Basic Computer Skills
1.87K subscribers
1.22K photos
100 videos
576 files
833 links
#በዚህ የቴሌግራም ቻናል
↪️ Programming
↪️ ቴክኖሎጂ ነክ ትምህርቶችን
↪️ ኮምፒውተር ነክ ትምህርቶችን
↪️Basic Computer Skills
↪️ Software
↪️ AI and AI Skills (Like ChatGPT)

ከላይ የተዘረዘሩትና ሌሎችም ገራሚ ትምህርቶች ይለቀቅበታል!

t.me/BasicComputerSkillsGroup

𝘽𝙮 𝙍𝙚𝙨𝙝𝙖𝙙
Download Telegram
LOGO Commands

Programming concepts
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በቴሌግራም በጉሩፓችን ወይም በቻናላችን አባሎች Poll'ን በመጠቀም የተለያዩ ጥያቄዎችን እንዴት እናዘጋጃለን ለሚለው ለአንድ ወንድሜ የተሰራ ቪድዮ‼️

#Quiz_Bot
#Poll_Questions

By Reshad Muzemil

tiktok.com/@techmasterpage

YouTube.com/@TechnologyMasterPage
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
‍ ‌➨ ቴሌግራም ቻናል ከፍተው በቻናላችሁ ያሉ አባሎች መልዕክት እንዲቀበሉ ይፈልጋሉን?

➧እኖግዲያውስ የሚከተሉትን Steps በቅደም ተከተል ተግባራዊ ያድርጉ
@BotFather ይህን በቴሌግራም search ማረጊያ ይፈልጉ
@BotFather የሚለው ሲመጣ ይጫኑት
❸/Start ይበሉ
@BotFather ሚሴጅ ሲልክላችሁ /New bot የሚለውን ይጫኑ
❺ለBot የፈለጋችሁትን ስም አስገቡ
❻ /Set picture (ፕሮፋይል እንዲኖረው ከፈለጋችሁ)
❼ /Set description(ስለ ቦታችሁ አገልግሎት ገለፃ መፃፍ ከፈለጋችሁ)



➨ከላይ የከፈታችሁትስ አዲስ ቦት መልዕክት አልቀበል አላችሁ?

▩አድስ ቦት ከፍተው መልዕክት አልቀበልለዎት ካለ እነዚህን ስቴፖች ይከተሉ።
Δ▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂Δ

ቪድዮው ከላይ አለላችሁ!

http://tiktok.com/@techmasterpage
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ወደሌላ ቦት ጋር ማገናኘት ለምሳሌ
ወደ @LimitatiBot ጋ ወይም @livegrambot ጋ ማገናኘት።

ወደ @livegrambot ለማገናኘት በዚህ መልኩ በቀላሉ ማስተካከል ይችላሉ።

⇓⇓
በመጀመሪያ @BotFather ላይ ገብተው
/mybot የሚለውን ok ይበሉ ከዛም የርሰዎ ቦት ላይ ክሊክ ያድርጉ።
ከዛ Api token የሚለውን ይጫኑ በመቀጠል የሆነ ኮድ ይላክሎዎታል።  ያንን የተላከውን
☟☟
554887452:AAG-A8KB5t8yQlSLPQLbMcR3PEPQpjEY
👆👆
የዚህ አይነት ጽሁፍ  ኮፒ አድርገው ይያዙና እዚህ

@LivegramBot 👈 bot ላይ ይግቡና start ብለው / 👈 ሲጽፉ /Addbot የሚለውን ክሊክ ብለው ይላኩ ከዛ

Agree continue የሚል ሲመጣልዎት ክሊክ ያድርጉ።
ከዛም የቡትዎን Apitoken paste  አድርገው ይላኩለት

🔘አውቶማቲክ አክቲቭ ያደርገዋል።  ቀጥታ ስራውን ጀምሯል ማለት ነው አለቀ። 

በመጨረሻም @BotFather ውስጥ በመግባት

✪ editname,
✪ about,
✪ discription
መሙላት ይችላሉ።

  ባይሞሉም ግን ቀጥታ የሚላክለዎት መልክት ይደርሰወታል።

⚠️ያስታውሱ ለሚልኩለዎት ሰዎች መልስ ለመስጠት ሲፈልጉ ለያንዳንዱ ሰው reply እያደረጉ መሆን አለበት።
ካልሆነ ግን ሜሴጅወዎ አይሄድለትም ።

