Basic Computer Skills
1.87K subscribers
1.22K photos
100 videos
576 files
833 links
#በዚህ የቴሌግራም ቻናል
↪️ Programming
↪️ ቴክኖሎጂ ነክ ትምህርቶችን
↪️ ኮምፒውተር ነክ ትምህርቶችን
↪️Basic Computer Skills
↪️ Software
↪️ AI and AI Skills (Like ChatGPT)

ከላይ የተዘረዘሩትና ሌሎችም ገራሚ ትምህርቶች ይለቀቅበታል!

t.me/BasicComputerSkillsGroup

𝘽𝙮 𝙍𝙚𝙨𝙝𝙖𝙙
Download Telegram
ሞባይል  ባትሪና  ቻርጀር ስንገዛ ኦርጅናልና ፌክ ኮፒ
መሆኑን እንዴት ማወቅ (መለየት) እንደምንችል እነሆ...

✔️ከሌሎች በይበልጥ ሳምሰንግ ስልኮች ተፈላጊነታቸዉ እየጨመረ በመጣ ቁጥር፣ ከኦርጂናሉ ጋር ተመሳስለዉ በቻይና የሚመረቱ ፌክ ሳምሰንግ ስልኮችም📱 በዛዉ መጠን ይጨምራሉ፡፡

ሳምሰንግ የጉግልን አንድሮይድ ኦፐሬቲንግ ሲስተም ይጠቃማል፣ የአንድሮይድ ሲስተም ኮድ ደግሞ ማንኛዉም ፍላጎት ያለዉ አካል ኮዱን እንዲጠቀም የሚያስችል
ፍቃድ ስለሚሰጥ፣ አጭበርባሪ ድርጅቶች ከኦርጂናሉ ስልክ ከፍተኛ ቅናሽ ያለዉን ተመሳሳይ ፌክ ሳምሰንግ ስልክ በማምረት ገበያዉን ያጥለቀልቁታል፡፡

⚠️ኦርጂናሉን ስልክ ከፌኩ በቀላሉ መለየት ያስቸግራል፣ ነገር ግን እነዚህን 👇 መንገዶች በመጠቀም ፌክ ሳምሰንግ
ስልኮችን መለየት ይችላሉ...

የስልኩን  ቀፎ አካላዊ ገጽታዎች በመገምገም 👇

ፌክ ሳምሰንግ ስልክ፡

1⃣. የስክሪኑ መስታወት ጥራት የለዉም‼️

2⃣. ስክሪኑ ከቀፎዉ ጠርዝ በጣም ይርቃል‼️

3⃣. ስክሪኑ ድምቀት ይጎድለዋል‼️

4⃣. የሳምሰንግ ሎጎ (ሳምሰንግ የሚለዉ ጽሁፍ) ሲነካ
ይሻክራል፣ በደንብ ከተጫኑት ይለቃል‼️

5⃣. ከኦርጂናል ስልኮች ጋር ሲያስተያዩት፤ የባትሪ መክደኛዉን ሲከፍቱ የሚታዩ ትንንሽ አካሎች እና ባትሪዉ ላይ የሚገኙት መረጃዎች የተለያዩ መሆናቸዉን ይመለከታሉ‼️

የስልኩን ፍጥነት እና የትእዞች አፈጻፀም በመገምገም *

1⃣. በስልኩ ፎቶዎችን ለማንሳት ይሞክሩ፣ በፌክ ሳምሰንግ
ስልኮች የሚያነሱት ፎቶ ጥራት የወረደ ይሆናል

2⃣. በተመሳሳይ ጊዜ በርካታ ጌሞች እና አፕሊኬሽኖችን
ለመክፈት ይሞክሩ፣ ፌክ ስልኮች ስታክ(ቀጥ) የማለት ባህሪይ ያሳያሉ፡፡

3⃣. ስልኩን አጥፍተዉ ያብሩት፣ ፌክ ስልኮች ቶሎ አይከፍቱም

የስልኩን የምርት መረጃዎች በመገምገም *

1⃣. ወደ ዋናዉ ማዉጫ ይሂዱ እና አፕስ(Apps) የሚለዉን ቁልፍ ይጫኑ...

