Basic Computer Skills
1.87K subscribers
1.22K photos
100 videos
576 files
833 links
#በዚህ የቴሌግራም ቻናል
↪️ Programming
↪️ ቴክኖሎጂ ነክ ትምህርቶችን
↪️ ኮምፒውተር ነክ ትምህርቶችን
↪️Basic Computer Skills
↪️ Software
↪️ AI and AI Skills (Like ChatGPT)

ከላይ የተዘረዘሩትና ሌሎችም ገራሚ ትምህርቶች ይለቀቅበታል!

t.me/BasicComputerSkillsGroup

𝘽𝙮 𝙍𝙚𝙨𝙝𝙖𝙙
Download Telegram
📲 የሞባይል ስልክ ቀፏችን ሀክ(Hack) ከተደረገ የሚከተሉት ምልክቶች ያሳያል

📌 1ኛ የማታውቋቸው አፕሊኬሽኖች ስልካችሁ ላይ ዳውንሎድ ተደርጎ ካያችሁ፡-

📲 የስልክ ቀፏችን ሀክ(Hack) እንደተደረገ ለማረጋገጥ አንደኛው መንገድ ስልካችሁ ላይ እናንተ የማታቋቸው ወይም ያልጫናችኋቸው አፕሊኬሽኖች ስልካችሁ ላይ ካገኛችሁ ስልክ ቀፎዋችሁ ተጠልፏል ማለት ነው፡፡

📌 ይህን ቼክ ለማድረግ ስልካችሁ ላይ Settings > Apps > App Manager ግቡና ካሉት አፕሊኬሽን ዝርዝሮች ውስጥ እናንተ ያልጫናችሁት አፕሊኬሽን ፈልጉ፡፡ የማታውቁት ወይም ያልጫናችሁት አፕሊኬሽን ተጭኖ ካገኛችሁ ስልክ ቀፎዋችሁ ተጠልፋዋል ማለት ነው፡፡

#መፍትሄ፡- እንደ ተጠቀሰው አይነት አፕሊኬሽን ስታገኙ አፕሊኬሽኑ ላይ ክሊክ አድርጉና Uninstall ብላችሁ ከስልካችሁ አስወጡ፡፡

📌 2ኛ፡- ኢንተርኔት ስትጠቀሙ ከመጠን በላይ ብር የሚበላ ከሆነ፡-

📲 እንደ ዩተዩብ ፤ ፌስቡክ የመሳሰሉ አፕሊኬሽኖች ከሌሎች ሲነፃፀር ከፍ ያለ ብር ይበላሉ፡፡ ነገር ግን ከነዚህ አፕሊኬሽኖች ውጪ ሌላ አፕሊኬሽን ከፍተኛ ገንዘብ የሚበላ ከሆነና ይህንን አፕሊኬሽን የማትጠቀሙበት ከሆነ ስልካችሁ ተጠልፋል ማለት ነው፡፡

ይህንን ለማረጋገጥ Settings > Connections & WiFi > Data Usage ግቡና አጠራጣሪ ዳታ የሚጠቀም አፕሊኬሽን ስታገኙ Uninstall ብላችሁ ከስልካችሁ አስወጡ፡፡

📌 3ኛ፡- ስልካችሁ በጣም በፍጥነት ባትሪ የሚጨርስ ከሆነ፡-

📲 ስልካችሁ በፍጥነት ወይም ከሚጠበቀው በታች ባትሪ የሚጨርስ ከሆነ ችግር አለ ማለት ነው፡፡

Settings > Battery > Battery Usage ግቡና አላግባብ ባትሪ የሚበላ አፕሊኬሽን ካለና ያ አፕሊኬሽን አዘውትራችሁ የማትጠቀሙበት ከሆነ አፕሊኬሽኑን Uninstall ብላችሁ ከስልካችሁ አስወጡ።

#ከቴክኖሎጂ_ማህደር

t.me/TechnologyMasterPage
✴️ ኮምፒውተራችን እንዴት በቀላሉ ከፕሪንተር ጋር ማስተዋወቅ እንችላለን

🔆 ኮምፒውተራችንን ከፕሪንተር ጋር ለማስተዋወቅ የሚጠቅሙ ብዙ ሶፍትዌሮች እንዳሉ ይታወቃል እንዲሁም ተመሳሳይ  wifi በመጠቀምም በዋየርለስ ወይም ያለ ኬብል ፕሪንተራችንን ከኮምፒውተራችን ጋርም ማስተዋወቅ እንችላለን።
🔆 እኔ ግን ዛሬ ይዤላችሁ የቀረብኩት ያለምንም wifi እና software ኮምፒውተራችንን ከፕሪንተር ጋር እንዴት ማስተዋወቅ እንደምንችል ነው።
🔆 ኮምፒውተራችንን እንዴት ከፕሪንተራችን ጋር ማስተዋወቅ እንችላለን።
1⃣ control panel ውስጥ በመግባት device printer እንመርጣለን ወይም start ን በመንካት search box ላይ device and printer ብለን እንፅፋለን።
ኮምፒውተራችንን ከፕሪንተር ጋር ማያያዙን እንዳንረሳ።
2⃣ በመቀጠል add printerን  እንመርጣለን ።search እስኪጨርስ እንጠብቃለን።
3⃣ add alocal printer የሚለውን መርጠን next እንለዋለን።
4⃣ በመቀጠል ፕሪንተራችንን ያያዝነው በኬብ ስለሆነ ከሚመጣልን ምርጫ የመጀመሪያውን USB portን እንመርጣለን።next እንለዋለን
5⃣ አሁን ከሚመጡልን ዝርዝሮች ውስጥ የፕሪንተራችንን ስም በመፈለግ መርጠን next ቀጥሎም next እንለዋለን።
6⃣ በመጨረሻም print a test page የሚል ይመጣልናል click አርገን test እናደርግና finish ብለን እንጨርሳለን።

ለወዳጆ ያጋሩ

#ከቴክኖሎጂ_ማህደር!


t.me/BasicComputer_Skills
Page_Number_እንዴት_ነው_የምንሰራው_በአማርኛ_የቀረበ_#Amharic360p.mp4
10.8 MB
#ለProposal'ችን ወይም ለሪሰርቻችን Page Number እንዴት ማስገባት እንችላለን?

