Al EHSAN አል_ኢህሳን
182 subscribers
417 photos
45 videos
2 files
662 links
የቻናሉ አላማ
1 ባለን አቅም እስልምናን በአግባቡ ለኡማው ማድረስ
2 ሙስሊሞችን በድናቸውም ይሁን በዱኒያ እውቀታቸው የነቁ እንድሆኑ መገፋፋት
3 ለወጣቶች ምክር
4 በልዩ መልኩ ሴቶችን ማንቃትና ሌሎቹም አለማዊና መንፈሳዊ ት/ቶች ይገኙበታል።

ውድና የተከበራቹ የአል ኢህሳን ቻናል ቤተሰቦች ሆይ ውብና ማራኪ የሆኑ ሀሳብ አስተያያታቹ እንዳይለይን

ለአስተያት @S1u9l
አሁኑኑ ይቀላቀሉን
👇
Download Telegram
Forwarded from ተውሒድ የሁሉም ነብያቶች ጥሪ ነው። (Bint Mohammed አላህ ከዐርሹ በላይ ነው።)
አሠላምአለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካትሁ

ውድና የተከበራችሁ እህት ወንድሞች ይች እህታችን ስሟ ተምሬ አራጋው ጎቸል ትባላለች ከፓስፖርቱላይ እንዳለው በጠለብ ከአራትና አምስት ወር በፊት ሳኡድ ጂዳ ከተማ ገብታ ነበር እናም አሰሪዋ መንገድ ላይ ጥላታለች አሉን። አእምሮዋም ትክክል አይደለም ቪዶወውላይ እንደምታዩት።የቀረጿትም ልጆች ልንወስዳት ስንል ሴትየዋ እምቢአለችን አሉ በሰአቱ ዘወር ብለው ሲመለሱም ከቦታው እንዳላገኙዋት ነው የተናገሩት እና ጂዳ አካባቢ ያላችሁ በተለይ እባካችሁ ይችን እህታችንን ያያት ካለ እንድትተባበሩን በአክብሮት እንጠይቃለን።

አላህ ሁላችንም ይጠብቀን እሷንም ያስገኛት!!

እኔ የሰፈሯ ልጂ ነኝ ካገኛችኋት

0532053175 Bint Mohammed በዚህ ቁጥር በዋሳብም ወይም በመስመር ያገገኙኛል ይደውሉ የሠማችሁም አደራ ሸር አድርጉልኝ
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በሱፊያው ዓለም በርካታ የሚመለኩ ቀብሮች አሉ። ቀብሮቹ ዘንድ በመሄድ ልጅ፣ ዝናብ እና የተለያዩ ሐጃዎችን ይማፀናሉ። የሞተ ሰው እንኳን የነሱን ጉዳይ ሊፈፅም ከራሱ፣ ከተሰራለት ዶሪሕ እንኳ መከላከል አይችልም። ይሄው ይሄ "ወሃቢ" የሆነ ጎርፍ ዶሪሑን ነቅሎ እየወሰደው ነው።
{ أَیُشۡرِكُونَ مَا لَا یَخۡلُقُ شَیۡـࣰٔا وَهُمۡ یُخۡلَقُونَ (191) وَلَا یَسۡتَطِیعُونَ لَهُمۡ نَصۡرࣰا وَلَاۤ أَنفُسَهُمۡ یَنصُرُونَ (192) }
"ምንንም የማይፈጥሩትንና እነርሱም የሚፈጠሩትን (በአላህ) ያጋራሉን? ለእነርሱም መርዳትን የማይችሉትን ነፍሶቻቸውንም የማይረዱትን (ያጋራሉን)?" [አልአዕራፍ፡ 191-192


https://t.me/B1e9h
ስለ የታላቁ ነጃሺ ዜሮ ዜሮ (00) መንደር አጭር ማብራሪያ
(Grand Al Najashi 00 Village Project)

📎የፖሮጀክቱ ሰያሜ ፡ የታላቁ ነጃሺ 00 መንደር
📎 የሚሰራበት ቦታ፦ ትግራይ ክልል፣ ውቅሮ ነጃሺ
📎የዜሮ ዜሮ [00] መጠሪያ ሃሳብ የሸክ ሃጂ ኢበራሂም ቱፋ ሲሆን የታሪኩ መነሻና መገኛ ስፍራ (ትግራይ፣ ነጃሺ) ያመላክታል።

