Basic Computer Skills
1.87K subscribers
1.22K photos
100 videos
576 files
833 links
#በዚህ የቴሌግራም ቻናል
↪️ Programming
↪️ ቴክኖሎጂ ነክ ትምህርቶችን
↪️ ኮምፒውተር ነክ ትምህርቶችን
↪️Basic Computer Skills
↪️ Software
↪️ AI and AI Skills (Like ChatGPT)

ከላይ የተዘረዘሩትና ሌሎችም ገራሚ ትምህርቶች ይለቀቅበታል!

t.me/BasicComputerSkillsGroup

𝘽𝙮 𝙍𝙚𝙨𝙝𝙖𝙙
Download Telegram
የሞባይል ባትሪን እድሜ ለማስረዘም እነዚህን 5 ነጥቦች ይተግብሩ

1 👉 Original ( ትክክለኛ ) ሳይሆኑ ለገንዘብ ተብለው በርካሽ ዋጋ ለገበያ የሚቀርቡ ኦርጅናል ያልሆኑ ቻርጀሮች ዋጋቸው ሪካሽ ብሆንም ጥራታቸው ዝቅተኛ በመሆናቸው ቻርጅ በምናደርግበት ጊዜ ለሞባይል ባትሪው ያልተመጣጠነ የኤሌትሪክ ሀይል በመስጠት ይጎደዋል ወይም የሞባይሉን ባትሪ እድሜ ያሳጥራል፡፡
2 👉 ሞባይላችንን ቻርጅ እያደረግን አለመጠቀም
ሞባይል ስልኮች ቻርጅ በሚደረጉበት ጊዜ ስልክ መደወል፣ ጌም መጫወት፣ ኢንተርኔት መጠቀም የባትሪውን እድሜ ከማሳጠሩ ባለፈ ለተጠቃሚዎቹ አደጋ ሊያስከትል ይችላል በተጨማሪም ሞባይላችንን ራሱ ሊፈነዳብን ይችላል።
3 👉 ሞባይሎቻችንን ቻርጅ ሰክቶ አለማሳደር ( ሌሊቱን ሙሉ ቻርጅ አለማድረግ ) ሌሊቱን ሙሉ ቻርጅ ማድረግ አንዱ ባትሪን ከሚገድሉ ችግሮች መካከል አንዱ ነው፡፡ ባትሪው ከምሽት ጀምሮ ሌሊት ሙሉ ቻርጅ ሲያደርግ 100 ፐርሰንት መሙላቱ የማይቀር ሲሆን ከሞላ በኋላ የኤሌክትሪክ ፓወሩ ባትሪውን መደብደቡ የማይቀር ነው፡፡
የሞላ ነገር ሁሉ መፍሰሱ እንደማይቀር ሁሉ ሞልቶ የሚፈስ ነገር ደግሞ እቃው ላይ ጉዳት ያስከትላል፤ በተመሳሳይ ሁኔታ ተሰክቶ ያደረ ባትሪ ከአቅሙ በላይ ስራ ይበዛበታል፡፡
4 👉 ሞባይል ስልክን አልፎ አልፎ ማጥፋት ሞባይል ስልክን አለማጥፋት ሌላው የባትሪን እድሜ ከሚቀንሱ ውስጥ አንዱ ሲሆን ሞባይል ስልኮች እንደማንኛውም ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች እና ማሽን እረፍት ያስፈልጋቸዋል፡፡ ቢቻል በምሽት ወደ መኝታ ስንሄድ አልፎ አልፎ ስልኮቻችንን ብናጠፋ ይመከራል፡፡ ብዙዎቻችን የሞባይል ስልካችን በስራ ላይ የሚመስለን ስንደውል፣
ሲደወልልን፣ አንዳንድ ነገሮችን በስልኮቻችን ስንጠቀም ብቻ ባትሪ የሚጠቀም ይመስለናል፤ ሆኖም ግን የባትሪው የመጠቀም መጠን ይለያያል እንጂ ሞባይሉ ሲከፈት በላዩ ላይ ያሉት ክፍት የተደረጉ ሰርቪሶች ማለትም ብሉቱዝ፣ጂፒኤስ፣ ዳታ ወዘተ ባትሪውን ይጠቀማሉ፡፡
5 👉 ባትሪው 0% እስኪሆን ድረስ አለመጠበቅ 0% እስክሆን ጠብቀን ቻርጅ ማድረግ ይህም የባትሪውን እድሜ የሚያሳጥሩት አንዱ ነው ባትሪው ግማሽ ወይም ሩብ ሲቀረው ቻርጅ ብናደርግ የተሻለ የባሪውን እድሜ ይጨምርልናል።

