👇 share👇

Join our channel

t.me/Grade1_4Info

t.me/Grade5and6Info

t.me/Grade7Info

t.me/Grade8Info

t.me/Grade9Info

t.me/BasicComputer_Skills
🐸 Microsoft Office LTSC 2024 for Mac v16.89.2

Microsoft Office LTSC 2024 for Mac v16.89.2 merupakan salah satu software terbaru yang di rancang untuk pekerjaan office yang sangat terkenal dari microsoft untuk pengguna sistem operasi macOS. Terdapat program versi Word, Excel, PowerPoint, Outlook, dan OneNote yang modern, yang menggabungkan antarmuka Office yang familier dengan fitur Mac unik yang Anda sukai.

💠 password: @software_application
💠 download 2 part pada satu folder,
Extract part1 sahaja

💠 saiz selepas extract 2.69 GB
3
#tech_tip
የwindows ተጠቃሚ ከሆናችሁ ኪቦርዳችሁ ላይ የሚገኘውን የwindow key ከሌሎች ቁልፎች ጋር አንድ ላይ በመንካት የምታገኟቸው shortcuts (part 2)

Win + tab = task view ወይም እንደስልክ የተከፈቱ መተግበሪያዎችን ለማየት።
Win + Ctrl + D= አዲስ  virtual desktop ለመፍጠር።
Win + Ctrl + Left/Right= የፈጠርናቸውን virtual desktops ለመቀያየር።
Win + Ctrl + F4= የፈጠርነውን virtual desktop ለመዝጋት።
Win + Print Screen=ኮምፒውተራችን ላይ screenshot ለማንሳት።
Win + Arrow keys= ሁለትና ከሁለት በላይ ነገሮችን ስክሪናችን ላይ ለመክፈት እንጠቀምባቸዋለን። ሞክሯቸው!
Win + Number (1-9)= taskbar (ከታች) pin የተደረጉ መተግበሪያዎችን ለመክፈት ለምሳሌ መጀመሪያ ላይ Microsoft store ከሆነ ያለው Win+1 ስንነካ Microsoft store ይከፈታል።

©bighabesha
5
Basic Computer Skills
Photo
📚 የህልማችሁ ቁልፍ በእጃችሁ ነው! 📚

ውድ ተማሪዎች!
በምስሉ ላይ የምታዩትን ልጅ ተመልከቱት እስኪ። ጠረጴዛው ላይ ቁጭ ብሎ በፈገግታ እየጻፈ ነው፤ በአዕምሮው ግን ወደፊት ምን መሆን እንደሚፈልግ እያሰበ ነው። ዶክተር ሆኖ ሰዎችን ሲያድን፣ ፓይለት ሆኖ አውሮፕላን ሲያበር፣ ወይም መሀንዲስ ሆኖ ትልልቅ ህንጻዎችን ሲገነባ ይታየዋል። እንዴት የሚያስደስት ህልም ነው!
እናንተስ? ወደፊት ምን መሆን ትመኛላችሁ? ምናልባት ዶክተር፣ ፓይለት፣ መሀንዲስ፣ መምህር፣ ፕሮግራመር ወይም ዲዛይነር መሆን ትፈልጉ ይሆናል። እነዚህ ሁሉ በጣም ግሩም ህልሞች ናቸው።

መልካም ነገር ማለም መልካም ነው፤ ነገር ግን የምናልመውን ህልም እውን ለማድረግ የተቻለንን ሁሉ ጥረት ማድረግ አለብን።

ታዲያ ይህንን ጣፋጭ ህልም እውን የምናደርገው እንዴት ነው? መልሱ በጣም ቀላል እና አሁን ባላችሁበት ቦታ ላይ የሚገኝ ነው፤ እርሱም ጠንክሮ መማርና ማንበብ ነው!
ህልማችሁን የምትገነቡበት እውን የምታደርጉት በትምህርታችሁ ነው!

ዶክተር መሆን ከፈለጋችሁ፣ ዛሬ በክፍል የምትማሩት የሳይንስ ትምህርት የሰውነትን አሰራር ለመረዳት የመጀመሪያው እርምጃችሁ ነው።
ፓይለት የመሆን ህልም ካላችሁ፣ የሂሳብ ትምህርት አውሮፕላኑን ለማብረር እና አቅጣጫዎችን ለማወቅ ወሳኝ ነው።
መሀንዲስ ሆናችሁ ድልድይና ህንጻ ለመስራት ስታስቡ፣ ዛሬ የምትሰሯቸው የስዕል እና የሂሳብ መልመጃዎች መሰረታችሁ ናቸው።

📚 ስለዚህ ዛሬ በክፍል ውስጥ የምትማሩት እያንዳንዱ ትምህርት፣ የምትጽፉት እያንዳንዱ አረፍተ ነገር እና የምትፈቱት እያንዳንዱ የቤት ስራ ወደ ህልማችሁ የሚወስዳችሁ አንድ መንገድ መሆኑን አስታውሱ።

⭕️ ተስፋ አትቁረጡ፣ ሁሌም ሞክሩ!
አንዳንድ ጊዜ ትምህርት ከባድ ሊሆን ይችላል። አንድ የሂሳብ ቀመር ሊከብዳችሁ ወይም አንድ የእንግሊዝኛ ቃል ሊጠፋባችሁ ይችላል። ይህ ማለት ግን አትችሉም ማለት አይደለም። ተስፋ በፍጹም አትቁረጡ!