2⃣. ከአፕሊኬሽን ማዉጫዉ ላይ Settings የሚለዉን ይጫኑ...

3⃣. ከ Settings ላይ More የሚለዉን ይጫኑ እና Storage የሚለዉን በመጫን ስልኩ ላይ መጫን ሚችሉትን የዳታ መጠን ይመልከቱ፤ ከኦርጂናሎቹ ስልኮች በጣም ያነሰ ከሆነ ፌክ መሆኑን ያረጋግጣሉ፡፡

4⃣. እንዲሁም About device የሚለዉን ይጫኑ እና
የስልኩን ሞዴል ቁጥር እና baseband, build number
ጉግል ላይ ይፈልጉት፣ የሚያገኙት መልስ ፌክ ወይም ኦርጅናል መሆኑን ይነግሮታል፡፡

የሳምሰንግ ኮዶችን በመጠቀም *

ወደ ስልክ📱 መደወያዉ በመሄድ፣ ከዚህ በታች የተጠቀሱትን ኮዶች ያስገቡ እና Call የሚለዉን ይጫኑ፤ ስልኩ
ያስገቡትን ኮድ አዉቆ መልስ መስጠት ከቻለ ኦርጅናል ✔️
መሆኑን ያረጋግጣሉ፡፡ ካልሆነ ግን ፌክ ስልክ ነዉ፡፡

1⃣. *#0*# 👉 አጠቃላይ መገምገሚያ

2⃣. *#1234# or *#9999# 👉 ስልኩ የሚጠቀመዉን
ሶፍትዌር እና ሞደም ማወቂያ

3⃣. *#12580*369# 👉 ስለ ስልኩ ሶፍትዌር እና ሀርድዌር ማወቂያ

4⃣. *#06# 👉 የስልኩን ኢንተርናሽናል መለያ ቁጥር
ማወቂያ

5⃣. *#9998*246# 👉 የስልኩን የባትሪ እና ሚሞሪ መረጃዎች ማወቂያ

ሳምሰንግ ኪይስ(Samsung Kies) ሶፍትዌርን በመጠቀም *

ከላይ 👆 በተጠቀሱት መንገዶች ፌክ ሳምሰንግ ስልክን መለየት ካልቻሉ ይህን ሶፍትዌር ይጠቀሙት፡፡

1⃣. Samsung Kies ሶፍትዌርን ኮምፒዉተሮት💻 ላይ
ይጫኑት...

2⃣. ለማረጋገጥ የፈለጉትን ስልክ ከኮምፒዉተሮት ጋር ያገኛኙት

3⃣. ሶፍትዌሩ ስልኩን 📱ያነበዉ እና የስልኩን ስም ፣የሚጠቀመዉን ሶፍትዌር እና ሀርድዌር ያሳያል
ሶፍትዌሩ ስልኩን ማንበብ ካልቻለ በድጋሚ ይሞክሩት በድጋሚ ማንበብ ካልቻለ ሰልኩ ፌክ መሆኑን ያረጋግጣሉ፡፡


▒▓⇨→መረጃዎች ቶሎ ቶሎ እንዲደርሶት ስልኮቻችሁ ላይ ላሉ
     ❖ Contact
     ❖ Group and Channel share አድርጉለን ከምስጋና ጋር።
     
       
━━━━━━━━━━━━━━━
http://t.me/TechnologyMasterPage

http://Fb.com/TechnologyMasterPage
▬▬▬▬▬📌Share📌▬▬▬▬▬
ማህበራዊ ገጾች 100 ሚሊየን ተጠቃሚ ለማግኘት ምን ያህል ጊዜ ወሰደባቸው?