®የዚህ ፕሮጀከት የበላይ መሪ ሸክ ሃጂ ኢብራሂም ቱፋ (የኢትዮጵያ እሰልምና ጉዳይች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት)

የፕሮጀክቱ አጋር ተቋማት።

©የትግራይ ክልል እሰልምና ጉዳዮች ጠቅላይ መክርቤት
©የአልነጃሺ መልሶ ግንባታና ልማት ኢኒሼቲቭ( Al-Nejashi Reconstruction and Development initiative (ARDI)

የፖሮጅክቱ ዓላማ

📎በኢትዮጵያ ብሎም የአለም ትልቁ የሙሰሊሞች የታሪክ ቅርሰ የሆነው፤ ለሙሰሊሞች በከባዱ ፈተና ወቅት ከለላ(መጠጊያ) የሆኑት ንጉስ ነጃሺ መካነ ቀርስ አሻራ ያለበት ቦታ በትግራይ ክልል በነጋሺ ከተማ ክብራቸውና ታሪካችው የሚመጥን አለም አቀፍ የቱሪሰት መዳረሻ ቦታ አንዲሆን ሁሉም አቀፍ መንደር (ቪሌጅ) ለመገንባት ያለም ነወ፡፡

የሚገነበው መንደር Educational, health and Development facilities የሚያካትት ሲሆን በውስጡ የተለያዩ ንኡስ ፕሮጀክቶች የሚኖሩት ሲሆን በዋናነት:-

📌መስጂድ እና መድረሳ
📌ሙዚየም
📌ሐላል ሆቴል እና ሎጅ
📌የስፖርት ማዘውተሪያዎች
📌ኢስላሚክ የጥናትና ምርምር ተቋም
📌የቴከኒከና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጆች
📌ሆስፒታል
እና ሌሎች
Mohammedawel Hagos

https://t.me/B1e9h
በኮንትራት ለስራ የሄዳችሁ ወገኖች
~
ከአሰሪያችሁ ጋር ለምሳሌ የሁለት አመት የስራ ውል (ኮንትራት) ገብታችሁ የተቀጠራችሁ ወገኖች ቃላችሁን ጠብቁ። የተሻለ ደመወዝ ፍለጋ በሚል ምክንያት አትጥፉ። ማንም ቢሆን ወጭ አውጥቶ ቃል አስገብቶ ካገሩ ያስመጣው ሰራተኛ ቃሉን አፍርሶ ጥሎት ቢጠፋ ደስ አይለውም። ራሳችሁ ላይ እንዲሆን የማትፈልጉትን ነገር ሌሎች ላይ አታድርጉ። ቃል ያስጠይቃል። አላህ እንዲህ ይላል፦
{ وَأَوۡفُوا۟ بِٱلۡعَهۡدِۖ إِنَّ ٱلۡعَهۡدَ كَانَ مَسۡـُٔولࣰا }
"በቃል ኪዳናችሁም ሙሉ፡፡ ቃል ኪዳን የሚጠየቁበት ነውና። [አልኢስራእ: 34]

አስገዳጅ ሁኔታ ካልገጠመ በስተቀር።

=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ኢማሙ አሽ _ሻፊዒይ ከኢማሙ አህመድ ጋር

ኢማሙ አህመድ ከኢማሙ አሽ _ሻፊዒይ ከትልልቅ ተማሪዎች አንዱ ነው። ኢማሙ አህመድ ኡስታዛቸውን በጣም ይወዷቸው ነበር በሰዎች እና በልጆቻቸውም አጠገብ ያወድሷቸው ነበር ስለ ጀግንነታቸውም ያነሱ ነበር።ከዚህ የተነሳ የኢማሙ አህመድ ልጃቸው ሁልጊዜ ኢማሙ አሽ _ሻፊዒይን ለማየት ዒባዳቸው እንዴት እንደሆነ ለማየት ትጓጓ ነበር።

        ከእለታት አንድ ቀን ኢማሙ አሽ _ሻፊዒይ ወደ ኢማሙ አህመድ ቤት እንግድነት ሄደው አደሩ ።የኢማሙ አህመድ ልጅ ሁኔታቸውን በማየት ነበር እና ከኢማሙ አሽ _ሻፊዒይ የማይጠበቅ 3 ነገራቶችን ተመለከተች።

