Basic Computer Skills
1.88K subscribers
1.22K photos
100 videos
576 files
833 links
#በዚህ የቴሌግራም ቻናል
↪️ Programming
↪️ ቴክኖሎጂ ነክ ትምህርቶችን
↪️ ኮምፒውተር ነክ ትምህርቶችን
↪️Basic Computer Skills
↪️ Software
↪️ AI and AI Skills (Like ChatGPT)

ከላይ የተዘረዘሩትና ሌሎችም ገራሚ ትምህርቶች ይለቀቅበታል!

t.me/BasicComputerSkillsGroup

𝘽𝙮 𝙍𝙚𝙨𝙝𝙖𝙙
Download Telegram
አሰላሙ አለይኩም ወረህመቱሏሂ ወበረካቱ

ሰላም ለእናተ ይሁን። እንዴት ናችሁ ውድ የቻናላችን ተከታታዮች (አባሎች)⁉️

#የሚቸግራችሁ ነገር አለን፤ ፈልጋችሁ ያጣችሁት ነገር አለን!?

እገዛ ካስፈለጋችሁ በግል አካውንቴ አሳውቁኝ!! በአላህ ፍቃድ የምችለውን ለማድረግ ዝግጁ ነኝ።

▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

በዚሁ አጋጣሚ ቻናሉ ለሌሎች እንዲዳረስና ከዚህም የተሻለ ጠንክሮ ለመስራት በሐሳብም ሆነ በሌላ ነገር ድጋፍ ማድረግ የምትፈልጉ በሩ ክፍት ነው❗️❗️

➤ በአላህ ፍቃድ በ2017 E.C ልክ እነደዚህኛው ቻናል ከፍቼ ከ9-12 ክፍል ላሉ ተማሪዎች የምችለው እገዛ እንደማደርግ ከወዲሁ ላሳውቃችሁ። [[በአላህ ፍቃድ]]

አሁን ላይ ከ1-8ኛ ክፍል ላሉት ተማሪዎች ድጋፍ እንደምናደርገው ማለት ነው።

▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

⭕️ ትውልድን ❝ትክክለኛው መንገድ ይህ ነው በዚህ መንገድ ሂዱ ማለት ብቻ ሳይሆን፤ ለትክክለኛው መንገድ (ለስኬት) ማዘጋጀትም ተገቢ ነው ባይ ነኝ❞ !

▬▭▬▭▬▭▬▭▭▬▭▬
⭕️ ለማስታወስ ያህል:-
▮ነገ ለምትፈተኑት ሞዴል እገዛ እንዲሆናችሁ በ2016 E.C Second Semester የተዘጋጀ ሞዴል ለቅቄያለሁ።
(ለ8ኛ እና ለ6ኛ)

👇👇👇👇👇

t.me/AndalusGrade7and8/1004?single

የግል አካውንቴ:- t.me/ReshadMuzemil
1
#ጥቆማ

የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት በክረምት የስልጠና መርሐግብር የሚሳተፉ ተማሪዎች ምዝገባ ጀምሯል።

እነማን ይመዘገባሉ?
የመጀመሪያ እና የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች

የምዝገባ ጊዜ፦
ከሚያዝያ 17 እስከ ግንቦት 7/2016 ዓ.ል

ስልጠናው መቼ ይጀምራል?
ከሐምሌ 1 እስከ ጳጉሜን 1/2016 ዓ.ል
(ለሁለት ወራት) (በሳምንት ለአራት ቀናት)

ስልጠናው ትኩረት የሚያደርግባቸው፦

➭ የሰው ሰራሽ አስተውሎት መሰረታውያን፣
➭ ሮቦቲክስ፣
➭ ፕሮግራሚንግ፣
➭ ማሽን ለርኒንግ እና ሌሎችም።

ምዝገባ የማድረጊያ አማራጮች፦

👉 forms.gle/9B79pzGLdo84W2LY8

👉 https://www.aii.et/summer-camp-registration-form-for-student/

Via= tikvahuniversity

[[በድጋሚ የተለጠፈ]]

