Basic Computer Skills
1.87K subscribers
1.22K photos
100 videos
576 files
833 links
#በዚህ የቴሌግራም ቻናል
↪️ Programming
↪️ ቴክኖሎጂ ነክ ትምህርቶችን
↪️ ኮምፒውተር ነክ ትምህርቶችን
↪️Basic Computer Skills
↪️ Software
↪️ AI and AI Skills (Like ChatGPT)

ከላይ የተዘረዘሩትና ሌሎችም ገራሚ ትምህርቶች ይለቀቅበታል!

t.me/BasicComputerSkillsGroup

𝘽𝙮 𝙍𝙚𝙨𝙝𝙖𝙙
Download Telegram
💢ስልካችንን📲 እንዴት ከሌላ ስልክ ላይ ቻርጅ ማድረግ እንችላለን?

#አስፈላጊ ነገሮች⬇️⬇️⬇️

ሌላኛው ስልክ
OTG
data cable

1⃣. አሰራር፦ ኬብሉን #OTG ላይ ይሰኩና በቀላሉ #OTG ያለበትን ጫፍ ቻርጅ ሰጪው ስልክ📲 ላይ ይሰኩት።

2⃣. ሌላኛውን ጫፍ ቻርጅ ማድረግ የሚፈልጉት ስልክ ላይ ይሰኩት።

አለቀ፤ ዳይ ወደ ዘረፋ


#መረጃዎችን ላላወቁት እንዲደርሳቸው በማጋራት (Share በማድረግ) ተባበሩን↘️

🌐 ዘመኑ #የቴክኖሎጂ ነው 📲 ከዘመኑ ጋር አብረው ይዘምኑ💻

Telegram: t.me/BasicComputer_Skills

tiktok.com/@basiccomputerskills

Umma Life: ummalife.com/ReshadMuzemil
╚═══📌Share📌════
#የኮምፒውተር_ሀርድ_ዲስክ_ብልሽት_ምልክቶችን_ይዘንላቹ_ቀርበናል!
▄▄▄▄▄▄▄▄▄▄▄▄▄▄▄

✏️ያው ሃርድ ዲስክ ሲበላሽ ብዙ ዳታዎች የጠፋሉ እናም ብዙ ችግሮች ሊያጋጥሙዋቹ ይችላል! ነገር ግን ሃርድ ዲስክኩ መበላሸቱ በፊት በሚያሳያቸው ምልክቶችን ይህንን መከላከልሊያስችላቹ ይችላል።


❶. ኮምፕዩተራችሁ የመዘገም (ስሎው) የማለት ባህሪ ሲያጋጥሞ

❷. ሰማያዊ ነጭ ቀለም ያለው ፊደላትን ሲያዩ

❸. በተደጋጋሚ እስታክ ማረግ ሲጀም

❹. የተለያዩ ኢረሮችን(ችግሮችን) ማሳየት ሲጀምር

❺. ኮምፕዩተሩ ጠፍቶ ሲበራ የተለያየ ችግሮች ካሉት

❻. የተለያዩ ሶፍትዌሮች ክራሽ ሲያረጉ

❼. አላስፈላጊ የሆኑ ነገሮች ሲያወጣ
ለምሳሌ፦ ፕሪንት ሊደረግ ሲል የተለየ ነገር የሚያወጣ ከሆነ

❽. ዳታዎቻቹ ሲጠፉ ወይም ኮራፕት ሲያረጉ

❾. አንድን ዳታ ለመክፈት ብዙ ሰዓታትን ሲፈጅ

❿. የተለያዩ አላስፈላጉ የሆኑ ድምጽ ከኮምፕዩተራቹ ሲወጣ ኮምፕዩቹህ ይህንን ሁሉ የሚያረግ ከሆነ በቅርብ ጊዜ ውስጥ ሃርድ ዲስክ ሊበላሽ ይችላል ማለት ነው::

❖ሰለዚህ ይህንን ብልሽት እናንተ ላይ ችግር እንዳያስከተል የተወሰኑ ነገሮችን ብታረጉ የተመረጠ ነው።

እኛ በበኩላችን የምን መርጣችው ሁለት አማራጮች አሉ እነሱም፡

■የመጀመሪያው S.M.A.R.T (Self-Monitoring, Analysis and Reporting Technology) የተባለን ሶፍትዌር ዳውንⶀድ (በማውረድ) ብልሽቱ ከመፈጠሩ በፉት በማስታወስ ኮምፕዩተሮ ላይ ያሉትን ችግሮች ለመፍታት የሚያስችሉ ፍንጮችን እንድታገኙ ያስችላቹሃል!