1ኛ  ምግብ ቀረበላቸው እና ኢማሙ አሽ _ሻፊዒይ ምግቡን አብዝተው በሉ ሆዳቸው እሰከሚሞላ ድረስ።

2ኛ   ከበሉ በኋላ ገብተው ተኙ ሰላተ ለይል ሳይሰግዱ አደሩ።

3ኛ  የሱብሂ አዛን ሲደረግ ውዱእ ሰያደርጉ ወደ መስገጃ ቦታ ሄደው ሰገዱ።

ከእነዚህ ክስተቶች የተነሳ ኢማሙ አሽ _ሻፊዒይን በጠበቀቻቸው መንገድ ስላላገኘቻቸው በጣም ደነገጠች ፈዘዘችም መታገስ አቃታት ።
አባቷን እንዲህ ብላ ጠየቀች፦ እንዴት ኢማሙ አሽ _ሻፊዒይን በመሰለ ትልቅ ዓሊም እነዚህ ነገሮች ይታያሉ?
ኢማሙ አህመድም ይህን ጉዳይ ከራሳቸው መስማት አለብኝ ብለው ሄደው ስለ ሁሉም ነገር ጠየቋቸው።

ኢማሙ አሽ _ሻፊዒይም እንዲህ ብለው መለሱላቸው፦

1ኛ  ምግቡን ሆዴ እስከሚሞላ የበላሁት ምግብህ ከሀላል መሆኑን ስላወኩኝ እና የደጋግ ሰዎች ምግባቸው መዳኒት መሆኑን ስላወኩኝ ነው።የበላውት ስለራበኝ ሳይሆን ለመዳኒትነት ነው የበላውት።

2ኛ ስለመተኛቴ ደሞ ወሏሂ አይኖቼ ሳይተኙ ነው ያደሩት ምክንያቱም ፊቅሃዊ በሆነ በአንድ መስአላ( በአንድ ሀዲስ)  ላይ እያስተነተንኩኝ ነው ያደርኩት በአንዷ ሀዲስ ውስጥ 72 ለሙስሊሞች የሚጠቅሙ ነገራቶችን አውጥቼበታለው በእውቀት ፍለጋ ቢዚ መሆን ከሌሊት ሰላት ስለሚበልጥ ነው።

3ኛ  ውዱእ ሳላደርግ የሰገድኩት ስላልተኛውኝ ውዱእ አልፈታውም።

ባላወቅነው ነገር ሰውን ከመፈረጅ እንጠንቀቅ

قصة الإمام الشافعي مع الإمام
أحمد

كان الإمام أحمد من أبرز طلاب الإمام الشَّافعي وكان يحبُّه حباً كبيراً، وكان دائم الثناء عليه أمام النَّاس وأمام أبنائه، فلمَّا قام الإمام أحمد باستضافة الإمام الشَّافعي في بيته، كانت ابنة الإمام أحمد متشوِّقة إلى رؤية الشَّافعي وعبادته.[٣] ولمَّا وُضع الطعام أكثر الشَّافعي من تناول الطَّعام، ثمَّ نام إلى الفجر ولم يقم الَّليل، وقام فصلَّى بهم الفجر بدون وضوء، فذُهلت ابنة الإمام أحمد لما رأته، ولم تطق صبراً، فسألت أباها عن ذلك إذ كيف يمكن أن يصدر هذا من إمامٍ بوزن الشافعي؟.[٣] فدخل الإمام أحمد إلى الشَّافعي وسأله عن تلك الأمور، فقال له الإمام الشافعي: أمَّا الطعام فما أكثرت منه إلَّا لأنِّي أعلم أنَّ طعامك حلالٌ، وطعام الصَّالحين شفاءٌ، فما أكلت جوعاً إنَّما أكلت تداوياً، وأمَّا نومي بعد الطعام وعدم قيامي لليل فوالله ما نامت عيني وإنَّما كنت أتفَّكر في مسائلَ من الفقه، فاستنبطت اثنتين وسبعين مسألةً ينتفع بها المسلمون، أمَّا صلاتي بكم الفجر بدون وضوء، فما نمت حتى أتوضأ، إنَّما كنت مستيقظاً طول الَّليل.

https://t.me/B1e9h
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#Palestine