#ይህን የሚያሳይ ቪድዮ ነዎ

#አዘጋጅ:- ሙሐመድ ኮምፒውተር (የዩቲዩብ)

#MB size: 10.8MB


#ሰውን ሳትለምኑ ቪድዮውን አይታችሁ ብቻ Page Number ማስገባት ትችላላችሁ!

#ሞክራችሁት_የሚያስግራችሁ_ነገር_ከተፈጠረ እኔን በውስጥ መስመር ማናገር ትችላላችሁ!👇👇

@ReshadMuzemil

#Reshad_Muzemil
ለማስተርስና_ለዲግሪ_ተመራቂ_ተማሪዎች_Automatic_Reference,_Citation,_List_of_Table.mp4
66.1 MB
ይህ ቪድዮ ደግሞ

#ለProposal'ችን ወይም ለሪሰርቻችን

Automatic በሆነ መንገድ
●Reference
● List of table
● List of Figures
እንዴት ማስገባት እንችላለን?

#ይህን የሚያሳይ ቪድዮ ነው!

#አዘጋጅ:- ሙሐመድ ኮምፒውተር (የዩቲዩብ)

#MB size: 66.1MB


#ሰውን ሳትለምኑ ቪድዮውን አይታችሁ ብቻ List of table and List of Figures ማስገባት ትችላላችሁ!

#ሞክራችሁት_የሚያስግራችሁ_ነገር_ከተፈጠረ እኔን በውስጥ መስመር ማናገር ትችላላችሁ!👇👇

@ReshadMuzemil

#Reshad_Muzemil
Basic Computer Skills Exercise. Test Yourself-signed.pdf
502.6 KB
#Title:- Basic Computer Skills Exercise

#MB_size:- 502.6KB

#Format:- Colour PDF

#Page:- 3 Pages

#Prepared_by:- Reshad Muzemil


t.me/TechnologyMasterPage
Week 4:
Lesson 1:

#How to Connected Computer Parts with the CPU?

#Step_by_Step
#The End!
Week 4

Lesson 2: #Painting
Window and Hard Disk
Week 5:

#Lesson 5: Parts of the CPU
👇👇👇👇👇👇
① Motherboard


❖ Motherboard የኮምፒውተር ክፍል ዋናው የኤሌክትሪክ ሰርኪዩት ሰሉዳ ሲሆን ተለቅ ያለ እና ዋና የኮምፒውተር ክፍል ነው፡፡
ሁሉም የኮምፒውተር ክፍሎች ከ Motherboard ጋር በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ የተገናኙ ሲሆን ይህም በመሰረታዊነት የኮምፒውተሩ ክፍሎች እርስ በርስ መረጃ እና ትዕዛዞችን እንዲለዋወጡ ያስችላል፡፡

❖ ካለ Motherboard ኮምፒውተር የማይታሰብ ነው፡፡ ለምሳሌ፡- የኮምፒውተሩ ኤሌክትሪክ አቅራቢ(Power Supply) ለሲዲ ማንበቢያው (CD drive) የኤሌክትሪክ ሃይል መስጠት ካልቻለ ሲዲ ማንበቢያው መስራት አይችልም፡፡
②Central Processing Unit (CPU)


❖ CPU የኮምፒውተሩ ማዕከላዊ ማቀነባበሪያ ክፍል ሲሆን ማቀናበሪያ(processor) አልያም የኮምፒውተር አዕምሮ ሌላኛው መታወቂያ ስሞቹ ናቸው፡፡

❖ CPU ከተጠቃሚ ወደ ኮምፒውተሩ የሚገቡትን ትዕዛዞች በሙሉ በመቀበል ኮምፒውተሩ በአግባቡ ትዕዛዙን እንዲከውን የሚያደርገው በ motherboard ላይ የሚገኝ ትንሽ የኤሌክትሮኒክ ቺፕ ነው፡፡

❖የማቀናበር ሃይል(processing power) የኮምፒውተርን ፍጥነት ግልፅ በሆነ መልኩ ይጨምራል፡፡
ስለሆነም ፈጣን ማቀነባበሪያ ኮምፒውተሮችን ፈጣን ያደርጋቸዋል፡፡
③ Random Access Memory (RAM)


❖RAM ማሕደረ-ትውስታ የኮምፒውተሩ ጊዜያዊ መረጃዎችን አልያም ስሌቶችን የሚያኖርበት እና በሚያስፈልግ ጊዜ(ኮምፒውተሩን ከማጥፋታችን አልያም ዳግም ከማስነሳታችን በፊት) መረጃዎችን ወይንም ስሌቶችን የሚሰጠን ነው፡፡

❖RAM ከ CPU ጋር በመተባበር ዳታዎች በተሳካ ሁኔታ የሚያቀነባብር ወሳኝ የኮምፒውተር ክፍል ነው፡፡

❖የRAM መጠን በመጨመር የኮምፒውተሮችን የማህደረ-ትውስታ በማስፋት የማቀነባበር አቅሙን ማሻሻል ይችላል