■ሁለተኛው ደሞ ኮምፕዩተራቹህ ውስጥ ያሉትን ፋይሎች በየጊዜው ባካፕ(ሌላ ኮፒ በማስቀመጥ) መጠንቀቅ እና ሊጠፉ የሚችሉ ፋይሎችን መታደግ እንችላለን። ባክ አፕ ለመውሰድ ግድ ፍላሽ ወይም ሌላ መሳሪያ አያስፈልጋቹም በኢንተርነት ላይ የተለያዩ የመጫኛ ሳይቶችን መጠቀም ተችላላቹ
══════❁✿❁ ══════

   #መረጃዎችን ላላወቁት እንዲደርሳቸው በማጋራት (Share በማድረግ) ተባበሩን↘️

🌐 ዘመኑ #የቴክኖሎጂ ነው 📲 ከዘመኑ ጋር አብረው ይዘምኑ💻

Telegram: t.me/BasicComputer_Skills

tiktok.com/@basiccomputerskills

Umma Life: ummalife.com/ReshadMuzemil
╚═══📌Share📌════
አግራሞቴን በብዕር

[[ልቧ የተሰበረ ብዕር የሞነጫጨረችው ፅሑፍ]]


ለሰዎች አዘኔታህን ስታሳያቸው እነሱ ያስባሉ እየለመንካቸው እንደሆነ!
እሺታህ ባበዛህ ጊዜ ጅል መስለህ ትታያቸዋለህ። እነሱ ያስባሉ ምንም እንደማታውቅ፣ ምንም እንዳልከፋህ!!

ወዳጄ አንተ በምታደርገው ነገር ከሰዎች መልካም ምላሽን ከጠበቅክ እጅጉኑ ትጎዳለህ፣ ታዝናለህ፣ ክፉኛ ትቆስላለህ!

⭕️ ከዚህ ሁሉ የባሰ የሚያቆስለው፦
*ወንድም እህቶችህ ስህተት ላይ ሲወድቁብህ ይህ ስህተት እንደሚጎዳቸውና ከጌታቸው እንደሚያጣላቸው ደጋግመህ ነግረሃቸው ነገር ግን እነሱ ከስህተታቸው ሳይመለሱ ሲቀሩ ልብህ ስብርብሩ ይወጣል።

ደጋግመህ ይህ ስህተት ነው ስትላቸው እንደ ጠላታቸው ያዩሃል። የበደልካቸው ይመስላቸዋል። በድፍረት አላህንም ሳይፈሩ እየጎዳሃቸው መሆኑን ይናገራሉ።

➤ የሚገርም ትውልድ!
➤ አንድን ነገር እንደሚጎዳው እያወቀ የሚጎዳውን ነገር የሚጨብጥ ትውልድ።
➤ እሳት መሆኑን እያወቀ እሳቱ ላይ እራሱንና ጓደኞቹን የሚወረውር ትውልድ።
➤ ወደ መጥፎ ጎዳና የሚመራውን ወዳጅ፣ ወደ መልካም መንገድ የሚያቅጣጨውን ደግሞ ጠላት አድርጎ የሚያይ ትውልድ።

▬▭▬▬▭▭▬▬▭▭▬▬▬▭▭
🇵🇸 ብዙ ለመፃፍ ብዕሬም እሺ አላለችኝም።

◆ አምላካችን አላህ ቀልብ ይስጠን‼️ ሌላ ምን ይባላል!?


[[በረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል]]

ቀን:- ረቡዕ/ሚያዝያ 16/2016 ዓ.ል



ummalife.com/ReshadMuzemil
Data Afalagi (ዳታ አፋላጊ)
የተለያዩ የሀገር ውስጥ ስም ዝርዝር ሲወጣ ሰማችንን ለመፈለግ አዳጋች ይሆናል።
✔️የፓስፖርት ዝርዝር
✔️የኮንዶሚንየም ዕጣ
ወዘተ
ፓስፖርት ተመዝጋቢዎች ረጅም ግዜ ህትመት ሲጠብቁ ቆይተው ነገር ግን ለመፈለግ አዳጋች በሆነ መልኩ ከኢምግሬሽን በቴሌግራም ቻናል በPDF ይለቀቃል።

ይህ application በቀላሉ ፓስፖርቱ መድረሱን የመናውቅበት ማፈላለግያ አፕልኬሽን ነው።
በቀጣይ የኮንደምንየም እጣ ወዘተ መረጃዎች ስለሚጠቅም ዳውንሎድ በማድረግ ተጠቀሙበት።

🖥 Playstore link

https://play.google.com/store/apps/details?id=com.app.datasearch


   #መረጃዎችን ላላወቁት እንዲደርሳቸው በማጋራት (Share በማድረግ) ተባበሩን↘️

🌐 ዘመኑ #የቴክኖሎጂ ነው 📲 ከዘመኑ ጋር አብረው ይዘምኑ💻

Telegram: t.me/BasicComputer_Skills

tiktok.com/@basiccomputerskills

Umma Life: ummalife.com/ReshadMuzemil
╚═══📌Share📌════
✳️ ይህን ሞክረውታል

🔺ስልክን በሚስጢራዊ ቁጥሮች በፓተርን ወይም በፊት ቅርጽ፣ በአሻራ የመቆለፊያ መንገዶች በመጠቀም የግል መረጃዎችንና ልዩ ልዩ መተግበሪያወችን መቆለፍ ወይም ደብቆ ማስቀመጥ እንደሚቻል የታወቀ ነው፡፡

