Basic Computer Skills
1.87K subscribers
1.22K photos
100 videos
576 files
833 links
#በዚህ የቴሌግራም ቻናል
↪️ Programming
↪️ ቴክኖሎጂ ነክ ትምህርቶችን
↪️ ኮምፒውተር ነክ ትምህርቶችን
↪️Basic Computer Skills
↪️ Software
↪️ AI and AI Skills (Like ChatGPT)

ከላይ የተዘረዘሩትና ሌሎችም ገራሚ ትምህርቶች ይለቀቅበታል!

t.me/BasicComputerSkillsGroup

𝘽𝙮 𝙍𝙚𝙨𝙝𝙖𝙙
Download Telegram
🇵🇸 ለእናንተ እና ለቤተሰባችሁ በፍቅር፣ በሳቅ እና በበረከት የተሞላ የደስታ ኢድ እንዲሆን እመኛለሁ። ...

ይህ ኢድ ለቤታችሁ ሰላም ፣ ደስታ እና ብልጽግና ያድርግላችሁ። ...

በዚህ መልካም አጋጣሚ አላህ በእናንተና በቤተሰቦቻችሁ ላይ መለኮታዊ ፀጋውን እንዲያወርድ እማፀነዋለሁ። ...

🇵🇸 ኢድ ሙባረክ!

🇵🇸 ይድረስ ለወንድም እህቶቼ (ለተማሪዎቼ) እና ለቤተሰቦቻቸው!

በረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል
✳️ ኢንተርኔትን በብርሃን ጨረሮች ተደራሽ የማድረግ ሙከራ❗️

🔺የሌዘር ጨረር ሥርዓት ላይ በመመስረት ኢንተርኔትን ተደራሽ የማድረግ ሙከራ በስኬት መከናወኑ ተገለፀ፤ ሙከራው የተከናወነው የኮንጎ ወንዝ በሚያካፍላቸው ብራዛቪል እና ኪንሻሳ ከተሞች መካከል መሆኑን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

🔺ኤክስ በተባለው የአልፋቤት የምርምር ተቋም ለሶስት ዓመታት ሲበለፅግ የቆየው አዲስ ሥርዓት ለአይን የማይታዩ የብርሃን ጨረሮችን በመጠቀም ፈጣን ኢንተርኔትን ተደራሽ ማድረግ መቻሉ ታውቋል፡፡

🔺በዚህ ገመድ አልባ የግንኙነት መንገድ 99.9 በመቶ አስተማማኝነት 7 መቶ ቴራባይት የሚጠጋ ዳታ በ20 ቀናት ውስጥ ማቅረብ እንደተቻለ ተገልጿል፡፡

🔺የኮንጎ ወንዝ ቆርጦ በሚያልፋቸው ሁለቱ ከተሞች መካከል ገመድን መሰረት ያደረገ ፈጣን የብሮድባንድ ኢንተርኔት ለማቅረብ ቢሞከር አምስት እጥፍ ውድ እንደሚሆን ተዘግቧል፡፡

🔺ፍሪ ስፔስ ኦፕቲካል ኮምዩኒኬሽንስ የሚል መጠሪያ በተሰጠው በዚህ ቴክኖሎጂ በቀጣይ ከሰሐራ በታች ያሉ ሀገራትን የፈጣን ኢንተርኔት ተጠቃሚ ለማድረግ ኩባንያው ማቀዱ ተነግሯል፡፡
🇵🇸 ለ6ኛ እና ለ8ኛ ክፍል ተፈታኝ  ተማሪዎች አጭር ማስታወሻ!

የ8ኛ ክፍል

👉 ሞዴል ሚያዚያ 15-18/8/2016 ዓ.ል  ሲሰጥ  ክልል አቀፍ ፈተና (Ministry Exam)  ከሰኔ 4-5/10/2016 ዓ.ል ይሰጣል።

6ኛ ክፍል

👉 ሞዴል ፈተና ከሚያዚያ 15-18/8/2016 ዓ.ል  የሚሰጥ ሲሆን ክልል አቀፍ   ፈተና ከሰኔ  12-14/10/2016 ዓ.ል የሚሰጥ ይሆናል!!