▬▬▬በረሻድ ሙዘሚል


#በቪድዮ ከላይ አስቀምጬላችኋለሁ‼️

t.me/TechnologyMasterPage

http://tiktok.com/@techmasterpage
የኮምፒውተር 32 ቢት እና 64 ቢት ሲፒዮ ልዩነት እና ጥቅም
ምንድነው?
=======================================
ዛሬ በ32ቢት እና በ64 ቢት ፕሮሰሰር መሃል ያለውን ልዩነት
ይዘን
ቀርበናል ይህ ጽሁፍ ኮምፒውተር ለምትገዙ፤ የምትጠቀሙበትን
ኮምፒውተር/ላፕቶፕ የተጫነበትን ኦፕሬቲንግ ሲስተም ከፍ
(አብግሬድ) ለማድረግ እንዲሁም የምትጭኑትን ሶፍትወዌር
ለመወሰን
ያግዛል፡፡ የኮምፒውተር ሲፒዩ በሁለት አይነት 32 እና 64 ቢት
በሚል
የሚከፈል ሲሆን የፕሮሰሱ አይነት በኮምፒውተር ላይ ምንም
አይነት እክል
የማይፈጥር ቢሆንም የምንጭናቸው ኦፕሬቲንግ ሲስተምና
ሶፍትዌሮች
ይወስኑታል፡፡
1. 32 ቢት ፕሮሰሰር
32 ቢት ፕሮሰሰር ከ1990 ጀምሮ በሁሉም ኮምፒውተሮች ላይ
የሚገኘው ሲሆን የፕሮሰሰር አምራች የሆኑት ኢንቴል እና
ኤኤምዲ እየሰሩ
ለገበያ በማቅረብ ላይ ይገኛሉ ፡፡ ኦፕሬቲን ሲስተም እና
ሶፍትዌር የሚሰሩ ድርጂቶች 32 ቢት
ፕሮሰሰርን መሰረት በማድረግ ሲሰሩ ከነዚህም ውስጥ
ማይክሮሶፍት ዊንዶውስ 95፣
98 እና ኤክስፒን ሁሉም 32 ቢት ኦፕሬቲንግ ሲስተም ተደርገው
የተሰሩ ናቸው፡፡
32 ቢት ፕሮሰሰር የሆነ ኮምፒውተር 64 ቢት የሆነ ኦፕሬቲንግ
ሲስተም
መጫን የማንችል ሲሆን ምንጊዜም 32 ቢት ፕሮሰሰር መጫን
የሚችለው
32 ቢት የሆነ ኦፕሬቲን ሲስተም እና ሶፍትዌሮች ብቻ ነው፡፡
2. 64 ቢት ፕሮሰሰር
64 ቢት ፕሮሰሰር ያለው ኮምፒውተር በ1961 አካባቢ
አይቢኤም IBM
7030 Stretch supercomputer የሚባል የሰራ ቢሆንም
እስከ 2000
ድረስ ለቤት መጠቀሚያ ተብለው በሚሰሩ ኮምፒውተሮች ላይ
አልነበረም:: ማይክሮሶፍት 64
ቢት ፕሮሰሰርን የሚጠቀም 64 ቢት ዊንዶ ኤክስፒ ኦፕሬቲንግ
ሲስተም ለገበያ አቀረበ
በመቀጠል ዊንዶ ቪስታ፣ ዊንዶ 7፣ ዊንዶ 8 እና ዊንዶ 10 64
ቢት ፕሮሰሰር የሚጠቀሙ
ባለ 64 ቢት ኦፕሬቲንግ ሲስተም ለገበያ ቀርበዋል፡፡ 64 ቢት
