Basic Computer Skills
1.86K subscribers
1.22K photos
100 videos
575 files
833 links
#በዚህ የቴሌግራም ቻናል
↪️ Programming
↪️ ቴክኖሎጂ ነክ ትምህርቶችን
↪️ ኮምፒውተር ነክ ትምህርቶችን
↪️Basic Computer Skills
↪️ Software
↪️ AI and AI Skills (Like ChatGPT)

ከላይ የተዘረዘሩትና ሌሎችም ገራሚ ትምህርቶች ይለቀቅበታል!

t.me/BasicComputerSkillsGroup

𝘽𝙮 𝙍𝙚𝙨𝙝𝙖𝙙
Download Telegram
ምክር ለተፈታኞች

ተፈታኝ ተማሪዎች እንኳን በጉጉት ስትጠብቁት ለነበረው ፈተና  በሰላም አደረሳችሁ። ይህ ለእናንተ ወሳኝ ጊዜ ነው። እስካሁን ትምህርታችሁን እያጠናችሁ ቆይታችኋል። መልካም ነው። ነገር ግን በፈተና ወቅት የምታከናውኗቸው ተግባራትም የጥናታችሁን ያህል ውጤታችሁ ላይ ተጽዕኖ አላቸው። ስለዚህ በዚህ ወቅት ምን ማድረግ እንዳለባችሁና ምን ማድረግ እንደሌለባችሁ ጠንቅቃችሁ ማወቅ ይጠበቅባችኋል። ለዚህም ይረዳችሁ ዘንድ የሚከተሉትን ምክሮችን ከወዲሁ ተረድታችሁ ለመተግበር ዝግጁ ሁኑ!

➊ በዋዜማው ስልክ መዝጋትና ከሚረብሹ ነገሮች ራስን ማራቅ ያስፈልጋል። ስልካችሁን መዝጋት ሀሳባችሁን ሊሰርቁ ከሚችሉ ማህበራዊ ሚዲያዎች መራቅ ይገባችኋል። በዚህ ወቅት ትኩረታችሁን ፈተናችሁ ላይ ብቻ አድርጉ፤

❷ በቂ እንቅልፍ ተኙ። በፈተና ዋዜማ ለማንበብ ብላችሁ በፍጹም አታምሹ። ባጭሩ በዚህ ቀን ተጨማሪ ሰዓት ከማንበብ ይልቅ ተጨማሪ ሰዓት መተኛት የተሻለ ዉጤት አለው። በቂ እንቅልፍ አለመተኛት በፈተና ወቅት ለድብርትና ለራስ ምታት ሊዳርግና ሥራችሁን ሊያበላሽ ይችላል። ጥሩ እንቅልፍ ለመተኛት ከባድ ምግቦችን አለመመገብ፤ ብዙ ቡና አለመጠጣት፤ እና ሌሎች አነቃቂ ነገሮችን አለመውሰድ ይመከራል፤

➌ ጠዋት ማልዶ መነሳት: በጊዜ ተነስቶ መዘጋጀት ከመቻኮል ጋር ተያይዞ ከሚመጣ መታወክ ያድናል። በተጨማርም ወደፈተናው አዳራሽ በጊዜ ለመድረስ ያስችላል፤

❹ ቁርስ በአግባቡ መብላት: በፈተና ወቅት ቁርስ አለመብላት አእምሮአችን የሚፈልገውን ያህል ኃይል እንዳያገኝ ስለሚያደርግ ለማሰብ አቅም እንዲያንስ ያደርጋል። ስለዚህ ቀለል ያሉ ምግቦችን ተመግባችሁ መሄድ ይኖርባችኋል። ከባድ ምግቦችን መመገብ ደግሞ አእምሮአችን ምግብ የመፍጨት ሥራ ላይ ብቻ እንዲወጠር ስለሚያደርግ ድካምና እንቅልፍ ያመጣል፤

❺ ወደ መፈተኛ ቦታው ፈተናው ከሚጀምርበት ሰዓት በፊት ቀድሞ መድረስ ያስፈልጋል። ይህም ለመረጋጋት ከፍተኛ አስተዋጽዖ አለው፤

❻ ከቤት ስትወጡ የፅህፈት መሳሪያዎቻችሁንና የመታወቅያ ካርዳችሁን መያዛችሁን እርግጠኛ ሁኑ። ይህም ከመንገድ ከመመለስና ከማርፈድ ያድናችኋል። ትርፍ እርሳሶችን እና የእርሳስ መቅረጫዎች መያዝ በጣም አስፈላጊ ነው፤