➞ ከተማሪዎች ምን ይጠበቃል⁉️

👉 የ6ኛ ክፍል ተማሪዎች የ6ኛ ክፍል ብቻ (5ኛ ክፍል ሳይጨምር) የሁለቱን ሴሚስተር እቅድ አውጥቶ  በአግባቡ ማጥናት።

👉 የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች የ8ኛ ክፍል ብቻ (7ኛ ክፍል ሳይጨምር) የሁለቱን ሴሚስተር እቅድ አውጥቶ በአግባቡ ማጥናት።

⭕️ ከመምህራንና ከት/ቤቶች ምን ይጠበቃል?

◆ መምህራና እና ት/ቤቶች አስፈላጊውን ትኩረት በመስጠት የይዘት የማጠናቀቅ ምጣኔ (portion coverage ) በአግባቡ እንዲጠናቀቅ ማድረግ።

👉 ለተፈታኝ ተማሪዎቻችን የስነ ልብና ምክርና አስፈላጊው እገዛ (ወርክሽት፣ ሞዴል ፈተናዎች እና ያለፋ አመታት ፈተናዎችን በማሰራት)  እገዛ ማድረግ።

⭕️ ከተማሪ ወላጆች ምን ይጠበቃል??

👉 ተማሪዎች እቅድ አውጥተው እንዲያጠኑ ማበረታታት እና አስፈላጊውን እገዛ ማድረግ::


🔚 በጋራ ርብርብ የተማሪዎችን ውጤት እና ስነ ምግባር መልካምና አስደሳች እንዲሆን ሁላችንም ጥረት እናድርግ‼️ (ኢንሻአላህ)

🀄🀄ሉን👇👇👇 share👇

t.me/AndalusGrade7and8

t.me/AcademicEducations

t.me/BasicComputer_Skills
✳️ የምልክት ቋንቋን ወደ ድምፅ ተርጓሚው የጆሮ ማዳመጫ❗️

🔺በኒውዮርክ የሚገኘው ቡፋሎ ዪኒቨርሲቲ የተመራማሪዎች ቡድን የጆሮ ማዳመጫን ከስማርት ስልክ ጋር በማገናኘት የምልክት ቋንቋን ወደ ድምፅ መተርጎም ወደሚችል መሣሪያ መቀየራቸው ተነገረ፡፡

🔺መሣሪያው ዶፕለር የተባለውን ቴክኖሎጂ ጥቅም ላይ በመዋል የድምጽ ሞገድን በመልቀቅ የምልክት ቋንቋን ከሚያሳየው ሰው እጅ ላይ ነጥረው የሚመጡ የድምፅ ሞገዶችን ቅርፅ መተርጎም ማስቻሉን ተገልጿል፡፡

🔺ሶኒክኤ.ኤስ.ኤል በሚል ስያሜ በተጠራው በዚህ መሳሪያ ለጊዜው የአሜሪካን የምልክት ቋንቋ ተጠቅሞ በቤት ውስጥ በተደረገ ሙከራ 93.8 በመቶ ውጤታማ መሆን መቻሉ ተዘግቧል፡፡

🔺መሣሪያው መስማት በተሳናቸው እና በሌሎች ሰዎች መካከል የሚደረግ ተግባቦትን በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚያቃልል የተመራማሪዎቹ እምነት ነው፡፡

🌐 ዘመኑ #የቴክኖሎጂ ነው 📲 ከዘመኑ ጋር አብረው ይዘምኑ💻

Telegram: t.me/BasicComputer_Skills

tiktok.com/@basiccomputerskills

Umma Life: ummalife.com/ReshadMuzemil
╚═══📌Share📌════
የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት የቡና ቅጠል በሸታን የሚለይ መተግበሪያ እያበለፀገ መሆኑን ገለፀ

