Basic Computer Skills
1.87K subscribers
1.22K photos
100 videos
576 files
833 links
#በዚህ የቴሌግራም ቻናል
↪️ Programming
↪️ ቴክኖሎጂ ነክ ትምህርቶችን
↪️ ኮምፒውተር ነክ ትምህርቶችን
↪️Basic Computer Skills
↪️ Software
↪️ AI and AI Skills (Like ChatGPT)

ከላይ የተዘረዘሩትና ሌሎችም ገራሚ ትምህርቶች ይለቀቅበታል!

t.me/BasicComputerSkillsGroup

𝘽𝙮 𝙍𝙚𝙨𝙝𝙖𝙙
Download Telegram
① Motherboard
    

❖ Motherboard የኮምፒውተር ክፍል ዋናው የኤሌክትሪክ ሰርኪዩት ሰሉዳ ሲሆን ተለቅ ያለ እና ዋና የኮምፒውተር ክፍል ነው፡፡
ሁሉም የኮምፒውተር ክፍሎች ከ Motherboard ጋር በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ የተገናኙ ሲሆን ይህም በመሰረታዊነት የኮምፒውተሩ ክፍሎች እርስ በርስ መረጃ እና ትዕዛዞችን እንዲለዋወጡ ያስችላል፡፡

❖ ካለ Motherboard ኮምፒውተር የማይታሰብ ነው፡፡ ለምሳሌ፡- የኮምፒውተሩ ኤሌክትሪክ አቅራቢ(Power Supply) ለሲዲ ማንበቢያው (CD drive) የኤሌክትሪክ ሃይል መስጠት ካልቻለ ሲዲ ማንበቢያው መስራት አይችልም፡፡

Tech's Skills by Reshad Ibnu Muzemil

t.me/TechnologyMasterPage
②Central Processing Unit (CPU)
 

❖ CPU የኮምፒውተሩ ማዕከላዊ ማቀነባበሪያ ክፍል ሲሆን ማቀናበሪያ(processor) አልያም የኮምፒውተር አዕምሮ ሌላኛው መታወቂያ ስሞቹ ናቸው፡፡

❖ CPU ከተጠቃሚ ወደ ኮምፒውተሩ የሚገቡትን ትዕዛዞች በሙሉ በመቀበል ኮምፒውተሩ በአግባቡ ትዕዛዙን እንዲከውን የሚያደርገው በ motherboard ላይ የሚገኝ ትንሽ የኤሌክትሮኒክ ቺፕ ነው፡፡

❖የማቀናበር ሃይል(processing power) የኮምፒውተርን ፍጥነት ግልፅ በሆነ መልኩ ይጨምራል፡፡
ስለሆነም ፈጣን ማቀነባበሪያ ኮምፒውተሮችን ፈጣን ያደርጋቸዋል፡፡


Tech's Skills by Reshad Ibnu Muzemil

t.me/TechnologyMasterPage
③ Random Access Memory (RAM)


❖RAM ማሕደረ-ትውስታ የኮምፒውተሩ ጊዜያዊ መረጃዎችን አልያም ስሌቶችን የሚያኖርበት እና በሚያስፈልግ ጊዜ(ኮምፒውተሩን ከማጥፋታችን አልያም ዳግም ከማስነሳታችን በፊት) መረጃዎችን ወይንም ስሌቶችን የሚሰጠን ነው፡፡

❖RAM ከ CPU ጋር በመተባበር ዳታዎች በተሳካ ሁኔታ የሚያቀነባብር ወሳኝ የኮምፒውተር ክፍል ነው፡፡

❖የRAM መጠን በመጨመር የኮምፒውተሮችን የማህደረ-ትውስታ በማስፋት የማቀነባበር አቅሙን ማሻሻል ይችላል



Tech's Skills by Reshad Ibnu Muzemil

t.me/TechnologyMasterPage
④Hard Drive


❖Hard drive ለኮምፒውተሮች እንደ ትልቅ ቤተ-መፀሃፍት ነው፡፡ ምክኒያቱም ፋይሎችን፤ሙዚቃዎችን፤ምስሎችን፤ሰነዶችን፤ ወዘተ ለዘለቄታው የምናኖርበት ሁነኛ ክፍል ነው፡፡

❖Hard drive በግል ከምናኖራቸው መረጃዎች ባለፈ የኮምፒውተሩ አሰራር ሂደት(operating system) የሚጫንበት እና በአግባቡ ኮምፒውተሩ ለተጠቃሚዎች አገልግሎት ምቹ የሚያደርጉትን የአሰራር ሂደት ፋይሎች(operating system files) የሚቀመጡበት የኮምፒውተር ክፍል ነው፡፡