❼ ወደ ፈተና አዳራሽ ከመግባት በፊት ወደ መፀዳጃ ቤት መሄድ መልካም ነው። ምናልባት የፈተናው ሰዓት ረዥም ቢሆንና ሽንት ቢይዛችሁ መጨናነቅን ያመጣል። አቋርጣችሁ መውጣት ላይፈቀድላችሁ ይችላል፤

❽ የመልስ መስጫ ወረቀቱ ላይ ስማችሁን በአግባቡ መጻፋችሁን እርግጠኛ ሁኑ። አንድ ፊደል እንኳን ብትሳሳቱ ኋላ የት/ት ማስረጃችሁ ላይ ስለሚቀመጥ ለማስቀየር ዋጋ ያስከፍላል፤

❾ መመሪያዎችን (instructions) በአግባቡ ማንበብና መተግበር ያስፈልጋል። በእያንዳዱ ፈተና ወረቀት ላይ ወይም የፈተናው ክፍሎች ላይ የሚሰጡትን መመሪያዎች በአግባቡ ማንበብና መተግበር ይኖርባችኋል፤

❿ አትደንግጡ! በደንብ ተንፍሱ! ብዙ ኦክስጂን ወደ ውስጣችን ማስገባት ብዙ ምግብ እንዲቀጣጠልና ኃይል እንዲመረት ስለሚያደርግ ጉልበትና ድፍረት ይጨምርላችኋል፤

⓫ መልስ መመለስ ከመጀመራችሁ በፊት እያንዳንዱ የፈተና ክፍል ስለያዛቸው የጥያቄ አይነቶች ገረፍ ገረፍ እያደረጋችሁ ብታዩ መልካም ነው። ይህም የተሰጣችሁን ሰዓት በጥያቄው ክብደት ልክ ከፋፍላችሁ ለመጠቀም ያግዛችኋል፤

⓬  አንዱ ጥያቄ ከከበዳችሁ ዝለሉት፤ አንድ ጥያቄ ላይ ተጠምዳችሁ ብዙ ጊዜ የምታጠፉ ከሆነ ቀጥለው ለሚጠብቋችሁ ጥያቄዎች ጊዜ ሊያጥራችሁ ይችላል። ስትዘሉት ግን የጥያቄ ወረቀቱ ላይ ምልክት ማድረጋችሁን እንዲሁም መልስ መስጫ ወረቀቱ ላይ ከተሰጡት አማራጮች አንዱን መልስ በግምት ማጥቆራችሁን አትርሱ። አጥቁሮ ማለፍ ምናልባት በኋላ የተሰጠው ጊዜ ቢያልቅና ወደ ጥያቄው መመለስ ቢያቅታችሁ መልስ መስጫ ቦታው ባዶ ሆኖ እንዳይቀር ያደርጋል፤

⓭ ቶሎ ለመውጣት አትቸኩሉ፤ ምንም አይጠቅማችሁም፤ ሰዓታችሁን አሟጥጣችሁ መጠቀማችሁን፤ ሁሉንም ጥያቄዎች በአግባቡ መመለሳችሁንና ማጥቆራችሁን አረጋግጡ። ጊዜ ቢተርፋችሁ ጥያቄዎቹን ለመከለስ ተጠቀሙበት፤

⓮ ያልገባችሁ ማንኛውንም ነገር ሲኖር ፈታኞችን ለመጠየቅ አትፍሩ (ከመልስ በስተቀር ☺️)፤

⓯ ልክ የፈተና ወረቀቱን ከመለሳችሁበት ጊዜ ጀምሮ የዚያ ትምህርት (subject) ነገር ማክተሙን በመገንዘብ ለቀጣዩ ፈተና እራስን ማዘጋጀት ይገባል። እንጂ፤ ስላለፈው ፈተና እያሰላልሰሉ መጨነቅ ለቀጣዩ ፈተና በምታደርጉት ዝግጅት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ያሳድራል።

📚 መልካም የፈተና ጊዜ!


©️ eec1227

✍️ For Grade 6 and 8 Students
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
አላህ ይርዳችሁ!! 🤲🤲
3
🇵🇸 I wish you and your family a happy Eid filled with love, laughter and blessings.  ...

May this Eid bring peace, happiness and prosperity to your homes.  ...

On this auspicious occasion, I pray to Allah to shower His divine blessings upon you and your families.  ...

🇵🇸 Eid Mubarak!

🇵🇸 To my brothers and sisters and their families!

By Reshad Ibnu Muzemil


🇵🇸 ለእናንተ እና ለቤተሰባችሁ በፍቅር፣ በሳቅ እና በበረከት የተሞላ የደስታ ኢድ እንዲሆን እመኛለሁ።  ...