🔺ነገር ግን በስልካችን ውስጥ የሚገኙ በአፋጣኝ የምንፈልጋቸውን መተግበሪያዎች ስልካችን እንደተቆለፈ መጠቀም የምንችልባቸው ዘዴወች አሉ፡፡ ለምሳሌ ያክል እንደ ጎግል እና ሴሪ (Google Assistant and Siri) ፎቶ ማንሳትና የአደጋ ጊዜ ስልክ ጥሪ ማድረግ (emergency calls) ያስችለናል።

🔺አንድሮይድ ስልክ ያለው ሰው መጀመሪያ የጎግል መተግበሪውን (Google Assistant app) ይከፍታል፡፡ ከዚያም በታች ቀኝ በኩል የሚገኘውን የኮምፓስ ምልክት መንካት በላይኛው የግራ ክፍል በመሄድ (Settings
Assistant and Phone) የሚሉትን መምረጥ ከዚያም የድምጽ ማመሳሰያ ምልክቱን ማብራት ከዚህ በፊት ስልኩ የተጠቃሚውን ድምፅ የማያውቅ ከሆነ መጀመሪያ ስልኩ ድምፅ መለየት (voice recognition) እንዲችል ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ አንድ ጊዜ ይህ ከተስተካከለ በኋላ የ Google Assistant ለማግኘት "Hey Google" ወይም "Okay Google" ማለት ብቻ ነው የሚጠበቅብን፡፡ ከዚያም የምንፈልገውን አገልግሎት ማግኘት እንችላለን፡፡
#Tech_Tips

   #መረጃዎችን ላላወቁት እንዲደርሳቸው በማጋራት (Share በማድረግ) ተባበሩን↘️

🌐 ዘመኑ #የቴክኖሎጂ ነው 📲 ከዘመኑ ጋር አብረው ይዘምኑ💻

Telegram: t.me/BasicComputer_Skills

tiktok.com/@basiccomputerskills

Umma Life: ummalife.com/ReshadMuzemil
╚═══📌Share📌════
12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና አጋዥ አፕሊኬሽናችን አሁን Play Store ላይ ይገኛል። Download እና Upgrade በማድረግ ይጠቀሙባቸው!!

በነጻ ለውስን ቀናት
አዲሱን ስርአተ ትምህርት ያካተተ
አጫጭር ኖቶችና አጋዥ ቪድዮዎች የያዘ

አሁኑኑ ይሞክሩት!!
ለማውረድ ይህን ማስፈንጠሪያ መጠቀም ይቻላል ➝ Playstore
ጥቆማ
=======
(የመጀመሪያና የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪ ልጅ ላላችሁ ወላጆች በሙሉ!)
||
እኔ በዚህ ጉዳይ የምነግራችሁን ነገር ጆሯችሁን አቁማችሁ ማዳመጥ፣ ዓይናችሁን ከፍታችሁ ማየት ግደታ አለባችሁ። ልጆቻችሁን ፍጠኑን ለቀጣይ ክረምት ለዚህ ትሬይኒንግ አሁኑኑ መዝግቧቸው። የሚቀበሉት 200 ሰው ብቻ ነው። ማስታወቂያውን የለቀቁት ገና አሁን ነው። ልጆቻችሁ ገና ከወዲሁ ለቀጣዩ ጊዜም ተራማጅ የሆኑ መስኮችን በማወቅ ዓይን እንዲከፍቱና ፍላጎቱ እንዲያድርባቸው ያደርጋቸዋል። ተናግሪያለሁ!

«ማስታወቂያ
ለኤ.አይ ሰመር ካምፕ 2024 የክረምት ስልጠና ፈላጊ ታዳጊዎች በሙሉ

የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ለ2 ወራት የሚቆይ የኤ.አይ ሰመር ካምፕ 2024 የስልጠና መርሓ ግብር በአዲስ አበባ አዘጋጅቷል፡፡

ስልጠናዉ በ
🎯AI basics
🎯Robotics
🎯Programming
🎯Machine learning
🎯Internet of Things (IoT) ላይ ትኩረቱን ያደርጋል፡፡

የመመዝገቢያ መስፈርቶች
👉🏼የመጀመሪያ እና ሁለተኛ ደረጃ ተማሪ የሆነ/ የሆነች
👉🏼ስልጠናውን በሳምንት 4ቀን መከታተል የሚችል/ የምትችል

የምዝገባ ቀናት     
👉🏼ከሚያዝያ 17 - ግንቦት 07፣ 2016 ዓ.ል ባሉት ቀናት

አመልካቾች ከታች የተቀመጡትን ሊንኮች በመጠቀም መመዝገብ የሚችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