Tech's Skills by Reshad Ibnu Muzemil

t.me/TechnologyMasterPage
⑤Power Supply Unit


❖Power supply unit የኮምፒውተሩ የሃይል አቅርቦት ክፍል ሲሆን ከግርግዳ ወይንም ከኤሌክትሪክ ማከፋፈያ የሚቀበለውን ኤሌክትሪክ ለኮምፒውተሩ በሚመጥን የኤሌክትሪክ መጠን እና አቅርቦት ለክቶ እና መጥኖ ወደ ኮምፒውተሩ ክፍሎች የሚያዳርስ የኮምፒውተር ቁልፍ ክፍል ነው፡፡



Tech's Skills by Reshad Ibnu Muzemil

t.me/TechnologyMasterPage
ዩቲዩብ ገቢ ለማግኘት 500 ‘ሰብስክራይበር’ ይበቃል እያለ ነው፣ ይህ ምን ማለት ነው?

ዩቲዩብ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ በይነ መረብ ብቅ ያለው በፈረንጆቹ ሚያዚያ 23/2005 ነበር።

የድርጅቱ ሽርክ መሥራች የሆነው ጃዌድ ካሪም ከዝሆኖች ፊት ቆሞ የለጠፈው የ19 ሰከንድ ተንቀሳቃሽ ምስል የመጀመሪያው የዩቲዩብ ይዘት ነው።

ዩቲዩብ ተጠቃሚዎች የራሳቸውን ይዘት፤ራሳቸው ቀርፀው እንዲለጥፉ ያበረታታል።

ለዚህ ነው ይድዲያ የቅጂ [ኮፒራይት] ጉዳይ ጥንቃቄ ሊደረግበት ይገባል የሚለው።

የመጀመሪያው እርምጃ ግን ‘አፕላይ’ ማድረግ ነው።

“ወደ ዩቲዩብ አካውንትህ ስትገባ የሞኒታይዜሽ (ገንዘብ የማግኛ) ቦታ አለ።አንድ ሺህ ሰብስክራይበር እና 4 ሺህ ሰዓት መታየቱን ለማመልክት አረንጓዴ ጭረት አለ። ሁለቱ አረንጓዴ ሲሆኑ ነው ‘አፕላይ’ የምታደርገው (የምታመለክተው) ።”

ተጠቃሚዎች የዩቲዩብ መስፈርት ካሟሉ በኋላ ገቢ ማግኛውን ተጭነው ይሁንታ እስኪሰጣቸው ከ24 አስከ 48 ሰዓታት ሊጠብቁ ይችላሉ።


ከወደዱት ለወዳጅዎ  ሼር ያድርጉልን!

📢:
t.me/TechnologyMasterPage
🤔2
                  🌙🌙🌙

🌺 عيدكم مبارك 🌺

🔶 🌸Eid Mubarak 🌸 🔶

🌹 ዒድ ሙባረክ 🌹

تقبل الله منا ومنكم صالح الأعمال

💎ከእኛም ከእናንተም አሏህ መልካም ስራዎቻችንን ይቀበለን💎


ረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል
       
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
⭕️ ውድ የ6ኛ እና 8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ተፈታኝ ተማሪዎች ይህ ማስታወሻ በፈተና ወቅት ይጠቅማችኋል በትኩረት ይነበብ።
▬▭▬▭▬▭▬▭▬▬▭▬▭▬▭▬▭
🛑 ውድ ወላጆች እና ተማሪዎች!

➤ በፈተና ወቅት በተማሪዎች ላይ የሚፈጠረውን ውጥረት እና መጨናነቅ ለመቀነስ ይህንን ምክር በማስገንዘብ እንድትተባበሩን እንጠይቃለን።

🎯 በፈተና ጊዜ የሚፈጠርን ጭንቀት ወይም ቴንሽንን ልንቆጣጠር የምንችልባቸው ዘዴዎች:-

📙 ፈተና የመፈተኛ ጊዜ ሲቃረብ ሁላችንም በመጠኑ መጨነቅ እና ከወትሮው ከፍ ባለ መጠን ውጥረት ውስጥ መግባታችን የተለመደ ነገር ነው።
ይህን አይነቱን ከፍተኛ ውጥረት መቆጣጠር የምትችሉበትን መንገድ አንድ በአንድ እንመልከት።

