Basic Computer Skills
1.85K subscribers
1.22K photos
100 videos
575 files
833 links
#በዚህ የቴሌግራም ቻናል
↪️ Programming
↪️ ቴክኖሎጂ ነክ ትምህርቶችን
↪️ ኮምፒውተር ነክ ትምህርቶችን
↪️Basic Computer Skills
↪️ Software
↪️ AI and AI Skills (Like ChatGPT)

ከላይ የተዘረዘሩትና ሌሎችም ገራሚ ትምህርቶች ይለቀቅበታል!

t.me/BasicComputerSkillsGroup

𝘽𝙮 𝙍𝙚𝙨𝙝𝙖𝙙
Download Telegram
Advanced Excel

⌨️ Keyboard Shortcut Keys


══════════════
✍️ Basic Computer Skills

🌐ዘመኑ #የቴክኖሎጂ ነው 📲 ከዘመኑ ጋር አብረው ይዘምኑ💻

Telegram:
t.me/BasicComputer_Skills

tiktok.com/@basiccomputerskills

t.me/Grade1_4Info

t.me/Grade5and6Info

t.me/Grade7Info

t.me/Grade8Info

t.me/Grade9Info
📚 Study Time Table for Grade 8 Students

✍️ Contains only Six Subjects that the Ministry Exam includes

Evening = Grade 8
Morning = Grade 7


ከ7ኛ እና ከ8ኛ ጋር ተያያዥ ያላቸውን ርዕሶች አብራችሁ አንድ ላይ አንብቧቸው

▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
አላህ ይርዳችሁ!! 🤲🤲
1
📚 Study Time Table for Grade 6 Students

✍️ Contains only Five Subjects that the Ministry Exam includes


Evening = Grade 6
Morning = Grade 5

ከ5ኛ እና ከ6ኛ ጋር ተያያዥ ያላቸውን ርዕሶች አብራችሁ አንድ ላይ አንብቧቸው።

▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
አላህ ይርዳችሁ!! 🤲🤲
Basic Computer Skills
Photo
የሚኒስትሪ መልስ መስጫ ወረቀት አጠቃቀም መመሪያ ለተማሪዎች

➊ የተማሪዎች መለያ ቁጥር እና የትምህርት ዓይነት መለያ ቁጥር ለእያንዳንዳቸው በተቀመጠው ሳጥን ውስጥ ከላይ ወደ ታች መፃፍ አለበት፡፡

❷ በተፃፈው መለያ ቁጥር ፊት ለፊት የተፃፈውን ቁጥር የያዘውን አራት ማዕዘን ቅንፍ (Square Bracket) ብቻ ማጥቆር አለበት፡፡

➌ ተማሪዎች የመረጡትን መልስ ትይዩ በተሰጠው አራት ማዕዘን ቅንፍ (Square Bracket) ላይ በትክክል ማጥቆር አለባቸው፡፡

❹ ተማሪዎች ያጠቆሩትን መልስ መቀየር ቢፈልጉ መጀመሪያ ያጠቆሩትን የአራት ማዕዘን ቅንፍ (Square Bracket) በደንብ ማጥፋት አለባቸው፡፡

❺ በአንድ ረድፍ ከአንድ በላይ መልስ (የአራት ማዕዘን ቅንፍ/Square Bracket) ማጥቆር የተከለከለ ነው፡፡

❻ ለመፃፍ እና ለማጥቆር ከተፈቀደው ቦታ ውጭ ምንም አይነት ፅሁፍም ሆነ ጭረት ማድረግ የተከለከለ ነው፡፡

❼ ለመፃፍ ከተፈቀደው ቦታ ውጭ ተፅፎ ወይም ትንሽ ጭረት እና ነጥብ ከተገኘ የመልስ መስጫ ወረቀቱ ሙሉ  በሙሉ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡

❽ መልስ በሚጠቆርበት ጊዜ እርሳሱ ከተሰጠው አራት ማዕዘን ቅንፍ (Square Bracket) መውጣት የለበትም። ከወጣም በማጥፊያ ማጥፋት ይጠበቅባችኋል።