ፕሮሰሰር ያለው ኮምፒውተር
64 ቢት እና 32 ቢት ኦፕሬቲንግ ሲስተም መጫን የሚችል
ሲሆን 32 ቢት ፕሮሰሰር 64 ቢት የሆነን
ኦፕሬቲን ሲስተም መጫን አይችልም፡፡ ማስታወሻ 64 ቢት
ፕሮሰሰር ያለው ኮምፒውተር 16 ቢት ተብለው የተሰሩ
ፕሮግራሞችን/ሶፍትዌሮች የማይሰራ ሲሆን ብዙ 32 ቢት የሆኑ
ፕሮግራሞች/ሶፍትዌሮች 64 ቢት ፕሮሰሰር እና ኦፕሬቲን
ሲስተም ላይ
የሚሰሩ ሲሆን አንዳንድ የድሮ ወይም የቆዩ 32 ቢት
ፕሮግራሞች/
ሶፍትዌሮች በትክክል አይሰሩም (compatibil አይደሉም)
32 ቢት እና 64 ቢት ፕሮሰሰር ትልቅ የሆነ ልዩነት ያላቸው ሲሆን
አንድን ስራ በኮምፒውተር ላይ ስንሰራ ፕሮሰሰሩ ያለው ፍጥነት
አንዱ
ልዩነታቸው ሲሆን 64 ቢት ፕሮሰሰር ትልቅ ፍጥነት አለው፡፡ 64
ቢት
ፕሮሰሰር ለገበያ ተሰርቶ የሚመጣው በdual core፣ በquad
core፣ በsix
core እና በeight core ቨርዥን በሆኑ ኮምፒውተሮች ላይ
ነው፡፡
32 ቢት እና 64 ቢት ፕሮሰሰር አንዱ ሌላው ልዩነታቸው
በኮምፒውተሩ
ላይ የሚያስፈልገው የሚሞሪ(ራም) መጠን ሲሆን 32 ቢት
ፕሮሰሰር
ያለው ኮምፒውተር በጠቅላላ 4GB የሆነ ራም ብቻ መጠቀም
የሚያስችል ሲሆን 64 ቢት የሆነ ፕሮሰሰር ያለው ኮምፒውተር
ከ4GB
በላይ የሆነ ራም መጠቀም ያስችላል ይሄም ግራፊክስ ዲዛይን፣
ኢንጂነሪንግ እና ቪዲዮ ኤዲቲንግ ለሆኑ ሶፍዌሮች በጣም
አስፈላጊ ነው፡፡
በአሁን ጊዜ በርካታ ኦፕሬቲንግ ሲስተሞች እና ሶፍትዌሮች 64
ቢት እየሆኑ የመጡ በመሆኑ ተጠቃሚዎች ኮምፒውተሮቻቸው 64 ቢት ቢሆኑ ይመረጣል።
ሼር ማድረግዎን አይርሱ፤፤ መልካም ቀን ይሁንልዎ
Like እና Share ማድረግ አይርሱ!
====================
#የተማሩትን_ማስተማር #ያወቁትን_ማሳወቅ #ብልህነት ነው
#ለሰው መልካሙን እንጅ መጥፎውን አትመኝ
በተጨማሪም በቴሌግራሜ ቻናል ምርጥ ምርጥ ስለኮምፒውተር የምለቃቸውን መረጃዎችን ለመከታተል እንዲያመችዎ ይህንን ይጫኑ https://t.me/TechnologyMasterPage በቴሌግራም መከታተል ትችላላችሁ