♻️ ከፈተና በፊት ማድረግ የሚገባን ዜዴዎች

◆ ፈተና ሲመጣ መጠነኛ ውጥረት እና ጭንቀት ተፈጥሮአዊ እና ሁሉም ተፈታኝ ተማሪ እንደሚያጋጥመው መረዳት።
◆ ለፈተና ስንዘጋጅ አዎንታዊ እና በጎ ሀሳቦችን ማሰብ፡፡
◆ ፈተና ማለት ከዚህ ቀደም ከተማርነው ነገር የተረዳነውን እና የቀሰምነውን እውቀት የምንለካበት መመዘኛ እንጂ የኛ የህይወት ምዕራፍ ማብቂያ ወይም አጠቃላይ ችሎታችንን የሚያመላክት አለመሆኑን መረዳት። 
◆ ማወቅ ያለብን አንድ ነገር ቢኖር መሳሳትን አለመፍራት እና ሁሌም ለማወቅ እና ራስን ለማሻሻል ዝግጁ መሆንን ነው ። እንዲሁም አሁን የምንፈተነው ፈተና እንዳሰብነው እንኳን ውጤቱ ባያስደስት ለቀጣይ ማስተካከል እና ማሻሻል እንደሚቻል ማመን።
◆ ከጓደኞቻችን ወይም ከወላጆቻችን ጋር ያጠናነውን ነገር በጋራ ሆነን መጠያየቅ እና እርስ በርስ ያወቅነውን ነገር መለዋወጥ፡፡ ይህ ዘዴ ይበልጥ የማስታወስ ብቃታችንን እንደሚጨምር እና የተጠያየቅነው ነገር እንዳይረሳን ያረጋል ። ከዚህም በተጨማሪ እርማት እንድናረግም ያግዘናል።
◆ የፈተና ቀን ሲቃረብ እንደ ወትሮው ዘና ማለት እና በቂ እረፍትና በቂ እንቅልፍ  መተኛት ። ይህም ጭንቀትን ይቀንስልናል፣ እንዲሁም ተረጋግተን ያጠናነውን ነገር አስበን እንድንሰራ ይረዳናል። 
◉ ፈተና ከጀመርን በኋላ ማድረግ የሚገቡን ነገሮች (ፈተና ላይ እያለን)፤
◉ ወደ ፈተና ከመሄዳችን ቀደም ብለን ለፈተና የሚረዱንን መሳሪያዎች እና የመፈተኛ ቁሶችን ማዘጋጀት።
◉ አብዝተን ፈተናን እና የምናመጣውን ነጥብ ስሌት አለመገመት ።
🔰 ፈተና ስንጨርስ የተሳሳትነውን ጥያቄ አብዝቶ ማሰብ እና ሌላ ተማሪ መጠየቅ ጭንቀት ውስጥ ስለሚከተን ከዚህ ይልቅ  እረፍት ማድረግ እና ለቀጣይ ፈተና መዘጋጀት ።
◉ በፈተና ጊዜ ድንገተኛ ጭንቀት እና ድንጋጤ ከገጠመን ወዲያው የምንሰራውን ገታ አድርገን በጥልቀት አየር በአፍንጫችን ስበን ወደ ሳንባ እያስገባን መልሰን ማስወጣት ይህንንም እስክንረጋጋ መደጋገም።

ከዚህ በመቀጠል የማረጋጊያ ቃላትን ለራስዎ መንገር::
◉ ፈተና በምንሰራ ጊዜ ግራ ያጋባንን እና እርግጠኛ ያልሆንበትን ጥያቄ በይለፍ ማቆየት እና ወደ ቀጣዩ ጥያቄ መሄድ ይህም ጊዜያችንን በአግባቡ እንድንጠቀም ይረዳናል። ነገር ግን ምልክት አድርገን ማለፍ፤
◉ በተመሳሳይ እርግጠኛ ያልሆልንበትን መልስ ላይ ተደናግጠን መሰረዝ እና መደለዝን መቀነስ ይህም ስንደነግጥ እና ስንጨነቅ የምናውቀውን መልስ ትተን ወደ ሌላ መልስ እንድሰጥ ስለሚያረግ መሰረዝና መደለዝን መቀነስ ።
◉ ፈተናውን ወደ ማገባደድ ስንደርስ በይለፍ ያስቀመጥናቸውን ግራ ያጋቡንን ጥያቄዎች ጥቂት አስበንበት መልስ መስጠት ፤ ካልሆነም ደግሞ ብልሀት ተጠቅመን የግመታ መልስ ሰጥተን ወደ ቀጣዩ ጥያቄ መሄድ ።
◉ በተደጋጋሚ ሰአት በቃን አልበቃን እያልን አለመጨነቅ።

▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
➚ ሁሉም ነገር አላህ ከወሰነው ውጭ እንደማይሆን እርግጠኛ መሆንና ፈተና ማለት ለጀነትና ለጀኃነም ማለፊያ ትኬት እንዳልሆነ እርግጠኛ መሆን።

▮ከኛ የሚጠበቀው የአቅማችንን ያህል ማድረግ ሌላውን ለአላህ መተው ነው‼️
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

◉ ወቅቱ የፈተና ወቅት በመሆኑ ተማሪዎች እንዳየ እድሜያቸው እና የክፍል ደረጃቸው ይህን ማስታወሻ እንዲጠቀሙበት  አሳስባለሁ።


🎯 አላህ ይርዳችሁ‼️
👌2