Basic Computer Skills
1.88K subscribers
1.22K photos
100 videos
576 files
833 links
#በዚህ የቴሌግራም ቻናል
↪️ Programming
↪️ ቴክኖሎጂ ነክ ትምህርቶችን
↪️ ኮምፒውተር ነክ ትምህርቶችን
↪️Basic Computer Skills
↪️ Software
↪️ AI and AI Skills (Like ChatGPT)

ከላይ የተዘረዘሩትና ሌሎችም ገራሚ ትምህርቶች ይለቀቅበታል!

t.me/BasicComputerSkillsGroup

𝘽𝙮 𝙍𝙚𝙨𝙝𝙖𝙙
Download Telegram
⭕️ What are the three tasks that the control unit performs?

To store program instructions.
To perform logic functions. 
To decode program instructions.

So,

4. Control unit performs Logic Operation.

The answer is True
🏆1
Grade 7th CTE-signed.pdf
32.6 MB
Grade 7th CTE Short Ppt (Updated)

▲ From Unit 1 through Unit 8 (Full)

● Prepared by: Reshad Muzemil
🏆5👍1💯1
Grade 8th CTE-signed.pdf
23.5 MB
Grade 8th CTE Short Ppt (Updated)

▲ From Unit 1 through Unit 7 (Full)

● Prepared by: Reshad Muzemil
🏆31
🏆2
Basic Computer Skills
GRADE 7 SOCIAL STUDIES (EDITTED).pdf
👆ይሀው አንደሉሶች የጠየቃችሁኝ መፅሐፍ (Grade 8th Students)
🏆2
List of Irregular Verbs

Source: English-hilfen.de

ብልጥ ለሆናችሁ ተማሪዎች ብቻ‼️
🏆3
Irregular Verbs

Source: Grade 8 English book

ብልጥ ለሆናችሁ ተማሪዎች ብቻ!
3
Basic Computer Skills pinned «👆ይሀው አንደሉሶች የጠየቃችሁኝ መፅሐፍ (Grade 8th Students)»
አሰላሙ አለይኩም ወረህመቱሏሂ ወበረካቱ

ወድ የ Technology Master Page አባሎቻችን እንደምን ናችሁ⁉️ ቻናሉ እየጠቀማችሁ ነውን? (ትምህርት እየቀሰማችሁበት ነውን!?)

● ቻናሉ ላይ እንዲለቀቅላችሁ የምትፈልጉት ነገር ካለ፣
● ቴክኖሎጂ ነክ ነገሮችን ማብራሪያ አዘል ትምህርቶችን በቪድዮ እንዲሰራላችሁ የምትፈልጉት ነገር ካለ

● እንዲለቀቅላችሁ የምትፈልጉት Application Software (both Android and Computer) ካለ፣

እና ሌሎችንም ነገሮች በ Comment ልትፅፉልኝ (ልትጠይቁኝ) ትችላላችሁ። የቻልኩትን ያህል በአላህ እገዛ አግዛችኋለሁ‼️

t.me/TechnologyMasterPage

t.me/TechnologyMasterPages
1
በዝምታህ አወዛግባቸው...
በተግባርህ አስደምማቸው!!

Confuse them with your silence...
Amaze them with your actions!!

ummalife.com/ReshadMuzemil
⭕️ // ከትዝብቴ ማህደር //

🔰 ሀላፊነት

/// *« አስተዋይ አእምሮ ላላቸው ብቻ »* ///

ሀላፊነት ማለት በጥንቃቄ ካልተራመድንበት በሚደረመስ ሃዲድ ላይ እንዳለን ነው።

ልብ በሉ እዚህ-ጋር ሃዲዱ ቢደረመስ በሰዓቱ ቁልቁል የምንወረወረው እኛ ብቻ ነን። ሃላፊነት ግን ከዚህ ይለያል... ሃላፊነታችንን በአግባቡ የማንወጣ ከሆነ፣ ያለንን ስልጣን (ሃላፊነት/አደራ) በአግባቡ ማንጠቀምበት ከሆንና ክብራችንን ለማስጠበቅ የምንገለገልበት ከሆነ ወደ ቁልቁል የምንወረወረው እኛ ብቻ ሳይሆን በስራችንም ያሉትን ይዘን ነው። በሉ እንደውም ከኛ በፊት ቀድመን የምናወድማቸው (በጉርጓድ የምንከታቸው) በስራችን ያሉትን ሰዎችን ነው‼️

በስራችን ያሉ ሰዎች የሚችሉትን ያህል ጥረት ካደረጉና የሚችሉትን ያህል ከሰ፤ ... ለምን « እኔ የምፈልገውን ያህል አልሰራችሁም!? » ብሎ ጋጋታ መፍጠር አግባብ አይደለም!! ይህ የፈጠርነው ጋጋታ በስራችን ያሉ ሰዎችን ያቆስልብናል፣ ሞራላቸውን ይጎዳብናል ምናልባት መጀመሪያ የነበራቸው ጥንካሬ ተሸርሽሮ ስንፍናን ባህሪያቸው እንዲያደርጉ ያደርግብናል።

● ከዚህ በፊት ይጥሩ የነበረውን ጥረት ሊያቆሙብን ይችላሉ፣
● ከዚህ በፊት የነበረው ጉብዝናቸው ሊናድ ይችላል፣... ስለዚህ እኛ ስልጣኑ አለን የምንል ሰዎች ጥንቃቄ ልናደገርግ ይገባናል። ሰዎችን ያለአግባብ ማስጨነቅ አላህም አይወድልንም!!