Like Share Follow Invite በማድረግ ለሌሎች ያድርሱ !!

🌐ዘመኑ #የቴክኖሎጂ ነው 📲 ከዘመኑ ጋር አብረው ይዘምኑ💻

Telegram: t.me/BasicComputer_Skills

tiktok.com/@basiccomputerskills

instagram.com/basiccomputerskills

Umma Life: ummalife.com/ReshadMuzemil
╚═══📌Share📌════
👍4
Cup_Cut_Photo_Music_Video_Editor_and_Maker_Vidos_v2_34_326_Premium.apk
59.4 MB
⚡️ለtiktok ለYoutube. የሚሆኑ ቪድዮዎችን በስልካቹ Edit ለማድረግ ይጠቅማል።

#Android_Phone_App
① Motherboard


❖ Motherboard የኮምፒውተር ክፍል ዋናው የኤሌክትሪክ ሰርኪዩት ሰሉዳ ሲሆን ተለቅ ያለ እና ዋና የኮምፒውተር ክፍል ነው፡፡
ሁሉም የኮምፒውተር ክፍሎች ከ Motherboard ጋር በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ የተገናኙ ሲሆን ይህም በመሰረታዊነት የኮምፒውተሩ ክፍሎች እርስ በርስ መረጃ እና ትዕዛዞችን እንዲለዋወጡ ያስችላል፡፡

❖ ካለ Motherboard ኮምፒውተር የማይታሰብ ነው፡፡ ለምሳሌ፡- የኮምፒውተሩ ኤሌክትሪክ አቅራቢ(Power Supply) ለሲዲ ማንበቢያው (CD drive) የኤሌክትሪክ ሃይል መስጠት ካልቻለ ሲዲ ማንበቢያው መስራት አይችልም፡፡
②Central Processing Unit (CPU)


❖ CPU የኮምፒውተሩ ማዕከላዊ ማቀነባበሪያ ክፍል ሲሆን ማቀናበሪያ(processor) አልያም የኮምፒውተር አዕምሮ ሌላኛው መታወቂያ ስሞቹ ናቸው፡፡

❖ CPU ከተጠቃሚ ወደ ኮምፒውተሩ የሚገቡትን ትዕዛዞች በሙሉ በመቀበል ኮምፒውተሩ በአግባቡ ትዕዛዙን እንዲከውን የሚያደርገው በ motherboard ላይ የሚገኝ ትንሽ የኤሌክትሮኒክ ቺፕ ነው፡፡

❖የማቀናበር ሃይል(processing power) የኮምፒውተርን ፍጥነት ግልፅ በሆነ መልኩ ይጨምራል፡፡
ስለሆነም ፈጣን ማቀነባበሪያ ኮምፒውተሮችን ፈጣን ያደርጋቸዋል፡፡
③ Random Access Memory (RAM)


❖RAM ማሕደረ-ትውስታ የኮምፒውተሩ ጊዜያዊ መረጃዎችን አልያም ስሌቶችን የሚያኖርበት እና በሚያስፈልግ ጊዜ(ኮምፒውተሩን ከማጥፋታችን አልያም ዳግም ከማስነሳታችን በፊት) መረጃዎችን ወይንም ስሌቶችን የሚሰጠን ነው፡፡