ዛሬ አይርላንድ ፣ ኖርዌይ እንዲሁም ስፔን ለፍልስጤም የነጻ ሀገርነት እውቅና እንደሚሰጡ በይፋ አስታወቁ።

" የዛሬው ቀን ለፍልስጤም እጅግ ታሪካዊ ቀን ነው " ተብሏል።

የአየርላንድ ጠ/ሚኒስትር ሲሞን ሃሪስ " ዛሬ አየርላንድ ፣ ኖርዌይ እና ስፔን ለፍልስጤም የነጻ ሀገርነት እውቅና ሰጥተናል። ውሳኔውን ተግባራዊ ለማድረግ እያንዳንዳችን ማንኛውንም አይነት ብሔራዊ እርምጃ እንወስዳለን " ብለዋል።

ጠ/ሚኒስትሩ ፥ " #በሚቀጥሉት_ሳምንታት ተጨማሪ ሀገራት ይህን ጠቃሚ እርምጃ ለመውሰድ ከእኛ ጋር እንደሚተባበሩ እርግጠኛ ነኝ " ሲሉ አክለዋል።

የአይርላንድ መንግሥት ይህ የሀገርነት እውቅና የሁለት ሀገር መፍትሄን እንደሚደግፍና ለቀጠናው ዘላቂ ሰላም አስፈላጊ መሆኑን ገልጿል።

የስፔኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ፔድሮ ሳንቼዝ እና የኖርዌይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የሆኑት ኢስፔን ባርት ኢይድ ሀገራቸው ከግንቦት 28 (እ.ኤ.አ) ጀምሮ ለፍልስጤም ግዛት እውቅና እንደሚሰጡ በይፋ አሳውቀዋል።

የስፔኑ ጠ/ሚኒስትር ፔድሮ ሳንቼዝ ፥ " ምንም እንኳን ከአሸባሪው ቡድን #ሃማስ ጋር የሚደረገው ውጊያ ህጋዊ ቢሆንም ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ ለፍልስጤም የሰላም ፕሮጀክት የላቸውም " ብለዋል።

የኖርዌይ ጠ/ ሚኒስትር ጆናስ ጋህር ስቶር በበኩላቸው ፥ " እውቅና ከሌለ (የፍልስጤም) በመካከለኛው ምስራቅ ምንም ሰላም ሊኖር አይችልም " ብለዋል።

" ሽብር የተፈፀመው በሃማስና የሁለት ሀገር መፍትሄን በማይቀበሉ እንዲሁም የእስራኤልን መንግሥት በማይደግፉ ታጣቂ ቡድኖች ነው። " ሲሉ አክለዋል።

" ፍልስጤም ነጻ አገር የመሆን መሠረታዊ መብት አላት " ብለዋል።

የፍልስጤም #የነጻ_ሀገርነት እውቅና መስጠት በይፋ ከተሰማ በኃላ የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር #በኖርዌይ እና #በአይርላንድ የሚገኙ አምባሳደሮችን በአስቸኳይ ወደ እስራኤል እንዲመለሱ አዘዋል።

ሚኒስትሩ፤ " የዛሬው ውሳኔ ሽብርተኝነት እንደሚከፍል ለፍልስጤማውያን እና ለዓለም መልእክት ያስተላለፈ ነው " ብለዋል።

መረጃው የስካይ ኒውስ ነው።

More - @thiqahEth
ያልገባኝ ነገር ይህ ነው።

እንደምንሞት በርግጠኝነት እናውቃለን ነገር ግን ከሞት በኋላ ላለው ህይወት አልተዘጋጀንም በጤና ነው ወይ ቤተሰብ!!!?
فقد يكرهك البعض لأنك مختلف ...لكن في داخلهم يتمنون أن يكونو مثلك..