🌐 ዘመኑ #የቴክኖሎጂ ነው 📲 ከዘመኑ ጋር አብረው ይዘምኑ💻

Telegram: t.me/BasicComputer_Skills

tiktok.com/@basiccomputerskills

Umma Life: ummalife.com/ReshadMuzemil
╚═══📌Share📌════
✳️ ሀሰተኛ ፎቶዎችን ወይም ምስሎች እንዴት መለየት እንችላለን❗️

🔺በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ የሚያጠራጥራችሁን ፎቶ ስትመለከቱ በቀላሉ የትኛውንም ሚዲያ ወይም ግለሰብ እንዲያጣራላችሁ ሳትጠብቁ በእጅ ስልካችሁ ማረጋግጥ ትችላላችሁ።

🔺በቅደሚያ ሀሰተኛ የመሰላችሁን ፎቶ/ምስል ወደ ስልካችሁ Save አድርጉት።

🔺በቀላሉ ስልካችሁ ላይ "Google Chrome App" ክፈቱት፦

-ወደ Desktop Site ቀይሩት

-በቀኝ በኩል ከላይ Image የሚለውን ምረጡ

-በመቀጠል የካሜራ ምልክቱን ተጫኑ

ለማጣራት የፈለጋችሁትን ፎቶ Choose file የሚለው ላይ ፎቶውን Upload አድርጉት፤ ከዛ ውጤቱን አጣርቶ ይነግራቹኋል።

🌐 ዘመኑ #የቴክኖሎጂ ነው 📲 ከዘመኑ ጋር አብረው ይዘምኑ💻

Telegram: t.me/BasicComputer_Skills

tiktok.com/@basiccomputerskills

Umma Life: ummalife.com/ReshadMuzemil
╚═══📌Share📌════
የ2016 ዓ.ል የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና መስጫ ጊዜ ታወቀ

የ2016 የትምህርት ዘመን የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ (12ኛ ክፍል)ፈተና የሚሰጥበት ቀን ታውቋል።

የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና

ከሐምሌ 3-5  ለማህበራዊ ሳይንስ ከሐምሌ  9-11/2016 ዓ/ል ለተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች በበይነ መረብ (Online) እና በዩኒቨርሲቲ ውስጥ በወረቀት ይሰጣል።

በወረቀት ላይ የሚፈተኑ

የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች ሰኔ 30-ሐምሌ 01/2016 ዓ/ል እንዲሁም

የተፈጥሮ ሳይንስ ሐምሌ  6-7/2016 ዓ/ል ወደ ዩኒቨርስቲ የሚገቡ ይሆናል።


ስለሆነም ተፈታኞች እና የሚመለከታቸው ሁሉ ተገቢውን ዝግጅት እንዲያደርጉ አሳስቧል

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት

🌐 ዘመኑ #የቴክኖሎጂ ነው 📲 ከዘመኑ ጋር አብረው ይዘምኑ💻

Telegram: t.me/BasicComputer_Skills

tiktok.com/@basiccomputerskills

Umma Life: ummalife.com/ReshadMuzemil
╚═══📌Share📌════
👍2
✳️ መደበኛ ያልሆነ የልብ ምት መጠቆም የሚችል የሰውሰራሽ አስተውሎት ሞዴል ይፋ ሆነ❗️

🔺ተመራማሪዎች የልብ ምት መዛባት (Cardiac Arrhythmia) በመባል የሚታወቀውን መደበኛ ያልሆነ የልብ ምትን አስቀድሞ መጠቆም የሚያስችል የሰው ሰራሽ አስተውሎት ሞዴል ይፋ ማድረጋቸውን Wion TV ዘግቧል፡፡

🔺የሉክሰምበርግ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎችን ጨምሮ ከተለያዩ የምርምር ተቋማት በተውጣጣ ቡድን የበለፀገው ሞዴል ከመደበኛ የልብ ምት ወደ መደበኛ ያልሆነ የሚደረገውን ሽግግር በ80 በመቶ የትክክለኛነት መጠን መተንበይ መቻሉ ተመላክቷል፡፡