⭕️ ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ በፍጥነት መረጃ እንዲደርሳችሁ

⭕️ Like & share this page

#ሼር_ያድርጉ

#ፔጄን_ላይክ ማድረግዎን አይርሱ

Fb.com/TechnologyMasterPage

YouTube.com/@TechnologyMasterPage

Instagram.com/techmaster_page

tiktok.com/@techmasterpage
👍1
▮ልታውቋቸው የሚገቡ Commands እንዴት አድርገን የኮምፒውተራችንን Users ማስተዳደር እንችላለን?

🔶 በመጀመሪያ ደረጃ Command Prompt ወይም CMDን እንከፍታለን።

▮ለምክፈት በ3 አማርጮች እንጠቀማለን

1ኛ. Start-> All Program -> Accessories -> Command Prompt

2ኛ. Crtl+R በመጫን CMD ብለው በመጻፍ OKን ይጫኑ!

3ኛ. start -> Search Box ላይ CMD ወይም Command Prompt ብለው ይፈልጉ። ከዛም ከሶስቱ 1ን አማራጭ ተጠቅመው ሲከፍቱት Black Screen ይመጣላችኋል። ከዛም ከታች ከ1-8ኛ ድረስ ያለውን ተግባራቶችን ይሞክሩ።

#አዘጋጅ Muhammed Computer Technology

1ኛ. net user ይህ ኮማንድ የሚጠቅመን ከኮምፒውተራችን ያሉንት Users ይዘረዝርልናል። እንዲሁም ከማንኛውም ኮምፒውተር ላይ Administrator የሚል አካውንት አለ እሱ ምን እንደሆነ ከታች መልሱን ያገኛሉ።

2ኛ. net user Reshad /add ይህ ኮማንድ ከኮምፒውተራችን ላይ Reshad የሚባል User  Create(እንዲፈጠር ያደርግልናል)

3ኛ. net user Reshad * ይህ ኮማንድ ከላይ ለፈጠራችሁት Reshad ለሚባል User ወይም ከዚህ በፊት ላለ User ለምሳሌ amin የሚባል ቢኖር Reshad በሚለው ፈንታ amin የሚለውን ስታስገቡ ለUseሩ Password እንድታስገቡ ይጋብዛችኋል።

↪️ ትኩረት‼️ሁለት ጊዜ password እንድታስገቡ ይጠይቃችኋል ሁለቱም password ተመሳሳይ መሆን አለበት። እንዲሁም ፓስውርድ ስታስገቡ እይታያችሁም ወይም ፓስወርድ ስትጽፉ አይታያችሁም ግን በውስጥ ታዋቂነት እየጻፈ ስለሆነ ግራ እንዳትጋቡ።

ነገርግን ለUseሩ password ነስጠት ባትፈልጉ ዝም ብላችሁ 2 ጊዜ Enterን መጫን ብቻ ነው።


4ኛ. net user Reshad /add * ይህ ኮማንድ የሚያገለግለን አንድን User ከነ password Create(መፍጠር) ብትፈልጉ ይህንን መጠቀም አለባችሁ። ኮማንዱ በመጀመሪያ ደረጃ User create ያደርግና በተመሳሳይ ፓስወርድ እንድታስገቡ ይጋብዛችኋል።

password ማስገብት ከፈለጋችሁ አስገቡ ግን password ማስገባት ካልፈለጋችሁ Enterን 2 ጊዜ ይጫኑ።
▲ ይህ ማለት ከላይ ተ.ቁ 2ና 3ን በአንድ ጊዜ ለመስራት ያገለግለናል።


5ኛ. net localgroup Administrators Reshad /add ይህ ኮማንድ ከላይ የፈጠርነው user ምን ጊዜም Standard User ነው የሚሆነው።

📶 በኮምፒውተር ተጠቃሚዎች አይነት Users Type በ3 ይከፈላል 1ኛ Administrator 2ኛ Standard User 3ኛ Gusts ናቸው።

◈ እነዚህ Users ለምሳሌ ከላይ የፈጠርነው User Reshad የሚባለው ከላይ ባለው ኮማንድ ሲፈጠር Standard User ነው። Standard User ደግሞ በኮምፒውተሩ ላይ ሙሉ የሆነ የመቆጣጠር አቅም የለውም የግድ ምን መሆን አለበት Administrator መሆን አለበት።

▮ስለዚህ ከላይ ያለውን 5ኛ ተ.ቁን Command መጠቀም ይኖርብናል።


6ኛ. net localgroup Administrators Reshad /del ይህ ኮማንድ በተ.ቁ 5 ላይ Reshad የሚባለውን User ወደ Administratorነት ቀይረነዋል ነገር ግን ወደ Standar User ለመቀየር ከተፈለገ 6ኛውን ኮማንድ መጠቀም አለብን ማለት ነው። ይህም Reshad የሚባለውን User ከ Administrator Account Type ወደ Standard User Account Type ቀየርነው ማለት ነው።


7ኛ. ከማንኛው ኮምፒውተር ላይ Administrator የሚባል User አለ ይህ User ለአደጋ ጊዜ ተብሎ የተቀመጠ User አለ ይህ User ከኮምፒዩተሩ ተደብቆ ሁኖ ነው ያለው ይህንን User መሉ በሙሉ ከኮምፒውተሩ ማጥፋት አይቻልም ነገርግን ሌሎች የተፈጠሩ User Account ማጥፋት ትቻላል።

▮ለእናንተ የምመክራችሁ User Accountችን ሊጠፋብን ይችላል የሚል ስጋት ካለባችሁ Administrator የሚባለውን User Account Active ማድረግ አለባችሁ አሁን እሱን እናያለን!