❾ መልስ መስጫ ኮርነር ላይ ያሉትን አራት ጠርዞች መንካትም ፈጽሞ የተከለከለ ነው፡፡

➓ ተፈታኞች የመልስ መስጫ ወረቀታቸውን በንፅህና መያዝ አለባቸው ማለትም እንዳይቆሽሽ፣ እርጥበት  እንዳይነካው፤ እንዳይቀደድ እና እንዳይታጠፍ መጠንቀቅና ሙሉ ኃላፊነት መውሰድ አለባቸው፡፡

⓫ በእስክሪብቶ መፃፍ አይፈቀድም። ስለዚህ እርሳስ፣ ላጲስ እና መቅረጫ አይለያችሁ

⓬ ፈተና ጨረስኩ ብሎ አላስፈላጊ የሆነ ነገር፤ ስዕል ወይም ሌላ ከጀርባም ይሁን ከፊት አይፃፍበትም።

⓭ በጣም የተቀረፀ ሹል እርሳስ በምንጠቀም ወቅት ወረቀቱ እንዳይቀደድ መጠንቀቅ አለብን።

✍️ For Grade 6 and 8 Students
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
አላህ ይርዳችሁ!! 🤲🤲
👍3💯21
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
መልካምነት ያስለቅሳል!
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

አንዳንዶቻችን ግን የተጣለብንን ወይም የተረከብነውን ሀላፊነትና አደራ ልጆችን በማስጨንቅ እንወጣዋለን።

📚 አልተከበርኩም የሚል ጥማት ሰዎችም ሆነ ፈጣሪ ዘንድ ያዋርዳል! ለዛምው ህፃናት አላከበሩኝም የሚል የዘቀጠ የአላዋቂነት ጥማት!!


✍️ ወንድም እህቶቻችን (ተማሪዎቻችን) አላህ ይጠብቃችሁ።
👍4
Telegram በዛሬው ዕለት አዳዲስ update ለቋል።

Voice trimming
Voice record እያደረጋችሁ በመሀል የማይሆን ነገር ተናግራችሁ ቆርጣችሁ ማውጣት ከፈለጋችሁ Pause አድርጋችሁ trim ማድረግ ትችላላችሁ።

Direct message to channels
የቻናል owner ወይም አድሚኖችን በቀላሉ contact ማድረግ ትችላላችሁ።
አድሚኑ settings ውስጥ on ካደረገው ከቻናሉ ታች ላይ የmessaging icon ትመጣለች እሷን በመንካት መልዕክት ማስቀመጥ ይቻላል።

HD quality photo
ፎቶ ስትልኩ በHD quality መላክ ትችላላችሁ።

Split Long video for story
ረጅም Video story ማድረግ ከፈለጋችሁ telegram ራሱ ቪዲዬውን ቆራርጦ በpart story እንድታደርጉት ያስችላችኋል።

©️ bighabesha
👌42
ምክር ለተፈታኞች

ተፈታኝ ተማሪዎች እንኳን በጉጉት ስትጠብቁት ለነበረው ፈተና  በሰላም አደረሳችሁ። ይህ ለእናንተ ወሳኝ ጊዜ ነው። እስካሁን ትምህርታችሁን እያጠናችሁ ቆይታችኋል። መልካም ነው። ነገር ግን በፈተና ወቅት የምታከናውኗቸው ተግባራትም የጥናታችሁን ያህል ውጤታችሁ ላይ ተጽዕኖ አላቸው። ስለዚህ በዚህ ወቅት ምን ማድረግ እንዳለባችሁና ምን ማድረግ እንደሌለባችሁ ጠንቅቃችሁ ማወቅ ይጠበቅባችኋል። ለዚህም ይረዳችሁ ዘንድ የሚከተሉትን ምክሮችን ከወዲሁ ተረድታችሁ ለመተግበር ዝግጁ ሁኑ!