🔺ሞዴሉ በቻይና ዉሃን ከተማ ከሚገኘው ቶንግጂ ሆስፒታል በ24 ሰዓት ውስጥ የተወሰዱ 350 የታማሚ ናሙናዎችን በግብዓትነት በመጠቀም በዲፕ ለርኒንግ የማሽን ማስተማር ሂደት የበለፀገ ነው፡፡

🔺ቴክኖሎጂውን ሰዎች ከሚጠቀሟቸው የተለያዩ ተለባሽ ስማርት መሳሪያዎች ጋር በማቀናጀት ለታካሚዎች ስለልብ ምታቸው ሁኔታ ወቅታዊ መረጃዎችን መስጠት እንደሚችል ተጠቁሟል፡፡ መደበኛ ያልሆኑ ሁኔታዎች ሲኖሩም በአማካይ በየ30 ደቂቃ ማስጠንቀቂያ በመስጠት የቅድመ መከላከል እርምጃዎችን እንዲወስዱ ያስችላል፡፡

🔺ሞዴሉ ሰዎች የልባቸውን ደህንነት በየሰዓቱ ክትትል እንዲያደርጉና ቅድመ ማስጠንቀቂያዎችን ተጠቅመው ጤናቸውን እንዲጠብቁ በማስቻል ረገድ ጉልህ ሚና ይኖረዋ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

#Tech_News

🌐 ዘመኑ #የቴክኖሎጂ ነው 📲 ከዘመኑ ጋር አብረው ይዘምኑ💻

Telegram: t.me/BasicComputer_Skills

tiktok.com/@basiccomputerskills

Umma Life: ummalife.com/ReshadMuzemil
╚═══📌Share📌════
👍2
✳️ የዓለማችን ትልቁ 3ዲ ማተሚያ❗️

🔺ፋክትሪ ኦፍ ዘ ፊዩቸር (Factory of the Future) የተሰኘ የዓለማችን ግዙፍ 3ዲ ማተሚያ በአሜሪካው ሜይን ዩኒቨርሲቲ ይፋ ሆኗል፡፡ መሣሪያው በ2019 በዚሁ ዩኒቨርሲቲ ከተሰራዉና ማስተር ፕሪንት (Master Print) ከተሰኘዉ 3ዲ ማተሚያ በአራት እጥፍ የሚልቅ ነዉ፡፡

🔺ማተሚያው 29 ሜትር ርዝመት፣ 10 ሜትር ስፋት እና 5 ሜትር ቁመት ያላቸውን ቁሳቁሶች ማተም የሚችል ነው። በተጨማሪም በሰዓት 227 ኪሎ ግራም የማተም አቅም አለው።

🔺በትላልቅ የግንባታ ፕሮጀክቶች ላይ የሚሳተፈዉ ይህ መሣሪያ እንደ ድልድይ ግንባታ፣ የንፋስ ኃይል ማመንጫ እና መርከብን የመሳሰሉ ግዙፍ ቁሶችን በማምረት ሂደት ለአካባቢ ተስማሚ የሆነ የማምረቻ አማራጭ ይዞ መምጣቱን ከዩኒቨርሲቲው ድረ-ገጽ የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

#Tech_News

🌐 ዘመኑ #የቴክኖሎጂ ነው 📲 ከዘመኑ ጋር አብረው ይዘምኑ💻

Telegram: t.me/BasicComputer_Skills

tiktok.com/@basiccomputerskills

Umma Life: ummalife.com/ReshadMuzemil
╚═══📌Share📌════
👍3
ዴቪን የሚል መጠሪያ የተሰጠው ሶፍትዌር ማበልፀግና ኮድ መጻፍ የሚችል የሰውሰራሽ አስተውሎት ሞዴል ተዋወቀ

ኮግኒሽን በተባለው የቴክኖሎጂ ኩባንያ የበለፀገው ዴቪን፤ የመጀመሪያው የሰውሰራሽ አስተውሎት የሶፍትዌር ኢንጅነር ነው ተብሎለታል፡፡ ሞዴሉ የሚቀርብለትን ጥያቄ (Prompt) በመጠቀም ኮድ መጻፍ፣ ድረ-ገጾችን እና ሶፍትዌሮችን ማልማት እንደሚችል ዊዮን ዘግቧል፡፡