ሜታ በቅርቡ ያስተዋወቀው ትሪድስ በቀናት ውስጥ ከ100 ሚሊየን በላይ ተጠቃሚዎች አግኝቷል።

t.me/TechnologyMasterPage

Fb.com/TechnologyMasterPage
The Prophet (saw) emphasized fasting on the day of Ashura (the 10th day in the month of Muharram), which falls on Friday, July 28th inshAllah. It is highly recommended to fast both the 9th day and the 10th day (Thurs, Jul 27th and Fri, Jul 28th). If that is not possible, scholars have noted that one can fast on the 10th and 11th day (Fri, Jul 28, and Sat, Jul 29th). Nonetheless, it is still commendable to just fast on the 10th day. We ask Allah most High to accept our fasting, and to grant us His mercies and guidance.

t.me/Secrets_of_Truth
2
የኮምፒውተር ሀርድ ዲስክን እንዴት መክፈል እንችላለን?
ዛሬ የምናየው እንዴት አድርገን አንድ ሎካል ዲስክን ወደ ሁለት ከዚያ በላይ ክፍልፋዮች እንደምንቀይር ነው።
ለምሳሌ Local disk C: ካለን ከሁለት ለመክፈል ለምሳሌ
#1_right click on My computer
#2_ከዛ Manage የሚለውን እንነካለን
#3_ከዛ ከሚመጡት ምርጫዎች ውስጥ disk management የሚለውን እንመርጣለን
#4_ከዛ ለመክፈል የምንፈልገውን ዲስክ C:
በመምረጥ right click እናደርጋለን
#5_ከዛ shrink volume የሚለውን እንመርጣለን ትንሽ ሰከንድ ይቆያል
#6-ከዛ የምንፈልገውን መጠን በመፃፍ shrink የሚለውን click አድርጎ መጠበቅ
ማስጠንቀቂያ:- ቁጥሩ በሜጋ ባይት ነው የሚገባው ለምሳሌ 50GB መክፈክ ብትፈልጉ 1GB ማለት 1024 MB ነው ይህ ማለት 50*1024=51,200 ይሆናል ስለዚህ 51,200 ብለን ማስገባት ይጠበቅብናል።
#7_ከዛ በጥቁር ቀለም ከታች (unlocated) የሚለው ላይ right click ማድረግ
#8_click on "new simple volume
ከዛ next next next እያሉ እስከመጨረሻው መቀጠል::
ይሄን ስናደርግ ምንም  አይነት መረጃ አይጠፋብንም።
እስኪ ለምሳሌ 152 GB ለመክፈል ብንፈልግ ስንት ብለን መጻፍ ይጠበቅብናል? ኮሜንት ላይ ይጻፉልኝ!
እንዲሁም ከዚህ በፊት የለቀቅኳቸውን ቪዲዮዎችን ብትከታተሉ ምርጥ እውቀትን ልታገኙ ትችላላችሁ

አሁንም የቴሌግራምና የYouTube ቻናሌን Subscribe በማድረግ ድጋፋችሁን አሳዩኝ።

#ያወቁትን ማሳወቅ ብልህነት ነው!

የ YouTube ቻናል ሊንክ 👇👇👇

https://www.youtube.com/@Sharp_Swords

Telegram:

t.me/Sharp_Swords
Learn web developement completely free in 2023

🎯WEBSITES

☀️w3schools:
https://www.w3schools.com/

☀️Geeksforgeeks
https://www.geeksforgeeks.org/

☀️Sololearn:
https://www.sololearn.com/home

☀️freecodecamp:
https://www.freecodecamp.org/


🎯Practice and improve your skill

🚀Frontend mentor
https://www.frontendmentor.io/

🚀Codechef:
https://www.codechef.com/

🚀Hacker earth
https://www.hackerearth.com/

🚀Coderbyte:
https://coderbyte.com/


▒▓⇨→መረጃዎች ቶሎ ቶሎ እንዲደርሶት ስልኮቻችሁ ላይ ላሉ
     ❖ Contact
     ❖ Group and Channel share አድርጉለን ከምስጋና ጋር።
     
        
━━━━━━━━━━━━━━━


t.me/TechnologyMasterPage

▬▬▬▬▬📌Share📌▬▬▬▬▬
Plagiarism Checker.rar
15.4 MB
Plagiarism Checker

🔗 የማስተርስ ተማሪ፣ የፒኤችዲ፣ የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪ ነዎት? ጥናታዊ ጽሁፍ(Research) እየሰሩ ነው?