👉🏼 https://forms.gle/9B79pzGLdo84W2LY8

👉🏼 https://www.aii.et/summer-camp-registration-form-for-student/

በተጨማሪም እውቀት እና ክህሎታቸውን ለተማሪዎች በማካፈል በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂ ትውልዱን ለመገንባት ዕድሉን የሚፈልጉ አሰልጣኞች ተከታዮቹን ሊንኮች በመጠቀም መመዝገብ የሚችሉ መሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን፡፡

👉🏼 https://www.aii.et/ethiopian-ai-summer-camp-2024-application-form-trainer-for-summer-camp/

👉🏼 https://forms.gle/P2vAoZuWT7JgYQtT6

ለበለጠ መረጃ contact@aii.et ይጠቀሙ ወይም ድረ ገጻችንን www.aii.et  ይጎብኙ፡፡

አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ በሁሉም!»

©️ ©️
✳️ ፎቶግራፍን ወደ ግጥም የመቀየር አቅም ያለው በሰዉ ሰራሽ አስተዉሎት የታገዘ ካሜራ❗️

🔺ፖይትሪ ካሜራ (Poetry Camera) የሚል ስያሜ የተሰጠዉ ይህ ፈጠራ ምስሎችን በማንሳት ወደ ግጥም ስንኞች ለመቀየር የሚያስችል ነው።

🔺ካሜራዉ ፎቶዎች በተለምዶ ከሚያሳዩት የምስል ትዕይንት ባሻገር በምስሉ ውስጥ ያሉትን ትዕይንቶች ለመተንተን የሚውሉ የግጥም መግለጫዎችን ለመስራት ያገለግላል፡፡

🔺የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂ ግኝት የሆነዉ ይህ ካሜራ የኦፕን Ai ፈጠራ የሆነዉ ጂፒቲ 4 ሞዴልን እና ባለትናንሽ ነጠላ-ቦርድ ኮምፒዩተሮችን (Raspberry Pi) ይጠቀማል፤ ቴክኖሎጂዉ የፎቶዎቹን ቀለሞች፣ ባሕርያት እና ይዘቶችን ይመረምራል።

🔺በመቀጠልም ከፎቶው የሰበሰባቸዉን ዳታዎች ተጠቅሞ የግጥም ስንኞችን ይሰጣል፡፡ ኬሊን ካሮሊን እና ሪያን ማተር በተባሉ ወጣቶች የተሰራዉ ካሜራዉ ለጥበብ አፍቃሪያን አዲስ አማራጭ ይዞ መምጣቱን RT News ዘግቧል፡፡

▬▭▬▭▬▭▬▬▭▬▭▬▭▬
⭕️ ከቴክኖሎጂው ጋር በአግባቡ ተዋወቅ ብያችሁ አልነበር¡¿ ቴክኖሎጂው ዓለምን በምን አይነት ፍጥነት እየተቀየራት እንዳለ ተመልከቱ‼️

#Tech_News

   #መረጃዎችን ላላወቁት እንዲደርሳቸው በማጋራት (Share በማድረግ) ተባበሩን↘️

🌐 ዘመኑ #የቴክኖሎጂ ነው 📲 ከዘመኑ ጋር አብረው ይዘምኑ💻

Telegram: t.me/BasicComputer_Skills

tiktok.com/@basiccomputerskills

Umma Life: ummalife.com/ReshadMuzemil
╚═══📌Share📌════
4
*ተከፍተው ይሁን* ብለህ ትጨነቃለህ ለካ እነሱ አንተ ላይ ፊታቸውን አዙረውብህ ነው።

እኮ ብቻ ጌታ ፊቱን አያዙርብህ፤ የሰውስ ነገር ቀላል ነው።

ummalife.com/ReshadMuzemil
4
💢ስልካችን📲 "sync error" ሲለን እንዴት ማስተካከል እንችላለን???

1⃣.Date & Time አስተካክሉ።

⚠️#Setting ውስጥ ገብታችሁ Automatic Date and Time ብታደርጉት ይመረጣል።

2⃣. Background data'ዉ #restrict ሆኖ ከነበረ #unristrict ማድረግ።

⚠️Setting➡️ data usage➡️ restrict background data የሚለዉን unselect ማድረግ።

3⃣. ለምሳሌ እንደዛ ያለው #Gmail ቢሆን...

⚠️Settings➡️ Apps & Notifications➡️ App Info➡️ Gmail➡️ Storage➡️ Clear Data.