ዴቪን ውስብስብ ስራዎችን የማቀድና በሺዎች የሚቆጠሩ ውሳኔዎችን የመወሰን አቅም አለው፥ በጊዜ ሂደትም ከስህተቱ በመማር እና ራሱን እያሻሻለ በመሄድ ወደላቀ አፈጻጸም ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ቴክኖሎጂው ሰዎችን ከመተካት ይልቅ የተለያዩ ተግባሮችን በትብብር  በአንድ ጊዜ በመከወን ስራ ማቅለልን ዒላማው ማድረጉ ተነግሮለታል፡፡

ይህ የሰውሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ ውጤት በዘርፉ የተሰማሩ ሶፍትዌር አበልፃጊዎች ይበልጥ ውስብስብ በሆኑ ችግሮች ላይ እንዲያተኩሩ በማበረታታት በሶፍትዌር ልማት ውስጥ አዲስ የፈጠራ ዘመን እንዲመጣ መንገድ ይከፍታል።

#Tech_News

🌐 ዘመኑ #የቴክኖሎጂ ነው 📲 ከዘመኑ ጋር አብረው ይዘምኑ💻

Telegram: t.me/BasicComputer_Skills

tiktok.com/@basiccomputerskills

Umma Life: ummalife.com/ReshadMuzemil
╚═══📌Share📌════
✔️ የንግግር ችግር ለሚገጥማቸዉ ሰዎች የማሽን ማስተማር ሒደትን ያካተተ አዲስ የቴክኖሎጂ መፍትሔ ይፋ ሆነ❗️

በካሊፎርኒያ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች የተሰራው ይህ መሣሪያ በተለይ ከጉሮሮ ካንሰር ቀዶ ጥገና ለሚያገግሙ እና ድምፅ የማዉጣት ችግር ለሚገጥማቸዉ ሰዎች ታስቦ ተሰርቷል፡፡

ኔቸር ኮሙኒኬሽን የተሰኘው ጆርናል እንደዘገበዉ ይህ ፈጠራ አራት ማዕዘን ቅርጽ እና አነስተኛ መጠን ያለው ከጉሮሮ ውጭ ባለው ቆዳ ላይ የሚለጠፍ መሣሪያ ነው፡፡ መሣሪያዉ ዳሳሽ እና አንቀሳቃሽ የተባሉ ሁለት ክፍሎች አሉት፡፡ እነዚህ ክፍሎች ከሲልከን እና ለማግኔት ምላሽ ከሚሰጡ ቁሳቁሶች ጋር በመዋሀድ የተሠሩ ናቸዉ፡፡

በመሣሪያው ውስጥ ያለው ዳሳሽ በድምጽ ሳጥን ውስጥ ያሉትን ጡንቻዎች ማግኔቶላስቲክ የተባለ ልዩ ቴክኖሎጂን በመጠቀም እንዴት እንደሚንቀሳቀሱ ይገነዘባል፡፡ እነዚህን እንቅስቃሴዎች ወደ ኤሌክትሪክ ምልክቶች በመለወጥ የማሽን ማስተማሪያን በሚጠቀም ስማርት የኮምፒውተር ፕሮግራም ይጠናል፤ በመቀጠልም የመሳሪያው አንቀሳቃሽ ክፍል ለሞተሩ ኃይል በመስጠት የንግግር ድምፆችን ይፈጥራል፡፡

#Tech_News

🌐 ዘመኑ #የቴክኖሎጂ ነው 📲 ከዘመኑ ጋር አብረው ይዘምኑ💻

Telegram: t.me/BasicComputer_Skills

tiktok.com/@basiccomputerskills

Umma Life: ummalife.com/ReshadMuzemil
╚═══📌Share📌════
የኮምፒውተራችሁ sound system አልሰራ ካላችሁ የሚከተሉትን መፍትሄዎች ሞክሯቸው።