ስለተቃረንካቸው ብቻ ከፊሎቹ ሊጠሉህ ይችላሉ ግን በውስጣቸው አንተን መምሰልን ይመኛሉ።

https://t.me/B1e9h
የትናንቱን ወንጀላችንን ሳንረሳ፣ የምሽቱ ኃጢታችን ሳይደርቅ ዛሬም በማለዳ ተነስተን ሌላ የምንጀምረው ነገርስ።

አላህ ሆይ!አልፋታ ብሎ ዕድሜ ልካችንን የሚከታተለንን ጥፋታችንን ቁረጥ።

ኃጢአቱ አብሮት ያልተነሳ ሰው ምንኛ ታደለ!ለንፁህ ተውበት አድለን - ያ ረብ።

https://t.me/B1e9h
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
"ሙስሊም ነበርን" በሚል በፕሮቴስታንቱ አለም የሚገኙ ስመ ሙስሊሞች ምዕመኑን እንዴት እንደሚያታልሉት ከዚህ መመልከት ይቻላል። ትውልደ ሶማሌ የሆነችው ይህች ሴት በGMM ቲቪ የራሷ ፕሮግራም ያላት ሲሆን ሶማሌውን ለማክፈር ሆርን ኦፍ አፊሪካ ከአሜሪካ ከነ ቤተሰቧ አምጥቶ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን እያሰራት ይገኛል። ከስሟ ውጭ ግን ስለ እስልምና ምንም የምታቀው ነገር የላትም። በተለያዩ መድረኮች ግን "ሙስሊም ናት፣ የሸይኽ ቤተሰብ ናት" እየተባለች ተጋብዛ ምዕመኑን በሀሰት ትርክት ታታልለዋለች፥ ያሳዝናል..!
መረጃወችን ለወዳጄ ዘመድ ሼር ያርጉ!
የቴሌግራም ቻናላችን ከስር በሊንኩ ይቀላቀሉ👇

https://t.me/B1e9h
ብዕረ ሐኒፍ #3
🔖ሟች እና አልቃሽ

☞የሟችና አልቃሽ አስገራሚ ገፅታ!

በበስራ ከተማ ኗሪ የሆነ አላህን በጣም የሚያመልክ ሰው ወደ ሞት እየተቃረበ መጣ።
በዙሪያው ያሉ ቤተሰቦቹ ማልቀስ ጀመሩ።
ከዛም ይህ ሞት የተጣደው ሰው ለቤተሰቦቹ "ቁጭ አድርጉኝ" አላቸው።  ደግፈው አስቀመጡት።
ከዛ ወደ አባቱ ዞረና "አባቴ ለምንድነው ምታለቅሰው?" አለው።  አባትም" አንተን ማጣቴ ካንተ ቡሃላ ብቸኛ መሆኔ ነው ያስለቀሰኝ።" አለው።

ወደ እናቱም ዞረና "እናቴ ምንድነው ያስለቀሰሽ?" አላት።

እሷም "የልጅ ማጣት መሪር ሀዘን ነው ያስለቀሰኝ።" አለችው።

ወደ ሚስቱም ዞረና "ምንድነው የሚያስለቅስሽ?" አላት እሷም "ያንተን መልካም ነገር ስለማጣ ወደ ሌላ ሰው ስለምከጅል ሸክም ስለምሆን።" አለችው።

ወደ ልጆቹም ዞረና "ምንድነው የሚያስለቅሳቹ?" አላቸው። እነሱም "ከአንተ በኋላ ወደ የቲምነት፣ ወደ ውርደትና ደጋፊ ወደ ማጣት ስለምንጓዝ" አሉ።

ይሁን ሁሉ ከሰማ በኋላ ሟቹ በጣም አለቀሰ።
ቤተሰቦቹም  "ለምን ታለቅሳለህ?" አሉት።
እሱም "ሁላቹም ለኔ ብላቹህ ሳይሆን ለራሳቹህ ጥቅም ነው የምታለቅሱት። ይህን ስላየሁ አለቅሳለሁ።" አለ።

"ከናንተ ውስጥ ለጉዜዬ መርዘም ለስንቄ ማነስ የሚያለቅስልኝ የለም?
ከናንተ ውስጥ ከዚህ በኋላ መኝታዬ ለብቻዬ አፈር ለመሆኑ የሚያለቅስ የለም?
ከእናንተ ውሰጥ ከዚህ  በኋላ አስደንጋጭ ሂሳብ ስለሚጠብቀኝ የሚያለቅስ ሰው የለም?
ከእናንተ ውስጥ የአለማት ጌታ ፊት መቆሜን አስታውሶ የሚያለቅስልኝ የለም? አለና በፊት ለፊቱ ተደፋ።  ቢያንቀሳቅሱትም ህይወቱ አልፋለች። ሞቷል።

سَفَري بَعيدٌ وَزادي لَنْ يُبَلِّغَنـي
*وَقُوَّتي ضَعُفَتْ والمـوتُ يَطلُبُنـي

وَلي بَقايــا ذُنوبٍ لَسْتُ أَعْلَمُها
*الله يَعْلَمُهــا في السِّرِ والعَلَنِ.