4⃣. update google play service

⚠️Playstore ስትከፍቱ #Update ላድርገው ወይ ብሎ እራሱ ይጠይቃችኋል።

5⃣. ብዙ ስልኮች📲 #በData ስለሚያስቸግሩ #በWifi

🌐 ዘመኑ #የቴክኖሎጂ ነው 📲 ከዘመኑ ጋር አብረው ይዘምኑ💻

Telegram: t.me/BasicComputer_Skills

tiktok.com/@basiccomputerskills

Umma Life: ummalife.com/ReshadMuzemil
╚═══📌Share📌════
ዩኤስቢ ዋይፋይ አዳፕተር USB WiFi Adapter ምንድን ነው?
*ዩኤስቢ ዋይፋይ አዳፕተር የብሮድባንድ ገመድ ሳያስፈልግ በቀላሉ ኮምፒውተራችንን እና የዲሽ ሪስቨራችንን ከ ዋይፋይ ኔትዎርኮች ጋር በማገናኘት ኢንተርኔት ያስጠቅመናል ፡፡ ይህም በዩኤስቢ መሰኪያ ላይ በመሰካት ነው::

*እስከ 150Mbps ድረስ የማስጠቀም አቅም አለው::

* ከ15 - 20 ሜትር  እርቀት ላይ ሆነው መጠቀም  ይችላሉ::

*ለ Win 7, 8, 8.1, 10, Mac እና Linux ኦፕሬቲንግ ሲስተሞች ይሆናል::

*WLAN Driver አብሮ ያለው

*በሌላ ኮምፒውተር ላይ ለመጠቀም በሚፈለግበት ጊዜ ነቅለው መውሰድ ይችላሉ ፡፡

ዩኤስቢ ዋይፋይ አዳፕተርን መጠቀም ብዙ ጥቅሞች አሉት!
1.ዩኤስቢ ዋይፋይ አዳፕተርን ፈጣን የኢንተርኔት  ግንኙነት በማቅረብ ለኮምፒተርዎ አዲስ ሕይወት ይሰጣል፡፡ ኮምፒተርዎ በዝቅተኛ የግንኙነቱ ፍጥነቱ ኔትወርክን እያሰናከለ ነበር ፣ ስለሆነም ፍጥነት እንዲጨምር መደረጉ  ቀሪውን የቤት/መስርያ ቤት ውስጥ ኔትዎርኮችን ለፈጣን ግንኙነት ነፃ ያደርጋቸዋል ፡፡
2. ዩቲዩብ እና አይ.ፒ.ቪ ቻናሎችን በሳተላይት ዲኮደር (ዲሽ ሪሲቨር) አማካኘነት ዩኤስቢ ዋይፋይ አዳፕተሩን በመሰካት በቀላሉ  መመልከት ይቻላል፡፡
3.ምንም አይነት የውስጣዊ ሃርድዌር መጫን  ዘዴ የለውም - ስለዚህ ለዝቅተኛ የቴክኖሎጂ እውቀት ላለው ተጠቃሚ እንኳን ቀላል ነው::

#አስተዉሉ
የብሮድባንድ ገመድን በመሰካት ብቻ ይሰሩ የነበሩ ኮምፕዩተሮች (ዴስክቶፕም ሆነ ላፕቶፕ) ይሄ  ሁነኛ ዘላቂ መፍተሄ  ነው!

🌐 ዘመኑ #የቴክኖሎጂ ነው 📲 ከዘመኑ ጋር አብረው ይዘምኑ💻

Telegram: t.me/BasicComputer_Skills

tiktok.com/@basiccomputerskills

Umma Life: ummalife.com/ReshadMuzemil
╚═══📌Share📌════
window 10 installation giude.pdf
1.2 MB
Window 10 Installation Setps
​​✳️ በአለማችን ትልቁ የCreation Software Developing ካምፓኒ Adobe ሲሆን የአዶቤን ሶፍትዌር የማይጠቀም ፕሮዲውሰር ፣ Studio ፣ ዲዛይነር ፣ TV Company የለም ማለት ይቻላል። ከትላልቆቹ Hollywood እስከ ጀማሪዎቹ Art ባለሙያዎች ሁሉም ስፘቸውን የሚሰሩት በAdobe ነው።

◽️ በአለም ዙሪያ ብዙ ተጠቃሚ ያላቸውና በብዙ ሰዎች የሚወደዱ የAdobe ሶፍትዌሮች፡

🔺Adobe Photoshop | ፎቶና ግራፊክስ መስሪያና ማቀናበሪያ
🔺Adobe Premiere Pro | ቪዲዮ ማቀናበሪያ
🔺Adobe After effect | Motional ግራፊክስ መስሪያ
🔺Adobe Lightroom | የፎቶ ከለር ማቀናበሪያ
🔺Adobe illustrator | ዲጂታል ስዕልና ሎጎ መስሪያ
🔺Adobe xD | interface ዲዛይን ማድረጊያ
🔺Adobe InDesign | Logo, Banner, Mesh መስሪያ
🔺Adobe Premiere Rush | all In one ቪዲዮ ማቀናበሪያ
🔺Adobe Dimension | 2D እና 3D ነገሮች Design ማድረጊያ
🔺Adobe Character Animator | 2D Animation መስሪያ
🔺Adobe Bridge | file organize ማድረጊያ
🔺Adobe Dreamweaver | ዌብሳይት መስሪያ
🔺Adobe Acrobat | Pdf መፍጠሪያና ማቀናበሪያ
🔺Adobe Animate | Vector ግራፊክስ እና Animation መስሪያ
🔺Adobe Audition | ድምፅ ማቀናበሪያ