✔️ ከኮምፒውተራችሁ ወይም ከaudio player ላይ mute አለመሆኑን አረጋግጡ።
✔️ audio troubleshooter ተጠቅማችሁ ሙሉ ሲስተሙን ቼክ አድርጉ።
Task manager search bar ላይ audio troubleshooter, ብላችሁ ጻፉና Find and fix problems with playing sound የሚል ይመጣላችኋል ምረጡት።

Start > Settings > System  > Sound  > Troubleshoot አድርጋችሁም መክፈት ትችላላችሁ።
የሚከፍትላችሁን ምርጫ Speaker/Headphone ላይ አድርጉና next next እያላችሁ ሞክሩት።
ይህ ካልሰራላችሁ ወደቀጣዩ step ሂዱ።
✔️ Updated የሆነ Windows install ማድረጋችሁን እርግጠኛ ሁኑ። ይህን ለማረጋገጥ
Start  > Settings  > Update & Security  > Windows Update  > Check for updates.

 "You're up to date," ካለ update ሆኗል ማለት ነው ወደ ቀጣይ step ሂዱ።
    "Updates are available," ካላችሁ ደግሞ install አድርጉት።
ስትጨርሱ ኮምፒውተራችሁን restart አድርጉት።
✔️ Audio Driver መስራቱንና update መሆኑን ቼክ አድርጉ። ድራይቨሮች የኮምፒውተሩ ሃርድዌርና ሶፍትዌር እንዲናበቡ የሚያደርግ ሲሆን የማይሰራና ጊዜው ያለፈበት driver sound ሲስተሙ በትክክል እንዳይሰራ ያደርጋል።
✔️ audio driver update ለማድረግ
search ባር ላይ device manager ብላችሁ search አድርጉ።
የሚመጣላችሁን ከከፈታችሁ በኋላ Sound, video and game controllers የሚለው ጋ click አድርጋችሁ ከፍተቱት።
የሚዘረዘሩላችሁን sound ካርዶች right click እያደረጋችሁ search automatically for drivers በሉት።
✔️ በዚህ መንገድ ካልሰራ 
ኮምፒውተራችሁን የሰራው ድርጅት official website ላይ ገብታችሁ የራሱን driver ዳውንሎድ አድርጉና በተመሳሳይ step ሄዳችሁ Browse my computer for drivers የሚለውን በመምረጥ download ያደረጋችሁትን ፋይል browse አድርጋችሁ ጫኑት።

Part 2 ይኖረዋል.....

🌐 ዘመኑ #የቴክኖሎጂ ነው 📲 ከዘመኑ ጋር አብረው ይዘምኑ💻

Telegram: t.me/BasicComputer_Skills

tiktok.com/@basiccomputerskills

Umma Life: ummalife.com/ReshadMuzemil
╚═══📌Share📌════
#ጥቆማ

የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት በክረምት የስልጠና መርሐግብር የሚሳተፉ ተማሪዎች ምዝገባ ጀምሯል።

እነማን ይመዘገባሉ?
የመጀመሪያ እና የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች

የምዝገባ ጊዜ፦
ከሚያዝያ 17 እስከ ግንቦት 7/2016 ዓ.ል

ስልጠናው መቼ ይጀምራል?
ከሐምሌ 1 እስከ ጳጉሜን 1/2016 ዓ.ል
(ለሁለት ወራት) (በሳምንት ለአራት ቀናት)

ስልጠናው ትኩረት የሚያደርግባቸው፦

➭ የሰው ሰራሽ አስተውሎት መሰረታውያን፣
➭ ሮቦቲክስ፣
➭ ፕሮግራሚንግ፣
➭ ማሽን ለርኒንግ እና ሌሎችም።

ምዝገባ የማድረጊያ አማራጮች፦

👉 forms.gle/9B79pzGLdo84W2LY8

👉 https://www.aii.et/summer-camp-registration-form-for-student/

Via= tikvahuniversity

[[ለሶስተኛ ጊዜ የተለጠፈ]]

🌐 ዘመኑ #የቴክኖሎጂ ነው 📲 ከዘመኑ ጋር አብረው ይዘምኑ💻

Telegram: t.me/BasicComputer_Skills

tiktok.com/@basiccomputerskills

Umma Life: ummalife.com/ReshadMuzemil
╚═══📌Share📌════