ጉዞዬ ሩቅ ነው ስንቄም አያደርሰኝ
ሀይሌም ተዳከመ ሞትም ፈላለገኝ
የማላቃት ወንጀል አለች አሰፍስፋ
አላህ የሚያውቃት በምስጥር በይፋ

በዐብዱረዛቅ አል–ሐበሺይ

https://t.me/B1e9h
☀️እህቴ ሆይ እስቲ አንዴ ከሂወትሽ ትንሽን ደቂቃ ቀንሰሽ እህህ ብለሽ ስሚኝ ምናልባት ይጠቅምሽ ይሆናል...

قال الرسول ﷺ: "الحياء شعبة من الإيمان"
💫 ነቢዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም እንዲህ ይላሉ :- "ሀያዕ ( ማፈር ) ከኢማን ቅርንጫፎች ውስጥ ነው "

💫 ውዷ እህቴ ሀያዕ ማድረግ ለሴት ልጅ  ክብር ነው እንደውም ውበቷም ጭምር ነው ።

💫 አንዳንድ እህቶች አሉ አለባበሳቸው፣ አረማመዳቸው፣ አነጋገራቸው ሀታ ካፊሮች የሚሻሏዋቸው አላህን እንፍራ ዛሬ እንደዚ እንድትመፃደቂ እንደዚ እንድትሆኚ የሚያደርጉሽ ነገሮች ሁሉ ያልፋሉ ይጠፋሉ ግና ለሚያልፍ ነገር ለሚጠፋ ነገር ብለን የነገው አኼራችንን የንገው የዘላለማዊ ሂወታችንን አናበላሻት ...

💫 ውዷ እህቴ ዛሬ ባንቺ ንግግር፣ ባንቺ አረማመድ፣ ባንቺ አወራር ተማርከው የሚያሞግሱሽ እና የሚያደንቁሽ ነገ ከእሳት ነገ ከቀብር ጭንቀት አያድኑሽም ካንቺ ቅጣት ቅንጣትን አይጋሩልሽም ሁሉም ነፍሴ ነፍሴ ነው ሚለው ስለዚህ ዛሬ ስሜትሽን ነፍስያሽን አሸንፈሽ ለነገው ሀገርሽ ብትለፊ መልካም ነው።

💫 ወላሂ ይደንቁኛል እነዚያ ኒቃብን ለብሰው፣ ጅልባብን ለብሳ ንግግሯን፣ ሳቋን፣ ከሩቅ የምትሰሟት ያረህማን ቢያንስ ለለበስነው ልብስ ክብር ይኑረን የሰው ልጅ ያው ሰው ነው ምንም አያመጣም ነገር ግን አላህን እንፍራ የለበስነው ልብስ አይደለም ኒቃብ፣ እና ጅልባብ ሀታ ጭንቅላትሽ ግማሽ ላይ ጣል ምታደርጊያት እስከርብ አንቺን  ከመሸፈኑ ባሻገር ኢስላም የሚል ትልቅ ባንዲራን ነው ይዘሽ ምትጓዢው ባንቺ አንዲት ስህተት ጥርሳችው የወለቀለትን፣ ደማቸው የፈሰሰለትን፣ እርቧችው ሆዳቸው ላይ ዲንጋይ ያሰሩለትን የኛ ነቢይ አለይሂሙ ሰላቱ ወሰላም  ይዘውት የመጡትን ዲን ሰሀቦች አጥንታቸውን ከስክሰው ለኛ ያስረከቡትን ዲን ባንቺ ስህተት ታሰድቢዋለሽ ቢላህ አለይኩም እህቶቼ ሁሉም ነገር ያልፋል ይሄዳል ምንም ማንም ሚቀር የለም አላህ ሱብሀነሁ ወተዐላ ሲቀር ስለዚህ ለሚያልፍ ነገር የማያልፍን ድርጊት አትስሪ ይቅርብሽ ዲንሽን አጥብቀሽ ያዢ ዲንሽ ነው ላንቺ የሚሆንሽ ስሜትሽ ነፍሲያሽን አትከተዪ።