🎯 የሰሩት ሪሰርች ከፕላጃሪዝም ነጻ መሆኑን የሚያረጋግጡበት የኮምፒውተር አፕሊኬሽን

t.me/TechnologyMasterPage
ጠቃሚ የ Microsoft Word አቋራጭ ቁልፎች (Useful Microsoft word  Shortcut keys)

1.   To insert the current date (ቀን ለማስገባት)
              SHIFT+ALT+D
2.    To Insert the current Time (ሰአት ለማስገባት)

              SHIFT+ALT+T
  
3.     Insert page number / የገጽ ቁጥር ለማስገባት
              
               SHIFT +ALT+P   

4.    To make selected text superscript

              SHIFT+CTRL++

5.    To make select text /number
subscript

                   CTRL+=

6.   To change a text from Lower case to upper case and Vice Versa / ጽሁፎችን ከካፒታል ወደ ስሞል ሌተር ወይም ከስሞል ሌተር ወደ ካፒታል ለመቀየር

                SHIFT + F3

7.    Underline the text / መስመር ከጽሁፉ ስር ለማስመር

      CTRL+U

8.   To double underline a text / ሁለት መስመር ማስመር ከፈለግን

            SHIFT+CTRL+D

9.   To increase text size / የጽሁፉን መጠን ለመጨመር

              CTRL+ ]

10.  To minimize the text size / የጽሁፉን መጠን ለመቀነስ
               CTRL+ [

11.  To add copy right Symbol / የኮፒራይት ምልክት ለማስገባት
                
               ALT+CTRL+C

12.  To add Registered Symbol / ሬጊስተርድ የሚለውን ምልክት ለመጨመር

              ALT+CTRL+R

13.  To add Trade mark Symbol / ትሬድማርክ የሚለውን ምልክት ለማስገባት
       
                ALT+CTRL+T

14.    Center the selected text / የመረጥነውን ጽሁፍ ወደ መሃል ለማጣት
              
                  CTRL+E

15.   To make a text bold / የመረጥነውን ቴክስት ደማቅ ለማረግ
        
                    CTRL+B

16.   To select a text one line at a time / በአንድ ጊዜ አንድ መስመር ጽሁፍ ለመምረጥ
        
               SHIFT+up or down Arrow  

17.   To select a text one character at a time / በአንድ ጊዜ አንድ ፊደል ጽሁፍ ለመምረጥ
      
             SHIFT+Left or Right Arrow

18.   To perform a calculation in word / ማይክሮሶፍት ወርድ ላይ የሂሳብ ስሌቶችን ለመስራት

Press CTRL+F9, then type the equal sign (=) and then type the formula for the calculation you want in the square bracket {}, right click on it and select update field.


Different methods to insert random text / ለተለያዩ ጉዳዮች ተራ ጽሁፎችን በቀላሉ ለማስገባት ከፈለን የሚከተሉትን መንገዶች ይሞክሯቸው
1.   =lorem() , type this text and press enter
2.  =rand() , type this text and press enter
3.  =rand(10,5) , this will insert a text with 10 paragraph but each paragraph with one line

How to hide or unhide a text in word / ማይክሮሶፍት ወርድ ላይ ጽሁፍን ለመደበቅ ከፈለጉ

To a hide text, select it and then open Font dialog (press CTRL+D), the click on the check box next to
hidden, click Ok.
To unhide select the whole text or select the area where there is the hidden text (if you know), then
press CTRL+D, uncheck the check box, the click ok.

Remember: unless you select the text, it will hide the text where there is a cursor / መደበቅ የምንፈልገውን
ጽፉፍ ካልመረጥነው ፤ ከርሰሩ ያለበት ቦታ ያለውን ጽሁፍ ነው የሚደብቀው


▒▓⇨→መረጃዎች ቶሎ ቶሎ እንዲደርሶት ስልኮቻችሁ ላይ ላሉ
     ❖ Contact
     ❖ Group and Channel share አድርጉለን ከምስጋና ጋር።
     
  
━━━━━━━━━━━━━━━

tiktok.com/@techmasterpage
ሰበር ዜና!