ይህ ኢድ ለቤታችሁ ሰላም ፣ ደስታ እና ብልጽግና ያድርግላችሁ።  ...

በዚህ መልካም አጋጣሚ አላህ በእናንተና በቤተሰቦቻችሁ ላይ መለኮታዊ ፀጋውን እንዲያወርድ እማፀነዋለሁ።  ...

🇵🇸 ኢድ ሙባረክ!

🇵🇸 ይድረስ ለወንድም እህቶቼ እና ለቤተሰቦቻቸው!

✍️ በረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል
7
Basic Computer Skills pinned «ምክር ለተፈታኞች ተፈታኝ ተማሪዎች እንኳን በጉጉት ስትጠብቁት ለነበረው ፈተና  በሰላም አደረሳችሁ። ይህ ለእናንተ ወሳኝ ጊዜ ነው። እስካሁን ትምህርታችሁን እያጠናችሁ ቆይታችኋል። መልካም ነው። ነገር ግን በፈተና ወቅት የምታከናውኗቸው ተግባራትም የጥናታችሁን ያህል ውጤታችሁ ላይ ተጽዕኖ አላቸው። ስለዚህ በዚህ ወቅት ምን ማድረግ እንዳለባችሁና ምን ማድረግ እንደሌለባችሁ ጠንቅቃችሁ ማወቅ ይጠበቅባችኋል።…»
Keyboard ⌨️ Shortcut Keys
Forwarded from Grade 8 Info & Materials
📚 የተፈታኞች መብትና ግዴታ

📚 ማንኛውም ተፈታኝ የፈተና ደንብና ሥርዓት  አከባበር እንዲሁም የመልስ ወረቀት አጠቋቆርና   ተዛማጅ ሁኔታዎችን አስመልክቶ በሚሰጡ ገለፃዎች ላይ የመሣተፍ ግዴታ አለበት።

📚 ተፈታኙ በገለፃው ላይ ባለመሳተፉ ምክንያት በፈተና አሰጣጥ ዙሪያ ለሚያጋጥመው ችግር ኃላፊነቱን ይወስዳል።

📚 ተፈታኙ/ኟ የሰራበትን የመልስ ወረቀት ለፈታኙ በመስጠት  የጥያቄ ወረቀቱን ይዞ መውጣት ይችላል

📚ማንኛውም ተፈታኝ የፈተና ጥያቄዎቹን መስራት ከመጀመሩ በፊት በፈተና የመልስ መስጫ ወረቀት ላይ የግል መለያ መረጃዎችን በሙሉ ግልፅ በሆነ ሁኔታ በቅደም ተከተል ጽፎ ማጥቆር ይኖርበታል (በተለይ የመለያ ቁጥር እና የትምህርት አይነት ኮድ)።

📚ማንኛውም ተፈታኝ የራሱን ችሎታና ዕውቀት ተጠቅሞ መስራት ይጠበቅበታል፡፡

📚 የሚሠራባቸው የጥያቄና የመልስ መስጫ ወረቀቶች ለሌሎች ተፈታኞች ዕይታ የተጋለጡ እንዳይሆኑ ሸፍኖ መስራት ይኖርበታል

📚ማንኛውም ተፈታኝ ሞባይል፣ ካልኩሌተርና የመሳሰሉ ማንኛውንም ዓይነት  የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን ይዞ ወደ ፈተና ክፍል መግባት በጥብቅ የተከለከለ ነው ።

📚 እያንዳንዱ ተፈታኝ ይህንን አውቆ በቅድሚያ አስፈላጊውን ጥንቃቄ ማድረግ አለበት ።

📚 ይህንን ባለማድረጉ ምክንያት በፈተና አሰጣጥ ዙሪያ ለሚያጋጥመው ችግር ተፈታኙ  ራሱ ኃላፊነቱን ይወስዳል።

📚ማንኛውም ተፈታኝ በመፈተን ላይ እያለ ፈተናውን እንዳይሠራ የሚያውኩ ሁኔታዎች ቢያጋጥመው በፈታኙ ሲፈቀደለት ችግሩን በመግለጽ አስፈላጊውን እርዳታ ማግኘት ይችላል ይሁንና በማንኛውም ምክንያት ለባከነ ጊዜ ተጨማሪ ሰዓት አይፈቀድም

📚ማንኛውም ተፈታኝ ፈተናው ከሚጀመርበት ጊዜ ተኩል ሰዓት /30 ደቂቃ/ ቀደም ብለው ከመፈታኛው ቦታ በመገኘት መቀመጫቸውን መያዝ አለባቸው።