🌐 ዘመኑ #የቴክኖሎጂ ነው 📲 ከዘመኑ ጋር አብረው ይዘምኑ💻

Telegram: t.me/BasicComputer_Skills

tiktok.com/@basiccomputerskills

Umma Life: ummalife.com/ReshadMuzemil
╚═══📌Share📌════
ከF1 እስከ F12 ያሉ # የዊንዶውስ
ቁልፎች አገልግሎት
በኮምፒውተራችን ኪይቦርድ ከላይ ተደርድረው
የምናገኛቸው ከF1 – F12 ያሉ ቁልፎችን Function
Key እንላቸዋለን፡፡
በዋናነትም ከሌሎች # ቁልፎች ጋር
በማጣመር እንደ አቋራጭ እንጠቀምባቸዋለን፡፡ እንኘህ
ቁልፎች እንደ ምንጠቀመው የ ኦፐሬቲንግ ሲስተም እና
ሶፍትዌሮች አገልግሎታቸው ይለያያል፡፡: በዛሬው
ቱቶሪያላችንም የተወሰኑትን እናያለን፡፡
📍 F1
ብዙ ጊዜ የምንጠቀመው እርዳታ ስንሻ ነው፡፡ በአብዛኛው
ሶፍትዌሮች F1 ስንጫን # የ Help መስኮትን ይከፍቱልናል፡፡
ማይክሮሶፍት ወርድ ላይ ካለን Start እና F1 መጫን የ
Microsoft Online Help ይከፍታል፡፡
📍 F2
# የተመረጠን አይከን፤ፋይል ወይንም አቃፊ ስም ለመቀየር
F2 መጫን ይቻላል፡፡ ማይክሮሶፍት ወርድ ላይ ካለን Alt
+ Ctrl + F2 መጫን #የ Open መስኮትን ይከፍታል፡፡፡
📍 F3
ዴስክቶፕ ላይ ካን ስንጫን የፍላገ መስኮት ይከፈታል፡፡
ማይክሮሶፍት ወርድ ላይ ካለን ቃልን መርጠን Shift +
F3 መጫን # የተመረጠው ቃል ውስት የሚገኙ ፊደላትን
አንድላይ ካፒታል ወይን ስሞል ወይንም የመጀመሪያውን
ፊደል ካፒታል ያደርግልናል፡፡
📍 F4
አሁንም ማይክሮሶፍት ወርድ ላይ ካለን F4 # መጫን
ለመጨረሻ ጊዜ የተገበርነውን ይደግምልናን፡፡ ለምሳሌ
አበበ ብለን ብንጽፍ እና F4 ብናጫን በ የምትባለውን
ፊደለ በድጋሚ ይጽፍልናል፡፡ Alt + F4 መጫን አክቲቭ
#የሆነውን መስኮት ይዘጋልናል፡፡ Ctrl + F4 ስንጫን
ደግሞ አክቲቭ ከሆነው መሰኮት ውስጥ አክቲቭ የሆነውን
ታብ ይዘጋልናል፡፡ ለዚህ ጥሩ ምሳሌ የሚሆነው በ
ብራውሰራችን ከአንደ በላይ ታብ ከከፈትን Ctrl + F4
ስንጫን ያለንበትን ታብ ብቻ ይዘጋልናለን ነገር ግን Alt +
📍 F4 ብንጫን ሙሉ በሙሉ ብራውሰሩን ይዘጋብና ማት
ነው፡፡
📍 F5
አሁን ገበያ ላይ ባሉት አብዛኛዎ ብራውሰሮች ላይ F5
መጫን # Refresh ያደርገልና፡፡ ማይክሮሶፈት ወርድ ላይ የ
Find መስኮትን ይከፍትልናል፡፡ ማክሮሶፍት ፓወር ፖይንት
ላይ ደግሞ Slideshow ያስጀምርልና፡፡
📍 F6
በአብዛኛው ብራውሰሮች ላይ F6 ስንጫን የማውሳችን
አቅጣጫ መጠቆሚያ #(cursor) ወደ አድራሻ መጻፊያው
ይወስድልና፡፡ ከአንድ በላይ የማይከሮሶፍት ወርድ
ከከፈትን Ctrl + Shift + F6 መጫን # ወደቀጣዩ
የማይክሮሶፍት መስኮትያሸጋግረናል፡፡
📍 F7
ማይክሮሶፍት ወረድ ላይ Shift + F7 መጫን የ
#Thesaurus መስኮትን ይከፍትልናል የሚያገለግለውም
ሰፔሊንግ፤ ፍቺ እና ሰዋሰው ለማስተካከል ነው፡፡
📍 F8
ኮምፒውተራችን ሲነሳ የ Windows፤ # Startup menu
ለመግባት የጠቅማል፡፡
📍 F9
በዊንዶውስ ላይ ጥቅም የለውም ነገር ግን
በማይክሮሶፍት ኦፍስ እንጠቀምበታለን
#Ctrl + F9= እንዲህ አይነት ባዶ ቦታ ለማስገባት { }
ወይም የመረጥነው ቃል በዚህ ዉስጥ { } ለማስገባት
CTRL + SHIFT + F9 ሊንክ የነበረውን ሊንኩ
ለማጥፋት
📍 F10
አክቲቭ የሆነውን ዊንዶው ሜኑ ባርን አክቲቭ ለማድረግ
ያስችላል፡፡ Shift + F10 መጨን # ራይት ክሊክ
እንደማድረግ ይቆጠራል፡፡
📍 F11
በአብዛኛዎ ብርውሰሮች ላይ F10 ስንጫን
የምንመለከተው መስኮት ሙሉ በሙሉ የኮምውተራችንን
ስክሪን ይሞላዋል # (Fullscreen) ፡፡
📍 F12
ማይክሮሶፍት ወርድ ላይ # የ Save as ማስኮትን
ይከፍትልናል፡፡ Ctrl + Shift + F12 ፐሪንት ያዛል፡፡