የ2015 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ይፋ ሆነ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ በዛሬው እለት የ2015 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ማለፊያ ውጤትን አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጡ ሲሆን በመግለጫቸውም በዘንድሮው ማለፊያ ውጤት 50% እና ከዛ በላይ ያስመዘገቡ መደበኛ ተማሪዎች ወደ ዘጠነኛ ክፍል እንደሚዘዋወሩ ጠቁመው የተለያየ የአካል ጉዳት  ላለባቸው ተማሪዎች  የማለፊያ ነጥቡ 45% መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዘንድሮ 73,385 ተማሪዎች ፈተናውን ወስደው 70.6% ያህሉ 50 ፐርሰንትና ከዛ በላይ በማምጣት ማለፋቸውን ዶክተር ዘላለም ገልጸው 61,840 ከሚሆኑ የቀን ተማሪዎች መካከል 50,812 የሚሆኑት ማለትም 82.16 % ያህሉ የማለፊያ ውጤቱን በማስመዝገብ ወደቀጣዩ የትምህርት እርከን መዘዋወራቸውን አስረድተዋል፡፡

የፈተናውን ውጤት በአስቸኩዋይ ይፋ ለማድረግ ቢሮው ባለሙያዎችን መድቦ ቀን ከሌት ሲሰራ መቆየቱን ኃላፊው በመግለጫችው በመጥቀስ በመጪው ሳምንት የመጀመሪያ ቀናት ደግሞ የ6ኛ ክፍል ውጤት ይፋ እንደሚደረግም አስታውቀዋል፡፡ 

ተማሪዎች ውጤታችሁን ለማየት ሊንኩን በመጫን https://aa.ministry.et/#/result

Registration number ና first name በማስገባት መመልከት ትችላላችሁ

http://tiktok.com/@techmasterpage
2👍1🍓1
እንኳን ደስ አላችሁ!፤ እኳን ደስ አለን‼️


በቲክቶክ በዛሬው እለት ብቻ.........

ከ 1,000 /1K በላይ አባላቶችን አፍርተናል‼️

tiktok.com/@sharpswords1

tiktok.com/@secretsof_truth

tiktok.com/@techmasterpage
👍4
Technology Master Page

በሁሉም ማህበራዊ ገፆች እንቅስቃሴ ጀምረናል

በ TikTok በሁለት ቀናቶች ብቻ 1000+ ( 1K ) አባላትን አፍርተናል።

⭕️ ይቀላቀሉን፤ አብረን ራሳችንን በቴክኖሎጂ እናዘምን። ሰዎችን እንጥቀም እኛም እንጠቀም‼️ 👇👇

tiktok.com/@techmasterpage
✳️ የሞባይል ባንኪንግ ሲጠቀሙ ሊያደርጓቸው የሚገቡ ጥንቃቄዎች

🚩የሞባይል ባንኪንግ የባንክ አገልግሎቶችን ወደ ባንኮች ቅርንጫፍ መሄድ ሳያስፈልግ በተንቀሳቃሽ ስልኮች አማካኝነት ብቻ የባንክ አገልግሎቶችን ማለትም ገንዘብ መላክ እና መቀበል እንዲሁም የተለያዩ ክፍያዎችን ለመፈፀም የሚያስችል ቴክኖሎጂ ነው፡፡

🚩የሞባይል ባንኪንግ አገልግሎት የተጠቃሚዎችን ድካም ከመቀነስ ጋር በተያያዘ አገልግሎቱን ተመራጭና ቀላል ያደርገዋል፤ ታዲያ ይህ አገልግሎት የቴክኖሎጂ ውጤት ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ተጓዳኝ የመረጃ መረብ ጥቃት ተጋላጭነት አያጣውም፡፡

🚩ተጠቃሚዎች አገልግሎቱን ሲጠቀሙ የሚከተሉትን ጉዳዮች ሊያውቋቸው እና ጥንቃቄ ሊያደርጉባቸው ይገባል ሲል የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አስተዳደር ይመክራል፡፡