❖RAM ከ CPU ጋር በመተባበር ዳታዎች በተሳካ ሁኔታ የሚያቀነባብር ወሳኝ የኮምፒውተር ክፍል ነው፡፡

❖የRAM መጠን በመጨመር የኮምፒውተሮችን የማህደረ-ትውስታ በማስፋት የማቀነባበር አቅሙን ማሻሻል ይችላል
④Hard Drive


❖Hard drive ለኮምፒውተሮች እንደ ትልቅ ቤተ-መፀሃፍት ነው፡፡ ምክኒያቱም ፋይሎችን፤ሙዚቃዎችን፤ምስሎችን፤ሰነዶችን፤ ወዘተ ለዘለቄታው የምናኖርበት ሁነኛ ክፍል ነው፡፡

❖Hard drive በግል ከምናኖራቸው መረጃዎች ባለፈ የኮምፒውተሩ አሰራር ሂደት(operating system) የሚጫንበት እና በአግባቡ ኮምፒውተሩ ለተጠቃሚዎች አገልግሎት ምቹ የሚያደርጉትን የአሰራር ሂደት ፋይሎች(operating system files) የሚቀመጡበት የኮምፒውተር ክፍል ነው፡፡
1
⑤Power Supply Unit


❖Power supply unit የኮምፒውተሩ የሃይል አቅርቦት ክፍል ሲሆን ከግርግዳ ወይንም ከኤሌክትሪክ ማከፋፈያ የሚቀበለውን ኤሌክትሪክ ለኮምፒውተሩ በሚመጥን የኤሌክትሪክ መጠን እና አቅርቦት ለክቶ እና መጥኖ ወደ ኮምፒውተሩ ክፍሎች የሚያዳርስ የኮምፒውተር ቁልፍ ክፍል ነው፡፡

🇪🇹 #ግዴላችሁም_ማወቅ_መልካም_ነው!!
 

🌐ዘመኑ #የቴክኖሎጂ ነው 📲 ከዘመኑ ጋር አብረው ይዘምኑ💻

Telegram: t.me/BasicComputer_Skills

tiktok.com/@basiccomputerskills

instagram.com/basiccomputerskills

Umma Life: ummalife.com/ReshadMuzemil
Information about system unit.
🇵🇸 አዲስ Smart ሞባይል ስልክ ሲገዙ ማገናዘብ የሚገባዎ 10 ነገሮች ከምሳሌ ጋር

🇵🇸 መግዛት ያሰቡት smart ሞባይል ስልክ iPhone ወይም Samsung ወይም ሌላ ሊሆን ይችላል። ማንኛውም smart ሞባይል ስልክ ሲገዙ ስልኩ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን 6 መመዘኛዎች  ማሟላቱን ማረጋገጥ ያስፈልጋል። 🇵🇸

➊ ፕሮሰሰር(Processor)
       ብዙ ግዜ ጌም የሚጫወቱ ከሆነ፣ቪድዮ የሚያዩ ከሆነ ወይም የቪድዮ ኤዲቲንግ የሚሰሩ ከሆነ የስልኩ ፕሮሰሰር Qualcom Snapdragon(652/820/821) ቢሆን ይመረጣል።ለመካከለኛ ተጠቃሚ ፕሮሰሰሩ MedaTek ከሆነ በቂ ነው።
❷ ካሜራ
   ፎቶ የማንሳት ልምድ ያለው ሰው የስልኩ ካሜራ 13mp(Megapixels) በላይ መሆኑን ማረጋገጥ ያስፈልጋል።ለመካከለኛ ተጠቃሚ ግን 8mp በቂ ነው።

➌ ባትሪ
  ብዙ ሰዓት ቪድዮ ለሚያይ፣ጌም ለሚጫወት ሰው ባትሪው 3500mAh(Miliamp Hour) በላይ መሆኑን ማረጋገጥ ያስፈልጋል። ለመካከለኛ ተጠቃሚ 3000mAh በቂ ነው።