ሁሉም የራሱ እምነት እንዲሁም አስተሳሰብ አለው ነገር ግን የትኛውም እምነት ሆነ አስተሳሰብ ሰዎች ከአቅማቸው በላይ መስራት አለባቸው አይልም፤ ቢል ራሱ አግባብ አይደለም!

➤ እኛ የምንጨነቀው ለሰዎቹ ሞራል ደስታና ስኬት ሳይሆን ለኛ ክብር ከሆነ፤ እኛ የማንጠቅም እርባና-ቢሶች ነን ማለት ነው‼️

➤ እኛ ትግላችን በስራችን ያሉ ሰዎች የሚችሉትን ያህል እንዲሰሩ ሳይሆን እኛ የምንፈልገውን ያህል ብቻ እንዲሰሩ የምናዛቸው ከሆነ፤ የሰጧንን ባህሪ የተላበስን ቆሻሾች ነን ማለት ነው‼️

〽️ ቆይ ከቅማቸው በላይ ኬት አምጥተው ይስሩ!?
የሆነ ነገር እንዲሰሩን የፈለግን እንደሆነ እኛም « ይህን የሰጠናችሁን ስራ በዚህ መልክ ከሰራችሁ ትጨርሱታላችሁ ወይም ጥሩ አድርጋችሁ ትሰሩታላችሁ» የሚል ቀመር ልናስቀምጥላቸው ግድ ይለናል‼️ በዚህ ባስቀመጥንላቸው ቀመር ራሱ ሁሉም እኩል አይሰራም ሊሰራም አይችልም። ይሄኔም ጋጋታ ከመፍጠር ይልቅ መፍትሄ ለማበጀት መሞከርና የሰጠናቸውን ስራ በአግባቡ አልሰሩም ያልናቸውን «ቆይ ግን የአቅማቸውን ያህል ሰርተዋል ወይስ አልሰሩም» የሚለውን መለየት ይኖርብናል! ...

ያአቅማቸውን ያህል ካልሰሩና ካፌዙ (ካሾፉ) ያኔ ጋጋታ ብንፈጥርም ያምርብናል‼️

⭕️ ስልጣን አለን በሚል በወረደና በዘቀጠ አስተሳሰብ ሰዎችን ያለአግባብ ልንጎዳ፣ ሞራላቸውን ልንነካ፣ ክብራቸውን ልናጎድፍ አይገባንም መብቱም የለንም‼️
⭕️ እኛን «እረፉ የፈጠራችሁን ፍሩ» የሚለን የለንም ማለት በስራችን ያሉ ሰዎችን እንዳሻን እንጫወትባቸው ማለት አይደለም። ህሊና የሚባል ነገር አለ‼️

ፈጣሪያችንን ልንፈራ ይገባል። በተለይ አዋዋላችን ከልጆች፣ ከህፃኖችና ከተማሪዎች የሆንን ሰዎች ቆም ብለን ልናስብ ይገባናል። ለክብራችን መጨነቅ ትተን በስራችን ላሉት (ለተማሪዎች) ስኬትና ውጤት ልንጨነቅ ይገባናል። ተማሪዎቻችን የአቅማቸውን፣ የሚችሉትን ያህል ከሰሩ ለምን «እኔ የምፈልገውን ያህል አልሰራችሁም» በሚል በዘቀጠ ሀሳብ እነሱን ልንጎዳቸው አይገባንም መብቱም የለንም።

አዎ እሩፉ የሚለን ላይኖር ይችላል፤ ያው ሁሉም እኔ «ምንናገባኝ» ስለሚል ማለቴ ነው። ነገር ግን ህሊናስ የለንም⁉️ እምነታችንስ ምንድነው የሚያዘን...⁉️ ይህን ጥያቄ ለራሳችን ደጋግመን እንጠይቀው!

😭 እናተ *ያለአቅማችሁ ለምን አልሰራችሁም* ተብላችሁ የተገፋችሁ ሆይ አብሽሩ አላህ ከናተ ጋር ነው። አብሽሩ ይህ ጊዜ ያልፍና ነገ በአላህ ፍቃድ ትልቅ ቦታ ትደርሳላችሁ‼️ ...........🔰 ኢንሻአላህ!!

እናተ ለምን «እኔ የምፈልገውን ያህል አልሰራችሁም» ብላችሁ በስሮቻቹ ያሉትን ክብር የምትነኩ ሆይ.....
እናተ የምትጨነቁት ለራሳችሁ ክብር እንጂ ለሌሎቹ ስኬት አይደለም። ለሌሎቹ ስኬት፣ ደስታና ተድላ ሳይሆን ለራሱ ክብር ብቻ የሚጨነቅ ደግሞ እሱ የሰጧንን ባህሪ የተላበሰ የሰው ሰጧን ነው‼️ እናም እናተ የሰው ሰይጧኖች ሆይ አምላካችሁን ፍሩ‼️

▬▬▬▬▬▬▬
⭕️ መልዕክቴ አስተዋይ አእምሮ ላላቸው ይድረስልኝ‼️
▬▬▬▬▬▬▬

በረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል

ቀን: ህዳር 17/2016 አ.ል

Join:-

YouTube.com/@SecretsofTruth

tiktok.com/@secretsof_truth

Instagram.com/secretsof_truth

t.me/Secretsof_Truth

Fb.com/SecretsofTruth1

https://ummalife.com/ReshadMuzemil

t.me/ReshadMuzemil