➊. የተረጋገጡና ትክክለኛ የሞባይል ባንኪንግ መተግበሪያዎችን (application) ከተረጋገጡ ምንጮች አውርዶ መጠቀም፦ የሞባይል ባንኪንግ መተግበሪያዎች ትክክለኛ በባንኩ እውቅና ያላቸው መሆኑንና የሚገኙትም በትክክለኛው የመተግበሪያ ቋት ማለትም ለአንድሮይድ የመተግበሪያ ቋት ወይም ለአይ.ኦ.ኤስ ኦፕሬቲንግ ሲስተም በማውረድ መጠቀም ተገቢ ነዉ፡፡

➋. በስልኮች ላይ ያሉ ሌሎች መተግበሪያዎች ፍቃዶችን ማጥናት፡- በስልክዎ ላይ የሚገኙ ሌሎች መተግበሪያዎች የሚጠይቋቸውን ግንኙነቶች (አክሰስ) ልብ ይበሉ፡፡
መተግበሪያዎች ለአገልግሎቶቻቸው ከሚያስፈልጋቸው የሞባይል መረጃ ዉጪ ሌሎች መረጃዎች እንዲዳረሱ እንዳይፈቅዱ፡፡

➌. አፕሊኬሽኖችን /መተግበሪያዎችን ማዘመን፡- በስልኮች ላይ የሚገኙ የባንኪንግ መጠቀሚያ መተግበሪያዎችን ወቅቱን ጠብቀዉ ያዘምኑ፡፡
መተግበሪያዎች ላይ ለስርቆት የሚዳርጋቸው ክፍተቶች ሲገኙ በየወቅቱ ማዘመኛ ስለሚለቀቅላቸው የደህንነት ክፍተቶቹን ለመድፈንና የባንክ ሂሳብዎን ደህንነት ለማስጠበቅ በየጊዜው ያዘምኗቸው፡፡

➍. የሞባይል ስልክ ኦፕሬቲንግ ሲስተምን ማዘመን፡- የስልክዎን ደህንነት ክፍተት ለመሙላት በየጊዜው ክፍተት መሙያና ማሻሻያ እድሳቶች ስለሚለቀቁ በየወቅቱ እየተከታተሉ ያዘምኗቸው፡፡

➎. ከህዝብ መገልገያ ዋይፋይ ይልቅ የሞባይል ዳታ ይጠቀሙ፡- የሞባይል ባንኪንግ አገልግሎቶችን በሞባይልዎ ለመጠቀም ለህዝብ መገልገያ የቀረቡ ነፃ ዋይፋዮችን ከመጠቀም ይልቅ የሞባይል ዳታዎችን ይጠቀሙ፡፡

➏. ዘርፈ-ብዙ የደህንነት ማስጠበቂያ የይለፍ-ቃሎችን ይጠቀሙ፦ ሞባይል ስልክዎን በአሻራ፣ ፊት ማንበብያ (ፌስ ሪኮግኒሽን)፣ ፓተርን፣ ፓስወርድ እና ፓስ ኮድ የመሳሰሉትን በመጠቀም ስልክዎን ይቆልፉ፡፡

➐. በማህበራዊ ሚዲያ የሚለቋቸውን ግላዊ መረጃዎች ይገድቡ፡- በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ የሚለቀቁ መረጃዎች የተገደቡ ሊሆኑ ይገባል፡፡

➑. ፀረ-ቫይረስ (ማልዌር) ይጠቀሙ

➒. የሞባይል ስልክዎን አካላዊ ደህንነት ያስጠብቁ

➓. የባንክ ሂሳብዎን ዘወትር ይከታተሉ፡- በተጨማሪ ተገቢውን ሁሉ ጥናቃቄ ካደረጉ በኋላም ስለ ባንክ አካውንትዎ የሚደርሱ ማንቂያዎችን (notifications) በአግባቡ መከታተል እንዲሁም በየጊዜው ስለ አካውንትዎ ሁናቴ (ስታተስ) መከታተል እና የማያውቁት የሂሳብ ለውጥ ካለ በአፋጣኝ ለባንክዎ ያሳውቁ፡፡

http://tiktok.com/@techmasterpage
ቫይረሶች ወደ ኮምፒውተሮች እንዴት ነው የሚገቡት?