የቡና ቅጠል ምስልን በመጠቀም ብቻ የቡና ቅጠል በሸታን ለመለየት፣ የጉዳት መጠንን ለማወቅ የሚያስችል ኮፊኔት የተሰኘ መተግበሪያ እያበለፀገ መሆኑን የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት አስታወቀ።

የሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ ውጤት ነው የተባለው ይህ መተግበሪያ ከሰው ሰራሽ አስተውሎት የምርምር መስክ በሆነው ኮምፒውተር ቪዥን መበልፀጉ ተሰምቷል። ቴክኖሎጂው ሶስት የቡና ቅጠል በሽታዎችን መለየት ይችላልም ነው የተባለው።

ምንጭ: Tikvaheth Magazine

🌐 ዘመኑ #የቴክኖሎጂ ነው 📲 ከዘመኑ ጋር አብረው ይዘምኑ💻

Telegram: t.me/BasicComputer_Skills

tiktok.com/@basiccomputerskills

Umma Life: ummalife.com/ReshadMuzemil
╚═══📌Share📌════
✳️ ደምብ አስከባሪው ሮቦት በሲንጋፖር ጎዳኖች❗️

🔺በሲንጋፖር የእግረኛ እንቅስቃሴ በሚበዛበት አካባቢ ሥርዓተ አልበኝነትን እየተዘዋወረ የሚቆጣጠር ዣቪየር የተባለ ሮቦት ወደ ስራ ገብቷል።

🔺ሮቦቱ በጎዳናዎች እየተዘዋወረ ከአምስት በላይ የሆኑ የሰዎች ስብስብን፣ ባልተፈቀደ አካባቢ ሲጋራ ማጨስ፣ ሕገ-ወጥ የጎዳና ላይ ንግድ ፣ያለአግባብ የቆሙ ብስክሌቶችን እና በእግረኛ መንገድ ሕገ-ወጥ የባለ ሞተር ተሸከርካሪ እንቅስቃሴዎችን ይቆጣጠራል፡፡

🔺እርስዎም ከላይ ከተጠቀሱት አንዱን ፈፅመው ቢገኙ ሮቦቱ በቀጥታ የቪዲዮ ስርጭቱ ወደ ማዕከላዊ የመቆጣጠሪያ ጣቢያው ሁኔታውን ያሳውቃል፡፡ ለተላለፉት ደንብም አግባብ የሆነውን የማስጠንቀቂያ መልዕክት በተገጠመለት ስክሪን እና ድምጽ ማጉያ ያስተላልፋል፡፡
#Tech_News #Robotics
Basic LOGO commands
👍1
Loop and Double Loops
MSW-LOGO practice
✳️ኤርባስ A380 ሱፐርጃምቦ የምግብ ማብሰያ ዘይትን እንደ ነዳጅ ተጠቅሞ በረራ ያደረገው አውሮፕላን❗️

🔺የዓለማችን ግዙፉ አውሮፕላን “ኤርባስ A380 ሱፐርጁምቦ” በፈረንሳይ ቱሉዝ እና ኒስ ከተሞች መካከል የምግብ ማብሰያ ዘይትን እንደ ነዳጅ በመጠቀም የተሳካ የሶስት ሰዓት በረራ ማድረጉ ተገለፀ።

🔺ኤርባስ A380 ሱፐርጁምቦ አውሮፕላን መቶ በመቶ የምግብ ማብሰያ ዘይት ዘላቂነት ያለው የአቪዬሽን ነዳጅ በረራ ሲያደርግ የመጀመሪያ ነው የተባለ ሲሆን፤ ሌሎች የኤርባስ ስሪት አውሮፕላኖች ግን ባሳለፍነው ዓመት 3 የተሳካ በረራ አድርገዋል።

🔺የካርበን ልቀትን በ80 በመቶ ይቀንሳል ተብሎ የሚጠበቀው አዲሱ የምግብ ዘይት ነዳጅ፤ ጥቅም ላይ ከዋለ የምግብ ዘይት፣ ከስብ እንዲሁም ለምግብነት ከማይውሉ ሰብሎች የሚሰራ ነው ተብሏል።