➊ በዋዜማው ስልክ መዝጋትና ከሚረብሹ ነገሮች ራስን ማራቅ ያስፈልጋል። ስልካችሁን መዝጋት ሀሳባችሁን ሊሰርቁ ከሚችሉ ማህበራዊ ሚዲያዎች መራቅ ይገባችኋል። በዚህ ወቅት ትኩረታችሁን ፈተናችሁ ላይ ብቻ አድርጉ፤

❷ በቂ እንቅልፍ ተኙ። በፈተና ዋዜማ ለማንበብ ብላችሁ በፍጹም አታምሹ። ባጭሩ በዚህ ቀን ተጨማሪ ሰዓት ከማንበብ ይልቅ ተጨማሪ ሰዓት መተኛት የተሻለ ዉጤት አለው። በቂ እንቅልፍ አለመተኛት በፈተና ወቅት ለድብርትና ለራስ ምታት ሊዳርግና ሥራችሁን ሊያበላሽ ይችላል። ጥሩ እንቅልፍ ለመተኛት ከባድ ምግቦችን አለመመገብ፤ ብዙ ቡና አለመጠጣት፤ እና ሌሎች አነቃቂ ነገሮችን አለመውሰድ ይመከራል፤

➌ ጠዋት ማልዶ መነሳት: በጊዜ ተነስቶ መዘጋጀት ከመቻኮል ጋር ተያይዞ ከሚመጣ መታወክ ያድናል። በተጨማርም ወደፈተናው አዳራሽ በጊዜ ለመድረስ ያስችላል፤

❹ ቁርስ በአግባቡ መብላት: በፈተና ወቅት ቁርስ አለመብላት አእምሮአችን የሚፈልገውን ያህል ኃይል እንዳያገኝ ስለሚያደርግ ለማሰብ አቅም እንዲያንስ ያደርጋል። ስለዚህ ቀለል ያሉ ምግቦችን ተመግባችሁ መሄድ ይኖርባችኋል። ከባድ ምግቦችን መመገብ ደግሞ አእምሮአችን ምግብ የመፍጨት ሥራ ላይ ብቻ እንዲወጠር ስለሚያደርግ ድካምና እንቅልፍ ያመጣል፤

❺ ወደ መፈተኛ ቦታው ፈተናው ከሚጀምርበት ሰዓት በፊት ቀድሞ መድረስ ያስፈልጋል። ይህም ለመረጋጋት ከፍተኛ አስተዋጽዖ አለው፤

❻ ከቤት ስትወጡ የፅህፈት መሳሪያዎቻችሁንና የመታወቅያ ካርዳችሁን መያዛችሁን እርግጠኛ ሁኑ። ይህም ከመንገድ ከመመለስና ከማርፈድ ያድናችኋል። ትርፍ እርሳሶችን እና የእርሳስ መቅረጫዎች መያዝ በጣም አስፈላጊ ነው፤

❼ ወደ ፈተና አዳራሽ ከመግባት በፊት ወደ መፀዳጃ ቤት መሄድ መልካም ነው። ምናልባት የፈተናው ሰዓት ረዥም ቢሆንና ሽንት ቢይዛችሁ መጨናነቅን ያመጣል። አቋርጣችሁ መውጣት ላይፈቀድላችሁ ይችላል፤

❽ የመልስ መስጫ ወረቀቱ ላይ ስማችሁን በአግባቡ መጻፋችሁን እርግጠኛ ሁኑ። አንድ ፊደል እንኳን ብትሳሳቱ ኋላ የት/ት ማስረጃችሁ ላይ ስለሚቀመጥ ለማስቀየር ዋጋ ያስከፍላል፤

❾ መመሪያዎችን (instructions) በአግባቡ ማንበብና መተግበር ያስፈልጋል። በእያንዳዱ ፈተና ወረቀት ላይ ወይም የፈተናው ክፍሎች ላይ የሚሰጡትን መመሪያዎች በአግባቡ ማንበብና መተግበር ይኖርባችኋል፤

❿ አትደንግጡ! በደንብ ተንፍሱ! ብዙ ኦክስጂን ወደ ውስጣችን ማስገባት ብዙ ምግብ እንዲቀጣጠልና ኃይል እንዲመረት ስለሚያደርግ ጉልበትና ድፍረት ይጨምርላችኋል፤

⓫ መልስ መመለስ ከመጀመራችሁ በፊት እያንዳንዱ የፈተና ክፍል ስለያዛቸው የጥያቄ አይነቶች ገረፍ ገረፍ እያደረጋችሁ ብታዩ መልካም ነው። ይህም የተሰጣችሁን ሰዓት በጥያቄው ክብደት ልክ ከፋፍላችሁ ለመጠቀም ያግዛችኋል፤