✴️በዚህ የቴክኖሎጅ ዘመን ኮምፒውተራችን አልያም ስማርት ስልኮቻችን ሁነኛ የመረጃ ማግኛ እና መዝናኛ ከሆኑ ሰነባብተዋል።

✴️ይሁን እንጂ የሰዎችን መረጃ አላስፈላጊ በሆነ መልኩ ለመጠቀም ብሎም መረጃ እና ንብረትን ወደ ግል ለማዞር የሚሞክሩ ሰዎች ስጋት ከሆኑም ቆይተዋል።

✴️ቫይረሶች በማወቅም ይሁን ባለማወቅ ወደ ኮምፒውተራችን ሲገቡ ሙሉ በሙሉ አልያም በከፊል ከጥቅም ውጭ ሊያደርገው ይችላል፤
የተለያዩ ጠቃሚ መረጃዎቻችንም ለሌሎች አሳልፈው የመስጠት እድልም አላቸው።

✴️እናም በተቻለ መጠን ቫይረሶች ወደ ኮምፒውተራችን ገብተው ጉዳት እንዳያደርሱብን ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል።

🔰ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ነጥቦችም የኮምፒውተር ቫይረሶች ወደ ኮምፒውተሮች የሚገቡበትን መንገድ ያስገነዝባሉ።

✴️የማንቂያ መልዕክቶችን (ኖቲፊኬሽን) ሳናነብ መቀበል
ቫይረስ ወደ ኮምፒውተራችን ከሚገባባቸው መንገዶች ዋነኛው የማንቂያ መልዕክቶችን ሳንረዳ መክፈት ነው።
♻️ለምሳሌ፦♻️
✴️1. በኢንተርኔት መረጃዎችን ስናፈላልግ a unique plugin is necessary is required የሚል ማስታወቂያ ሲመጣ ምንም አይነት የደህንነት ስጋት ይኑረው አይኑረው ሳናውቅ እንዲከፍትልት የሚያዘንን ቅደም ተከተል መከተል፤

✴️2. በነፃ የሚለቀቁ ፕሮግራሞችን ከጫንን በኋላ በተደጋጋሚ እንድንጭናቸው የምንጠየቀውንና እያንዳንዱን የኢንተርኔት እንቅስቃሴያችንን ለመረጃ በርባሪዎች አሳልፈው የሚሰጡ ፕሮግራሞችን ማውረድ
የተበከለ ሶፍትዌር መጫን
ከኢንተርኔት
የምናወርዳቸው ነገሮች ከታማኝ ምንጮች የተገኙ መሆናቸውን ማረጋገጥ ይኖርብናል።

✴️ካወረድን በኋላ ወደ ኮምፒውተራቸን ስንጭን (install ስናደርግም አንቲቫይረስ ሶስትዌር ሊኖረን ይገባል።

✴️ላኪያቸው የማይታወቁ የኢሜል መልዕክቶችን መክፈት
ማንኛውንም ላኪያቸውን የማናውቃቸውን የኢሜል መልዕክቶች ከመክፈታችን በፊት በኦንላይን አንቲቫይረስ ሶፍትዌሮች ስካን ማድረግ ይኖርብናል።

✴️በኢሜል መልዕክቶች አማካኝነት የተለያዩ ቫይረሶች ስለሚላኩ ጥንቃቄ ማድረግ ተገቢ ነው።

✴️የተበከሉ ውጫዊ ስቶሬጅ መሳሪያዎች (ሚሞሪ፣ ፍላሽ ዲስክ፣ ሀርድ ዲስክ ወዘተ ኮምፒውተራችን ላይ መሰካትም ሌላኛው ቫይረስ ወደ ኮምፒውተራችን የሚገባበት መንገድ ነው።

✴️የኮምፒውተር ሶፍትዌሮችን በየጊዜው አለማሳደግ አፕዴት አለማድረግ ችግር ላይ እንደሚጥል ይታመናል።

http://www.tiktok.com/@techmasterpage

http://www.YouTube.com/TechnologyMasterPage