🌐 ዘመኑ #የቴክኖሎጂ ነው 📲 ከዘመኑ ጋር አብረው ይዘምኑ💻

Telegram: t.me/BasicComputer_Skills

tiktok.com/@basiccomputerskills

Umma Life: ummalife.com/ReshadMuzemil
╚═══📌Share📌════
የቢዝነስ ፕላን (እቅድ) ዝግጅት
የቢዝነስ ፕላን (እቅድ) ምን ማለት ነው?
ማንኛውም አንተርፕራይዝ ሊተገብር ያሰበው የንግድ ስራ ግብና ዓላማ ምን እንደሆነ፣ የስራው ሂደት ምን
እንደሚመስልና እንዴት እንደሚሠራ እንዲሁም እያንዳንዱ ክንውን መቼ እንደሚሰራ የሚያስረዳ ዶኩመንት (ሰነድ) ነው፡፡
የታለመውን ግብ ለመምታት የሚያስችል የአሰራር መመሪያን የያዘ ነው፡፡
የኢንተርፕራይዙን የቢዝነስ /የንግድ ስራ አሰራር ፍኖተ ካርታ ያሳያል፡፡
የኢንተርፕራይዙን የቢዝነስ/የንግድ ስራ ያለውን እድል ለገንዘብ ተቋማትና ባለሀብቶች ሊያስረዳ የሚችል ሰነድ ነው፡፡
የኢንተርፕራይዙን የቢዝነስ/የንግድ ስራ ሊኖረው የሚችለውን ማንኛውንም እድል /ሁኔታ በመዘርዝር የሚታቀድበት በቂ ቅድመ ዝግጅት የሚደረግበት ነው፡፡

የቢዝነስ / የንግድ ስራ ፕላን (እቅድ) ለምን ይዘጋጃል?

የቢዝነስ / የንግድ ስራ ፕላን (እቅድ) በተዘጋጀው ግብና ዓላማ ላይ ትኩረት / አጽንኦት በመስጠት ስራን ለማከናወን ይረዳል፡፡
የገንዘብ አቅምን ከተለያየ ምንጭ ለማግኘት ይረዳል፡፡
ቢዝነሱ/የንግድ ስራው የሚጀመርበትንና ሊመራበት የሚገባውን ስርዓት በማሳየት አቅጣጫ ጠቋሚ ይሆናል፡፡
በተነደፈው የቢዝነስ /የንግድ ስራ ዘርፍ ለመሰማራት ፍላጎት ካላቸው አጋር ድርጅቶች ጋር ግንኙነት ለመፍጠር
ይረዳል፡፡
የተነደፈው የቢዝነስ /የንግድ ስራ የስኬት እድል ያለው መሆኑን ለማሳየት ይጠቅማል፡፡
በኢንተርፕራይዙ ውስጥ ቢዝነሱን /የንግድ ስራውን ለማስተዳደር የሚያስፈልገው በቂ ችሎታ እንዳለ መኖሩንና ለሚመረተው ምርትና አገልግሎት የገበያ እድል መኖሩን ለማረጋገጥ ይጠቅማል፡፡
ስራው ከተጀመረ በኃላ በጊዜ ሂደት ውስጥ በእቅድ ደረጃ የተቀመጠውን ውጤት በተግባር ከሚሆነው ጋር ለማወዳደር የቢዝነስ / የንግድ ስራ ፕላን (እቅድ) እንዴት ይዘጋጃል?
በቢዝነስ / በንግድ ስራ ውስጥ የሚጠየቁ ማንኛውንም ጥያቄዎች በመዘርዘርና ለጥያቄዎቹ መልስ በመስጠት
ከተጠየቁት / ሊጠየቁ ከሚችሉት ጥያቄዎች መካከል ምላሽ ለመስጠት ተጨማሪ መረጃ በማሰባሰብ
አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎችን በሙሉ በማሰባሰብ
የተለያዩ አማራጮችን በማወዳደርና የተሻለውን አማራጭ ለመውሰድ በመወሰን።

በቢዝነስ ፕላን (እቅድ) ምን ሊደረግ ይችላል?