⓬  አንዱ ጥያቄ ከከበዳችሁ ዝለሉት፤ አንድ ጥያቄ ላይ ተጠምዳችሁ ብዙ ጊዜ የምታጠፉ ከሆነ ቀጥለው ለሚጠብቋችሁ ጥያቄዎች ጊዜ ሊያጥራችሁ ይችላል። ስትዘሉት ግን የጥያቄ ወረቀቱ ላይ ምልክት ማድረጋችሁን እንዲሁም መልስ መስጫ ወረቀቱ ላይ ከተሰጡት አማራጮች አንዱን መልስ በግምት ማጥቆራችሁን አትርሱ። አጥቁሮ ማለፍ ምናልባት በኋላ የተሰጠው ጊዜ ቢያልቅና ወደ ጥያቄው መመለስ ቢያቅታችሁ መልስ መስጫ ቦታው ባዶ ሆኖ እንዳይቀር ያደርጋል፤

⓭ ቶሎ ለመውጣት አትቸኩሉ፤ ምንም አይጠቅማችሁም፤ ሰዓታችሁን አሟጥጣችሁ መጠቀማችሁን፤ ሁሉንም ጥያቄዎች በአግባቡ መመለሳችሁንና ማጥቆራችሁን አረጋግጡ። ጊዜ ቢተርፋችሁ ጥያቄዎቹን ለመከለስ ተጠቀሙበት፤

⓮ ያልገባችሁ ማንኛውንም ነገር ሲኖር ፈታኞችን ለመጠየቅ አትፍሩ (ከመልስ በስተቀር ☺️)፤

⓯ ልክ የፈተና ወረቀቱን ከመለሳችሁበት ጊዜ ጀምሮ የዚያ ትምህርት (subject) ነገር ማክተሙን በመገንዘብ ለቀጣዩ ፈተና እራስን ማዘጋጀት ይገባል። እንጂ፤ ስላለፈው ፈተና እያሰላልሰሉ መጨነቅ ለቀጣዩ ፈተና በምታደርጉት ዝግጅት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ያሳድራል።

📚 መልካም የፈተና ጊዜ!


©️ eec1227

✍️ For Grade 6 and 8 Students
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
አላህ ይርዳችሁ!! 🤲🤲
3
🇵🇸 I wish you and your family a happy Eid filled with love, laughter and blessings.  ...

May this Eid bring peace, happiness and prosperity to your homes.  ...

On this auspicious occasion, I pray to Allah to shower His divine blessings upon you and your families.  ...

🇵🇸 Eid Mubarak!

🇵🇸 To my brothers and sisters and their families!

By Reshad Ibnu Muzemil


🇵🇸 ለእናንተ እና ለቤተሰባችሁ በፍቅር፣ በሳቅ እና በበረከት የተሞላ የደስታ ኢድ እንዲሆን እመኛለሁ።  ...

ይህ ኢድ ለቤታችሁ ሰላም ፣ ደስታ እና ብልጽግና ያድርግላችሁ።  ...

በዚህ መልካም አጋጣሚ አላህ በእናንተና በቤተሰቦቻችሁ ላይ መለኮታዊ ፀጋውን እንዲያወርድ እማፀነዋለሁ።  ...

🇵🇸 ኢድ ሙባረክ!

🇵🇸 ይድረስ ለወንድም እህቶቼ እና ለቤተሰቦቻቸው!

✍️ በረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል
7
Basic Computer Skills pinned «ምክር ለተፈታኞች ተፈታኝ ተማሪዎች እንኳን በጉጉት ስትጠብቁት ለነበረው ፈተና  በሰላም አደረሳችሁ። ይህ ለእናንተ ወሳኝ ጊዜ ነው። እስካሁን ትምህርታችሁን እያጠናችሁ ቆይታችኋል። መልካም ነው። ነገር ግን በፈተና ወቅት የምታከናውኗቸው ተግባራትም የጥናታችሁን ያህል ውጤታችሁ ላይ ተጽዕኖ አላቸው። ስለዚህ በዚህ ወቅት ምን ማድረግ እንዳለባችሁና ምን ማድረግ እንደሌለባችሁ ጠንቅቃችሁ ማወቅ ይጠበቅባችኋል።…»