💥 አፍወን አረዘምኩት አሁን ላይ የምናየው የምንሰማው ቢፃፍ ቢፃፍ አያልቅም አላህ ሁላችንንም ከመጥፎ ነገር ይጠብቀን ።

منقول

https://t.me/B1e9h
ጌታዬ ሆይ! እስረኛህና ኸዳሚህ አድርገህ አኑረኝ፡፡ በግልጋሎትህ እስከዘላለሙ አሰማራኝ፡፡ ካንተ ጉያ የማልጠፋ፣ ከመንገድህ የማልርቅ፣ ከትዕዛዝህ የማልወጣ አድርገኝ። ቤትህን የማዘወትር፣ በቁርኣንህ የማተኩር፣ አንተን ፈርቼ የማድር ባርያህ አድርገኝ። ዘወትር ስላንተ የማስተማርና ወዳንተ የማመላክት እሆን ዘንድ አግዘኝ። ሀሳቤን ሰብስብልኝ ቃላቴን አሳምርልኝ።


https://t.me/B1e9h
እዝነት እና መተዛዘን
ኢብኑ/ሙነወር
👆👆👆👆👆👆
ይደመጥ ወሳኝ የሆነ ወቅታዊ ሙሓዶራ
“እዝነት እና መተዛዘን”
ግንቦት 20/2016 በሜክሲኮ ጀርመን ግቢ ተባረክ መስጂድ የቀረበ ሙሓዶራ

https://t.me/B1e9h
👇👇👇


በጣም የሚገርም ወንድማማችነት

ሰለፎች ዘንድ
👇


ከቀደምት ሰለፎች መካከል አንድ ሰው ወደ ጓደኛው ቤት ይሄዳል።
ጓደኛውም ምነው በዚህ ሰአት መጣህ? ይለዋል። "እሱም አራት መቶ ዲርሃም አለብኝና ክፈልልኝ" ይለዋል ።
ጓደኛውም ቤቱ ይገባና አራት መቶ ዲርሀም መዝኖ ይሰጠዋል።
ከዘም ወደ ቤቱ ገብቶ ማልቀስ ይጀምራል ሚስቱም ማልቀሱን ስታይ ገንዘቡን የሚትፈልገው ከሆነና መስጠት የማትችል ከሆነ ለምን የለኝም ብለህ ምክንያት አታቀርብም ነበር? አሁን ማልቀስህ ምን ያደርግልሃል ? አለችው

እሱም በጣም የሚገርምና ልብን የሚነካ ንግግር ተናገራት 👇

👉እኔ እኮ የማለቅሰው ወንድሜ ቤቴ ድረስ መጥቶ ቸግሮት ችግሩን እስኪነግረኝ ድረስ ወንድሜ የሚኖርበትን ሁኔታ ባለማወቄ ነው ኣላት

📚 አት-ተብሲራ 2/263
ዛሬ እኛና እነሱ ዬት ነው ያለነው ሰዎች? እኛም አሁን ከነሱ ጀነት ለመግባት እናስባለን? አላህ በእዝነቱ ይድረስልን እንጂ ከባድ ነው

https://t.me/B1e9h
አንዘርቱኩሙ ናር
አህመድ አደም
አዋጅ አዋጅ አዋጅ

ወላሂ አው ጀሃነም በጣም ያስፈራል አላህ ሁላችንም ጀሃነም ከመውረድ ይጠብቀን አደራ ሁላችንም እናድምጠው እንዳታልፍ

ሸይሃችን አህመድ አደም አላህ ይጠብቅልን

https://t.me/B1e9h
☞  ተራራን  መውጣት የፈራ, ሁሌ በሸለቆ  ውስጥ  ይኖራል❗️

☞ አኬራን የዘነጋ ሰው , በዱንያ ፍቅር እንደተጠማ ይሞታል !

☞" በኢልም ጥላ ስር ጥቂት ሰዓታትን መታገስ ያቃተው ሰው እድሜ ልኩን በጃሂልነት ጥላ ሰር ይኖራል❗️"

https://t.me/B1e9h
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ይህንን የሸይኹን መልዕክት በምገባ አድምጡት በተለይ እህቶች

ሸይኽ አብዱረዛቅ አልበድር

https://t.me/B1e9h