➍ ኦፐሬቲንግ ሲስተም(OS)
የተለያዩ ኦፐሬቲንግ ሲስተም(OS) ቨርዥኖች አሉ።ለምሳሌ samsung galaxy ስልኮች ኪትካት፣ሎሊፓፕ፣ማርሽሜሎ...ወዘተ የተባሉ ቨርዥኖች አሉ። ስለዚህ latest ቨርዥን መምረጥ ይመከራል።

➎ Storage
      ስልኩ በቂ የማጠራቀሚያ አቅም ቢኖረው ይመረጣል። 16GB/32GB/64GB..ከነዚህ ውስጥ መምረጥ ነው። ስልኩ ኤክስተርናል ሜሞሪ(microSD card) የሚቀበል መሆን አለበት።

❻ Headphone Jack
  HeadPhone 3.5mm audio
jack ቢሆን ይመረጣል።

❼ RAM ከተቻለ ከ4GB በላይ ቢሆን ጥሩ ነው ነገርግን ለመካከለኛ ተጠቃሚ 2GB በቂ ነው

❽ USB File transfer  USB 2.0 በአሁኑ ጊዜ ያለ ስለሆነ ይህ ፖርት ያለው ቢሆ ይነረጣል , USB 3.0 ቢሆን ጥሩ ነው።

❾ Physical Size በኢንች ለናንተ የሚቸውንም መምረጥ አለባችሁ በተለይ ለአያያዝ ምቹ መሆኑን አረጋግጡ።

❿ የሚቀበለው የሲም ካርድ አይነት መለየት።
ምሳሌ ከታች ያለውን Specification ተመልከቱ።
Dimensions: 75.8 x 164 x 8.9 mm
Weight : 205 g
SoC: MediaTek Helio P35 (MT6765)
CPU : 4x 2.3 GHz ARM Cortex-A53, 4x 1.8 GHz ARM Cortex-A53, Cores : 8
GPU : PowerVR GE8320, 680 MHz
RAM : 3 GB, 4 GB, 6 GB
Storage : 32 GB, 64 GB, 128 GB
Memory cards : microSD, microSDHC, microSDXC
Display : 6.5 in, TFT, 720 x 1560 pixels, 24 bit
Battery : 5000 mAh, Li-Ion
OS: Android 10
Camera : 8000 x 6000 pixels, 1920 x 1080 pixels, 30 fps
SIM card : Nano-SIM
Wi-Fi : a, b, g, n, n 5GHz, ac, Dual band, Wi-Fi Hotspot, Wi-Fi Direct
USB: 2.0, Micro USB
Bluetooth: 5.0
Positioning: GPS, A-GPS, GLONASS, BeiDou

🌐ዘመኑ #የቴክኖሎጂ ነው 📲 ከዘመኑ ጋር አብረው ይዘምኑ💻

Telegram: t.me/BasicComputer_Skills

tiktok.com/@basiccomputerskills

instagram.com/basiccomputerskills

Umma Life: ummalife.com/ReshadMuzemil
👍3
የሰዎች ሙገሳ አይጠቅምህም፣ ወቀሳቸውም አይጎዳህም።

People's praise will not help you, and their criticism will not hurt you.

ummalife.com/ReshadMuzemil
👍3
📱ስማርት ስልክ ባትሪ ለረጅም ሰዓት አገልግሎት

🇵🇸 Background process ሚያደርጉ አፖችን ማስቆም
🇵🇸 የማትጠቀሙባቸውን Apps Uninstalled ማድረግ Apps በበዛ ቁጥር ባትሪ የመጠቀም አቅም ስለሚጨምር።
🇵🇸 ስልካችሁን በማይግልበት መልኩ ይጠቀሙ።
🇵🇸 የስልኩን Back cover በማውለቅ ይጠቀሙ።
🇵🇸 የያልኩ Internal Storage and SD Memory full  ማለት የለበትም።
🇵🇸 ቪዲዮ ሲመለከቱ Brightness ይቀንሱ።
🇵🇸 ባትሪዎን በጣም የሚጠቀሙ አፕ ማወቅ እና እገዳ መጣል ወይም እንዳይሰሩ ማድረግ