📚 ፈተናው ከተጀመረ ከ15 ደቂቃ በኋላ የሚመጣ ተፈታኝ ወደ ፈተናው አዳራሽ መግባት አይፈቀድለትም።

📚ማንኛውም ተፈታኝ ፈተናው ተጀምሮ 45 ደቂቃ ሳይሞላ ፈተናውን ሠርቶ ቢያጠናቅቅም እንዲወጣ አይፈቀድለትም።

📚 ይሁን እንጂ ፈተናው ከተጀመረ ከ45 ደቂቃ በኋላ ከፈተና አዳራሹ ለመውጣት   እንዲፈቀድለት ሲጠይቅ የመልስ ወረቀቱን ለፈታኙ አስረክቦ በጸጥታ እንዲወጣ ይፈቀድለታል።

📚 ፈተናው ሊጠናቀቅ ከ10 ደቂቃ ያነሰ ጊዜ ሲቀረው የሚጨርስ ተፈታኝ የሁሉም ተፈታኞች የመልስ ወረቀቶች እስኪሰበሰቡና ለፈተናው የተፈቀደው የጊዜ ገደብ አብቅቶ እስኪደወል ድረስ በቦታው ተቀምጦ እንዲቆይ ይደረጋል።

📚 ፈተናው በሚሰጥበት ጊዜ ማንኛውም ተፈታኝ ትክክለኛ ያልሆነ የተቀደደ ወይም የተበላሸ የፈተና ጥያቄ ጥራዝ ከገጠመው ወይም የተሰጠው የመልስ ወረቀት የተበላሸ ከሆነ ወይም በራሱ እጅ ቢበላሽበት እጁን አንስቶ በመጠየቅ ሲፈቀድለት ሊያስቀይር ይችላል።

ለተፈታኞች የተፈቀዱ

እርሳስ
የተማሪዎች የደንብ ልብስ (UNIFORM)
ADMISSION CARD
ላጲስ፣ መቅረጫና ማስመሪያ

ለተፈታኞች የተከለከሉ

ስልክ ይዞ መግባት አይቻልም
ካልኩሌተር
የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን
ሰዓት
በሀኪም ከታዘዘ ውጪ የሆኑ መነጽሮች
የሚነበቡ ጽሁፎች በሙሉ

የፈተና ኦረንቴሽን ቀን
➤ የ8ኛ ክፍል በ2/10/2017 እና የ6ኛ ክፍል በ9/10/2017 ዓ/ም

👉ፈተናው የሚሰጥበት ጊዜ
➤ 8ኛ ክፍል ሰኔ 3 እና 4 /2017 ዓ/ም
➤ 6ኛ ክፍል ከሰኔ10-12/2017 ዓ/ም ይሆናል

©️ dam76

▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
አላህ ይርዳችሁ!! 🤲🤲
3
📚 ነገ ሚኒስትሪ ፈተና ላይ ለምትቀመጡ ለ8ኛ ክፍል ተሪዎች አጠር ያለና አበረታች የሆነ መልዕክት 📚

📚 ውድ ተማሪዎች!
ነገ የጥረታችሁን ፍሬ የምታዩበት ትልቅ ቀን ነው። ለዚህ ፈተና ስትዘጋጁ የነበራችሁበት ጊዜ፣ የደከማችሁበት ልፋት እና ያፈሰሳችሁት ላብ ሁሉ ነገ እንደ አላህ ፍቃድ ፍሬ ያፈራል።

አሁን ማድረግ ያለባችሁ አንድ ነገር ብቻ ነው፤ በራሳችሁ መተማመን! በእውቀታችሁ እና በተማራችሁት ነገር ላይ ሙሉ እምነት ይኑራችሁ። አላህ ከእናንተ ጋር እንደሆነ እመኑ። ይህ ፈተና የእውቀታችሁ፣ የመረጋጋታችሁ እና የድፍረታችሁ መለኪያ ነው።

ጭንቀትን አስወግዱ! ጭንቀት የሚያደናቅፍ እንጂ የሚረዳ አይደለምና። በጥሞና ተንፍሱ፣ አእምሮአችሁን አረጋጉ።

ፈጣሪ ሁሉንም ነገር እንደሚያቀልላችሁ እመኑ። በቀ የቻላችሁትን ያህል ሰርታችኋልና፣ አሁን ደግሞ ውጤቱን ለፈጣሪያችሁ ስጡ።

መልካም ፈተናን እመኝላችኋለሁ!
ነገ የድል፣ የመረጋጋትና የጥሩ ውጤት ቀን ይሁንላችሁ!