የቢዝነስ/ የንግድ ስራ ፕላን (እቅድ) አስቀድሞ ማዘጋጀት ለክትትል ይረዳል፡፡ ይህም ማለት በእቅድ የተያዘውን ስራ ከተከናወነው ስራ ጋር በማነጻጸር ለመገምገም ይጠቅማል፡፡
ከገንዘብ ተቋማት እንዲሁም ፍላጎት ካላቸው አጋር ድርጅቶች ጋር ለሚደረግ ውይይት የመነሻ ሃሳብ ይሆናል፡፡

የቢዝነስ / የንግድ ስራ እቅድ ለጅምላ ንግድ፣ ለችርቻሮ ንግድ፣ አገልግሎት የሚሰጥ የንግድ ድርጀት፣ ምርት
የሚያመርት (አምራች) ድርጅት፣ ማንኛውም የንግድ ድርጅት፣ ለገንዘብ ተቋማትና ለንግድ ዘርፍ ባለቤቶችና ስራ አስኪያጆች ሊዘጋጅ ይችላል፡፡

የቢዝነስ ፕላን (እቅድ) ገጽታ ምን ይመስላል?
የተተየበና በጥራዝ የተቀመጠ፣ በንጽህና የተጠበቀ/የተያዘ፣ ማጠቃለያና እዝል ያለው (ዋናውን እቅድ ላለማስረዘም ማለት ነው)፣ እያንዳንዱ ገጽ የገጽ ቁጥር የተሰጠው፣ በሚመለከተው አባል የተፈረመ መሆን የተገባው ሲሆን የቢዝነስ እቅድ መድብል ብዙ ወይም ጥቂት መሆን የሚወሰነው እንደ ንግዱ የዘርፍ ዓይነት ነው፡፡

የቢዝነስ / የንግድ ስራ ፕላን (እቅድ) ማንን ያካትታል?

የንግድ ዘርፉ ተጠቃሚ የሆኑ ደንበኞችን፣ በዘርፉ የሚሰሩ ተወዳዳሪ ግለሰቦችና ድርጅቶች፣ አቅራቢዎች፣ ተቀጣሪዎች፣ ለገበያ የሚቀርቡ ምርቶች፣ የንግድ ስራው የሚካሄድበት ስፍራ ወይም አድራሻ፣ ለንግዱ ስራ የሚያስፈልገው ቁሳቁስ. ወዘተ
(ከአማራ ክልል የቴክኒክና ሙያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ቢሮ የተገኘ)
ሙሉ ቢዝነስ ፕላን PDF ማግኘት ከፈለጉ ከታች ያለውን ቢዝነስ ፕላን የሚለውን ይጠቀሙ።

©️©️©️

🌐 ዘመኑ #የቴክኖሎጂ ነው 📲 ከዘመኑ ጋር አብረው ይዘምኑ💻

Telegram: t.me/BasicComputer_Skills

tiktok.com/@basiccomputerskills

Umma Life: ummalife.com/ReshadMuzemil
╚═══📌Share📌════
Small Business Entrepreneurship Ideas_V1.0_281019140824.apk
3.1 MB
Small Business Plan Idea

Android Phone Application
የእቅድ form.pdf
643.9 KB
ቢዝነስ ፕላን Business Plan Form
1
የ4 ገፅ የቢዝነስ ፕላን.pdf
355.1 KB
የቢዝነስ ፕላን/ 4 Pages Business Plan
በ4 ገፅ የቢዝነስ ፕላን እንዴት ማዘጋጀት ይቻላል?፦ በቀላሉ ሁሉንም መስፈርት ባሟላ መልኩ የቢዝነስ ፕላን እንዴት ማዘጋጀት እንደሚቻል በምሳሌ በ100ሺ ብር የሚሰራ የምርጥ ቡና ቢዝነስ ፕላን በአማርኛ አዘጋጅቻለሁ እስከመጨረሻው ተመልከቱት፤ ናሙናውን በመጠቀም ወደ የምትፈልጉት ቢዝነስ አይነት መለወጥ እንዲሁም ለሌሎች ማጋራት ትችላላችሁ።

የቢዝነስ ፕላን/ 4 Pages Business Plan
በ4 ገፅ የቢዝነስ ፕላን እንዴት ማዘጋጀት ይቻላል

©️©️©️

🌐 ዘመኑ #የቴክኖሎጂ ነው 📲 ከዘመኑ ጋር አብረው ይዘምኑ💻

Telegram: t.me/BasicComputer_Skills

tiktok.com/@basiccomputerskills

Umma Life: ummalife.com/ReshadMuzemil
╚═══📌Share📌════
👍2