🛑 net user Administrator active:yes
ከኮምፒውተሩ የተፈጠረን User Account ሳናጠፋ Inactive ለማድረግ ወይም እንዳይሰራ ለማድረግ ለምሳሌ Reshad የሚለውን እንዳይሰራ ለማድረግ።

🔷 net user Reshad active:no ይህ ኮማንድ Reshad የሚባለው user inactive ሁኗል ማለት ነው። እንደገና ግን Active ለማድረግ ከፈለጋችሁ
🔶 net user Reshad active:yes የሚለውን ኮማንድ ተጠቀሙ።


8ኛ. ከኮምፒውተሩ ያለውን User Account ሙሉ በሙሉ ለማጥፋት  ከፈለጋችሁ ለምሳሌ Reshad የሚባለውን ማጥፈት ብትፈልጉ

🛑 net user Reshad /del
ማስጠንቀቂያ ይህ ኮማንድ ለምሳሌ Reshad የሚባለውን user መረጃ ሙሉ በሙሉ ነው የሚያጠፋው ያ ማለት በውጡ ያስቀመጣቸው Desktop ላይ My Documents ላይ My Music ላይ My Picture ላይ ያስቀመጣቸውን ሙሉ መረጃ ያጠፋብናል ስለዚህ ትኩረት ማድረግ አለባችሁ።

▮ግን ለትምህርት ለምሳሌ እንደእስካሁኑ Reshad የሚባል User Account ላይ እንደ መለማመጃ ልትጠቀሙበት ትችላላችሁ።
#ይሞክሩት!

ከተመቻችሁ ለሌሎች እንዲደርሳቸው #ሼር ቢያደርጉ ጥሩነት ነው።


t.me/TechnologyMasterPage

www.youtube.com/@TechnologyMasterPage

Twitter.com/TechMasterPage

tiktok.com/@techmasterpage

Fb.com/TechnologyMasterPage
👍1
Secrets of Truth // የእውነት ሚስጥሮች

🎯 My goal is to expose the Secrets of Truth‼️

🎯 ዓላማዬ የእውነትን ሚስጥሮች ማጋለጥ ነው‼️
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

● Short and most important information Islam and Muslim

ሙስሊሞችንና እስልምናችንን በሚመለከት አጫጭርና በጣም ጠቃሚ የሆኑ መረጃዎችን።

● Fatwas and Muhadera issued by the Sunnah Scholars

● በሱና ኡለሞች የተሰጡ ፈትዋዎችንና ሙሐደራዎችን

● Advisory opinion


🔗 ሌሎችንም አንገብጋቢ ጉዳዮችን የምንተዋወስበት የናተው መድረክ ነው‼️

YouTube:

YouTube.com/@SecretsofTruth

TikTok:

tiktok.com/@secretsof_truth

Twitter:

Twitter.com/Secretsof_Truth

Instagram:

Instagram.com/secretsof_truth

Telegram:

t.me/Secretsof_Truth

Facebook

Fb.com/SecretsofTruth1

ለየትኛውም ለአስታየትና ድጋፍ:-

t.me/ReshadMuzemil
📍  መረጃ ቴክኖሎጂ  📍

#ፓስዋርድ_ሲጠፋን_ኮምፒውተራችንን_መክፈቻ_ዘዴ

የኮምፒውተርዎ ፓስዋርድ ከነአካቴው ቢጠፋብዎት ብዙም አይጭነቅዎ መፍትሄ አለው ።

የሚያስፈልገው ሶፍትዌር “Spotmou Bootsuite.iso” ወይም "isee password Windows password Recovery pro" ሲሆኑ ሁለትም ከ internet ላይ ማውረድ ትችላላችሁ ነገር ግን isee password windows password recovery pro የሚለውን ገዝታችሁ የምታገኙት ስለሆነ እኛ የገዛንውን ለውድ የቻናላችን ተከታታዮች sofrwarun ከላይ ለቀንላችኋል።