🔺ዓለም አቀፍ የአየር ትራንስፖርት ማህበር (IATA) ዘላቂነት ያለው የአቪዬሽን ነዳጅ የተባለው ዘይት የካርበን ልቀትን በመቀነስ ረገድ 65 በመቶ ሚና ይኖረዋል ብሏል። በአየር ትራንስፖርት ዘርፍ በ2050 የካርበን ልቀትን ወደ ዜሮ ለማምጣት የተያዘውን እቅድ ለማሳካት እንደሚረዳም ማህበሩ አስታውቋል።

🔺እንደ ኤርባስ ገለጻ በአሁኑ ወቅት ሁሉም አውሮፕላኖቹ እስከ 50 በመቶ የሚሆነውን ዘላቂነት ያለው የአቪዬሽን ነዳጅ ማለትም መደበኛውን ነዳጅ ከኬሮሲን ጋር ቀላቅለው ለመብረር የሚያስችላቸው የምስክር ወረቀት አግኝተዋል።
#Tech_News #Airplane
👍4
✳️የ TikTok እገዳ በኪርጊስታን ተግባራዊ ሆነ❗️

🔺ኪርጊስታን ቲክቶክ በመላ ሀገሪቱ  እንዲታገድ ውሳኔ ማስለፏ ይታወሳል በዚሁ ውሳኔ መሰረት የቴሌኮም አገልግሎት የሚሰጡ ድርጅቶች ትዕዛዙን ወደ መፈጸም እርምጃ ገብተዋል።

🔺በሀገሪቱ " ቲክቶክ " መስራት እንዳቆመም ተነግሯል፤ ሰዎች መተግበሪያውን ሲከፍቱን የሚያገኙት መልዕክት "Unable to load, please try again" የሚል ነው።

🔺ውሳኔው በሀገሪቱ ብሔራዊ ደህንነት ም/ቤት የተላለፈ ነው፤ የኪርጊስታን ዲጂታል ሚኒስቴር ቲክቶክን የሚያስተዳድረው "ባይት ዳንስ" ኩባንያ የልጆችን፦
- አእምሯዊ፣
- አካላዊ፣
- መንፈሳዊ እና ሥነምግባራዊ እድገትን ለመጠበቅ በህግ የተዘረዘሩ ህጋዊ መስፈርቶችን ማክበር አልቻለም ብሏል።

🔺በዚህም ምክንያት ቲክቶክ በሀገሪቱ እንዳይሰራ ተደርጓል። ውሳኔው የተቃወሙ አካላት ይህ ተገቢ እንዳልሆነ በመግለጽ ገደቡ እንዲነሳ ጠይቀዋል። ከገደብ ይልቅ ቁጥጥር ይደረግበት ብለዋል።

©TikvahEth
#Tech_News

🌐 ዘመኑ #የቴክኖሎጂ ነው 📲 ከዘመኑ ጋር አብረው ይዘምኑ💻

Telegram: t.me/BasicComputer_Skills

tiktok.com/@basiccomputerskills

Umma Life: ummalife.com/ReshadMuzemil
╚═══📌Share📌════
የተሻለ ውጤት የሚያመጡ  ተማሪዎች የአጠናን ልምዳቸው ምን ይመስላል

📢 12 ወሳኝ ነጥቦች

📖➊ ጥናት ከመጀመራቸው በፊት ለምን ዓላማ እንደሚያጠኑ ቀድመው ዓላማ ያስቀምጣሉ።
ይህ ማለት ምን ለማወቅ እንደሚያጠኑ ቀድመው ያቅዳሉ።

📖❷ መፅኃፍ ገልጠው ጥናት ከመጀመራቸው በፊት ስለሚያጠኑት ርዕሰ ጉዳይ የራሳቸውን ግምት ያስቀምጣሉ። መፅሀፍ ገልጠው ጥናት ከጀመሩ በኃላ የነበራቸውን ግምት እያጠናከሩ...የተሳሳተውን እያስተካከሉ ይጓዛሉ።

📖➌ ሲያጠኑ ያገኙትን አንኳር ነጥብ አጠር አድርገው ማስታወሻቸው ላይ ያሰፍራሉ።

📖➍ አንብበው ለመረዳት ያስቸገራቸውን ነጥብ /ሀሳብ/ ደጋግመው ያነባሉ....