➊ ስትሳሳቱ አትፍሩ፦ ስህተት የትምህርት አንዱ አካል ነው። ከስህተታችሁ ትማራላችሁ።
❷ ጥያቄ ጠይቁ፦ ያልገባችሁ ነገር ሲኖር መምህራኖቻችሁን በድፍረት ጠይቁ።
➌ ደጋግማችሁ ሞክሩ፦ አንዴ ካልተሳካላችሁ፣ ደግማችሁ ሞክሩ። ጥረት ማድረግ ውጤት አለው!

📚 መጽሐፍትን ጓደኛችሁ አድርጉ!
ከክፍል ትምህርታችሁ በተጨማሪ መጽሐፍትን ማንበብ አዲስ አለምን ያሳያችኋል። ታሪኮችን፣ ግጥሞችን እና የተለያዩ መረጃዎችን ስታነቡ አዕምሯችሁ ይዳብራል፣ የቃላት እውቀታችሁ ይጨምራል፣ ከሁሉም በላይ ለምህርታችሁ ቅርብ ትሆናላችሁ።

አስታውሱ፣ የወደፊት ህይወታችሁ የሚቀረፀው በዛሬው ጥረታችሁ ነው። ስለዚህ በየቀኑ በደስታና በተነሳሽነት ተማሩ፣ አንብቡ፣ ጥረት አድርጉ። የዛሬው ትንሽ ጥረት የነገውን ትልቅ ህልም እውን ያደርጋል!
በርቱ፣ ጎብዙ! ለሁላችሁም መልካሙን ሁሉ እመኛለሁ!

✍️ በረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል

════════════════
📚 ጠንካራ ተስፋዎቻችን የህልሞቻችን ክንፎች ናቸው!
📚 የዛሬ እርምጃዎቻችን የነገ ስኬቶቻችን ናቸው!

ቀን:- ሐምሌ 6/2017 ዓ.ል [ሙሐረም 18/1447 አ.ሒ]


https://t.me/Grade8Info
3👏1
ጉዳዩ፡- የ2018 ትምህርት ዘመን ለኮተቤ ሳይንስ ሼርድ ካንፓስ የ9ኛ ክፍል የተማሪዎች
ውድድርን ስለማሳወቅ፤

📚 ኮተቤ ትምህርት ዩኒቨርሲቲ የኮተቤ ሳይንስ ሼድ ካንፓስ 9ኛ ክፍልን በ8ኛ ክፍል በከተማ አቀፍ ፈተና ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡትን ተማሪዎች በማወዳደር በማስተማር ላይ ይገኛል፡፡

📚 በ2017 ትምህርት ዘመን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ውስጥ 8ኛ ክፍል ተምረው ከፍተኛ ውጤት በማምጣት ወደ 9ኛ ክፍል የተዘዋወሩ ተማሪዎች የኮተቤ ሳይንስ ሼርድ ካምፓስ አወዳድሮ በ2018 ትምህርት ዘመን ቅበላ ያደርጋል፡፡

⭕️ ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩ መስፈርቶችን የሚያሟሉ ተማሪዎች ሳይንስ ሼርድ ካምፓስ መወዳደር ይችላሉ፡፡

1. በ2017 ትምህርት ዘመን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 8ኛ ክፍል በመንግስትና የግል ት/ቤቶች በመማር ላይ የነበረ/ች፤

2. በ2017 ትምህርት ዘመን በ8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና አማካኝ /Average/ ውጤት 80% እና በላይ ያስመዘገበ/ች፤

3. በ2017 ትምህርት ዘመን በስነምግባሩ/ሯ በትምህርት ቤቱ የተመሰገነ/ች፤

4. የምዝገባ ቀን ሐምሌ 14 ቀን እስከ 18 ቀን 2017 E.C ይካሄዳል፤

5. መመዝገቢያ ቦታ፡- የኮተቤ ሳይንስ ሼርድ ካምፓስ፤

6. የፈተና ቀን ሐምሌ 23 ቀን 2017 E.C የሚሰጥ መሆኑ ታውቆ ይህ ደብዳቤ በሁሉም ትምህርት ቤቶች ተደራሽ እንዲሆን አሳስባለሁ፡፡

⭕️ 📚 ከዚህ ምዝገባና ፈተና ወቅት ቀድሞም እንዲሁም ዘግይቶ የመጣ አይስተናገድም፡፡


https://t.me/Grade8Info
2