በ "Spotmou Bootsuit.iso ሶፍትዌር ፓስዎርዳችሁን መክፈት ለምትፈልጉ:- ቀጣዮቹን 10 ስቴፖች ተከትለው ኮምፒውተርዎን መክፈትና መጠቀም ይችላሉ፡፡

#Step 1: መጀመረያ ሶፍትዌሩን በፍላሽ ወይም CD ላይ እንጭናላን።

#Step 2: ኮምፒዩተራችንን Turn OFF ማድረግ፡፡

#Step 3: ፍላሹን /ሲዲውን/ ኮመፒዩተሩን ጋር አገናኝተን Turn ON ማድረግ፣ ከዛ F12 (Boot key) (ለHp ላፕቶፕ F9) መንካት፡፡

#Step 4: “Boot Sequence” የሚል ሲመጣልን “USB” የሚለውን መርጠን “Enter”ን መንካት ከዛ ትዕዛዙን መከተል፡፡

#Step 5: ኮምፒዩተሩ ከተከፈተ በኋላ “Spotmou Bootsuite 2012 Application” ይከፈትልናል፡፡

#Step 6: ከአፕልኬሽኑ ላይ “Password and Key Finder” የሚለውን “Menu” እንመርጣለን፡፡

#Step 7: “Admin Password Resetter” የሚል መንካት፡፡

#Step 8: “Please select the target widows” ከሚለው ሥር የኮምፒዩተሩን “Window Version (XP/7/8/8.1/ 10)” ይመርጣሉ፡፡ ቀጥሎ “please select the target user” ከሚለዉ ሥር ደግሞ መክፈት የሚፈልጉትን “User Account” መርጠዉ “Reset” የሚለውን መጫን፣ ከዛ “OK” ከዛ “YES” የሚለውን እንጫናለን፡፡

#Step 9: መጨረሻ ላይ “Password is reset successfully” የሚል መልዕክት ይደርሶታል፡፡

#Step 10: ኮምፒዩተሩን ዘግተው ይክፈቱት (Reboot). በትክክል 100% ይሰራል።

በ "iSee password windows password recovery Pro" ፓስዎርዳችሁን መክፈት ለምትፈልጉ ሶፍትዌሩን ቻናላችን ላይ ለቀንዋል Registered የሆነውን የሚከተለውን step ይከተሉ። ሶፍትዌሩን Download ያድርጉ ።

ሌላ Computer ላይ install ያደርጉት ሶፍትዌሩን ስከፍቱት ከላይ በምስል እንደምታዩት ያመጣላችኋል። ባዶ Flash or CD ትከቱና ፍላሽ ከሆነ የከተታችሁት Create password Reset Usb Flash drive ከሚለው ስር የፍላሹን ስም መርጣችሁ "Burn Usb" የሚለውን ስነኩት Burn አድጎ ሲጨርስ flashun ትነቅላላችሁ።

ከዛ በፓስዎርድ የተዘጋብንን ኮምፒዩትራችንን Turn OFF ማድረግ ፍላሹን/ሲዲውን/ ከኮምፒዩተራችን ጋር አገናኝተን Turn On ማድረግ ከዛም (F12 ለቶሽባ/ዴል) F9 ለHp Computer (Boot key) መንካት " Boot sequence" የሚል ሲመጣልን " USB" የሚለውን መርጠን "Enter"ን በመንካት ትዕዛዙን መከተል።

ኮምፒዩተራችን ከተከፈተ ብኋላ "isee password Windows recover pro" ይከፍትልናል ከአፕልኬሽኑ ላይ ካሉት አማራጭች(Option) ውስጥ "Admin Password Resetter" የሚለውን መንካት ከዛም "yes" የሚለውን እንጫናለን።