📖➎ ጥናት ከመጀመራቸው በፊት ማጥናት ስለ ፈለጉት ርእሰ ጉዳይ ጥያቄዎች ይፋጥራሉ። መፅኃፍ ገልጠው ጥናት ከጀመሩ በኋላ ለጥያቄዎቻቸው መልስ ይፈልጋሉ እንጂ ሁሉም ነገር በማንበብ ጊዜያቼውን አያጠፉም።

📖❻ ሲያነቡ ያገኙትን አዲስ ሀሳብ ወይም መረጃ ከ አሁን በፊት ከሚያወቁት ጋር አብሮ ሊሄድ የሚችል መሆኑን እና አለመሆኑን ይመረምራሉ::

📖❼ በአንድ ጊዜ ብዙ ነገር ለማጥናት አይሞክሩም፡፡ በአንድ ጊዜ ብዙ ነገር ለማጥናት መሞከር ትርፉ ድካም መሆኑን ተረድተውታል፡፡

📖❽ ሁልጊዜም ቢሆን ለትምህርት ጉዳዮች የሚጠቀሙበት የተለየ ጊዜ አላቸው፡፡

📖❾ ያሰቡትን ነገር ተግባራዊ ለማድረግ ቁርጠኝነት አላቸው...አያፈገፍጉም፣ አያቅማሙም፡፡

📖❿ ሲያጠኑ የሚከብዳቸውን ክፍል ቅድሚያ ሰጥተው ያነባሉ፡፡

📖⓫ ተባብሮ በመስራት ያምናሉ፡፡ ያግዛሉ፣ ይጠይቃሉ፡፡

📖⓬ እራሳቸው ይገመግማሉ፡፡ ደካማ ጎናቸዉ በፍጥነት ያስተካክላሉ፡፡


join us 👇👇👇

Join🔻
══════════════
🀄🀄ሉን👇👇👇 share👇

t.me/AndalusGrade7and8

t.me/AcademicEducations

t.me/BasicComputer_Skills

t.me/AndalusGrade5and6
👍4🤔1
❇️ የሞባይል ስልክን #operating System አፕዴት የማድረግ ጠቀሜታው
===========================

በፊት ከነበረው ሶፍትዌር በተጨማሪ #አዳዲስ ሶፍትዌሮችና መገልገያዋችን ያመጣል

ሞባይሉ አንዳንድ የሶፍትዌር ችግሮች ካሉበት 'አፕዴት' አድርጎ ሲጨርስ የነበሩበትን ችግሮች #ያስተካክለዋል

ሞባይሉ በፊት ከነበረው ይዘት በተለያዪ ነገሮች ለውጥን ያመጣል

⚠️ ማስጠንቀቂያ
▣ ሞባይል ስልክ 'አፕዴት' ከማድረጋችን በፊት ሊደረጉ የሚገባቸው ጥንቃቄዋች👇
➠ ሞባይሉ ትክክለኛ(Original ) መሆኑን ማረጋገጥ
➠ ሞባይሉ Root ያልተደረገ መሆን ይኖርበታል
➠ ሞባይሉ አፕዴት እያደረገ ባትሪ መነቀል የለበትም
➠ ባትሪ ከ50% በላይ ቻርጅ ሊኖረው ይገባል
በተጨማሪም ሞባይሉን እራሳችን አፕዴት ማድረግ ከፈለግን ጥሩ ፍጥነት ያለው
(WiFi internet ብንጠቀም ጥሩ ነው)