👉 🔧Setting-battery
🇵🇸 Facebook E-mile, Instagram, Twitter, You tube... ከፍተው አለመተው
🇵🇸 Bluetooth, WiFi, GPS... በተርታ ክፍት ሲቀመጡ ስልክዎ ሁሌም Searching process ሲለሚጫወት ባትሪዎን ይጨርስቦታል
🇵🇸 ስልክዎን በማይጠቀሙበት ወቅት Ultra Power Save 🔐Øn ማድረግ ስልክዎ ከመደወል እና ሜሴጅ ከመቀበል ሌላ ስራ አይኖረውም ሰለዚህ ባትሪዎን ለረጅም ሰዓት ይጠቀማሉ።

🇵🇸 Animation app አይጠቀሙ
🇵🇸 Screensaver ጥቁር ነገሮችን መጠቀም
🇵🇸 Night mode መጠቀም ለምሳሌ የፌስቡክ፣ የቴሌግራም ወደ Night mode መቀየር
🇵🇸 የስልክዎ Brightness በዝቅተኛው ደረጃ🔅ማድረግ

➞ Setting 🔄Manage 🔄apps  🔄Process ማይገለገሉትን አፕ Force #stop ማድረግ።

🇵🇸 ስልካችሁን በማይጠቀሙበት ሰአት Lock ያድርጉት
🇵🇸 የስልካችሁን Auto Lock ዝቅተኛውን ያድርጉ።
🇵🇸 ስልክዎ ላይ 24ሰዓት ሙጭጭ አይበሉ
🇵🇸 ስልክዎን Power off በማድረግ ይቻርጁት።
🇵🇸 ቢያንስ በ24 ሰአታት ውስጥ ለ1 ሰአት Off ቢደረግ ይመረጣል ወይም 1 ግዜ off አድርጎ እንደገና ማስነሳት።

⬆️ እነዚህ ተግባራዊ ያድርጉ!

ለተጨማሪ መረጃ፦

➞ እኛን ይቀላቀሉ።

🌐ዘመኑ #የቴክኖሎጂ ነው 📲 ከዘመኑ ጋር አብረው ይዘምኑ💻

Telegram: t.me/BasicComputer_Skills

tiktok.com/@basiccomputerskills

instagram.com/basiccomputerskills

Umma Life: ummalife.com/ReshadMuzemil
👍21
ICT 2nd Sem.pdf
301.4 KB
Grade 7 and 8 ICT worksheet

Unit 4: Internet

2016 E.C Academic Year
CTE and ICT 2nd Semester Test One-signed.pdf
3.5 MB
Grade 7 and 8

ICT Test

Unit 4: Internet

In addition

CTE test
MSW-LOGO.pdf
1.1 MB
MSW LOGO short description for Grade 7th-8th Students and Teachers

🌐ዘመኑ #የቴክኖሎጂ ነው 📲 ከዘመኑ ጋር አብረው ይዘምኑ💻

Telegram: t.me/BasicComputer_Skills

tiktok.com/@basiccomputerskills

instagram.com/basiccomputerskills

Umma Life: ummalife.com/ReshadMuzemil
╚═══📌Share📌════
✳️ቫይረሶች ወደ ኮምፒውተሮች እንዴት ነው የሚገቡት?