ትንሽ ከቆየ በኋላ(max. 2mint) "password is reset እናደርጋለን።


t.me/TechnologyMasterPage

www.youtube.com/@TechnologyMasterPage

Twitter.com/TechMasterPage

tiktok.com/@techmasterpage

Fb.com/TechnologyMasterPage
👍1
① Motherboard
    

❖ Motherboard የኮምፒውተር ክፍል ዋናው የኤሌክትሪክ ሰርኪዩት ሰሉዳ ሲሆን ተለቅ ያለ እና ዋና የኮምፒውተር ክፍል ነው፡፡
ሁሉም የኮምፒውተር ክፍሎች ከ Motherboard ጋር በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ የተገናኙ ሲሆን ይህም በመሰረታዊነት የኮምፒውተሩ ክፍሎች እርስ በርስ መረጃ እና ትዕዛዞችን እንዲለዋወጡ ያስችላል፡፡

❖ ካለ Motherboard ኮምፒውተር የማይታሰብ ነው፡፡ ለምሳሌ፡- የኮምፒውተሩ ኤሌክትሪክ አቅራቢ(Power Supply) ለሲዲ ማንበቢያው (CD drive) የኤሌክትሪክ ሃይል መስጠት ካልቻለ ሲዲ ማንበቢያው መስራት አይችልም፡፡
②Central Processing Unit (CPU)
 

❖ CPU የኮምፒውተሩ ማዕከላዊ ማቀነባበሪያ ክፍል ሲሆን ማቀናበሪያ(processor) አልያም የኮምፒውተር አዕምሮ ሌላኛው መታወቂያ ስሞቹ ናቸው፡፡

❖ CPU ከተጠቃሚ ወደ ኮምፒውተሩ የሚገቡትን ትዕዛዞች በሙሉ በመቀበል ኮምፒውተሩ በአግባቡ ትዕዛዙን እንዲከውን የሚያደርገው በ motherboard ላይ የሚገኝ ትንሽ የኤሌክትሮኒክ ቺፕ ነው፡፡

❖የማቀናበር ሃይል(processing power) የኮምፒውተርን ፍጥነት ግልፅ በሆነ መልኩ ይጨምራል፡፡
ስለሆነም ፈጣን ማቀነባበሪያ ኮምፒውተሮችን ፈጣን ያደርጋቸዋል፡፡
③ Random Access Memory (RAM)


❖RAM ማሕደረ-ትውስታ የኮምፒውተሩ ጊዜያዊ መረጃዎችን አልያም ስሌቶችን የሚያኖርበት እና በሚያስፈልግ ጊዜ(ኮምፒውተሩን ከማጥፋታችን አልያም ዳግም ከማስነሳታችን በፊት) መረጃዎችን ወይንም ስሌቶችን የሚሰጠን ነው፡፡

❖RAM ከ CPU ጋር በመተባበር ዳታዎች በተሳካ ሁኔታ የሚያቀነባብር ወሳኝ የኮምፒውተር ክፍል ነው፡፡

❖የRAM መጠን በመጨመር የኮምፒውተሮችን የማህደረ-ትውስታ በማስፋት የማቀነባበር አቅሙን ማሻሻል ይችላል
④Hard Drive


❖Hard drive ለኮምፒውተሮች እንደ ትልቅ ቤተ-መፀሃፍት ነው፡፡ ምክኒያቱም ፋይሎችን፤ ቪድዮዎችን፤ ምስሎችን፤ ሰነዶችን፤ ወዘተ ለዘለቄታው የምናኖርበት ሁነኛ ክፍል ነው፡፡

❖Hard drive በግል ከምናኖራቸው መረጃዎች ባለፈ የኮምፒውተሩ አሰራር ሂደት(operating system) የሚጫንበት እና በአግባቡ ኮምፒውተሩ ለተጠቃሚዎች አገልግሎት ምቹ የሚያደርጉትን የአሰራር ሂደት ፋይሎች(operating system files) የሚቀመጡበት የኮምፒውተር ክፍል ነው፡፡

#Reshad_Muzemil
⑤Power Supply Unit


❖Power supply unit የኮምፒውተሩ የሃይል አቅርቦት ክፍል ሲሆን ከግርግዳ ወይንም ከኤሌክትሪክ ማከፋፈያ የሚቀበለውን ኤሌክትሪክ ለኮምፒውተሩ በሚመጥን የኤሌክትሪክ መጠን እና አቅርቦት ለክቶ እና መጥኖ ወደ ኮምፒውተሩ ክፍሎች የሚያዳርስ የኮምፒውተር ቁልፍ ክፍል ነው፡፡