ሁላችሁንም አላህ ይርዳችሁ! መልካም የሆነን ውጤት ይስጠችሁ!!


✍️ በረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል
6
🇵🇸 የአላህ ለእህት ወንድሞቻችን ያማረ ውጤትን ስጣቸው!
🇵🇸 የአላህ በሄዱበት ሁሉ መልካም ነገርን አግራላቸው።
የአላህ ወደ መልካም የሚጣራ ወዳጅ አበርክትላቸው!
🇵🇸 አብሽሩ፤ እየተገፋ ላለው ማህበረሰብ ግርማ-ሞገስ የሆነን ውጤት አላህ ይሰጣችኋል!! ኢንሻአላህ!!

◆ ለአላህ ብዬ ሁላችሁንም እውዳችኋለሁ!

ለ8ኛ ክፍል Ministry ለተፈተናችሁ ወንድምና እህቶቼ!!

✍️ የእናንተው ወንድም ረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል
6
Truecaller v15.17.6 (Premium) amoled.apk
114.1 MB
Truecaller v15.17.6 (Premium) amoled.apk
ከነዚህ ውስጥ የትኛውን ትጠቀማላችሁ?
ChatGPT
Revolutionize interaction, creativity, and innovation with the leader in AI.
Claude4
Revolutionize workflows with AI-driven text, analytics, automation.
Midjourney
Unlock digital artistry: AI transforms text into stunning visuals.
Perplexity
Delivers concise, real-time answers with source citations.
Google Gemini
Multimodal reasoning across text, images, audio, and video.
Grok 3
Generate answers, code, and images in real time.
Leonardo AI
Generate stunning, customizable artwork effortlessly with AI.

©️©️
4
Online Exam Orientation.pptx
1 MB
ለ12ኛ ክፍል ተማሪዎች በኦን ላይን ፈተና ዙሪያ የተሰጠ ኦረንቴሽን
3
ስትጠብቁት የነበረው የ12 ክፍል ማትሪክ ፈተና አጋዥ አፕሊኬሽናትችን አሁን playstore ላይ ይገኛል። ዳውንሎአድ አድርጎ መጠቀም ብቻ ነው የሚጠበቅባችሁ።
በነጻ
አዲሱን ስር አተ ትምህርት ያካተተ
አጫጭር ኖቶችና አጋዥ ቪድዮዎች የያዘ
አሁኑኑ ይሞክሩት!!!!!!!!!

  መተግበርያውን ለማግኘት👇                                                             
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.exam_time.exam
3
📚 ነገ ሚኒስትሪ ፈተና ላይ ለምትቀመጡ ለ6ኛ ክፍል ተሪዎች አጠር ያለና አበረታች የሆነ መልዕክት 📚

📚 ውድ ተማሪዎች!
ነገ የጥረታችሁን ፍሬ የምታዩበት ትልቅ ቀን ነው። ለዚህ ፈተና ስትዘጋጁ የነበራችሁበት ጊዜ፣ የደከማችሁበት ልፋት እና ያፈሰሳችሁት ላብ ሁሉ ነገ እንደ አላህ ፍቃድ  ፍሬ ያፈራል።

አሁን ማድረግ ያለባችሁ አንድ ነገር ብቻ ነው፤ በራሳችሁ መተማመን! በእውቀታችሁ እና በተማራችሁት ነገር ላይ ሙሉ እምነት ይኑራችሁ። አላህ ከእናንተ ጋር እንደሆነ እመኑ። ይህ ፈተና የእውቀታችሁ፣ የመረጋጋታችሁ እና የድፍረታችሁ መለኪያ ነው።

ጭንቀትን አስወግዱ! ጭንቀት የሚያደናቅፍ እንጂ የሚረዳ አይደለምና። በጥሞና ተንፍሱ፣ አእምሮአችሁን አረጋጉ።

ፈጣሪ ሁሉንም ነገር እንደሚያቀልላችሁ እመኑ። በቀ የቻላችሁትን ያህል ሰርታችኋልና፣ አሁን ደግሞ ውጤቱን ለፈጣሪያችሁ ስጡ።

መልካም ፈተናን እመኝላችኋለሁ!
ነገ የድል፣ የመረጋጋትና የጥሩ ውጤት ቀን ይሁንላችሁ!


ሁላችሁንም አላህ ይርዳችሁ! መልካም የሆነን ውጤት ይስጠችሁ!!


✍️ በረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል
5