🔰 በዚህ የቴክኖሎጅ ዘመን ኮምፒውተራችን አልያም ስማርት ስልኮቻችን ሁነኛ የመረጃ ማግኛ እና መዝናኛ ከሆኑ ሰነባብተዋል።

✴️ ይሁን እንጂ የሰዎችን መረጃ አላስፈላጊ በሆነ መልኩ ለመጠቀም ብሎም መረጃ እና ንብረትን ወደ ግል ለማዞር የሚሞክሩ ሰዎች ስጋት ከሆኑም ቆይተዋል።

✴️ ቫይረሶች በማወቅም ይሁን ባለማወቅ ወደ ኮምፒውተራችን ሲገቡ ሙሉ በሙሉ አልያም በከፊል ከጥቅም ውጭ ሊያደርገው ይችላል፤
የተለያዩ ጠቃሚ መረጃዎቻችንም ለሌሎች አሳልፈው የመስጠት እድልም አላቸው።

✴️ እናም በተቻለ መጠን ቫይረሶች ወደ ኮምፒውተራችን ገብተው ጉዳት እንዳያደርሱብን ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል።

🔰ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ነጥቦችም የኮምፒውተር ቫይረሶች ወደ ኮምፒውተሮች የሚገቡበትን መንገድ ያስገነዝባሉ።

✴️ የማንቂያ መልዕክቶችን (ኖቲፊኬሽን) ሳናነብ መቀበል
ቫይረስ ወደ ኮምፒውተራችን ከሚገባባቸው መንገዶች ዋነኛው የማንቂያ መልዕክቶችን ሳንረዳ መክፈት ነው።
♻️ለምሳሌ፦♻️
✴️ 1. በኢንተርኔት መረጃዎችን ስናፈላልግ a unique plugin is necessary is required የሚል ማስታወቂያ ሲመጣ ምንም አይነት የደህንነት ስጋት ይኑረው አይኑረው ሳናውቅ እንዲከፍትልት የሚያዘንን ቅደም ተከተል መከተል፤

✴️ 2. በነፃ የሚለቀቁ ፕሮግራሞችን ከጫንን በኋላ በተደጋጋሚ እንድንጭናቸው የምንጠየቀውንና እያንዳንዱን የኢንተርኔት እንቅስቃሴያችንን ለመረጃ በርባሪዎች አሳልፈው የሚሰጡ ፕሮግራሞችን ማውረድ
የተበከለ ሶፍትዌር መጫን
ከኢንተርኔት
የምናወርዳቸው ነገሮች ከታማኝ ምንጮች የተገኙ መሆናቸውን ማረጋገጥ ይኖርብናል።

✴️ ካወረድን በኋላ ወደ ኮምፒውተራቸን ስንጭን (install ስናደርግም አንቲቫይረስ ሶስትዌር ሊኖረን ይገባል።

✴️ ላኪያቸው የማይታወቁ የኢሜል መልዕክቶችን መክፈት
ማንኛውንም ላኪያቸውን የማናውቃቸውን የኢሜል መልዕክቶች ከመክፈታችን በፊት በኦንላይን አንቲቫይረስ ሶፍትዌሮች ስካን ማድረግ ይኖርብናል።

✴️ በኢሜል መልዕክቶች አማካኝነት የተለያዩ ቫይረሶች ስለሚላኩ ጥንቃቄ ማድረግ ተገቢ ነው።

✴️ የተበከሉ ውጫዊ ስቶሬጅ መሳሪያዎች (ሚሞሪ፣ ፍላሽ ዲስክ፣ ሀርድ ዲስክ ወዘተ ኮምፒውተራችን ላይ መሰካትም ሌላኛው ቫይረስ ወደ ኮምፒውተራችን የሚገባበት መንገድ ነው።

✴️ የኮምፒውተር ሶፍትዌሮችን በየጊዜው አለማሳደግ አፕዴት አለማድረግ ችግር ላይ እንደሚጥል ይታመናል።

🌐ዘመኑ #የቴክኖሎጂ ነው 📲 ከዘመኑ ጋር አብረው ይዘምኑ💻

Telegram: t.me/BasicComputer_Skills

tiktok.com/@basiccomputerskills

instagram.com/basiccomputerskills

Umma Life: ummalife.com/ReshadMuzemil
╚═══📌Share📌════
1