✳️ ሞባይሉ በ WiFi internet አፕዴት ለማድረግ👇👇
1. ከ WiFi internet ማገናኘት
2. Settings የሚለውን መክፈት
3. ወደ ታች በመውረድ About መንካት
4. Check for Updates መንካት
5. Update
በዳታ አፕዴት ማድረግ ብዙ ብር ይበላል።ስለዚህ በWiFi update አድርጉ።


#መረጃዎችን ላላወቁት እንዲደርሳቸው በማጋራት (Share በማድረግ) ተባበሩን↘️

🌐 ዘመኑ #የቴክኖሎጂ ነው 📲 ከዘመኑ ጋር አብረው ይዘምኑ💻

Telegram: t.me/BasicComputer_Skills

tiktok.com/@basiccomputerskills

Umma Life: ummalife.com/ReshadMuzemil
╚═══📌Share📌════
👍2
ህልማችን የማይሳካ የሚመስላቸው አሉ.....

በቀ እየመሰላቸው ይኑሩ❗️

▬▭▬▬▭▬▬▭▭▬▬▭▭▬
⭕️ ትውልድን ❝ትክክለኛው መንገድ ይህ ነው በዚህ መንገድ ሂዱ ማለት ብቻ ሳይሆን፤ ለትክክለኛው መንገድ (ለስኬት) ማዘጋጀትም ተገቢ ነው ባይ ነኝ❞ !

▬▭▬▬▭▬▬▭▭▬▬▭▭▬

Join🔻
══════════════
🀄🀄ሉን👇👇👇 share👇

t.me/AndalusGrade7and8

t.me/AcademicEducations

t.me/BasicComputer_Skills

t.me/AndalusGrade5and6
📝📝📝📝
✍️✍️✍️✍️
የአለማችን ትልቁ 3D ፕሪንተር ሙሉ የመኖሪያ ቤት በራሱ ፕሪንት ማድረጉ ተገለፀ።
በአሜሪካ ሜን ዩኒቨርስቲ ዉስጥ የተሰራው ይህ ፕሪንተር ከውስጡ በሚወጣ ቴርም ፕላስቲክ ፖሊመር አማካኝነት ግዙፍ ቤቶችን የመስራት አቅም አለው ተብሏል።
ቴክኖሎጂው በዚህ ከቀጠለ በቅርብ አመታት ጊዜ ውስጥ ሙሉ በሙሉ በማሽን ፕሪንት የተደረገ የመኖሪያ መንደር ማየታችን አይቀሬ ይመስላል።

የዜና ምንጭ፡ AP

#መረጃዎችን ላላወቁት እንዲደርሳቸው በማጋራት (Share በማድረግ) ተባበሩን↘️

🌐 ዘመኑ #የቴክኖሎጂ ነው 📲 ከዘመኑ ጋር አብረው ይዘምኑ💻

Telegram: t.me/BasicComputer_Skills

tiktok.com/@basiccomputerskills

Umma Life: ummalife.com/ReshadMuzemil
╚═══📌Share📌════
💢ስልካችንን📲 እንዴት ከሌላ ስልክ ላይ ቻርጅ ማድረግ እንችላለን?

#አስፈላጊ ነገሮች⬇️⬇️⬇️

ሌላኛው ስልክ
OTG
data cable

1⃣. አሰራር፦ ኬብሉን #OTG ላይ ይሰኩና በቀላሉ #OTG ያለበትን ጫፍ ቻርጅ ሰጪው ስልክ📲 ላይ ይሰኩት።

2⃣. ሌላኛውን ጫፍ ቻርጅ ማድረግ የሚፈልጉት ስልክ ላይ ይሰኩት።

አለቀ፤ ዳይ ወደ ዘረፋ


#መረጃዎችን ላላወቁት እንዲደርሳቸው በማጋራት (Share በማድረግ) ተባበሩን↘️

🌐 ዘመኑ #የቴክኖሎጂ ነው 📲 ከዘመኑ ጋር አብረው ይዘምኑ💻

Telegram: t.me/BasicComputer_Skills

tiktok.com/@basiccomputerskills

Umma Life: ummalife.com/ReshadMuzemil
╚═══📌Share📌════